የዐፄ ኃ/ሥላሴ መንግሥት በደርግ ወታደሮች ሲገለበጥ በወቅቱ የነበሩት ፓትርያርክ አቡነ ቴዎፍሎስ ነበሩ። ደርግም ሥልጣኑን እንደያዘ በአቡነ ቴዎፍሎስ ላይ የውሽት ክስ በመመሥረት እና በማሳጣት ከሥልጣን አውርዶ ወደ ወኅኒ አወረዳቸው። በዚያ ወቅት እሳቸው በእስር ላይ እያሉ አቡነ ተ/ሃይማኖት ሦስተኛው ፓትርያርክ ሆነው በ1967 እንዲሾሙ አደረገ። እንግዲህ ይህ በፓትርያርክ ላይ ፓትርያርክ መሾም የሚለው ስሕተት በዚያ ጊዜ ተጀመረ ማለት ነው። ፓትርያርኩም በእስር ላይ ስለነበሩ በመጨረሻ ደርግ ምን እንደሚያደርጋቸው ግራ ስለገባው በ1971 ዓም በግፍ እኝህን አባት አንቆ ገድሏቸዋል።
ነገር ግን ደርግ እኝህን አባት ሲያስር፤ በወቅቱ ከነበሩት የሲኖዶስ አባላት አባቶች መካከል አንዳንዶች፤ ደርግ በአቡነ ቴዎፍሎስ ላይ የወሰደውን እርምጃ እንደግፋለን ብለው በመጻፍ ፈንታ፤ ልክ እንደ ግብጽ ቤተ ክርስቲያን ሲኖዶስ፤ አንዋር ሳዳት አቡነ ሺኖዳን አስሮ ሌላ ፓትርያርክ ሹሙ ሲላቸው፤ በሕይወት እያሉ ሌላ ሰው አንሾምም ብለው በሲኖዶስ ለረጅም ጊዜ ሲተዳደሩ ቆይተው አንዋር ሳዳት ሲሞት አቡነ ሺኖዳ ወደ ሥልጣን እንደተመለሱ ሁሉ፤ የእኛም አባቶች እንደዚያ ቢያደርጉ ኖሮ ሥርዓት ባልተፋለሰና፤ አቡነ ቴዎፍሎስም ባልተገደሉ ነበር። አቡነ ተ/ሃይማኖትም ሦስትኛው ፓትርያርክ ሆነው ቤተ ክርስቲያንን ሲመሩቆይተው በመጨረሻ ሲያርፉ አቡነ መርቆሬዎስ አራተኛው ፓትርያርክ ሆነው ተመረጡ።
በዚህ መሐከል ደርግ ተንኮታኩቶ ሲወድቅ ወያኔ ሥልጣን እንደያዘ ያተኮረው የኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን ላይ ነው። በወቅቱ በመንበሩ ላይ የነበሩትን አቡነ መርቆሬዋስን የደርግ ሹም ናቸው በማለት ከሥልጣን እንዲነሱ በእጅ አዙር በመገፋፋት ወይም በማስተባባር ግፊት ስላበዛባቸው፣ በመጨረሻም በሕመም የተነሣ ለመሥራት አልቻልኩም ብለው ሥልጣኑን ለቀው ከቆዩ በኋላ ከሀገር ወጥተው ተሰደው ወደ አሜሪካ ገቡ። ደርግ ሥልጣን በያዘ ጊዜ አስሯቸው ከነበሩት ጳጳሳት መካከል አንዱ የሆኑት አባ ጳውሎስ ከተፈቱ በኋላ ወደ አሜሪካ በመሔድ ምዕምናን እያስተማሩ እያገለገሉ ነበር። እኝህ ሰው በሎስ አንጀለስ ለተከፈለችው የቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አንዱ ምክንያት ሲሆኑ፤ ከተከፈሉት አንዷ የድንግል ማርያም ምዕመናን የራሳቸው ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ገዝተው ለማስመረቅ የተለያዩ እንግዶች እንዲገኙ የግብዣው ጥሪ የላኩት አባ ጳውሎስ ነበሩ። ይሁን እንጂ በዓሉ ሊከበር ጥቂት ጊዜ ሲቀረው ወያኔ ሥልጣን ስለያዘ አባ ጳውሎስ ማንንም ሳያማክሩና ሳይነግሩ ፕሮግራሙን ትተው ተነስተው ወደ አዲስ አበባ ሄዱ።
እዚያ ሰንብተው ከተመለሱ በኋላ በሎስ አንጀለስ አካባቢ የሚኖሩትን አባላት የሆኑትንም ሆነ ያልሆኑትን ሁሉ የትግርኛ ቋንቋ ተናጋሪ ምዕመናንን በቤተ ክርስቲያኗ ሰብስበው የቪዲዮ ቀራጭ በግላቸው አዘጋጅተው ለተሰበሰበው ምዕመናን ንግግር ሲያደርጉ፤ "እስከዛሬ ድረስ የበኩር ቋንቋ የሆነውን የትግርኛ ቋንቋ ትቼ በአማርኛ በማስተማሬ አዝናለው" ብለው ሲናገሩ፤ አባላቱም ከዚህ በፊት ያልነበረ እንዲህ ዓይነት የሚከፋፋል ቃል ለምን ይናገራሉ በማለት አቋርጧቸዋል። ከዚያ ቀን በኋላ በሎስ አንጀለስ አካባቢ የሚኖሩትን የትግራይ ሰዎች አቡነ አረጋዊ የሚባል በትግርኛ ግልጋሎት የሚፈፀምበት ቤተ ክርስቲያን ከፈቱ። እንግዲህ በውጭው ዓለም አባ ጳውሎስ በቤተ ክርስቲያናችን በዘር ላይ እንድትከፈል በመጀመር ግንባር ቀደም ሆኑ ማለት ነው። አባ ጳውሎስ ድንገት አዲስ አበባ ደርሰው ከመጡ በኋላ የትግርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች ቤተ ክርስቲያን እንዲከፈቱ በግልጽ መንገዱን ቢከፍቱም፤ ሁኔታዎች እስኪመቻቹ ውስጥ ውስጡን ከወያኔ ጋራ ይሠሩ እንደነበር ከአድራጎታቸው መገመት አያዳግትም።
ባለፈው ሰኔ ወር ላይ ቀሲስ አስተርአየ "የነ ፋሌቅ ወጥመድ" በሚል ርዕስ ከዶ/ር አረጋዊ የዶክትሬት ምረቃ ጽሑፍ ላይ፤ ወያኔ ከጫካ ጀምሮ እንዴት አድርጎ የኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን እንደሚያዳክም፣ እንደሚያጠፋና፤ የእዚህ ሰይጣናዊ አስተሳሰብ ዋና ጠንሳሾች እነ ስብሐት ነጋና ገብረ ኪዳን ደስታ እንደሆኑ ግልጽ አድርገው ጽፈውታል። ቀሲስ አስተርአየ ተርጉመው የጠቀሱትን መልሼ እዚህ ላይ ማሳየት እፈልጋለው " … ቤተ ክርስቲያን ለረዥም ዘመናት በሕዝቡ አዕምሮ ላይ ስትቀርፅ የኖረችውን ብሄራዊ የኢትዮጵያዊነት ስሜት ከትግራይ ሕዝብ አዕምሮ ጠራራጎ በጠባቡ ትግሬአዊነት ስሜት በመተካት የቤተ ክርስቲያኒቱን ይዘት እያጠበቡ ራሷን ቤተ ክርስቲያኒቱን መምታት ነው። …የኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን ጠቅላላ መዋቅራዊ አስተዳደር በትግራይ ነፃ አውጪ ድርጅቶች ባለሟሎች መተካትና በቤተ ክርስቲያኒቷ አካባቢ የትግርኛ ቋንቋ እንዲሰፍን ማድረግ ነው።" ታዲያ አባ ጳውሎስ ባለፉት 20 ዓመታት ቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ የፈጸሙትን ካየን አንዱ ምልምል ናቸው ብንል ስሕተት አይሆንም።
አባ ጳውሎስም ሥራቸውን አስቀድመው በአሜሪካ ስለጀመሩና ለወያኔ ስላስመሰከሩ፤ ደርግ በወደቀ ጊዜ በግርግሩ መሐል ወደ አዲስ አበባ መጥተው የመንበረ ጵጵስናውን በቀላሉ ለመያዝ ችለዋል። አባ ጳውሎስ መንበሩን ከያዙ ጀምሮ የፈጸሟቸው በደሎች ቁጥር ስፍር የሌላቸው ሲሆኑ፤ ልክ ከላይ እንደጠቀስኩት ወያኔ ከጫካ ጀምሮ የዘረጋውን ተንኮል ተግባራዊ ለማድረግ፤ በየአድባራቱ የሚሾሟቸው አብዛኛዎቹ የቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪዎች፣ ጸሐፊዎች የመሳሰሉት የትግሬ ዝርያ ያላቸው እንዲሆኑ አድርገዋል። በእሳቸውም ዙርያ ከወንድማቸው አንስቶ የእሳቸው ዘር በሆኑ የተከበቡ ሲሆን፤ እነዚህ ሰዎች ፓትርያርኩን በመተማመን ሌሎች ጳጳሳት ላይ የሚያሳዩት ንቀት፣ስድብ አልበቃ ብሏቸው ቤታቸውን እየሰበሩ በመግባት እስከ መደብደብ መድረሳቸው የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው። እንዲህ ዓይነት አስፀያፊቆሻሻ ተግባር እንኳን ከቤተ ክርስቲያን አካባቢ ቀርቶ ከአንድ ጥሩ ኢትዮጵያዊ የማይጠበቅ ነው።
በተጨማሪም እንደ ሀገራችን ባሕል ሰው ቤተ ክርስቲያን ገብቶ ደውሎ አስታርቁኝ፣ አማልዱኝን ካለ አባቶች በሁኔታው ገብተው ለማስታረቅ ይሞክሩ ነበር። ነገር ግን በአንድ ወቅት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችረብሸው ፖሊስ ሲያሳድዳቸው ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ገብተው አስጥሉን ባሉ ጊዜ አሳልፈው ለወያኔ ወታደሮች ሰጥተዋቸዋል። እኝህ ሰው እንደ ዓለማዊ መሪም ባሕታዊውን በቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን ዓውደ ምሕረት ያስገደሉት ሳያንሳቸው፤ እሳቸው ሾመው የላኩትን አለቃ አንቀበልም በማለታቸው በልደታ ቤተ ክርስቲያን ካህናትና ምዕመናን ላይ ፖሊስ አዘመቱባቸው። በዚያም የተነሣ የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ላልተወሰነ ጊዜ ተቋረጠ። አባ ጳውሎስ በዚህ ብቻ አላቆሙም ነገር ግን ሌሎች የሚጠሏቸውን ሰዎች እንደ ዓለማዊ መሪ የሚበቀሉና የሚያሳድዱ፤ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ወይምቀኖናን ከምንም ያልቆጠሩ፤ ለሥጋዊ ተድላ ያመዘኑና ምግባራቸውና ባህሪያቸው መንፈሳዊ ስላልሆነ፤ ከመኖሪያቸው ሲወጡ ልክ እንደ አንድ አምባገነን መሪ ጥይት በማይበሳው መኪና የሚጓዙ ነበሩ።
በዚህ የተነሳ አባ ጳውሎስ በቤተ ክርስቲያናች ታሪክ ሆኖ የማያውቀውን በየሄዱበት ጫማ፣እንቁላልና ድንጋይ እየተወረወረባቸው እሳቸው ተዋርደው ቤተ ክርስቲያንን መሳቂያና መሳለቂያ አድርገዋታል።
በዚህ የተነሳ አባ ጳውሎስ በቤተ ክርስቲያናች ታሪክ ሆኖ የማያውቀውን በየሄዱበት ጫማ፣እንቁላልና ድንጋይ እየተወረወረባቸው እሳቸው ተዋርደው ቤተ ክርስቲያንን መሳቂያና መሳለቂያ አድርገዋታል።
በንብረትና ገንዘብ ዘረፋውም ከአንድ የሃይማኖት አባት በማይጠበቅ ሁኔታ ራሳቸውን አስገመቱ። ለዚህ ሁሉ ውርደት የተዳረጉት ከላይ በፈጸሟቸው ተግባራት ሆኖ ሳለ፤ እሳቸው ግን በአንድ ወቅት ሕዝቡ የጠላኝ ትግሬ በመሆኔ ነው ብለው ጥፋታቸውን ለመሸፈን ሞክረዋል። ረስተውት ነው እንጂ የኢትዮጵያ ሕዝብ ለ1600 ዓመታት ጆሮአቸውን ቢቆርጧቸው አማርኛ ወይ ግዕዝ በማይሰሙ ግብጻውያን ይመራ እንደነበር እንዴት እንደዘነጉት የሚገርም ነው። ታዲያ ከዚህ እንደምንረዳው ኢትዮጵያውያን የሚፈልጉት ጥሩ አባት ሁሉን በእኩል የሚያይ፤ ሕይወቱ ሌሎችን የሚያስተምር እንጂ ዘሩ ምን እንደሆነ ግድ እንደማይሰጣቸው ነው።
በመጨረሻም መንግሥት ካልጠፋ ቦታ ሄዶ ለዘመናት ተከብሮ ከኖረው የዋልድባ ገዳም አጠገብ የስኳር ፋብሪካ እሠራለሁ ብሎ የገዳሙ ባሕታውያንና አባቶች በመቃወማቸው በፖሊሶች ተደበደቡ። ፓትርያርኩም በገንዘብ ሊደልሏቸው ሞከሩ ግን አልሆነም። የእነዚያ አባቶች ጸሎት የደረሰ ይመስላል ላለፉት 21 ዓመታት ሀገርንና ቤተ ክርስቲያንን ሲበድሉ፤ እንዲሁም ሕዝብንና ሲያስለቅሱ ኖረው መለስ እያለ ማንም አይነካኝም እያሉ ከተማመኑበት ሰው ጋር ተከታትለው በድንገት ሞቱ። እንደ ሃይማኖታቸው በእግዚአብሔር ቢታመኑ ግን አይሻልም ነበርን? አባ ጳውሎስ በሞቱ ሰሞን በየድኅረ ገጾች ላይና በፌስ ቡክ ሌሎችም ላይ ያየነው ከሠሩት ደግ ሥራ ወይም አስተዋፅዖ ይልቅ ይህቺን ቤተ ክርስቲያን እንዴት በድለዋት እንደሄዱና ይህች ቤተ ክርስቲያን ከእኝህ ሰው የተበላሸ አመራር እፎይ እንዳለች ነው።
አንዳንዶች ደግሞ ምንም በደል ቢያደርጉም ይቅር ማለት ነው በማለት ሐዘናቸውን ገልፀዋል። በአንጻሩ ደግሞ የግብጽ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ አቡነ ሺኖዳ ሲያርፉ ግን በሁሉም ድኅረ ገጾች ላይ የተነበበው ግን አንድ ዓይነት የሀዘን መልዕክት ነበር።ይህ የሚያሳየው የኢትዮጵያ ሕዝብ ስለሚሾመው ፓትርያርክ ዘር ግንድ ስሜት እንደማይሰጠው፤ ነገር ግን ምግባሩ ጥሩ የሆነና መንጋዎቹን የሚጠብቅ አባትን እንደሚፈልግ ነው። ባለፈው ነሐሴ 2004 መጨረሻ ላይ ዓቃቤ መንበር የነሆኑት አቡነ ናትናኤል "…ቤተ ክርስቲያኒቷ ሁለንተናዊ ዕድገት ለሀገሪቱ ሰላምና አንድነት የሚበጅ ተተኪ አባት (ፓትርያርክ) ለቤተ ክርስቲያኗ እግዚአብሔር ባወቀ መርጦ እንዲያስቀምጥ……ከጳጉሜ 1 ቀን 2004 እስከ መስከረም 10 ቀን 2005 ጸሎተ ምህላ እንዲደረግ ቅዱስ ሲኖዶስ መወሰኑን አውጀዋል።" ሐሳቡ በቅንነት እስከሆነ ድረስ በጣም አስፈላጊ ነው። ይህ ምስኪን ሕዝብም አዋጁን ሰምቶ ሱባኤውን በጾምና በጸሎት አሳልፏል።
ይሁን እንጂ እያፈተለኩ ከሚወጡት ወሬዎች እንደተረዳነው፤ ወያኔ መጀመሪያ ላይ ሲገቡ በነበረው ግርግር ያደረገው
ማጭበርበር አንሶ አሁንም የወያኔን ዓላማ ያራምዱልኛል ብሎ የሚያሰባቸውን ፓትርያርክ ነው በመንበሩ ላይ እንዲቀመጡ የሚፈልገው። በጥቅምት ወር አካባቢ ላይ የተሰማው ጭምጭምታ ወያኔ እንዲመረጡ ያሰባቸው ሰዎች አቡነ ማትያስ ወይም አቡነ ጎርጎርዮስ የተባሉትን ወይም የአባ ጳውሎስ ቀኝ እጅ ከነበሩት ዋነኛው አቡነ ገሪማ መሆኑን ተደምጧል። እንዲሁም ዐቃቤ መንበር የሆኑት አቡነ ናትናኤል ደግሞ በስደት የሚገኙትን ብፁዕ አቡነ መርቆሬዎስን ማነጋገራቸው ሲታወስ፤ ባለፈው ሳምንት የወቅቱ የኢትዮጵያ ፕሬዜዳንት ብፁዕ አቡነ መርቆሬዎስ ወደ ሀገር ተመልሰው ሥልጣኑን እንዲረከቡ ከጋበዙ በኋላ ወዲያው ውሎ ሳያድር ደግሞ ጥሪውን ማንሳታቸውን ተናግረዋል። መጀመሪያ ላይም ከብፁዕ አቡነ መርቆሬዎስ ጋር ንግግር የጀመሩት አቡነ ናትናኤልም መንግሥት በቤተ ክህነቱ አስተዳደር ውስጥ ጣልቃ መግባት የለበትም በማለት የፕሬዜዳንቱን ጥሪ እንደማይቀበሉ አስታውቀዋል። በእርግጥ ፓትርያርኩን ለማስቀመጥ በሚደረገው ምርጫ ላይ መንግሥት ጣልቃ ካልገባ ምናልባት ሁኔታዎች ሊስተካከሉ ይችሉ
ይሆናል። ይሁን እንጂ ካለፉት ዘመናት ልምድ እስከምናውቀው ድረስ መንግሥት በቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ውስጥ ያልገባበት ጊዜ የለም። አሁንም በመንበሩ ላይ የሚቀመጠው አባት የወያኔንን ዓላማ የሚያራምድ ሳይሆን፤ ከእምነቱና ዕውቀት ባሻገር ሁሉን በእኩል ዐይን የሚመለከትና ለቤተ ክርስቲያን ዕድገት ደከመኝ ታከተኝ ሳይል የሚሠራ መሆን ይኖርበታል።

እንዲሁም ምዕመናን ደግሞ እኔ የጳውሎስ ወይም የአጵሎስ ሳይሉ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ተከትሎ በመንበሩ ላይ በመንፈስ ቅዱስ ተሾሞ ለተቀመጠው መታዘዝ ይኖርባቸዋል። አሁንም የሚሾመው ፓትርያርክ በመንግሥት ትዕዛዝ ከሆነ፤ የወያኔ መንግሥት ሲወድቅ የተሾመው ፓትርያርክ ከሥልጣን ይወርዳል አልፎም ተርፎም ለስደት ተዳርጎ ሌላ ሦስተኛ ሲኖዶስ ሊቋቋም ይችል ይሆናል ማለት ነው። ስለዚህ ብፁዓን አባቶች እንዲሁም ምዕመናን ምርጫው በሕገ ቤተ ክርስቲያን እንዲፈጸምና የተበላሸው ሥርዓት እንዲስተካከል የማድረግ ኃላፊነት አለባቸው። አባ ጳውሎስ በሕይወት በነበሩ ጊዜ በውጭ ሀገር በስደት ካለው ሲኖዶስ ጋራ ስብሰባ መካሄዱ ይታወሳል። ነገር ግን ወደ የትም እንደማያደርስ የታወቀ ነበር። ይሁን እንጂ ይህ ቤተ ክርስቲያንን ከሁለት የከፈለና ምዕመናን የጎሪጥ እንዲተያዩ ያደረገ ስለሆነ፤ ይህ አሁን ያለው አጋጣሚ ተጠቅሞ ቤተ ክርስቲያንን ወደ አንድነት ለማምጣት ሁሉም አባቶች፣ ካህናት እንዲሁም ምዕመናን ከልባቸው ሊጥሩ ይገባል።
እዚህ ላይ የወያኔ ዓላማ ምን እንደሆነ ከዶ/ር አረጋዊ በርሔ ጽሁፍ ተረድተናል ማለትም ቤተ ክርስቲያንን የሚያዳክምና የሚያጠፋ ማለት ነው። ታዲያ እንዴት አድርገን ነው በራሳችን ላይ አጥፊ ሲሾምብን ዝም ብለን ለዚህ አረመኔ መንግሥት የምንታዘዘው? ቤተ ክርስቲያናችንን የመጠበቅ መስዋዕትነት የሚከፈለው መቼ ነው? ይህን አጋጣሚ በዝምታ ካለፍንና መንግሥት አሁንም ጣልቃ ገብቶ የሚረብሽ ከሆነ፤ እንደ እነ አቡነ ጴጥሮስ እና አቡነ ሚካኤል የመሳሰሉ የጣሊያንን ጥይት ሳይፈሩ ስለ እውነት፣ ስለ ሃይማኖታቸውና ሀገራቸው ተናግረው መስዋዕትነት የተቀበሉ አባቶችን የመሰሉ በቤተ ክርስቲያናችን የሚፈጠሩት መቼ ነው ብለን እንዳናዝን እፈራለው። የአጤ ምኒልክ የክተት አዋጅ "ሀገርህን የሚወር፣ ሃይማኖትህን የሚለውጥ ጠላት መጥቶብሃል፤ ተነስ ተከተለኝ ነበር።" አሁን ደግሞ የሁላችንም አዋጅ መሆን ያለበት፤ ወገኔ ሆይ ከዚች ምድር ላይ የተፈለፈሉ በሥልጣን ላይ ያሉ ሃይማኖትህን ሊያጠፉ፣ሀገርህን ሊያፈራርሱ ሲያሴሩ ውለው አድረዋልና በቃ ተነሥ ነው መሆን ያለበት።
መደምደሚያ
ከላይ እንዳየነው ባለፉት 21 ዓመታት ወያኔ በሀገራችንና በቤተ ክርስቲያናችን ላይ ያደረሰውን ጥፋቶች ጠቅለል ባለ መልኩ ለማሳየት ሞክሬአለሁ። ታዲያ አክሱም በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ግንባር ቀደም ሚና የተጫወተችና ከዚያችም ክፍለ ሀገር እንደ ዐፄ ካሌብ፣ ቅዱስ ያሬድ፣ ዐፄ ዮሐንስ፣ ራስ አሉላ አባ ነጋ ሌሎችም በታሪካችን ውስጥ ከፍተኛ አስተዋፅዖ ያደረጉ ከወጡባት ምድር፤ ወያኔ የተባሉ ከአንድ መንደር የመጡ ሀገር አፍራሾች፣ ዘረኞች፣ ዓይን ያወጡ ዘራፊዎችና ይሉኝታ ቢሶች እንዴት ሊፈጠሩ እንደቻሉ የሚገርም ነው። እነዚህ ወያኔዎች የሚያካሄዱት የሀገር ንብረትና ገንዘብ ዘረፋ፣ የግል ሀብትን በማካበት ላይ የሚደረገው ዐይን ያወጣ ዝርፊያ እና ይኽን ጥቅም ለማስጠበቅ ሀገሪቷ ላይ የዘረጉት የከፋፍለህ ግዛው ቆሻሻ አመራር አሳፋሪ ነው። በስደት ያለው አቶ አርአያ ወልዱ ኢየሩሳሌም አርአያ በሚል በብዕር ስም በተከታታይ በሚጽፋቸው ጽሑፎች ላይ ያለውን የፖለቲካ ሽኩቻና ምዝበራ እያጋለጠና እያስገነዘበን ይገኛል። ባለፈውም "ከፖለቲካው ፍጥጫ ጀርባ" ብሎ የጻፈውን ማንበብ ጥሩ ግንዛቤን ይሰጣል (http://www.ethiomedia.com/assert/behind_the_scene.pdf )።

ወያኔዎች እንዴት አድርገው ሀገሪቷን በዘረኝነት መንፈስ እንደከፋፈሉና ያለምንም ይሉኝታና ዕፍረት መጥፎ ሥራቸው እንደ ታላቅ ጀብዱ ለሕዝብ ለማሳየት ለሆዳቸው በተገዙ ወይም በዚህ አገዛዝ የተጠቀሙትን መሣሪያ በማድረግ ኅብረተሰቡን እንደከፋፈሉትና በሕዝብ መካካል ያለውን መፋቀር እንዳጠፉት በዓይናችን እያየነው ያለ ሂደት ነው። እንዲሁም ደግሞ አንዳንድ የትግራይ ተወላጅ የሆኑ የሚሠራውን ግፍ እያዩ፤ ነገር ግን ሥልጣን ከትግሬ ዘር ውጭ መውጣት የለበትም በማለት በጭፍን የሚደግፉ በታሪክ ወደፊት ከመወቀስ አይድኑም። ለጊዜው የጠ/ሚኒስትርነቱን ቦታ የያዘው ሰው የትግሬ ተወላጅ ባይሆንም ደኅንነቱንና ጦር ኃይሉንም ተቆጣጥረነዋል፤ የሚያሰጋን ነገር የለም በሚል ትዕቢት የሚመኩም ሊጠነቀቁ ይገባል። ምክኒያቱም ነገሮችም እኛ ብቻ እንደምናስበው ስለማይሄዱ ። ደግሞም ብልጥነት ሁልጊዜ ደግሞ አያዋጥም። አንድ አባባል አለን "ሥራ ለሠሪው እሾህ ላጣሪው" ማለትም ሌላውን ዘር እናጠቃለን ብለን ተንኮል ስንሸርብ፣ ሕዝብ ስናሳድድ ስናሰቃይ፤ በፈጠርነው የተንኮል አሠራር እኛው ራሳችን ተመልሰን የራሱ ሰለባ እንዳንሆን ያሰጋል።
እንደ ስብሐት ነጋ ደግሞ ያለ የሽማግሌ ቀላል፤ ወደፊት ምን ያስከትላል ብሎ ባለማሰብ አማራንና ኦርቶዶክስን ሰብረነዋል ብሎ በአደባባይ ሲናገር ስንሰማ፤ የወያኔን መርዝ ዓላማ በግልጽ እንድንረዳው ከዚህ የበለጠ ምስክር አያስፈልገንም። እንዲህ ዓይነት በዘር ላይ የተመሠረተ ጥላቻን ይዘው ተነስተው ብዙ ጥፋት ያደረሱ ለምሳሌ ያህል በሩዋንዳ በዩጎዝላቪያ ታይተዋል ነገር ግን መጨረሻቸው አላማረም። እዚህ ላይ አንድ መገንዘብ ያለብን ነገር ምናልባት በስመ ትግሬነት ብቻ የወያኔን መንግሥት ወይም ደግሞ የስብሐት ነጋን ሐሳብ የሚደግፉ፤ የእምነታቸው ሕልውና በአንጻሩ ደግሞ ፈተና ላይ መሆኑን መዘንጋት የለባቸው። ይህ ስብሐት የሰጠው ዓይነት አስተያየቶች አብሮ ለብዙ ዘመናት የኖረን ሕዝብ የሚከፋፍልና የሚያቃቅር ነው። በመጽሐፈ ሲራክ ላይ እግዚአብሔር አምላክ 6 ነገሮችን አይወድም ነገር ግን ሰባተኛውን ነፍሱ አጥብቃ ትፀየፋለች፤ ይኽውም "በወንድማማቾች መካከል ፀብን የሚዘራ" ይላል።
ስለዚህ ይህን ሰይጣናዊ አስተሳሰብ ስብሐት ነጋም ሆነ የእሱ ፓርቲ ከአእምሮአቸው አውጥተው ወደ ፍቅር ወደ አንድነት እንዲመጡ፤ ልቡናቸው ይመለስ ዘንድ ልንጸልይ ይገባል ምክንያቱም ክርስትና የፍቅር እምነት ነውና።
በቅርቡም የጠቅላይ ሚኒስትርነቱን ቦታ የተረከቡት አቶ ኃ/ማርያም ደሳለኝ በሚቀጥሉት ዓመታት ሟቹ አቶ መለስ የጀመሩትን ዕቅድ ብቻ ሳይሆን የተነፈሱትንም አየር ነው የምተነፍሰው ብለው ሲናገሩ መስማቱ የሰውየውን የፖሊቲካ ብስለት ገና ከመጀመሪያው እንድንጠራጠርና፤ ጉልቻ ቢለዋወጥ ወጥ አያጣፍጥም የሚለውን የሀገራችን አባባል እንድናስብ አድርጎናል። አሁን እሳቸው በሚመሩበት ዘመን ለሚፈጠሩት ችግሮች ተጠያቂው አቶ ኃ/ማርያም እንጂ ከመቃብር ዓለም አቶ መለስ አይደለም። አስተዋይ የሆነ መሪ የሚያደርገው ከዚህ በፊት የተደረጉ ስህተቶች በማስተካካል አስተዳደርን ያሻሽላል፣ በደል ተፈፀመ ሲባል እንዲጣራና አስፈላጊ እርምጃ እንዲወሰድ ያደርጋል እንጂ ምንም አልለወጥም ብሎ መናገር አሳዛኝ ነው።

በቅርብ ጊዜ ባልና ሚስት ዕርቃነ ሥጋቸውን በአደባባይ እየታየ እንዲፈጽሙ የተደረገውን ላየና ለሰማ በእውነቱ ይህ ዓይነት ባሕርይ ኢትዮጵያውያን ከየት እንዳመጡት የሚያሳዝን ነው። ሉሉ ከበደ የጻፉትን ማንበብ ጥሩ ግንዛቤ ይሰጣል http://www.ethiomedia.com/assert/yewenjelegnochu_mengist.pdf ።
ይህ የአቶ ኃ/ማርያም ግትር አባባል የሮብዓምን ታሪክ እንዳስታውስ አደረገኝ። ንጉሥ ሰለሞን ሞቶ ሮብዓም በነገሠ ጊዜ ኢዮርብዓምና ሕዝቡ ወደ እርሱ መጥተው አባትህ ቀንበር አክብዶብን ነበር፤ አሁንም አንተ ጽኑውን የአባትህን አገዛዝ፥ በላያችንም የጫነውን የከበደውን ቀንበር አቃልልልን፤ እኛም እንገዛልሃለን ብለው ተናገሩት። እርሱም ሂዱ፥ በሦስተኛውም ቀን ወደ እኔ ተመለሱአላቸው። ሕዝቡም ከሄዱ በኋላ ንጉሡ ሮብዓም ለዚህ ሕዝብ እመልስለት ዘንድ የምትመክሩኝ ምንድር ነው? ብሎ አባቱ ሰሎሞን በሕይወቱ ሳለ በፊቱ ይቆሙ ከነበሩት ሽማግሌዎች ጋር ተማከረ። እነርሱም ለዚህ ሕዝብ አሁን ባሪያ ብትሆን ብትገዛላቸውም፥ መልሰህም በገርነት ብትናገራቸው፥ በዘመኑ ሁሉ ባሪያዎች ይሆኑልሃል ብለው ተናገሩት።እርሱ ግን ሽማግሌዎች የመከሩትን ምክር ትቶ ከእርሱ ጋር ካደጉትና በፊቱ ይቆሙ ከነበሩት ብላቴኖች ጋር ተማከረ። እርሱም አባትህ የጫኑብንን ቀንበር አቃልልልን ለሚሉኝ ሕዝብ እመልስላቸው ዘንድ የምትመክሩኝ ምንድር ነው? አላቸው። ከእርሱም ጋር ያደጉት ብላቴኖች። አባትህ ቀንበር አክብዶብናል፥ አንተ ግን አቃልልልን ለሚሉህ ሕዝብ። ታናሺቱ ጣቴከአባቴ ወገብ ትወፍራለች። አሁንም አባቴ ከባድ ቀንበር ጭኖባችኋል፥ እኔ ግን በቀንበራችሁ ላይ እጨምራለሁ፤ አባቴ በአለንጋ ገርፎአችኋል፥ እኔ ግን በጊንጥ እገርፋችኋለሁ በላቸው ብለው ተናገሩት። ንጉሡም በሦስተኛው ቀን ወደ እኔ ተመለሱ ብሎ እንደ ተናገረ ኢዮርብዓምና ሕዝቡ ሁሉ በሦስተኛው ቀን ወደ ሮብዓም መጡ። ንጉሡም ሽማግሌዎች የመከሩትን ምክር ትቶ ለሕዝቡ ጽኑ ምላሽ መለሰላቸው።

እንደ ብላቴኖችም ምክር። አባቴ ቀንበር አክብዶባችሁ ነበር፥ እኔ ግን በቀንበራችሁ ላይ እጨምራለሁ፤ አባቴ በአለንጋ ገርፎአችሁ ነበር፥ እኔ ግን በጊንጥ እገርፋችኋለሁ ብሎ ተናገራቸው። እስራኤልም ሁሉ ንጉሡ እንዳልሰማቸው ባዩ ጊዜ ሕዝቡ ለንጉሡ። በዳዊት ዘንድ ምን ክፍል አለን? በእሴይም ልጅ ዘንድ ርስት የለንም። እስራኤል ሆይ፥ ወደ ድንኳኖቻችሁ ተመለሱ፤ ዳዊት ሆይ፥ አሁን ቤትህን ተመልከት ብለው መለሱለት። እስራኤልም ወደ ድንኳኖቻቸው ሄዱ። (መጽ ነገ ቀዳ ም 12፦4) ሙሉ ታሪኩን ስናነብ በንጉሥ ሮብዓም እብሪት ጥጋብ ብዙም ሳይቆይ እስራኤል ከሁለት እንደተከፈለች ከዚህ አሳዝኝ ታሪክ እንማራለን። ስለዚህ አቶ ኃ/ማርያም በሥልጣን ላይ በሚቆዩበት የሚቀጥሉት ጥቂትዓመታት የተበላሸውን ሊያስተካክሉ፣ የተጣመመውን ሊያቃኑ፣ በግዞትና በእስር አለ አግባብ የሚንገላቱትን ጉዳያቸውን ሊመለከቱና ነፃ ሊያወጧቸው፤ እንዲሁም ይህች ጥንታዊ ሀገራችን አንድነቷ ተጠብቆ ሕዝቦቿም በፍጹም ዲሞክራሲና ፍትሕ ሊመሩ የሕሊና እና ኢትዮጵያዊ ግዴታ አለባቸው። በቤተ ክህነቱም ቢሆን ወደፊት በመንበሩ የሚቀመጠው ፓትርያርክ ሕገ ቤተ ክርስቲያንን ተከትሎ መሰየም ሲኖርበት፤ በአጠቃላይ በአገልግሎት ከድቁና አንስቶ እስከ ላይ ፕትርክናው ድረስ የተሾሙ ካህናት ሕይወታቸውን እንደ ቅዱስ መጽሐፉ ትዕዛዝ ሊያስተካክሉና፤ የተጣለባቸውን ኃላፊነት በቅንነት ሊወጡ ይገባል።
አንድ ካህን ሥልጣነ ክህነት ሲቀበል መሥዋዕትነት ድረስ የመቀበል መከራ እንደሚደርስበት ማወቅ አለበት። ለምሳሌ ከሐዋርያቱ አንዱ የሆነው ይሁዳን ለመተካት ከዮሴፍና ማትያስ አንዱን ለመምረጥ ዕጣ አውጥተው ነበር። የሐዋርያት ሥራ (ምዕራፍ 1፤26) እንደሚለውም በማትያስ ላይ ዕጣ ወደቀበት/ወጣበት እንጂ ወጣለት አይልም ምክኒያቱም የተመረጠበት ዓላማ መስዋዕትነት የሚቀበልበት ነገር ግን ዋጋው በዚያኛው ዓለም የሚያገኘው ስለ ነበረ ነው። ስለዚህ መንፈሳዊ ሥልጣን ለመቀበል ስንዘጋጅ ታዲያ በትክክል መንፈሳዊ ኃላፊነታችንን ለመወጣትና መስዋዕትነት ለመቀበል ዝግጁ ነን ወይብለን ራሳችንን መጠየቅ ያስፈልጋል። ከላይ እንደገለጽኩት ባለፈው አባ ጳውሎስን ለማስመረጥ የተደረገው ዐይነት ማጭበርበር እንዳይደገም፤ በተለይም ደግሞ የወያኔን ዓላማ አሁን በደንብ ስላወቅን፤ ቅዱስ ሲኖዶስ አለምንም መንግሥት ተጽዕኖ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን በሚያዘው መንገድ መንበሩን ማስከበር ይኖርበታል። በመንበሩ ላይ የሚቀመጠውም ፓትርያርክም ኦርቶዶክሳዊ ሃይማኖታችን የምትስፋፋበትን፤ ፍትህና ርትዕ በሀገሪቱ ላይ እንዲሰፍን የሚችለውን ማድረግ ይጠበቅበታል። በአጠቃላይ በአመራር ላይ ያሉም ይሁኑ ወይም የኢትዮጵያ ሕዝብ ይህች ጥንታዊ ሀገራችን አንድነቷ ተጠብቆ፣ ሕዝቦቿ ተከባብረው በአንድነት በፍቅር እንዲኖሩ ሊታገል ይገባዋል። ፍቅርና ቅንነት ካለ ይህች ሀገራችን ከእኛ አልፎ ለሌሎች ሀገሮች ትተርፋለች። የኢትዮጵያ ሕዝብ ለቂም በቀል የፈጠነ አይደለም፤ የሆኖ ሆኖ ያለው ስሕተትና አሳፋሪ ተግባሮች ግን ካልተስተካከሉ ጥፋትን ያስከትላል።
ለምሳሌ ባለፈውሉሉ ከበደ ወደፊት ምን ማድረግ እንደሚገባ "ህልሜ ቅዥት ባይሆን" ሲሉ የጻፉት ጥሩ ማሳሰቢያነው። (http://www.ethiomedia.com/assert/hilme_qzhett_baihon.pdf) አለበለዚያ ግን የግፍ ጽዋ ሲሞላ እግዚአብሔር ሰው ሊገምት እና ሊያስብ በማይችለው ሁኔታ ነገሮችን ይለዋውጣል። አምላካችን እንደ እኛ ቶሎ ቸኩሎ የሚበቀል ስላልሆነ ለንስሐ ጊዜ ይሰጣል። አሁንም ያሉ መሪዎች በትዕቢት ተወጥረው፣ አምላክነቱን ንቀው፣ ሕዝብ መበደልን ከቀጠሉ፤ አወዳደቃቸው ከትላንትናዎቹ ባልተሻለ ሁኔታ ይሆናል። የሞቱትም ሆነ አሁን በሕይወት ያሉት የሠሩት በደል ወደፊት ሲወጣ፤ ይህ ሙት ወቃሽ አታድርገኝ ብሎ እንባውን ያፈሰሰላቸው ሕዝብ ምን ነክቶኝ ነበር ብሎ ራሱንየሚወቅስበት ጊዜ ይመጣል። አሁንም ሁላችንም መከፋፈሉን፣ መጠላለፉን፣ ጎጠኝነቱን፣ በጎሪጥ መተያየቱን ትተን በአንድነት ሆነን እግዚአብሔር አምላክ ሆይ ሕዝብህንና ይህቺን ቅድስት ሀገር ጠብቅ ብለን ልንጸልይ ይገባል።
ይደነቃል ፍርዱ
ይደነቃል ፍርዱ
http://www.ethiolion.com/
No comments:
Post a Comment