Saturday, December 29, 2012

የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት መተማ ወረዳ አለንጌ በተባለ ቦታ ጥቃት ፈፀመ


ታህሳስ  ፳(ሃያ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት ታህሳስ 18 ቀን 2005.ዓ.ም በመተማ ወረዳ ልዩ ስሙ አለንጌ በተባለው አካባቢ ከመከላከያ ሰራዊት ጋር በተካሄደው ውጊያ 8 የጠላት ወታደሮችን ገድሎ 11 በማቁሰል ከፍተኛ የህይወትና የንብረት ኪሳራ ማድረሱን ግንባሩ ገልጿል።
ግንባሩ በርካታ የጦር መሳሪያዎችን መማረኩንም ገልጿል።
መንግስት በጉዳዩ ዙሪያ የሰጠው መልስ የለም። ዜናውንም ከገለልተኛ ወገን ለማረጋገጥ አልተቻለም።                                      
                    

በኢሳት እርዳታ ሳጅን ሽታየ ወርቁ ራሱን ከማጥፋት ተቆጠበ 

  ታህሳስ  ፳(ሃያ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ከሁለት ቀናት በፊት በደቡብ ክልል በዳዉሮ ዞን በሎማ ወረዳ ገሣ ከተማ ላይ ይደረግ በነበረዉና የሎማ ዲሣ ህዝብ የአዲስ ወረዳ አግባብነት ስብሰባ ላይ የግል አስያየቱን የሰጠዉ የፖሊስ ባልደረባ ሳጅን ሽታየ ወርቁ እራሱን ከምግብ እና ከውሀ ለ24 ሰዓታት ከልክሎ በወጣበት ዛፍ ላይ ራሱን ከማጥፋቱ በፊት ከኢሳት ጋር ተገናኝቶ አላማውን ለህዝብ ይፋ ለማድረግ በመፈለጉ የኢሳት ባልደረቦች በስልክ አግኝተው ራሱን እንዳያጠፋ በመምከራቸው፣ ከድርጊቱ ታቅቦ በፖሊስ ታጅቦ ወደ እስር ቤት ተጉዟል።
ሣጅን ሽታዬ ወርቁ ሺበሺ ከሁለት ቀናት በፊት “ወረዳ አያስፈልም ካላችሁ ለምን ድሮ ለሲዳማ 9 ለወላይታ 5 እያለችሁ ሸንሽናችሁ ሰጣችሁ በማለት” በስብሰባ ላይ በሰጠዉ አስተያየት ምክንያት በዕለቱ ለስብሳበ የወጡ የወረዳዉ የመንግሥት ሠራተኞች የእርሱን ሀሳብ በመደገፍ ስብሰባዉን አቋርጠዉ በመዉጣታቸዉ ምክንያት ከትላንቱ ስብሰባ የወረዳዉ ፖሊስ አባላት በሙሉ እንዳይገቡ መከልከላቸዉን መግለጻችን ይታወሳል፡፡
ሳጅን ሽታየ በእለቱ ያጋጠመውን ድርጊት በዝርዝር አስረድቷል ።
     
   
        

የባለራእይ ወጣቶች ማህበር አባላት ጉባኤ እንዳናካሂድ ተከለከልን አሉ


       ታህሳስ  ፳(ሃያ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የማህበሩ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ወጣት ብርሀኑ ተግባረእድ እና ምክትል ሊቀመንበሩ ወጣት ሚካኤል አለማየሁ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ጉባኤያቸውን ለማዘጋጀት አዳራሽ ፍለጋ ቢንከራተቱም የጸጥታ  ሀይሎች በሚያደርሱባቸው ተጽእኖ ለመከራየት አልቻሉም።
ወጣቶቹ በመጪው እሁድ ጉባኤ ለማካሄድ የተከራዩትን አዳራሽ፣ የጸጥታ ሀይሎች ባሳረፉት ጫና ሆቴሉ ፈቃደኝነቱን እንደሰረዘባቸው ገልጸዋል።
ሀሳባችንን በነጻነት መግለጽ አልቻልንም የሚሉት ወጣቶቹ፣ ለማን አቤት እንደሚባልም ግራ እንደገባቸው ገልጸዋል
ከወጣቶቹ ጋር ያደረግነውን ሙሉ ቃለምልልስ በትኩረት ዝግጅታችን መከታተል ትችላለችሁ።

No comments:

Post a Comment