ታህሳስ ፲(አስር) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ለረጅም አመታት በተለያዩ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ውስጥ በከፍተኛ የኃላፊነት ደረጃ ሲሰሩ የቆዩት ዶ/ር ኃይሉ አርአያ ከአንድነት ፓርቲ ኃላፊነታቸው በፈቃዳቸው ተነሱ።
የፓርቲው ብሔራዊ ም/ቤት ባለፈው እሁድ ባካሄደው ስብሰባ ላይ የዶ/ር ኃይሉ ጥያቄን በመቀበል በእሳቸው ምትክ ወጣት ዳንኤል ተፈራን ተክቷል።
የፓርቲው ብሔራዊ ም/ቤት ባለፈው እሁድ ባካሄደው ስብሰባ ላይ የዶ/ር ኃይሉ ጥያቄን በመቀበል በእሳቸው ምትክ ወጣት ዳንኤል ተፈራን ተክቷል።
ዶ/ር ኃይሉ አርአያ ከኃላፊነታቸው መነሳት የፈለጉት ከጤና ችግር እና ኃላፊነትን ለወጣቶች ለማስረከብ ካላቸው ፍላጎት በመነሳት መሆኑን ተናግረዋል።
ዶክተር ሀይሉ ቀደም ባሉት ዓመታት በ ኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ(ኢዴፓ) ውስጥ በአመራርነት፣ ከዚያም በቅንጅት ለአንድነትና ዴሞክራሲ ውስጥ በሥራ አስፈፃሚነትና በህዝብ ግንኙነት ሀላፊነት ሰለቸኝና ደከመኝ ሳይሉ በብቃት፣በቅንነትና በታማኝነት ያገለገሉ ሲሆን፤ በተቃዋሚው ጎራ ውስጥ ባሳለፉት ረዥም የትግል ዓመታት በተደጋጋሚ እስከመከሰስና እስከመታሰር ድረስ ዋጋ ከፍለዋል።
ዶክተር ሀይሉ አርአያን በቅርብ የሚያውቋቸውና አብረዋቸው የሠሩ ሁሉ ስለ ብስለታቸው፣ ስለ ስክነታአውና እጅግ ጥሩ ባህርይ የተላበሱ ሰው ስለመሆናቸው ይመሰክሩላቸዋል።
No comments:
Post a Comment