Tuesday, December 31, 2013

በአዲስ አበባ የቅርብ ጊዜ የጅምላ መቃብር ተገኘ


mekabir 1

mekabir
ሁኔ አቢሲኒያዊ ከፒተርቦሮው ዩ.ኬ
ነገሩ የተከሰተው አርብ እና ቅዳሜ እለት ነው ከስድት ኪሎ ወደ ፈረንሳይ በሚወስደው መንገድ ላይ በሚገኘው የጃንሜዳ ጦር ካምፕ(በቀድሞ ስሙ ሦስተኛ ሻለቃ) ግቢ ውስጥ በትንሹ ወደ 6 የሚጠጉ አስከሬኖች በብርድልብስ እንደተጠቀለሉ ተገኝተዋል! አስከሬኖቹ ሊገኙ የቻሉት ለመንገድ ስራ የጦር ካምፑ ግቢ አጥር ወደ ውስጥ ፈርሶ መቆፈር ነበረበት፡፡ በዚህ ሂደት ላይ ነው እንግዲህ በስካቫተር ሲቆፈር በመጀመሪያ ሁለት አስከሬኖች በብርድልብስ እንደተጠቀለሉ ተንከባለሉ፡፡ በዚህ የተደናገጡት ሰራተኞች ለጊዜው ስራቸውን ያቋረጡ ሲሆን በበነጋው ቅዳሜ እለት ረፋዱ ላይ በሌላ አቅጣጫ ቁፋሮ ሲያደርጉ በዛም በኩል እንዲሁ በብርድ ልብስ የተጠቀለሉ አራት አስከሬኖች በተመሳሳይ ሁኔታ ከአፈሩ ዉስጥ ተገኙ፡፡ በዚህ መሃል ከጦር ካምፑ አካባቢ የተወሰኑ መኮንኖችና ከፍተኛ ማዕረግ(ጄነራሎች) በትከሻቸው ላይ ያለባቸው ሰዎች ወደ ቦታው በመምጣት ስራው እንዲቆም ትእዛዝ ያስተላለፉ ሲሆን በአካባቢው የነበረውንም ሰው ከቦታው አባረው በትነዋል፡፡
በስፋራው ተገኝተው ሁኔታውን ሲከታተሉ እና በስራው ላይም ተሳታፊ የነበሩ ለሰማያዊ ፓርቲ ቅርብ የነበሩ ሰዎች ፎቶ ለማንሳት ጥረት ቢያደርጉም በወታደሮቹ ተመናጭቀዉ ክልከላ ደርሶባቸዋል፡፡ እንደምንጮቻችን እና የምስል ማስረጃዎች ከሆነ አስከሬኖቹ የተጠቀለሉበት ብርድልብስ አንዳችም ሳይቀደድና ሳይበሰብስ ከነአዲስነቱ መገኘቱ ጅምላ ግድያው በቅርቡ የተፈፀመ ሊሆን እንደሚችል ከፍተኛ ጥርጣሬን አሳድሯል። በጉዳዩ ላይ ማጣራት ለማድረግ ሙከራ ያደረጉት ሰማያዊ ፓርቲ አባሎችንም ፊት እንደተነሳቸውና ለማናገርም ፈቃደኛ የሆነ ሰው አለማግኘታቸዉንም እንዳዉም ቦታውን ባስቸኳይ እንዲለቁ ከሀይለ ቃል ጋር መታዘዛቸውንም ጨምረው ተናግረዋል፡፡
ከወታደሮቹ መሀከል የሆነ አንድ ስምና ሀላፊነቱ ለጊዜው ያልታወቀ ምናልባትም የግቢው አዛዥ ሊሆን የሚችል ሰው ይህ ግቢ ሶስት ስርዓቶችን ያገለገለ በመሆኑ የማናቸው እንደሆነ ለማወቅ ባይቻልም ሰዎች በመሆናቸው ክቡር ናቸውና አፈር አልብሷቸው ብሎ ትእዛዝ ሲሰጥ የሰሙ የአይን ምስክሮች ለምንጫችን ስለሁኔታው አስረድተዋል! በሁኔታው በአካባቢው የነበሩ ሰዎች በእጅጉ ያዘኑና የተደናገጡ ሲሆን የሚመለከታቸው አካላትና መንግስት ይህne ጉዳይ አጣርተው ለህዝብ ይፋ እንዲሆን አስተያየት ሲሰጡም ተደምጠዋል። በአሁኑ ሰዓት በስፍራው ምንም አይነት የስራ እንቅስቃሴ አይታይም፡፡ አካባቢውም በቆርቆሮ ተከልሏል፡፡
ተጨማሪ ብርድልብሱ ደብረ ብርሃን ሲሆን ዲዛይኑ በኢህአዲግ ዘመን በቅርብ የተጀመረው ነው።
Ze-Habesha

Sunday, December 29, 2013

Abune Mathias arrested and released


Ethiopian Review:-The TPLF-installed illegal patriarch in Ethiopia, Abune Mathias, has been temporarily placed under arrest and was released after being interrogated for 72 hours by Tsegaye Berhe, National Security Adviser to the Prime Minister, and other security officials, according to Ethiopian Review sources in Addis Ababa.Leaders of the TPLF junta are apparently upset with statements that have been uttered by Abune Mathias over the past 3 weeks that were critical of the tribal regime. In one particular meeting, Abune Mathias was heard saying that much of the problems facing the church are caused by the ruling party.The Ethiopian Orthodox Church’s
administration in Addis Ababa is currently paralyzed by a growing leadership crisis. Many church leaders are in open revolt and have refused to take orders from the Holy Synod.
Abune Mathias arrested and released

በቁም እስር ላይ ያሉት ብጹእ ኣቡነ ማቲያስ ከአሜሪካን መልስ በደህንነት ቢሮ ለ72 ሰአታት ታስረው ነበር::



ኢትዮጵያ ውስጥ ኢትዮጵያዊ አሸባሪ የለም::" ብጹእ አቡነ ማትያስ


"ከኦሮሞ እና አማራ ጳጳሳት ጋር ትፈተፍታላችሁ::" አቶ ጸጋዬ በርሄ ..የአፋኝ ደህንነቶች ሹም

በጳጳሳቶች እና በፌዴራሉ ሚኒስትሮች መካከል በስብሰባ ላይ በተነሳው አለመግባባት እና የጳጳሶቹ ድምጽ በደል እና ግፍን በማስተጋባቱ እንዲሁም ለመጣው ችግር ሁሉ ተጠያቂው የኢሕኣዴግ መንግስት ነው:ማለታቸውን ተከትሎ እንዲሁም ጳጳሱ አሜሪካን ተጉዘው ከመጡ በኋላ የሚያሳዩትን የቁጥብነት ባሕሪ ተከትሎ እንዲሁም በቤተክህነት ውስጥ የሚወስዱትን አስተዳደራዊ እርምጃ ያልጣመው ኢሕኣዴግ በአቶ ጸጋዬ በርሄ የሚመራው የአፈና እና የቶርች ቡድን ብጹእ አቡነ ማትያስን ለ72 ሰአታት በደህንነት ቢሮ በቁጣ እና በስድብ በማስጠንቀቂያ አሰቃይተው እና አንገላተው ወደ መኖሪያቸው እንደመለሱዋቸው ከደህንነት ቢሮ ምንጮቻችን ገልጸዋል::ጻጻሱ ለ72 ሰአታት ከመኖሪያቸው ሲታጡ በጠቅላይ ቤተክህነት ውስጥ ካድሬ ቄሶች አቡኑ ለህክምና ውጪ አገር ሂደዋል የሚል ወሬ ሲያስወሩ ነበር::

ብጹ አቡነ ማትያስ በደህንነት ቢሮ ውስጥ በተሰጣቸው ማስጠንቀቂያ መሰረት ከአገሪቱ የመንግስት አካልት ጋር እንዲሁም ከጠቅላይ ቤተክህነት ውስጥ ካሉ የትግራይ ተወላጆች ጋር በቅርበት እንዲሰሩ የተነገራቸው ሲሆን በዙሪያቸው ያሉ የሲኖዶስ አባላትን ፊት እንዳይሰቷቸው እና አማራ እና ኦሮሞ ጳጳሳቶች እንቅስቃሴያቸው ሁሉ ከአቡነ መልከጻዲቅ እና ከተቃዋሚ ሃይላት መሆኑ አውቀው ጥንቃቄ እንዲወስዱ እንዲሁም አስተዳደራዊ ስራዎችን ለንብረዑድ ኤልያስ አብርሃ እንዲያስረክቡ ተነግሯቸዋል:: ከሳቸው ጋር በረዳትነት አቡነ ሳሙኤል እንዲሰሩ መመሪያ የተሰጣቸው መሆኑ ታውቋል::

ብጹእ አቡነ ማቲያስ በደህንነት ቢሮ የአቶ ጸጋዬ በርሄ ቡድን ማስፈራሪያ ሲሰጣቸው ፊታቸውን ቅጭም አድርገው በሃዘን እና በቁጭት ስሜት ያዳምጡ እንደነበር ታይተዋል:: መልስ ሲሰጡ የነበሩት እጅግ ዘግይተው በትካዜ እንደነበር ታውቋል::አሸባሪዎችን መዋጋት አለብዎ ሲባሉ በኢትዮጵያ ምድር ኢትዮጵያዊ አሸባሪ የለም ብለው የመለሱት አቡኑ አብዛኛው መልሶቻቸው "...እስኪ ካላችሁ ይሁን እግዛብሄር እንደፈቀደው...' የሚል እንደነበር የደህንነት ቢሮ ምንጮች ጠቁመውናል::

በዚህም መሰረት አቡነ ማትያስ የፖለቲካ ፍጆታ በሚያስፈልጋቸው መንፈሳዊ ስብሰባ ላይ አይገኙም:: በተገኙበትም ቦታ ደሞ ስለ ልማት ካልሆነ በቀር ስለ አስተዳደራዊ ጉዳይ እና ስለ ብሶት ቀስቃሽ ንግግር እንዳያደርጉ ተነግሯቸዋል:: በአሁኑ ወቅት ማንኛውም የአገር ውስጥ እንቅስቃሴያቸው በደህንነት አይን ስር ያለ ሲሆን የቁም እስር ላይ ናቸው::

  ሚኒሊክ ሳልሳዊ

በደቡብ ሱዳን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን መንግስት እንዲታደጋቸው እየተማጸኑ ነው

ኢሳት ዜና :-ዩኒቲ በሚባለው ግዛት ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያን በጦርነት አጣብቂኝ ውስጥ መገኘታቸውንና ህይወታቸው አደጋ ውስጥ መውደቁን ተናግረዋል።
በግዛቱ ውስጥ በአንድ የመንገድ ስራ ድርጅት ውስጥ ተቀጥረው የሚሰሩ 6 ኢትዮጵያውያን እንደተናገሩት በሁለቱ ተፋላሚ ሀይሎች መካከል የሚደረገውን የተኩስ ልውውጥ ለማምለጥ ያለፉትን ሁለት ቀናት በከባድ ማሽነሪዎች ውስጥ በመደበቅ ለማሳለፍ ተገደዋል። በአካባቢያቸው 2 ኢትዮጵያውያን መገደላቸውንና 3ቱ ደግሞ መቁሰላቸውን ተናግረዋል።
እስካሁን ድረስ ምን ያክል ኢትዮጵያውያን እንደሞቱ ባይታወቅም፣ የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ በአገሪቱ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን በማነጋገር እንደዘገበው የሞቱ ኢትዮጵያውያን ቁጥር እስከ ታህሳስ 17፣ 2006 ዓም ድረስ ቢያንስ 30 ይደርሳል።
ኢሳት ያነጋገራቸው ኢትዮጵያውያን እንደሚሉት መንግስት እስካሁን ድረስ ዜጎቹን ለመሰብሰብ ጥረት እያደረገ አይደለም። ጎረቤት አገሮች ኬንያና ኡጋንዳ ዜጎቻቸውን ሲያስወጡ የኢትዮጵያ መንግስት ምንም አይነት እርምጃ ለመውሰድ አለመፈለጉ ለብዙዎች እንቆቅልሽ ሆኗል። ኢትዮጵያውያን አሁንም መንግስት እንዲደርስላቸው ጥሪ አቅርበዋል
በጆንግሌ ግዛት የተደፈሩ 4 ኢትዮጵያውያን ጁባ ውስጥ በሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሆስፒታል ውስጥ ህክምና እንዲያገኙ ተድርጓል።x
ይህ በእንዲህ እንዳለ የምስራቅ አፍሪካ መንግስታት በናይሮቢ ኬንያ ያደረጉትን ስብሰባ ተከትሎ የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር በግላቸው ተኩስ እንደሚያቆሙ አስታውቀዋል። አገራቱ የመንግስትን እርምጃ የደገፉ ሲሆን፣ የኬንያው መሪ ኡሁሩ ኬንያታ በዲሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠን መሪ በሀይል ለማውረድ የሚደረገውን እንቅስቃሴ እንደማይደግፉ ገልጸዋል።
የተቃዋሚዎች መሪ የሆኑት ሪክ ማቻርም በተመሳሳይ መንገድ ተኩስ እንዲያቆሙ የምስራቅ አፍሪካ መሪዎች ተማጽኖ አሰምተዋል። መሪዎቹ በሚቀጥሉት 4 ቀናት ፊት ለፊት ተገናኝተው እንዲወያዩ ኢጋድ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል።እስካሁን በተካሄደው የእርስ በርስ ጦርነት ከ1 ሺ በላይ ሰዎች መገደላቸውን አለማቀፍ የመገናኛ ብዙሀን ዘግበዋል;፡

የአንድነት ጠቅላላ ጉባኤ አባላት በእምባ የተራጩበትን ክስተት ይመልከቱ

http://freedom4ethiopian.wordpress.com/2013/12/28/908-6/

Wednesday, December 25, 2013

ቆይታ ከጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ እና ከአቶ በቀለ ገርባ ጋር


Woubshet-Taye-300x242
ሰሞኑ ጥቂት ጋዜጠኞች ወደ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት አምርተን ነበር። ወደ ማረሚያ ቤቱ የሄድነው ወዳጃችን ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬን ለመጠየቅ ነበር።
ጋዜጠኛ ውብሽት ከኩላሊት ህመም ጋር በተያያዘ ከዝዋይ ማረሚያ ቤት ወደ ቃሊቲ መዛወሩን በመስማታችን ነበር ለጥየቃ ወደ ቃሊቲ ያመራነው።
ከቀኑ አምስት አካባቢ ይሆናል። አስፈላጊውን ፍተሻ አጠናቀን ወደ ውስጥ የዘለቅነው። ቀኑ የአዘቦት ቀን በመሆኑ በማረሚያ ቤቱ የጠያቂዎች መጨናነቅ
አልነበረም። ፍተሻውም ሆነ ሥነስርዓቱ ሰላማዊ ነበር። ታራሚዎችና ጠያቂዎች ወደሚገናኙበት ቦታ ስንደርስ ማንን ለመጠየቅ እንደመጣን ተናግረን ውብሸትን
መጠባበቅ መርን። ሲቪል ከለበሱ የማረሚያ ቤቱ አስተባባሪዎች አንዱ የድምፅ መነጋገሪያ (ማይክ) አንስቶ ከፍ ባለ ድምፅ ደጋግሞ የውብሸትን ስም ጠራ።
ብዙም ሳይቆይ ውብሸት መጣ። በዚህ አጋጣሚ የማረሚያ ቤቱ አስተባባሪዎች ያሳዩን ትብብር በመልካምነቱ ሊጠቀስ የሚገባው ነው። ትብብራቸውና ቀናነታቸው
የተለየ ስለነበር ሊመሰገኑ ይገባል። ውብሸት በርከት ያልን የሙያ አጋሮቹን ሲመለከት ፊቱ ላይ የመደነቅ ስሜት ይታይ ነበር። ፈጠን ባለ እርምጃ ሣቅ ባሞቀው
ገፅታ እኛ ወዳለንበት አካባቢ መጣ። በእንጨት በታጠረው ፍርግርጉ ላይ እየተንጠራራን ሰላምታ ተለዋወጥንና ወጋችንን ቀጠልን። የወጋችን መጀመሪያ የጤንነቱ ጉዳይ
ነበር። እንደተባለውም ካለፉት አራት ወራት ወዲህ የኩላሊት ህመም ላይ መሆኑን ነገረን። “ከእኔ የባሱ አልጋ ላይ የወደቁ ታራሚዎች እያሉ የእኔን ጉዳይ ማስጮህ አልፈለኩም።
ነገር ግን ሕመሙ ከዕለት ወደ ዕለት እየጨመረ በመምጣቱ ሕክምና እንዳገኝ ጥያቄ አቀረብኩ” ብሎናል። “በተፈጥሮዬ መድሐኒት መውሰድ አልወድም” የሚለው ጋዜጠኛ ውብሸት ህመሙ ቢበረታም ታመምኩ ብዬ ጥያቄ ማቅረቡን አልፈለኩትም። ነገር ግን ከውሃ ሽንቱ ጋር ደም እየተቀላቀለ መውጣቱ በኩላሊቱ ላይ ከበድ ያለ ችግር ማጋጠሙን በመረዳቱ ለህክምና ጥያቄ ለማቅረብ መገደዱን ይገልፃል። ባቀረበው የህክምና ጥያቄ መሠረት በመጀመሪያ አልትራሳውንድ መነሳቱን፣ በኋላም ውጤቱ በመጥፋቱ በድጋሚ መነሳቱንና
ውጤቱም በኩላሊቱ ውስጥ አሸዋ የሚመስል ነገር የሚያሳይ መሆኑን ገልጾልናል። ውጤቱ ይሄን ቢመስልም የማረሚያ ቤቷ ዶክተር “ውሃ ጠጣበት” ከማለት ባለፈ ህክምና አለማግኘቱን ገልጿል። ወትሮውንም “በተፈጥሮዬ በርከት ያለ ውሃ እጠጣለሁ” የሚለው ጋዜጠኛ ውብሸት “ውሃ ጠጣበት” የሚለው የሕክምና ምክር ባለፈ ተጨማሪ ሕክምና እንደሚያስፈልገው ተናግሯል። በዝዋይ ማረሚያ ቤት የታንከር ውሃ በመጠጥነት መጠቀሙ ምናልባትም ለኩላሊት ህመሙ መንስኤ ሊሆን እንደሚችል የሚጠቅሰው ውብሸት፤ ለዚሁ ችግር ትኩረት እንዲሰጥ በዚሁ አጋጣሚ ገልጿል። “ሕክምና እንዳላገኝ የተደረገው ሆን ተብሎ ነው ብዬ መቀበል ይቸግረኛል” ያለን ጋዜጠኛ ውብሸት ታራሚዎች ተገቢውን ህክምና የማግኘት በዓለም አቀፍ ደረጃ የተያዙ ሰዎች መብት ከመሆን ባለፈ የሰብአዊነት ጉዳይ መሆኑን አስታውሷል። በሽብርተኝነትም ሆነ በሌላ በማናቸውም መልክ የተከሰሱ ፍርደኞች
ሚዛናዊና ፍትሐዊ የሕክምና አገልግሎት እንዲያገኙ ማድረግ ተገቢ መሆኑንም ጠቅሷል። የማረሚያ ቤት ህይወት በርካታ አስቸጋሪ መልኮች እንዳሉት ፍርደኞችም ቢሆኑ መብታቸው መከበር እንዳለበት ጋዜጠኛ ውብሸት ሳይናገር አላለፈም። በአሁኑ ወቅት ያለበት ማረሚያ ቤት ውስጥ ከሁለት መቶ በላይ ታራሚዎች ጋር መታሰር አስቸጋሪ መሆኑንም ነግሮናል። ከአእምሮ መታወክ ጋር በተያያዘ የታሰሩ ፍርደኞች ጉዳይ በሌሎች ፍርደኞች ላይ ጉዳት የሚያደርሱበት አጋጣሚ በመኖሩንና ለዚሁ ችግርም መፍትሄ መፈለጉ ተገቢም ተመካሪም እንደሆነ ገልጿል። ጋዜጠኛ ውብሸት ይሄንን ሁሉ ነገር ያጫወተን ቡና እየጋበዘን ነበር። ውብሸት ማረሚያ ቤት ሆኖ “ብሉ ጠጡ” ያለን እቤቱ ብንሄድ ምን ሊሆን እንደሚችል ታሰቦኝ ነበር። በዕለቱ ልንጠይቀው የሄድነውን ሁሉ እንደየምርጫችን ቡና፣ ማኪያቶና ለስላሳ ጋብዞናል። ግብዣው ፍቅር የተሞላበትና ደጋግመን እንድንጠይቀው የሚያደርግ ነበር።
ውብሸትን እያነጋገርንበት በነበረበት ወቅት አንድ አዛውንት መጥተው ሰላም አሉን። አዛውንቱ በተመሳሳይ በሽብርተኝነት ክስ ጥፋተኛ ተብለው የ13 ዓመት ፍርደኛ ናቸው።
ወዲያው ደግሞ አንድ ጎልማሳ ፍርደኛ መጥቶ ሰላምታ ሰጠን። ይህም ሰው የተመሳሳይ ክስ ፍርደኛ ነው። ይህንን ፍርደኛ ከሌሎች የሚለየው ሜዲካል ዶክተር መሆኑ ነው።
ጋዜጠኛ ወዳጃችንን ለመጠየቅ ሄደን “እነእገሌ ደህና ናቸው” የሚል ጥያቄ መነሳቱ አይቀርም። “እነእገሌ” ከተባሉት መካከል አቶ በቀለ ገርባ አንዱ ነበሩ። በአጋጣሚ እኚህ
ምሁር ፍርደኛ ፍርዳቸውን እየፈፀሙ ያሉት ከእነ ውብሸት ጋር ስለነበር ተጠርተውልን መጡ። አቶ በቀለ ገርባ 26 ዓመት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የስነ-ልሳን መምህር እንደነበሩ
ቢነግሩንም የሰውነት አቋማቸው ግን ገና 26 ዓመታትን የሚሰሩ ያስመስላቸዋል። ቁምጣ በነጠላ ጫማ ተጫምተዋል። ዘና ባለ መንፈስ ሰላምታ ተለዋወጥን። አቶ በቀለ ስክነትና
መረጋጋት በፊታቸው ላይ ይንፀባረቃል። ሲናገሩ በስሜት ሳይሆን በረጋ መንፈስ ነበር። በሽብርተኝነት ክስ ጥፋተኛ መሆናቸውበፍርድ ቤት በመረጋገጡ 3 ዓመት ከ8 ወር
ነበር የተፈረደባቸው። በመጀመሪያ ስምንት ዓመት ቢፈረድባቸውም ተከራክረው ወደ 3 ዓመት ከስምንት ወር ዝቅ በማስደረጋቸው የአመክሮ ጊዜአቸው ተቃርቧል። ይህንን መብት
የሚያገኙ ከሆነ በመጪው ጥር እሳቸውና ቃሊቲ ሊለያዩ ይችላሉ። አቶ በቀለ በማረሚያ ቤት ቆይታቸው ወቅት ያሳዩት መልካም ባህሪ የአመክሮ መብታቸውን እንደማያሳጣቸው ተስፋ አድርገዋል። “የሆነው ሁሉ የምጠብቀው ነበር” የሚሉት አቶ በቀለ፤ በዚህም ወቅት በሀሰት ጥሩ ያልሆነ አጋጣሚ በስተቀር የሚረብሻቸው ነገር እንደሌለ ነበር
የጠቀሱት። የሁለት ወጣት ልጆች አባት የሆኑት አቶ በቀለ በተመሳሳይ ክስ ጥፋተኛ ሆኖ የዕድሜ ልክ ፍርደኛ ለሆነው አንዱዓለም አራጌ የነበራቸውን አድናቆት “የተለየ” ወይም
(Unique) በሚል ቃል ነበር የገለፁት። ለአንድ ዓመት አብረው በታሰሩበት ወቅትና የመድረክ የስራ አስፈፃሚ አባል ሆነው በሰሩባቸው ጊዜአት ይበልጥ መተዋወቃቸውን ይናገራሉ። አቶ በቀለ በታሰሩበት ወቅት ባለቤታቸውም ከስራ በመባረራቸው ለጥቂት ጊዜያት በቤተሰባቸው ላይ መጉላላት ቢያጋጥምም አሁን ግን ባለቤታቸው የግል ስራ በመስራት ኑሮን ለማሸነፍ እየተጣጣሩ መሆኑንም፣ ልጆቻቸውም ቢሆኑ አንዳንድ ለጋሽ ሰዎች እየረዱአቸው እየተማሩ መሆኑን በመጥቀስ ፈጣሪያቸውን አመስግነዋል። የማረሚያ ቤት ህይወት አስቸጋሪ መልኮችን በሰፊው ያወጉን አቶ በቀለ በታራሚዎች መካከል እኩልነት ሊኖር እንደሚገባም መስክረዋል። በማረሚያ ቤት አቅርቦት ከቃሊቲ ይልቅ ዝዋይ በተነፃፃሪ ሻል
ያለ መሆኑንም ሳይጠቅሱ አላለፉም።አቶ በቀለም ሆኑ ጋዜጠኛ ውብሸት የሀገሪቱ የፖለቲካ ልዩነት መቻቻልና በመግባባት መንፈስ እንዲቃኝ ያላቸውን በጎ ስሜት ገልፀዋል። በተለይ ጋዜጠኛ ውብሸት በሙያው ተስፋ አለመቁረጡን ነው የገለፀው። “ከዚህ ማረሚያ ቤት ብወጣ ጁስ ቤት አልከፍትም፤ ተመልሼ ጋዜጠኛ ነው የምሆነው” በማለት ለሙያው ያለውን ታማኝነት ገልጿል። የመቻቻልና የእርቅ መንፈስ ለሀገር እንደሚበጅ የሚሰብከው ውብሸት፤ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም በደቡብ ሱዳን ተገኝተው ሁለቱን ወንድማማቾች ለማስታረቅ የሄዱበትን ርቀት በእኛም ሀገር ቢተገብሩት እንዴት መልካም ነበር ሲል ምኞቱን ገልጿል።
Source-http://ethioforum.org/

ቴዲ አፍሮ እና ጥሬ ጨዋዎች

ሁኔ አቢሲኒያዊ

ፒተርቦሮው ዩ.ኬ
ቴዎድሮስ ካሣሁን (ቴዲ አፍሮ) በብዙዎች ሙዚቃ አፍቃሪያን ዘንድ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው ወጣት ከያኒ ነው፤ በሙዚቃዎቹ በሚያነሳው ሀገራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊ፣ታሪካዊና ወቅታዊ ጉዳዮች የተነሳ የብዙዎችን ቀልብ ለመግዛት የቻለ ይመስለኛል፡፡ የእርሱን ታላቅነት መግለፅ የዚህ ጹሑፍ ዓላማ፣ ጥያቄም፣ የማወቅም ፍላጎት አይደለም፡፡Ethiopian Artist Teddy Afro
ይልቁንም ለዚህ አጭር መጣጥፍ መነሻ የሆነኝ ከሰሞኑ በአንዳንድ ጥቃቅን እና አነስተኛ ካድሬዎች እንዲሁም መንግስትን ለምን እንደሚቃወሙ እንኳን በማያውቁት እንደ እነ ጃዋር መሀመድ የመሳሰሉ ሰሞንኛ ትችታቸውን በመሰንዘራቸውን ምክንያት እኔም የተሰማኝን ልጨምር በሚል ነው፡፡
እንደምናውቀው ቴዎድሮስ ካሣሁን በዚህች የሙዚቃ ህይወቱ ከዛቻ እስከመታሰር ድረስ የደረሰ መሆኑ እሙን ነው ይህም የደረሰበት የተለየ ሰው ስለሆነ ነው
ቴዲ ሺህ ዘመናት ስልጣኔያችንና ታሪካችን፣ ጥበባችን በፍቅር፣ ፍቅራችን በጥበብ የተገመደበት ውሉ ከየት ተጀምሮ የት እንደተቋረጠ ታሪክን እንጠይቅ ዘንድ እንዲህ ሲል በቅኔው ተመራምሮ ያመራምረናል፡-
ብራናው ይነበብ ተዘርግቶ ባትሮኖሱ ላይ፣
የእነ ፋሲለደስ የእነ ተዋናይ፣
የት ጋር እንደሆነ ይታይ የእኛ ጥበብ መሰረቱ…፡፡
እናም እስቲ ታሪክ ይታይ፣ ይመርመር፣ ዘመናትን ያስረጁና የተሻገሩ ብራናዎቻችን ይውጡ፣የሺህ ዘመን የሃይማኖት፣ የጥበብ፣ የታሪክ፣ የሥልጣኔና የፍልስፍና ድርሳኖቻንን ይታዩይመርመሩ… በአክሱም ስልጣኔ፣ በላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ትንግርት፣ በጎንደርበእነ ፋሲለደስ የስልጣኔ አየር ዝናዋ የናኘላት፣ እነዛ ፍቅርን በጥበብ አስውበው በቅኔያቸውናበማኅሌታቸው ሰማይ ሰማያትን ሰንጥቀው በመንፈሳቸው ጸባዖት የደረሱ፣ በፍቅር ጧፍ የነደዱበማሕሌታዩ ያሬድ መንፈስ የተነሱ እንደ ተዋናይ ያሉ የቅኔ የጥበብ ጉልላቶች እንደ አጥቢያኮከብ በደመቁባት ምድር ዛሬን ፍቅር የተራብን፣ ጥበብን የተራቆትን፣ ስለ ፍቅር የደከመንምንድነው ምክንያቱ የሚል ይመስለኛል ቴዲ…፡፡
ቴዲ በሙዚቃው ለታሪክ ያለውን ስሱነትና (sensitivity) እውቀትም (Indigenous Knowledge)አሳይቶናል፡፡ ተዋናይን ስንቶቻችን እናውቀዋለን ተብለን ብንጠየቅ የሚያስተዛዝበን ሳይሆን ይቀራል፡፡ በተለይ ደግሞ ለዘመናችን ትውልድ ለአፉም ለልቡም ቅርቦቹ እነ አርሴናል፣ቼልሲ፣ ሜሲ፣ ሮናልዶ፣ እነ ፊፍቲ ሴንት እነ ቢዮንሴ፣ ወዘተ… የባሕር ማዶዎቹ ዝነኞች ናቸውእንጂ እነ ተዋናይን እነ ቅዱስ ያሬድን፣ እነ አጼ ፋሲልን ሊያስባቸው ወኔው ያለውአይመስልም፣ ኅሊናውንም ይደክመዋል እናስ እንዴት፣ ምን ሲደረግስ ሊያስባቸው ይችላል የኔትውልድ፡፡ በቅኔው የተራቀቀና በመንፈሳዊ እውቀቱ አንቱ ስለተባለው ስለ ተዋናይለመስማትም ሆነ ለማወቅ የታሪክ መዛግብትን ማገላበጥ ግድ ይላል፡፡ አሊያም ከቤተክርስቲያን ሊቃውንት አባቶች እግር ስር ቁጭ ማለት ያስፈልግ ይመስለኛል፡፡
ቴዲ በየትኛው መንገድ የሀገሩንና የቤተ ክርስቲያኑን የጥበብ እና የሥልጣኔ ከዋክብቶችን ሊያውቅ እንደቻለ ባይነገረንም የትናንትናዎቹን የሀገራችንን ባለውለታዎችና የዘመንፈርጦች ማንነት ለማወቅ እና እንዲሁም ታሪኩን ለመመርመር ግን የተጋና የሰላ አእምሮ እንደተቸረው/እንዳለው የግጥሞቹ መልእክቶች ይነግሩናል፡፡ እናም ከታሪካችንና ከስልጣኔያችን መሰረት ከአክሱም ተነስቶ በጊዜና በታሪክ ሃዲድ ላይ አሳፍሮን በትላንት ታሪካችን ውስጥ ራሳችንን እንድንመረምር፤ ራሳችንን እንድናይ ይወተውተናል፡፡ ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ ይለናል ቴዲ ስለ ፍቅር ዜማው ውብ የግጥሞቹ ስንኞች፡-
. . .የኋለው ከሌለ የለም የፊቱ፣
ሳይራመድ በታሪክ ምንጣፍ፣
ሰው አይደርስም ከዛሬ ደጃፍ፡፡
በማለት ከታሪካችን ጋር እጅ ለእጅ በምናብ ሊያጨባብጠንና ሊያስተያየን ይፈልጋል፤ እናምያለ ትላንት ዛሬ የለም፣ ያለ ዛሬ ደግሞ ነገ አይታሰብም በሚል የመጣንበትና የተጓዝንበትንአኩሪና አሳፋሪ የታሪካችንን ምእራፍ ለማገላበጥ ለደከምን ለእራሱ እና ለእኛ ትልቅ ቁም ነገርያለው ምክር ያስተላልፋል፡፡ ይህ የከያኒው የግጥም ስንኝ የሮማውን ታላቅ የሕግ ሊቅ፣ፈላስፋና አስተማሪ የሆነውን የሲስሮን አባባል አስታወሰኝ፡- ‹‹ከመወለዳችን በፊት ያለውንታሪክ ካላወቅን ዕድሜ ልካችንን ሕጻን ሆነን እንቀራለን፡፡›› ታሪካችንን ለመመርመር እናከታሪካችን ለመማር የደከምን እኛ ዛሬም እንደ አዲስ ሰናፈርስ ስንጀምር ከመጀመር ሀ ሁሳንወጣ እንደ ህጻን ባለህበት እረገጥ የሆንበትና ታሪክን እንድንደግም የተፈረደብን ምስጢሩምን ይሆን በማለት ታሪክ ጠያቂ፣ የታሪክ ወዳጅ፣ ከታሪክ የምንማር እንድንሆን ያተጋናል፡፡
ከምንኮራበት ታሪካችንና ስልጣኔያችን ባልተናነሰ አንገት የሚያስደፋ ስማችንና ማንንታችን በዓለም ፊት በቀየረብን በበርካታ የራብ፣ የእርስ በርስ ጦርነትና መበላላት ታሪክ ዘመናትን ውስጥ አልፈናል፡፡ እናም የመጣንበት መንገዱ ረጅም ዘመናቶቻችንም መከራ ሰቆቃና ዋይታ የነገሰባቸው ናቸው ሲል የትናንቱን ታሪክ ለመድገም የተፈረደብን ይመስል ታሪክ ደጋሚዎች እንድንሆን የሆንበትን እውነታ መመርመርና ማየት እንችል ዘንድ ትልቅ ጥያቄ ያጭርብናል፡፡ ዛሬም እግራችን መሄድ ተስኖት ቆመናል የእርሱ ደጋፊዎች እንዳሉ ሁሉ የእርሱ ተቃዋሚዎች መኖራቸው ተፈጥሮአዊ ነው ነገር ግን በአሉባልታ የቴዲን ስራዎች ጥላሸት ለመቀባት የሚደረግ ትግል ወይ ቅናት ነው አልያም ለተቀማጭ ሰማይ ቅርቡ ነው እንደሚባለው ይሆናል፡፡
ለእምዬ ምንሊክ ያላቸው ጥላቻ ሰሞኑን ተቀስቅሶባቸው ያዙኝ ልቀቁኝ ሲሉ ከርመዋል አስገራሚው ነገር ምንሊክን ለመሳደብ ቴዲን ሰበብ ማድረጋቸው ነው ሌላው ደግሞ መረጃውን እኔ ለቅቄዋለው ብሎ ማንም ኃለፊነቱን እሰከዚች ሰዐት ድረስ ሳይወስድ እነርሱ ቴዲን እና ምንሊክን መዝለፍ የየእለት ተግባራቸው አድርገውታል፡፡
ምንሊክን ህዝቡ እምዬ ብሎታል ቴዲን ደግሞ የዘመናችን የሙዚቃው ንጉስ ብሎ ሰይሞታል
ደበበ ሰይፉ ጥሬ ጨው በሚለው ግጥሙ እንዲህ ነበር ለነፈዞች የገጠመው
ጥሬ ጨው – ደበበ ሰይፉ
————
መስለውኝ ነበረ ፣
የበቁ የነቁ
ያወቁ የረቀቁ
የሰው ፍጡሮች ፣
ለካ እነሱ ናቸው ፣
ጥሬ ጨው..ጥሬ ጨው
ጥሬ ጨዋዎች ፣
መፈጨት-መሰለቅ-መደለዝ-መወቀጥ-
መታሸት-መቀየጥ
ገና እሚቀራቸው ፣
“እኔ የለሁበትም !”
ዘወትር ቋንቋቸው ።
ለማንኛውም እኔም እንደ ደበበ ሰይፉ ሰሞንኛ የቴዲ ተቸዎችን ጥሬ ጨው ብዬ ሰይሜያቸዋለው፡
ሁኔ አቢሲኒያዊ
ፒተርቦሮው ዩ.ኬ

ፖለቲካና ሃይማኖተኝነት የሚያቃርናቸው ነገር አለን?


(ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው)

politics and religion


ፖለቲካ የሚለው ቃል የባዕድ ቃል ነው እምነተ-አሥተዳደር ማለት ነው፡፡ ከባዕድ ከመምጣቱም ቃሉንና ተግባሩን በመልካም ጎኑ ቀምሰን ሳናጣጥመው ወዲያውኑ ምሬቱን ስላሳየን ለቃሉና ለተግባሩ መልካም ስሜት የለንም፡፡ አንድ አባባልም ፈጥረንለት ከሥነ-ቃሎቻችን ቀላቅለንለታል ‹‹ፖለቲካንና ኮረንቲን በሩቁ ነው›› የሚል፡፡ በእርግጥ ግን ፖለቲካን ርቆ መራቅ ይቻላል? ለዚህ ቃልና ለተግባሩ ባለን ጥሩ ያልሆነ አመለካከት የተነሣ ፖለቲካ ያለውን የሀገርንና የሕዝብን እጣ ፈንታ የመወሰንን ያህል ግዙፍ አቅምና ሚና ዘንግተን ፖለቲካንና ፖለቲከኛነትን ጭንቅላታችን ውስጥ የጭራቅ ምስል ሥለን በመፍራት በመጥላትና በመሸሽ በዜግነታችን ለሀገራችን ልናበረክተው የሚገባንን ተግባርና አገልግሎት እንዳናበረክትና ሀገሪቱም በፖለቲካ ምክንያት ከሚከሰቱ ትብትብ ችግሮች እንዳትወጣ አድርጓታል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ ይህ ሁኔታ ማለትም ሕዝቡ ፖለቲካን መጥላቱ ከፖለቲካ መራቁ መገለሉ ገዥዎች በመድረኩ ላይ ያለጠያቂ እንደፈለጉ እንዲፋንኑ ምቹ ሁኔታን ፈጥሮላቸዋል፡፡ ይህ ሁኔታ ሕዝቡን ለፖለቲካ በሚሰጠው የተሳሳተ ግንዛቤ ሊያስጨብጠው ከሚችሉት ልፈፋዎች (propaganda) ከሚፈጠር ፍርሐት የተነሣ በርከት ያሉ የመገለያ ሰበቦችን እንዲፈጥር አስገድዶታል፡፡
ሕዝባችን አሁን ያለበትን አስቸጋሪ ሁኔታ ማየት ለዚህ በቂ ምሥክር ነው፡፡ ሕዝቡ ሀብታም ከድሀ ሳይለይ የግፍ አገዛዙ ከልክ በላይ ያንገፈገፈው ቢሆንም ሊከፍለው የሚገባውን ዋጋ ከፍሎ የተነጠቀውን ነጻነት በእጁ ለመጨበጥ ያለው ቁርጠኝነት እጅግ ደካማ ሆኗል፡፡ ከዚያ ይልቅ በዝምታ ግፍን ተንጋሎ መጋት የመረጠ አስመስሎታል፡፡  ይህ ግምት የተጋነነ መስሎ የሚታየው ዜጋ ይኖራል ብየ አልገምትም፡፡ ነገር ግን ሁሉም ሊባል በሚችል ደረጃ ይህ ሁኔታ እንዳለ ያምንና ለድካማችን ለስንፍናችን ለፍርሐታችን ለዳተኝነታችን ምክንያት የእናታችንን ቀሚስ የምንጠቅስ ነን፡፡ ይሄንን ጉዳይ ተጨባጭነት ባለው ምሳሌ ለማስረዳት ልሞክር፡፡
እኔ ለአቅመ አዳም ከመድረሴ በፊት ጀምሮ ማለትም ገና የ2ኛ ደረጃ ተማሪ እያለሁ ጀምሮ ባቅሜ ግፍና በደልን በመቃዎም ትግል ያለፈ ነው፡፡ በዚህ ጊዜ ውስጥ ብዙ የታዘብኳቸው ነገሮች አሉ እንደኔና እኔን እንደመሰሉ ሁሉ የሚፈጸሙ ግፍና በደሎችን እነሱም ይቃወሙ ዘንድ ከምንጠይቃቸው ወገኖች ከፊሎቹ “አይ እኔ ፈሪ ነኝ፣ ራስ ወዳድ ነኝ፣ የግል ጥቅሜን አሳዳጅ ነኝ የሌላው አይገደኝም ” ላለማለት ዘወትር የሚናገሩት ነገር ነበር አለም፡፡ ‹‹አይ ይሄ ፖለቲካ ነው አያገባኝም›› የሚል በተለይ ቤተክርስቲያን አካባቢ ያሉትና ሃይማኖተኛነትን በተሳሳተ መንገድ የተረዱ ሰዎች፡፡ ይመስለኛል በሌሎች ሃይማኖቶች ተከታዮችም ዘንድ ተመሳሳይ ሁኔታ አለ፡፡
እነኝህ ሰዎች በደሉን ያደረሱት ፖለቲከኞች እንደሆኑና በደሉም የደረሰው በቤተክርስቲያን ላይ ሆኖም እንኳ እያለ ያንን በደል መቃወም እንዴት ፖለቲካ ሆኖ እንደሚታያቸው አስገራሚ ነው፡፡ እንግዲህ ይህ ችግር የሚፈጠረው አንደኛው ከላይ እንዳልኩት ራስን ከኃላፊነት ለማሸሽ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ፖለቲካ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ካላመረዳትም ነው፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ ማንኛውም ዜጋ ወዶም ይሁን ተገዶ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ፖለቲካዊ ጉዳይ ይመለከተዋል ይገደዋል፡፡ ፖለቲካ ነው አያገባኝም ብሎ ማለት በሌላ አማርኛ እኔ ዜጋ አይደለሁም ሀገርንም ሆነ ሕዝብን እራሱን ጨምሮ እንደፈለጉ እንዳሻቸው ቢያደርጉ አይመለከተኝም ማለት ነው፡፡ እንዲህ ብሎ የሚል ሰው ደግሞ በዜግነቱ ሊያገኛቸው የሚችላቸውን ወይም የሚገባውን ማለትም የመሥራት፣ የመማር፣ የመኖር ወዘተ መብቶች ለእኔ አይገቡኝም አልጠይቅም ማለቱ እንደሆነ ያለመረዳትን ያህል ድንቁርና የተጫነው አባባልና አስተሳሰብም ነው፡፡
አንድ ሃይማኖተኛ ወይም መንፈሳዊ ሰው ሃይማኖተኛ ወይም መንፈሳዊ ቢሆንም በሌላ በኩል ደግሞ ዜጋም ነው፡፡ ሃይማኖተኛነቱ ዜጋነቱን አይከለክለውም ዜጋነቱም ሃይማኖተኛነቱን አይከለክለውም፡፡ እነዚህ ጉዳዮች በተለይ በኢትዮጵያ ሲሆን ደግሞ ምክንያቱም ኢትዮጵያ በመጽሐፍ ቅዱስና በፍልስፍና መጸሐፍትም ጭምር ሀገረ እግዚአብሔርነቷ እንደመመስከሩ ተጣጥመው ያሉ እንጅ የሚቃረኑ አይደሉም፡፡ እንግዲህ ይህ ሰው ሊወጣቸው የሚገባቸው ሁለት የማንነት መገለጫዎች አሉት ማለት ነው፡፡ የሃይማኖት ሰው ቢሆንም እንደዜጋነቱ ደግሞ ሀገሪቱ እንዲያደርግላትና እንዲወጣላት ከሱ የምትጠብቀው ብዙ ግዴታዎች ደግሞ አሉ፡፡ ይሄም ስለገባቸው ነው አባቶቻችን ለሀገራቸው ታቦት ተሸክመው ጦርነት ይወጡ ይዋደቁ ይሞቱላትም የነበሩትና የሀገራችንን ነጻነት ሉዓላዊነትና ክብር አስጠብቀው ሊቆዩ የቻሉት፡፡
ከሁለት ሦስት ዓመታት በፊት ጀምሮ ስደተኛውን ሲኖዶስ ለመመለስ ወይም ሀገር ቤት ካሉ አባቶች ጋር ለማስታረቅ ሰፊ እንቅስቃሴ እየተደረገ በነበረበት ጊዜ በመሀሉ አባ ጳውሎስ ዐረፉ፡፡ አይ አግዚአብሔር ባወቀ ነገሩን አስተካከለው ተብሎ ሲታሰብ የሀገር ቤቶቹ አጋጣሚው የፈጠረው ነገር አልተመቻቸው ሆኖ የእርቅ ድርድሩን ለማሰናከል አንድ ሰበብ ፈጠሩ በመግለጫም ስደተኞቹን አባቶች ከቤተክርስቲያን ጋር ግንኙነት የሌለውን ፖለቲካዊ ጉዳይ ያነሣሉ ስለሆነም የእርቅ ድርድሩ መሰናክል ገጥሞታል ወይም ወደፊት ማስቀጠል አልቻልንም አሉ ፡፡
በወቅቱ ይህ መግለጫ እጅግ ካስቆጣቸውና ካሳዘናቸው ወገኖች አንዱ ነበርኩና ወዲያውኑ በመጽሔት፣ በመካነ ድሮች ይሄንን የተሳሳተና ሸፍጥ ያዘለ ፍረጃ የሀገር ቤቶቹ አባቶች የዘነጉትን የታሪክ እማኝነት በማንሣት እርቃኑን ያስቀረ ጽሑፍ ለንባብ አበቃሁ፡፡ ለራሳቸው ለስደተኛው ሲኖዶስም በመካነ ድራቸው በኩል እንዲደርሳቸው በማድረግ እነዚህ የዛሬዎቹ ‹‹አባቶች›› ፖለቲካ ብለው ያሉት ነገር የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ባለባት ታሪካዊ ኃላፊነት ወይም ባለ አደራነት ከኦሪት ጀምራ ከዚያም በፊት ከሕገ ልቡና ጀምራ ስትወጣው ስትከውነው የኖረችው የተቀደሰ ተግባር መሆኑን፣ ነገሥታትን በዕውቀትና በጥበብ በሥነ-ምግባር አሳድጋ ቀብታ ስታነግሥ የኖረች መሆኗን ወደ ኋላ ደግሞ ማለትም በ13ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ሲሦ መንግሥት ተሰጥቷት እስከ ቅርብ ጊዜ 20ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ቆይቶ ለየት ባለ መልኩ ሀገሪቷ በፈተናዎች የተዋጠች ብትሆንም፤ ከሀገሪቱ ነጻነት እስከ ሥልጣኔዋ የማይተካ ቁልፍ ሚና የተጫወተች ኃላፊነቷን በሚገባ የተወጣች መሆኗን፤ አሁን በስደት ላይ ያሉ አባቶችን የሀገር ጉዳይ በማንሣታቸው ፖለቲከኞች ብለው የሚነቅፏቸው የሚኮንኗቸው ከሆነ እየነቀፉ ያሉት እነሱን ብቻ ሳይሆን በስንክሳሩ የሚዘከሩ ቅዱሳን አባቶቻችንን፣ የቤተክርስቲያኗን ተጋድሎ እና ታሪክ መሆኑን “ድሀ ተበደለ ፍርድ ተጓደለ” ብሎ ስለ ተበደሉ ፍትሕ ስለተነፈጉ ወገኖች መጮህ መሟገት አምላካዊ ኃላፊነትን መወጣትና ሐዋርያዊ ግዴታ መሆኑን፣ ከሐዋርያት ሕይዎትና ከክርስቶስ ቃል ጋር በማመሳከር ለዚያ የደነቆረ ፍረጃና ነቀፋ አጥጋቢ ምላሽ እንደሰጠሁ ብዙ ሳይቆዩ ማለትም ከሁለት ሳምንታት በኋላ እስከዚያ ጊዜ ድረስ ፖለቲከኛ ሲሏቸው ይሸማቀቁና በዜግነታቸው የሚሰማቸውን ሁሉ አፋቸውን ሞልተው በሀገራዊ ጉዳይ ላይ ለመናገር ይሳቀቁ የነበሩ ስደተኞቹ አባቶች የጽሑፌን ሐሳብ ሙሉ ለሙሉ በማካተት እንዲህ እንዲህ በማለታችን ፖለቲከኞች ተባልን፤ እንዲህ እንዲህ ማለት ፖለቲከኛነት ሳይሆን ሐዋርያነት ነው የሚል መግለጫ አወጡና ለብዙኃን መገናኛዎች ለቀቁ፡፡ እኔም በእውነት እንዲያ ብዙ ስደክምለት የኖርኩትን አስተሳሰብ ያውም በሲኖዶስ ደረጃ ሲንጸባረቅ የተሰማኝ ደስታ የላቀ ነበር፡፡ ከዚያ በኋላማ እንዲያውም በተለይ ከሀገር ውጭ ያሉ ሰባክያን ይሄንን አስተሳሰብ በደንብ እያንጸባረቁት እንደሆነ በመገናኛ ብዙኃን ሳይቀር እየሰማናቸው ነው፡፡ ጎሽ እንዲያ ነው ከዚህ በኋላ ፈሪውና ራስ ወዳዱ ለዳተኝነቱ የዜግነት ኃላፊነቱን ላለመወጣቱ የሚጠቅሰው ሌላ ምክንያት ምን እንደሆነ እንግዲህ ደሞ እንሰማለን፡፡
በእርግጥ እነኝህ አባቶች ይሄንን እውነታ አተውት ወይም ሳያውቁት ቀርተው ነው ማለቴ አይደለም፡፡ ልቦናቸው ይሄንን ሀቅ ስለሚያውቅማ ነው በቂም ባይሆን አምነውበት ለመተግበር ሲሞክሩ የቆዩት፡፡ ነገር ግን በሀገራችን ፖለቲካን ወይም ሀገራዊ ጉዳይን ከዜግነት ግዴታና ከቤተክርስቲያን ለመነጠል ከፋሽስት ጣሊያን ጀምሮ በደርግ በተለይም ደግሞ በወያኔ የተሰበከው ማወናበጃና ማምታቻ በሁሉም ኢትዮጵያዊያን አስተሳሰብ ላይ እንዳጠላ ሁሉ ይህ ሁኔታ ከባድ ጫና ፈጥሮባቸው በዜግነታቸው ለሀገራችን ልናበረክት ይገባል ብለው የያዙትን ቀናና ትክክለኛ አስተሳሰባቸው ከልብ ወጥቶ ወደ አንደበት ስላልደረሰ ነበር በሀገራዊ ወይም በፖለቲካዊ ጉዳይ ላይ በሚጠሩና በሚከወኑ መድረኮች ተገኝተው ያለ ሀፍረትና መሸማቀቅ እንደ ቀድሞዎቹ ሁሉ የቅርብ የሆኑትንም ማንሣት እንችላለን እንደ አርበኛው አቡነ ጴጥሮስ ሁሉ በግንባር ቀደምትነት በወኔና በስሜት ምላት መናገር ያለባቸውን ለመናገር ተሳትፏቸውንም ለማበርከት ይቸገሩ የነበሩት፡፡ አሁንም ቢሆን ገና ይቀራል ይቀራል፡፡ እንደ ሐዋርያትና ሠማዕታት ሁሉ ባለ 30,60,100 ፍሬ ባለ አዝመራ መሆን የፈለገ አባት ወይም የሃይማኖት ሰው ቢኖር መንገዱ ይሄው ነው ሌላ የለምና ያለ ማመንታት በልበ ሙሉነትና በወኔ ውጡ ተሳተፉ ተጋደሉ፡፡
ከዚሁ አካባቢ ካሉ ሰዎች ከሕዝቡም ቢሆን የሚነሣው ሌላኛው ሰበብ ደግሞ ‹‹እግዚአብሔር ያመጣውን ምን ማድረግ ይቻላል እሱ ያመጣውን እሱ እስኪመልሰው ዝም ብለን መቀበል ነው እንጅ›› የሚል ነው፡፡ ለአሁኑ ባጭሩ ለመመለስ አንደኛ ነገር ‹‹ማንም ሲፈተን  በእግዚአብሔር እፈተናለሁ አይበል እግዚአብሔር በክፉ አይፈትንምና፤ እርሱ ራሱስ ማንንም አይፈትንም፡፡ ነገር ግን እያንዳንዱ በራሱ ምኞት ሲሳብና ሲታለል ይፈተናል፡፡ ከዚህ በኋላ ምኞት ፀንሳ ኃጢአትን ትወልዳለች ኃጢአትም ካደገች በኋላ ሞትን ትወልዳለች፡፡ ያዕ. 1÷13-15 ተብሎ መጻፉን ልብ ይሏል፡፡ ሁለተኛ ስኬት የሚገኘው ከጥረት ከግረት ከልፋት መሆኑን አዳምን ጥረህ ግረህ በግንባርህ ወዝ ብላ እደር ዘፍ. 3÷19 ባለውና ሊሠራ የማይወድ አይብላ  2ኛተሰ. 3÷8-13 ባለው ቃል እጅና እግርን አጣምሮ ቁጭ ብሎ በማየት የሚገኝ ነገር እንደሌለ እንቅጩን ተናግሯል፡፡ በዚህም ላይ የሚሠሩ እጆችና እግሮች የሚያስብ ጭንቅላት የሰጠን የሚበጀንን ነገር እንደወደድን እንድናደርግበት መሆኑ ይታወቃል፡፡
እስከዛሬም ድረስ በዓለም ታሪክ ያለውን ብንመለከት ሰዎች በጥረታቸው አንዱ አንዱን ይጥላል አንዱ አንዱን ያነሣል እንጅ እግዚአብሔር እራሱ ወርዶ እናንተ ይበቃቹሀል ወግዱ እናንተ ተቀመጡ ብሎ አያውቅም፡፡ ነገር ግን በእያንዳንዱ ነገር ላይ የእርሱ ፈቃድ እንዳለበትና አድራጊውም ሥራውን በርትቶ እየሠራ በሚሠራው ነገር ሁሉ የእሱ ፈቃድና እረድኤት እንዲኖርበት መለመን መጠየቅ ማሳሰብ እንዳለበት እሙን ነው፡፡
የሀገራችንንም የቅርብ ጊዜ ታሪክ ብናይ ያለው እውነታ ይሄው ነው፡፡ ደርግን የሸኘው እግዚአብሔር መሆኑ ግልጽ ነው ፡፡ ይሁን እንጅ እግዚአብሔር እራሱ ወርዶ ደርግን ከመንበሩ አውርዶ ወያኔን ደግሞ ና ተቀመጥ ብሎ አስቀምጦ አይደለም፡፡ ወያኔን ምክንያት አድርጎ ደርግን ሸኘው እንጅ፡፡
በደርግ የተማረሩ ወያኔዎች ወተው ባይታገሉ ኖሮ ለነገሩ ወያኔ ብቻም አልነበረም ምርኩዙ መጠቀሚያው የሆኑ ሌሎችም ነበሩ አሉም፡፡ ለማንኛውም እነሱ ‹‹አይ እግዚአብሔር ያመጣውን እኛ ምን ማድረግ እንችላለን? ›› ብለው እጅ እግራቸውን አጣምረው ቁጭ ቢሉ ኖሮ ደርግን ታግለው ለመጣልና ሥልጣን ለመጨበጥ ለመቆናጠጥ መቻላቸው የማይታሰብ በሆነ ነበር፡፡ በይነ ሕዝባዊ (ዲሞክራሲያዊ) ሥርዓት ኖሮ ተመርጠው ለሥልጣን ካልበቁ በስተቀር፡፡ በመሆኑም ቁጭ ብሎ ዓይንን በማቁለጭለጭ የሚገኝ ምንም ነገር የለም፡፡ ሰው ማግኘት የፈለገውን ነገር የእግዚአብሔር ፍቃድ ታክሎበት በልፋት በጥረት ይገኛል እንጅ እጅና እግርን አጣምሮ ቁጭ ካሉበት ከሰማይ ዱብ የሚል ነገር ጨርሶ የለም፡፡ ስትቃዥ ኖረህ እንደቃዥህ አፈር ትገባታለህ እንጅ፡፡
ይህ ዑደት እስካሁን እንደነበረ ሁሉ ወደፊትም ይቀጥላል በወያኔ የተማረረ ሕዝብ ወያኔ እንዲወገድና ነጻነቱን በእጅ መጨበጥ ማስገባት ከፈለገ ከላይ እንደገለጽኩት ሁሉ ያለው አማራጭ አንድና አንድ ብቻ ነው ተራ ሰበብና ምክንያትን ነቅሎ ጥሎ፣ የፍርሐትንና የራስ ወዳድነትን ማቅ አውልቆ ጥሎ፣ ዋጋ ለመክፈል ተዘጋጅቶ፣ ቆረጥ ቆፍጠን ጨከን ብለህ እከሌስ ለምን? እከሌ… ሳትልና ሳትተያይ በዜግነትህ ማድረግ ስላለብህ እንደምታደርገው ብቻ አምነህና ዐውቀህ መታገል ብቻ፡፡
ሦስተኛው የሰበበኞች ሰበብ ደግሞ በመሠረተ ሐሳብ ደረጃ ከሁለተኛው ጋራ ተመሳሳይ ሆኖ ነገር ግን ብልጠት አይሉት ድንቁርና የተሞላበት አስገራሚ ሰበብ ነው፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ በሮሜ መልእክቱ 13÷1-7 ያለውን ይጠቅሱና ሰጥ ለበጥ ብለን የመገዛት አምላካዊ ግዴታ አለብን ይላሉ፡፡ እጅግ አሳፋሪና ነውረኛነትም ነው፡፡ ቃሉን እንይ “ ነፍስ ሁሉ በበላይ ላሉ ባለ ሥልጣኖች ይገዛ ፡፡ ከእግዚአብሔር ካልተገኘ በቀር ሥልጣን የለምና፤ ያሉትም ባለሥልጣኖች በእግዚአብሔር የተሾሙ ናቸው፡፡ ስለዚህ ባለ ሥልጣንን  የሚቃወም የእግዚአብሔርን ሥርዓት ይቃወማል የሚቃወሙትንም በራሳቸው ላይ ፍርድን ይቀበላሉ፡፡ ገዥዎች ለክፉ አድራጊዎች እንጅ መልካም ለሚደርጉት የሚያስፈሩ አይደሉምና ፡፡ ባለ ሥልጣንን እንዳትፈራ ትወዳለህን? መልካሙን አድርግ ከእርሱም ምስጋና ይሆንልሀል፡፡ ለመልካም ነገር ለአንተ የእግዚአብሔር አገልጋይ ነውና፡፡ በከንቱ ግን ሰይፍ አይታጠቅምና ክፉ ብታደርግ ፍራ ቁጣውን ለማሳየት ክፉ አድራጊውን የሚበቀል የእግዚአብሔር አገልጋይ ነውና፡፡
ለሁሉም የሚገባውን አስረክቡ ግብር ለሚገባው ግብርን፣ቀረጥ ለሚገባው ቀረጥን፣ መፈራት ለሚገባው መፈራትን፣ ክብር ለሚገባው ክብርን ስጡ ” ይላል ቃሉ እንግዲህ ይሄንን ቅዱስ ቃል እንዴት ለፍላጎታቸው አጣመው እንደተጠቀሙበት አያቹህ? ቃሉ ምንም በማያሻማና ጥርት ባለ መልኩ ነው የቀረበው፡፡ ቁጥር 3-4 ያለውን ቃል ልብ ብለው ቢመለከቱት ቅዱስ ጳውሎስ ስለ የትኞቹ ባለ ሥልጣኖች እየተናገረ እንደሆነ በተረዱ ነበር፡፡ “ገዥዎች ለክፉ አድራጊዎች እንጅ መልካም ለሚያደርጉ የሚያስፈሩ አይደሉምና፡፡ ባለ ሥልጣንን እንዳትፈራ ትወዳለህን? መልካሙን አድርግ ከእርሱም ምስጋና ይሆንልሀል” ይሄንን ቃል በሚገባ መረዳት እንድንችል አሁን ካለንበት ሥርዓት ሥራ ጋር እንይ ፡፡ ቃሉ እንዳለው ‹‹ገዥዎች ለክፉ አድራጊዎች እንጅ መልካም ለሚያደርጉ የሚያስፈሩ አይደሉምና›› በሚለው ቃል ግልጽ ባለ መልኩ ስለ የትኞቹ ገዥዎች እንደተናገረ አሳይቷል፡፡
በዘመንኛ አገላለጽ ለፍትሕ ለቆሙ ወይም ዲሞክራት ለሆኑ ማለቱ እንጅ እጃቸውን በንጹሐን ደም ለሚያጥቡ ግፈኞች ማለቱ እንዳልሆነ ግልጽ ነው ምክንያቱም ‹‹መልካም ለሚያደርጉ የሚያስፈሩ አይደሉምና›› ብሏልና ለፍትሕ የቆሙ ወይም ዲሞክራት መሪዎች መልካም ለሚያደርጉት ማለትም ለሕግ የበላይነት ለሚታገሉት፣ ለሰብአዊ መብቶች ለሚጮሁት፣ ፍርድ ተጓደለ ደሀ ተበደለ እያሉ ስለተበደሉትና መብታቸውን ስለተነፈጉት ለሚጮሁት፣ ግፉና ጭቆናን ለሚቃወሙት ለሚሟገቱት የሚያስፈሩ አይደሉምና ብሏልና፡፡ እንኳን ሊያስፈሩ ይሄንን በማድረጋቸው ማለትም መልካም ሥራ በመሥራታቸው ፍትሕ እንዲሰፍን በመታገላቸው እንዲያውም ከእነሱም ምስጋና ይሆንልሀል፡፡ በማለት እያወራላቸው ያላቸው ባልሥልጣናት ስለ የትኞቹ ዓይነቶች እንደሆነ ግልጽ አድርጓል፡፡
ይሄንን ጉዳይ በሀገራችን ላይ ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ብናየው ነገሩ የተገላቢጦሽ ሆኖ እናገኘዋለን ምክንያቱም የኛ ባለሥልጣናት የሚያስፈሩት ክፉ ለሚያደርጉት ማለትም ሰብአዊ መብትን ለሚረግጡት ፍርድ ለሚያጓድሉት፣ ለሚጨቁኑት፣ ግፍ ለሚያበዙት፣ ለሚመዘብሩት፣ በደል ለሚያደርሱት፣ ፍትሕ ለሚነፍጉት፣ ለሚያንገላቱት ሳይሆን ለሕግ የበላይነት ለሚታገሉት፣ የፍትሕ ያለሕ፣ የመንግሥት ያለህ፣ የዳኛ ያለህ፣ የሕግ ያለህ ለሚሉት ለተጨቆኑት የሰብአዊ መብት እረገጣ ለደረሰባቸው ወገኖች ለሚጮሁት፣ ፍርድ ተጓደለ ድሀ ተበደለ ለሚሉት፣ ግፉና በደል ስለ ደረሰባቸው ምስኪኖች ለሚጮሁት፣ ለሕዝብ ሁለንተናዊ ነጻነት ለሚታገሉት፣ እውነት ለሚናገሩት እንደሆነ አእምሮ ላለው ሁሉ ግልጽ ነው፡፡
በመሆኑም እራሳቸው ክፉ አድራጊዎችና መልካም የሚያደርጉትንም የሚያመሰግኑ ሳይሆኑ የሚሳድዱ የገቡበትም ገብተው ድራሻቸውን የሚያጠፉ መሆናቸው ግልጽ ነው በመሆኑም ይህ የአገዛዝ ሥርዓት ቃሉ ከሚልላቸው ባለሥልጣናት ዓይነቶቹ በተቃራኒ ያለ መሆኑ ግልጽ ነውና ይሄንን ቃል ለሚጠቅሱ አባዮችና እራሳቸውን ለሚያታልሉ የዋሀን በቃሉ የሚያምኑ ከሆነ ጥቅሱ ላይ በቁትር 4 ላይ ያለውን ማለትም ‹‹ቁጣውን ለማሳየት ክፉ አድራጊውን የሚበቀል የእግዚአብሔር አገልጋይ ነውና›› እንዳለ ሁሉ በሀገርና በሕዝብ በቤተክርስቲያንም ላይ ክፉ የሚያደርገውን በመበቀል የእግዚአብሔር አገልጋይ ለመባል እንዲተጉ ማሳሰብ እወዳለሁ፡፡
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
እናም ቃሉ ምንም የሚያምታታ ነገር የሌለበት ጥርት ባለ መልኩ እንዳስቀመጠው ቅን ፈራጅ ለሆኑት ለሕዝብ ልብ በሉ “ለሕዝብ” ሁለንተናዊ ደኅንነት ሰላምና ጤና ለቆሙት ባለሥልጣናት ማለቱ እንጅ እንደነ ዲዮቅልጥያኖስ ፣ መክስምያኖስ በሀገራችን ደግሞ ዮዲት ጉዲት፣ ግራኝ መሐመድ፣ በወረራ መጥቶ ለነበረው ለፋሺስት ጣሊያን ዓይነቶች ሁሉ ተገዙ ማለቱ አይደለም፡፡ ለእንደነዚህ ዓይነቶቹ እንኳን ልንገዛላቸውና ክብር ልንሰጣቸው የእግዚአብሔር ሰላምታ እንኳን እንዳንሰጣቸው ሐዋርት በበርካታ ቦታዎች ላይ እያለቀሱም ጭምር አበክረው አስጠንቅቀዋል፡፡ ተስፋ አደርጋለሁ ነገሩን ግልጽ እንዳደረኩት ቸር ይግጠመን፡፡
amsalugkidan@gmail.com

ኢኮኖሚያችን ሲያድግ የህዝቡ ኑሮ ለምን አሽቆለቆለ?


ማስተዋል ደሳለው

ላለፉት 8 እና ዘጠኝ ዓመታት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በሁለት አሃዝ አያደገ ነው ሲባል እንሰማለን፤  የእድገት ፍጥነቱ  ላይ የሚነሱ በርካታ ጥያቄውች  ቢኖሩም መንግስት  የመንገድ ግንባታ ፣ የኃይል ማመንጫ ግንባታወችን እና መሰል ነገሮችን  በመጥቀስ እድገት እንዳለ አስረግጦ ይከራከራል::  በሌላ በኩል የኢኮኖሚ እድገቱ ተመዘገበ በሚባልባቸው ዓመታት በዋጋ ንረት የህዝቡ ኑሮ ከጊዜ ወደጊዜ እያሽቆለቆለ  እንደሆነ በግልፅ የሚታይ ነገር ነው:: ታዲያ  የኢኮኖሚ እድገት አለ በተባለባቸው ዓመታት የህዝቡ ኑሮ ለምን አሽቆለቆለ? ይህን ጥያቄ ከ 7 ዓመት በፊት ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ  ተጠይቀው የሰጡት መልስ የዋጋ ንረቱን የኢኮኖሚ እድገቱ እራሱ የፈጠረው ጉዳይ ነው ነገር ግን ቀስ በቀስ እድገቱ ሲቀጥል ራሱ እድገቱ ችግሩን ይፈታዋል ብለው ነበር፤ ነገር ግን ከሰባት ዓመት በዃላም እንኩአን ሊሻሻል  የህዝቡ የኑሮ ሁኔታ ከቀን ወደቀን እየባሰበት ሂዷል::  ችግሩ የተለያዩ  ምንጮች ቢኖሩትም በዋናነት በ 2 ከፍሎ ማየት ይቻላል::
፩. የኢኮኖሚ እድገቱ ምንጭ
፪. የሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ መዋቅር
የኢኮኖሚ እድገት ማለት በአጭሩ ኢኮኖሚዉ ዉስጥ ተጨማሪ ሀብት መፍጠር ማለት ነው::  በመጀምሪያ ላለፉት 8  እና ዘጠኝ ዓመታት ኢትዮጵያ ዉስጥ  የተፈጠሩት ተጨማሪ ሀብቶች ምንድን ናቸው ብሎ መጠየቅ ያስፈልጋል ፤  በአብዛኛዉ ሀገሪቱ ዉስጥ የተፈጠሩት ሀብቶች ከመንገድ ፣ ከሕንፃ እና ከ ከኃይል ማመንጫ ከግንባታ ጋር የተያያዙ ናቸው:: በመቀጠልም የዚህ ሀብት የገንዝብ ምንጭ ምንድን ነው ብሎ ማየት ያስፈልጋል፤ የገንዘቡ ምንጭ በዋናነት ከብድር እና እርዳታ የተገኘ ሀብት ነው ፣ በተለይም በኢትዮጵያ አቆጣጠር ከ 1998 ዓም ጀምሮ በሶማሊያ በመጀመሪያ የእስላማዊ ፍርድ ቤቶች ህብረት በመቀጠልም የአልሻባብ እንቅስቃሴ መጠናከር ለኢትዮጵያ ትልቅ ሲሳይ ይዞ ነው የመጣው:: በሶማሊያ ያለዉን ሁኔታ  ለመቆጣጠር ምዕራባዉያኑ የሚያደርጉትን ጥረት በመደገፍ  በዋና አጋርነት የተሰለፈችዉ ኢትዮጵያ ላለፉት ስምንት ዓመታት በየዓመቱ በቢልየን ዶላር የሚቆጠር ገንዘብ በእርዳታ መልክ ከምዕራብ ሃገራት እንድታገኝ አድርጓታል:: ይህም ማለት ሀገሪቱ ዉስጥ የጎላ  የኢኮኖሚያዊ መዋቅር ፣ የአሰራር ስርዓት  እና የቴክኖሎጅ ለውጥ ሳይኖር ከፍተኛ ገንዘብ ወደኢኮኖሚው ፈሰስ እንዲሆን አድርጓል:: በሌላ አገላለፅ  የቆየው የሀገሪቱ  ኢኮኖሚ የጎላ የምርት ጭማሪ ሳይኖረው ከዉጭ የተገኘ ብድር እና እርዳታ ኢኮኖሚዉ ዉስጥ ተጨመረ እና የኢኮኖሚዉ መጠን አደገ ማለት ነው::  ስለዚህ የህዝቡን የኑሮ ሁኔታ እና የሀገሪቱን ተወዳዳሪነት ሊያሻሽል የሚችል የግብርና እና የኢንዱስትሪ ዘርፎች ላይ የጎላ  ለዉጥ ሳይታይ ለመሠረት ልማት ኢኮኖሚዉ ዉስጥ ፈሰስ የተደረገው ገንዝብ የገንዘብ አቅርቦትን (Money Supply) በመጨመር እና  የአገልግሎት ዘርፉ ( Service sector) ከሌሎቹ የኢኮኖሚ ዘርፎች ተነጥሎ እንዲለጠጥ እንዲሁም ዋጋ እንዲንር በማድረግ አብዛኛዉን ሕዝብ ለችግር አጋለጠ ::
ከብድር እና እርዳታ የተገኘው ገንዘብ መሰረተ ልማት ላይ ሲዉል ከላይ የተገለፀው ችግር ቢኖርበትም በአንፃሩ የመሰረተ ልማት መስፋፋት የማምረቻ ወጭ ( cost of production) እንዲቀንስ በማድረግ የሚያስገኘው ጥቅም አለ ፤ በተጨማሪም ገንዘብ ገንዘብን ይፈጥራል “ money creats money” በሚለው የኢኮኖምክስ  መርህ መሰረት ኢኮኖሚዉ ዉስጥ የተረጨው ገንዘብ በአብዛኛዉ አገልግሎት ዘርፉ ላይ የፈጠረው ተጨማሪ ሀብት አለ:: ነገር ግን ይህ የተፈጠረ ተጨማሪ ሀብት በጠንካራ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ መዋቅር ስላልተመራ ወደጥቂት ሰወች እጅ እንዲገባ ሁኗል::  ሃብቱ እጃቸው የገባ ሰወችም የኢኮኖሚዉን መዋቅር ሊለዉጡ የሚችሉ እንደኢንዱስትሪ አይነት ዘርፎች ላይ ከመሰማራት ይልቅ ከሙሰኛ ባለስልጣናት ጋር በመመሳጠር ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያለዉን የከተማ ቦታ በኢንቨስትመንት እና በሊዝ ስም በመዉሰድ ህንፃ በመገንባት እየተለጠጠ ላለው የአገልግሎት ዘርፍ በማከራየት በአቁአራጭ ከፍተኛ ገቢ ለመሰብሰብ ተጠቀሙበት::
በሌላ በኩል የሀገሪቱ የመሬት አስተዳደር ስርዓት በሙስና የተጨማለቀ እና ወጥ ስላሆነና አዳዲስ ብቅ ለሚሉ ባለሀብቶች መሬት ማግኘት ከባድ ስለሆነ ሀገሪቱ አሁን ባለችበት ተጨባጭ ሁኔታ ወሳኝ ሀብት (strategic resource) የሆነዉን የከተማ ቦታ ቀድመው የያዙ ባለሀብቶች የገቢያ ዉድድሩን ሚዛናዊ እንዳይሆን በማድረግ አዲስ የሚፈጠሩ ተወዳዳሪያቸውን በቀላሉ ከገቢያ ያስወጣሉ:: በተጨማሪም እንደነዚህ አይነቶቹ  ባለሀብቶች በአብዛኛው የፖለቲካዉ እና የግዥዉ ፓርቲ ጥገኛ ስለሆኑ የሚጠበቅባቸዉን ያክል  ግብር እና ታክስ አይከፍሉም:: ሥራቸዉን ስለሚያውቁም በሀገሪቱ በረጅም ጊዜ ሊከሰት ይችላል ብለው የሚፈሩትን ፖለቲካዊ አለመረጋጋት ስለሚሰጉ የሚያገኙትን ትርፍ ወደዉጭ ያሽሻሉ ፤ በጎን ሙሰኛ ባለስልጣናትም የሚዘርፉትን ገንዘብ ከሀገር ያሸሻሉ:: ከዚህ ላይ ፋይናንሽያል ትራንስፓረንሲ ኳሊሽን  ያወጣዉንና ኢትዮጵያ በህገወጥ የገንዘብ ፍሰት (illicit financial flow) በፈረንጆቹ ከ 2000 እስከ 2009 ያጣችዉን 11. 7 ቢልየን ዶላር ልብ ይሏል::
ለማጠቃለል የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ጤናማ ሁኖ እንዲያድግ ከተፈለገ ከላይ የተጠቀሱት  የሀገሪቱ የኢኮኖሚ እና የፖለቲካ መዋቅር ድክመቶች መስተካከል የሚገባቸዉ ሲሆን ፤ በዉጭ ብድር እና እርዳታ ላይ መንጠልጠሉን ቀንሶ ከሀገር ቤት በፍትሃዊነት ከሚሰበሰብ ግብር ሊሆን ይገባል:: ከዉጭ የሚገኘዉን ሀብትም  በብዛት መሰረተ ልማት ላይ ብቻ ማዋሉ የሚያስከትለዉን ችግር ጥልቅ ጥናት በማካሄድ  መመርመር እና  ገንዘቡ ከመሰረተ ልማቱ ጎን ለጎን የኢንዱስትሪው እና የእርሻዉን ዘርፍ መዋቅር ወደተሻለ ደረጃ እንዲደርስ ለማስቻልም መሰራት አለበት:: ከሁሉም በላይ ግን የኢኮኖሚ ነቀርሳ የሆነዉን ሙስና ለማስወገድ ከአንድ ፓርቲ የበላይነት ወደ መድብለ ፓርቲ ስርዓት መሸጋገር እንዲሁም ተጠያቂነትን ሊያጠናክሩ የሚችሉ እንደገለልተኛ ፍርድ ቤቶች ፣ የግል መገናኛ ብዙሃን  የመሳሰሉትን ተቋማት መፍጠር ያስፈልጋል:: ይህ ካልሆነ ግን ሀገሪቱ ሽህ ጊዜ ብታድግ የኢኮኖሚውን ፍሬ ጥቂቶች እየበሉ የአብዛኛዉ ሕዝብ  ኑሮ ማሽቆልቆሉ ይቀጥላል::

Monday, December 23, 2013

ከአቶ አያሌው መነሳት ጀርባ የአቶ ደመቀ ሚና


"የቆየ ቁጭትና ቁርሾ ነው"

ayalew n demeke


በአማራ ክልል የተካሄደውን ሹም ሽር ተከትሎ የተሰጠው ሹመትና የሹም ሽሩ አካሄድ መነጋጋሪያ ሆነ። “በቃኝ አሉ የተባሉትን ባለስልጣን አውርዶ እንደገና መሾም የተነቃበት የህወሃት የማረጋጊያ ጨዋታ ነች” ሲሉ ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ተናገሩ። በሹም ሽሩ የአቶ ደመቀ መኮንን እጅ እንዳለበትና መንስዔውም “የቆየ ቁጭትና ቁርሾ” እንደሆነ ተጠቆመ።
የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አያሌው ጎበዜ ከመንበራቸው እንዲነሱ ተደርጓል። የመንግስት ልሳን መገናኛዎች እንዳመለከቱት አቶ አያሌው ከሃላፊነታቸው የተነሱት ታህሳስ 9/2006 በተጠራ አስቸኳይ የክልሉ ጉባኤ ነው። አዲስ ሹመት ያስፈለገው አቶ አያሌው ባቀረቡት “የመተካካት” ጥያቄ እንደሆነም ተመልክቷል። ምትካቸው የነበሩት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የክልሉ ፕሬዚዳንት ሆነዋል።
አቶ ገዱ ፕሬዚዳንትነታቸው በጉባኤ ተወስኖ ይፋ ከመደረጉ ጎን ለጎን ዜና የሆነው የሳቸው ሹመት ሳይሆን የአቶ አያሌው ስልጣናቸውን በፍላጎታቸው መልቀቃቸው ነው። አቶ አያሌው የ”በቃኝ” ጥያቄ ማቅረባቸው ከተሰማ ብዙ የቆየ ቢሆንም አሁን አስቸኳይ ጉባኤ ተጠርቶ የተወሰነበት ምክንያት ዜናውን አነጋጋሪ ያደረገው ጉዳይ ነው።
የአቶ አያሌው ከሃላፊነታቸው መነሳት ከግራና ቀኝ መነጋገሪያ በሆነ ማግስት ኢህአዴግ የሙሉ አምባሳደርነት ሹመት እንደሰጣቸው ይፋ መደረጉም ሌላ ግርምት ፈጥሯል። በ”መተካካት” ሰበብ ከስልጣን ተነሱ የተባሉት አቶ አያሌው “ባለሙሉ ስልጣን” አምባሳደር ሆነው መሾማቸው ደግሞ የሹም ሽር ተውኔቱን “ኮሜዲ” አሰኝቶታል ያሉና በማህበራዊ ድረገጾች መዝናኛ ያደረጉት ጥቂት አይደሉም።
ምክትላቸው የነበሩትና አሁን ዋናውን መንበር የጠቀለሉት አቶ ገዱ “ብዙ ጉድ አለባቸው” የሚሉ ወገኖች ወቀሳ መሰንዘርና መጠየቅ አለባቸው በማለት መከራከር ከጀመሩ ቆይተዋል። የአማራ ክልልን እንዳሻቸው ይጋልቡታል ከሚባሉት አቶ በረከት ስምዖን ጋር የጠነከረ ወዳጅነት እንዳላቸውና ከህወሃት የደህንነት ቁንጮ መዋቅር ጋር በቅርበት እንደሚሰሩ የሚታሙት አቶ ገዱ “ጉዳቸው የተሸፈነው ባላቸው የታማኝነት መረብ (ኔትወርክ) ነው” በማለት የቅርብ ሰዎቻቸው ይከሷቸዋል።
gedu
ገዱ አንዳርጋቸው
በድርጅት በተወሰነ ውሳኔ አቶ አያሌው እንዲለቁ የተደረገውን ወንበር የተረከቡት አቶ ገዱ “ህወሃት ለሚያወርደው ማናቸውም መመሪያ ለመተግበር የፈጠኑና የታመኑ ከመሆናቸው በዘለለ ክልሉን የመምራት ብቃት እንደሌላቸው እናውቃለን” በማለት አስተያየት የሰጡ፤ የአቶ አያሌው ወንበር ለመነጠቁ ደረጃቸው በውል የማይታወቀውን ምክትል ጠ/ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን እንደ ምክንያት ያነሳሉ።
አቶ ደመቀ በክልሉ በግልጽ በሚታወቅ ስልጣን የአቶ አያሌው የበታች ሆነው የሚሰሩ ቢሆንም፣ የክልሉን የጸጥታና የደህንነት ጉዳይ ከህወሃት ሰዎች ጋር በመሆን ይሰሩ ስለነበር ከአቶ አያሌው ቁጥጥርና ትዕዛዝ ውጪ እንደነበሩ የሚጠቁሙት ክፍሎች “አቶ አያሌው በስብዕና ደረጃ እስካሁን በክልሉ ከተሰየሙት መሪዎች የተሻሉ፣ በባህሪያቸው ረጋ ያሉና ለክልሉ ህዝብም በንጽጽር ተቆርቋሪ የነበሩ” በማለት ይገልጹዋቸዋል። በዚህም የተነሳ “ሎሌ” በሚል ስያሜ የሚጠሩት አቶ ደመቀ ብዙም እንደማይፈልጓቸው፣ በዚህ ምክንያት የልብ ወዳጃቸውና ለህወሃት በታማኝነት በመታዘዝ የሚመሳሰሏቸውን አቶ ገዱን ለሃላፊነት እንዳበቋቸው ይገልጻሉ። በሌላም በኩል ለሱዳን እንዲሰጥ በተወሰነውና ሰሞኑንን የድንበር ማካለሉ ተግባራዊ እየሆነ እንዳለ የሚነገርለትን የኢትዮጵያን መሬት ለሱዳን እንዲሰጥ የተፈረመውን ስምምነት የሚያነሱም አሉ።
አቶ አያሌው ስምምነቱን አልፈርምም በማለታቸው ሳቢያ አቶ ደመቀ እንዲፈርሙና የኢትዮጵያን ህጋዊ መሬት ለሱዳን አጨብጭበው እንዲያስረክቡ በታዘዙት መሰረት ተግባራዊ ማድረጋቸው በክልሉ የተተፉ፣ በመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ዘንድ ደግሞ የተረገሙ አድርጓቸዋል። እኚሁ ከህወሃት በቀር ዘመድና ወዳጅ የላቸውም የሚባሉት አቶ ደመቀ “አያሌው ተገዶ መፈረም ነበረበት” በሚል ሲቆጩ እንደነበር የሚናገሩ አሉ። በባህር ዳር የሚኖሩና ለአቶ ደመቀ ቤተሰቦች ቅርብ የሆኑ “አቶ ደመቀ በኩራት የኢትዮጵያን ድንበር እልል ብለው በባንዳነት ወደውና ፈቅደው ካስረከቡ በኋላ ልጆቻቸው ፊደል ከሚቆጥሩበት የህጻናት ማሳደጊያ እንኳን መቀመጥ አልቻሉም ነበር” በማለት አቶ ደመቀ ላይ የደረሰውን የጥላቻ ስርና ጥንካሬ ያስረዳሉ። እንደ እኚሁ ሰው ገለጻ ከሆነ አቶ ደመቀ የትምህርት ሚኒስትር ሆነው አዲስ አበባ እንዲዛወሩ የተደረገበት አንዱ ምክንያት ይኽው ልጆቻቸው ድረስ የዘለቀው ጥላቻ ጉዳይ ነው።
ከዚህ ማህበራዊ ቀውስ በኋላ አቶ አያሌውን በመልካም የማያይዋቸው አቶ ደመቀ የብአዴን ሊቀመንበርና ከአራቱ ጠ/ሚኒስትሮች መካከል አንዱ በመሆናቸው ጊዜ ወስደው አቶ አያሌው እንዲነሱ ጉባኤ ላይ ድምጽ ያሰጡባቸው፣ ድምጹንም አስቆጥረው ደስታቸውን የገለጹ፣ ወዲያውም ተመሳሳያቸውን መንበር አሰጥተው ደስታቸውን እጥፍ ድርብ ማድረጋቸውን ጉባኤው ላይ የነበሩ ለጎልጉል ገልጸዋል።
አቶ አያሌው በትክክል “ስልጣን በቃኝ፣ ለተተኪው ክፍል አስረክባለሁ” ቢሉ አምባሳደር ሆነው ባልተሾሙ ነበር የሚሉት እነዚሁ ወገኖች፣ “በቃኝ፣ ደከመኝ፣ ተኩኝ፣ ልተካ ብሎ የጠየቀ ባለስልጣን ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር አድርጎ በበነጋው መሾም ከሹም ሽሩ ጀርባ ችግር እንዳለ የሚያሳይ ነው” ብለዋል። አቶ አያሌው ባስቸኳይ ስብሰባ ከስልጣናቸው መነሳታቸው ቅሬታ እንዳይፈጥርና ሌሎች ባለስልጣናት ላይ የመደናበር ስሜት እንዳያስከትል በሚል “ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር” ተደርገው መሾማቸውን ያመለከቱት ወገኖች “አካሄዱ የህወሃት የተቃጠለ ስልት ነው። ብአዴን ውስጥ ውስጡን እየጨሰ ነው። አቶ ገዱ ያበርዱት እንደሆን ለወደፊቱ የሚታይ ይሆናል” ሲሉ ከሁሉም ጨዋታ ጀርባ ሌላ ችግር መኖሩን አመላክተዋል። አቶ አያሌው የልማት አርበኞችን ከማፍራት አኳያ በስኬት ጉድለት አቶ ገዱን ክፉኛ መገምገማቸውም ይታወሳል። አቶ ደመቀ የትምህርት ሚኒስትር ከሆኑ በኋላ ስራው ከክልል የስለላ ስራ የተለየ አቅም የሚጠይቅ በመሆኑ በሃላፊነታቸው ደስተኛ እንዳልነበሩ ሲገለጽ መቆየቱ አይዘነጋም።

የኢህአዴግ አዲሱ አሰላለፍ ፪ – ከተመስገን ደሳለኝ (ጋዜጠኛ)


በድህረ-መለስ ኢትዮጵያ የፖለቲካው ሥልጣን በስርዓቱ ልሂቃን መካከል ከሚደረገው የኃይል መተናነቅ አንጻር፣ ዛሬም ከመፈራረቅ ጣጣው የተላቀቀ የማይመስልባቸው ምልክቶች መታየታቸው እንደቀጠለ ነው፡፡ ከአራት ወር በፊት በዚህ መፅሄት ላይ ‹‹አዲሱ የኢህአዴግ አሰላለፍ›› በሚል ባቀረብኩት ፅሁፍ በገዥው ፓርቲ ውስጥ ተፈጥሮ ከነበረው ክፍፍል የትኛው ቡድን የበለጠ ጉልበት አግኝቶ በአሸናፊነት መውጣት እንደቻለ ከገለፅኩ በኋላ ፅሁፉን የቋጨሁት እንዲህ በማለት ነበር፡- ‹‹የፓርቲው የታሪክ ድርሳን እንደሚነግረን ‹ይሆናሉ› የተባሉት ተቀልብሰው፣ ባልተጠበቁ ሁነቶች (የኃይል መገለባበጥ ተከስቶ) ፖለቲካው የሚመራበት አጋጣሚ ሊፈጠር የሚችልበት ዕድል ሊኖር እንደሚችልም መዘንጋት አያስፈልግም፡፡››
እነሆ በዚህ ፅሁፍ ደግሞ በቅርቡ በተጨባጭ የታዩትን አዳዲስ ኩነቶች እና ይህንኑ ተከትለው ሊመጡ ይችላሉ ብዬ የምገምታቸውን ‹የቢሆን ዕድሎች› (Scenarios) ለማየት እሞክራለሁ፡፡ 
ሰላም የራቀው-ኢህአዴግ 
በግንባሩ አባል ድርጅቶች መካከል ዛሬም ድረስ ሙሉ በሙሉ የተረጋጋ ፖለቲካ አልሰፈነም፤ የዚህ ዋነኛ ምክንያቱ ደግሞ፣ ቁልፍ የሥልጣን ቦታዎችን ጠቅልሎ ይዞ በነበረው በቀድሞ ሊቀ-መንበሩ ህልፈት ሳቢያ የተፈጠረው የአመራር ክፍተት እና እርሱን ሊተካ የሚችል መሪ ማግኘት ባለመቻሉ ይመስለኛል፡፡ እንዲህ አይነት አጋጣሚዎችም በተለይ እንደ ኢትዮጵያ ባለ ከሕግ ይልቅ የጠመንጃ ኃይልና የግለሰብ አምባገነናዊነት በገነነበት ሀገር ‹የማይገመቱ ክስተቶች› (Unpredictable Event) ማምጣታቸው የሚጠበቅ ነው፡፡
የሆነው ሆኖ በዚህ አጀንዳ ለመመልከት የምሞክረው ጉዳይ፣ በአሁኑ ጊዜ ሀገር እየመራ ያለው ኃይል ለሁለት የተከፈለ ቢሆንም፣ በአንፃራዊነት በጥምር የሚሰራ መሆኑን በማስረገጥ ነው፡፡ የእነዚህ ሁለት ቡድኖች የጉልበት ምንጭም የታጠቀውን ኃይል በመቆጣጠር እና የፖለቲካውን ሥልጣን በመያዝ ላይ የተመሰረተ ነው፤ ይኸውም ሠራዊቱ እና የደህንነት መስሪያ ቤቱ ሙሉ በሙሉ በህወሓት ሰዎች ሲንቀሳቀሱ፣ ፖለቲካውን ደግሞ የብአዴን መሪዎች፣ ከተወሰኑ የኦህዴድና ደህአዴን የአመራር አባላት ጋር ተባብረው መያዛቸውን የሚያሳዩ ምልክቶች መኖራቸው ነው፡፡
የህወሓት ኃይል
ህወሓት የቀድሞው ፍፁማዊ የበላይነቱን ለመመለስ ዋና ችግር የሆነበት በውስጡ ለተፈጠረው መከፋፈል እስካሁን መፍትሄው ተለይቶ አለመታወቁ ነው፤ ከዚህ ቀደም በዚሁ መፅሄት፣ አንዱ ኃይል የተሻለ ጉልበት በማግኘቱ ሌላኛውን (እነአዜብ መስፍንን ጨምሮ አባይ ወልዱና ቴዎድሮስ ሀጎስን የመሳሰሉ ከፍተኛ ካድሬዎች የተሰባሰቡበትን) በመብለጥ በተወሰነ ደረጃም ቢሆን እንቅስቃሴያቸውን መገደቡ ተሳክቶለት እንደነበረ ማስነበቤ ይታወሳል፡፡ ይህ ክፍፍል ምንም እንኳ እንደ 1993ቱ ከፓርቲ እስከ ማስወጣት የሚደርስ አለመሆኑ ቢታወቅም፣ ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል እና ጌታቸው አሰፋ የተሰለፉበት ቡድን ተፅእኖ ፈጣሪ ሆኖ መውጣት ችሏል፤ ይህም ሆኖ ውስጥ ውስጡን የሚገመደው ተንኮልም ሆነ ሽኩቻ ገና መቋጫ አለማግኘቱ ግልፅ ነው፡፡
በዚህ ፅሁፍ ጠመንጃ የታጠቀውን ክፍል ‹የህወሓት ኃይል› እያልኩ የምገልፀበት ዓብይ ምክንያት፣ በጄነራል ሳሞራ የኑስ ኤታ ማዦር ሹምነት የሚመራው የመከላከያ ሠራዊት እና በማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ጌታቸው አሰፋ ስር ያለው የደህንነት ኃይል ለሚደግፉት ቡድን መጠናከር እያበረከቱት ያለውን አስተዋፅኦ ከግምት በመክተት ነው፡፡ ሁለቱም ሰዎች ለመለስ ፍፁም ታማኝ የነበሩ ቢሆንም፣ ከህልፈቱ በኋላ እንደእርሱ ተጭኖ ሊቆጣጠራቸው የሚችል ጉልበታም ህወሓትን ጨምሮ በሁሉም የግንባሩ አባል ፓርቲ ውስጥ አለመኖሩ፣ በፖለቲካው ‹ቼዝ› የ‹ዘመነ መሳፍንቱ›ን ሚካኤል ስሁል አይነት ሚና እንዲጫወቱ አስችሏቸዋል፤ ሁለቱም ከስራቸው የነበሩትንና ‹ስልጣን ሊጋፉ ይችላሉ› ብለው የጠረጠሯቸውን ባልደረቦቻቸውን አስቀድሞ ገለል ማድረጉ ከሞላ ጎደል የተሳካላቸው ይመስለኛል፡፡
በተለይም ጌታቸው አሰፋ ከራሱ ወንበር አልፎ ከእነአዜብ መስፍንና አባይ ወልዱ ጋር በመተባበር አንድ ቀን በጠቅላላው የመንግስት የሥልጣን እርከን ላይ ‹ናቡቴ ሊሆን ይችላል› የሚል ስጋት ያሳደረበትን እና ‹መለስ ዜናዊ ሞት ባይቀድመው በእርሱ ቦታ ሊተካው ነበር› እየተባለ የሚነገርለትን የመረጃ ኃላፊ ወልደስላሴ ወልደሚካኤል በሙስና የሚወነጀልበትን መንገድ አመቻችቶ ለእስር ባይዳርገው ኖሮ ‹‹ለቁርስ ያሰቡንን…›› አይነት ታሪክ ራሱን መድገሙ አይቀሬ ነበር ብዬ አስባለሁ፡፡
ጄነራል ሳሞራ የኑስ በበኩሉ ተቀናቃኙ አድርጎ ይመለከታቸው የነበረው ሶስቱ ከፍተኛ መኮንኖች እንደ ወልደስላሴ ‹ፍንቀላ መሳይ ነገር ሊሞክሩ ይችላሉ› ተብለው አይደለም፡፡ የእነርሱ የመጀመሪያው ችግር ከወታደራዊ ዲሲፕሊን በማፈንገጥ አለቃቸውን አለማክበራቸው ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ ሳሞራ ‹በየትኛውም ምክንያት ከኃላፊነቴ ብነሳ የቆየ ፋይል አገላብጠው አደጋ ላይ ሊጥሉኝ ይችላሉ› በሚል ስለሚጠረጥራቸው ነው፡፡ እነዚህ መኮንኖች የሰሜን ዕዝ አዛዥ ሌፍተናንት ጄነራል ሰዓረ መኮንን፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ መልካም ግንኙነታቸው እንደቀድሞው እንዳልሆነ የሚነገረው የሰሜን ምዕራብ ዕዝ አዛዥ ሌፍተናንት ጄነራል አበባው ታደሰ እና የአየር ኃይሉ አዛዥ ሜጀር ጄነራል ሞላ ኃይለማርያም ናቸው፡፡ እናም ሰዓረ እና አበባው በቀጥታ ሠራዊት ከሚያዙበት ቦታ ተነስተው በመከላከያ ሚኒስትር ውስጥ በቢሮ ስራ ላይ ሲመደቡ፣ ሞላም ከነበረበት ኃላፊነት አኳያ ብዙም ይመጥነዋል የማይባል የቢሮ ስራ ተሰጥቶታል፤ በእርሱም ቦታ ሜጀር ጄነራል አደም መሀመድ ተተክቷል፡፡ የሳሞራ እና የሞላ ልዩነት በመለስ ዘመንም በአደባባይ የሚታወቅ እንደነበረ ሰምቻለሁ፡፡
ለጉዳዩ ቅርብ ከሆነ የመረጃ ምንጬ እንዳረጋገጥኩት የአስተዳደር ዘይቤውን በማኪያቬሊያዊ አስተሳሰብ (ከፋፍለህ ግዛ) የሚያሳልጠው የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ፣ ለሞላ ትዕዛዝ የሚሰጠውም ሆነ ማንኛውንም ጉዳይ በተመለከተ የሚያነጋግረው የዕዝ ተዋረዱን ጠብቆ በኤታ ማዦሩ በኩል ሳይሆን፣ በቀጥታ በመገናኘት መሆኑ፣ አየር ኃይሉን ከመከላከያ ሚኒስቴር የተገነጠለ አስመስሎት ነበር፤ ይህ ሁኔታም በሁለቱ መኮንኖች መካከል ያለው ግንኙነት የሥልጣን ተዋረድን የጠበቀ እንዳይሆን በማሰናከሉ በጄነራሉ ላይ ደፍሮ የማይናገረው ቅሬታ ሊያሳድርበት ችሏል፤ ከመለስ ህልፈት በኋላም ሳሞራ ሂደቱን ለማስተካከል መሞከሩ፣ በየግምገማው ላይ እስከ መዘላለፍ አድርሷቸው ነበር (በነገራችን ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ወደ ሥልጣን ከመጣ በኋላ እንደ ጦር ኃይሎች አዛዥነቱ፣ ከጄነራሎቹ ጋር መደበኛ /Official/ በሆነ መንገድ ትውውቅ አላደረገም፤ እነዚህ ሶስት ጄነራሎችም ለዚህ አይነቱ የአሰራር መፋለስ ጥፋተኛ የሚያደርጉት አለቃቸውን ሳሞራ የኑስን ነው፤ ከምንጮቼ እንደሰማሁት ከሆነም ከወራት በፊት ኃይለማርያም ደሳለኝ በተገኘበት ‹ጎልፍ ክለብ› በሚባለው የጄነራሎቹ መዝናኛ በተዘጋጀ ፕሮግራም ማጠናቀቂያ ላይ ሳሞራ አንድ ጠረጴዛ ከበው ወደ
ተቀመጡት እነዚህ ጄነራሎች ጋ ሄዶ ‹ኑ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ላስተዋውቃችሁ› ማለቱን እና እነርሱም በጥያቄው ተበሳጭተው ቢሮ ያላቸው መሆኑን እና ክብራቸውን በሚመጥን መልኩ መተዋወቅ እንደነበረባቸው በኃይለ ቃል መመለሳቸውን ነው)
የሳሞራ የኑስ እና ሰዓረ መኮንን መነቋቆር ከትግሉ ዘመን ጀምሮ የመጣ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ሆኖም ሳሞራ ከማንም በላይ የሚፎካከረውም ሆነ መበለጥ የማይፈልገው በሟቹ ጄነራል ኃየሎም አርአያ እንደ ነበር የቀድሞ ጓዶቻቸው ያስታውሳሉ፤ ይህ ሁኔታ ዛሬም ድረስ በስራ ላይ ያሉ መኮንኖችን ‹የሳሞራ› ወይም ‹የኃየሎም ተከታይ› በማለት መከፋፈሉ በጓዶቻቸው እና በፓርቲው መሪዎች አካባቢ የሚታወቅ ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ለማዕረግ እድገት የተለየ የድጋፍ አስተያየት የሚያገኙት በዛን ዘመን ‹የሳሞራ ተከታይ› የሚባሉት እየተመረጡ እንደነበረ በወሬ ደረጃ ይናፈሳል (በነገራችን ላይ ጄነራል ሳሞራ ከጤንነት ጋር በተያያዘ በአጭር ጊዜ ውስጥ በጡረታ ይሰናበታል በተባለበት ጉዳይ ላይ እያንገራገረ እንደሆነ ከመከላከያ አካባቢ የሚወጡ መረጃዎች ያመላክታሉ፤ እንደ ምክንያት የሚጠቀሰው ደግሞ ‹ለእኔ በጎ አመለካከት የላቸውም› በሚል የሚጠራጠራቸው ጄነራሎች በሥራ ላይ እያሉ የእሱ ጡረታ መውጣት ከመስሪያ ቤቱ ጋር ተያይዘው የሚነሱ ያደሩ የሙስና ካርዶች የሚመዘዙበትን ዕድል ያሰፋዋል የሚል ነው፤ በተለይም በግዙፍ የቢዝነስ ሥራዎች ላይ በታላቅ ተፎካካሪነት እየተሳተፈ የሚገኘው ‹መቴክ› ምንም እንኳ ማረጋገጫዎች ባይቀርቡበትም በመከላከያ ሥር ከነበረበት ዘመን እስከ 2002 ዓ.ም መጨረሻ ድረስ ከግዥዎች ጋር ተያይዘው የሚነሱ በርካታ የሙስና ሁኔታዎች በመኖራቸው ነው፡፡
መቴክ ካለፉት አራት ዓመታት ጀምሮ በአዋጅ የልማት ድርጅት እንዲሆን ቢደረግም፣ ዛሬም ዳይሬክተሩ የሠራዊቱ አባል ብርጋዴር ጄነራል ክንፈ ሲሆን፣ መከላከያ ደሞዝ የሚከፍላቸው ጥቂት የማይባሉ ሠራተኞችንም እንዳቀፈ ይታወቃል፡፡ እናም ሳሞራ ሃሳቡ ከተሳካለት ለጥቂት ተጨማሪ ዓመታት በሥልጣኑ ላይ ሲቀጥል፣ አሊያም ‹የወንድ በር› ለማግኘት በትግሉ ዘመን የእርሱ ሰልጣኝ እንደነበረ የሚነገርለትን እና በቅርቡ ብቸኛው ከሜጀር ወደ ሌፍተናት ጄነራል ማዕረግ ያደገው ዮሀንስ ገ/መስቀል እንዲተካው መንገድ ጠረጋውን ማመቻቸቱ ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራበት ጉዳይ ይመስለኛል)
ይህም ሆኖ የተኮረኮርን ያህል የምንስቀው ጄነራል ሳሞራ የኑስ በቅርቡ ለታተመው ‹‹ህብረ ብሔር›› መፅሄት ሙስና ለሠራዊቱ አደገኛ መሆኑን እንዲህ በማለት መግለፁን ስናነብ ነው፡-
‹‹ሙስና ሠራዊቱን ሊያበላሸው ይችላል፡፡ ሙስና ፀረ-ልማት ነው፤ ሠራዊቱን ሊበትነው እና ሕዝባዊ ባህሪውን እንዲያጠፋ ሊያደርገው ይችላል፤ አንድ ሠራዊት ሠራዊት ነው የሚባለው እንደ ወታደር እንደ አንድ አካል ሲያስብ እንጂ ለግሉ ሲያስብ አይደለም፡፡ …በአጠቃላይ (ሠራዊቱ) በዚህ ነው የሚፈርሰው፡፡›› 
መቼም ጄነራሉ ይህንን የተናገረው እራሱን ጨምሮ በርካታ ከፍተኛ መኮንኖች እንደ እንግሊዝ ንጉሳውያን ቤተሰቦች በተንጣለለ ቪላ ቤት ውስጥ፣ የተቀማጠለ ኑሮ መኖራቸውን ረስቶት አይመስለኝም፤ ‹ይህ የተንዛዛ ወጪያቸውም የሚሸፈነው ከደሞዛቸው በሚያገኙት ገቢ ነው› ብሎ ቧልት መሳይ ክርክር ሊያመጣ አይችልም፡፡ ይሁንና እታች ያለው ጭቁን የኢትዮጵያ ሠራዊት ምንም እንኳ በአለቆቹ ‹ቴክሳስ›ነት ላይ ለመቆጣት ባይደፍርም፣ እንደማንኛውም ዜጋ ለኑሮ ውድነትና አስከፊ ድህነት የተጋለጠ መሆኑን መካድ አይቻልም፡፡
የሆነው ሆኖ ተሰሚነታቸው እየተቀዛቀዘ የመጣው አቦይ ስብሃት ነጋ ከወራት በፊት ለ‹‹ውራይና›› መፅሔት ‹‹ህወሓት ትንሳኤ ያስፈልገዋል›› በማለት የሰጡትን ምክር ተከትሎ፣ ጄነራል ሳሞራ እና አቶ ጌታቸው አሰፋ፣ ከድርጅቱ ምክትል ሊቀ-መንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ጋር በመተባበር ህወሓትን ለማጠናከር እና በፖለቲካ ውስጥ የነበረውን የአንበሳውን ድርሻ ለማስከበር (ጉዳዩን ከለጠጥነው ደግሞ ‹ለማስመለስ›) እየሰሩ እንደሆነ ይነገራል (በነገራችን ላይ የሳሞራና ጌታቸው ተፅእኖ መጨመሩን ለመረዳት፣ መከላከያ ‹አገራዊ ጥቅምንና ደህንነትን ለመከላከል› በሚል ‹እጅግ ጥብቅ ሚስጢር ብሎ የሰየማቸውን የሰው ኃይል ፕሮፋይል፣ የሒሳብ መዝገቦችና ሰነዶች እና የክፍያ ማስረጃዎች ለማንም አካል እንዳይገለፅ› የሚያስችለውን ስልጣን፣ ደህንነቱ ደግሞ በስራ ላይ የሚፈፅማቸው ማንኛውም ጉዳዮች ወደፊት በህግ እንዳይጠይቅ እስከ መከላከል የሚደርሰውን አዲስ የተዘጋጁትን አዋጆች ማንበቡ በቂ ነው፡፡ በርግጥ እነዚህ ባለሥልጣናት እንዲህ ባለ ተመሳሳይ መንገድ እንዲጓዙ ያስተሳሰራቸው አንዱ ጉዳይ ‹ህወሓት ተዳከመ፣ ተሸነፈ፣ አበቃለት…› የሚለው የካድሬውና ደጋፊው ቁጭት እንጂ ወትሮም መልካም ግንኙነት ኖሯቸው አይመስለኝም)
ለማንኛውም በጥቅሉ ሲታይ የህወሓት ትልቁ ችግር ተብሎ በአመራር አባላቱ የሚጠቀሰው ‹በዚህ ወቅት ወደፊት መምጣት የሚችሉ ጠንካራ ቴክኖክራቶችን አለማፍራቱ፣ ሁለንተናዊ ድጋፍ የሚያደርግለትን የታጠቀውን ኃይል ተጠቅሞ የፖለቲካ ልዩነቱን ጨፍልቆ በአሸናፊነት ይዞት መውጣት የሚችል መሪ እንዳይኖረው አደረገ› የሚል ነው፡፡ በርካታ የላይኛ እና የታችኛው ካድሬዎችም ‹ለእንዲህ አይነቱ ክፉ ጊዜ ድርጅቱ የሚያስፈልገው፣ በትግሉ ዘመን ልምድ ያካበተ ታጋይ ብቻ ነው› የሚል አቋም እንዳላቸው ይነገራል፡፡ ስርዓቱ ከሚያራምደው ርዕዮተ-ዓለም ጋር ጠንካራ ትውውቅ ያሌለውን እና የትግሉን ዘመን በአሜሪካን ሀገር በማሳለፉ ‹የምዕራባውያን ድጋፍ አለው› ለሚባለው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም የሚሰጡት ዝቅተኛ አመለካከት መግፍኤም ይኸው ይመስለኛል፡፡
ለነገሩ እርሱም ቢሆን በጠንካራ ድርጅታዊ ዲሲፕሊን ካለመታነፁ እና መሰል ጉዳዮች ጋር በሚያያዙ ምክንያቶች ለትንፋሽ ጊዜ የማይሰጠውን የድርጅት ሊቀ-መንበርነትንም ሆነ የጠቅላይ ሚኒስትርነት ቦታ የሚወራውን ያህል ይፈልገዋል ብሎ መደምደሙ አስቸጋሪ ነው ብዬ አስባለሁ፤ ከዚህ ይልቅ በተፈጥሮ ከታደለው የተግባቢነት ባህሪው አኳያ እንደ ሕዝብ ግንኙነት የመሳሰለ ብዙም የማያጨናንቅ ሥራን ይመርጣል፡፡ ለዚህም ይመስለኛል ከሰለጠነበት ሙያ ጋር የቀጥታ ተያያዥነት ያለውን የጤና ጥበቃ ሚኒስትር በሚመራበት ዘመን፣ ከውጭ ሀገር በርካታ የተቋረጡ ፈንዶችን እንደገና ለማስለቀቅ መቻሉ እንደ ታላቅ ስኬት የሚወራለት፤ አልፎ ተርፎም ‹ወባን ከኢትዮጵያ ምድር ለማጥፋት ብርቱ ትግል አደረገ› ተብሎ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሳይቀር እስከ መሸለም የደረሰው እዚህ መስሪያ ቤት እያለ እንደሆነም ይታወቃል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ በፓርቲውም ሆነ በመንግስት አስተዳደር ከህወሓት ሰዎች ትልቁን ስልጣን የያዘው ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ከምዕራባውያን ጋር የቆየ ቀረቤታ እንዳለው ሰምቻለሁ፤ እንደሚታወሰው ደብረፅዮን ከክፍፍሉ በፊት (የደህንነት መስሪያ ቤቱ እንዲህ እንደ ዛሬው እጅግ ዘመናዊ በሆነው የቻይና ቴክኖሎጂ ሳይጥለቀለቅ) ከነበረው ከፍተኛ የሥልጣን ቦታ ላይ ተነስቶ፣ ቁልቁል ወርዶ በሁመራ በአንድ ዞን እንዲሰራ የተመደበው (ሁላችንም ስንገምት እንደነበረው) የአንጃው አባል ወይም ደጋፊ ሆኖ አይደለም፤ ይልቁንም የእነስዬ-ተወልደ ቡድን በመባል የሚታወቀው (‹አፈንጋጩ› ኃይል) ደብረፅዮንን በሲ.አይ.ኤ እና ሞሳድ ወኪልነት የመክሰሱ ጉዳይ የድርጅቱን በርካታ አባላት ቀልብ በመሳቡ፣ መለስ ይህንን ተከትሎ ከሚመጣበት አደጋ ራሱን ለመከላከል የወሰደው እርምጃ በመሆኑ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት እስከ 1998 ዓ.ም መጨረሻ ድረስ በሁመራና ራያ አካባቢዎች በዞን ደረጃ ለማገልገል ተገዷል፡፡ እናም እርሱን የምዕራቡ ዓለም ፊት-አውራሪ አሜሪካና ሸሪኮቿ ወዳጅ ነው የሚያስብለው በቀድሞ መስሪያ ቤቱ በኩል በነበረው ግንኙነት ይመስለኛል።
የፖለቲካውን መዘውር የጨበጠው ኃይል
የዚህ ቡድን አምበል እንደ ድርጅት ብአዴን ቢሆንም፣ በቋሚ ተሰላፊነት ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ አባዱላ ገመዳ፣ ሙክታር ከድር እና ሬድዋን ሁሴን እንደሚገኙበት ይነገራል፤ ለብአዴን ‹በተሻለ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ላይ ለመገኘቱ መደላድል ፈጥሮለታል› የሚለውን ሙግት ምክንያታዊ የሚያደርገው ደግሞ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፖሊሲና ጥናት ምርምር አማካሪ በረከት ስምዖን፣ የኢህአዴግን የካድሬ ማሰልጠኛ ማዕከል በዳይሬክተርነት የሚመራው አዲሱ ለገሰ፣ ደርቦ ይዞት የነበረውን የትምህርት ሚኒስትርነት ለሽፈራው ደሳለኝ በመልቀቅ፣ በአሁኑ ወቅት ሙሉ የስራ ጊዜውን በግንባሩ ፅ/ቤት የሚያውለው ም/ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን እና የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ-ጉባኤው ካሳ ተክለብርሃን የያዙት ሥልጣን ያለውን የፖለቲካ አቅም መመዘኑ ይመስለኛል፡፡ በመከላከያ ሠራዊቱ ውስጥም ከሳሞራ አንድ እርከን ዝቅ ባለ ሥልጣን ከሌሎች ሁለት ጄነራሎች ጋር የሚገኘው አበባው ታደሰ እንደ ቀድሞው በዕዝ አዛዥነቱ (በቀጥታ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ወታደሮችን ማንቀሳቀስ የሚችልበት) ላይ ቢሆን ኖሮ ጥንካሬውን የተሟላ ማድረጉ አይቀሬ እንደነበረ መገመት ይቻላል፡፡
ከዚህ ሌላ ለእነበረከት ቡድን ተጨማሪ የፖለቲካ ጉልበት እየሆናቸው ያለው የኃይለማርያም ደሳለኝ ቢሮ እና በአባዱላ ገመዳ አፈ-ጉባኤነት የሚመራው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ነው፡፡ አባዱላ፣ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ሪፖርት ለማቅረብም ሆነ ለመታዘዝ ፍቃደኛ ያልሆኑ አንዳንድ ባለስልጣናት፣ በውስጥ መስመር በሚተላለፍለት ‹ጥቅሻ› በምክር ቤቱ በኩል የሚመለከተው የቋሚ ኮሚቴ አባላት አስጠርቶ የተሰጠውን ኃላፊነት የሚገመግምበት ስልት እየተገበረ ነው፡፡ በአናቱም ምን ጊዜም የሳምንቱን የሥራ መጨረሻ ቀን አርብን ጠብቆ የሚሰበሰበው የሚኒስትሮች ም/ቤትን ከሞላ ጎደል ይህ ቡድን እየጠቀመበት ይመስለኛል፡፡ በርግጥ ሚኒስትሮቹ በሚገናኙበት አብዛኛውን ሰዓት ሳይግባቡ (በጭቅጭቅ) ማሳለፋቸው ይነገራል፤ የዚህ ምክንያቱ ደግሞ በአቶ መለስ ዘመን ም/ቤቱ የሚሰበሰበው የተለያዩ አጀንዳዎችን ለማቅረብ እና በቀረበው አጀንዳ ላይ ለመከራከር (ለመመካከር) ሳይሆን፣ መለስ ወስኖ የመጣበትን የሥራ ድርሻ ተቀብሎ ለመበተንና ሪፖርት ለመስማት የነበረው አሰራር፣ ዛሬ ተቀይሮ በርካታ የተነቃቁ ሚኒስትሮች የየራሳቸው ሃሳብ ተቀባይነት እንዲያገኝ (ለማንፀባረቅ) የሚታገሉበት መድረክ ወደ መሆን በመሸጋገሩ ነው፡፡ ይህም ሁናቴ ዋናውን የመንግስት ሥራ የመገምገም እና የማስፈፀም አቅምን ሳይቀር ከሚኒስትሮች ም/ቤት ወደ ኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ አሻግሮታል የሚያስብሉ ማሳያዎች አሉ፡፡ ይሁንና በዚህስብሰባ ላይም ቢሆን ደፈር ብሎ ከበረከት ስምዖን እና አባይ ፀሀዬ የተሻለ አዳዲስ ሃሳብ የሚያቀርብ ባለሥልጣን እንደሌለ ሰምቻለሁ (በነገራችን ላይ ምክንያቱን ባላውቅም የጠቅላይ ሚኒስትሩ ‹የፖሊሲና ጥናት ምርምር አማካሪ› ተደርገው የተሾሙት በረከት ስምዖን፣ አባይ ፀሀዬ፣ ኩማ ደመቅሳ እና ዶ/ር ካሱ ኢላላ የሥራ ቦታቸው በጠቅላይ ሚኒስትሩ ፅ/ቤት ሳይሆን መገናኛ አካባቢ በሚገኝ አንድ ህንፃ ላይ ነው፡፡ የተሰጣቸው ኃላፊነት ኃይለማርያምን በቅርብ እንዲያገኙ ከማስገደዱ እና በግልፅ ከሚታወቀው የአማካሪ አስፈላጊነት አኳያ ካየነው ግን ግራ የሚያጋባ ይመስለኛል)
ጠቅላይ ሚኒስትሩ…
ኃይለማርያም ደሳለኝ ይህንን ቦታ ከያዘ በኋላ፣ ብዙዎች በስልጣኑ የማዘዝ አቅሙ ላይ አመኔታ እንደሌላቸው (አንጋፋ ታጋዮች እንደ ‹አሻንጉሊት› ሊጠቀሙበት እንደሚችሉ) ደጋግመው መግለፃቸው ይታወሳል፡፡ በግልባጩ ‹አፈንግጦ ለመውጣት መሞከሩ አይቀሬ ነው› የሚሉ ግምቶች ነበሩ፡፡ በርግጥ እነዚህ መላ-ምቶች ዛሬም ድረስ እልባት ባያገኙም፣ እዚህ ጋ ያልጠቀስኳቸው አንዳንድ ጉዳዮች ላይ ያሳያቸው ወጣ ያሉ አቋሞቹን ሳስተውል ግን፣ አሁን ያለው አሰላለፍ (የአነበረከት እና አባዱላ ፖለቲካዊ መጠናከር) ለእርሱም የተረፈው ይመስለኛል፡፡ እንዲሁም ከቤንች ማጂ የተባረሩ አማርኛ ተናጋሪዎችን አስመልክቶ በድርጅቱ ውስጥ ባልተለመደ መልኩ ‹አጥፊዎቹ ላይ እርምጃ እወስዳለሁ› ከማለት አንስቶ (በነገራችን ላይ በአማካሪ ብዛት እንዲከበብ ካደረገው ምክንያት አንዱ ጓዶቹ በዚህ ንግግሩ መበሳጨታቸው ነው) በቅርቡ ህወሓትን ለመሸምገል በተዘጋጀ መድረክ ላይ ‹ሁኔታዎች እንዲህ እየተካረሩ ከሄዱ ወደ ማሰሩ መግባታችን አይቀርም› በማለት ማስፈራራቱ እና በቴዎድሮስ አድህኖም የሶሻል ሚዲያ አጠቃቀም ላይ የመቆጣቱ ጉዳይ ድረስ የሚካተቱ እውነታዎች ሰውየው የራሱን መንገድ ለመከተል እየሞከረ መሆኑን ያሳያሉ ብዬ አስባለሁ፡፡
የሆነው ሆኖ እነዚህ ሁናቴዎች የፖለቲካውን ጉልበት ሙሉ በሙሉ በብአዴንና በተባባሪነት በጠቀስኳቸው የኦህዴድና ደህአዴን የአመራር አባላት አካባቢ ቢያከማቻቸውም፣ በማንኛውም ሰዓት ያሻውን ማድረግ የሚችለው የታጠቀው ኃይል ደግሞ ከህወሓት ጎን እንደተሰለፈ ይገኛል፡፡ መጪውን ጊዜም አዲስ ክስተት እንድንጠብቅ ገፊ ምክንያት ይህ አይነቱ የኃይል አሰላለፍ ይመስለኛል፡፡
ምን እንጠብቅ?
ከረጅሙ የፓርቲ ፖለቲካና መንግስታዊ መንገራገጮች በኋላ፣ የሁለቱንም የኃይል መሰረቶች ጠቅልሎ በመዳፉ ሥር የከተተው መለስ ዜናዊ በሞተ ማግስት ‹የኃይል መገዳደሮች ሊከሰቱ ይችላሉ› የሚለው የብዙዎቹ ግምት ነበር፤ ከወራት በፊት አስነብቤ በነበረው ከላይ በተጠቀሰው ፅሁፍም ግምቶቹ እውን መሆን እንደ ጀመሩ ማሳያዎች ማቅረቤ ይታወሳል፡፡ ኢህአዴግ ውስጥ ራሳቸውን ያቧደኑት ኃይሎች ዋነኛ ግብ ከሥልጣን የሚነሱ ጥቅሞችና አነስተኛ የየራሳቸው ፓርቲ ፍላጎቶች የፈጠሩት በመሆኑ፣ እንደ ሟቹ ደመ-ቀዝቃዛ አምባገነን አይነት በጠንካራ መዳፍ ሥር የሚያሰባስባቸው ባለመገኘቱ በየጊዜው የኃይል መሸጋሸጎች ሊከሰቱ እንዲችሉ አድርጓቸዋል፤ አሁንም እየተስተዋለ ያለው ይኸው እውነታ ነው፡፡ በዚህ አውድ ላይ ቆመን ሊፈጠሩ የሚችሉ የቢሆን ሃሳቦችን ስናስቀምጥም በጠረጴዛው ላይ የምናገኘው ሁለት ዕድሎችን ይመስለኛል፡፡
የመጀመሪያ ሲናሪዮ የሚሆነው ከላይ የጠቀስኩት ቡድንተኝነት እንዳለ ሊቀጥል ይችላል የሚል ነው፤ ይህም የሚሆንበት ምክንያት ባለኝ መረጃዎች መሰረት የፖለቲካውን መስመር የያዘው ቡድን መሪ አባላት፣ አሁን ያላቸውን መንግስታዊ ሥልጣን ጠብቀው መቆየትን መሰረታዊ መሰባሰቢያ አጀንዳ ማድረጋቸው ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የሳሞራና ጌታቸው ጥምረት ህወሓትን ወደ ቀደመው ዘመኑ ለመመለስ ቢሻም፣ ሊሄድበት የሚችልበት መንገድ አደገኛ መሆኑ (ወታደራዊ ላዕላይ መዋቅሩንና የደህንነት ኃይሉን ከመያዙ አኳያ) ሁኔታዎችን ባሉበት ይዞ መቀጠልን በትርፍ-ኪሳራ ስሌት የተሻለ አማራጭ አድርጎ ይወስደዋል ብዬ አስባለሁ፡፡
ሁለተኛው የቢሆን ዕድል፣ ዳግመኛ የኃይል መሸጋሸግ ሊፈጠር መቻሉ ነው፤ ሰዎቹ ጥቅመኛ በመሆናቸው የቋንቋ ተናጋሪነት ልዩነቶቻቸውንና የኋላ የመቆራቆስ ታሪኮቻቸውን ተሻግረው፣ አንዳቸው ከአንዳቸው ጋር ሌላ መልክ ያለው ስብስብ ሊፈጥሩ ይችሉ ይሆናል፤ ይህ አይነቱ አዲስ የኃይል አሰላለፍም፣ ከቀጣዩ ሀገራዊ ምርጫ በፊት በማይታወቀው ተሰዊና ሰዊ ሊጠናቀቅም ይችላል፡፡
በመጨረሻም ምንም ይፈጠር ምን፤ እኛን ሊያግባባን የሚገባው ጭብጥ፣ የትኛውም ቡድን በግንባሩ ውስጥ ቢነሳ፣ የማዕከላዊ መንግስቱን ህልውና ወደሚበታትን ሂደት መግባቱ ሊሰካለት አለመቻሉ ነው፤ ምክንያቱም በዚህ መልኩ ሄዶ የሚጣሉበትን ጠረጴዛ መስበሩ ምን እንደሚያስከትል ያውቁታልና ወደዚህ ምዕራፍ እንደማይሻገሩ አምናለሁ፡፡ ይሁንና ከፓርቲው ዝግነት እና ከፖለቲከኞቹ አቋም የለሽነት አንፃር አሁንም ሆነ በቀጣይ ጊዜያት ከማንም ግምት ውጪ ያሉ ክስተቶች እንደ ደራሽ ውሃ ድንገት ሳይታሰብ ግንባሩን ሊያተራምሱት ይችላሉ ብሎ መገመቱ አግባብ ይመስለኛል፡ ,,,,,,       / ዘሀበሻ/

የደቡብ ሱዳን ሁኔታ ዓለምአቀፉን ማኅበረሰብ እያሳሰበ ነው

የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት የፖለቲካ ተቃዋሚያቸው ደጋፊዎች መፈንቅለ-መንግሥት ሞከሩብኝ ባሉ ማግሥትም ዛሬ በዋና ከተማይቱ ጁባ የተኩስ ልውውጡ ቀጥሎ ውሏል፡፡
sudan
የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት የፖለቲካ ተቃዋሚያቸው ደጋፊዎች መፈንቅለ-መንግሥት ሞከሩብኝ ባሉ ማግሥትም ዛሬ በዋና ከተማይቱ ጁባ የተኩስ ልውውጡ ቀጥሎ ውሏል፡፡
በሁከቱ ቢያንስ ሃያ ስድስት ሰው መገደሉንና በሺኾች የሚቆጠሩ ሲቪሎች መፈናቀላቸውን የመንግሥቱ ባለሥልጣናት አስታውቀዋል፡፡
የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር የሰዓት ዕላፊ ገደብ መደንገጋቸውን ከቢሯቸው በገለፁበት ወቅት፤ ሰኞ፣ ታኅሣስ 7/2006 ዓ.ም
የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር የሰዓት ዕላፊ ገደብ መደንገጋቸውን ከቢሯቸው በገለፁበት ወቅት፤ ሰኞ፣ ታኅሣስ 7/2006 ዓ.ም
የጎረቤቶቿ የሱዳንና የኬንያ መሪዎችም ለሳልቫ ኪር ስልክ እየደወሉ አለኝታነታቸውን ገልፀውላቸዋል፡፡
የሱዳን መንግሥት “ሁኔታውን በቁጥጥር ሥር አውያለሁ” ካለ በኋላ ውጊያው መቀጠሉ ያሳሰባቸው መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ ባን ኪ ሙንና የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናትም ገልፀዋል፡፡
ጎረቤቶቿ ሱዳንና ኬንያም እንዲሁ ሥጋታቸውን እየገለፁ ነው፡፡
ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡


Saturday, December 21, 2013

አድርባይነት (ለጥቅም ሕሊናን መሸጥ)

December 21, 2013
ከማርቆስ ዐብይ
ኢትዮዽያ ሀገሬ ሞኘ ነሸ ተላላ፣
የሞተልሸ ቀርቶ የገደለሸ በላ፣
The Ethiopian government spokesman Shimeles Kemal
እኚ ሰው የኮሚኒኬሸን ጉዳዮች ሚንስትር ዴእታ አቶ ሽመልሰ ከማል ይባላሉ…
አድርባይነት ቀለል ባለ አገላለጽ ማስመስል ወይም ለጥቅም ሲባል ሕሊናን መሸጥ እንደማለት ነው፣፣ ይህ እኩይ ባሕሪ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ቀላል የማይባል እድሜ አስቆጥሯል የሩቁን ትተን የቅርቡን ከጣሊያን ወረራ ቦኋላ ያለውን አሁን እስካለንበት ጊዜ ያለውን ለማየት ብንሞክር እንኳ በጣም ብዙ ነገሮችን መታዘብ እንችላለን።
ጣሊያን ኢትዮጵያን በግፍ በወረረበት ወቅት የክርስቶስን ወንጌል ይሰብኩ ከነበሩ የሐይማኖት አባቶች መካከል በጥቅማ ጥቅም የተደለሉ ጥቂት የሐይማኖት አባቶች በየአውደ ምሕረቱ ለምዕመናን ከመጽሃፍ ቅዱስ ላይ ኤሳው ለምስር ወጥ ሲል ብኩርናውን አሳልፎ ለወንድሙ ለያዕቆብ መሸጡን በመጥፎ ተምሳሌትነት እንዳላስተማሩ ሁሉ ራሳቸው ለቁራሽ እንጀራ ሲሉ ሕሊናቸውን በመሸጥ ከወራሪው ከጣሊያን ጎን በመሰለፍ ለምዕመናኑ በሃሰት በእግዚአብሔር ሃምሳል ኢትዮጵያን ለመታደግ የመጣ ነው በማለት ሕዝቡ ወራሪው ጣሊያንን አሜን ብሎ እንዲቀበል ያግባቡ ነበር።
በዚህ የወረራ ዘመን የንጉሠ ነገሥቱ የቅርብ ባልሙዋል ከነበሩ መኩዋንንቶች እና መሳፍንቶች መካከል ሳይቀር ለጣሊያን ያደሩ ነበሩ፣፣ እነዚህ ሹማምንቶች ህዝቡ ተቃውሞውን በማቆም ይዘውለት የመጡትን እውቀት እና ስልጣኔ በመቅሰም ሀገሩን ያለማ ዘንድ ሰዎቹን በትዕግሰት እንዲጠብቃቸወ በሀሰት ይሸነግሉት ነበር።
ታዋቂው ደራሲ አቤ ጎበኛ የረገፉ አበቦች በሚል ርዕሰ ያሳተሟት ልብ ወለድ መፅሃፍ ውስጥ ስለነዚህ ከዳተኞች የአድርባይነት መጠን ማሳያ የሚሆን አንድ ታሪከ ያሰነብቡናል፣ ይህውም በዚያ ዘመን የነበሩ በአካባቢው ህብረተሰብ ዘንድ ትልቅ ስም ያላቸው አንድ ሰው ነበሩ እኚ ሰው ባለቤታቸው ሲወልዱ ትልቅ ግብዣ አዘጋጅተው ብዙ ሰው ይጋብዛሉ ከተጋባዡቹ መካከል የጣሊያን ወታደሮች የክብር ቦታ ተዘጋጅቶላቸዋል በግብዣው ሰፍራ ላይ ተገኝተዋል አሳላፊዎች ሰውን ለማስደሰት ከወዲህ ወዲይ ይራወጣሉ በዚህ መሀል ከክብር እንግዶች አጠገብ ተጎልተው የነበሩት ጋባዠ በእጅ ምልክት ሰውን ፀጥ እንዲል በማድረግ የልጃቸውን ሰም በታዳሚው ፊት ለማውጣት እንደሚፈልጉ ገለፁ በማሰከተልም ልጄን ሮማ (ROMA) ብያታለሁ አሉ አድናቆትና ጭብጨባ የክብር እንግዶች ካሉበት አካባቢ ብቻ ቀረበ የተቀረው ተጋባዠ እነሱን ተከትሎ አጨበጨበ እንጂ ሰለሰሙ የሚያውቀው ነገር ስለሌለ ነገሩ እሰከሚገለፅለት ድረሰ አላወቀም ነበር፣ በመቀጠልም ሮማ አሉ በአሰመሳይነት ኩራት የጌቶቻችን ሀገር ዋና ከተማ ነች ብለው ተቀመጡ፣ ሰው ሕሊናውን ሲሸጥ መቼም እራሱንብቻ ሳይሆን ቤተሰቡንም ለመሰዋትነት ያቀርባል።
መቼም እንዳያልፈው የለምና ያ የመከራ ጊዜ አለፈና በአርበኞች ፅናትና ተጋድሎ ዘመቻው በድል ተጠናቀቀ ፣ ወራሪው ጣሊያን በኩራት የተመላለሰባቸው እነዛ ጎዳናዎች በሃፍረት አንገቱን አቀርቅሮ የሞተው ሞቶ የተረፈው በደመነፍሰ ተራወጠባቸው በግፍ የወረራትን ሃገር በሃፍረት ጥሉዋት ፈረጠጠ ፣ እነዛ ወራሪውን አዝለው ህዝቡን ሲያሰጨንቁት የነበሩት ሆዳደሮች ግን ያዘሉትን ያህል እንኩዋን ሊያዝላቸው ቀርቶ እጃቸውን ይዞ የሸሸበት ያህል እንኩዋን ይዟቸው ሊሄድ አልወደደም እንደ ፓሰታ መቀቀያው ዕቃ የትም ጥሏቸው ሄደ እንጂ፣ እነዚ ከመጣው ጋር እንደ ሴተኛ አዳሪ ወዳጅ መሰለው መቅረብ እንደ መልካም በሐሪ የተጣባቸው ግለሰቦች አርበኞች ወደ ከተማ ሲገቡ ፀጉራቸውን አሳድገው ተቀላቀሉዋቸው እኛ ልጃቸውን ሮማ ብለው የሰየሙ ግለሰብም የልጃቸው ሰም ላይ ’ን’ በመጨመር ሮማን በማለት አይናቸውን በጨው አጥበው ከአርበኞች ጋር ላይ ታች ሲሉ ያያቸው የሀገሬው ሰው በትዝብት እጁን አፉ ላይ ጭኖ በመገረም ነበር የሚያያቸው ይሉናል አቤ ጎበኛ።
እሰካሁን ለመቃኝት የሞከርነው ህሊናቸውን ሸጠው ታሪክ አበላሸተው ወደማይቀረው ሞት ሰለነጎዱ ሰዎች ነው፣ አሁን ደግሞ በህይወት ያሉ ነገር ግን ህብረተሰቡ አፈር ካለበሳቸውና ሃውልታቸው ላይ ሆዳደር ብሎ ካተመባቸው ግለሰቦች መካከል ለናሙና አንዱን በመውሰድ እናወጋለን ከዛ አሰቀድመን ግን እንደመሸጋገሪያ ይሆነን ዘንድ ከጥቂት አመታት በፊት ጠቅላይ ምኒሰትር መለሰ ዜናዊ የሀገር ሸማግሌዎችን ሰብሰበው ሲያወያዩ አንድ የሃይማኖት አባት የተናገሩትን አሰገራሚ ንግግር እናሰቀድም እንዲህ ነበር ያሉት “በአባቶቻችን እሰከ አሁን ድረስ ሲነገር የቆየው ከወደ ሰሜን በመነሳት ኢትዮዽያን በጠነከረ አንድነት የሚያሰተዳድራት ንጉስ ይመጠል የተባለው ትንቢት ተፈፀመ ይህውም አንተ ነህ ብለው ጣታቸውን ወደሰብሳቢው ጠቆሙ” እሳቸውም በትዝብት ፈገግ ብለው ምላሸ ሰጡ፣ እኝህ አሰተያየት ሰጪግለሰብ ሀገሪቱ ቋንቋን መሰረት ባደረገ ክልል ተሸንሸና እንደባቢሎን ሰዎች እርስ በእርሰ መግባባት እንዳልተቻለ ሳያውቁ ቀርተው አይደለም ይህን ባሉበት ወቅት ሰዎች በዘመቻ መልክ ክልላችሁ አይደለም እየተባሉ የዘሩትን ሳይሰሰቡ ከየቦታው የሚፈናቀሉበት ውቅትም ነበር ይህንንም አሳምረው ያውቃሉ ነገር ግን እሳቸው እያሰሉ ያሉት ይህን መናገራቸው እንደውለታ ተቆጥሮላቸው ወደ ቅያቸው ሲመለሱ ስለሚደረግላቸው ከንቱ ውዳሴ ወይም ስልጣን ብቻ ነው፣ ይህን እዚህ ላይ ቋጭተን እሰኪ በአዲሰ መስመር ላይ እላይ ወደጀመርነው አንድ አስገራሚ ሰው እንመለስ።
እኚ ሰው የኮሚኒኬሸን ጉዳዮች ሚንስትር ዴእታ አቶ ሽመልሰ ከማል ይባላሉ፣ አቶ ሽመልሰ በመጀመሪያ ኒሻን የምትባል የግል ጋዜጣ በማቋቋም የመንግስትን ስህተት እየነቀሱ በጣም ጠንከር ባለ አገላለፅ ይተቹ ነበር ከዚህ ጎን ለጎን ሌላው የሚታወቁበት ደግሞ መንግስት በውሃ ቀጠነ የሀሰት ክሰ ጋዜጠኞችን ፍርድ ቤት ሲያቆማቸው እሳቸው ባላቸው የህግ እውቀት በነፃ ፍርድ ቤት በመቆም ለንፁሃን ጋዜጠኞች ሸንጣቸውን ገትረው በመከራከራከረቸው ነበር ፣ እኚህ ስው ታዲያ ትንሽ ጠፋ ብለው ከራርመና ሲመለሱ ባንዴ ጎፈር ሆነው ሲያወግዙት የነበረው መንግስት ባለስልጣን በመሆነ ከኔ በላይ ታማኝ የለም ብለው ቁጭ አሉ፣ ያኔ በደጉ ጊዜ ከህሊናቸው ጋር በነበሩ ሰአት ሲሟገቱላቸው የነበሩ በቅርብ የሚያውቋቸውን ንፁሃን ጋዜጠኞችን መሰረተ ልማት ለማውደምና የመንግሰት ባለስልጣናት ለመግደል ከአሸባሪዎች ጋር ሲያሴሩ እጅ ከፍንጅ ያዝናቸው ብለው በአደባባይ ህጉን እያወቁት ከፍርድ ቤት ቀደመው ፍርድ አስተላለፉ፣ እነዚያ ንፁሃን ጋዜጠኞችም ያለጥፋታቸው የእድሜአቸውን እኩሌታ ዘብጥያ እንዲያሳልፉ የፖለቲካ ውሳኔ ተወሰነባቸው እናቃሊቲ ተወረወሩ፣ እኚህ ግለሰብ መንግስት እራሱን አሻሸሎ ነው የተቀላቀሉት እንኩዋን እንዳይባል እርሳቸው ስልጣን ላይ ከመውጣታቸው በፊት የነበረው የጋዜጠኞች የመሰራት ነፃነት አሁን ካለው ዘጠና በመቶ ይሻል ነበር ታዲያ ምን ነካቸው ከተባለ መልሱ ለጥቅም ሲባል ሕሊናቸውን ሸጡ ይሆናል።
ሰው ሕሊናውን በጥቅም ከተያዘ ዕውቀትና ስልጣን መጠሪያው ከመሆን የዘለለ ፋይዳ የለውም ፣ በጣም የሚገርመው እኚህ ሰው መንግስትን በመወከል በተደጋጋሚ የተናገሩዋቸውን ንግግሮች አለቆቻቸው ውድቅ በማድረግ ሸመልስ ያለው ውሸት ነው በማለት በአደባባይ ሲያዋርዱአቸው በፊት ለሎች ሲከራከሩ የነበሩ ሰው እንዳልነበሩ ሁሉ በጥቅም ስንሰለት እግር ተወርቸ ታሰረው እራሳቸውን እንኩዋን መከላከል አቅቷቸው ሲወራጩ በመታዘብ አይተናል።
ባጠቀላይ ህሊና ትንሹ እግዚአብሔር ነው ይባላል መልካም ስንሰራ የሚያበረታታን መጥፎ ሰንሰራ ደገሞ እንድንፀፀተና ዳግም እንዳንሰራ እረፍት የሚነሳን ታድያ ሰው ይህንን ትልቅ ነገር አጥቶ ሀብትና ዝናን ቢሰበሰብ እንዴት የዓይምሮ ሰላም ሊያገኝ ይችላል?
“ሰው እግዚአብሔርን አጥቶ አለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ምን ይጠቅመዋል” እንዳለው መፀሃፍ ቅዱስ፣
ኢትዮጵያን እግዚአብሔር ይጠብቅ!

ከ35 ሚ.ብር በላይ በሙስና አከማችቷል የተባለ የጉምሩክ ኃላፊ ተከሰሰ


የአዳማ ገቢዎችና ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የህግ ማስከበር ሃላፊ የነበረው አቶ ተመስገን ጉላን በራሱና በወንድሙ ስም ከገቢው ጋር የማይመጣጠን ከ35 ሚሊዮን ብር በላይ ጥሬ ገንዘብ እና ንብረት ይዞ በመገኘቱ ክስ የቀረበበት ሲሆን በፖሊስ ክትትል ስር የነበረው ወንድሙም ከትናንት በስቲያ ፍ/ቤት ቀርቦ ክሱ ተነቦለታል፡፡ ቀደም ሲል ተከሳሹ ሁለት ዶዘሮችን በ15ሚ.ብር መግዛቱን ደርሼበታለሁሲል አቃቤህግ መግለጫ መስጠቱ ይታወሣል፡፡ 
የ33 ዓመቱ የህግ ማስከበር ሃላፊ አቶ ተመስጌን ጉላን ዓለሙ፣ በሌላ ስሙ ተመስገን ስዩም አሰፋ፤ ሁለት ክሶች የቀረቡበት ሲሆን በግብረአበርነት በተያዙት የወልደሚካኤል ሃለፎም አጠቃላይ አስመጪና የፈሣሽ ትራንስፖርት ድርጅት ባለቤት አቶ ወ/ሚካአል ሃለፎም፣ የታደለ ብርሃኑ አስመጪና ላኪ ድርጅት ባለቤት አቶ ታደለ ብርሃኑ፣ ስራው ያልተገለፀውና እስካሁን በቁጥጥር ስር ያልዋለው አቶ ብርሃኑ ዝናቡ ሹመይ እንዲሁም የ24 አመቱ የ1ኛ ተከሣሽ ወንድም አቶ ካህሣይ ጉላን ዓለሙ ደግሞ በአንድ መዝገብ ተከሰዋል፡፡ 
በአቶ ተመስጌን ጉላን ላይ በተናጠል የቀረበው 1ኛው ክስ፤ ተከሣሹ በገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን በተለያየ ሃላፊነት ላይ ተመድቦ ከ1999 ዓ.ም እስከ 2004 ዓ.ም ለስድስት ዓመታት ሲሠራ፣ አስቀድሞ በነበረበት የመንግስት ስራ ወይም በሌላ መንገድ ሲያገኘው ከነበረው ህጋዊ ገቢ ጋር የማይመጣጠን፣ በወንድሙ በካህሣይ ጉላን ስም በዳሽን ባንክ ከ13 ሚሊዮን ብር በላይ፤ በራሱ ስም ደግሞ በወጋገን ባንክ ከ7 ሚሊዮን ብር በላይ በማስቀመጥ እና በማንቀሳቀሱ በአጠቃላይ በራሱና በወንድሙ ስም ከ20 ሚሊዮን ብር በላይ ጥሬ ገንዘብ አስቀምጦ በመገኘቱ ተከሷል፡፡ 
ተከሣሹ በጓደኛው ብርሃኑ ዝናቡ ስም ስድስት ቦቴ መኪናዎችን ከነተሳቢያቸው፣ በአቶ ወ/ሚካኤል እና ታደለ ብርሃኑ አማካኝነት ከባንክ 10.5 ሚሊዮን ብር በመበደር ከራሱ 10.5 ሚሊየን ብር በመጨመር በድምሩ በ21 ሚሊዮን ብር ከሰኢድ ያሲን ኃላ.የተ.የግል ማህበር ገዝቶ መኪኖቹን በ2005 ዓ.ም ለተለያዩ ግለሰቦች በመሸጥ፣ በወንድሙ ስም ከቢዩ ኃ/የተ/የግ/ማህ ሁለት ዶዘሮችን በብር 15 ማሊዮን ብር መግዛቱ ተመልክቷል፡፡ በተጨማሪም በወንድሙ ስም በቦሌ ክ/ከተማ 325 ሜ.ካ ቦታ ላይ የተሠራ መኖሪያ ቤት በማፍራቱ እና በ2.8 ሚሊየን ብር በመሸጡም ተከሷል፡፡ 
ቀሪዎቹ ተከሣሾች ደግሞ፣ አቶ ተመስገን ሙስና ፈፅሞ ያገኘው ገንዘብ እና ንብረት መሆኑን እያወቁ መኪኖቹ የሚገዙበትን ሁኔታ ሃሣብ በማፍለቅና በመርዳት፣ የባንክ ብድር እንዲገኝ በማመቻቸት እና በመበደር እንዲሁም በራሱ አስመጪና የትራንስፖርት ድርጅት ስር መኪኖቹ ተጠቃለው እንዲሠሩ በማድረግ አቶ ወ/ሚካኤል ሃለፎም ተጠያቂ ሲሆን አቶ ታደለ ደግሞ በሙስና ወንጀል የተገኘው ገንዘብና ንብረት እንዳይታወቅ ለማድረግ አቶ ብርሃኑ ዝናቡ እና ካህሣይ ጉባል የቀበሌ መታወቂያ እንዲያወጡ በማመቻቸት እና በቀበሌው መታወቂያ መነሻነት የተጠቀሡትን ወንጀሎች እንዲፈፅሙ በማድረጉ  በወንጀሉ በመሣተፉ መከሠሡ ተመልክቷል፡፡ በቁጥጥር ስር ያልዋለው አቶ ብርሃኑ ዝናቡ፤ መኪኖቹ በስሙ እንዲገዙ፣ የባንክ ብድርም በስሙ እንዲበደር በማድረጉ ክስ የቀረበበት ሲሆን ወጣት ካህሣይ ደግሞ ለወንድሙ ውክልና ሠጥቶ በስሙ ገንዘብ እንዲያስቀምጥና እንዲያንቀሣቅስ እንዲሁም መኖሪያ ቤት እንዲገዛ በማድረጉ ተከሷል፡፡ 
ቀደም ብሎ በነበሩት ሁለት ቀጠሮዎች አቶ ተመስገን፣ አቶ ወ/ሚካኤል እና አቶ ታደሰ፤ ክሡ ተነቦላቸው መቃወሚያቸውን አቅርበው፣ አቃቤ ህግም ለመቃወሚያው መልስ የሠጠ ሲሆን ካህሣይ ጉላል ለመጀመሪያ ጊዜ ከትናንት በስቲያ ቀርቦ ክሡ ከተነበበለት በኋላ፣ ፍ/ቤቱ ጉዳዩን ከሌሎች ተከሳሾች ጋር አብሮ እያየው ነው፡፡ 
አቃቤ ህግ በተከሣሾቹ ላይ 14 የሠውና 14 የሠነድ ማስረጃዎችን ከክሡ ጋር አያይዞ አቅርቧል፡፡ 
ከትናንት በስቲያ የዋለው የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት 15ኛው ችሎት፤ በመዝገቡ ላይ የተለያዩ ትዕዛዞችን ያስተላለፈ ሲሆን በእለቱ የቀረበው 5ኛ ተከሣሽ፤ የዋስትና መብቱ ተከልክሎ በቀጣይ ቀጠሮ ከጠበቃ ጋር እንዲቀርብ ትዕዛዝ በመስጠት፣ መዝገቡን ለጥር 6 ቀን 2006 ዓ.ም ቀጥሯል፡፡ -

Thursday, December 19, 2013

ከወያኔ ክፋትና እብሪት እንጂ ፍትህ አይጠበቅም

December 19/2013

ወያኔ ባለፉት ሃያ ሁለት አመታት የአገራችንን የፍትህ ተቋሞች አንዴ አንደ ቂም መበቀያ ሌላ ግዜ ደግሞ እንደ ማጥቂያ መሳሪያ እየተጠቀመባቸዉ የፖለቲካ ተቀናቃኞቹንና ጥርስ የነከሰባቸዉን የህብረተሰብ አባላት እያሰረ፤ እያሳደደና እየገደለ ከርሞ ዛሬ ላይ ደርሷል። በተለይ ከግንቦት 1997ቱ ምርጫ በኋላ ወያኔ ብዕርና ወረቀት ይዘዉ በሃሳብና በአመክኖ የታገሉትን ሰላማዊ ዜጎች “ሽብርተኞች”፤ ድምጻችን ይሰማ ብለዉ የመብትና የነጻነት ጥያቄ አንግበዉ በሰላማዊ መንገድ የታገሉትን ኢትዮጵያዉያን የእስልምና እምነት ተከታዮች ደግሞ “አክራሪዎች” እያለ ፍርድ ቤት በማቅረብ በፍትህ ተቋሞች በኩል የፖለቲካ ዉሳኔ በማሳለፍ ሠላማዊ ዜጎችን ለረጂም ግዜ እስርና እንግልት ዳርጓል።
ወያኔ ለኢትዮጵያና ለዜጎቿ ደንታ የሌለዉ እና ከስህተቱ የማይማር የግብዞችና የዘረኞች ስብስብ ስለሆነ አሁንም የአገሪቱን የፍትህ ተቋሞች እንደ ማጥቂያ መሳሪያ እየተጠቀመ የኢትዮጵያን ህዝብ በፍርሃት ጨለማ ዉስጥ ሸብቦ እየገዛ ለመኖር የቆረጠ ይመስላል። ባለፈዉ ሳምንት አጋማሽ ላይ የወያኔ አገዛዝ ከአንድ አመት ተኩል በላይ እስር ቤት ዉስጥ አጉሮ ያቆያቸዉን የድምጻችን ይሰማ መሪዎች ከፊሎቹን በነፃ ተለቅቀዋል የሚል ከፊሎቹን ደግሞ ተከላከሉ የሚል ትርጉም የለሽ ብይን ሰጥቷል። በህወሀት ታጋዮች የተሞላዉ ፍርደ ገምድሉ የወያኔ ፍርድ ቤት እንኳን ተከሳሾቹ በተከሰሱበት ሽብር የመፈጸም ወንጀል ምንም አይነት ማስረጃ አልተገኘባቸዉም ሲል አገዛዙ ግን የፖለቲካ ክንዱን በመጠቀም ማስረጃ ያልተገኘባቸዉን ሠላማዊ ዜጎች የተከሰሱበትን መሰረተ ቢስ ክስ ተከላከሉ የሚል የፖለቲካ ዉሳኔ ሰጥቷል።
የወያኔ አገዛዝ የሙስሊሙን ህብረተሰብ የመፍትሄ አፈላላጊ ቡድን መሪዎች ፍርድ ቤት ያቀረባቸዉ ለምዕራባዉያን ለጋሾቹና ለአለም አቀፍ አበዳሪ ድርጅቶች ኢትዮጵያ ዉስጥ ፍትህ ያለ ለማስመሰል ነዉ እንጂ ወያኔ የድምጻችን ይሰማ መሪዎችን የፈረደባቸዉ ያሰራቸዉ ቀን ነዉ። የወያኔ የፍትህ ታሪክ በግልጽ እንደሚያሳየን ወያኔ ግለሰቦችን የሚያስረዉ ለክስ የሚያበቃ ማስረጃ አግኝቶባቸዉ አይደለም፤ ይልቁንም ወያኔ ማስረጃዎችን እየፈበረከ ለፍረድ ቤቶች የሚያቀርበዉ ግለሰቦችን ካሰረና ሰብዓዊ መብታቸዉን ከገፈፈ በኋላ ነዉ። ለምሳሌ የድምጻችን ይሰማ መሪዎችን አስሮ ብዙም ሳይቆይ የእነዚህን ሰላማዊ ዜጎች ተክለ ሰዉነት ጥላሸት የቀባና ግለሰቦቹን ያለ ማስረጃ ወንጀለኛ አድርጎ የፈረጀዉን “ጂሐዳዊ ሀረካት” የሚል የፈጠራ ድራማ ሰርቶ ለህዝብ አቅርቧል።
የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሽብር በመፈጸም ወንጀል ተጠርጥረዉ የቀረቡለትን ግለሰቦች በተከሰሱበት ወንጀል ማስረጃ አላገኘሁባቸዉም ካለ በኋላ ሁሉንም በነጻ አለማሰናበቱ የሚያሳየን የወያኔ ፍርድ ቤቶች ከፖለቲካ ተፅዕኖ ነጻ አለመሆናቸዉን ብቻ ሳይሆን፤ ኢትዮጵያ ዉስጥ ፍርድ ቤቶች የገዢዉ ፓርቲ የማጥቂያ መሳሪያዎች መሆናቸዉን ጭምር ነዉ። የወያኔን አገዛዝ ከሌሎች አምባገነኖች ለይቶ አደገኛ የሚያደርገዉና በምዕራባዉያን መንግስታትና በቀላጤዎቻቸዉ እንዲወደስ ያደረገዉም ይሄዉ አገዛዙ የሚቃወሙትን ኃይሎች የሚያጠፋቸዉ እንደሌሎቹ አምባገነኖች በግልጽ ሳይሆን በህግ ሽፋን ዉስጥ በስዉር መሆኑ ነዉ።
የወያኔዉ ፍርድ ቤት በተመሳሳይ ወንጀል ተከስሰዉ የቀረቡለትን ነገር ግን ምንም መረጃ ያላገኘባቸዉን የድምጻችን ይሰማ መሪዎች ገሚሶቹን በነፃ ለቅቆ የተቀሩትን ጥፋተኛ አለመሆናችሁን አረጋግጡ ብሎ መወሰኑ የወያኔን ሁለት እኩይ አላማዎች ያሳየናል። የመጀመሪያዉ የወያኔ አላማ በአላማቸዉ ጸንተዉ የቆሙትን የድምጻችን ይሰማ መሪዎች መከፋፈል ሲሆን፤ ሁለተኛ አላማዉ ደግሞ የኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች የቀረቡላቸዉን የክስ መዝገቦች በሚገባ አጣርተዉ ዉሳኔ የሚሰጡ መሆናቸዉን ለአለም አቀፉ ህብረተሰብ ለማሳየት ነዉ።
የኢትዮጵያ ህዝብ ግን እንደዚህ አይነቶቹን የወያኔ እኩይ ተግባሮች ካወቀ ዉሎ አድሯል፤ ስለሆነም ከወያኔ ፍትህ ጠብቆ አያዉቅም፤ ወያኔ የክፋትና የበቀል ምንጭ ነዉና ለደፊትም አይጠብቅም። የድምጻችን ይሰማ መሪዎችም ሆኑ ከእነሱ በፊት በግፍ ታስረዉ መከራቸዉን የሚያዩት የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች፤ ጋዜጠኞችና የሲቪክ ማህበራት መሪዎች የታሰሩት ለቆሙለት የፍትህ፤ የነጻነትና የእኩልነት አላማ እንደ አለት ጸንተዉ በመቆማቸዉ ነዉ። እነዚህ ጀግኖች የታሰሩለት አላማ የሁላችንም አላማ ነዉና ፍትህ፤ እኩልነትና ነጻነት የጠማን ኢትዮጵያዉያን ክንዳችንን አስተባብረን የችግሮቻችን ሁሉ ምንጭ በሆነዉ በወያኔ ስርዐት ላይ ክንዳችንን በጋራ እናንሳ!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!

የአማራ ክልል ፕሬዝዳት አቶ አያሌው ጎበዜ ስልጣናቸውን በፍቃዳቸው ለቀቁ::

mmm
imagesየአማራው ክልል ፕሬዚዳት ስልጣናቸውን በገዛ ፍቃዳቸው በመልቀቅ ስራቸውን ያቆሙ ሲሆን በምትካቸው ምክትላቸው አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የተተኩ መሆኑ ታውቋል:: በቅርቡ ኢሕኣዴግ ከሱዳን ጋር የተፈራረመውን የድንበር ማካለል ተግባራቶች በመኮነን የተቃወሙት አቶ አያለው ከዚህ ቀደምም ይህንን የድንበር ጉዳይ በተመለከተ አልፈርምም ብለው ምክትላቸው የነበረው ደመቀ መኮንን ፈርሞ ለታማኝነቱ ከፍተኛ የስልጣን እርከት ላይ እንደወጣ ይታወቃል:: ይህ በድርጅቱ ውስጥ የመተካካት ጉዳይ ሳይሆን አቶ አያሌው በገዛ ፍቃዳቸው ስልጣናቸውን የለቀቁ መሆኑ ታውቋል:: አቶ አያሌው ጎበዜ ኢሕኣዴግን የተቀላቀሉት ከደርግ ውድቀት በኋላ ሲሆን በአቋማቸው ጽኑ እና ለአላማቸው ወደኋላ የማይሉ ጠንካራ ሰው እንደሆኑ ይወራላቸዋል:: የኢሕኣዴግ ታማኞች ሊያሰሯቸው እንዳልቻሉ በተደጋጋሚ ሙከራቸው ያልተሳካ እና ሰሚ አካል ያላገኙ የነበረ ሲሆን ከዚህ ቀደም ጄኔራል ዮሃንስ ገብረመስቀል በግል ጸብ የበላይነትን ተጠቅመው በላንቻ መኖሪያ ቤታቸው የግል እስረኛ አድርገዋቸው እንደነበር አይዘነጋም:: አቶ አያሌው ስልጣን ይልቀቁ እንጂ ድርጅታቸውን ያለቀቁ እና ወደፊትም በአምባሳደርነት እንደሚመዱ ውስጥ አዋቂ ምንጮች ጠቁመዋል:

Tuesday, December 17, 2013

“ሕወሓት ከመለስ ሞት በኋላ እየተዳከመ ያለ ድርጅት ነው፤ ኢህአዴግ ለዘለዓለም መግዛት አለብኝ የሚል ድርጅት ነው” ወ/ሮ አረጋሽ አዳነ


ወ/ሮ አረጋሽ አዳነ ከህወሓት ጋር 17 ዓመታት በትግል ያሣለፉ እና ከፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች መካከል አንዷ ነበሩ፡፡ በ1993 ዓ.ም ከፓርቲው ከተሰናበቱ አባላት አንደ ናቸው፡፡ በአሁኑ ወቅት የ“አረና” ፓርቲ አባል የሆኑት ወ/ሮ አረጋሽ በአጠቃላይ ጉዳዮች ዙሪያ ከ“ሎሚ” አዘጋጅ ቶማስ አያሌው ጋር ያደረጉት ቆይታ የመጀመሪያ ክፍል እንደሚከተለው ቀርቧል፡-

ሎሚ፡- የኢህአዴግ ጭቆናና፣ አፈና፣ የተንሰራፈው በመላው ሀገሪቱ ነው የሚል አቋም ካላችሁ፣ ብሔር ተኮር ፓርቲ የመሰረታችሁበት ምክንያት ምንድነው;
አረጋሽ፡- ፓርቲ የሚመሰረተው በአካባቢ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ መሰረት አድርጐ ነው፡፡ ተጨባጭ ሁኔታ ስል የማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ሰብዓዊ መብት፣ የኢኮኖሚ ችግሮችን ለመጥቀስ ፈልጌ ነው፡፡ ማንኛውም ድርጅት በዚህ መልኩ ነው የሚመሰረተው፡፡ አረናም በዚሁ መሠረት የተመሠረተ ፓርቲ ነው፡፡
ከሕወሐት ክፍፍል በኋላ አረና ሲደራጅ፣ ለአገራችን የታገልንለት ዓላማ ሙሉ በሙሉ ስላልተሣካ፣ ያልተሣካው እንዲስተካከል አለያም የተሻለ ለማድረግ የራሣችንን ጫና ማሣደር አለብን ብለን ነው አቋም የያዝነው፡፡ ስንደራጅ ሀገራዊ ፓርቲ የመመስረት ዓላማም ፍላጐትም ነበረን፡፡ ነገር ግን በነበርንበት ሁኔታ አገራዊ ድርጅት መመስረት ቀላል አልነበረም፡፡ ጠንካራ ርዕዮተ ዓለም፣ በጣም ወሣኝ አባላት ያሉት አገራዊ ድርጅት መመስረት አሁንም ቢሆን አስቸጋሪ ነው፡፡ ሀገራዊ ድርጅት የመመስረት ፍላጐት ቢኖረንም የነበርንበት ተጨባጭ ሁኔታ አልፈቀደልንም፡፡ በተግባር ስንመለከተው የብሔረሰቦች መብት ሙሉ ለሙሉ ባይከበሩም፣ ሀገራዊ ፓርቲ ለመመስረት ሁኔታዎች እስኪፈቅዱልን ድረስ ብለን አረናን መሰረትን፡፡
ይህን ካደረግን በኋላ አረናን ይዘን ቁጭ አላልንም፡፡ ሀገራዊ ፓርቲ ካልተመሠረተ የትግራይም ይሁን የሌላው ብሔር ብሔረሰቦች ችግር ይፈታል ብለን አናምንም፡፡ ሀገራዊ ፓርቲ የሚመሠረትበትን ሁኔታ መፍጠር አለብን ብለን ከሌሎቹ ኢትዮጵያ ውስጥ ህጋዊ እውቅና ካላቸውና በሰላማዊ መንገድ ከሚታገሉ ፓርቲዎች ጋር በአጭር ጊዜ ውይይት ጀመርን፡፡ መድረክ በሚባለው ድርጅትም የገባነው በዚሁ ምክንያት ነው፡፡
ሎሚ፡- ከክፍፍሉ በኋላ ተዘጋጅቶ የነበረው “ሕዝባዊ” የተባለ ጋዜጣ በምርጫ 97 በጋዜጣው ርዕሰ አንቀፅ ከገዢው ፓርቲ ይልቅ ቅንጅት ላይ ጠንካራ ትችት ታቀርቡ ነበር ይባላል፤ እንዲያ ተደርጎ ከሆነ ትኩረታችሁን ወደ ተቃዋሚ ፓርቲ ያነጣጠራችሁበት ምክንያቱ ምንነበር;
አረጋሽ፡- ከኢህአዴግ ይልቅ ወደ ቅንጅት ያተኮረ ነበር የሚለው አስተያየት ለኔ ትክክል አይመስለኝም፡፡ ጋዜጣውን በትክክል አንብቦ ተረድቶ የተሰጠ አስተያየት አይመስለኝም፡፡ ያኔ ኢህአዴግን ነበር የምንታገለው፡፡ ከዴሞክራሲ አንፃር፣ ከህግ ልዕልና አንፃር፣ ከመናገርና መደራጀት አንፃር፣ ከፕሬስ ነፃነት አንፃር… እነዚህን እና ሌሎች ተጨባጭ ሁኔታዎችን መነሻ እያደረግን በጋዜጣችን ጠንከር ጠንከር ያሉ አስተያየቶችን እንሰጥ ነበር፡፡ የ97 እንቅስቃሴ ሲመጣም ኢህአዴግ “ዴሞክራሲያዊ፣ ግልፅ እና ነፃ ምርጫ ይመጣል” ብሎ ከጀመረ በኋላ ኃይሉ ሲዛባበት፣ ስልጣኑ እየተንገዳገደ መሆኑን ሲረዳ ቀድሞ የገባውን ቃል ማጠፍ ጀመረ፡፡ እንዲያውም የመሸነፍ አዝማሚያ ሲያይ ባልተጠበቀ ሁኔታ ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ በቴሌቪዥን በመቅረብ “ኢህአዴግ አሸንፏል” ነበር ያለው፡፡ ይህ ብቻም አይደለም፤ ፀረ-ዴሞክራሲ የሆኑ አዋጆችን አውጇል፡፡
ከዚህ በመነሣት ተገቢ አለመሆኑን በሚመለከት በርካታ ነገሮች ፅፈናል፡፡ “ይሄ የዴሞክራሲውን አካሄድ ማጥበብ እንደሆነ፣ ገና ቆጠራው ሣይጠናቀቅ እኛ አሸንፈናል ብሎ መናገር ኢ-ዴሞክራሲያዊ እና አምባገነናዊነት እንደሆነ፣ ተቃዋሚዎቹም ቢሆኑ በህጉና በአግባቡ መያዝ እንዳለባቸው፣ የሕዝብ ድምፅ በአግባቡ ሊቆጠርና ተግባራዊ ሊሆን እንደሚገባው፣ መሸነፉን አምኖ ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ መቀበል እንዳለበት በሚመለከት ደጋግመን ፅፈናል፡፡ ከዚህ አንፃር ካየነው ቅንጅትን የሚያጠቃ አቋም ነበራችሁ የሚለው አስተያየት አሳማኝ አይደለም፡፡ ቅንጅት ላይ ጫና ወይም ትኩረት ማድረግ ሳይሆን፣ ቅንጅቶች ምን ማድረግ እንዳለባቸው የጠቆምንበት ሁኔታ ነበር፡፡
ሎሚ፡- ፓርቲያችሁ አረና በ2006 ዓ.ም. ምን ዓይነት እንቅስቃሴ እያደረገ ነው;
አረጋሽ፡- አረና ጳጉሜ ውስጥ ሦስተኛ ጉባዔውን አካሂዷል፡፡ አንዳንድ ሕገ ደንቦቹን አስተካክሏል፤ የሚሻሻሉ ነገሮችን አሻሽሏል፡፡ አዳዲስ አመራሮችን መርጧል፤ ለምሣሌ የቀድሞው የፓርቲው ሊቀ-መንበር በአዲስ እንዲተኩ አድርገናል፡፡ ወጣቶችን ወደ አመራር አምጥተናል፡፡ ለውጥና የማሸጋሸግ ስራ ተሰርቷል፡፡ ወጣቱ ወደ ፖለቲካው መድረክ ቢመጣ የትግል ሂደቱን እየተላመደና እየተማረበት ይሔዳል በሚል ነው፡፡ እኛ የወደፊት መሪዎች አይደለንም፤ የወደፊት መሪዎቹ ወጣቶቹ ናቸው፡፡ ይህ ብቻም አይደለም፤ የዕቅድ አቅጣጫዎችም ተቀምጠዋል፡፡ በተቻለ መጠን በአጭር ጊዜ ውስጥ ሀገራዊ ፓርቲ እንዲፈጠር የማድረግ ስራው ተጠናክሮ እንዲቀጥል እያደረግንም ነው፡፡ በእውነቱ ይህ በእኛ ፍላጐት ብቻ የሚወሰን አይደለም፡፡ የሌሎቹም ፍላጐት ያስፈልጋል፡፡
እንዲሁም ሀገሪቱ የወጣት ምሁራን የተሻለ አመራር እንድታገኝ የማድረግ ኃላፊነት አለብን የሚሉ ግለሰቦችን የማሰባሰብ አቅም ያስፈልጋል፡፡ እኛ ይህ ሁኔታ እንዲፈጠርና እንዲመቻች ካሉት ፓርቲዎች ጋር በፕሮግራሞቻችን ተስማምተን ሀገራዊ ፓርቲ እንዲመሠረት እንቅስቃሴ እያደረግን ነው፡፡ ለዚህ ጉዳይ ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራ ንዑስ ኮሚቴ ከኛም ከሌሎችም ድርጅቶች ተውጣጥቶ እየተንቀሣቀሰ ነው፡፡ የአረና ጉባኤ አንደኛው ማጠንጠኛም ይሔ ነው፡፡ ሌላው የጉባኤው አጀንዳ ፓርቲው በተጠናከረ መልኩ ከሕዝቡ ጋር መገናኘት፣ እስከ ገጠር የዘለቀ እንቅስቃሴ ማድረግ እንዳለብን የሚያሳስብ ነው፡፡ ይሁንና እነዚህን ነገሮች እንዳናደርግ የሚያግዱን ችግሮች አሉ፡፡ አንዱ የገንዘብ አቅም ነው፡፡ ህዝቡ ከስጋትና ከፍራቻ አልወጣም፡፡ ቢሆንም ባለን አቅምና ችሎታ በትናንሽ ከተማዎች ስብሰባ በማድረግ እንቅስቃሴያችንን ጀምረናል፡፡ እንዲሁም ከመድረክ ጋር በመሆን በናዝሬት፣ ሀዋሳ፣ መቀሌ ከተማዎች ሕዝባዊ ስብሰባ ለመጥራት በመንቀሳቀስ ላይ እንገኛለን፡፡
ሎሚ- ፓርቲያችሁ ባደረገው ጉባኤ ማጠናቀቂያ ላይ ባወጣው መግለጫ “ውህድ ፓርቲ” እንደሚያስፈልግ ደጋግሞ ገልጿል፡፡ ወደዚህ አቋም የመጣችሁበትን አቋም ቢያብራሩልን;
አረጋሽ፡- ቀደም ብዬ እንደገለፅኩት ሀገራዊ ድርጅት ቁልፍ ሚና አለው፡፡ በተበታተነ መንገድ በክልሎች ብቻ ተደራጅቶ ለውጥ ማምጣት ከባድ ነው፡፡ ስለዚህ ያሉት ችግሮች ሀገራዊ መፍትሔ ካልተቀመጠላቸው በስተቀር በክልል ደረጃ ብቻ በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች የምንፈልገውን ለውጥ አናመጣም፡፡ ጠንካራ አመራር ያስፈልጋል፡፡ ሀገር የሚቀይር ኃይል ያስፈልጋል፡፡ ሀገር እንዲቀየር ከተፈለገ ሀገራዊ ፓርቲ መኖር አለበት፡፡ ይሕም ማለት ውህደት መፍጠር ማለቴ ነው፡፡ ውህደት ሲኖር ነው በሀገርም ሆነ በክልል ደረጃ ያለውን ችግር አብሮ መፍታት የሚቻለው፡፡ በግንባር ደረጃ ብቻ አብሮ መታገል መንግስትን ላይፈትነው ይችላል፡፡ ተገቢውን ጫና አሳድሮ መንግስት ነፃና ግልፅ የሆነ ምርጫ እንዲያደርግ ሊያስገድደው አይችልም፡፡ ስለዚህ ሀገራዊ ፓርቲ ተፈጥሮ፣ ሀገራዊ አመራር ካልተመሠረተ ለየብቻ በሚደረግ ትግል የሚመጣ ለውጥ የትም አያደርስም በሚል ነው ለውህደት የተነሳነው፡፡
ሎሚ፡- የህወሓት መመስረቻና መቀመጫ በሆነው ትግራይ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በርካታ ወጣቶች በማህበራዊ ድረ ገፆችና በሌሎች ሚዲያዎችም በገዢው ፓርቲ ላይ ተቃውሟቸውን እየገለፁ ነው፡፡ ይሔ ምንን ተከትሎ የመጣ ይመስልዎታል;… በአንፃሩ የሴቶች እንቅስቃሴ የማይንፀባረቀውስ ለምንድን ነው;
አረጋሽ፡- የዚህ ዓይነቱ ሁኔታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተጠናከረ እየሄደ ነው፡፡ መሠረታዊ መነሻውም ትግራይ ውስጥ ያለው ኢ-ፍትሃዊ ስርዓት አካሄድ ነው ብዬ ነው የማምነው፡፡ ያ ሁኔታ በወጣቱ ላይ ተንፀባርቋል፡፡ ሕዝቡ ደጋግሞ የታገለ ሕዝብ ነው፡፡ ብዙ መስዋዕትነት የከፈለ ሕዝብ ነው፡፡ መስዋዕትነት የከፈለው ደግሞ የዲሞክራሲ፣ የኑሮ፣ የኢኮኖሚ ለውጥ እንዲመጣ ነው፡፡ ሕዝቡ ከዚህ በኋላ የምንበደልበት ስርዓት አይኖርም ብሎ ነው ሦስትና አራት ልጆቹን ከአንድ ቤት ልኮ ያታገለው፡፡ ያንን እምነት ይዞ የታገለ ሕዝብ፣ መልሶ ለዚህ ዓላማ ነው የታገልኩት የሚለው ድርጅት (ህወሓት) ሲጨቁነው ምሬት ሊሰማው የማይችልበት ምክንያት የለም፡፡
አስተዳደሩ ሕዝቡን ከሌሎች ክልሎች በበለጠ ተቆጣጥሮና ወጥሮ ይዞታል፡፡ በትግራይ ውስጥ ሁሉንም ሕዝብ በወጣት፣ በሴቶች፣ በተለያዩ ማህበሮች አደራጅቶ ከህወሓት ትዕዛዝ ውጭ እንዳይመራ እየተደረገ ነው፡፡ የወገንተኝነት፣ የዝምድና ሥራ፣ የሙስናም ጉዳይ አለ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ችግሬ እየተሰማ አይደለም የሚል ስሜትም አለ፡፡ ይህንን መሠል እሮሮዎች እየወጡ ነው፡፡ በተለይ ደግሞ የተማረው ክፍል በተወሰነ መልኩም ቢሆን የነፃነት ስሜት ስላለው ያንን ማስተጋባት ጀምሯል፡፡ ተቃውሞው ከዚህ የመነጨ ይመስለኛል፡፡ ሌላኛው የሕወሓት ሥጋት ተጨማሪ ኃይል እየፈጠረ ያለው የአረና እንቅስቃሴ ነው፡፡ የአረና እንቅስቃሴ ወጣቶችን እያደራጀ ነው፤ ወጣቶችን ወደ አመራርነት እያመጣ ነው፡፡ ዓላማውን እየገለፁ ነው፤ ትግራይ ውስጥ ያለውን ችግር አብሮ እየተወያየበትና እየመከረበት ነው፡፡ ይሔ ደግሞ የበለጠ እንዲነቃቃ አድርጐታል፡፡ በተለይ እኛ የቀድሞ የህወሓት አባላት ለሕዝብ ችግር መታገል አለብን ብለን መንቀሳቀሳችን ትልቅ ራስ ምታት ሆኖባቸዋል፡፡ የዚህ ሁሉ ድምር፣ የሕዝቡ ምሬት፣ የእኛ እንቅስቃሴ ተዳምሮ ወጣቱን እንዲነሳሳ እያደረገው ነው፡፡
የሴቶች ተሳትፎን በሚመለከት… አረና ከተመሰረተ ገና አምስት ዓመቱ ነው፡፡ እንቅስቃሴያችን ደግሞ ውሱን ነበር፡፡ ሴቶችን ማግኘት አስቸጋሪ ነው፡፡ በማህበር ተደራጅተዋል፤ ዩኒቨርስቲ ውስጥ ሳይቀር በሊግ (በአንድ ለአምስት) ተጠርንፈዋል፡፡ ይሕም ሆኖ የአረና አባላት የሆኑ ሴቶች አሉ፡፡ በአመራር ደረጃም የተወሰኑ አሉ፡፡ ፖለቲካዊና ዲፕሎማሲያዊ እንቅስቃሴያችን እየጠነከረ ሲሄድ ሴቶቹ የመምጣታቸው ነገር ይጨምራል የሚል እምነት አለኝ፡፡ ኢህአዴግ ዋነኛ ኃይሎቹ ሴቶች ናቸው ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ በልማት፣ በማህበር አደራጅቶ እንዲንቀሣቀሱ ያደረገው ሴቶችን ነው፡፡ ይህም ጥቅም ፈጥሮለታል፡፡ እኛ ይህን አዝማሚያ መስበር አለብን፡፡ ግን በሂደት ለውጦች ተፈጥረው የሴቶች እንቅስቃሴም እየጐላ መምጣቱ አይቀርም፡፡
ሎሚ፡- በኢትዮጵያ ፖለቲካ የሴቶች እንቅስቃሴ በማይታይበት ሁኔታ እንደ ብርቱካን ሚደቅሳና፣ ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ ያሉ ሴቶች እስከ መታሰር የሚከፍሉትን መስዕዋትነት እንዴት ይመለከቱታል;
አረጋሽ፡- የእነሱ ወደ እስር ቤት መሄድ በተናጠል የሚታይ ነገር አይደለም፡፡ የኢህአዴግ መንግስት ስልጣኑን በሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ መንገድ መልቀቅ የማይፈልግ ድርጅት ስለሆነ፣ ለይስሙላ ዴሞክራሲ አለ፣ ነጻ ምርጫ እናደርጋለን እያለ በሚዲያ ቢያስተጋባም በተግባር ግን ዜሮ ነው፡፡ በሕዝብ ድምፅ ተሸንፎ ሥልጣኑን ለማስረከብ የተዘጋጀ ድርጅት አይደለም፡፡ ከስልጣን የመውረድ ስጋትና ፍራቻ ስላለው፣ ዴሞክራቲክ የሆኑ እንቅስቃሴዎችን አይፈልግም፡፡ ኃይል ያለው ሀሳብን፣ ኃይል ያለው ፅሁፍን ይፈራል፡፡
የሕዝብ ተቀባይነት ያላቸው ድርጅቶች… እንዲጠናከሩ፣ እንዲያብቡ ወደ መድረክ እንዲመጡ አይፈልግም፡፡ ብዙኃኑን ሕዝብ ያንቀሳቅሳሉ ያላቸውን ሰዎች በአጭር ጊዜም ይሁን በረጅም ጊዜ ለይቶ ያዳክማቸዋል፡፡ ምክንያቱም ሀሣባቸው ወይም የሚያነሱት ጥያቄ የራሣቸው “የግል” አይደለም ብሎ ስለሚያስብና ሕዝብ ጋ ከደረሰ ችግር ይፈጥራል ብሎ ስለሚሰጋ በአጭሩ የመቅጨት ስራ ይሰራል፡፡
የብርቱካንም ይሁን የርዕዮት እንዲሁም የሌሎች የፖለቲካ ታሳሪዎች ሁኔታ ከኢህአዴግ ስጋት የመነጨ ነው፡፡ ምንም ዓይነት ሀሣብ እንዲስተጋባና እንዲሰማ አይፈልግም፡፡ አዲስ ሀሣብ ሕዝቡ ጋር ደርሶ ኃይል እንዲፈጥር አይፈልግም፡፡ በሽብር እና በሌሎች ምክንያቶች በማሳበብ ሊወጡበት የማይችሉበት ቦታ ውስጥ ያስገባቸዋል፡፡ ይህ ብቻም አይደለም፤ ከማሰር ጐን ለጐን የማሳቀቅና ከመንገዳቸው የማስወጣት ሥራዎችም ይሰራል፡፡ በአጠቃላይ በብዙ መንገድ ይኮረኩማል፡፡ ኢህአዴግ ነፃና ግልፅ የሆነ ምርጫ አካሂዶ ሲሸነፍ ሊወርድ፣ ካልተሸነፈ ሊቆይ የተዘጋጀ ፓርቲ አይደለም፡፡ ለዘላለም እኔ ነኝ መግዛት ያለብኝ ብሎ የሚያምን ድርጅት ነው፡፡ ይሔንን አስተሳሰቡን የሚፃረረውን ድርጅትም ይሁን ግለሰብ ማጥፋት የለመደ ፓርቲ ስለሆነ የሚወስዳቸው እርምጃዎች ከዚህ ጋር የተያያዙ ናቸው፡፡
ሎሚ፡- ህወሓት “የአዲስ አበባ እና የመቀሌ” በሚል ቡድን ለሁለት መከፈሉ ይነገራል፤ የኢህአዴግ “አስኳል” ነው የሚባለው ህወሓት ውስጥ መከፋፈል መከሰቱ የሚፈጥረው አሉታዊም ሆነ አዎንታዊ ውጤት ይኖራል;
አረጋሽ፡- በህወሓት ውስጥ ክፍፍል አለ፤ ለሁለት ተከፍሏል የሚባለውን ነገር ላውቀው አልቻልኩም፡፡ ክፍፍል አለ ብዬ ለመውሰድ ትክክለኛ መረጃ የለኝም፡፡ “ተከፋፍለዋል” የሚል እምነት የለኝም፤ አንድ ናቸው፡፡ በአሁኑ ጊዜ እንኳን ተከፋፍለው አንድ ሆነውም ለመዝለቅ የማይችሉበት ሁኔታ ላይ ናቸው የሚለው ጥያቄ ቢነሣ ነው የሚሻለው፡፡
በአጠቃላይ ሕወሓት ከመለስ ሞት በኋላ እየተዳከመ ያለ ድርጅት ነው፡፡ ሁልጊዜም ደጋግመው “የጠ/ሚ መለስን ራዕይ እናስተገብራለን” ነው የሚሉት፡፡ ራዕይ ለተወሰነ ጊዜ ትቶላቸው ሊሆን ይችላል፡፡ ሁኔታዎች ግን በየጊዜው ነው የሚቀያየሩት፡፡ ከሁኔታውና ከጊዜው ጋር የሚሄድ “ራዕይ” ካልያዙ የያዙት እምነት የሚገድላቸው ይመስለኛል፡፡ አዳዲስ ሀሣቦችን፣ አዳዲስ አቅጣጫዎችን ከነባራዊው ሁኔታ ጋር እያስተሳሰሩ መሔድ ካልቻሉ ለውጥ ሊመጣ አይችልም፡፡ ሕዝብ የሚጠይቃቸውን ጥያቄዎች ግምት ውስጥ የሚያስገባ ራዕይ ሊኖራቸው ይገባል፡፡ ሕዝቡ ተበደልን ሲል፣ ዴሞክራሲ የለም ሲል የህግ ልዕልና የለም ሲል፣ ፍትህ የለም ሲል፣ ጉቦና ወገንተኝነት እየተስፋፋ ነው ሲል፣ መፍትሄ አምጡልን ሲል፣ “ሀገሪቱ በእድገት ላይ ነች፤ አንዳንድ ችግሮች ብቻ ነው፤ እነሱንም በሂደት እንፈታቸዋለን” የሚል ምላሽ እየሰጡ መዝለቅ አይችሉም፡፡ ተከፋፍለዋል የሚለው ግን እኔ የተከፋፈሉበትን ሁኔታ ስላላየሁ ስለሱ አስተያየት ለመስጠት ይከብደኛል፡፡
ሎሚ፡- የትግራይ ሕዝብና የህወሓት ግንኙነትስ ምን ይመስላል;
አረጋሽ፡- ህወሓት ከትግራይ ሕዝብ ጋር የተሳሰረ ታሪክ አለው፡፡ 17 ዓመት ሙሉ ሕዝቡ ታግሏል፡፡ አመራሩ ተለወጠ እንጂ አሁንም ሕዝቡ የችግሩ ገፈት ቀማሽ ነው፡፡ ያንን ሁሉ ትግል ያደረገው ደግሞ ደህና ስርዓት ይመጣል ብሎ ነው፡፡ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር አብሮ በመኖር ፍትሃዊ፣ ዴሞክራሲያዊ የሆነ ስርአት ይመጣል ብሎ ነው መስዕዋትነት የከፈለው፡፡ ከጊዜ ወደ ጊዜ ደግሞ ህወሓት ይሔንን እንዳይቀጥል እያጠፋ፣ ኢ-ዴሞክራሲያዊ፣ ኢ-ፍትሃዊ እየሆነ፣ አፋኝ እየሆነ ነው ያለው፡፡ ከዚህ አንፃር የትግራይ ሕዝብ በህወሓት ላይ እየተማረረ ነው፡፡ መፍትሄ ስጡን እያለ ነው፡፡ ስብሰባ በተደረገ ቁጥር ችግሩን በስፋት ይገልፃል፡፡ እንዲሰሙትም እየጠየቀ ነው፡፡ ይሁንና ተደጋግሞ ጥያቄ ቢያቀርብም መፍትሄ ግን አላገኘም፡፡ በዚህ ምክንያት ቅሬታ እየተፈጠረ ነው፡፡ ጠንካራ የሆነ ድርጅት ከተፈጠረ የትግራይ ሕዝብ አብሮ ከመታገል ወደኋላ አይልም፡፡ አሁን ግን የእኛ አቅም ነው የሚወስነው፡፡ ሀገራዊ በምንለውና ይፈጠራል በምንለው ፓርቲ ዙሪያ የሚወሰን ነው፡፡ ለትግልም ሆነ ለመብቱ በሰላማዊ መንገድ በዴሞክራሲያዊ መንገድ ለመታገል የትግራይ ሕዝብ ዝግጁ ነው፡፡ እኛ ጋ ድረሱ፤ ከተማ ብቻ ቁጭ አትበሉ እያለ ነው፡፡ አንድ ጊዜ አለን ትላላችሁ፤ ሌላ ጊዜ ትጠፋላችሁ የሚለው ጥያቄ ተደጋግሞ እየተነሳ ነው፡፡ የህወሓትና የትግራይ ሕዝብ ሁኔታም እየሻከረ ያለበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ የትግራይ ሕዝብ ለውጥ ፈላጊ ነው፡፡
Ze-Habesha