Saturday, June 29, 2013

የጠ/ሚ ኃይለማርያም ደሣለኝ የመጀመሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ …

ኢትዮጵያዊያን በኅዳሴ ግድብ ዙሪያ የአቋም ልዩነት የላቸውም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ደሣለኝ “በዚህ ወሣኝ ወቅት እራሣቸውን አጋልጠው ሰጡ” ያሏቸውን ወገኖች ግን “ያበዱ” ሲሉ ገልፀዋቸዋል፡፡
ጠ/ሚ ኃይለማርያም ደሣለኝ - /ፎቶ - ፋይል/
ኢትዮጵያዊያን በኅዳሴ ግድብ ዙሪያ የአቋም ልዩነት የላቸውም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ደሣለኝ “በዚህ ወሣኝ ወቅት እራሣቸውን አጋልጠው ሰጡ” ያሏቸውን ወገኖች ግን “ያበዱ” ሲሉ ገልፀዋቸዋል፡፡ኢትዮጵያ ከግብፅ ጋር የምትደራደረው “መሠረታዊ አቋሞቿን ባልነካ ሁኔታ ነው” ብለዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን የተናገሩበት የዓርብ፣ ሰኔ 21/2005 ዓ.ም ጋዜጣዊ መግለጫ መንበረ መራኂ-መንግሥቱን ከያዙ ወዲህ የመጀመሪያቸው መሆኑ ነው፡፡
ሊንኩን በመንካት ዝርዝር የያያዘውን የእስክንድር ፍሬውን ዘገባ ያዳምጡ፡፡

ተመስገን ደሳለኝ ለማን ደስ ይበለው ብሎ ጠፋ!?

ተሜ
ተመስገን ደሳለኝ ለማን ደስ ይበለው ብሎ ጠፋ!?
ባለፈው ጊዜ አንድ ወዳጄ ጋር አዲሳባ ስልክ ደውዬ ሳናግረው በአካባቢው ከእርሱ ድምጽ ጎልቶ የሚሰማ የመኪና ጥሩንባ ሰማሁና ይሄ ሁሉ የመኪና ጥሩምባ ምንድነው… ብዬ ጠየኩት፡፡
ሃይለማሪያም ደሳለኝ እየገቡ ወይም እየወጡ ነው መሰለኝ መንገድ ተዘጋግቷል፡፡ አለኝ፡፡
ወዲያውም ቀጠል አድርጎ፤  እንደ ሀቁ ቢሆን ኖሮ መንገድ መዘጋጋት የነበረበት ለሀይለማሪያም ደሳለኝ ሳይሆን ለተመስገን ደሳለኝ ነበር… አለኝና በቁጭት፤ ይሄው የሚያጅቡትን አያቀውቁምና… እልኩ እያታዘብኩ ነው…! ሲል አወጋኝ!
ተመስገን ደሳለኝ ገዢውም ተገዢውም ፓርቲ ሊያመሰግነው የሚገባ ጋዜጠኛ ነው፡፡ ነገር ግን ገዢዎቻችን ማመስገን የሚቆጥር ይመስል ሰውን ማመስገን አይወዱም፡፡  ስለዚህ ተሜንም በማመስገን ፈንታ ከሰሱት፡፡ ጎሽ በማለት ፈንታ እንደ ጎሽ ሊወጉት ቀንዳቸውን አሾሉበት፡፡ እሰይ በማለት ምትክ ሰይ ባንከረባብት ብለው ለሁለቱም አሰቡት፡፡ (ለማሰርም ለማሰደድም) (ሰይ ባንከረባብት በልጅነታችን ብይ ጨዋታ ላይ ተወርዋሪዋ ብይ ጉድጓዳ ውስጥ ብትገባም የተቃራኒውን ብይ ብትመታም ነጥቡ እንዲያዝልን ውል የምንገባባት ቃል ነበረች፡፡)
ተመስገን ደሳለኝ እንዲሰደድ መንግስት ከፀሎት ጀምሮ ሁሉንም አይነት የትግል ስልቶችን እንደተጠቀመበት ትዝ ይለኛል፡፡ ለምሳሌ ባለፈው ጊዜ ምንም የቀጠሮ ወረቀት ወይም መጥሪያ ሳይሰጠው በራዲዮን፤ “ተመስገን ደሳለኝ በሌለበት የፍርድ ሂደቱ ታየ ለሚቀጥለው ጊዜ ፖሊስ ይዞ እንዲያቀርበው ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል!” የሚል አይነት ዜና በሰላም ቁጭ ብሎ ሻይ በሚጠጣበት ካፌ ውስጥ ሰማ፤ (እናጋን ካልን ደግሞ ዜናውን እንደውም ያነበቡት ተሜ ልክ ዜና ሲሰማ አይተው ነው…! ማለት እንችላለን…) የዚህ ዜና አላማ ግልፅ ነበር፡፡ ተሜ ደንግጦ ፖሊስ ሳይዘው በፊት መንገዱን እንዲያያዘው ማድረግ ነበር፡፡ ወዳጃችን ግን፤ ብታስሩኝ ባለ ጊዜም ባለ ብረትም ናችሁና እግሬ እምቢ ማለት አይቻለውም፡፡ ለመሰደድ ግን እሺ የሚል እግር የለኝም፡፡ ብሎ እንቅጩን ነገራቸው እና የመጣው ምጣ ብሎ ቁጭ አለ…
በነገራችን ላይ ተመስገን እስከ አሁን ድረስ በመንግስት የተሰነዘረበት ክስ ስፍር ቁጥር የለውም፡፡ እንደው የሪከርድ መዝጋቢ መስሪያ ቤቶች የሚያስታውሳቸው አጥተው እንጂ ከዚህ ሁሉ ክስ ጋር አብሮ መኖር የቻለ ጋዜጠኛ ብለው ድንቃድንቅ መዝገብ ላይ የሚያሰፍሩት ሁሉ ይመስለኛል፡፡ መንግስታችን በክስ ላይ ክስ ሲደራርብ ሲደራርብ ክሱ ተቆልሎ አለመናዱም የእግዜር ተዓምር ነው፡፡ አንዱ ሳይቋጭ አንዱን አንዱ ሳይቋጭ አንዱ ክስ ሲመጣ በአሁኑ ሰዓት ተመስገን ደሳለኝ ከሃምሳ በላይ ክሶች ጋር ተመስገን ብሎ እየኖረ ነው፡፡
የተሜ እና የእኛ ፍትህ ጋዜጣ “መለስ ሞቱ” በማለቷ እኛ ሳንል ምን ሲደረግ እንዲህ ትያለሽ ተብላ ከሳላሳ ሺህ ኮፒ በላይ እንድትቃጠል ተደረገች፡፡ (የመለስ አምልኮ ይሎዎታል ተመስገን…!) አንዱ ሲዘጋ በአንዱ እንከሰታለን በምትለው ስትራቴጂ መሰረት፤ አዲስ ታይምስ ተተካች፡፡ አዲስ ታይምስ ደግሞ “ብር ከየት አምጥታችሁ ነው…” ተብላ ህትመቷ ተከለከለ፡፡ መንግስታችን እንደሆነ ኮሚክ ነው ጮክ ብለን በያይነቱ ስናዝ ራሱ “ብር ከየት አምጥተው ነው” ብሎ ይጨንቀዋል፡፡ በእርሱ ቤት እርሱ አበል ያልሰጠው ሰው፤ ወይም ከአዲስ ብድርና ቁጠባ ተቋም ያልተበደረ ሰው ምንም ገንዘብ የለውም…!
ተመስገን እና ጓደኞቹ እጅ መስጠት ብሎ ነገር አያውቁም ነበር፤ እና ከየትም ከየትም ብለው ድጋሚ ልዕልና ጋዜጣን አበረከቱልን፡፡ መንግስት መንግስት ሆኖ እንጂ… በብስጭት ካቲካላ ይጠጣ ነበር፡፡ ግን ሳይጠጣም ሞቅ አለው፡፡ ሰከረም፡፡ እናም ልዕልናንም ጥርቅም አድርጎ ዘጋት፡፡ (ይህ ውሳኔ የሞቅታ ካልሆነ ሌላ ሊሆን አይችልም)
ተመስገን ደሳለኝ ሲናገር ሰዎቻችን ደስ አይላቸውም፡፡ እናም በተቻለ አቅም ዝም ማሰኘት ይፈልጋሉ፡፡ ልጁ ግን በቀላሉ ዝም ብሎ የሚያስደስታቸው አልነበረም፤ በማህበራዊ ድረገፆች የሚተነፍሰውን ይተነፍስ ጀመር፡፡
ኢህአዴግ ሰው እንደማትንቅ ያወኩት እኔ ምስኪኑን ሳይቀር ለመከታተል የደህንነት ሰው የመደበች ዕለት ነው፡፡ ለተመስገን ደሳለኝማ ሁሉን አቀፍ የትግል ስልት ነው የተጠቀመችበት፡፡ በእውነቱ ከሆነ፤ ለአንድ ግለሰብ ሁሉን አቀፍ የትግል ስልት መጠቀም ትልቅ የሀይል ብክነት ነው፡፡ ፍጹም ተመጣጣኝ ያልሆነ ርምጃ፤ ጎጆ ቤትን በሚሳኤል እንደ መደብደብ በሉት…
ተሜ በኢህአዴግ ክሶች ብዛት፤ በኢህአዴግ ሚዲያዎች ማስፈራራት፣ በኢህአዴግ የደህንነት ሰዎች ከበባ፣ በኢህአዴግ ማተሚያ ቤቶች አድማ አበሳውን አየ፡፡
“አንበሳው” መንግስታችን ተመስገን ግለሰብ ነው ብሎ አልናቀውም፡፡ ያለውን አቅም ሁሉ ተጠቅሞ ሊገድበው ተንቀሳቅሷል፡፡ እርሱን ለመገደብ ያላደረገው ነገር ቢኖር ቦንድ ግዙ ብቻ አላለንም፡፡ ለአባይ የምንገዛው ቦንድ ብዙ ነገር ይገድባልና!
አሁን ተመስገን ደሳለኝ ከሜዳው ላይ ጠፍቷል፡፡ ከመንግስታችን ሃይል የተሞላበት አጨዋወት አንጻር እስከዛሬም በቃሬዛ አለመውጣቱ የሚገርም ነበር፡፡ ነገር ግን ያንን ሁሉ ችሎ ሜዳው ላይ ስናየው እኛ ደስ ይለን ነበር፡፡ አሁን ታድያ ሲጠፋብን ጊዜ በአዲስ መስመር ላይ ጮክ ብለን እንጮሃለን እንጂ እንደምን ዝም እንላለን…
ተመስገን ደሳለኝ ሆይ ማን ደስ ይበለው ብለህ ጠፋህ…!

Thursday, June 27, 2013

በረከት ስምኦን በሰማያዊ ፓርቲ ዙሪያ እየዶለቱ ነው – (ከኢየሩሳሌም አርአያ)

2
(ከኢየሩሳሌም አርአያ) በዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ሊቀመንበርንት ከሚመራው ግንቦት ሰባት ጋር በተያያዘ በሰማያዊ ፓርቲ ዙሪያ በረከት ስምኦን የሚመሩት የመንግስት አካል በምስጢር እየዶለተ መሆኑን ምንጮች ጠቆሙ። በቅርቡ በአንድ ድረገፅ ላይ የወጣውን የዶ/ር ብርሃኑን ንግግር በማስረጃነት ይዘው እየተንቀሳቀሱ ያሉት አቶ በረከትና ተከታዮቻቸው በአገር ውስጥ እየተንቀሳቅሰ የሚገኘው ሰማያዊ ፓርቲ « ከግንቦት ሰባት ጋር ግንኙነት አለው፤ ከግንቦት ሰባት የገንዘብ ድጋፍ ይደረግለታል» በሚል እነበረከት ድምዳሜ ላይ መድረሳቸውን የጠቆሙት ምንጮቹ የፓርቲውን አመራሮች «ከሽብረተኛ ቡድን ጋር በመገናኘት» ብለው ለመክሰስ ሴራ እያበጃጁ መሆኑን አስውታውቀዋል። የፓርቲው አመራሮችን ከማሰር ባለፈ «ሰማያዊ ፓርቲ በሽብርተኛ ድርጅት የሚረዳ ነው» በሚል በአገር ውስጥ የሚኖረውን የፓርቲው ቀጣይ ህልውና ለማክሰም ጭምር እየዶለቱ መሆኑን ምንጮቹ ጠቁመዋል። ከበረከት በተጨማሪ ደብረፂዮን ይህንን ሴራ በበላይነት እየመከሩበት እንደሆነ ምንጮቹ አያይዘው ገልፀዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ አሜሪካ ለሚገኝ አንድ ጋዜጠኛ ከገዢው ባለስልጣናት ዳጎስ ያለ ገንዘብ እንደተላከለት የቅርብ ምንጮች አጋለጡ። መጀመሪያ 250.00 (ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) ፣ በማስከተል 50.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) ሃዋላ እንደተደረገለትና ባጠቃላይ 300.00 (ሶስት መቶ ሺህ ብር) በዶላር ተመንዝሮ በእጁ እንደደረሰው ምንጮቹ ጠቁመዋል። ገንዘቡ ከነበረከት በኩል በምስጢር የተላከ መሆኑን ያጋለጡት ምንጮቹ በዚሁ መሰረት ጋዜጠኛው ለሕወሐት/ኢህአዴግ ማገልገል መቀጠሉንና በተለይ አሁን በሰማያዊ ፓርቲ ዙሪያ እየተሸረበ ያለው ሴራ መነሻው ይህ ሰው እንደሆነ አያይዘው ገልፀዋል።

በገዋኔ በፌደራል ፖሊስና በህዝቡ መካከል በተፈጠረ ግጭት ሰዎች ተጎዱ


576820_643438789017118_1777115518_n
ሰኔ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና :-ዛሬ ሰኔ 20፣ 2001 ዓም አንድ የአፋር ወጣት በኢሳዎች መገደሉን ተከትሎ የከተማዋ ነዋሪዎች ሬሳውን በመያዝ ተቃውሞአቸውን ለመግለጽ ፖሊሶች ወደ ሚገኙበት ካፕም ሲያመሩ የፌደራል ፖሊሶች ” ዘወር በሉ” በማለት ሰልፈኞችን ሲጠይቁ፣ ሰልፈኞችም ” ጥያቄያችን ሳይመለስ አንሄድም” በማለታቸው ተኩስ እንደተከፈተባቸው እና ሁለት ሰዎች እንደቆሰለባቸው ነዋሪዎች ገልጸዋል። የሞቱ ሰዎች እንዳሉ የተጠየቁት የአካባቢው ነዋሪዎች ፖሊሶች ሊያስጠጉን ስላልቻሉ ለማወቅ አልቻልም የሚል መልስ ሰጥተዋል። ከቆሰሉት መካከል አንዱ ሆዱን ሌላው ጭንቅላቱን መመታታቸው ተናግረዋል።
የፌደራል ፖሊስ አባላት በአካባቢው የመሳሪያ ፍተሻ እናደርጋለን በማለታቸው ከወረዳው ፖሊሶች ጋር መጋጨታቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል።
በገዋኔ አካባቢ በአፋር እና በፌደራል ፖሊሶች መካከል የሚታየውን ተደጋጋሚ ግጭት በተመለከተ የአካባቢውን ባለስልጣናት ለማነጋገር ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።

ESAT Daily News Amsterdam June 27, 2013 Ethiopia


Wednesday, June 26, 2013

ምነዋ ! ማንዴላችን ? !

(ነብዩ ሲራክ)
ምነዋ ማንዴላ ታከተህ
 ጉዞህን በአጭሩ ገታህ ?
mandelaa እስር እንግልቱ ሳያቆምህ
 የእሳት ወላፈን ሳይገድብህ
 የአሸባሪነት ሰሙ ተሰጥቶህ
 ደብድባ ግርፋት መገለሉ ሳይበግርህ
ፍትህን ብለህ ፣ ፍትህ ናፍቀህ ፣ ፍትህ ተነፍገህ
 የነገን ብሩህ ህይዎት ሰንቀህ
በቆፍጣና ወኔ ተሞልተህ ፣
 መስመር ማለፋቸውን ነግረህ
ወጥ የመርገጣቸውን ነውር ፣
 በፈርጣማ ጡንቻ አንበርክከህ
ጭቆናን በጽኑ አውግዘህ
 ወህኒ በኩራት መውረዱ ሳያቆምህ
ረጅሙን መንገድ ተጓዠ አንተ እኮነህ !

አባት ማንዴላ !
ተምረህ ተመራምረህ
 ወኔን በጽናት ተክተህ
አድልኦን በአደባባይ አውግዘህ
 ትግሉን በህቡዕ መርተህ
ደቡበ አፍሪካን ነጻ አውጥተህ
 የአፖርታይድን አከርካሪ ሰብረህ
የመቻቻልን ፍቅርን አብሮነት
 በድል አጥቢያ አስመስክረህ ደም የተቃባ ህዝብን
አጨባብጠህ ነጭ ከጥቁር አስተቃቅፈህ
 የዘረኝነት በቀልን አጽድተህ
በቀልን በይቅርታ ሽረህ
 ጥላቻ የዘር ፖለቲካን አሸቀንጥረህ
አንድ ሁኑ ብለህ ፣ አንድ አድርገህ
 የአፍሪካን የነጻነት ችቦ ለኩሰህ
ከአጽናፍ እስከ አጽናፍ አብርተህ
 የአለም ጭቁን ህዝብ ተስፋ ሆነህ
ረጅም አድካሚውን ጉዞ ተጉዘህ
 የስልጣን ሽግግርን አምንህ
 የህዝብን አደራ ለተተኪው አስረክበህ
(ይህ ከግጥሙ ተቀንጭቦ የተወሰደ ሲሆን ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)
http://www.goolgule.com/why-mandela/

“ምስጢር ካወጣህ ቤተሰቦችህን እንፈጃቸዋለን”

“ብዙ አይነት የድብደባና የስቃይ መአት ደርሶብኛል”
tesfaye


“የደረሰብኝን ስቃይ ለማንም ብናገር ቤተሰቦቼን በሙሉ እንደሚፈጁ አስጠንቅቀውኛል”
ወጣት ተስፋዬ ተካልኝ በዝዋይ እስር ቤት ለወራት ስቃይ የተፈፀመበት
ወጣት ተስፋዬ ተካልኝ መኮንን ይባላል፤ አርሲ አርባ ጉጉ ተወልዶ አዳማ/ናዝሬት አድጎ፣ በ1998 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሶሲዮሎጂ ተመርቋል፡፡ በ2000 ዓ.ም በባህልና ቱሪዝም ሚ/ር በሲኒየር ካልቸራል ኤክስፐርትነት የስራ መደብ እስከ ሚያዝያ 2003 ሰርቷል፡፡ ሚያዝያ 12 ቀን 2003 ዓ.ም በግልፅ ባልተረዳው ምክንያት የመንግስት ደህንነት ሀይሎች ተይዞ ለ23 ወር በዝዋይ እስር ቤት ከፍተኛ ስቃይ እየተፈፀመበት መቆየቱን ይናገራል፡፡ መጋቢት 26 ቀን 2005 ዓ.ም ከእስራት ሲለቀቅም አንድ ጊዜም እንኳን ፍርድ ቤት እንዳልቀረበ ለፍኖተ ነፃነት አስረድቷል፡፡ ከወጣት ተስፋዬ ተካልኝ መኮንን ጋር ያደረግነውን ቆይታ ተከታተሉን፡፡
ፍኖተ ነፃነት፡- ማን ነበር ያሰረህ?
ወጣት ተስፋዬ:- ሚያዝያ 12 ቀን 2003 ዓ.ም በማለዳ ቤቴ ተንኳኳ፤ ተነስቼ ከፈትኩኝ፡፡ የማላውቃቸው ሰዎች ናቸው፡፡ “ና ውጣ፤ ልብስህን ለብሰህ ውጣ” አሉኝ፡፡ እኔ እናቴ ሞታ ሊያረዱኝ የመጡ መስሎኝ “ምነው ቤተሰብ ደህና አደለም? የተፈጠረ ችግር አለ?” አልኳቸው “ዝም ብለህ ናውጣ” አሉኝ፡፡ ልብሴን ለበስኩኝና ወጣሁ፤ አንቀው መኪና ውስጥ ከተው ወደ ማዕከላዊ ወሰዱኝና 3 ወር አሰሩኝ ከዛም አንድ አመት ከ8 ወር ዝዋይ ማረሚያ ቤት፡፡
ፍኖተ ነፃነት፡- መታሰርህን ለቤተሰብ ተናግረሀል?
ወጣት ተስፋዬ:- ለማንም ሰው እንድናገር አልፈቀዱልኝም፤ መስሪያ ቤቴ አልጠየቀኝም፣ ደሃዋ እናቴ ያለችው ናዝሬት ነው እሷም የምታውቀው ነገር አልነበረም፡፡ አባቴ አቶ ተካልኝ አስተማሪ ነበር አርባ ጉጉ ላይ ነው በ1985 ዓ.ም በነበረው ግጭት ነው የተገደለው፡፡ ማንም ሳይጠይቀኝ፣ፍ/ቤት ሳልቀርብ 23 ወር ታሰርኩ ልብስ ምግብም የሚያመጣልኝ ሰው አልነበረም፡፡ እናቴም መታሰሬን እንኳ አታውቅም መስሪያ ቤቴም ስኮላርሽፕ አግኝቷል፤ ወደ ውጪ ሃገር ሊማር ሊሄድ ነው የሚባል ነገር ስለነበረ አልጠየቁኝም፡፡
ፍኖተ ነፃነት፡- የት ነበር ስኮላርሺፕ ያገኘኸው?
ወጣት ተስፋዬ:- የዛሬ 2 ዓመት አካባቢ የራስመስ ሙንደስን ስኮላርሽፕ አግኝቼ ነበር፡፡ ከዩኒቨርስቲ ኦፍ ካሊፎርኒያና ከዩኒቨርስቲ ኦፍ ቶክዮ ባሉ ምሁራን ሪኮመንድ ተደርጌ በጣሊያኑ ፌራሪ ዩኒቨርሲቲ ለመማር ተዘጋጅቼ ነበር፡፡ እንደተፈታሁ ሄጄ ስጠይቃቸው ብዙዎቹ ጓደኞቼ በጣም ደነገጡ፡፡ በማላውቀው ነገር 23 ወር ሙሉ ቅማል ተወርሬ … ባካችሁ ተውኝ … ምንም የሌለ ነገር የለም በጣም ተጎድቻለሁ፡፡ ከማረሚያ ቤት እንደወጣሁ እናቴ ጋ ስሄድ በጣም ደነገጠች፣ በሕይወት ያለሁ አልመሰላትም 23 ወር ሙሉ ከቤተሰብ ስለተለየሁ ግራተጋባች፡፡
ፍኖተ ነፃነት፡- በእስር ወቅት የደረሰብህ ድብደባና ማሰቃየት ነበር?
ወጣት ተስፋዬ:- ከፍተኛ ጉዳት ደርሶብኛል፡፡ በኤሌክትሪክ ጀርባዬ ላይ አቃጥለውኛል፣ በብልቴ ላይና በኩላሊቴ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ስላደረሱብኝ ሽንት ችዬ አልሸናም፣ ሽንቴን መቆጣጠርም አልችልም፡፡ ኩላሊቴንም በጣም ያመኛል፡፡ ውሃ ውስጥ እየነከሩ በጣም ደብድበውኛል፡፡ አሁን ስናገር ያመኛል ብዙ አይነት የድብደባና የስቃይ መአት ደርሶብኛል፡፡
ፍኖተ ነፃነት፡- እንደው ስታስበው ለእስር ያበቃህ ወይም ከመንግስት ጋር ያጋጨህ አጋጣሚ ነበር?
ወጣት ተስፋዬ:- መስሪያ ቤቴ ውስጥ የኢህአዴግ አባላት ነበሩ፤ በጣም ይከታተሉኛል፡፡ በቢ.ፒ.አር ላይ ስብሰባ በተደጋጋሚ ይጠራ ነበር፡፡ እኔም ሠራተኛ ላይ ተፅእኖ የሚያደርሱ ነገሮች ሲመጡ እኔ አልቀበልም በግልፅ እናገር ነበር፤ ሠራተኛውም እኔን ይደግፋል፡፡ ከመታሰሬ ጥቂት ጊዜ በፊት ገነት ሆቴል ስብሰባ ነበረን፡፡ በዛ ስብሰባ ላይ በጣም ተከራከርኩ፤ ከሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር አቶ ፀጋዬ ማሞ የሚባሉ አሰልጣኝ፣ ከውጭ ጉዳይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲና ከንግድና ኢንዱስትሪም የመጡ ነበሩ ስማቸውን የማላስታውሳቸው ባለስልጣን ነበሩ፤ እዛ ላይ ሀሳብ አንስቼ ተከራክሬ ነበር፡፡ “የሠራተኛን ሀሳብ ዳይቨርት ያደርጋል” ይሉኝ ነበር፡፡ መቼም ግን ሀሳቤን በመናገሬ ይህን የመሰለ ስቃይ ይደርስብኛል ብዬ አስቤ አላውቅም ነበር፡፡ “አሸባሪ፣ ግንቦት ሰባት” እያሉ እኔ በማላውቀው ነገር 23 ወር ሙሉ ፍርድ ቤት ሳልቀርብ ያለምንም ፍርድ በርሜል ውስጥ ውሃ ጨምረው እያስተኙ አሰቃዩኝ፡፡
ፍኖተ ነፃነት፡- እንደዚህ ያሰቃዩህ ምን አይነት ምንም አይነት መረጃ ሳያገኙ ነው?
ወጣት ተስፋዬ:- እኔን ጥፋተኛ የሚያስደርግ ምንም መረጃ አላገኙም፣ እኔን አስረው ወደ መስሪያ ቤት በተደጋጋሚ ይደውሉ እንደነበር ይነግሩኝ ነበር፡፡ የኢሜይል አድሬሴንም ተቀብለው በርብረዋል ግን ምንም አላገኙም፡፡ እኔ ከማንም ጋር ሊንክ የለኝም ኢሜሌ ላይ የስኮላርሺፕ መልዕክት ካልሆነ በስተቀር ምንም የለውም፡፡ በመስሪያ ቤቴ ሪሰርቸር ነበርኩ፣ በሶሲዮሎጂ ነው የተመረኩት፡፡ ሉሲ የተገኘችበት ሣይት ላይ አፋር፣ ጋምቤላ ብዙ ሳይቶች ሰርቻለሁ፡፡ ከአለቆቼ ጋር ያለኝ ግንኙነት ሰላማዊ ነው እነሱ ናቸው ስኮላርሽፕ ሪኮመንድ ያደረጉኝ፡፡ አንደኛው ፕሮፌሰር 25 ዓመት ሙሉ እዚህ አገር ሰርቷል፣ አርዲን ያገኘው እሱ ነው፡፡ ሄነሪ ጊልበርት ይባላል፤ እሱም ሪኮመንድ አድርጎኛል፡፡ እኔ በጣም የሚቆጨኝ ደሃዋ እናቴ አረቄና ጠላ ሸጣ ነው ያስተማረችኝ ምን ብዬ ልንገራት እንደዚህ አትጠብቀኝም ከበደኝ፣ አሁን እሷ የምትሰጠኝ ምግብ ራሱ ደምደም አለኝ… (ረጅም ለቅሶ)፡፡ ልጄ በደህናው አይደለም የጠፋው ሞቷል ወይም መኪና ገጭቶታል ብላ ነበር የምታስበው፡፡
ፍኖተ ነፃነት፡- የከመታሰርህ በፊት ፖለቲካ ተሳትፎ ነበረህ?
ወጣት ተስፋዬ:- 1997 ዓ.ም የቅንጅት ደጋፊ ነበርኩ፡፡ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪ ነበርኩ በ97 የነበረው ሁኔታ ስንት ሰው አለቀ በጣም ተስፋ አስቆራጭ ነበር ታውቃላችሁ ምንም የምናደርገው ነገር አልነበረም ፡፡ በምርጫ አሸንፎ ሥልጣን መያዝ እንደማይቻል ተረዳሁኝ፡፡ ከ1997 ዓ.ም በኋላ የማንም የፖለቲካ ፓርቲ አባል አልሆንኩም፡፡ ከዚህ በኋላ ከምንም ነገር የተገለልኩ ሆኛለሁ፡፡ አንድ ብርጭቆ ሳትሰብር አሸባሪ ስትባል አስብ እንግዲህ አንድ ብርጭቆ እንኳን ሰብሬ አላውቅም ባለኝ እውቀት እንደውም ለእውቀት ነው የምጓጓው እውቀቴን አሳድጌ አገሬን ለመለወጥ ነው የማስበው እኔን ምንም የሚመለከተኝ ነገር የለም አሸባሪም ግንቦት ሰባትም አይደለሁም፡፡ስትደበደብ፣ ስትሰቃይ ያላደረከውን አድርጌያለሁ ትላለህ፤ በርሜል ውሃ ሞልተው ይከቱሃል ያሰቃዩሃል፡፡ አያሳዝንም ይሄ? እንዴት አድርጎ እዚህ አገር ይኖራል? 23 ወር ሙሉ አስረው ማሰቃየታቸው ሳያንስ የደረሰብኝን ስቃይ ለማንም ብናገር ቤተሰቦቼን በሙሉ እንደሚፈጁ አስጠንቅቀውኛል፡፡ እኔ ግን ከዚህ በላይ ሞት የለም ብዬ ነው የነገርኳችሁ፡፡
ፍኖተ ነፃነት፡- አሁን የት ነው የምትኖረው?
ወጣት ተስፋዬ:- መኖሪያ የለኝም … (ረጅም ለቅሶ)
ወጣት ተስፋዬ ተካልኝን ለመርዳት የምትፈልጉ አንባብያን ከፍኖተ ነፃነት መረጃ ማግኘት ትችላላችሁ፡፡ (ምንጭ ፍኖተ ነጻነት)

Tuesday, June 25, 2013

የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ፕሬዚዳንቱ ስራ የሚ ለቁ ዳኞች ቁጥር መጨመሩን ተናገሩ

ሰኔ ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና :-የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ተገኔ ኔታነህ ሰሞኑን ለፓርላማ የመ/ቤታቸውን የ11 ወራት ሪፖርት
ባቀረቡበት ወቅት  ዳኞች በርካታ ችግሮች የተጋረጠባቸው በመሆኑ መስሪያቤቱን እየለቀቁ ነው ብለዋል።
የዳኞች መኖሪያ ቤት ችግርን በዘለቄታነት ለመፍታት ሕንጻ ለመገንባት እየተደረገ ያለው ጥረት የተወሰነ መጓተት እንደሚታይበት ፕሬዚዳንቱ ጠቁመው እስከዚያ ድረስ እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ መንግስት የኪራይ ቤት መስጠቱን እንዲቀጥል የተላለፈውን ውሳኔ የመንግስት ቤቶች ኤጀንሲ ተግባራዊ ባለማድረጉ ችግሩ ቀድሞ ከነበረበት ተባብሶ መቀጠሉን ፕሬዚዳንቱ  ገልጸዋል፡፡
የዳኞች እጥረትንም በተመለከተ አቶ ተገኔ ሲያስረዱ በዚህ ዓመት 58 ያህል ዳኞች በመሾማቸው የነበረውን የዳኞች
እጥረት በመጠኑም ቢሆን ለመቅረፍ የተቻለ ሲሆን ነገር ግን ቀደም ሲል በርካታ ዳኞች ፍ/ቤቶቹን የለቀቁ
በመሆናቸው ካለው ፍላጎት አንጻር በቂ ሆኖ አልተገኘም ብለዋል፡፡
በተለይ በድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች በኩል እያጋጠመ ያለው ፍልሰት ከፍተኛ ችግር መሆኑን ፕሬዚዳንቱ ገልጸዋል፡፡ ብዙዎቹ ሰራተኞች ስራ የሚለቁት በሚሄዱበት መ/ቤት የተሻለ ደመወዝና ጥቅማጥቅም በተለይም የሰርቪስና ሌሎች አገልግሎቶች በማግኘታቸው ነው ያሉት አቶ ጌታነህ በለቀቁ ሰራተኞች ምትክ ሰራተኛ ለመቅጠር የሚደረገው ሙከራ አብዛኛውን ጊዜ አይሳካም ሲሉ ምሬታቸውን ለፓርላማው
አስረድተዋል፡፡
ብዙዎቹ በክፍት ቦታዎች በሚወጡ ማስታወቂያዎች መሰረት ተወዳድረው ማሸነፋቸው ከተገለጸላቸውና የሐኪም ማስረጃ እንዲያቀርቡ ከተነገራቸው በኋላ በዚያው ነው የሚቀሩት ሲሉ ገልጸዋል፡፡
በማስቻያ ቦታና በቢሮ ጥበት በኩል ያለው ችግር አሁንም አለመቃለሉን ጠቅሰው እንደ አብነት የፌዴራል ከፍተኛው ፍ/ቤትን አንስተዋል፡፡ በፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 33 ችሎቶች ተቋቁመው አገልግሎት የሚሰጡ ሲሆን ለነዚህ ችሎቶች መጠቀሚያ የሚያገለግሉ 15 የማስቻያ አዳራሾች ብቻ ናቸው፡፡ በዚህ ምክንያት ችሎቶች በፈረቃ ለመስራት ተገደዋል፡፡ ይህም ዳኞችን በሙሉ አቅማቸው እንዳይሰሩ ከማድረጉም በላይ ባለጉዳዮች እየተጉላሉ ነው ሲሉ
በሪፖርታቸው ጠቅሰዋል፡፡
ፍ/ቤቶች የሕግ የበላይነት እንዲረጋገጥ ፣መልካም አስተዳደር እንዲሰፍን፣ለልማትና ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ
እየተደረገ ባለው ጥረት ውስጥ የድርሻቸውን እንዲወጡ ችግሮቻቸው ሊቀረፉላቸው እንደሚገባ ፕሬዚዳንቱ ጠቁመዋል፡፡
ብዙ ዳኞች በፖለቲካ ተጽኖ የተነሳ ስራቸውን በነጻነት ለመስራት ባለመቻላቸው ስራቸውን እንደሚለቁ የተለያዩ ጥናቶች ቢያመለክቱም፣ የፖለቲካውን ችግር ፕሬዚዳንቱ በሪፖርታቸው አላከተቱም። ኢትዮጵያ ውስጥ ነጻ የሆነ የፍትህ ስርአት አለመኖሩን በቅርቡ የአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት ባወጣው አመታዊ ሪፖርት ላይ ተመልክቷል።

ባለ ሀገር እስከምንሆን ትግሉ ይቀጥላል


ሳምንቱ በስራ ውጥረት ሽው ብሎ እንዳለፈ ያወቅሁት እሁድ ማለዳ ከቤተሰቤ ጋር ሳሳልፍ ነው፡፡ ሳምንቱንም ሙሉ ትኩረት ሳልሰጣቸው በምትኩ ሃገራዊ ሃላፊነቴን አቅሜ በፈቀደው መጠን ለመወጣት በርከት ያለውን ጊዜ እንደሰጠሁ የገባኝም እሁድ እለት ነው፡፡
እንደዚህ ‹‹ቢዚ›› ያደረገኝ አንድነት ፓርቲ ሕዝባዊ ንቅናቄውን ይፋ ከማድረጉ በፊት ማለቅ የሚገባቸው በርከት ያሉ ተግባራት ስለነበሩን ነው፡፡ እነዚህን ተግባራት ከትግል አጋሮቼ ጋር የኢትዮጵያ ሕዝብ ጥሞት እንዲውጣቸው ስናጣፍጥ ሰነበትን፡፡ ሰንብተንም በእለተ ሐሙስ የሃገር ውስጥና የውጭ ጋዜጠኞች በተገኙበት ይፋ አደረግን፡፡ ባለ ሃገርነታችንን የነጠቀንን የፀረ-ሽብር ህጉንም ለማሰረዝ በይፋ ‹‹የሚልዮኖች ድምፅ ለነፃነትን›› አበሰርን፡፡ በግልፅም ሚሊዮኖች የሚሳተፉበት ንቅናቄ በግልፅ ተጀመረ፡፡
ይሄ ሁሉ የሚሆነው ለምንድነው? አዎ! ይሄ ሁሉ እየተደረገ ያለው ባለሃገር ለመሆን ነው፤ ከምንደኛነት (ተመፅዋችነት) ለመላቀቅ ነው፣ የሁላችንን ሃገር ኢትዮጵያን ለመፍጠር ነው፣ አንገታችንን ቀና አድርገን ለመሄድ ነው፣ እውነተኛ ልማት ለማ ምጣት ነው፣ አምባገነንነትን፣ ሙሰኝነትን፣ ጉልበተኝነትን ለመታገል ነው፤ በነፃነት የኖረችውን ሃገር ነፃነት ለማረጋገጥ ነው፣ መንግስትን ላለመፍራት ነው፣ ሃሳብን በነፃነት መግለፅ እንዲረጋገጥ ነው፤ የእምነት ነፃነት እንዲረጋገጥም ነው፡፡ በአጠቃላይ በሰጪና ነሺ የተዋቀረውን አገዛዝን ለማስተማር ነው፡፡ ይሄ ማለት ባለ ሃገር ለመሆን ነው፡፡
ሃገሩ የኔ ነው፡፡ ሃገሩ የእኛ ነው፡፡ የሁላችን፡፡ ሁላችንም ላባችንን የምናንጠፈጥፍበት፣ አባቶቻችን ደማቸውን ያፈሱበት እኛም ደማችንን ለማፍሰስ የማንሰስትባት ኢትዮጵያ የሁላችን ናት፡፡ የህዝባዊ ንቅናቄው ዓላማም ይሄ ነው፡፡ ብዕር ነጣቂ መንግስት ያላት ሃገር ጉድፏን እንዴት ታያለች? ስለ ኢትዮጵያ ገዥ ሃይል ብእር ነጣቂነት እማኝ ለመጥራት ሩቅ አልሄድም፡፡ ከተወዳጁ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ጋር ሃሳባችንን እንዳንገልፅ ብእር ከተነጠቅነው መካከል ነኝ፡፡ በተወዳጇ ፍትህ ጋዜጣ አዲስ ታይምስና በኋላም ልእልና የጋዜጠኞች ብእር ተነጥቆ በጉልበት እስከሚዘጉ ድረስ በአምደኝነት ፖለቲካዊ ፅሁፎችን ጫጭሬያለሁ፡፡ ከብእር ነጠቃው በኋላ ለመጀመርያ ጊዜ የፃፍኳት ፅሁፍ ይቺ ናት፡፡ የተነጠቀውን ብእር ማስመለስ የምንችለው በትግል ብቻ ነው፣ ባለ ሃገር ስንሆን ብቻ ነው፣ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ስንፈጥር ብቻ ነው፡፡ መፍትሄው ይሄው ነው፡፡ የፖለቲካ ትግል፡፡
ስለዚህ በአንድነት ፓርቲ በኩል ይፋ የተደረገ ሕዝባዊ ንቅናቄ አንድምታው ብዙ ነው፡፡ ባለ-ሀገር ለመሆን ለምንፈልገው ወሳኝ የትግል ምዕራፍ ነው፡፡ ምንደኛ ላደረጉንና ለማድረግ ለሚፈልጉት ሃይሎች ደግሞ ህመም ነው፡፡ ለህመምተኞች የሚያም ህመም፡፡ ኢትዮጵያን አጥብቀን ለምንወድድ ሁሉ ግን ብስራት መሆኑ ሊሰመርበት ይገባል፡፡
የአንድነት ፓርቲ ህዝባዊ ንቅናቄ ካመማቸው የስርዓቱ ጥገኞች መካከል ሚሚ የተባሉት ግለሰብ አንዷ ናቸው፡፡ ሚሚ ስብሃቱ የተባሉት ሴትዮ የእሁድ ረፋድ ክብ ጠረጴዛ በተባለው ፕሮግራማቸው የፀረ-ሽብር ህጉን ለማሰረዝ የሚደረገውን ህዝባዊ ትግል እንደተለመደው ጥላሸት ለመቀባት ጥረት ሲያደርጉ ነበር፡፡ ሚሚ የተባሉት ግለሰብ ፕሮግራማቸው ሚዛናዊነት የጎደለውና ዘላፊ መሆኑ በአደባባይ የሚታወቅ ቢሆንም አንዳንድ ሰዎችን ለማደናገር ይችል ይሆናል፡፡ ሚሚና አፈ-ቀላጤዎቻቸው ‹‹ለምን የፀረ-ሽብር ህጉ ይሰረዛል፤ እንዴውም መጠናከር አለበት…›› በማለትና እንደ አለቆቻቸው አንድነትን ባልዋለበት ለማዋል መቁረጣቸው የፀረ-ሽብር ሕጉን እየጠቀሱ አፈናውና ነፃነት ገፈፋው እንዲቀጥል ያላቸውን ጥልቅ ምኞት ሲገልጡ ነበር፡፡ እኛ እያልን ያለነው ሁላችንም በነፃነት እንኑር ነው፡፡ ሁላችንም ባለ ሀገር እንሁን ነው፡፡
የሚሚና ቀላጤዎቿ ስህተት የፀረ-ሽብር ህጉ ከህገ-መንግስቱ ጋር ስንት ጊዜ እንደሚጋጭ አለማወቃቸው ነው፡፡ በአንድ በኩል ህገ-መንግስቱ ተናደ እያሉ ሲናገሩ የነበሩ ህገ-መንግስት የሚጥስ ህግ ምን ይሰራላቸዋል? ይሄ ህግ እየተጠቀሰ አንገታችንን እንድንደፋ የተደረግን ኢትዮጵያውያን ይሄ ህግ እንዲሻር እንታገላለን፡፡ ሁላችንም ባለ ሀገር እስከምንሆንም ትግሉ ይቀጥላል፡፡፡

በቤተመንግስት ግቢ ዙሪያ አንድ ሰው ተገድሎ ተገኘ

ኢሳት ዜና :-ባለፈው ሀሙስ ከጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ ጽህፈት ቤት ጀርባ  ሁለተኛው በር ከ150 እስከ 200 ሜትር  ባለ ርቀት ላይ አንድ ጎልማሳ አንገቱ ተቆርጦ  መገኘቱን የአይን እማኞች ለኢሳት ገልጸዋል።  -
እማኞች እንደሚሉት  ሟቹ እድሜው ከ45 እስከ 53 የሚጠጋ ጸጉር አልባ ጎልማሳ ነው። የሟቹ የራስ ቅል  ባእታ ክሊኒክ አቅራቢያ ባለ አንድ ቦታ ላይ ተጥሎ መገኘቱን የጠቆሙት ነዋሪዎች፣ ፖሊስ በአካባቢው ተገኝቶ አስከሬኑ እንዲነሳ ከአደረገ በሁዋላ ለአስከሬን ምርመራ ወደ ሚኒሊክ ሆስፒታል እንዲወሰድ አድርጓል።
የአይን እማኞች ” አካባቢው 24 ሰአት ሙሉ በስለላ ካሜራዎች የሚጠበቅ በመሆኑ ድርጊቱ በቤተመንግስት ጠባቂዎች ካልተፈጸመ በስተቀር በሌሎች ዜጎች ተፈጽሟል ብሎ  ለማመን አስቸጋሪ ነው” ይላሉ።
በጉዳዩ ዙሪያ የሚኒሊክ ሆስፒታልንና አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽንን ለማነጋገር ላለፉት 5 ቀናት በተደጋጋሚ ሙከራ ብናደርግም የሚኒሊክ ሆስፒታል ዛሬ መልስ ለመስጠት ፈቃደኛ ሲሆን፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር፣ የህዝብ ግንኙነት እና የወንጀል ምርመራ ክፍሎች ስልኮች አይነሱም። ሚኒሊክ ሆስፒታል የአስከሬን ምርመራ ውጤቱን በተመለከተ መውሰድ የሚችለው ፖሊስ በመሆኑ ፖሊስን መጠየቅ አለባችሁ የሚል መልስ ሰጥተዋል።
የአካባቢውን ሁኔታ በደንብ የሚያውቁ አንድ ሰው እንደገለጹት አስከሬኑ በተገኘበት አካባቢ፣  በምሽት  ሰዎች እንደሚይዘዋወሩ ገልጸው ግድያው የተፈጸመው ምናልባትም በጠባቂዎች ሊሆን ይችላል ብለዋል። ያም ካልሆነ ግን መንግስት በመገናኛ ብዙሀን መረጃውን ይፋ ማድረግ ይጠበቅበታል ብለዋል ግለሰቡ ።

ESAT Daily News - Amsterdam June 25, 2013 Ethiopia


Saturday, June 22, 2013

የትኛው አማራጭ ለአሜሪካ?…..“ኢህአዴግን ምን እናድርገው? ንገሩን!”

123
አሜሪካ ከመቼውም ጊዜ በላይ ደንግጣለች። ኦባንግ እንዳሉት ለህዝባቸው “ሬት” ለምዕራባውያንና “ማር” (የቤት ቀጋ፤ የውጭ አልጋ) የነበሩት አምባገነን በድንገት እንደ ተነቀለ ቡሽ ተስፈንጥረው ከሲስተም መውጣታቸው አሜሪካንን አስጨንቋታል። በተለይም እሳቸው አፍነው የያዙት የስርዓቱ “ክፉ ጠረን” አሁን እነርሱ (አሜሪካውያኑ) ደጅ የደረሰ ያህል መፍትሄ ለመፈለግ የወሰኑ ይመስላሉ። አውቀውና ፈቅደው ሲታለሉ የቆዩበትን ጊዜ አስልተው መንገዳቸውን የማስተካከል ስራ የጀመሩት ዛሬ አይደለም። አንዳንድ ምንጮች እንደሚሉት ከመለስ ሞት በኋላ አሜሪካ በምስራቅ አፍሪካ ላይ ሚዛኗን ሊያስታት የሚችል ውድቀት የሚደርስባት ኢትዮጵያ ላይ ያላትን አቋም ማስተካከል ሲያቅታት ብቻ እንደሆነ ይናገራሉ።
“… ሆን ተብሎ በተቀነባበረ እቅድ ህወሃት አዲስ አበባን እንዲቆጣጠር የተወሰነው ውሳኔ አሳዛኝና ከቶውንም ሊታመን የማይችል ነው። የሰከረ ርዕዮት ዓለም የሚከተሉ፣ በብሄርና በጎሳ ፖለቲካ ላይ የተተከሉ ጠባብ ቡድኖች፣ በስታሊናዊ መርህ የተጠመቁ፣ እንኳንስ 50 ሚሊዮን ህዝብ ያላት አገር ቤተሰብን የመምራትና የማስተዳደር ተሞክሮ የሌላቸው፣ አገርን መምራትን የሚያክል ታላቅ ሃላፊነት ማሸከም ለኔ ከአእምሮ በላይ ነው …” የዛሬ 22ዓመት ኮሎኔል ጎሹ ወልዴ ከተናገሩት፡፡
“አሜሪካኖች ነጻ እንድታወጡን አንጠይቃችሁም። የኢትዮጵያ ህዝብ እንዴት ነጻ እንደሚወጣ ያውቃል። እናንተ ግን በነጻነት መንገዳችን ላይ ዕንቅፋት አትሁኑብን፤ (የነጻነት መንገዱን አትዝጉብን)። ከመንገዱ ላይ ገለል በሉ … እስካሁን ያልተሞከረ መንገድ አለ … እሱም እርቅ ነው … ከመንግሥትም ሆነ ከተቃዋሚው በኩል ዓመኔታ የሚጣልባቸው አሉ … ” አቶ ኦባንግ ሜቶ፡፡
“የሚታየኝ ጦርነት ነው፣ የርስ በርስ ግጭት ነው። የርስ በርስ ግጭት በኢትዮጵያ የመነሳቱ ጉዳይ የማይቀር ነው። አገሪቱ ላለፉት 21 ዓመታት በተጓዘችበት መንገድ አትቀጥልም። … ሕዝብ በጭቆና አገዛዝ እየተገዛ ዝም ብሎ የማይኖርበት ደረጃ ላይ ደርሷል … ዝም ብሎ ግን አይቀመጥም … ይፈነዳል … ይህን እንድትገነዘቡ እፈልጋለሁ” ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ፡፡
አቶ መለስ “አሮጋንት /እብሪተኛ/፤ የፈለገውን ነገር በፈለገው ጊዜ የሚያደርግ ሰው … እንደነበር አዲስ አበባ ሄጄ ባነጋገርኩበት ወቅት አረጋግጫለሁ” ክሪስ ስሚዝ፡፡
“እድሜ ልካችሁን አትገዙም ብለን መክረናቸዋል” ዶናልድ ያማሞቶ፡፡
23የምክክሩ መድረክ
“ኢትዮጵያ ድኅረ መለስ፤ የዴሞክራሲና ሰብዓዊ መብቶች የወደፊት ዕጣ በኢትዮጵያ” በሚል ርዕስ፤ ከኢትዮጵያ ሁለት ተናጋሪዎች ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ እና አቶ ኦባንግ ሜቶ፤ በኢትዮጵያ የአሜሪካን አምባሳደር የነበሩትና በአሁኑ ወቅት በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር የአፍሪካ ጉዳዮች ተጠባባቂ ጸሐፊ ዶናልድ ያማሞቶ፣ የአሜሪካ የዓለምአቀፍ የልማት ተራድዖ የአፍሪካ ቢሮ ረዳት አስተዳዳሪ ኤሪል ጋስት፤ የማይክል አንሳሪ የአፍሪካ ተቋም ዳይሬክተር ዶ/ር ፒተር ፓሃም እንዲሁም በአምነስቲ ኢንተርናሽናል የመንግሥት ጉዳዮች ዋና ዳይሬክተር አዶቴ አክዌ የተጋበዙበት የምክክር ሸንጎ ላይ የቀረቡት ሃሳቦች በርካታ ጉዳዮችን የዳሰሱ ነበሩ። ሰብሳቢው በአሜሪካ የተወካዮች ምክርቤት በአፍሪካ፣ በዓለምአቀፍ ጤናና ሰብዓዊ መብቶች እንዲሁም ዓለምአቀፋዊ ድርጅቶች ንዑስኮሚቴ ሰብሳቢ ክሪስቶፈር ስሚዝ ደግሞ ኢህአዴግ ከፍተኛ ገንዘብ አፍስሶ ያኮላሽው ኤችአር2003 የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ረቂቅ ህግ ከሟቹ ዶናልድ ፔይን ጋር በማዘጋጀት በምክርቤት ለማስወሰን ያስቻሉ ነበሩ።
የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ፣ እንዲሁም በበክኔል ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ ተባባሪ ፕሮፌሰር የሆኑት የግንቦት 7 ሊቀ መንበር ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ እንደ እምነታቸው ንግግር አድርገዋል። ለተጠየቁት ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል። በምክክር ሸንጎው ላይ ከተጋበዙት መካካል ኢህአዴግ በቀጥታ ባለመወከሉ “ያለመመጣጠን (ያለመወከል)” ችግር አልነበረም፡፡ ኢህአዴግም ተገኝቶ ቢሆን ኖር ሊናገረው ከሚችለው በላይ ተናጋሪና ተከራካሪ ስለነበረው የኢህአዴግ መኖር አስፈላጊ አልነበረም የሚል አስተያየት ስብሰባውን በአካል ተገኝተው ከታዘቡና በቀጥታ ስርጭት ከተከታተሉ ወገኖች ተደምጧል።
ያም ሆኖ ግን ምክክሩ ከመካሄዱ ቀደም ብሎ በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የበላይ ሰው ክሪስ ስሚዝ ቢሮ በመገኘት አሉ የሚሏቸውን መከራከሪያዎች አቅርበው ነበር። የጎልጉል ምንጮች ለማረጋገጥ እንደቻሉት ኢህአዴግ ምክክሩን ተከትሎ ኤች አር 2003 ረቂቅ ሕግ እንዳይጸድቅ የተጠቀመበትን መንገድ ገና ካሁኑ በድጋሚ ጀምሯል።
ለኢትዮጵያውያን ሁሉ እያደር የእግር እሳት ሆኖ ያለፈውን የ1997 ምርጫ ተከትሎ ወደ ኢትዮጵያ በማምራት ከኢህአዴግ መሪ አቶ መለስ ጋር በርካታ ዲፕሎማቶች ተነጋግረዋል። አንዱ ከኒውጀርሲ ጠቅላይግዛት የአሜሪካ ም/ቤት ተወካይ ክሪስ ስሚዝ ነበሩ። “ኢትዮጵያ ከመለስ በኋላ” በሚል የተዘጋጀውን የምክክር ሸንጎ በመሪነታቸው ሲከፍቱ አቶ መለስን “አሮጋንት /እብሪተኛ/፤ የፈለገውን ነገር በፈለገው ጊዜ የሚያደርግ ሰው …” በማለት ነበር የገለጹዋቸው። የርሳቸው ገለጻ ታዲያ ከሁለት ዓስርተ ዓመታት በፊት ኢህአዴግ እንዲነግስ ሲወሰን ከቃል በላይ እሳት እየተፉ ንግግር ያደረጉትን ኢትዮጵያዊ አስታወሰ – የቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኮ/ሎ ጎሹ ወልዴ!
“… ሆን ተብሎ በተቀነባበረ እቅድ ህወሃት አዲስ አበባን እንዲቆጣጠር የተወሰነው ውሳኔ አሳዛኝና ከቶውንም ሊታመን የማይችል ነው። የሰከረ ርዕዮት ዓለም የሚከተሉ፣ በብሄርና በጎሳ ፖለቲካ ላይ የተተከሉ ጠባብ ቡድኖች፣ በስታሊናዊ መርህ የተጠመቁ፣ እንኳንስ 50 ሚሊዮን ህዝብ ያላት አገር ቤተሰብን የመምራትና የማስተዳደር ተሞክሮ የሌላቸው፣ አገርን መምራትን የሚያክል ታላቅ ሃላፊነት ማሸከም ለኔ ከአእምሮ በላይ ነው …” ኮሎኔል ጎሹ ወልዴ የትንቢት ያህል፤ ሳግ እየተናነቃቸው የኢትዮጵያን ተላልፎ መሰጠት በዚሁ በሰኔ ወር ከ22ዓመት በፊት አስረግጠው በማስረጃና በማስጠንቀቂያ በመቃወመ፣ በማሳሰብ፣ እንደማይሆን በመምከር፣ አድሮ እንደሚያቃጥል በማስጠንቀቅ፣ ላቀረቡት ንግግር የክሪስ ስሚዝ ገለጻ በማረጋገጫነት የሚቆም እውነት ይሆናል።
አሜሪካ ራስዋ ቀብታና ባርካ በትረ ሹመት የሰጠቻቸውን ሰዎች ከ22ዓመት በኋላ መልሳ “ገምግሙልኝ” ማለቷ አስገራሚ የሚሆንባቸው ጥቂት አይደሉም። ሰብሳቢው በመግቢያቸው የተናገሩት የኢትዮጵያ መንግስት ወቅታዊ መገለጫ፣ ቀደም ሲል ሚ/ር ያማሞቶን በመጥቀስ ዊኪሊክስ ይፋ ያደረጋቸውን መረጃዎች ለተከታተሉ “አሜሪካኖቹ ምን የማያውቁት ነገር አለና ነው የሚጠይቁት ያሰኛል” በሚል የሚገረሙ በርካታዎች ናቸው።444ለዚህ ይመስላል የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ ታሪካዊውን የኮሎኔል ጎሹ “ትንቢትና የኢትዮጵያ ህዝብን የሚወክል የምልጃ መቃተት” በማስታወስ ቀዳሚ የሆኑት። አስከትለውም “አሜሪካኖች ነጻ እንድታወጡን አንጠይቃችሁም። የኢትዮጵያ ህዝብ እንዴት ነጻ እንደሚወጣ ያውቃል። እናንተ ግን በነጻነት መንገዱን ላይ ዕንቅፋት አትሁኑበት። (ከመንገዱ ላይ ገለል በሉ)” የሚል መልክት አስተላለፉ።
የጋራ ንቅናቄው መሪ በድርጅታቸው መርህ ላይ ተመሥርተው በሰጡት የምስክርነት ቃል “ህወሓት እስካሁን በነጻአውጪ ስም አገር እየመራ እንደሆነ፤ መለስ ለህዝባቸው “ሬት” ለምዕራባውያንና “ማር” (የቤት ቀጋ፤ የውጭ አልጋ) ዓይነት መሪ እንደነበሩና የኢትዮጵያ ሕዝብ ላለፉት 22ዓመታት በመከራ ውስጥ ያለና የዛሬ 8ዓመት በዚሁ ቦታ ላይ ያማሞቶ ኢትዮጵያ በአቋራጭ መንገድ (ክሮስሮድ) ላይ እንደምትገኝ” መናገሩ አቶ ኦባንግ ካስታወሱ በኋላ “መቼ ነው መንገዱን የምናቋርጠው? ከስምንት ዓመት በኋላ አሁም አንሻገርም ወይ፤ አናቋርጠውም ወይ” በማለት ተሰብሳቢውን ያስደመመ ለሰብሳቢዎቹ ግልጽ ጥያቄ ጠይቀዋል፡፡
አቶ ኦባንግ ሲቀጥሉም “ኢትዮጵያውያን የምንጠይቀው በጣም ቀላል ጥያቄ ነው፤ አሜሪካኖች የሚመኩበትን ሰብዓዊ መብት እኛ ተነፍገናል፤ የራሳችን ክሪስ ስሚዝ ይኑሩን ብቻ ነው የምንለው” ካሉ በኋላ በኃይለሥላሴም ሆነ በመንግሥቱ ጊዜ ኢትዮጵያውያን ዕድላቸውን እንደተነፈጉ አስታውሰዋል፡፡ በወቅቱም በዚሁ ም/ቤት የዛሬ 22ዓመት በወርሃ ሰኔ ኮ/ሎ ጎሹ ወልዴ የዛሬዋን ኢትዮጵያን መተንበያቸውን አቶ ኦባንግ በንግግራቸው አስታውሰዋል፡፡ አሁንም የኢትዮጵያውያንን ቁርጠኛ አቋም ምን እንደሆነ ለአሜሪካውያኑ ግልጽ አድርገዋል “አሜሪካ እንድታድነን አይደለም የምንጠይቀው፤ ራሳችንን ማዳን እንችላለን፤ በነጻነት መንገዳችን ላይ ግን ዕንቅፋት አትሁኑብን፤ ራሳችንን ነጻ እናወጣለን፤ ኦባማ ለፕሬዚዳንትነት ሲወዳደር በርካታ ኢትዮጵያውያን ከሚያገኙት ጥቂት ደመወዝ ለምርጫው ዘመቻ ረድተው ነበር፤ ከኦባማ ግን የሰማነው ነገር እስካሁን ምንም የለም፤ ነጻነታችንን እየለመንን አይደለም፤ ራሳችንን ነጻ እናወጣለን” በማለት የበርካታ ኢትዮጵያውያንን የነጻነት መንፈስ የቀሰቀሰ ንግግር አድርገዋል፡፡
በመጨረሻም አሜሪካ ለኢትዮጵያ መንግሥት የዴሞክራሲ ለውጥ 300 ሚሊዮን ዶላር ዕርዳታ ሰጥቻለሁ እንደሚል ከጠቀሱ በኋላ “ይህ ሁሉ ገንዘብ የት ነው የገባው፤ የት ነው የሄደው” በማለት ኢህአዴግ ከቀበሌ ጀምሮ እስከላይ ሥልጣኑን እንደተቆጣጠረ፤ ሙስሊሙ መሪውን እንምረጥ ሲል አሸባሪ ተብሎ እንደሚፈረጅ ነገር ግን እኛ ኢትዮጵያውያን ከሙስሊም ወገኖቻችን ጋር አገርና መሬት ብቻ ሳይሆን የምንጋራው በደም የተሳሰርን መሆናችን አስረግጠው ተናግረዋል፡፡ አንድ ጊዜም እንኳን ጦርነት ሰብከውም ሆነ መሳሪያ አንስተው የማያውቁ መሆናቸውን የተናገሩት ኦባንግ፤ በኢትዮጵያ መንግሥት “አሸባሪ” መባላቸውን በመናገር የኢህአዴግን አሸባሪነት አጋልጠዋል፡፡ እስካሁን በአገራችን ላይ የፈሰሰው ደም በቂ እንደሆነ የጠቆሙት የጋራ ንቅናቄው መሪ፤ በኤድስና ምግብ በማጣት የረደሰብን ዕልቂት በቂ እንደሆነና ከእንግዲህ ወዲህ መጋደል እንደሌለብን ሆኖም ከኢህዴግም ሆነ ከተቃዋሚ በኩል አመኔታ የሚጣልባቸው ሰዎች ስላሉ እስካሁን ያልተሞከረውን የዕርቅ መንገድ (ሥራ) በኢትዮጵያ መከናወን እንዳለበት አቶ ኦባንግ ሜቶ በሚመሩት ድርጅት መርህና በሚታገሉለት የማዕዘን ሃሳብ ላይ ተተርሰው ሃሳባቸውን አጠቃልለዋል፡፡
በምክክር ሸንጎው ላይ የተገኙት የግንቦት 7 ሊቀመንበር ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ በበኩላቸው የንግግራቸውና የማሳሰቢያቸው ማሳረጊያ ሊባል የሚችል መልዕክት አስተላልፈዋል። ዶ/ር ብርሃኑ “አስተውሉ፣ ልብ ብላችሁ ተገንዘቡ” በማለት ያሳሰቡት ዛሬ ኢትዮጵያን የሚወዱ ሁሉ የሚጠበቡበት፣ እንዲከሰት የማይፈልጉትን የመጨረሻው ስጋት ነው።32በምክሩ ላይ በቀዳሚነት ምልከታቸውን ያብራሩት ዶ/ር ብርሀኑ ኢህአዴግ የዘረጋው የአፈና ስርዓት ያስመረረው ህዝብ፣ ኢህአዴግ ሆን ብሎ የሚያንኮታኩታቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ሆን ብሎ የሚተናኮለው ህዝብ፣ ያለው ብቸኛ አማራጭ ብረት ማንሳት ብቻ እንደሆነ አመልክተዋል። በቅርቡ የኢህአዴግ የአፈና ስርዓት ፈተና እንደሚገጥመው ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ አለመረጋጋት ቀጣናውን በሙሉ እንደሚረብሽና የአሜሪካንን ጥቅም በእጅጉ እንደሚጎዳ ዶ/ር ብርሃኑ በግልጽ በማስረዳት አሜሪካ ገንዘቧን በተገቢው ቦታ ላይ ማዋል እንዳለባት ምክር ሰጥተዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ የተቃዋሚ ኃይሎች አማራጭ ከማጣት የተነሳ ብረት ማንሳታቸውን የጠቆሙት የግንቦት 7 ሊቀመንበር፤ ሕዝብ ዝም ብሎ በአስከፊ አገዛዝ ሥር እየኖረ እንደማይቀጥል አስጠንቅቀዋል፡፡ በመሆኑም አማራጭ ሲጠፋ ባገኘው መንገድ ሁሉ መብቱን ወደማስጠበቅ እንደሚገፋና በአሁኑ ወቅትም የተቃዋሚ ኃይሎች በመተባበር በኢህአዴግ ላይ ጥቃት መሰንዘር የሚስችላቸውን ብቃትና ኅብረት እንደፈጠሩ ጠቁመዋል፡፡ ይህ ሊሆን የቻለውም ኢህአዴግ በምንም መልኩ የማይሰማና በሰላማዊ መንገድ ሥልጣን ለማስረከብ የማይችል መሆኑን በተለይ በ1997 ምርጫ ካስታወቀ ወዲህ በግልጽ የሚከተለው መርህ በራሱ ማስረጃ እንደሆነ ዶ/ር ብርሃኑ በጥያቄ መልክ ለቀረበላቸው ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
የኢህአዴግ የደምሥር የውጭ ዕርዳታ እንሆነ የተናገሩት የግንቦት 7 መሪ አሜሪካ ከአውሮጳውያን ጋር በመተባበርና ለእያንዳንዱ የተሃድሶ ዕርምጃ ቀነ ገደብ በመሥጠት በተሰጠው ገደብ ውስጥ እስረኞች ካልተፈቱ፤ የምርጫ ኮሚሽን ካልተቀየረ፤ ወዘተ በማለት ዕርዳታው እንደሚቆም በማስጠንቀቅ አሜሪካውያኑ ለኢህአዴግ መመሪያ ቢሰጡ ለገንዘብ ሲል ኢህአዴግ ሊታዘዝ እንደሚችል አስረድተዋል፡፡
በመጨረሻም በድጋሚ የሰብሳቢውን ስም በመጥራት ትኩረት የጠየቁት ዶ/ር ብርሃኑ “የሚታየኝ ጦርነት ነው፣ የርስ በርስ ግጭት ነው። የርስ በርስ ግጭት በኢትዮጵያ የመነሳቱ ጉዳይ ነው። አገሪቱ ላለፉት 21 ዓመታት በተጓዘችበት መንገድ አትቀጥልም። ይህን እንድትገነዘቡ እፈልጋለሁ” ብለዋል።
ከክሪስ አንደበት
ሰብሳቢው ክሪስ ስሚዝ በምክርቤት ስብሰባ ላይ ድምጽ መስጠት በሚገባቸው ረቂቅ ህጎች ላይ ሲሳተፉ ስለነበር ምክከሩ የጀመረው ከታቀደው ሰዓት 1፡30 ያህል ዘግይቶ በመሆኑ ይቅርታ በመጠየቅ ነበር መንበራቸው ላይ ተሰይመው ንግግር ጀመሩት። የምክክሩ ሊቀመንበር አቶ መለስ የዘረጉት አገዛዝ የሰብዓዊ መብት ረገጣ ልዩ ባህሪው እንደሆነ የተለያዩ ማስረጃዎችን በመጥቀስ ምክከሩን ከፈቱ። ምክክሩ በኢትዮጵያ ስላለው ወቅታዊ የሰብዓዊ መብቶችና የዴሞክራሲ ጉዳይ ላይ እንደሚያተኩርና የአሜሪካ መንግሥት ምን ማድረግ እንዳለበት የሚያመላከት ምክር የሚካሄድበት እንደሆነ አስገነዘቡ።
ኢትዮጵያ እስላማዊ አሸባሪነትን በቀጣናው በመዋጋት የአሜሪካ ደጋፊ አገር ሆና መቆየቷን፣ ሆኖም ግን በተመሳሳይ መልኩ የኢትዮጵያ መንግሥት ለሚፈጽመው ተደጋጋሚ የሰብዓዊ መብቶች ረገጣ የአሜሪካ መንግሥት የኢትዮጵያን መንግሥት ተጠያቂ ማድረግ እስካሁን አለመቻሉን ሳይሸሽጉ ተናገሩ።55የፖለቲካ ድርጅቶች በነጻነት መንቀሳቀስ አለመቻላቸውን፣ መንግስታዊ ባልሆኑ የግብረ ሰናይ ድርጅቶች (መያዶች) ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እንደሚደረግ፣ ጋዘጠኞች እንደሚታሰሩ፣ በርካታ ዜጎች ከመሬታቸው እንደሚፈናቀሉ ወዘተ በመዘርዘር አስረዱ።
የአሜሪካ የዕርዳታ ድርጅት – ዩኤስኤይድ እንደሚለው ከሆነ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ግልጽ ግንኙነት ማድረግ ወደፊት የዴሞክራሲና የለውጥ ሂደቶችን ለማሳካት ይረዳል ተብሎ ቢታሰብም፣ በክሪስ ስሚዝ አመለካከት ግን እምነቱ ሊተገበር የሚችል ቢመስልም እስካሁን ምንም ፍሬ እንዳላመጣ ሳይሸሽጉ ተናግረዋል።
እንደ አምነስቲ ኢንተርናሽናል መረጃ መሠረት በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው ስልታዊ አፈናና የሰብዓዊ መብቶች ረገጣ ለሌሎች አገራት መጥፎ ምሳሌ እየሆነ መሄዱን ሊቀመንበር ስሚዝ ጠቅሰዋል፡፡ ንጹሃን ዜጎች ስቃይ፣ ድብደባ እንደሚደርስባቸው፣ በኤሌክትሪክ እንደሚጠበሱና የግዳጅ ወሲብ እንደሚፈጸምባቸው፣ የአምነስቲ ሪፖርት መዘገቡን ክሪስ ስሚዝ በእማኝነት ተናግረዋል፡፡
ራሳቸው ክሪስ ስሚዝ በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ረቂቅ ህግ አዘጋጅተው እንደነበርና በወቅቱ የነበረው የጆርጅ ቡሽ አስተዳደር ግን ኢትዮጵያን በአሸባሪነት ላይ ወዳጅ በማድረጉ ምክንያት በነበረው ቸልተኝነት የተነሳ ተፈጻሚ ሳይሆን መቅረቱን አስታውቀዋል። ሚ/ር ስሚዝ እነዚህን ጉልህ ህጸጾች በመጠቆም ምክክሩ ላይ ተናጋሪ እንዲሆኑ የተጋበዙትን ክፍሎች በየተራ በማስተዋወቅ ጋብዘዋል። ከንግግሩ በኋላም ጥያቄዎችን ጠይቀዋል። ሌሎች ተሳታፊዎችም ጥያቄ በመሰንዘር ማብራሪያ እንዲወስዱ ተደርጓል።
ያማማቶ ምን አሉ?
ያማሞቶ በመግቢያ ንግግራቸው መለስን አወድሰዋል። አፍሪካን በዓለም መድረክ ከፍ እንድትል ያደረጉ መሪ በማለት አመስግነው ኢትዮጵያ ተሰሚነቷ እንዲጨምር ያደረጉ፣ ተሟጋችና ጎበዝ ተናጋሪ እንደነበሩ መስክረዋል። ኢኮኖሚውን አሳድገዋል፣ ኢትዮጵያን በቀጣናውና በዓለም ታዋቂ አድርገዋል፣ በሶማሊያ ተሟጋች፣ በሱዳን አስታራቂ፣ በአፍሪካ የአየርንብረት ጉዳይ ደግሞ አንደበተ ርዕቱ አፈቀላጤ ነበሩ በማለት የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንና ሬዲዮ ድርጅት ከሚደረድረው በላይ ቃል አከማችተው ምስጋና ቸረዋቸዋል።
ያማማቶ በማያያዝ እንደ አምባሳደርነታቸው በኢትዮጵያ ያለውን የፖለቲካ ምህዳር መጥበብ አስመልክቶ አቶ መለስን ማነጋገራቸውን ጠቁመዋል። በሰብዓዊ መብቱን መጓደል ዙሪያም በተመሳሳይ መነጋገራቸውን አክለዋል።
ካሊፎርኒያ ሎሳንጅለስ “ትንሿ ኢትዮጵያ” ወረዳ ተወካይ የምክርቤት አባል ሚስዝ ባስ፤ ያማሞቶን መስቀለኛ ጥያቄ አቅርበውላቸው ነበር። ጠያቂዋ “የኢህአዴግ መንግሥት ዋናው ችግር ምንድነው? ለምንድነው ይህንን ሁሉ መከራና አፈና የሚያካሂደው” በማለት የመገረም የሚመስል ጥያቄ ጠይቀዋል። ያማሞቶ እንደ መንተባተብ ሲሉ “ችግሩ ምንድ ነው?” በማለት ባስ በድጋሚ ጥያቄያቸውን ወረወሩ። “ችግሩ እንዳለ ነው” ሲሉ ደግመው መልስ የሰጡት ያማሞቶ “ጠቅላይ ሚ/ር ሃይለማርያም አፍሪካ ኅብረት ስብሰባ ላይ እንዳሉት ነው፣ የዴሞክራሲ እሴቶች አስፈላጊ ናቸው፣ መጥፎ ህጎች መወገድ አለባቸው፣ እንስራ፣ እንሞክር ብለዋል” አሉና መለሱ።
ኮንግሬስማን ሜዶውስ በኢትዮጵያ ኢህአዴግ ሁሉን ተቆጣጥሮዋል፤ እኛ አሜሪካኖች ምን ልናደርግ እንችላለን? እንዴት ነው ልናስተካክለው የምንችለው? የሚል ጥያቄ ለያማሞቶ ወረወሩ። ያማሞቶም “ከምርጫው በኋላ ደስተኞች አለመሆናችንን ተናግረናል፡፡ ከበስተጀርባና በፊትለፊት እየሰራን ያለነው ነገር አለ፡፡ ጊዜ የሚወስድ ነው፡፡ ለምሳሌ በሴቶች ላይ የሚደረግ የመብት ጉዳይ አለ እናም ይህንን ከዩስኤድ ጋር እየሰራን ነው” አሉ፡፡
ሜዶውስ የረኩ አይመስልም “እና ያለው ፍርሃት ምንድርነው?” ሲሉ በድጋሚ መልስ መፈለጋቸውን አመለከቱ። “ነግረናቸዋል ፣ ለዘላለም ልትገዙ አትችሉም። ስለዚህ የተቃዋሚውን ተሳትፎ ማበረታታት አለባችሁ ። እነዚህ ተቃዋሚዎች አንድ ቀን መንግሥት ይሆናሉ። ስለዚህ ዝግጅት መደረግ አለበት ብለናቸዋል” የሚል የደፈና መልስ ከያማሞቶ ተሰጠ።
ጋንት፤ የዩኤስ ኤይድ ረዳት ዳይሬክተር
የሴፍቲኔት ፕሮግራም እየተካሄደ መሆኑንና በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያ እየተረጋጋች እንደሆነ፣ ከዚህም ጋር በማከል ኢኮኖሚው እያደገ እንደሆነ ልክ የኢህአዴግ ወኪል መስለው ተናገሩ። ሰብሳቢው ስሚዝ “ቶርቸር በየቦታው አለ እና ይህንን እንዴት ነው ለማስታረቅ ወይም ለማቆም የሚቻለው?” ሲሉ ማብራሪያ ጠየቁ። ሚ/ር ጋንት “አስቸጋሪ ነገር ነው። ቶርቸር እንዳለ እናውቃለን ግን ዋናው ሥራችን መልካም ነገሮችን ለማበረታታት ነው የምንሞክረው” የሚል ምላሽ ሰጡ።
በሚ/ር ጋንት ንግግር ላይ ተንተርሰው ተጨማሪ ጥያቄ ያቀረቡት ክሪስ ስሚዝ፣ ኢትዮጵያ ትምህርትን አስመልክቶ የሚሊኒየም ጎል ተሳክቷል ማለታቸውን ጠቅሰው “ጋንት ግን እኮ ጥራቱ በጣም የዘቀጠ እንደሆነ ነው ሪፖርቱ የሚያሳየው” ሲሉ ሞገቱዋቸው። የዩኤስ አይዲው ዳይሬክተር ጋንት “አዎ ችግር አለ ግን በርካታ መምህራን ተሰማርተዋል በትምህርቱ በኩል ዕድገት አለ” የሚል መልስ መመለሳቸው ለግንዛቤ ያህል የሚጠቀስ ሆኖ አግኝተነዋል።
ያማሞቶና ጋንት ያቀረቡትን ንግግርና ምስጋና ያደመጡ፣ በአካል ተገኝተው የተከታቱተሉ እንዳሉት በምክክሩ ላይ ኢህአዴግ ቢገኝም የሚጨምረው ምንም ነገር ሊኖር እንደማይችል አመልክተዋል።
ዳግም HR2003
የዛሬ አስር ዓመት፤ ኤች አር 2003 በምክር ቤት ደረጃ ከፍተኛ የሸንጎ (ኮንግሬስ) አባላትን ድጋፍ ካገኘ በኋላ የሕግ መወሰኛ ም/ቤት (ሴኔት) አጽድቆት በፕሬዚዳንቱ ተፈርሞ ፖሊሲ ሆኖ እንዲጸድቅ ባለመደረጉ ተቋማዊና አስተዳደራዊ ለውጥ ሊያመጡ የሚችሉ ጉዳዮች መከኑ። የህጉ መርቀቅና እንዲጸድቅ የተጀመረው እንቅስቃሴ ያስበረገገው ኢህአዴግ ጡረተኛ የሴኔት አባላት ከሚመሩት ዲኤልኤ ፓይፐር ከተባለ የጎትጓች (ሎቢ) ቡድን ጋር ከፍተኛ በጀት በጅቶ ታገለ። ባፈሰሰላቸው መጠን ጎትጓቾቹ ባልደረቦቻቸውን ጠመዘዙና ህጉ አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የምትከተለው አዲስ የዴሞክራሲና የሰብዓዊ መብት ህግ እንዳይሆን ተደረገ። ይህንኑ ህግ በማዘጋጀት ከሟቹ የምክርቤት አባል ዶናልድ ፔይን ጋር በወቅቱ ብዙ ደከሙት ክሪስ ስሚዝ የወቅቱን የቡሽ አስተዳደርን በንዝላልነት መድበው አሁን ይሀንኑ ህግ ተግባራዊ የሚደረግበትን አግባብ እንደሚገፉበት አመልክተዋል።
እንዴት እዚህ ተደረሰ?
የኢህአዴግን የአገዛዝ ዘመን ተቃዋሚዎችን አጃቢ አድረጎ የህግ ሽፋን በመስጠት የሚያራዝመው ዋና ተቋም ምርጫ ቦርድ፣ የፕሬስ ነጻነት፣ የመናገርና የመሰብሰብ ነጻነት፣ የህግ የበላይነት፣ ሕግን የማክበርና የማስከበር ሃላፊነት፤ ወዘተ በኢትዮጵያ ነጻ ከሆኑ ኢህአዴግ ከፊትለፊቱ ካለው ምርጫ የመዝለል አቅም እንደሌለው ይታመናል። ስለዚህም ለድርድር አያቀርባቸውም። ኢህአዴግ ከጅምሩ በህዝብ የማይታመነውና እውቅና የሚነፈገው ራሱን በነጻ አውጪ (ህወሓት) የሰየመ መንግስት ስለሆነ ነው። ነጻ አውጪ እየተባለ አገር መምራቱ አቅዶ፤ ተልሞና መድረሻውን አስልቶ የሚጓዝ ስለመሆኑ ያሳብቅበታል። ለዚህም ይመስላል ስርዓቱ በሙስና የሸተተ፣ በግፍ የገለማ፣ የሚመራውን ህዝብ የሚገል፣ የሚያስር፣ የሚያሰቃ፣ መንግስት ሆኖ የሚሰርቅ፣ ብሔራዊ ክብርን የሚጠላ፣ ህብረትንና አንድነትን የሚጠየፍ፣ ጎሳና ጠባብ አመለካከት ላይ የተቀረጸ፣ በተራና በወረደ ተግባሩ ለመንግስትነት የማይመጥን መሆኑን የተረዱት አጋሮቹ አሁን ያመረሩበት ደረጃ ስለመዳረሳቸው ምልክቶች እንዳሉ አቶ ኦባንግ ሜቶ ለጎልጉል ተናግረዋል።
ይህ የምክክር ሸንጎ እንዴት ሊዘጋጅ ቻለ ለሚለው ጥያቄ በርካታ ጥረቶች መካሄዳቸውን በመግለጽ ዝርዝር ያላቀረቡት አቶ ኦባንግ ሐሙስ በተካሄደው ምክክር በመካከል ላይ ሚ/ር ስሚዝና ሌሎቹ ተወካዮች በምክርቤት ድምጽ መስጠት ስለነበረባቸው ምክክሩ ተቋርጦ እንደገና ሲጀመር ያልታዩበትን ምክንያት ተናግረዋል። ምክክሩ በተባለው ሰዓት ተጀምሮ ያልቃል የሚል እምነት ስለነበራቸው ሌላ ተደራራቢ የጉዞ መርሃግብር አመቻችተው እንደነበር አመልክተዋል።
“አሁን ስራ ላይ ነኝ” ያሉት አቶ ኦባንግ “እስራኤል አገር ለሁለት ከፍተኛ ጉዳዮች መጓዝ ነበረብኝ። አንዱ የወገኖቻችን ጉዳይ ነው። ሌላኛው ደግሞ የአገራችን ጉዳይ ነው። ከጉዞዬ በኋላ ማብራሪያ ለመስጠት እችላለሁ” በማለት ሁለተኛው ስብሰባ ሲካሄድ እርሳቸው ወደ እስራኤል ለሥራ እየተጓዙ እንደነበር አስታውቀዋል።
ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (http://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Thursday, June 20, 2013

መሬታቸው የተወሰደባቸው ከ50-60 የሚጠጉ የመተማ አርሶአደሮች ጫካ መግባታቸውን ሲያስታውቁ ከ30 ያላነሱት ደግሞ ታስረዋል

ሰኔ ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:- በመተማ ዮሐንስ እና በኮኪት ቀበሌዎች የሚኖሩ አርሶአደሮች መሬታችን አድሎአዊ በሆነ መልኩ ለባለሀብቶች እየተሰጠብን ነው” በማለት ተቃውሞአቸውን ማሰማታቸውን ተከትሎ ጸረ ሽምቅ እና ልዩ ሀይል የሚባሉ የመንግስት ታጣቂዎች ከ30 ያላነሱትን የአካባቢውን ሰዎች ሲያስሩ፣ በታጣቂዎች ከሚፈለጉት መካከል ደግሞ ከ50- 60 የሚሆኑት አርሶደሮች ጫካ መግባታቸውን አስታውቀዋል።
ባለፉት ሳምንታት  አቤቱታቸውን አዲስ አበባ ተገኝተው ለም/ል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን እንዲሁም በባህርዳር ለአማራ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አያሌው ጎበዜ ካቀረቡት የህዝቡ ተወካዮች መካከል የተወሰኑት በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን ፣ ሌሎች ደግሞ ጫካ መግባታቸውን የህዝቡ ተወካይ የሆኑት እና በአሁኑ ጊዜ ጫካ መግባታቸውን የገለጹት አንድ አርሶአደር ገልጸዋል።
የመንግስት ባለስልጣናት በዛሬው እለት 30 የሚሆኑ እስረኞችን ከመተማ አውጥተው ወደ ሌላ ቦታዎች ለመውሰድ ሲሞክሩ፣ የአካባቢው ህዝብ አናስወስድም በማለት ተቃውሞውን አሰምቷል። ይህን ዘገባ እሳከጠናከርንበት ጊዜ ድረስ በህዝቡና በመንግስት ባለስልጣናት መካከል የተፈጠረው ውዝግብ በምን ሁኔታ እንደተቋጨ ለማወቅ አልተቻለም።
በአሁኑ ሰአት ሽፍትነትን መርጠናል፣ ከማንኛውም የመንግስት ሀይል የሚመጣውን ጥቃት ለመመከት ተዘጋጅተናል” በማለት  አስተባባሪው ገልጸዋል ።
ከተያዙት መካከል ከህዝቡ ጋር አብራችሁ መንግስትን ወግታችሁዋል የተባሉ  ጥጋቡ አቸነፍ የተባለ የመተማ ወረዳ የሚኒሻ ኮማንደር እና ውብሸት የተባለ የቀበሌ ሹምም በቁጥጥር ስር ውለዋል።
መንግስት መሬት በብሎክ የመከፋፈል አሰራር ተግባራዊ ማድረጉን ተከትሎ  የአካባቢው ባለስልጣናት ለም የሆኑ መሬቶችን ለባለሀብቶች እና ለእነሱ ቀረቤታ ላላቸው ሰዎች ሰጥተዋል በሚል ተቃውሞ መቀስቀሱ ይታወቃል ።
የአካባቢውን ባለስልጣናትን ለማነጋገር ተደጋጋሚ ሙከራ ብናደርግም አልተሳካም።

የአሜሪካ ኮንግረስ አባላት በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ዙሪያ ውይይት አደረገ

ሰኔ ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:- የአፍሪካ ጉዳዮች ሃላፊ ዶናልድ ያማማቶ፣ በአፍሪካ የዩሴ አይ ዲ ዳይሬክተር ኤሪል ጋስት፣ በአፍሪካ  ጉዳዮች ተመራማሪ  ዶ/ር ፒተር ፓሀም፣ የግንቦት7 ሊቀመንበር ዶ.ር ብርሀኑ ነጋ ፣ ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዳይሬክተር  አቶ ኦባንግ ሜቶና የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የአሜሪካ ተወካይ  ሚስተር አዶቲ አኪዌ እና ሌሎችም ታዋቂ ምሁራን ፖለቲከኞች የተሳተፉበት ውይይት የተካሄደ ሲሆን፣ አምባሳደር ያማማቶ እና ዶ/ር ጋስት ኢትዮጵያ በመስቀለኛ መንገድ ላይ እንድምትገኝ ገልጸዋል።
የኢህአዴግ መንግስት የኢኮኖሚ እድገት ማምጣቱን የገለጹት አምባሳደር ያማማቶና ሚስተር ጋስ፣  በሌላ በኩል ግን መንግስት ከፍተኛ የሆነ የሰብአዊ መብቶች ረገጣ በመፈጸሙ የአገሪቱን መጻኢ እድል አደጋ ላይ ጥሎታል ብለዋል።
ዶ/ር ብርሀኑ ነጋ፣ አቶ ኦባንግ ሜቶ እና ሚ/ር አክዌ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በዝርዝር ያቀረቡ ሲሆን፣ ዶ/ር ብርሀኑ ከአቶ መለስ ሞት በሁዋላ ያለው የኢትዮጵያ ሁኔታ በመለስ ጊዜ እንደነበረው ምናልባትም ከዚያ በበሳ ሁኔታ አስከፊ እየሆነ መሄዱን ገልጸዋል። የኢህአዴግ ባለስልጣናት ከፍተኛ ገንዘብ የዘረፉ እና ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን የፈጸሙ በመሆናቸው እንጠየቃለን በሚል ፍርሀት ስልጣን በቀላሉ ለመልቀቅ እንደማይፈልጉ ዶ/ር ብርሀኑ አክለዋል።
ዶ/ር ብርሀኑ መንግስትን በሀይል ለማውረድ የሚንቀሳቀሱ ሀይሎች እየተጠናከሩ መሄዳቸውን፣ አገሪቱ ወደ አልተፈለገ ግጭት ከማምራቷ በፊት የአሜሪካ መንግስት አሁን የሚከተለውን ፖሊስ ቆም ብሎ እንዲፈትሽ አሳስበዋል።
አቶ ኦባንግ ሜቶ በበኩላቸው ኢትዮጵያውያን አሜሪካ ነጻ ታወጣናለች ብለው እንደማይጠብቁ፣ የራሳቸውን መብት በራሳቸው ለማስከበር እንደሚችሉ ገልጸው፣ አሜሪካ ከአምባገነኑና ዘረኛው የህወሀት መንግስት ጋር የምታደርገውን ግንኙነት እንደገና እንድትፈትሽ ጠይቀዋል።
የውይይቱ ሊቀመንበር የተከበሩ ሚስተር ክሪስ ስሚዝ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የሰብአዊ መብቶች ጥሰት በዝርዝር ለተሰብሳቢው አቅርበዋል።

ESAT Daily News - Amsterdam June 20, 2013 Ethiopia


Monday, June 17, 2013

ከእሁድ እስከ እሁድ

(የሳምንቱ አጫጭር ዜናዎች)

post meles



ኢትዮጵያ ከመለስ ሞት በኋላ!!
አቶ መለስ ከሞቱ በኋላ ኢትዮጵያ ውስጥ ስላለው የፖለቲካ ሁኔታ የአሜሪካ ኮንግረስ የውጪ ጉዳዮች ኮሚቴ የተለያዩ ተናጋሪዎችን ጋብዟል። እኤአ ሰኔ 20፤2013 ቀን በሚካሄደው የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ የሚሰማበት ውይይት ከኢትዮጵያ ሁለት ተናጋሪዎች ተጋብዘዋል።
ታዋቂው የመብት ተሟጋች፣ በከፍተኛ ደረጃ የኢትዮጵያዊያንን ድጋፍ እያገኙ ያሉትና   በውጭው ዓለም የዲፕሎማሲና የፖለቲካ መስመር ተሰሚነታቸው እያደገ የመጣው የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ ፣ እንዲሁም በበክኔል ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ ተባባሪ ፕሮፌሰር የሆኑት ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ በዕለቱ ተናጋሪ መሆናቸውን ስብሰባውን ያዘጋጁት ክፍሎች ይፋ አድርገዋል።
ከሁለቱ ኢትዮጵያዊያን በተጨማሪ  ቀደም ሲል በኢትዮጵያ የአሜሪካን አምባሳደር የነበሩትና በአሁኑ ወቅት የአሜሪካ የአፍሪካ ጉዳዮች ተጠባባቂ  ጸሐፊ ሆነው እየሰሩ ያሉት ዶናልድ ያማማቶ፣  የአሜሪካ የዓለምአቀፍ የልማት ተራድዖ የአፍሪካ ቢሮ ረዳት አስተዳዳሪ ኤሪል ጋስትና የማይክል አንሳሪ የአፍሪካ ተቋም ዳይሬክተር ዶ/ር ፒተር ፓሃም ንግግር ያቀርባሉ። ምክከሩ በቀጥታ ስርጭት የሚተላለፍ ሲሆን የውይይቱ ዋና ጉዳይ ስለ ኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታና ከመለስ ሞት በበኋላ በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት አያያዝና የዲሞክራሲ አተገባበር ዙሪያ ጭብጥ የሚያዝበት ነው። (የጥሪው ደብዳቤ መሉ ቃል እንዲህ ይነበባል)
SUBCOMMITTEE HEARING NOTICE
COMMITTEE ON FOREIGN AFFAIRS
Subcommittee on Africa, Global Health, Global Human Rights, and International Organizations Christopher H. Smith (R-NJ), Chairman
TO: MEMBERS OF THE COMMITTEE ON FOREIGN AFFAIRS
You are respectfully requested to attend an OPEN hearing of the Committee on Foreign Affairs, to be held by the Subcommittee on Africa, Global Health, Global Human Rights, and International Organizations in Room 2172 of the
Rayburn House Office Building (and available live on the Committee website atwww.foreignaffairs.house.gov):
DATE: Thursday, June 20, 2013
TIME: 10:00 a.m.
SUBJECT: Ethiopia After Meles: The Future of Democracy and Human Rights
WITNESSES: Panel I
The Honorable Donald Y. Yamamoto
Acting Assistant Secretary of State
Bureau of African Affairs
U.S. Department of State
The Honorable Earl W. Gast
Assistant Administrator
Bureau for Africa
U.S. Agency for International Development
Panel II
 Berhanu Nega, Ph.D.
Associate Professor of Economics
Bucknell University
 J. Peter Pham, Ph.D.
Director
Michael S. Ansari Africa Center
Atlantic Council
Mr. Obang Metho
Executive Director
Solidarity Movement for a New Ethiopia
ግብፅ የያዘችው አቋም ተቀባይነት የለውም
ግብፅ የታላቁ የህዳሴ ግድብ ጉዳይ ለውስጥ የፖለቲካ ችግሯ መፍቻነት እያዋለችው መሆኑን የመንግስት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ሚኒስትር  በረከት ስምኦን ገለፁ፡፡ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ አቶ አለማየሁ ተገኑ በበኩላቸው ግብፅ የግድቡን የሃይል ማመንጨት አቅም መቀነስ እንደመፍትሔ ማቅረቧ ተቀባይነት የለውም ብለዋል፡፡
abay1የመንግስት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ሚኒስትርና የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ፅ/ቤት ዳይሬክተር አቶ በረከት ስሞኦን ግብፅ ለውስጥ የፖለቲካ ችግሯ መፍቻነት እያዋለችው መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የግንባታ ሂደቱ 22 ነጥብ 5 በመቶ የደረሰውና በተያዘው ዓመት 26 በመቶ ስራው እንደሚጠናቀቅ የሚጠበቀው የህዳሴው ግድብን አስመልክቶ አንዳንድ የተቃዋሚ ፓርቲዎች የያዙት አቋም ትክክል አለመሆኑንም ሚኒስትር በረከት ተናግረዋል፡፡
ሚኒስትር በረከት አያይዘው እንደገለፁት ግብፅ ጉዳዩን የውስጥ የፖለቲካ ችግሯን ለማርገብ እየተጠቀመችበት መሆኑን ጠቅሰው ሀገሪቱ የጦርነት አማራጭ የተዘጋ አይደለም ትበል እንጂ ወደዚህ ተግባር ትገባለች ተብሎ አይጠበቅም ብለዋል፡፡
የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር አለማየሁ ተገኑ በበኩላቸው የጦርነት አማራጭ እንደማያዋጣ የተገነዘበ የሚመስለው የግብፅ መንግስት የህዳሴን ግድብ የማመንጨት አቅም፣ የሚይዘውን የውሃ መጠንና ከፍታ እንዲቀንስ የሚያነሳው የመፍትሔ ሃሳብ ተቀባይነት የለውም ብለዋል፡፡
የመንግስት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ሚኒስትርና የታላቁ ህዳሴ ግድብ የህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ፅ/ቤት ዳይሬክተር በረከት ስሞኦን እና የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር አለማየሁ ተገኑ በተገኙበት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ሬድዮና በ ኤፍ ኤም አዲስ 97.1 በህዳሴው ግድብ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙርያ ባተኮረው  የቀጥታ ውይይት ላይ በአገር ውስጥና ውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እያሳዩት ያሉትን ግድቡን የመገንባት ቁርጠኝነትና ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ሃላፊዎቹ ጥሪ አቀርበዋል፡፡ (ምንጭ፤ ኢሬቴድ)
ፓርላማው የቅኝ ግዛት ዘመን ውል የሚተካ አዲስ ህግ አፀደቀ
አሥራ አንዱ የአባይ ተፋሰስ ሃገሮች ሩዋንዳ፣ ቡሩንዲ፣ ኮንጎ ፣ ታንዛኒያ፣ ኬንያ፣ ዩጋንዳ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሱዳን፣ ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ግብፅ ናቸው፡፡ የተፋሰሱ አገራት በተመለከቱበት ካርታ ላይ ደቡብ ሱዳን አልተካተተችም። ካርታው ሲሰራ ደ/ሱዳን በወቅቱ ነጻ አገር አልነበረችም ነበር።
nile_basin_countries
የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ33ተኛው መደበኛ ስብሰባው ከመከረባቸው አምስት ጉዳዮች አንዱ የሆነውን የአባይ ተፋሰስ የትብብር ስምምነት ረቂቅ አዋጅ እንዳፀደቀ የምክር ቤቱ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ አያና ከበደ ለቪኦኤ ገልፀዋል።
ስምምነቱ አባይን በጋራና በፍትሃዊ መንገድ ለመጠቀም በተፋሰሱ አባላት አገሮች ካሁን ቀደም ኢንቴቤ-ዩጋንዳ ውስጥ የተፈረመ መሆኑ ይታወቃል።
ከኢትዮጵያ በስተቀር አምስቱ አገሮች ማለትም የርዋንዳ፣ የታንዛኒያ፣ የዩጋንዳ፣ የኬንያና የቡሩንዲ ፓርላማዎች ቀደም ብለው ውሉን ያፀደቁት መሆኑን የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያው ተናግረዋል።
የኢንቴቤ ስምምነት እየተባለ የሚጠራው ውል ቅኝ ገዢ በነበረችው ታላቋ ብሪታኒያ በአውሮፓ የዘመን አቆጣጠር በ1929 ዓ.ም የተረቀቀና በናይል ወንዝ አጠቃቀም ላይ ከተፋሰስ አገሮች ይልቅ ለግብፅ ሙሉ መብት የሚሰጠውን ውል የሚተካ መሆኑ ይታወቃል።
ውሉ ዛሬ በኢትዮጵያ የተወካዮች ምክር ቤት መፅደቁ ሰሞኑን በግብፅና በኢትዮጵያ መካከል በአባይ ወንዝ አጠቃቀም ዙሪያ ከሚካሄደው ውዝግብ ጋር ግንኙነት እንደሌለው የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያው ተናግረዋል፡፡(ምንጭ የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ)
በአባይ ግድብ ዙሪያ ከፍተኛ ጥበቃ ማድረግ ተጀመረ
ለኢሳት የደረሰው የደህንነት መረጃ እንዳመለከተው ከፍተኛ ወጪ የወጣባቸው ቻይና እና ሩሲያ ሰራሽ ራዳሮች ሰሞኑን በአካባቢው ተተክለዋል።
radarመንግስት ማንኛውንም አይነት ድንገተኛ የአየር ወይም የሰርጎ ገቦች ጥቃት ለመከላከል ዘመናዊ ራዳሮችን ከመትከል በተጨማሪ የተወሰኑ የአጋዚ ክፍለ ጦር አባላት በአስችኳይ ወደ አካባቢው እንዲንቀሳቀሱ አድርጓል። በፌደራል ፖሊስ ሲደረግ የነበረው ጥበቃ በመከላከያ ሰራዊት አባላት እንዲጠናከር ያደረገው መንግስት ፣ በሻለቃ አበራ ወረታው አዛዥነት የሚመራው የምእራብ እዝ የ44ኛ ዳሎል ክፍለ ጦር አራተኛ ሪጂመንት በቤንሻንጉል እንዲቀመጥ ተወስኗል።
በደቡብ ሱዳን ያለው ጦር የአቅም ግንባታ ስልጠና እንዲያገኝም አብዩታዊ ዴሞክራሲ እና ወታደራዊ አመራር የሚል ርእስ ያዘለ የመወያያ ጽሁፍ ተዘጋጅቶ በ ስልጠና ዋና መምሪያ ሌ/ጄኔራል ታደሰ ወረደ የሚመራ ቡድን ወደ አብየ አቅንቷል፡፡
ኢሳት የደረሱትን ሙሉ ወታደራዊ የደህንነት መረጃዎች ለአገር ደህንነት ሲባል ይፋ ከማውጣት መቆጠቡን ለመግለጽ ይወዳል። የኮሚኒኬሽን ሚኒስትሩ አቶ በረከት ስምኦን ኢትዮጵያ ምንም አይነት ወታደራዊ ዝግጅት እያደረገች አይደለም በማለት ሰሞኑን መግለጫ ቢሰጡም፣ ለኢሳት የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው ከሆነ ግን ኢትዮጵያ ግድቡን ከጥቃት ለመከላከል እንቅስቃሴዎችን ጀምራለች።
በሌላ ዜና ደግሞ የግብጽ መንግስት ኢትዮጵያ በግድቡ ላይ የማሸሻያ እርምጃ እንድታደርግ መጠየቁ ታውቋል። የግብጽ መንግስት ያቀረበው ጥያቄ የግድቡ ከፍታ ከነበረበት 145 ሜትር ወደ 100 ሜትር ዝቅ እንዲል፣ 74 ቢሊዩን ሜትር ኩብ ውሃ እንደሚይዝ የሚጠበቀው አዲሱ ሀይቅ   ከ 32 እስከ   40 ቢሊዩን ሜትር ኩብ ውሀ እንዲቀንስ መጠየቁን የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡ የሀይል አቅርቦቱም ወደ 3000 ሜጋ ዋት እንዲቀንስ የግብጽ መንግስት ጥያቄ አቅርቧል። (ምንጭ፤ ሰኔ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና)
ለአማራው መፈናቀል ተጠያቂ የተባሉ 2 የቤኒሻንጉል ም/ቤት አባላት ያለመከሰስ መብት ተነሳ
የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ምክር ቤት ትናት ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ በክልሉ ነባር የአማራ ብሄረሰብ ተወላጆች መፈናቀል ምክንያት ናቸው ያላቸውን 2 የምክር ቤት አባላትን ያለ መከሰስ መብት አነሳ።
benishangulያለ መከሰስ መብታቸው ተነስቶ በቁጥጥር ስር ውለው በህግ እንዲጠየቁ የተደረገው በክልሉ ከማሺ ዞን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መለተጊ ቦጋለና የመንግስት ኮሙኒኬሽን መምሪያ ሃላፊው አቶ ገርቢ በጊዜው ናቸው።
እነዚህ አመራሮች የክልሉ መንግስትና ፓርቲው በማያውቀው ሁኔታ በዞኑ ያሶ ወረዳ ነባር የአማራ ብሄረሰብ ተወላጆችን እንዲፈናቀሉ ማድረጋቸው በመረጃ በመረጋገጡ ነው እርምጃው የተወሰደባቸው።
በዚህ የማፈናቀሉ ተግባር ተሰማርተዋል ተብለው የተጠረጠሩ 18 የሚደርሱ ከቀበሌ እስከ ዞን የሚገኙ አመራሮች ጉዳያቸው እየተጣራም ይገኛል።
የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ አቶ ይስሀቅ አብዱልቃድር ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳሉት ፥ የክልሉ መንግስት ጉዳዩን በማጣራት ባአሁኑ ጊዜ ተፈናቃዮች ተረጋግተው ወደቀያቸው ተመልሰው መደበኛ ኑሮዋቸውን እያከናወኑ ነው። አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 8 ፣ 2005 (ኤፍ.ቢ.ሲ)
“ዋነኛው የእንግልት ሰለባ አህያው ነው”
ፖሊስና እርምጃው በግንቦት 30 እትሙ በምስራቅ ሸዋ መቂ ከተማ ውስጥ አንድ ግለሰብ ጅብ አጥምዶ ፤ ከማጥመዱም በአህያ በሚጎተት ጋሪ ጭኖ ሲዘዋወር በመገኘቱ ‹‹እንሰሳትን በማንገላታት›› ክስ መታሰሩን ነግሮናል፡፡
donkeyሰውየው ‹‹ጅቡን ከነነፍሱ ያጠመድኩት እየተፋፋመ ያለውን የፀረ ሙስና ትግል መቀላቀሌን ለማሳየት ነው›› ካላለ በስተቀር ትንሽ በቁጥጥር ስር ሳይቆይ አይቀርም፡፡
‹‹እንሰሳትን በማንገላታት›› የሚለው ክስ እንግልቱ በየትኛው እንሰሳ ላይ እንደተፈፀመ አጥርቶ ባይገልፅም፤ እንደኔ በዚህ ጉዳይ ዋነኛው የእንግልት ሰለባ አህያው ነው፡፡
መደበኛ የሸክም እንግልቱን ተዉት፡፡ ይህ አህያ ታሪካዊ አዳኙን/ ጠላቱን ከነነፍሱ ተሸክሞ ሲዞር ‹‹ካሁን አሁን ዘነጠለኝ›› እያለ መሳቀቁ ብቻ ከባድ የስነልቦና እንግልት አይደለም?
ይህን ጅቦችን ተሸክመው ሲሄዱ የኖሩ ምስኪን አህዮች ሁሉ ጠንቅቀው ያውቃሉ፡፡
ወጣም ወረደ፤ ክሱ ጅቡን የእንግልቱ ተጠቂ አድርጎ ያቀረበ መሆኑን ከሰማን ‹፣ድሮም የኛ ሕግ ለጅቦች ያዳላል›› ማለታችን የማይቀር ነው፡፡
(ምንጭ፤ ነቆራ እና ሌሎችም ወጎች ከሕይወት እምሻው ጋር – Hiwot Emishaw)

ESAT Daily News - Amsterdam June 17, 2013 Ethiopia


ከውስጥ በአምባገነን ስርዓት የታፈነችና ከውጭ ዙሪያዋን በጠላት የተከበበች አገር



“ወንዝም ገነትን ያጠጣ ዘንድ ከዔድን ይወጣ ነበር፤ ከዚያም ለአራት ክፍል ይከፈል ነበር፡፡
የአንደኛው ወንዝ ስም ፊሶን ነው፤ እርሱም ወርቅ የሚገኝበትን የኤውላጥ ምድርን ይከብባል፤ የዚያም ምድር ወርቅ ጥሩ ነው፤
ከዚያም ሉልና የከበረ ድንጋይ ይገኛል፡፡
የሁለተኛው ወንዝ ስም ግዮን ነው እርሱም የኢትዮጵያን ምድር ሁሉ ይከብባል…” ይላል መጽሓፍ ቅዱስ በኦሪት ዘፍጥረት 2፡10-13፡፡
ግዮን የተባለው አባይ ነው፤ የአባይ ምንጭ ደግሞ ኢትዮጵያ ናት፡፡ ብዙ ሰዎች የአባይ መነሻ ጣና ሐይቅ እንደሆነ ያምናሉ፡፡ ነገር ግን የአባይ ትክክለኛ መነሻ በምዕራብ ጎጃም ሰከላ ወረዳ ውስጥ የመትገኘው ፈለገ ግዮን ናት፡፡ አባይ ፈልቆ ከምንጭነት ወደ ጎርፍነት በመቀየር ከዚያም ነብስ ዘርቶ ወደ ጅረትነት ከፍ የሚልበትን የተቀነበበ አነስተኛ ጉድጓድ ለአንድ የኃይማኖት አባት ለማሳየት “አባ እይ” ከሚል የሌላ ሰው ንግግር አባይ የሚለውን ስያሜም እንዳገኘ በአፈ ታሪክ በሰፊው ይነገራል፡፡ የአባይን ምንጭ አስሶ ለመጀመሪያ ጊዜ ያገኘው ጀምስ ብሩስ የተባለ አውሮፓዊ እንደሆነ ይታመናል፡፡
አባይ ዘይት ሆኖ በጣና ላይ ጋልቦበት ኢትዮጵያን ልክ እንደ መቀነት ወገቧን ዞሮ ድንበሯን በመበጠስ ከድቷት ከምድሯ በመውጣት ዜግነቱንም ስሙንም ይቀይራል፡፡ ብሉ ናይል ተብሎ ከቪክቶሪያ ሐይቅ ከሚነሳው ነጭ አባይ ጋር ካርቱም ላይ በመደባለቅ አስር አገራትን አቆራርጦ በርዝመቱ በዓለም አንደኛ በመሆን ሜዲትራኒያን ባህር ይገባል፡፡
ከሰማንያ በመቶ በላይ የሚሆነውን የውሃ መጠን ከኢትዮጵያ የሚያገኘው ናይል ከሚያልፍባቸው አገሮች ግብፅና ሱዳን ይገኙባቸዋል፡፡ እነዚህ ሁለት አገሮች ኢትዮጵያ ወደ እነሱ ምድር የሚፈስ ወንዝ መነሻ ሆና በመፈጠሯ ምክንያት ብቻ በጠላትነት ፈርጀዋት ለረጅም ዘመናት ኖረዋል፡፡ በተለይም ግብፅ ይህችን ስልጣኔን ከዓለም ሁሉ ቀድማ ጀምራ ኃያል የነበረችና ዛሬ ጭራ የሆነች የድሆችና የመከረኞች ምድር ኢትዮጵያ የወደፊት የመኖርና ያለመኖር ህልውናዋ ጠንቅና ስጋቷ ምንጭ እንደሆነች አድርጋ ስትመለከታት አያሌ ዘመናት ነጉደዋል፡፡ ግብፅ ኢትዮጵያን ያለኃጥያቷ በጠላትነት ዓይን ትከታተላት ብቻ አልነበረም፡፡ ከኢትዮጵያ በምታገኘው ውሃ ከተሞላው ናስር ሐይቋ ወደ ሰማየ ሰማያት በምትለቀው የመሰርይነትና የበቀል ትነት በኢትዮጵያ አድማስ ላይ ያጠላውን ጥቁር ደመና በመበከል በኢትዮጵያ ምድር ላይ አሲድ እያዘነበች ህዝቦቿን ስታነፍራቸው፣ ቡቃያዎቿን አቀጭጫ ስታጠፋቸው፣ ወንዞቿንና ሐይቆቿን ወደ መርዝ ፈሳሽነት ስትቀይራቸው ከተፈጠረች ጀምሮ እስካሁን ድረስ አለች፡፡ አባይን ከነምንጩ በቁጥጥር ስር በማዋል በምስራቅ አፍሪካ ብቸኛዋ ኃያል አገር ለመሆን ካላት ቅዠት የተነሳ በተደጋጋሚ ኢትዮጵያን ወርራለች፡፡ ነገር ግን ክብር ለቀደሙት ጀግኖች አባቶቻችን ይሁንና ህልሟ እንደ ጉም በንኖ ቀርቷል፡፡
አፄ ዮሃንስ ግብፅ የምትፈፅመው ማባሪያ የሌለው ግፍና በደል ሲያንገፈግፋቸው ለእንግሊዝ ንግስት ለንግስት ቪክቶሪያ በፃፉት ምሬትን ያዘለ ደብዳቤ ውስጥ “…በአገሬ ምድር ሰላምን አምጥቼ ከህዝቤ ጋር ወደ ልማት ልዞር ባሰብኩበት ወቅት መሃመድ ባሻ ሳልደርስበት ጠብ እየጫረ አላስቀምጠኝ ብሏል፤ እኔ ጦርነት መግጠም አልፈለግም እባክዎን ንግስት ሆይ ተው ይበሉልኝ…” የሚል ሀሳብ ይገኝበታል፡፡
ከመሃመድ ፓሻ እስከ ከዲቭ ኢስማኤል ፓሻ፣ ከጀማል አብደልናስር እስከ አንዋር ሳዳት፣ ከሙባረክ እስከ አሁኑ ሙርሲ የሚገኙት የግብፅ መሪዎች በጠቅላላ ኢትዮጵያን አንድም ቀን ተኝተውላት አያውቁም፡፡ ጉልበቷን ቄጠማ አድርገው በማሽመድመድ እንዲህ አቅም እንዳጠራት ቀጭጫ እንድትቀር አድርገዋታል፡፡ ከገዛ ምድሯ የሚመነጨውን የአባይ ውሃ “በእፍኝሽ እንኳን ጨልፈሽ ብትጎነጭ እናጠፋሻለን” እያሉ ሲያስፈራሯት ኖረዋል፡፡
ግብፅ ዋነኛዋ የኢትዮጵያ የውስጥ ሰላም እባጭ ህመም ነቀርሳ ናት፡፡ ለዚህ ማስረጃ ወደ ኋላ ተጉዞ ዘመናትን መሻገር አያስፈልግም፤ ወያኔና ሻዕብያ በእሷ የጦር መሳሪያ እየታጠቁ የገዛ አገራቸውን ሲወጉ እንደነበር ብቻ መጥቀሱ በቂ ነው፡፡ በዚህ ኢትዮጵያ ከእርስበርስ ጦርነት ተላቅቃ የሰላም አየር እንዳትተነፍስና ፊቷን ወደ ልማት እንዳታዞር በማድረጉ ሴራ ሱዳንም አለችበት፡፡ በደርግ ጊዜ ህወሓት ካርቱም ውስጥ ጽህፈት ቤት ነበረው፡፡ ዋና መግቢያና መውጫ በሩም ሱዳን ነበረች፡፡ ጀብሃን ያደራጀችው ግብፅ ናት፡፡
ግብፅም ሆነች ሱዳን በየጊዜው የኢትዮጵያን ጨቋኝ የአገዛዝ ስርዓት የሚቃወሙትን ቡድኖች የሚያስታጥቁት የኢትዮጵያን ህዝብ ነፃ ለማውጣት አይደለም አገሪቱን በጦርነት ለማዳከምና የኢኮኖሚ አቅም ለማሳጣት እንጂ፡፡ ምክንያቱም ኢትዮጵያ ከጦርነት ወጥታ እፎይ የምትልበት እድል ካገኘች በማንኛውም ጊዜ አባይን ገድባ ለልማት እንደምታውለው ጠንቅቀው ያውቃሉና፡፡
በእንድ አገር ላይ የተንሰራፋን አፋኝ ስርዓት ለማስወገድ ከሌላ አገር መንግስት እርዳታ መለመን በየትኛውም አለም ካሁን በፊት የነበረና ወደፊትም የሚኖር ነው፤ ለዚያች የአፈና አገዛዝ ለነገሰባት አገር ጠላቶች በመሳሪያነት ማገልገል ግን አገርንና ወገንን መካድ ነው፡፡ ግብፅ ደደቢት በረሃ ክሳድ ግመል ለሸፈተው አስገንጣይ ወንበዴ ህወሓት የደርግን ስርዓት እንዲፋለም ላዩ በማር የተቀባ የሬት ስንቅ ስታቀብለው ኖረች፡፡ ወያኔ ማሩን እየላሰ ኃይልና ሙቀት አግኝቶ ለ17 ዓመታት በመዋጋት አሸንፎ ኢትዮጵያን መልሶ በጠመንጃ አፍኖ ለ22 ዓመታት ለመግዛት በቃ፡፡ ይኸውና አሁን ደደቢት በረሃ ውስጥ እያለ ጀምሮ ይልሰው የነበረው ማሩ አልቆበት ሬቱ ብቻ ቀርቶት እሱን እየላሰ ይጎመዝዘው ይዟል፡፡
ወያኔ የደቂቃ የደስታ እሸትን ከሴት ብልት ማሳ ላይ ለመቅጠፍ ብሎ ከኤች.አይ.ቪ ህመምተኛ ጋር ልቅ የሆነ ግብረ ስጋ በመፈፀም የዓመታት ህይወቱን እንደሚቀጥፍ ስሜቱን ፈፅሞ መግራት የማይቻለው ቅንዝራም ጎረምሳ አይነት ነው፡፡ ዛሬ አንድ ተግባር ሲፈፅም ነገ ሊያስከትል የሚችለው ውጤት ምን ሊሆን እንደሚችል አያጤንም፡፡ ሳህል በረሃ ውስጥ የመሸገው የሻዕብያ ገንጣይ ወንበዴ ቡድን በአብዮታዊ ህዝባዊ ሰራዊት አከርካሪው ተሰብሮ እስከመጨረሻው ለመክሰም ሲቃረብ በአፉና ባፍንጫው ኦክስጂን ሰጥቶ የመጀመሪያ እርዳታ በማድረግ እስትንፋስ የሆነው ወያኔ ነው፡፡ ከዚያም አውራው መለስ ዜናዊ አገሬን ገንጥሉልኝ ብሎ ለተባበሩት መንግስታት በፃፈው ደብዳቤ ኤርትራ ከኢትዮጵያ ተቆርሳ ራሷን የቻለች በሻዕብያ የምትገዛ አገር ሆነች፡፡ በኋላ ሻዕብያ ለራሱ ለወያኔ የቂጥ እከክ ሆነበት፡፡ በእርግጥ ምንጊዜም ቢሆን የችግሩ ገፈት ቀማሽ የኢትዮጵያ ህዝብ ነው፡፡ በጦርነቱ በድህነት ቤቱ ያሳደጋቸውን መቶ ሺህ ልጆቹን በከንቱ የገበረው እሱ እንጂ ወያኔ ኢህአዴግ ምንም የጎደለበት ነገር የለም፡፡ በጦርነቱ ጊዜ ሰራዊቱ ኤርትራን እስከ ቀይ ባህር የመቆጣጠር ፍላጎት ነበረው፡፡ በመረብ በኩል ለፍልሚያ የተሰለፈው ሰራዊት ተሰኔ ገብቶ ከአስመራ የሚያገናኘውን አውራ ጎዳና ይዞ በታላቅ ወኔና ጉጉት ወደ ፊት መገሰገስ ሲጀምር ቁምና ቀኝ ኋላ ዙር ተባለ፡፡ በቡሬ ግንባር በኩል የተሰማራው ጦርም አንዲሁ የአሰብን መብራት አሻግሮ እያየ ያለፍላጎቱ ተመለሰ፡፡ ይህ ሁሉ የሆነው እንግዲህ ከኢትዮጵያ ይልቅ ለኤርትራ በሚቆረቆረውና “ባለራዕይ” በሚባለው መለስ ዜናዊ ብቻ ቀጭን ትዕዛዝ ነው፡፡ ይኸውና ዛሬ ኤርትራ ግብፅ ኢትዮጵያን ለማጥቃት የምትጠቀምባት ስትራቴጂክ ቦታ እንደሆነች በሰፊው እየተነገረ ነው፡፡ የመለስ ወንድም ኢሳያስ ደግሞ ይህን ከማድረግ ወደ ኋላ የሚል አይመስልም፡፡ ሻዕብያ አሰብና ምጽዋን ሲይዝ አንድ የኢትዮጵያ ጦር ጄነራል “ከእንግዲህ ወዲህ አገሬ ኢትዮጵያ የሬሳ ሳጥን ሆነች” ብሎ ነበር፡፡ ጀነራሉ ልክ ነበር እናት ኢትዮጵያ ባሁኑ ጊዜ ከሬሳ ሳጥን ውስጥ ገብታ የተጋደመች አሳዛኝ አገር ናት፡፡ የሬሳ ሳጥን በርና መስኮት የለውም፡፡ ይህን ያደረገው ደግሞ ወያኔ ነው፡፡
እናም ይሄ ለጠላት አገር በመሳሪያነት የማገልገሉ ጉዳይ መቼ ነው የሚቆመው? የግብፅ መሪዎች እኮ ኢትዮጵያን በማተራመስ የግድቡን ስራ እናስተጓጉለዋለን እያሉ ባደባባይ የሚናገሩት የኢትዮጵያን ጠመንጃ ያነሱ ተቃዋሚ ቡድኖች ላዩ ማር የተቀባ ሬት የመቀበልን የቆየ ባህል ከህወሓት ስለሚያውቁት ነው፡፡ ከንጉሱ ስርዓት ጋር የተኳረፉ መኳንቶችና ግለሰቦች ከጣልያን ጋር አብረው ወገናቸው የሆነውን የኢትዮጵያን አርበኛ አንደወጉት፤ ከደርግ ጋር የተጣሉት ኢህአፓዎችና ሻዕብያዎች ከሶማሊያ ጎን ተሰልፈው የእናታቸውን ልጅ እንደገደሉት፤ ዛሬም ቢሆን የግብፅን ላዩ ማር የተቀባ ሬት ተመፅውተው እየላሱ በመሳሪያነት ሊያገለግሉ የሚችሉ ከወያኔ ኢህአዴግ ጋር ተኳርፈው ጫካ የገቡ ቡድኖች ሊኖሩ አይችሉም ብሎ ለመደምደም ያዳግታል፡፡
ግብፅ ኢትዮጵያን ነፃ እናወጣለን በማለት ጠመንጃ ታጥቀው ጫካ ለገቡ “ነፃነትን የማያውቁ ነፃ አውጪዎች” ላዩ ማር የተቀባ ሬት ስንቅ ከማቀበሏ በተጓዳኝ የየብስ የባህርና የአየር ተዋጊ ሠራዊቷን በሚገባ ስትገነባ፣ ጡንቻውን ስታፈረጥም፣ በትጥቅ ስታዘምንና ስታገዝፍ ነው የኖረችው፡፡ የኢትዮጵያ ገዥዎች ግን በተቃራኒው ትራሳቸውን ከፍ አድርገው ተኝተው ነበር፡፡ በተለይ ወያኔ ኢህአዴግ ከንጉሱ ዘመን ጀምሮ ስንትና ስንት አንጡራ ሀብት ፈሶበት የተገነባውን የኢትዮጵያ ሠራዊት የደርግ ኢሠፓ በማለት በትኖ የአገሪቱን ወታደራዊ መሰረት በማፈራረስ ያለአለኝታ እርቃኗን አስቀራት፡፡ የአገሪቱን በጠላት ቀለበት ውስጥ የመገኘት ጉዳይ ወደ ጎን በመተው የራሱን ስልጣን ብቻ ለማራዘም ሲል ራሱ ያደራጀውን ሰራዊትም የትግርኛ ቋንቋ የማይናገሩትን በመመንጠር ባብዛኛው የአንድ ብሄር ጦር ብቻ አድርጎታል፡፡
ወያኔ ኢህአዴግ የኢትዮጵያን ህዝብ ረግጦ በጠመንጃ የሚገዛበትን ወታደር /አንደ አግአዚ ኮማንዶና ፌደራል ፖሊስ ዓይነት/ በደንብ ሲገነባና በትጥቅ ሲያደራጅ የአገሪቱን የውጭ ጠላቶች ችላ ብሏቸው ቆይቷል፡፡ ኢትዮጵያ ዙሪያዋን በጠላት የታጠረች አገር መሆኗን ግጥም አድርጎ እያወቀ 22 ዓመታትን በስልጣን ሲያሳልፍ በወታደራዊ ሳይንስ መስኩ አንድ እርምጃ እንኳን አልተራመደም፡፡ አንዴውም የአገሪቱ መከላከያ ተቋም በንግድ ስራ ላይ ተሰማርቶ ይገኛል፡፡
በተጨማሪም ወያኔ ኢህአዴግ የተራቀቀ ወታደራዊ የእድገት ደረጃ እንደደረሰ ሁሉ የአገሪቱ የመከላከያ ኃይል ገና እንጭጭና የግብፅን የመጠቀ የጦር ቴክኖሎጂ የታጠቀ የየብስ፣ የባህርና የአየር ተዋጊ ሠራዊት ሙሉ በሙሉ መመከት የማይችል ሆኖ እያለ ርካሽ የፖለቲካ ትርፍ ማግበስበሻ ፕሮፓጋንዳ በሰፊው እያናፈሰ ይገኛል፡፡ “አባይን ልገድብ ነው” ጩኸት፤ “የህዳሴ ግድብ የመሰረት ድንጋይ ጣልኩ” ሌላ ጩኸት፤ “ አጨብጫቢዎቹ ሰልፍ ወጥተው በጩኸት ላይ ጩኸት፤ “ቦንድ ግዙ” ተጨማሪ ጩኸት፤ የህዳሴው ግድብ ልደት ክብረ በዓል ጩኸት፤ “አባይን ተፈጥሯዊ የመፍሰሻ አቅጣጫውን አስቀየርነው” ጩኸት… የማያባራ ጩኸት፡፡ በቃ አገሪቱን የጫጫታ ምድር አደረጋት፡፡ ግብፅ እኮ አስዋንና ናስርን ስትገድብ በዝምታ ነው የልቧን የፈፀመችው፡፡ የወያኔ ኢህአዴግን ጫጫታ ምንአመጣው? የሚጮህ ውሻ እኮ አይናከስም፡፡ ደግሞም ወጡ ሳይወጠወጥ ወስከምቢያው ምንአለ ነው የሚባለው፡፡ ባለፈው ጊዜ የተከበረው የመከላከያ ሰራዊት ቀንም ከባዶ የጉራ ፕሮፓጋንዳ ተለይቶ አይታይም፡፡ ሲሉ ሰምታ ዶሮ ሞተች ከጭስ ገብታ፡፡ ወያኔ ኢህአዴግ እንደለመደው ቆስቁሶ ሊያነደው የፈለገው የጦርት እሳት ያለ ይመስላል፡፡
ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም “ኢትዮጵያ ከየት ወደየት” በሚል ርዕስ በ1986 ዓ.ም በጻፉት መጽሓፍ ውስጥ “የኢትዮጵያ ታሪክ የጦርነት ታሪክ ነው…” የሚል ጠንከር ያለሀሳብ ሰፍሮ ይገኛል፡፡ እውነትም የጦርነትን ገፈት ያልጨለጡ የኢትዮጵያ ትውልዶች ከቶ ሊገኙ አይችሉም፡፡ ስለሆነም ኢትዮጵያ ከእንግዲህ ወዲህ በምንም መልኩ ከጦርነት እሳት ውስጥ ገብታ መንደድ የለባትም፡፡ የሰላም አንጂ የጦርነት አሸናፊ የለውም፡፡
ዓለም ከአንደኛው እጅግ ዘግናኝ የሆነና ምንም መፍትሄ ያላመጣ የዓለም ጦርነት ምንም ሳትማር ወደ ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ሰተት ብላ ገባች፡፡ በጀርመኑ የናዚ ሰራዊትና በሶቭዬቱ ቀይ ጦር መካከል በተደረገ ከባድ ፍልሚያ ስታሊን ግራድ ነደደች፤ ለንደንና በርሊን በቦምብ ተቀጠቀጡ፤ ፓሪስ በሞርታር ታረሰች፤ ፒርል ሀርቦር በሚግ ተወገረች፤ ሂሮሽማና እና ናጋሳኪ በ“little boy” እና “fat man” አተሚክ ቦምቦች ተመትተው እንደ ሰም በመቅለጥ ከምድረ ገፅ ጠፉ… በቃ ምድር በጠቅላላ ተናጠች፤ በሰው ልጆች በድን ተሞላች፤ ሚሊዮኖች አለቁ፤ የመጨረሻ ድምር ውጤቱ ግን ዜሮ ነበር፡፡ በዓለም ታሪክ ከጦርነት ያተረፈ ማንም አገርና ህዝብ የለም፡፡ ሰላም ለማምጣት በጎተራ የሞላ ትዕግስት ሰንቆ መንቀሳቀስ ያስፈልጋል፡፡ ከጦርነት ይልቅ ለኢትዮጵያም ሆነ ለግብፅ ህዝብ የሚበጀው ይህና ይህ ብቻ ስለሆነ፡፡ በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት እኮ ያሁሉ ወጣት ከረገፈ በኋላ መሪዎች በቀጥታ ለሰላም ድርድር ወደ አልጀርስ ነው የሄዱት፡፡ ምናለበት ያ የሰላም ድርድር ከጦርነቱ በፊት በሆነ ኖሮ መቶ ሺህ የድሃ ልጆቸ ባልሞቱ ነበር፡፡
የግብፅ መሪዎች ማንገራገር ዛሬ የተጀመረ አዲስ አይደለም፤ የተለመደና ለሺህዎች ዓመታት የዘለቀ ነው፡፡ ማንገራገርን እንደ “psychological warfare” እየተጠቀሙበት ነው፡፡ ነገር ግን ኢትዮጵያ ልክ እንደወትሮው መዘናጋት የለባትም፡፡ ወያኔ ኢህአዴግም ምንም አንኳን ቢረፍድበትም ከእንቅልፉ መንቃት አለበት፡፡
Egypt is a gift of Nile” የሚለውን የሄሮደተስ አባባል “Nile is only a gift of Egypt” በማለት ገልብጠው የተረዱት የሚመስሉት የልበ ደንዳናው ፈርኦን ሽንቶች ከማንገራገር አልፈው እንደለመዱት ከመጡብን ግን ምን እናደርጋለን አንደ ቀደሙት ጀግኖች አባቶቻችን ደማችንን ገብረን የዚህችን ያልታደለች ድሃ ምድር ዳር ድንበር ከማስከበር ውጪ ሌላ ምን አማራጭ አለን፡፡ አንድ የግብፅ ገበሬ ከአረንጓዴ ማሳው መሃል በኩራት ቆሞ “የውሃችንን ምንጭ ለማቆም የሚሞክር ማንም አካል ቢኖር ያለምንም ድርድር በቀጥታ እንፋለመዋለን” በማለት እየተናገረ “Struggle over the Nile” በሚል ርዕስ በተሰራ ዶክሜንታሪ በአልጀዚራ ቴሌቪዥን ታይቷል፡፡
ምናልባት ኤርትራ የግብፅ ተባባሪ ከሆነች ከሻዕብያ ጋርም በድጋሚ ጦርነት መግጠማችን የማይቀር ጉዳይ ነው፡፡ ይህ ከሆነ ወያኔ ኢህአዴግ የተገኘውን አጋጣሚ ተጠቅሞ አስመራ ድረስ በመግባት ሻዕቢያን እስከመጨረሻው ደምስሶ ድንበራችንን መልሶ ቀይ ባህር በማድረግና ወደባችንን በማስመለስ አገሪቱን ከሬሳ ሳጥን ውስጥ አውጥቶ የተበላሸውን ታሪኩን ያድሳል እንጂ ለሁለተኛ ጊዜ አይሸወድም የሚል የበርካቶች እምነት አለ፡፡
ደግነቱ ዘውዱ

የምእራብ ጎንደር ወይና ደጋው ክፍል በር የሌላቸው የወያኔ እስርቤቶች ስለመሆናቸው፤


ከመካከለኛው ምስራቅ የሚነሱ ጠላቶች ሁልጊዜም ኢትዮጵያን ሲአጠቁ መረማመጃ ያደረጉት ዋና ከከሰላ እስከ ኦሜድላ (ጎጃም) ያለው አካባቢ ነበር። የነዚህ ተጋፊ የኢትዮጵያ ጠላቶችን የመጀመሪያ ገፈታ ቀማሽ የምእራብ ጎንደር ህዝብ ነበር። ለአጼ ተዌድሮስ መነሳት ለአጼ ዮሃንስም መሰዋእትነት ምክንያት የሆኑት በዚሁ አካባቢ የኢትዮጵያን ልእልና ለመድፈር የተደረጉ ሙከራዎችና ጦርነቶች ናቸው። የምእራብ ጎንደር ህዝብም ድንበሩን ለመከላከል ሲል ያልተቋረጠ መስዋእትነትን ከፍልበታል።
በአስራ አምስተኛዉ ምዕተ አመት (ከግራኝ መሃመድ ወረራ) ጀምሮ የአርማጭሆ፣ የወልቃይት፣ የጠገደ፣ የጫቆና የቋራ ህዝብ ‘ድንበር ጠባቂ’ ተብሎ ስያሜ ተሰጥቶት በማህል ኢትዮጵያ በሚነሳ ጦርነት እንዲይሳተፍ በአዋጅ የተከለከለ ነበር። በዚህም ምክንያት የወልቃይት፣ ጠገደ፣ የአርማጭሆ፣ የጭልጋና የቋራ ህዝብ ቤተሰቡን ያሰፈረው ከጠላት ለመመከት የተሻለ ከሆነው ከወይና ደጋው ነው። የምእራብ ጎንደር ወይና ደጋዎች፤ አዲረመጥ የተባለውን የወልቃይት ከተማና አካባቢውን፣ ቀራቅር የተባለውን የጠገደ ከተማና አካባቢውን፣ የአርማጭሆ የጭልጋና የቋራ ወይና ደጋ መሬቶችን ያጠቃልላል። ይሁንና የወይና ደጋው አፈር በውሀ የተሸረሸረ፣ መሬቱም በህዝብ ሰፈራ የተሰላቸና የተጣበበ በመሆኑ በቆሎና ድንች ከመሰለ አነስተኛ ምርቶች በስተቀር የወይና ደጋው ህዝብ የሚተዳደረው በቆላው መሬት በሚያመርተው ምርትና ከብት እርባታ ነው። ለአለፉት ሁለት መቶ አመታት ደግሞ የወይና ደጋው ህዝብ እርሻውንና ከብት ርቢውን በመከተል በቆላዎች ሰፈራዎችን አስፋፍቶ፤ በወልቃይት መዘጋ (አዲጎሹ፣መጉእ፣ቃሌማ፣እጣኖ፣ማይሃርገጽ)፣ የሁመራ፣ የዳንሻ፣ የአብደራፊ፣ የመተማና በቋራ እንደ ዮሀንስ የመሳሰለትን ከተሞችን ቆረቆረ። ይህ ደግሞ የድንበር
ጥበቃውን በይበልጥ አጠናከረው። በዚህም ምክንያት ነበር ጣሊያን በወልቃይት፣ በጠገደ፣ በአርማጭሆና በመተማ አካባቢ ከፍተኛ ሽንፈት የደረሰበትና አካባቢውም ከየትም ለመጣ የኢትዮጵያ አርበኛ ቡድን ከፍተኛ ምሽግ ሆኖ የቆየው። የወያኔ መሪዎች ግን ገና ሀ ብለው እንቅስቃሴ ሲጀምሩ ዋና ተልእኮ አድርገው የያዙት የዚህን ዳር ድንበር ጠባቂ ህዝብ የጀርባ አጥንት መስበር ነው።ይህንንም ህዝብ ነው ትግሬ ባለመሆኑና በተለይም አማራ በመሆኑ ከምድር ገጽ ለማጥፋት በወያኔ እቅድ የወጣለት።
ዛሬ የወልቃይት፣ የጠገደ፣ የአርማጭሆ፣ ጫቆና ቋራ ህዝብ አማራ በመሆኑ ብቻ ለዘመናት ከሞተለት መሬት ተፈናቅሎ በተጨናነቁ በምእራብ ጎንደር ወይና ደጋዎች ታጉሯል። የተጣበበው ህዝብ እንደ አባቶቹ ወደ ቆላ መሬቶቹ ወርዶ ከብት አርብቶና አርሶ እንዳይበላ የትግራይ ክልል አስተዳደር እስክ አፍንጫቸው ባስታጠቋቸው የትግራይ ሰዎች ይጠበቃሉ፤ ይህ አልበቃ ብሎ ደግሞ በወይና ደጋዎቹ ላይ በማንአለብኝነት የተደራጁት የወያኔ አስተዳዳሪዎች በሰበብ አስባቡ (መሳሪያ አሽገሀል ወዘተ) በማለት ሁለንም ቤተሰብ ያንገላቱታል፣ያስሩታል። በተለይ ወጣት ወንዶች ከፍተኛ ያፈና በደልም ይፈጸምባቸዋል።
በዘላቂ መንገድም የወይና ደጋው ህዝብ የሽንፈትና የወኔ መፍሰስ ስሜት እንዲያድርበት ወያኔ ከህዝቡ አብራክ የወጡትን ልጃገረዶችን በትግራይ ጎረምሳ ኮርማዎች ግብረ ስጋዊ አመጽ ያስፈጽምባቸዋል። ይህ በተለይ በወልቃይትና ጠገደ ወይና ደጋዎች በሰፊው የሚካሄድ ወንጀል ነው።
በአጠቃላይ ዛሬ የምእራብ ጎንደር ወይና ደጋዎች በር የማያስፈልጋቸው የወያኔ እስር ቤቶች ሆነዋል።
የመተማ ከተማና አካባቢው፤
ወያኔ በመተማ ከተማና በአካባቢው ያሉትን ገበሬዎችና የከተማው ነዋሪ ህዝብ ሰብስቦ ‚…አካባቢው ለጦር ክምችትና ለጦር ማእከላዊነት እንድሆን ስለተወሰነ ወደ ምስራቅ ባለው የወይና ደጋው ጥግ ለመስፈር ዝግጅት እንድታደርጉ…‛ የሚል ትዕዛዝ ተሰጣቸዉ። በ2009 (እ።አ።አ) ነብስ ገቢያ በሚባለው የቋራ ቆላ ክፍል የሱዳን ወታደር አርሻ አቃጥሎ፣ ንብረት ዘርፎና ወገኖቻችንን ማርኮ ወደ ሱዳን ሲወስድ መተማ የተከማቸው የወያኔ ወታደር አንድት ጥይት እንኳን አለመተኮሱን የኢትዮጵያ የድንበር ኮሚቴ በማያወላዳ ማስረጃ መመዝገቡ የሚታወስ ነው። ስለዚህም መተማ የተከማቸው የወያኔ ወታደር ዋና ተግባሩ የኢትዮጵያኖችን ድህንነት ለማስጠበቅ እንዳልሆነ ግልጽ ነው። ወታደሩ እስካሁን ድረስ ያሳየው ታሪክ ቢኖርም የአማራውን ገበሬ ማፈናቀል፤ ማሰር፣ መግደልና ሃብት ማቃጠል ነው። ወደፊትም ከዚህ
የተለየ አይጠበቅበትም። ይልቅስ በመተማ አቅጣጫ ያገረሸው የወያኔ መልቲ ዘመቻ ግልጽ ያደረገው ነገር፤
፩ .የትግራይ መስፋፋት በአብደራፊና በአካባቢው እንደማይቆም፤
፪. የትግራይን ግዛት ከጣና ባህርና ከተቻለም ባሁኑ ወቅት አባይን እገድባለሁ እያለ ከበሮ ከሚደልቅበት ቦታ ለማድረስ ለሚደረገው የመጨረሻው ዘመቻ የመጀመሪያው መስተንግዶ (አፒታይዘር) መሆኑ ነው።
አደፍርስ ደመላሽ

Friday, June 14, 2013

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን እኔ እንደማውቀው

ስመኝ ከፒያሣ የኢትዮጵያ ፕሬስ የሚታወሰው ወይም የሚነሳበት ዘመን ቢኖር ከ1985 ዓ.ም ጀምሮ ነው፡፡ ኢህአዴግ መላ ሀገሪቱን ከተቆጣጠረበት ከግንቦት 20/1983 ዓ.ም እስከ 1985 ዓ.ም ድረስ ምንም ያደረገው ነገር አልነበረም፡፡ ፀጥታ የነገሰበት ጊዜ ነበር፡፡ በዚህ ጊዜ ውስጥ ደግሞ ማለትም 1985 ዓ.ም ላይ የኤርትራ ሪፈረንደም የተፈቀደበት ጊዜ ነበር፡፡ ከዛ በኋላ ደግሞ በሙሉ ነፃነት ነገሮችን መግለፅ ተጀመረ፡፡ታዲያ በነዚህ ጊዜያት ከወጡትና ስለኢትዮጵያ የፕሬስ ነፃነት አለን ብለው መፃፍ ከጀመሩት መካከል ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ አንዱ ነው፡፡ እስክንድር ነጋ በምድረ አሜሪካ ይኖር የነበረ ሲሆን ወደ ኢትዮጵያ የተመለሰው ከደርግ ውድቀት በኋላ ነው፡፡ በቤተሰቦቹ ላይም ሆነ በእሱ ላይ ከፍተኛ እንግልት፣ ስቃይና በርካታ የንብረት ውድመት በደርግ መንግስት ደርሶባቸዋል፡፡ እሱና እናቱ በቀይ ሽብር ወቅት ከፍተኛ ጭፍጨፋ ፈፅመዋል ከሚባሉት አንዱ በሆነው ” ግርማ ከበደ” ከፍተኛ እንግልትና የንብረት ውድመት ሲያደርስባቸው ወደ አሜሪካ ተሰደዱ፡፡  እስክንድር በአሜሪካ በነበረበት ወቅት ደርግ ይፈፅማቸው ለነበሩ ያልተገቡ ተግባራት በሙሉ በአሜሪካ ይገኙ የነበሩ ኢትዮጵያዊያን በደርግ መንግስት ላይ ጫና ይደረግ የሚል መርህ ባነገቡ ሰላማዊ ሰልፎች ላይ ቀርተው አያውቁም፡፡ ሁሌም ስለሀገሩ ያስብም ነበር፡፡ የእስክንድር ፍላጐት ሀብት ንብረትና ገንዘብ ሣይሆን የኢትዮጵያ እድገትና ለውጥ ማየት ነው፡፡ ኢትዮጵያ ከሌላው ሀገር በተሻለ ለውጥ ማምጣት የምትችል ሀገር በመሆኗ ይህ ለምን መሆን አልቻለም ብሎ የሚናገር ጋዜጠኛም ነበር፡፡ ወደ ኢትዮጵያ ከመጣም በኋላ “ኢትዮጲስ” የተባለ ጋዜጣን ከሟች ጋዜጠኛ ተፈራ አስማረ ጋር በመሆን አቋቋመ፡፡ በወቅቱ በኢትዮጵያ ኢህአዴግ ዴሞክራሲን አስፍኛለሁ ያለበት ጊዜ ነበር፡፡ ዴሞክራሲ ያለገደብም ተብሎ ነበር፡፡ ከዚህ በመነሣት በርካታ ዜናዎች ማቅረብ ጀመሩ፡፡ በወቅቱ እነሱ የጀመሩት ጋዜጣ ዋጋ 75 ሳንቲም ቢሆንም ይዘውት የሚወጡት ዘገባ ከባድነት “ኢትዮጲስ” ጋዜጣ ሰባት ብር ድረስ ትሸጥ ነበር፡፡ የዛሬ 20 አመት ሰባት ብር የነበረውን ጥቅም ማንም ቢሆን የሚዘነጋው አይደለም፡፡ ታዲያ በዚህ ሁኔታ ላይ እያለ ኢትዮጲስ ተቋረጠች፡፡ እነ እስክንድርም ታስረው ወጡ፡፡ ከዛ “ሀበሻ” የተባለ ጋዜጣ በአማርኛና በእንግሊዘኛ ማሣተም ጀመረ፡፡ ይሁንና ግን ብዙም ሣይራመድ “ጐበዝ አምስት አመት ሞላ” የሚለው ዘገባ ችግር ፈጠረ፡፡ እስክንድር መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ያነበው ዘንድ ሀበሻን ይጠብቋት ብሎ የጋዜጣውን ማስታወቂያ በካርቶን ይዘው የሚዞሮ ወጣቶችን መድቦ ነበር፡፡ ይሁንና እስከ እነሱ ጭምር በድጋሚ ታሰረ፡፡ ወጣቶቹ ሲፈቱ እስክንድር ግን በማረሚያ ቤት ቀረ፡፡ የእስክንድር ቀኝ እጅ የተሰበረውም በዛ ጊዜ ነበር፡፡ እስክንድር ከተፈታ በኋላም ዳግም ታስሯል፡፡ እንደውም በ1987 አብሯቸው ከታሰራቸው መካከል የግብፁን ፕሬዝዳንት ሁሴኒ ሙባረክን ለመግደል ሙከራ ያደረጉና በቁጥጥር ስር ከዋሉ አሸባሪዎች ጋር ነበር፡፡ እዚህ ላይ የምገልፀው ነገር ቢኖሩ እስክንድር ነጋን እኔ እንደማውቀው ነው፡፡ ከዛ በኋላ ወይም ከረጅም ጊዜ እስር በኋላ ግን ተፈቶ እስክንድር ነጋ ወደ ጋዜጣ ሕትመት ሲመለስ “ምኒልክ” የተባለውን ጋዜጣ ይዞ ብቅ አለ፡፡ ምኒልክ ጋዜጣ መቼም በሀገሪቱ እስከተቋረጠበት ጊዜ ድረስ በህትመት ግንባር ቀደም የነበረ ጋዜጣ ነበር፡፡ እስክንድር ነጋ የተለየ ነገር ወይም ባህሪ አለው፡፡ ይህ ባህሪው ደግሞ ስለገንዘብና ጥቅም የሚያስብ ሰው አልነበረም፡፡ በወቅቱ ጋዜጦች በኪሳራ ከጨዋታ ሊወጡ ሲሉ የሚደጉም የለኝም ብሎ ለመጣ ሁሉ የሚሰጥ ሰው ነበር፡፡ እኔ እስክንድርን ከተዋወኩበት ጊዜ ጀምሮ ሁሌም እሱን ማወቅ ያጓጓኛል፡፡ ምክንያቱም ከእሱ የሚወጡት ሀሣቦችና ቃላት የተለዩና በውስጣቸው እውነትነት ያላቸው ነበሩና፡፡ እስክንድር ስለገንዘብ ጥቅም ወይም ተንደላቆ ስለመኖር የሚያስብ ሰው ፈፅሞ አይደለም፡፡ የየትኛውንም ሰው ሀሣብ ይቀበላል በፅሞናም ያዳምጣል፡፡ የትልቅነት መለኪያው ደግሞ ምንም ሣይሆን ሰዎችን ማዳመጥና መስማት መቻል ነው፡፡ እስክንድር በጋዜጦቹ ላይ በርካታ ነገር ይፅፋል፡፡ አንድም ጊዜ ቢሆን ግን ምስሉን ለጥፎ እኔ እስክንድር ነጋ ነኝ ብሎ አያውቅም፡፡ ከዛ ባለፈ ደግሞ “ሀበሻ” ጋዜጣ ከታገደበት በኋላ በስሙ ያወጣው ጋዜጣ የለም፡፡ ፎቶውን ሣይሆን ስሙን አውጥቶ የፃፋቸው ፅሁፎች ቢኖር የማስታውሰው የደርግ ባለስልጣናትን በሚመለከት በሚወጡ ፅሁፎች ላይ ነበር፡፡ ከዛ ውጭ ግን በሰራው ስራ በሕዝብ እንዲወደዱ እወቁኝ እወቁኝ እያለ በአደባባይ የወጣ ወይም ደረቱን ነፍቶ ይህ ይሁን ያለ ሰው አይደለም፡፡ እስክንድር የተለየ ቦታ ያለው ሰው ነው፡፡ አንድ ታሪክ ልንገራችሁ ይህን ታሪክ ግን ስም ሣልጠቅስ ባወራው እመርጣለሁ፡፡እስክንድር አሁንም በስራ ላይ ላለ ጋዜጣ ባለቤት እባክህ እከሌ የተባለን ባለሰልጣን ለማነጋገር ፈልጌ ሪፖርተሬን መላክ ፈለኩ እናም አስጨርስልኝ አለው፡፡ ይህ ሰውም ባለስልጣኑን ሲያናግር ባለስልጣኑ ሪፖርተሩ ሣይሆን ራሱ እስክንድር ነጋከመጣ ቃለመጠይቁን እሰጠዋለሁ አሉ፡፡ በዚህ ምክንያት እስከንድር ሣይሄድ ቀረ፡፡ እኚህ ባለስልጣን ታዲያ አሉ ወይም ተናገሩ በተባለው ቃል “እስክንድር የገንዘብ ችግር እንደሌለበት አውቃለሁ የሚሰራው ለጥቅም ወይም ለፖለቲካ ፓርቲ አይደለም፡፡ አላማው ምን እንደሆነ እሱን አግኝቼ ማናገር እፈልጋለሁ” ሲሉ ገለፁ፡፡ የእስክንድርን መንፈስ ስናስበው ታዲያ በዚህች ሀገር ላይ እውነተኛው ዴሞክራሲ መስፈን አለበት ከሚል አንፃር በመነጨ የሚሰራ እንጂ አትራፊ ጋዜጠኛ ወይም የሕዝቡ የልብ ትርታ ይሄ ነው ብሎ ምስሉን ለጥፎ የሚነግድ አይደለም፡፡ ርግጠኛ ሆኜ የምነግራችሁ በሀገሪቱ ከታተሙ ነፃ ጋዜጦች እስክንድር ነጋ የሚሰራባቸውን ጋዜጦችን በቁጥርና በጥራት የሚደርስ አልነበረም፡፡ይህ ሁሉ ሲሆን ታዲያ እስከንድር ሻይ እንጠጣ ብሎ ኪሱ ሲገባ ገንዘብ ሣይዝ ረስቶ የሚወጣ ሰው ነው፡፡ ስለገንዘብና ስለዝና አይኖርም፡፡ በእሱ ስር የሚሰሩ ሰራተኞች ግን የበለጠ እንዲጠቀሙ ያደርጋል፡፡ እስክንድር ተቸገርኩ ላለው ሰው ሆዱ የማይጨክንና የሚራራ ደግ የሚባል ጋዜጠኛም ጭምር ነው፡፡ የእስክንድር ጋዜጣ ነው ከተባለ ጋዜጣ አዙሪዎች ለማውጣት አይፈሩም፡፡ ምክንያቱም እስክንድር ጋዜጣ አደረብኝ የሚል አዙዋሪ በሙሉ ይመለስለታል፡፡ ጋዜጣ አዙዋሪ የሌላውን ለማውጣት መጠን ያበጃል በእስክንድር ጋዜጣ ላይ ግን ቢመለስብኝስ ብሎ አይፈራም፡፡ 12 ሰአት ካለፈ በኋላ እድሜ ለእስክንድር ብሎ ቤቱ ይገባል፡፡ ጠዋት አምጥቶ ይመልሳል፡፡ አዟሪ በሙሉ ሌላ አሣታሚ አልመልስ ካለው እስክንድር እንኳን እየመለሰ ሲል ሁሉም ለእሱ ክብር ሲል መመለስ ጀመረ፡፡ እስክንድር የየትኛውም ተቃዋሚ ፓርቲ አባል አይደለም፡፡ አልነበረምም፡፡ ሁሌም ተቃዋሚ ፓርቲዎችን ይወቅሳል፡፡ ይናገራል፡፡ ምኒልክ ጋዜጣ በነበረበት ጊዜ በመጀመሪያ የተጋጨው ከኢ/ር ኃይሉ ሻወል ጋር ነበር፡፡ የግጭቱ መንስኤ ደግሞ የፓርቲያችሁ አቋም ይሄ ነው ለምን ሆነ በሚል ነው፡፡ እውነት እንነጋገር ከተባለ ለኢህአዴግ ስጋት ፈጥሮ የነበረው ፓርቲ “ቅንጅት” በሚሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እስክንድር አንድም ቀን ተገኝቶ አያውቅም፡፡ በእነሱ አሰራር ወይም አካሄድ ላይ ቅሬታ ካለው ግን ይናገራል፡፡ ኢ/ር ኃይሉ ሻወል በልጃቸው አማካይነት ተቃውሞውት ወደ ክስ አመራለሁ ብለው ያውቃሉ፡፡ የፖለቲካ ፓርቲዎቹ በውስጣቸው ያለውን ችግር ይገልፃል፡፡ ሌላው ይቅርና አቶ ልደቱ አያሌውን ማንዴላ በተባሉበት ወቅት ሣይቀር የእሣቸው አካሄድ ላይ በድፍረት ቅሬታውን የገለፀ ሰው ቢኖር እስክንድር ነጋ ነው፡፡
ዘመን ሲቀየር ሕዝብ ሊቀየር ወዳጅም ሊከዳና ሊርቅ ይችላል፡፡ እስክንድር ነጋ ግን ዛሬ አብጠው ሲሰሩ ከማያቸው አንዳንድ ጋዜጠኞች የእሱ ምክርና ድጐማ የሌለባቸው አሉ ብሎ ለመናገር ይከብዳል፡፡ ይህቺ ሀገር ጋዜጠኛ አፈራች እስክንድር ነጋን ብል የማፍርበት ሰው አይደለም፡፡ ሁሌም የምኮራበት ሰው ነው፡፡ ከላይ እንደገለፅኩት እስክንድር የማንም የፖለቲካ ፓርቲ አባል አይደለም፡፡ ሁሌም “ምርጫ 97″ የሚለውን መፅሐፍ ሣስበው አለም የእሱን የእውቀት ደረጃ እንዲለካ እፈልጋለሁ፡፡ ከእሱ በኋላ እሱን አጣጥመው የማያውቁት ተነስተው ታሪክ ለመስራት ቢሞክሩ እነሱን በወንፊት አጥልሎ ማንነታቸውን ለማወቅ ይከብዳልና፡፡ የማያውቁት አገር አይናፍቅም እንደሚለው ዘፈን እስክንድር ነጋን ያየ ዛሬ በሌሎች ያልተጣራና ያልተረጋገጠ ተግባር ሊደመም አይችልም፡፡ የፅሁፌ ሳጠቃልል እስክንድር ነጋ በኢትዮጵያ የነፃ ፕሬስ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ቦታ ያለውና ስለእውነት ብቻ የሚናገር ምርጥ ጋዜጠኛ መሆኑን ምስክርነቴን በመስጠት ነው፡፡

http://www.zehabesha.com/amharic/wp-content/uploads/2013/06/eskindir.jpg