Thursday, February 28, 2013

ከኢህአዴግ ጋር ቅርበት እንዳላችው የሚታሙት ብፁዕ አቡነ ማቲያስ 6ኛው ፓትርያርክ ሆነው መመረጣቸው ይፋ ሆነ


February 28, 2013 10:28 am
  • digg
  • 1
     
    Share
Abune_Mathias_3
የአሜሪካው ሲኖዶስ ምርጫውን እንደማይቀበለው በመግለጫው አሳውቋል
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን 6ኛ የፓትርያርክ ምርጫ ዛሬ የካቲት 21 ቀን 2005 ዓ.ም. ተከናወነ፡፡ ቀደም ሲል የሟቹ ብፁዕ አቡነ ጳውሎስን ሞት ተከትሎ በአዲስ አበባና በአሜሪካ ባሉት ቅዱስ ሲኖዶስ መካከል የተቋረጠው እርቀ ሰላም እንዲቀድም የተለያዩ ጥረቶች ቢደረጉም ሳይሳካ በመቅረቱ ከአዲስ አበባው ቅዱስ ሲኖዶስ ጳጳሳት መካከል 6ኛ ፓትርያርክ እጩዎች ይፋ በተደረገው መሰረት ብፁዕ አቡነ ማቲያስ 6ኛ ፓትርያርክ ሆነው መመረጣቸው ይፋ ሆኗል፡፡
በእጩነት ከቀረቡት ሊቃነ ጳጳሳት መካከል ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የባሌ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ፣ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ የወላይታ ዳውሮ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ፣ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የጎንደር ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ፣ብፁዕ አቡነ ህዝቄል የከፋ ሸካ ቤንች ማጂ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ እና የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ጸሐፊ እና ብፁዕ አቡነ ማቲያስ የኢየሩሳሌም ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ እንደነበር ለምርጫው የተዘጋጀ የግል መኀደራቸው አመልክቷል፡፡
በእጩ አቀራረብ ዙሪያ በርካታ አነጋጋሪ ጉዳዮች በጳጳሳት መካከል መፈጠሩና ከዕጩዎች መካከል አሁን ፓትርያርክ ሆነው መመረጣቸው ይፋ የሆኑት ብፁዕ አቡነ ማቲያስ ዘ-ኢየሩሳሌም አሜሪካዊ ዜግነት ያላቸው ናቸው፤ስለዚህ እጩዎች ውስጥ መካተት የለባቸውም የሚል ተቃውሞ ቀርቦባቸው እንደነበር ተጠቁሟል፡፡
ዛሬ እየተደረገ በነበረው 6ኛው የፓትርያርክ ምርጫ ደጀ ሰላም በምታካሂደው “ኢ-ቀጥተኛ” የምርጫ ድምጽ አሰጣጥ ከመረጡት መካከል ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ በከፍተኛ ድምጽ በመምራት ላይ ሲሆኑ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ በሁለተኛነት ይከተላሉ። ዜናው በተጠናቀረበት
ሰዓት ያለው ዝርዝር ይህንን ይመስላል።
1) ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ፣ 328 ድምጽ (33%)
2) ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ፣ 185 ድምጽ (18%)
3) ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል፣ 160 ድምጽ (16%)
4) ብፁዕ አቡነ ማትያስ፣ 159 ድምጽ (16%)
5) ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ፣ 81 ድምጽ (8%) አግኝተው እንደነበር ቅርበት ያላቸው ድረገፆች ዘግበውት ነበር፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ በአሜሪካን ሀገር የሚገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ በአዲስ አበባ የተደረገውን 6ኛ ፓትርያርክ ምርጫ እንደማይቀበልና እውቅናም እንደማይሰጠው ባወጣው
- See more at: http://www.fnotenetsanet.com/?p=3520#sthash.ZoJzLRom.dpuf

በከፍተኛ ጉጉት ሲተበቅ የነበረው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ስድስተኛው ፓትርያርክ ምርጫ በአሁኑ ሰዓት ተጠናቋ ፡፡


በከፍተኛ ጉጉት ሲተበቅ የነበረው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ስድስተኛው ፓትርያርክ ምርጫ በአሁኑ ሰዓት ተጠናቋ ፡፡ ከተመዘገቡት 870 መራጮች መካከል ከ800 በላይ ያህሎቹ  ድምጻቸውን መስጠታቸው ታውቋል ፡፡  ከአሁን በኋላ የሚቀረው ሂደት የካርዱን ብዛትና የመራቹን ቁጥር ማነጻጸር ፤ ድምጹን ቆጥሮ ቃለ ጉባኤ መፈራረም ፤ የመገናኛ ብዙሃንን በመጥራት ማን ምን ያህል እንዳገኝ መግለጽ እና ቀጣይ ፓትርያርኩን የማወጅ ስራ ብቻ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
የአስመራጭ ኮሚቴው አባላትና የምርጫው ታዛቢዎች በጋራ÷ በምርጫው ላይ የተገኙና ያልተገኙ መራጮች ቁጥር እኩል መኾኑን፣ እንዲሁም መራጮች የተቀበሉት የድምፅ መስጫ ወረቀትና በሣጥን ውስጥ የተገኘው የድምፅ መስጫ ወረቀት እኩል መኾኑን አረጋግጠዋል፤ በቃለ ጉባኤም ተመዝግቧል፡፡በአሁኑ ወቅት የአስመራጭ ኮሚቴ አባላትና ታዛቢዎች በጋራ÷ እያንዳንዱ ድምፅ ሰጪ የሰጠው ድምፅ ዋጋ ያለው (የሚቆጠር) መኾኑን አለመኾኑን የመለየትና የመወሰን ሥራ በመሥራት ላይ ናቸው፡፡
ስድስተኛው ፓትርያርክ ብጹእ አቡነ…………… ሆነዋል የሚለውን ድምጽ እንጠብቃለን፡፡
የድምፅ ቆጠራው ውጤት ታውቋል፡፡
ብፁዕ አቡነ ማትያስ – በ500 ድምፅ አሸናፊ ! ! !
ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ – በ98 ድምፅ
ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ – በ98 ድምፅ
ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ – በ39 ድምፅ
በዚህም መሠረት ብፁዕ አቡነ ማትያስ የካቲት 24 ቀን 2005 ዓ.ም በመንበረ ተክለ ሃይማኖት የሚሾሙ ስድስተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያሪክ ይኾናሉ፡፡

Wednesday, February 27, 2013

ከነዳጅ ሐብት ፍተሻ ጋር በተያያዘ በደቡብ ኦሞ ዞን አቅጣጫ ያለው የኢትዮ-ኬኒያ ድንበር ተዘጋ


በፀጋው መላኩ
በኢትዮጵያ በነዳጅ ፍለጋና ምርመራ ሥራዎች ከተሰማሩት ቱሎ እና አፍሪካ ኦይል ከተባሉ ሁለት ኩባንያዎች ጋር የሚሰራጩ የቻይናው ‘‘BGP Inc’’ የተባለ ኩባንያ አሁን ሥራውን እያከናወነበት ካለው የደቡብ ኦሞ ዞን ወደ ኬኒያ ድንበር የፍተሻ መሳሪያዎቹ (ማሽኖቹን) በማንቀሳቀሱ በአካባቢው ያለው የሁለቱ ሀገራት ድንበር መዘጋቱን የብሉምበርግ ዘገባ አመላከተ። በአካባቢው የሚንቀሳቀሱት ከባድ ማሽኖች ቦታው አስቸጋሪ ከመሆኑ ጋር በተያያዘ ቀናትን ይወስዳሉ ተብሎ ይጠበቃል። የፕሮጀክቱ ኃላፊዎች በአካባቢው የተወሰኑ ሜትሮች ርቀት ያላቸውን ጉድጓዶች በመቆፈር የናሙና ጥናቶችን (Sesmic Studies) ለማከናወን የኬኒያንና ከኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ጋር በንግግር ላይ መሆናቸውን ዘገባው ያመለክታል።
ኩባንያው በአሁኑ ወቅት የተለያዩ ከባድ ማሽኖችን ቆፍሮ ማሽኖችን ወደ ኢትዮ-ኬኒያ ድንበር እያንቀሳቀሰ መሆኑ የታወቀ ሲሆን ከዚሁ ጋር በተያያዘ በደቡብ ኦሞ ዞን አቅጣጫ ያለው የሁለቱ ሀገራት አዋሳኝ ድንበር መዘጋቱ ታውቋል። እንደ ብሉምበርግ ዘገባ በኦሞ ወንዝ አካባቢ ተከትሎ ባለው የኢትዮ ኬኒያ ድንበር እስከ 10 ቢሊዮን በርሜል የሚደርስ የነዳጅና የጋዝ ክምችትን ይዟል ተብሎ የሚገመት መሆኑን ዘገባው ጨምሮ አመልክቷል። ቶሎ እና አፍሪካ ኦይል የተባሉ ሁለት ታላላቅ አለም አቀፍ የነዳጅ ፈላጊና አውጪ ኩባንያዎች በሁለቱ ሀገራት ድንበሮች አካባቢ በዚህ ዓመት 11 የነዳጅ ጉድጓድ ቁፋሮዎችን ለማካሄድ እቅድ ያላቸው መሆኑ ዘገባው አመልክቷል።
በኬኒያና በኡጋንዳ ነዳጅን ያገኘው ቱሎ የተባለው ኩባንያ በደቡብ ኦሞ ዞን የነዳጅ ፍለጋን እያከናወነ ሲሆን ብዙም ሩቅ ባልሆነ ጊዜ ውስጥም ውጤቱን ያሳውቃል ተብሎ ይጠበቃል። በዚሁ ጉዳይ ያነጋገርናቸው በማዕድን ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ባጫ ፉጆ በሀገሪቱ ነዳጅ መገኘቱ ከተረጋገጠ ይፋዊ በሆነ መንገድ በመንግስት የሚገለፅ መሆኑን ገልፀው ይሁንና እስከ አሁን ባለው ሁኔታ ኩባንያዎቹ በየሦስት ወሩ ለሚኒስቴር መስሪያቤቱ ሪፖርት በማቅረብ ከሚደረገው ሙያዊ ትንተና ውጪ የተሰጠ ይፋዊ መግለጫ የሌለ መሆኑን አመልክተዋል።n
(ምንጭ፡- ሰንደቅ ጋዜጣ 8ኛ ዓመት ቁጥር 390 ረቡዕ የካቲት 20 ቀን 2005 ዓ.ም )
Ze-Habesha Website is not responsible for accuracy of information or endorses the contents provided by external sources. All blog posts and comments are the opinion of the authors.

ዓቃቢ ህግ ዕዳ አለበት! አዎ ዕዳ አለበት!! – ከጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ


እንደ ጉርሻ 
በሽብርተኝነት ተከሰው በወህኒ ቤት የሚገኙ በጣም በርካታ እስረኞች የይቅርታ ፎርም እንዲሞሉ እየተደረገ ነው (ምንአልባት የሀይለማርያም መንግስት ሪፎርም /ማሻሻያ/ የማድርግ ዕቅድ ካለው በዚሁ ሊጀምር አስቦ ሊሆን ይችላል፤ አሊያም እንደተለመደው እስረኛ በመልቀቅ የፖለቲካ ማሻሻያ እንደተደረገ ለማስመሰል ይሆናል)፡፡ ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ እና ዘሪሁን ገ/እግዚአብሄርም በብዛት ከሚለቀቁት እስረኞች ጋር አብረው እንደሚፈቱ ምንጮቼ አረጋግጠውልኛል፡፡
አጀንዳችን…
ዛሬ በከፍተኛው ፍርድ ቤት የእነእስክንድር ነጋን ንብረት ለመውረስ ፍትህ ሚንስቴር የመሰረተው ክስ ሲታይ ውሎአል፡፡
እስክንድር ከዚህ ቀደም ‹‹የታሰርኩት በግፍ ስለሆነ ንብረቴን አትውረሱ ብዬ አልከራከርም፤ ዛሬውኑ ልትወስዱት ትችላላችሁ›› በማለት ያልተከራከረ ሲሆን፣ የአበበ በለውን ንብረት በሚመለከት በሌለበት ታይቷል፡፡ የአንዱአለም አራጌ ባለቤት ደግሞ በስሟ የተመዘገበው መኪና መወረሱ አግባብ እንዳልሆነ በጠበቃዋ አቶ ደርበው ተመስገን አማካኝነት ተከራክራለች፡፡ ፍርድ ቤቱም ለውሳኔ የፊታችን ሚያዚያ አስር ቀን ቀጠሮ ሰጥቷል (በእኔ ግምት ቀጠሮው እንዲህ የራቀው መጋቢት አስራ ስምንት ቀን እነእስክንድር የጠየቁት ይግባኝ የመጨረሻ ውሳኔ ስለሚሰጥበት ከዛ በኋላ የንብረቱን ጉዳይ ለመጨረስ ይመስለኛል)
የሆነ ሆኖ ዓቃቢ ህግ የእስክንድር ንብረት ተብለው ከቀረቡት ባለሁለት ፎቅ ዘመናዊ መኖሪያ ቤት፣ በባለቤቱ ጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲል ስም የተመዘገበ የቤት መኪና፣ እንዲሁም የእስክንድር እናት ንብረት የሆነ በአንድ ሺህ ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ መኖሪያ ቤትን ለመውረስ ጥያቄ ያቀረበ ቢሆንም፣ በዛሬው ዕለት በእናቱ ስም የተመዘገበውን ቤት እንደተወው ገልጿል (አዲስ ታይምስ መፅሄት የእናቱ ቤት ዝርዝር ውስጥ መግባቱ ተገቢ አለመሆኑን ደጋግማ መግለጿ የሚታወስ ነው)፡፡
ይህንና ዓቃቢ ህግ በእስክንድር እናት ስም የተመዘገበውን መኖሪያ ቤት ከሚወርሳቸው ዝርዝር ውስጥ በማውጣቱ ምንም አይነት ምስጋና የለኝም፡፡ ምክንያቱም እንኳን ንብረታቸው ተከሳሾቹም ምንም ጥፋት ያላጠፉ ንፁሀን ናቸው ብዬ ስለማምን፡፡ ስለዚህም አሁንም እንዲህ እላለሁ፡- ዓቃቢ ህግ ዕዳ አለብህ! አዎ እዳ አለብህ!! ንፁሀን ወንድሞቻችንን ይቅርታ ጠይቀህ እስክትለቅልን ድረስ!!!
* ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ይህን ዘገባ በፌስቡክ ገጹ ካሰፈረው ነው ያገኘነው።
Ze-Habesha Website is not responsible for accuracy of information or endorses the contents provided by external sources. All blog posts and comments are the opinion of the authors.
  http://www.zehabesha.com

ጠ/ሚ ኃ/ማርያምን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ሊከሰሱ ነው


Hailemariam_Desalegn_Ethiopia
ጠ/ሚ ኃ/ማርያምን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት
ባለስልጣናት ሊከሰሱ ነው
*ኢቴቪና ፌዴራል ፖሊስም ይከሰሳሉ
በዘሪሁን ሙሉጌታ ሰንደቅ ጋዜጣ 
በኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት በቅርቡ ከተላለፈው ‘‘ጅሃዳዊ ሃራካት’’ ዘጋቢ ፊልም ጋር በተያያዘ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃ/ማርያም ደሳለኝን ጨምሮ ከፍተኛ የሀገሪቱ የመንግስት ባለስልጣናት ላይ የወንጀልና የፍትሃብሔር ክስ ሊመሰረት ነው። ከመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ባሻገር በኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት (ኢሬቴድ) እና በፌዴራል ፖሊስ ተመሳሳይ ክስ ይመሰረትባቸዋል።
ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናቱ እና የተጠቀሱት ተቋማት ላይ ክስ የሚመሰረተው ሰሞኑን ‘‘ጃሃዳዊ ሃራካት’’ በሚል በኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ደርጅት የቀረበው ዘጋቢ ፊልም በሽብርተኝነት ተጠርጥረው በሕግ ጥላ ስር ያሉትን ተጠርጣሪዎች መብት ሲጣስ መከላከል ባለመቻላቸው፣ ስልጣናቸውን ያለአግባብ በመጠቀማቸው፣ በሕዝብ ሐብት ያለአግባብ በመገልገላቸው፣ የተሰጣቸውን የሕዝብ አደራ ባለመወጣታቸውና በሃይማኖት ጣልቃ በመግባታቸው የወንጀልና የፍትሐብሔር ክስ ይመሰረትባቸዋል። ክሱን የሚመሰርቱት በአሁኑ ወቅት በሽብርተኝነት ተጠርጥረው ጉዳያቸው በሕግ እየታየ ባሉት ተጠርጣሪዎች ጠበቆች አማካኝነት ሲሆን ክሱም በሁለት ደረጃ ተከፍሎ እንደሚቀርብ ለማወቅ ተችሏል።
ክሱን እያዘጋጁ ከሚገኙት ጠበቆች አንዱ የሆኑት ጠበቃ ተማም አባቡልጉ ክሱን በማስመልከት በተለይ ለሰንደቅ ጋዜጣ እንደገለፁት ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ በመንግስት ባለስልጣናት ላይ የሚመሰረተው ክስ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይቀርባል ብለዋል። በኢቲቪ ላይ የሚመሰረተው የፕሬስ ክስ ቀጥታ በከፍተኛው ፍርድ ቤት የሚቀርብ ሲሆን ክሱም ከሞራል ጉዳት ጋር እንደሚያያዝ ጠበቃው አስታውቀዋል።
‘‘መጀመሪያ ክርክራችን ዘጋቢ ፊልሙ እንዳይተላለፍ ነበር። ከተላለፈ በኋላ ግን ይግባኝ ማለት ሳይጠበቅብን ይሄንን ጉዳት ባደረሱ አካላት ማለትም ፊልሙን በሰሩት፣ ፖሊስና የደህንነት ኃይሎች ጨማምረን ክሱ እንመሰርታለን’’ ያሉት ጠበቃ ተማም በፕሬስ ህጉ መሰረትም ዘጋቢ ፊልሙ በተላለፈ በሦስት ወራት ውስጥ ክስ መመስረት እንደሚያስችልም አያይዘው ገልፀዋል።
በኢቲቪ በተላለፈው ዘጋቢ ፊልም ላይ በሚመሰረተው ክስ እስከ 100ሺህ ብር የሞራል ካሳ እንደሚጠየቅ በከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ክስ ደግሞ በሌላ መዝገብ በፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በሚመሰረተው ክስ ለደንበኞቻችን የሞራል ካሳ እንዲካሱ፣ ደንበኞቻችን ይቅርታ እንዲጠየቁ፣ በተመሳሳይ የአየር ጊዜ ተሰጥቷቸው ደንበኞቻችን የራሳቸውን ኀሳብ እንዲሰጡ፣ በሃይማኖት ውስጥ በተደረገ ጣልቃ ገብነት ለደረሰው ጉዳት ኃላፊነት እንዲወስዱ የሚያደርግ ክስ ነው ብለዋል።
‘‘ክሱ ጠቅላይ ሚኒስትሩን የማያካትትበት ምክንያት የለም። የሀገሪቱ መሪ እሳቸው ናቸው። ፖሊስም እያደረገ ላለው ነገር ለምሳሌ ተጠርጣሪዎችን ቶርች በማድረግ ጭምር እንከሳለን። የሀገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ዘጋቢ ፊልሙ ያግዱ፣ አያግዱ የሚለውን አጣርተን የሚመለከታቸውን አካላት ለይተን ክሱን ለመመስረት ተዘጋጅተናል። ክሱን ለማዘጋጀት አስፈላጊ መረጃዎችን እየሰበሰብን ነው። በቅርቡም ክሱን እንመሰርታለን’’ ሲሉ ጠበቃ ተማም ጨምረው ገልፀዋል።
ደንበኞቻችን እራሳቸውን በማይከላከሉበት ሁኔታ ታስረው፣ መልስ እንዲሰጡ ባልተደረገበት ሁኔታ ስማቸው እንዲጠፋ መደረጉ አግባብ አለመሆኑን የጠቀሱት ጠበቃው ዘጋቢ ፊልሙ የደንበኞቻችንን መልካም ባህሪ የገደለ (Character assination) ነው ብለዋል።
መንግስት በሽብርተኝነትና ከህገ-መንግስቱ በተቃራኒ ሃይማኖታዊ መንግስት ለማቋቋም ሲያሴሩ አግኝቻቸዋለሁ፤ በሶማሊያ ከሚንቀሳቀሰውና ከአለም አቀፍ አሸባሪ ቡድን አልቃይዳ ጋር ከሚንቀሳቀሰው አል-ሻባብ ጋር ተመሳጥረው ሲሰሩ አግኝቻቸዋለሁ ባላቸው ተጠርጣሪዎች ላይ ዘጋቢ ፊልም ማቅረቡ ይታወሳል።
ፊልሙ ከመተላለፉ በፊት የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት አራተኛ ወንጀል ችሎት የእግድ ትእዛዝ ቢያስተላልፍም ፊልሙ ለሕዝብ አይታ መቅረቡ አይዘነጋም፤ ፊልሙ ለተመልካቾች ከቀረበ በኋላም አነጋጋሪ ሁኔታ መፈጠሩም ይታወቃል።n
ምንጭ ሰንደቅ ጋዜጣ

ሀገር ወዳድ መሆን እኮ ጦርነትን በሀገር ላይ ማሰብ አደለም፤ ሀገር ወዳድ እኮ መንግስት ህዝቡን ሲበድለው የራስን ኑሮ ደልቀቅ አድርጎ ማየት አደለም፤ ህዝብ ሲራብ ቆሞ ማየት አደለም፡፡ ምን አልባትም ችግርን አብሮ መጋፈጥ ትልቅ እሴት አለው


ሶስተኛው ዙር የአፈና እና የስለላ መምሪያ ንድፍ/እቅድ



በፈረንጆቹ አዲስ አመት ተከትሎ ወያኔ ያቋቋመው የአፈና እና የስለላ መዋቅር በደረረሰን መረጃ መሰረት ባለሃብት ናቸው የሚባሉ ሙስሊሞችን ለመጉዳት...የቤት ለቤት አሰሳ እና ፍተሻ እንደሚያካሂድ እንዲሁም ወደ ኢንተርኔት ካፌዎች ሊዘምት እቅድ እንደነደፈ የምንሊክ ሳልሳዊ ምንጮች መረጃ መስጠታቸውን ተከትሎ ይኅን ጉዳይ ብሎግ ያደረግንበት ድህረገጻችን እትዮጵያ ዉስጥ ለ2ኛ ጊዜ ታግዶ ይገኛል::

የውስጥ አዋቂ ምንጮች ለምኒሊክ ሳልሳዊ ባደረሱት መረጃ መሰረት የስለላ እና የአፈና መምሪያው ከብሄራዊ መረጀ እና ደህንነት መምሪያ ጋር በመሆን አዲስ ሚስጥራዊ ያሉትን የአፈና ስልት ነድፈው በይፋ ለመጀመር ቅድመዝግጅት እያደረጉ መሆኑን ተደርሶበታል::
በዚሁ መሰረት 3ኛው ዙር የአፈና እና የስለላ እቅድ የሞባይል ጠለፋ እና ሰበብ በመፍተር ሙስሊም ወጣቶችን ከመንገድ ላይ አፍኖ የመውሰድ ሴራ ነድፈዋል:: ያሉት የምኒሊክ ሳልሳዊ ምንጮች ይህንን እቅድ ተከትሎ በሙስሊም ስሞች ተመዝግበው የሚገኙ ሲም ካርዶችን የባለቤቶቹን ስም እና አድራሻ በዝርዝር እንዲሰጠው በአቶ ደብረጺሆን በኩል ለቴሌ ምስጢራዊ ያሉት እነሱ ትእዛዝ የተላለፈ ሲሆን እያንዳንዱ የስልክ ግንኙነት እንዲመረመር ሲነገራቸው እንዲሁም የተቃዋሚ ሃይሎች እና ለቤተክርስቲያን ቅርብ ናቸው ተብለው በተቃዋሚነት የተፈረጁ ግለሰቦች የዚህ አፈና ኢላማ ናቸው::

ሌላኛው በንኡስ አንቀጽ የተቀመጠው በትምህርት በስለዋል የሚባሉ ሙስሊም ወጣቶችን እና የማህበረቅዱሳን `አማፂ` የተባሉ እንዲሁን የራእይ ወጣቶች ማህበር አባላትን ኢላማ አድርጎ ከመንገድ በሰባብ አስባቡ አፍኖ መውሰድ ሲሆን ይህም በብዛት የሚአተኩረው ፈረንሳይ ለጋሲዎንን መነሻ አድርጎ እስከ ጉለሌ እና ላፍቶ ድረስ ሊሰራ የታሰበ ሲሆን በመሃል ከተማ አከባቢ ጨለማን ተገን በማድረግ ተፈጻሚ ይሆናል::ሲሉ የምኒሊክ ሳልሳዊ ምንጮች ተናግረዋል::
ስለዚህ በሰፊው ማብራሪያው ደርሶን መርጃውን እስከምንሰጣቹህ ድረስ ይህንን መሰረታዊ መረጃ ተመርኩዛችሁ ቤያንዳንዱ እንቅስቃሴያችሁ ላይ ከ ፈጣሪ ጋር ተጠንቅቃችሁ እንድትታገሉ ምክር እየሰጠን ለሁላችንም ፈጣሪ ይረዳን ዘንድ በፆም እና በጸሎት እንድንተጋ መልእክታችንን እናስተላልፋለን::

የጁኔይዲ ሳዶን ወደ ኬኒያ መሰደድ ተከትሎ የፌደራል ፖሊስ ምላሽ ሰጠ


“ጁኔይዲ ሳዶ በወንጀል አልተከሰሱም፤ እንደማንኛውም ዜጋ የመውጣትና የመግባት መብት አላቸው”

የፌዴራል ፖሊስ

junedin
(ሰንደቅ ጋዜጣ) የቀድሞ የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትር አቶ ጁኔይዲ ሳዶ በጎረቤት ሀገር ኬኒያ በመሰደድ የፖለቲካ ጥገኝት መጠየቃቸውን ተከትሎ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀለኛ ስለመሆናቸው የማውቀው ነገር የለም ሲል ለሰንደቅ ጋዜጣ ገለፀ።
አቶ ጁኔይዲ ሳዶ ባለቤታቸው ወይዘሮ ሃቢባ መሐመድ በሽብር ተግባር ተሳታፊ ናቸው በሚል ጥርጣሬ በፌደራል አቃቤ ሕግ መከሰሳቸውን ተከትሎ በአዳማ የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ ባደረገው ስብሰባ ላይ ተገምግመው ከስራ አስፈፃሚነታቸው መሰናበታቸው ይታወቃል። ይህን የፖርቲውን ውሳኔ ተከትሎ ከሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትርነት ስልጣናቸውም ተሰናብተዋል። ከዚህ ተከታታይ ውሳኔዎች ጋር በተያያዘ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመከሰስ መብታቸውን በማንሳት ክስ ይመሰርትባቸዋል ተብሎ ይጠበቅ የነበረ ቢሆንም ይህ ሳይፈፀም ሰሞኑን ከሀገር መውጣታቸው ተሰምቷል።
የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የውጪና የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮማንደር አበበ ዘሚካኤል አነጋግረናቸው በሰጡን ምላሽ፤ “ጁኔይዲ ከሀገር ሊወጡ ይችላሉ ተብሎ በፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ሲደረግ የነበረ ክትትል አልነበረም። እኛ አቶ ጁኔይዲ የምናውቀው እንደማንኛውም ሰው ነው።”

አያይዘውም፤ “አቶ ጁኔይዲ ከሀገር እንዳይወጣ መከልከል የሚችለው በፍርድ ቤት ነው። ፍርድ ቤት ወንጀለኛ ወይም በወንጀል ይጠረጠራል የሚል ትዕዛዝ መስጠት አለበት። ስለዚህ ጉዳዩ በፍርድ ቤት እስካልተያዘ ድረስ እንደማንኛውም ዜጋ ከሀገር የመውጣትና የመግባት መብት አላቸው። በሕግ መብታቸው እስካተገፈፈ ድረስ ማንም ምንም ማድረግ አይችልም። ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽንም ግለሰቡን የመከታተል ሆነ ከሀገር እንዳይወጡ የሚከለክልበት ሕጋዊ መሰረት የለውም” ብለዋል።
ከወራት በፊት አዳማ በተደረገው የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ አቶ ጁኔይዲ ተገምግመው (ግለሂስ አድርገው) ጥፋታውን ማመናቸው ነው የሚነገረው። በዚህ ላይ ምን አስተያየት ይሰጣሉ ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ ኮማንደሩ በሰጡት ምላሽ፤ “አቶ ጁኔይዲ በድርጅቱ መገምገማቸውን አውቃለሁ። ድክመት እንደነበረባቸውም በግምገማው ጊዜ እንደተነገራቸው ይታወቃል። ድርጅቱ የሰጠውን ኃላፊነት በበቂ ሁኔታ አልተወጡም ማለት ግን ወንጀለኛ ናቸው ከሚለው ጋር ፈጽሞ የማይገናኝ ጉዳይ ነው” ብለዋል።
ባለቤታቸው በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው ከታሰሩበት ጉዳይ ጋር አቶ ጁኔይዲ እጃቸው አለበት ስለሚባለውም ጉዳይ ኮማንደር አበበ ተጠይቀው፤ “የምናውቀው ነገር የለም። መታወቅ ያለበት ባልና ሚስት አብረው ሲኖሩ ሚስት በመሰላት መንገድ የመኖር መብቷ የተጠበቀ ነው። ስለዚህ የአቶ ጁኔይዲ ሚስት የመረጠችው መንገድ ወይም መብቷን ተጠቅማ ይሆናል። የተከተለችው መንገድ ተገቢ ነው፣ አይደለም የሚለው የፍርድ ቤት ጉዳይ ነው የሚሆነው። አቶ ጁኔይዲ ግን ማድረግ የነበረበት ያላደረገው ነገር አለ ብሎ መከራከር ግን አስቸጋሪ ነው የሚሆነው። ምክንያቱም የሚስቱ መብት በሕግ የተጠበቀ መብት በመሆኑ ነው። ስህተት የሰራው ግን፣ ከሕግ በፊት ባለቤቴ ነፃ ነች። ፌደራል ፖሊስ ያለመረጃ ነው የያዛት ብሎ መናገሩ ነው። ከአንድ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣን ይህ መሰል ተግባር አይጠበቅም። በዚህም ድርጊታቸው ተገምግመዋል። ነገር ግን ጉዳዩ ወንጀለኛ ነው አያስብልም” ሲሉ ኮማንደር አበበ ዘሚካኤል ተናግረዋል።
ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የአቶ ጁኔይዲ የመከሰስ መብት በየተወካዮች ምክር ቤት እንዲሳም ጥያቄ ስለመቅረቡም ጉዳይ ኮማንደር አበበ “የማውቀው ነገር የለም” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ታህሳስ 18 ቀን 2005 ዓ.ም ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ “የአንድ የም/ቤት አባልን የሕግ ከለላ ስለማንሳት የቀረበ የውሣኔ ኀሳብን መርምሮ ስለማፅደቅ” በሚል ለውይይት አጀንዳ ከያዘ በኋላ አፈጉባዔ አቶ አባዱላ ገመዳ ባልታወቀ ምክንያት አጀንዳው ለሌላ ጊዜ እንዲተላለፍ መደረጉን ለም/ቤቱ አባላት በመግለፅ ም/ቤቱ አጀንዳው ላይ ሳይወያይ ቀርቷል።
ምንጮቻችን እንደገለፁት ይህ አጀንዳ አቶ ጁኔይዲንን የሚመለከት እንደነበር በማስታወስ ም/ቤቱ አጀንዳው ላይ ተወያይቶ ውሣኔ ባለመስጠቱ አቶ ጁኔይዲን ምንም ዓይነት ክስ ሳይቀርብባቸው ከአገር እንዲወጡ ምክንያት መሆኑን አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

Tuesday, February 26, 2013

የጠራራ ጸሃይ ሰርሳሪ ሌቦች (ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም)


በ2008 በጠራራ ጸሃይ ሰርሳሪ ሌቦች 16 ሚሊዮን ደላር የሚያወጣ የወርቅ ጥርብ
ሰርቀው ያለአንዳች ችግር ከባንኩ ቅጥር ሲወጡ ተስተውሏል፡፡ ምንም እንኳን
ድርጊቱ የውስጥ አዋቂወች ደባ መሆኑ ቢታወቅና በተወሰኑ ሰዎች ላይ ጣት ቢቀሰርም ምንም የተወሰደ የሕግ እርምጃ
አልታየምም አልተሰማም፡፡ በ2007 የመንግስት ሃብት የሀነውን 600 ሚሊየን ደላር ከክልሉ በጅረወንድ ካዝና
መሰወሩን ለማ አራጋው ይፋ ሲያደርግም መለስ ዜናዊ አፍንጫን ሲመቱት አይን ያለቅሳል ሆኖበት ለማን ከስራ አሰናብቶ
በህዝብ ፊት ክልሉ ካሽ ገንዘቡን ሊያቃጥል ይችላል በማለት የጎዳና ምላሽ ሰጠ፡፡ የዚያ የተቃጠለ ገንዘብ አመድም አልተገኘም፡፡
በፌብሪዋሪ 2011 ለዓለም ገበያ ሊቀርብ የተዘጋጀው 10000ቶን ቡና ከመጋዘኑ እምጥ ይግባ ስምጥጥ ሳይታወቅ መቅረቱን
መለስ ዜናዊ በይፋ ተናግሮ ነበር፡፡ በዚህ ሳቢያም ነጋዴዎችን ሰብስቦ በቪዲዮ
በተቀረጸ ቃለ መለስ መልእክቱ ‹‹ለአሁኑ ይቅርታ እናደርግላችኋለን ምክንያቱም
በዚህ ቡና መሰወር የሁላችንም እጅ ስላለበት አለ፡፡ ሁሉም አይፈራም ጋሜን እየዘፈኑ ቡና ጠጥተው ወደ የመጡበት
ተመለሱ፡፡
ባለፈው ዲሴምበር ላይ ፋይናንሻል ግለባል 
ኢንተግሪቲ ሲዘግብ ኢትየጵያ አነስተኛ
የኤኮኖሚ አቅም ያላት ሃገር በ2000 እና በ2009 መሃከል በህገወጥ መንገድ ሃገር
እየጣሰ የወጣው 11.7 ቢሊዮን ዶላር፤ 
ይበላጣል› በማለት ነበር የዘገበው፡፡

በሽብርተኝነት ተከሰው በወህኒ ቤት የሚገኙ በጣም በርካታ እስረኞች የይቅርታ ፎርም እንዲሞሉ እየተደረገ ነው


በሽብርተኝነት ተከሰው በወህኒ ቤት የሚገኙ በጣም በርካታ እስረኞች የይቅርታ ፎርም እንዲሞሉ እየተደረገ ነው (ምንአልባት የሀይለማርያም መንግስት ሪፎርም /ማሻሻያ/ የማድርግ ዕቅድ ካለው በዚሁ ሊጀምር አስቦ ሊሆን ይችላል፤ አሊያም እንደተለመደው እስረኛ በመልቀቅ የፖለቲካ ማሻሻያ እንደተደረገ ለማስመሰል ይሆናል)፡፡ ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ እና ዘሪሁን ገ/እግዚአብሄርም በብዛት ከሚለቀቁት እስረኞች ጋር አብረው እንደሚፈቱ ምንጮቼ አረጋግጠውልኛል፡፡
አጀንዳችን…
ዛሬ በከፍተኛው ፍርድ ቤት የእነእስክንድር ነጋን ንብረት ለመውረስ ፍትህ ሚንስቴር የመሰረተው ክስ ሲታይ ውሎአል፡፡
እስክንድር ከዚህ ቀደም ‹‹የታሰርኩት በግፍ ስለሆነ ንብረቴን አትውረሱ ብዬ አልከራከርም፤ ዛሬውኑ ልትወስዱት ትችላላችሁ›› በማለት ያልተከራከረ ሲሆን፣ የአበበ በለውን ንብረት በሚመለከት በሌለበት ታይቷል፡፡ የአንዱአለም አራጌ ባለቤት ደግሞ በስሟ የተመዘገበው መኪና መወረሱ አግባብ እንዳልሆነ በጠበቃዋ አቶ ደርበው ተመስገን አማካኝነት ተከራክራለች፡፡ ፍርድ ቤቱም ለውሳኔ የፊታችን ሚያዚያ አስር ቀን ቀጠሮ ሰጥቷል (በእኔ ግምት ቀጠሮው እንዲህ የራቀው መጋቢት አስራ ስምንት ቀን እነእስክንድር የጠየቁት ይግባኝ የመጨረሻ ውሳኔ ስለሚሰጥበት ከዛ በኋላ የንብረቱን ጉዳይ ለመጨረስ ይመስለኛል)
የሆነ ሆኖ ዓቃቢ ህግ የእስክንድር ንብረት ተብለው ከቀረቡት ባለሁለት ፎቅ ዘመናዊ መኖሪያ ቤት፣ በባለቤቱ ጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲል ስም የተመዘገበ የቤት መኪና፣ እንዲሁም የእስክንድር እናት ንብረት የሆነ በአንድ ሺህ ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ መኖሪያ ቤትን ለመውረስ ጥያቄ ያቀረበ ቢሆንም፣ በዛሬው ዕለት በእናቱ ስም የተመዘገበውን ቤት እንደተወው ገልጿል (አዲስ ታይምስ መፅሄት የእናቱ ቤት ዝርዝር ውስጥ መግባቱ ተገቢ አለመሆኑን ደጋግማ መግለጿ የሚታወስ ነው)፡፡
ይህንና ዓቃቢ ህግ በእስክንድር እናት ስም የተመዘገበውን መኖሪያ ቤት ከሚወርሳቸው ዝርዝር ውስጥ በማውጣቱ ምንም አይነት ምስጋና የለኝም፡፡ ምክንያቱም እንኳን ንብረታቸው ተከሳሾቹም ምንም ጥፋት ያላጠፉ ንፁሀን ናቸው ብዬ ስለማምን፡፡ ስለዚህም አሁንም እንዲህ እላለሁ፡- ዓቃቢ ህግ ዕዳ አለብህ! አዎ እዳ አለብህ!! ንፁሀን ወንድሞቻችንን ይቅርታ ጠይቀህ እስክትለቅልን ድረስ!!!

ESAT : Insight Felix Horne, Consultant at Human Rights Watch(Ethiopia)


በጋምቤላ ነዳጅ ተገኘ


ቱሎው ኦይል የሚባለው የነዳጅ ፍለጋ ላይ የተሰማራው ድርጅት እያካሄደ ያለው ቁፋሮ ውጤታማ መሆኑንና ቁፋሮው በተሳካ መልኩ እየተካሄደ በመሆኑ በአጭር ጊዜ ውጤቱን እንደሚያስታወቁ ሚኒስትሯ መናገራቸውን ተመልክቷል። በጋምቤላ ነዳጅ እየፈለገ ያለው የካናዳ ኩባንያ የተሳካ ውጤት እያስመዘገበ በመሆኑ ተጨማሪ ቦታ እንደተሰጠው ይፋ መደረጉ ይታወሳል። ከአካባቢው የሚወጡ መረጃዎች ነዳጅ እንዳለና ጥቅም ላይ መዋል እንደሚችል በመረጋገጡ ተጨማሪ ቦታ መከለል አስፈልጓል።
በፊርማው ወቅትም የማዕድን ሚኒስትሯ ወይዘሮ ስንቅነሽ እጅጉ “ነዳጅ ፈላጊ ኩባንያው በሃገሪቱ ጥናቶችን ሲያደርግ እንደመቆየቱና በሌሎች ሃገራትም ስኬታማ ስራዎችን እንደመስራቱ፣ ፍለጋው ውጤታማ ይሆናል ብለን እናምናለን” ብለዋል። የኩባንያው ዋና ስራ አስፈጻሚ ጀምስ ፍሊፕስ  “በኢትዮዽያም ተስፋ ሰጪ ጥናቶችን አካሂደናል ወጤታማ እንደምንሆነም እምነታችን ነው” ማለታቸውን ፋና ገልጿል።

የመናገር ነጻነት ዘመቻው ለህወሃት መራሹ መንግስት ምኑ ነው?


From Borkena blog/ ቦርከና
ሰሞኑን የዞን 9 አባላት የብሎጋቸውን በኢትዮጵያ መከልከል ተከትሎ ከክፈቱልን ያለፈ ፤ መሰረታዊ ሊባል የሚችል ዘመቻ በማህበራዊ ድህረ ገጾች ጀምረዋል፡፡ በዚህ ደረጃ ምላሽ መስጠቱ እና መጠቀም የሚቻለውን መድረክ ተጠቅሞ የችግሩን ጥልቀት ለማመላከት መሞከር ጥሩ ነው። ነገር ግን የመጻፍ እና ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት እየተጠየቁ ያሉትን ቡድኖች(‘ፎርማሊ’ ካወራን መንግስት ናቸው -ያውም ፈላጭ ቆራጪ) ባህሪ  ግምት ውስጥ በማስገባት፤ ዘመቻው እነዚሁ ቡድኖች አምነትውበት በማናለብኝነት የወሰዱትን ርምጃ ከማስቀየር ይልቅ በስነ ልቦናቸው ለተቀረጸው የትምክህት እና የበላይነት አስተሳሰብ ሃሴት የሚሰጥ ሆኖ ስለተሰማኝ ለነሱ ትምክህት ሃሴት ላለማዋጣት ስል በዚህ በዘመቻ አልተሳተፉኩም።
እንኳንስ የመናገር ነጻነት አይደለም ለእምነት ነጻነት ጀርባቸውን ሰጥተው የክስርቲያኑን የእምነት ተቋማት በቁጥጥር ስር አድርገው ሙስሊሙንም እንዲሁ እምነቱን ለመንጠቅ ቤት ለቤት ጭምር አሰሳ የገቡ ሰዎች ናቸው፡፡ የመናገር እና ሃሳብን የመግለጽ ነጻነት ጋር በእጂጉ የተቆራኘ  የጋዜጣ ህትመት ማስቆም ሳያንሳቸው ዜጎችን –ያውም ኩሩ ሀገር ወዳድ ዜጎችን በሽብረተኛነት በመክሰስ ፣ብዙ እንግልት በማድረስ እና ክብራቸውን ጭምር ለማዋረድ በመሞከር ሌሌች ዜጎች የዜግነት ክብር እና ነጻነት  ጥያቄ ቅብጠት እና በህይወት መቀለድ እንዲመስላቸው በማድረግ የባርነትን እስተሳሰብ በደህንነት ተቋማት ፣በህግ ተቋማት እንዲሁም የማህበራዊ ድንዝዝነት በሚያስፋፉ ሌሎች ልማዶች የሚስፋፉበትን መንገድ በስውርም በግልጽም በማበረታታት  የባርነትን መስረት ለማጽናት ሌት ከቀን የሚሰሩ ለመሆናቸው ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ሁኔታ ያለ ብዙ ምርምር ቁልጭ አድርጎ ያሳያል።
የህገ-መንግስት ጉዳይ እና የዜጎች መብት ፋይዳ ሳይገባቸው ቀርቶ ነው እንዳይባል፤ ትግል ጀመርንም ጨረስንም የሚሉባቸውን ቀናቶች በብሔራዊ ደረጃ ጭምር እንዲከበርላቸው የሚፈልጉ ናቸው። እንዲያውም ያለባቸውን የስነ-ልቦና ችግር ከሚያመላክቱ ነገሮች  እንደኛው ይሄው ነው። ህወሃት ስልሳ ሺህ  ሰው ሰዋበት የሚሉትን በዓላቸውን የሚያዳንቁትን እና ሰው እንዲያዳንቅላቸው የሚፈልጉትን ያህል ለኢትዮጵያ ነጻነት ከጎጠኝነት በጸዳ በንጹህ የሃገር ፍቅር ስሜት የወደቁ በሚሊየን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያኖች ጉዳይ እንዲነሳም እንዲታወስም እይፈልጉም። ታሪኩ ሲነገር ያሳንሳቸዋላ!የሃሳብ ነጻነት ወደሚያፈኑበት ጉዳይ ስመለስ -የሚያፍኑበት እና ሃሳብ እንደጦር የሚፈሩበት ጉዳይ ምንድን ነው የተባለ እንደሆነ መሳሪያ እንቆ የተኮፈሰ የፓለቲካ ስብዕናቸውን የሚያኮስስ ስለሚመስላቸው። እደፊኛ የሚነፉትን ፕሮፓጋንዳ የሚያስተነፍስ ስለሚመስላቸው። የሃሳብ ልውውጥ ላይ ያለ ስለት ስለሚያስፈራቸው። አንግበው ለተነሱት የትምክህት እና የበላይነት ግንባታ ዓላማ እንቅፋት እንደሆነ ጠንቅቀው ስለሚያውቁ ይመስለኛል። የእምነት ነጻነትም እስከመንጠቅ የሄዱበት ምክንያት ከፍራቻ ውጭ ሌላ ሊሆን አይችልም። የፍርሃት ገጹ ይለያያል።  የህወሃት መራሹ መንግስት ፍርሃት በአንድ በኩል በጥጋብ እና በማናለብኝነት የተከናነበ ይመስላል በሌላ በኩል ደሞ በልማት ዲስኩር ተከልሎ ከዲስኩሩ በስከጀርባ በምናቡ የሚስላቸውን “ጸረ-ልማት ሃይሎች” (ኢትዮጵያውያኖች እኮ ናቸው የኢትዮጵያ ልማት ጠላቶች?) እንደምክንያት እየተጠቀመ የአፈና የሚጧጡፍበት የሞራል ፈቃድ አብረውት ክሚሰሩት “እህት ድርጂቶች”  ይወስዳል፡፡ በህወሃት “የማይበገር ጀግንነት” ውስጥ ያለው እውነታ (‘ሪያሊቲ’) ሃሳብን በነጻነት የመግልጽ መብትን እስከመፍራት የሚያደርስ ፍርሃት ነው። የደህንነት ተቋማቱም እወቃቀር የሚሰማቸውን የፍርሃት ደረጃ ግምት ውስጥ ያስገባ ይመስላል።ስለ ህወሃቶች እና ስለገነቡት የማፈኛ ተቋም የራሴም የሰዎችም ተሞክሮ አለኝ። ገና በልጂነት ባደኩባት የደሴ  ከተማ ፓሊስ(ህወሃት ለአፈና ተግባር ካሰለጠናቸው ውስጥ ነበር)   አንዱን ያለ እግባብ እያንገላታ ለማሰር ዱብ እንቅ ሲል (እንደዛ ይደረግ የነበረው ደሞ ለሃገሩ በብሄራዊ ውትድርና ዘምቶ የመጣ ዜጋ ነው-የገባው የሚመስለው የፖለቲካ ሁኔታ እንገቱን ባያስደፋው ኖሮ የዛን ለፍዳዳ ፖሊስ ጥርሱን የሚያራግፍ ጎበዝ ነበር። አውቀዋለሁ ) ነገሩ ከንክኖኝ ከፖሊሱ ጋር “የምን እደረገህ” ያደረገውም ነገር ካለ በስነ-ስርዐት ውሰደው የሚል ሙግት ውስጥ ገባሁ። ከዚያ በኋላ ፖሊሱ ልጁን ትቶ ወደኔ ዞረ። ዱላም ጀመረ። ታሳሪው እኔ ሆንኩ፡፡ እና ሂድ እልሄድም ውዝግብ ተጀመረ።  ጓደኛየ ታደሰ ባየ( ፌስ ቡክ ላይ አለ) በዛ በዝናብ ተንበርክኮ ሁሉ ለመነው ፓሊሱን፡፡ እኔ ደሞ እንኳን ልለምነው እንዴት ድንጋይ እንደሆነ በተጋጋሚ እነግረዋለሁ። የመምታት አቅሙን ተጠቅሞ ያ ሁሉ የፖሊስ ዱላ ወረደብኝ። በመጨረሻ ላለመታሰር ጨለማውን ምክንያት እድርገን ሁለታችንም አመለጥነው። የተመታሁት ብዙ እንደነበረ የገባኝ ግን በነገታው  መሄድ እቅቶኝ ቀኑን አልጋ ላይ ሳሳልፍ ነው።  ያኔ ተናድጄ ስለነበር ምንም አልተሰማኝም።   ሶስት ቀን ያህል ሳያስነክሰኝ አልቀረም።
Eskinderኮተቤ እያለሁ ደሞ ሮብ  ሮብ መብራት ይጠፋ ነበር። በዚያ ምክንያት ረቡዕ ማታ አካባቢ ጥናት የለም ። ወክ ነው የምናደርገው። ወደ ገደራ እየሄድን ስናወራ የነበረውን ከኋላ ይሰማ የነበረ አስቁሞን መታወቂያችንን ከጠየቀ በኋላ እዚያው እካባቢ ወደ ነበረ ፓሊስ ጣቢያ ተወስደን ተመዝግበን የሚጠይቁትን ጠይቀው ተመልሰናል።  ሌላ ጊዜ እንዲሁ አራት ኪሎ ላይ የከተማ አውቶብስ ይዞ የነበረ የትግሪኛ ተናጋሪ ሾፌር  በራሱ ስህተት እና ትክምህት ምክንያት ተሳፋሪውን ከአራት ኪሎ ይዞ ሚኒሊክ እካባቢ ወደነበረው ፓሊስ ጣቢያ ወሰደን። በትግሪኛ አወራ ከሰዎቹ ጋር። እኛ “ጥፋተኞች ሆንን።” የተማሪዎች ዲን ነው ጣልቃ ገብቶ ነገሩ ያለቀው።የሌሎችን ተሞክሮ በሚመለከት እዚያው ያደኩባት ደሴ ከተማ ላይ በጠራራ ጸሃይ አፉን በደንብ ያልፈታ የህወሃት ታጣቂ እንድ ባዶ እጁን የነበረ ወጣት አሯሩጦ ከደረሰበት በኋላ ሰው እየተጯጯኽ የክላሹን አፈሙዝ ደረቱ  ላይ አድርጎ ተኩሶ ከገደለው በኋላ ክላሹን እንቆ እንደያዘ  ሲሄድ ያስቆመው ፓሊስ አልነበረም። ሌሎች ታጣቂዎችም ያሉት ነገር የለም። (በነገራችን ላይ ያኔ እስከማውቀው ድረስ የልጁ ገዳይ ለፍርድ እልቀረበም)እንደዛ እይነቱ የህወሃት ጭራቅነት በርሃ ባልነበሩት ዘመድ እዝማዶቻቸው ላይ ተጋብቶ “ምክንያታዊ” በሚመስል ሁኔታ  ስለፍትህ በሚጮሁ ኢትዮጵያውያን የሚያሳዩትን ቅጥ ያጣ ንቀት ማየት እሁን የተጀመረው እይነት ዘመቻ በበታችነት ስሜት በሚናጥ ስብናቸው እና እስተሳሰባችው ላይ የበላይነት እና የገዠነት ካባ ከሚደርብላቸው በስተቀር ትርጉም ያለው ጩኽት ይሆናል የሚል እምነት የለኝም። የማስጮህ ስሜት እንዲሰማቸው አልፈልግም። ዛሬ ፌስ ብክ ላይ እንዲህ ያለ ዘመቻ ባለበት ሰዐት እዚሁ ፌስ ቡክ ላይ እስክንድር ነጋን በሚመለክት የነዚሁ የህወሃት ወገን የሚመስሉ ሰዎች ያደረጉትን ምልልስ ለአብነት እንዲሆን ያህል ከ’ሆም ፔጂ ላይ ስክሪን ሾት’ ወስጃለሁ፡፡
ከዚያ ውጭ የህግ ስርኦት ያለበት ሃገር ቢሆን ኖሮ እንደ ዳንኤል ብርሃነ ያሉ የህወሃት ደጋፊዎች ሃገር ውስጥ ያለው የሃሳብ ሙግት በጸጥታ ሃይል እና በ”ፍትህ አካላት” እየታፈነ ባዶ ሆኖ ሙግታቸውን እና የሃሳብ ክርክራቸውን ከውጭ ሃገራት ሰዎች ጋር ሲያደርጉ ማየት የህወሃት ደጋፊዎች እና ዘመዶች ባይሆኑ ኖሮ ሊያስገርም ይችል ነበር። ከታች በሊንክ ባስቀመጥኩት የዳንኤል ጽሁፍ የሂውማን ራይቱ ቤን ራውለንስ የእንግሊዝ መንግስት የዕርዳታ እሰጣጥ የሚተች የመጽሃፍ ሪቪው  አወጣ ብሎ  የእንግሊዝ መንግስት ትችት ሳይሆን ምስጋና ነው የሚገባው የሚል ጽህፍ አውጥቶ ብሎጉም ላይ ጭምር ለጥፎታል። የጽሁፉ ዓላማ ምን ነበር የሚለው ሌላ ጥያቄ ሆኖ መነሳት ያለበት መሰረታዊ ጥያቄ እንደ ዳንኤል ያለው የህወሃት ፖለቲካ ደጋፊ ስለሆነ ብቻ ሃገር ቤት በሚታተሙም ራሱ በፈጠረውም ብሎግ ላይ የመጻፍ ነጻነት ሲሰጠው ሌሎች ዜጎች (ለምሳሌ የዞን ዘጠኝ ብሎገር አባላት) የሚታፈኑበት ምክንያት ከላይ የገለጽኩት ነው። እፈናውን ተቃውሞ የሚደረገውን ተቃውሞ ያልተቀላቀልኩበት ምክንያት የሚጨምርላቸውን -ተዋጋን እያሉ ለሚያወሩት ብቻ ሳይሆን ያኔ ልጆች ለነበሩት እና የደም ትስስር በሚመስል ምክንያት ብቻ እፈናን በምክንያታዊነት ለማስተባባል እና ተቀባይነት እንዲኖረው ለማድረግ ለሚሞክሩትም ጭምር- ለትምክህታቸው  የሚጨምረላቸውን ሃሴት ላለመስጠት ነው። የዳኤል ፓስት
ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው አምባገነናዊነት ሌላ ዓለም ከሚስተዋለው በመሰረታዊነት የሚለይ እንደሆነ እምኖ ተቀብሎ የሚደረገው ተቃውሞ የህወህትን እምባገነናዊ ባህሪ ግምት ውስጥ ያስገባ እና ህወሃቶች በመንፈስም በፖለቲካም የማይጠቀሙበት እና ትምክህት የማይጨምርላቸው መሆነ አለበት ብየ ስለማምን ነው፡፡  በሌላ አንጻር ደሞ የሚደረገው ዘመቻ መሬት ላይ ያለ እና ለህዝቡ ስነ-ልቦና እና አስተሳሰብ ቅርበት ያለው ፣ በቀላሉ የሚገባ ቢሆንም ጥሩ ነው። ምን ያህል ኢትዮጵያዊ ነው በፌስ ቡክ እና ትዊተር ላይ ያለው? ፌስ ቡክ ላይ ካለውስ የህወሃት ደጋፊ ከሆነው ውጭ ስለ ህወሃት መራሹ መንግስት አፈና እና ቅጥ ያጣ እምባገነናዊነት የማያውቀም ምን ያህሉ ነው? ለ “ዓለማቀፉ” ማህበረሰብ ነው እንዳይባል ለዚሁ አፈና ለሚያደርሰው መንግስት ትብብር እና ርዳታ የሚሰጡት እነዚሁ ወገኖች ናቸው። ዳንኤል የእንግሊዝን የእርዳታ አሰጣጥ በመደገፍ የእንግሊዝን መንግስት የሚከላከል ጽሁፍ መጻፍ ደረጃ ላይ የደረሰበት ”የዲፕሎማሲ” ልምምድ ሳይሆን የፖለቲካ ትስስርንም ጭምር የሚያመላክት ይመስለኛል። ለሃወሃት የጥጸጥታ ሃይሎች ስልጠና እና ሎጂስቲክ የሚያቀርበው ማን ነው? ብዙዎቹ የህወሃት ፖሊሲዎች በርግጥ ከህወህት ብቻ የመነጩ ናቸው? “የመለስ” ራዕይን ጨምሮ?

የደህንነት መስሪያ ቤት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞች ከአገር እንዳይወጡ አዘዘ


ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ አየር መንገድ 15 የትኬት እና 30 የኤርፖርት ሰራተኞችን ከስራ ካባረረ በሁዋላ ከአገር እንዳይወጡ አገደ። ከአየር መንገድ የውስጥ ምንጮች የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ሀብታሙ ጫኔ፣ ዳንኤል ገበየሁ፣ ኢማን ያሲን፣ ኤደን ካሳየ፣ ቤዛ ኤፍሬም፣ ይገርማል ታደሰ፣ ሰለሞን ይብራህ፣ ክንፈ ሚካኤል ሽጉጤን ጨምሮ በርካታ ሰራተኞች ከስራ የተባረሩ ሲሆን ፣ አየር መንገዱ ለደህንነት እና አሚግሬሽን መስሪያ ቤት በጻፈው ደብዳቤ ሰራተኞቹ ከአገር እንዳይወጡ አሳግዷል።
ሰራተኞቹ ከአገር እንዳይወጡ ሲታገዱ ከተዘረዘሩት ምክንያቶች መካከል ለህዳሴው ግድብ ገንዘብ ለማዋጣት ፈቃደኛ አለመሆን፣ የድርጅቱን ሚስጢራዊ መረጃዎች የአገር ጠላት ለሆኑት የሽብርተኞች ሚዲያዎች ለኢሳት እና ለፍትህ ጋዜጣ መስጠታቸው፣ እንዲሁም የባለራእዩን መሪ የአቶ መለስ ዜናዊን ራእይ ለማሳካት በሚል የተነደፈውን የስድስት ቀን የነጻ የስራ አገልግሎት እቅድ ተግባራዊ ለማድረግ ፈቃደኛ አለመሆን የሚሉት ይገኙበታል። የሰራተኞቹ ፓስፓርት ቁጥር ለኢሚግሬሽንና ደህንነት ክፍል በመላኩ ሰራተኞች ከአገር ለመውጣትና ራሳቸውን ለማዳን አልቻሉም።
ከዚህ ቀደም ከስራ ከተባረሩት መካከል ከሙስሊሙ እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ የታሰሩት ሰባ ማይልስ ስራ አስኪያጅ እስካሁን አልተፈቱም።
አካሉ አሰፋ፣ አንተሰናይ አማረ፣ ቤተልሄም ተፈራ፣ ቤተልሄም ጌታቸው፣ ኤደን በየነ፣ ኤደን ካሳየ፣ ኢማን ያሲን፣ ሳሙኤል እንዳለ፣ ሶሎሞን በቀለ፣ አይዳ ዘልኡል፣ አማኑኤል በልስቲ፣ አማኑኤል ነጋሽ፣ አማኑኤል ጸጋው፣ አንዱአለም ግርማ፣ ብርሀኑ ሰሎሞን፣ ቸርነት አለሙ፣ እኑ ገብረእግዚአብሄር፣ ሀይማኖት ንጉሴ፣ ሂሩት መለሰ፣ ቅድስት አበራ፣ ቅድስት ከበደ፣ ማትያስ አድማሱ፣ መቅደስ አበራ፣ ሜላት አስራት፣ ትንግርት ደምሴ፣ ሳምራዊት ገረመው፣ ሰሚራ አማን፣ ተዘራ ወርቁ፣ ወንዶሰን ሀብቴ፣ ዮሀንስ ፍሰሀ እና አልአዛር ተክለ ሚካኤል ከአገር እንዳይወጡ ትእዛዝ ከተላለፈባቸው መካከል ይገኛሉ።
የተባረሩ ሰራተኞችን በተመለከተ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ስራ አስኪያጅን ለማነጋገር ተደጋጋሚ የስልክ ሙከራ ብናደርግም አልተሳካልንም። አየር መንገዱ ነባር ሰራተኞችን እያባረረ በታማኝ የኢህአዴግ አባላት እየተካ መሆኑን በተደጋጋሚ መዘገባችን ይታወሳል።

Sunday, February 24, 2013

«ለዚህ ሕዝብ ብትወድቅ ክብር ነው»



በትግል ዘመንም ውስጥ ሆነ ከትግል ውጭ በስልጣን ዘመን አቶ መለስ ዜናዊ በተንኮል አሳሪነታቸው በጣም ከመታወቃቸውም በላይ ይፈሩም ነበር ለምን ሲባል የሚጠነሡት ሃሳብ ብዙዎችን በጭምብል እንዲጠፉ ማድረጋቸው ይታወቃል እና ነው እርግጥም ነው አንድ ነገር ተጀምሮ ለገሰ ዜናዊ አለበት ከተባለ ወደ ኋላ የማይሸሽ ማንም የለም ፣ለዚያም ይመስላል መስራቾቹ ትግላቸውን ከምእራፉ ሳይደርሱ ገና በእንጭጩ ለመለየት የተገደዱት ።ዛሬም ሆነ ትላንት ስለ መልካምነታቸው ከሚወራው ይልቅ ስለ ክፋታቸው የሚወራው ይበልጥ ይገን ነበር በተለይም ስልጣን ይዘው ለ14 አመታት እስከመሩበት ጊዜ ድረስ ማለትም 1997 ምንም ነገር በሃገሪቱ ላይ ሳይሰሩ ገንዘብ ከአለም አቀፍ አገራት በመቀበል እና በመሸኘት የተካኑት እና ለቅርብ ወገኖቻቸው እንዲሁም አባሎቻቸው በማደል ጥቅማቸው እንዳይነካ በማስከበር ትልቁን ሚና ሲጫወቱ መቆየታቸው ይታወሳል ።ሆኖም በምርጫ 97 አመተ ምህረት የህብረተሰቡን የፖለቲካ ንቃተ ህሊና የጠነሰሰ ጉዳይ ተፈጠረ ።በቅንጅት የተሰኘው የሰማይ ላይ ጉም ታይቶ ብን ያለ ለህዙ ተስፋ እንደ መና መግቦ ረሃብ የለቀቀ የጨለማ ተስፈኞች የተሰባሰበበት ድርጅት ፣በመሰረታዊ እድገቶች እና የሃገር ጉዳይ ጥቅም ላይ ሲያሽከረክራቸው በነበራቸው ቁም ነገሮች ላይ ወያኔን አይኑን ገልጦ እንዲመለከት እረዳው ዛሬም ድረስ አድገናል ብለው የሚደነፉበትን መንገድ እንዲጠርግላቸው እረድቶአቸዋል ።ይህም ሆኖ ሳለ በመለስ አስተዳደር የሚመራው ድርጅት ካፒታሉን በሃገሪቱ ላይ መሰረት ጥሎ ዘረፋውን ማከናወኑን ቀጥሎ ከበስተጀርባ በደሃው ህብረተሰብ ገንዘብ ደግሞ አባይን እንገድብ በማለት ጥንሥስ ሃሳብ ይዞ በመምጣት የህብረተሰብን ቀልብ ለመግዛት ቢሞክርም ከድጡ ወደ ማቱ መግባቱን አለማወቁን የተረዱት ወያኔዎች የትምኒትን እና እንደዚሁም የኢፈርትን ካፒታል ወደ ኋላ በመሸሸግ የህዝቡን ገንዘብ እና ደመወዝ በማራቆት ቁፋሮ በመጀመሩ የህዳሴው አባት እያሉ ማቆላመጣቸውን ተያያዙት ፣አዎ መለስ እውነትም የህዳሴው የለውጥ አርአያ ነው ተብሎ ሊወደስ የሚገባው አጡራ ሰው ነው ማለት የማይቻል ለመሆኑ የሃገሪቱ ህዝብ ብቻ ምስክር ሊሆን እንደሚችል ይታወቃል ፣ ምክንያቱም በመጀመሪያ ደረጃ ተፈጥሮ ያደለችንን ነሳነታችንን የነፈገን፣ብዙ ንጹሃኖችን ያስገደለ ፣ወዳጆቹን በመርዝ ያስጨረሰ ፣ብሎም ነጻ ፕሬሱን እና የሃገሪቱን ህግጋት በማገላበጥ ከብሄር ብሄረሰቦች አንድነት የቂም በቀልነት እና ጥላቻን የዘራብን የ እፉኝት እባብ መርዝ እንደነበር ሁላችንም ልንረዳው እና ልናውቀው የምንችለው ሃሳብ ነው ።ሆኖም ዛሬ ይህንን እንዲህ ለመናገር ያስቻለኝ የተለያዩ ህትመቶችን ሳገላብጥ የሃገሪቱ ከምታሳትማቸው እና በወያኔ መንግስት ስር ብቻ የሚተዳደሩት መገናኛ ብዙሃናት ያሉ የህትመት ድርጅቶች ፈቃድ አግኝተው ከሚያሳትሙት ዘመን መጽሄት ላይ ስለ አቶ መለስ ዜናዊ ስዩም መስፍን የተናገረውን ሃሳብ እኔም ለወዳጆቼ ላካፍላችሁ በማለት ከስር ሙሉ ቃለመጠይቁን አቀረብኩት ።አጠቃላይ ከርእሱ ጀምሮ ሙሉ ቃለመጠይቁ ከዘመን መጽሄት መወሰዱን ከመግለጽ አላልፍም ይህንንም ስናደርግ አሁን መንግስት በዚህ መገናኛ ብዙሃን ላይ ማስፈር የሚፈልገውን ሃሳብ ከመፍቀድ ወደ ኋላ አንልም ፣መማር ብቻም ሳይሆን ማስተማር እንደምንችል የምናሳይበት ትልቁ አብነታችን ነው ።
ላለፉት 40 ዓመታት አብረው ቆይተዋል፡፡ ከሰኔ 1964 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እንደ ወንድምም፣ እንደ ስራ ባልደረባም፣ እንደ ትግል ጓድም ሆነው ብዙ ውጣ ውረዶችን አብረው አሳልፈዋል፤ አቶ መለስና አምባሳደር ስዩም መስፍን፡፡ መለስ እንደ ማለዳ ጀንበር ለአፍታ ቀና ብሎ ሕዝቡ ለእርሱ ያሳየውን ክብርና ፍቅር ባየ እንዴት መልካም ነበር? የሚሉት አምባሳደር ስዩም በትግሉ ዘመን ከአቶ መለስ ጋር ስላሳለፉት መከራና ችግር፤ ስለ አቶ መለስ ባህሪም አጫውተውናል፡፡ አምባሳደር ስዩም በጓዳቸው ህልፈት ክፉኛ ማዘናቸው ያስታውቃል፡፡ ባነጋገርናቸው ጊዜም እንባቸው ለመውረድ ይታገላቸው ነበር፡፡ ሆኖም ግን ‹እንበርታ እግዚአብሄሔር ያፅናን› ብለዋል፡፡
 
ዘመን፦ እንደሚታወቀው በጠቅላይ ሚኒስትሩ ሞት የኢትዮጵያ ሕዝብ በጣም አዝኗል። ይህን ኀዘን እርስዎ እንዴት ይገልፁታል?
አምባሳደር ስዩም፦ ሕዝቡ ከሚገልፀው የተሻለ አንደበት የለኝም። ጥልቅ ኀዘን ውስጥ ነው ያለነው። አገሪቱ በሙሉ፤ በውስጥም በውጭም ያለው ሕዝባችን፣ የኢትዮጵያ ወዳጅ፣ጠቅላይ ሚኒስትሩን ያውቁዋቸው የነበሩና ጓደኞቻቸው በሙሉ ያልተጠበቀና ድንገተኛ ህልፈት ስለሆነባቸው ሁሉም ጥልቅ ሐዘን ውስጥ ነው ያሉት። እንግዲህ ይሄ የተፈጥሮ ሕግ ነው። የሰው ልጅ በህይወት እንደሚኖር ሁሉ ማለፉ ደግሞ የማይቀር ነው። በእርግጥ የጠቅላይ ሚኒስትር መለስን ህልፈት በብዙ መንገድ መቀበል አቅቶናል፡፡ ምክንያቱም ብዙ ውጥን ነበረው።
እንደሚታወቀው ድርጅቱ(ኢህአዴግ) የአመራር ሽግግር ላይ ነው ያለው። ከኔ የተሻለ ወጣቱ ትውልድ ቦታውን ይረከብ የሚል አቋም ነበረው፡፡ እናም ስልጣኔን እለቃለሁ ማረፍም እፈልጋለሁ ሲል ቆይቷል።የድርጅቱ ውሳኔ ስለሆነበትና እስከ መጪው ምርጫ ድረስ አምስት ዓመታቱን በግድ መቆየት አለብህ ተብሎ ነው በስልጣን ላይ እስካሁን የቆየው፡፡ ይህን ግን እርሱ ባያምንበትም ለድርጅቱ ዴሞክራሲያዊ ውሳኔ ተገዢ ሆኖ ነው የቀጠለው። በዚህ አምስት አመታት ውስጥም የወጣቱንና የአዲሱን ትውልድ የአገር ተረካቢነት ሚና የማጠናከርና በድርጅቱም፣ በመንግሥትም ውስጥ ተተኪና ጠንካራ አመራርን የመፍጠር እቅድ ነበረው፡፡ ምክንያቱም የድርጅቱንና የመንግሥትን አመራር ሳያጠናክሩ የልማቱን ጉዞ በተያዘው አቅጣጫና በተፈለገው ፍጥነት ለማስኬድ ስለማይቻል ነው፡፡ ይህን እንደ አይነተኛ ጉዳይ አድርጎ ነው ሲንቀሳቀስ የነበረው፡፡ ይህ ውጥን ነበረው። ራዕዩ እውን እንዲሆንና የሕዝቡም ልማት በሚያስተማምን ፅኑ መሰረት ላይ እንዲቆም ፍላጎት ነበረው፡፡ እድል አግኝቶ እንደጠለቀችና ተመልሳ በነጋታው የብርሃኗን ድምቀት እንደምትሰጥ ፀሀይ ለአፍታም ቢሆን ቀና ብሎ ቢያየው እንዴት ጥሩ ነበር? እርሱ የቀየሰው ራዕዩ፣ መስመሩ፤ የኢህአዴግ አባልና ደጋፊው ብቻ ሳይሆን መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ በተለይ ደግሞ ጭቁኗ ሴት፣ አፍላው ወጣት፣አርሶአደሩ፣ ሰራተኛው፣ ምሁሩ፣ ባለሀብቱ፣ ነጋዴው፣ ሁሉም መፍትሄያችን ነው፣ የሀገራችን ህዳሴ ነው፣ ድህነት ከፈጠረብን ውርደት የምንወጣበት መንገድ ነው እያለ ነው፡፡ ይሄ የሁሉም አስተሳሰብ ሆኖ ሁሉም በአንድ ድምጽ በድህነት ላይ የዘመተበት መሆኑንና በዚህ ደረጃ ለእርሱ እየገለፀ ባለው ፍቅርና ሀዘን ልቡ እየነደደ መሆኑን ለማየት ቢችል ኖሮ ‹የቀረብኝ ነገር የለም፣ መስራት ያለብኝን ሥራ ሰርቻለሁ› በማለት ረክቶ በተመለሰ ነበር። ግና ሳይረካ እሰራለሁ ሲል ነው ያለፈው። ይህ ነው ለሁላችንም እንደእሳትና እንደረመጥ እያቃጠለን ያለው። ለማንኛውም ይህን ሕዝቡም፣ ወጣቱም እየገለፀው ነው፡፡ ኢህአዴግም የመንግሥት አመራሩም ኀዘን ከዚህ የተለየ አይደለም። ይህንን ሕዝብ ይዞ የመለስን ራዕይ ከዳር ለማድረስ ይቻላል። እናም በቁርጠኝነት ታጥቀን መነሳት አለብን፤ ሕዝባችንን አሰልፈን። መለስን የሚተካ አንድም ሰው ባይኖርም ቢያንስ እንደ ድርጅትና እንደመንግሥት ኃይላችንን አጠናክረን እንቀጥላለን፡፡ ኢህአዴግ ብዙ ፈተናዎች ደርሰውበት አዝኖ ኀዘኑንም ተቋቁሟል። እንደዚህ አይነት ከባድ ነገር ገጥሞት ባያውቅም የተለያዩ የህልውና የመኖርና ያለመኖር ፈተናዎች ገጥመውታል፡፡ ይህንንም ችግር ከሕዝቡ ጋር ሆነን እንወጣዋለን የሚል እምነት አለን። የእኔም እምነት ይሄ ነው።
ዘመን፦ አቶ መለስ የትግል አጋርዎ ናቸው፡፡ ለእርሳቸው የበለጠ ቀረቤታ ይኖርዎታል ብዬም አስባለሁ። በትግሉ ጊዜ ከነበራችሁ አንዳንድ ትውስታዎች ሊነግሩኝ ይችላሉ?
አምባሳደር ስዩም፦ የመለስ ራዕይ የሕዝብ ፍቅር ነው፡፡ይህም በቁርጠኝነት ተግባር ላይ እንዲውል ድርጅቱንና ሕዝቡን መርቶ ወደ ተግባር የመግባቱን ጉዳይ በስፋት የሚያውቅ ነው። እንዳልከው ቢያንስ ለአርባ አመታት አብረን ነበርን። ከጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ጋር በወጣትነት እድሜዬ በ 1964 ዓ.ም ክረምት ላይ ነው ለመጀመሪያ ጊዜ የተገናኘነው። ያኔ እርሱ የዊንጌት ትምህርቱን ጨርሶ በ1965 ዓ.ም ዩኒቨርስቲ ለመግባት ይጠባበቅ ነበር፡፡ በወቅቱ በነበረው የተማሪ ንቅናቄ ምክንያት ከመጀመሪያው ሴሚስተር በኋላ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተዘግቶ ስለነበር የዩኒቨርሲቲ ተማሪው ሁሉም በተደራጀ መልክ በወቅቱ በየጠቅላይ ግዛቱ ሄዶ ሕዝቡን እንዲያነሳሳና ከሕዝቡ ጋር የሚያገናኙት አንዳንድ ነገሮችን ይዞ ተንቀሳቅሷል፡፡ በእንቅስቃሴው ውስጥም አመራር ነበር፡፡
አድዋ ላይ እንደዚሁ ከትግራይ የተውጣጣ ቡድን በየጠቅላይ ግዛቱ አውራጃዎች ርዕሰ ከተሞች ይንቀሳቀስ ስለነበር የቅርጫትና የእጅ ኳስ ጨዋታ አለን በሚል ከአዲግራትና ከመቀሌ ተወጣጥተን አድዋ ንግሥት ሳባ ድረስ በሄድንበት ጊዜ አቶ መለስም እዛው ከነበሩት የዩንቨርሲቲ ተማሪዎች ጋር አብሮ ስለነበር እዚያ ተገናኝተናል፡፡እና ከእዚያ ጊዜ ጀምሮ ነው የምንተዋወቀው። በ65 ዓ.ም ነው አቶ መለስ ዩኒቨርሲቲ የገባው፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የተማሪውን እንቅስቃሴ መሰረት ያደረገ የትግራይ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ማህበር ነበር። ይህ የተቋቋመው ማህበር የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ማህበር ጋር በተጓዳኝ ይንቀሳቀስ ነበር፡፡ አቶ መለስ ያኔ ከሁላችንም ያነሰ ወጣት ነበር፡፡ ነገር ግን ጥናታዊ ጽሁፎችን በማቅረብና ውይይቶችን በመምራት በኩል የጎላ ሚና ነበረው። በተለይ በ1966 ዓ.ም የአገሪቱ አጠቃላይና አብዮታዊ እንቅስቃሴ ከዳር እስከ ዳር እየተቀጣጠለ የመጣበት ሁኔታ ነበር። ያኔም አቶ መለስ ከሳይንስ ፋኩልቲ ተመርጦ የተማሪዎች መማክርት አመራር ውስጥ ተካቶ ነበር። በእንዲህ ያለ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ ነው እንግዲህ በቅርብ ልንተዋወቅ የቻልነው፡፡ አቶ መለስ ያን ጊዜ ወጣትና ከሁላችንም ያነሰ ቢሆንም ብልህና አስተዋይ ነበር።በሳልና ብዙ አስተዋፅኦ ያበረከተ ሰው ነው፡፡ እንግዲህ በኋላም ደርግ የሕዝቡን አመፅ አኮላሽቶ ወታደራዊ አገዛዙን አውጆ ስልጣን ከያዘ ጀምሮ የትግራይ ተራማጆች ብሔራዊ ንቅናቄ ህቡዕ ድርጅት ትግሉን አጠናክሮ ቀጠለ፡፡እርሱም በአመራሩ ውስጥ ባይኖርም ያኔም በንቅናቄው ውስጥ ከታቀፉትና ከፍተኛ ሚና ከነበራቸው ታጋዮች አንዱ ነበር።የደርግ አካሄድ እጅግ አስከፊና ሁለትና ሶስት ሆኖ በጋራ መምከር የማይቻልበት ሁኔታ ነበር፡፡ በወቅቱም ፋሽስታዊው ደርግ የጭካኔ አዋጅ በማወጁ ሠላማዊ ትግል የሚባል ነገር የሚቻል አልነበረም። በእዚህም የትጥቅ ትግሉን መጀመር አለብን ብሎ የትግራይ ተራማጆች ብሔራዊ ንቅናቄ ውሳኔ ሲያስተላልፍ አቶ መለስም ከዩኒቨርሲቲ ወጥቶ የትጥቅ ትግሉን ለመቀላቀል ከሚዘጋጁት አንዱ ነበር። እርሱ መጀመሪያ በጥር ወር 1967 ዓ.ም ወደ ኤርትራ ለስልጠና ከተላኩት ጥቂት የዩኒቨርስቲ ተማሪ ታጋዮች ውስጥ አንዱ ነበር።ወታደራዊ ስልጠናውን ሳይጨርስ እርሱና አቶ አባይ ተመልሰው ወደ ፖለቲካ ስራ እንዲገቡና የትግሉን አቅጣጫ በሰነድና በማኒፌስቶ መልክ እንዲያዘጋጁ የቤት ስራ ስለተሰጣቸው በትግራይ ከተሞች በአክሱምና በአድዋ ተደብቀው ይህንን እንዲያዘጋጁ መመሪያ ተሰጥቷቸው ሲያዘጋጁ ቆይተዋል።
በመጨረሻም በ1967 ዓ.ም ደደቢት ወደነበረውና እዚያ ወደተሰማራው ኃይል ተቀላቅሏል።ስለዚህ በእዚህ ሁሉ የአቶ መለስ ሚና የጎላ ነበር። በተለይ ትግሉን የሚፈታተኑ ሁኔታዎች በሚያጋጥሙ ጊዜ የችግሩን ባህሪ፣ መውጪያና መፍትሄውን አሳማኝ በሆኑ መንገዶች ጥናቶችን አጥንቶ በማቅረብ ድርጅቱንና የድርጅቱን ህልውና በማስጠበቅ ድርጅቱ ሕዝባዊ እንዲሆን አድርጓል፡፡ የትግራይ ሕዝብን ብሔራዊ ትግል ከኢትዮጵያ ብሔሮችና ብሔረሰቦች መደባዊ ትግል ጋር እንዴት ይቀናጃል? የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች እንዴት ይሰባሰቡ? የሚሉ ጥያቄዎችን በማንሳትና የጠራ መስመር በማቅረብ የጎላና ተኪ የሌለው ሚና ሲጫወት ቆይቷል።እነዚህን ጉዳዮች ሁሉም የሚያውቃቸው ናቸው፡፡ ምናልባት ጠቃሚ መስሎ የሚታየኝ ባህሪያቸው ምን አይነት ነበር የሚለው ነው፡፡
ዘመን፦ አዎ! ስብዕናቸው ምን ይመስል ነበር?
አምባሳደር ስዩም፦ ከመጠን በላይ ሩህሩህ ነው። ወገን፣ደም አይለይም፡፡ የተጨነቀ፣ የተቸገረ ሲያይ እንባው ነው የሚቀድመው፡፡ ለኢትዮጵያ ህዝብ ብቻ አይደለም፣ የሁሉንም ህዝብ ታሪክ ያነባል፡፡ የታጋይና የጭቁን ሕዝቦችን ታሪክ ያነባል። ችግራቸውን እንዴት እንዳለፉት ያጤናል።ሁሉም ሕዝብ ፍጡር ነው፣ ሰው ነው ብሎ ያምናል።ሰውን በጣም ያከብራል። ሰው ሁሉ እኩል ነው የሚል የፀና አቋም አለው። እያንዳንዱ ሰው ሚና አለው ብሎም ያምናል። ሁሉም የራሱ ሚና አለውና ያን ሚና ይዞ ሲመጣ ውጤት ይመጣል ይላል። ያበረታታል። ሚናውን ይበልጥ የሚያጎለብትበትን መንገድ ያሳያል፡፡
መለስ የጎላ የሰው ፍቅር አለው። መለስን ቀርቦ ለሚያየው ከእርሱ ብዙ እንደሚማር ያውቃል። ሰብአዊ ርህራሄ የነበረው ሰው ነው። ሲያዝንም ያለቅሳል፣ ሲደሰትም፣ ሲቀልድም እንባውን ያፈሳል፤ ከልቡ። ለይምሰል ብሎ ሳቅ አይስቅም። የመለስ ንግግሮች ከሕዝቡ ኑሮና ከሕዝቡ ትግል የተለዩ አይደሉም። መለስ ሲስቅ ጥርሱን ገልጦና ከልቡ ነው፡፡ ሰው ምን ይለኛል አይልም፡፡ይቀልዳል፣ ይጫወታል፣ ሰውን ይቀርባል፡፡ይህ የአቶ መለስ ባህሪ ነው። መለስ ከትምህርት፣ ከጥናት፣ ከንባብ ተለይቶ አያውቅም።
በአጠቃላይ ለእውቀት ብቻ ብሎ አያነብም፡፡ ጥያቄ ይጠይቃል፡፡ ለጥያቄዎች መፍትሄ ፍለጋም ነው የሚያነበው። የሕዝብ ጥያቄዎች ሲሆኑ አንብቤ መልስ አገኝበታለሁ ይላል። ጽሑፎቹ ወታደራዊ ጥበብና ሳይንስ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ በሁሉም ዘርፎች ፈጣን ጥያቄዎች ሲነሱ መልስ አገኝበታለሁ ብሎ ይንቀሳቀሳል። ከተግባር ይማራል፣ ከመጽሐፍት ይማራል።ይህን ከማድረግ ወደ ኋላ ብሎ አያውቅም፡፡ ሌሎችንም ያስተምራል።ያወቀውን ሁሉ ያካፍላል፤ያጋራል።ይሄ የእኔ ነውና አንብቡ ብሎ አያውቅም፡፡ የሰራውን ስራ እዩልኝ፣ ይሄ የእኔ ውጤት ነው፣ይህን ሰርቻለሁ ብሎ አይኩራራም፡፡መታወቅን አይፈልግም። ይሄ ጎድሎኛ፤ ይህን ስጡኝ፣ ይሄ ያስፈልገኛልና ይሄን አድርጉልኝም ብሎ አያውቅም።
አባቱ አቶ ዜናዊ የነገሩኝን ታሪክ ልንገርህ፡፡ ጀነራል ዊንጌት ፈተና አልፈሃል ተብሎ አባቱ ከአድዋ በአውቶቡስ ይዘውት ወደ አዲስ አበባ ሲመጡ ወልዲያ ያድራሉ። ምሽት ወልድያ እራት እየበሉ« ምን ትጠጣለህ?» ይሉታል፡፡ «ውሃ» ይላል። ልብ በል ያኔ ገና ወጣት ነው። ስምንተኛ ክፍልን ጨርሶ ወደ ዘጠነኛ ክፍል አልፎ ነው ጀነራል ዊንጌት ይሄድ የነበረው። ያን ዕለት ታዲያ አባቱ አቶ ዜናዊ«ኮካኮላ ጠጣ» ይሉታል፡፡ «የለም ውሃ ነው የምጠጣው» ይላል፡፡ አባትየውም «ለምን? ገንዘብ የለውም ብለህ ነው? ችግርኮ የለም መጠጣት ትችላለህ» ይሉታል፡፡ በኋላ «አይ ከሆነስ እሺ» ብሎ ጠጣ ብለውኛል፡፡ አየህ አባቱንም፣ ቤተሰቡንም ማስቸገር አይፈልግም። ርቦኛል፣ ያስፈልገኛል፣ ይህን አድርጉልኝ፣ ይህን ግዙልኝ አይልም። ኮካኮላ በወቅቱ 25 ሳንቲም ነበር ግን ሊያስቸግር አልፈለገም።
ሌላ ከማስታውሰው ምን ያህል ለሰው ያስባል? ለቆመለት ዓላማስ ምን ያህል የፀና ነው? የሚለውን አንድ ነገር ላንሳልህ። የትጥቅ ትግሉ በ1967 ዓ.ም በተጀመረበት ወቅት ክረምት ሐምሌና ነሐሴ ላይ ዝናቡ ከፍተኛ ነበር፡፡ያኔ እንግዲህ ቤት ወይም መንደር ገብተህ አታድርም፡፡ ራስህን ደብቀህ በረሃ ነው የምትንቀሳቀሰው፡፡ ድርጅቱም ጥቂት የነበሩት ታጋዮችም ራሳቸውን ደብቀውና ሰው ካለበት ርቀው ራሳቸውን በማደራጀት ላይ ነበሩ፡፡ እና ጠላት ታጋዮቹም ገና ሳይበራከቱና ወደሌላ ሳይሻገሩ፣ትግሉን በእንጭጩ መቅጨት አለብን በሚል ነጭለባሾችንና ሰላዮቹን ያሰማራበት ጊዜ ስለነበር በጣም ፈታኝ ወቅት ነበር፡፡ ይሄ የመጀመሪያው የትግሉ ዓመት ነበር። በዚህ ፈታኝ ወቅት አቶ መለስ የታይፎይድ በሽታ ይታመማል። ታይፎይድ መሆኑን ያወቅነው በኋላ ላይ ነው። በጣም ከፍተኛ አደጋ ላይ ደርሶ ነበር። ሕይወቱንም እስከ ማጣት የደረሰበት ሁኔታ ነበር የተፈጠረው፡፡ያኔ እንግዲህ በዋልክበት አታድርም፣ እራት በበላህበት አታመሽም፣አታድርም፡፡ ቀንም ሌሊትም ጉዞ ላይ ነህ። በጊዜው እንደ መለስ ሁሉ በወባም፣ በተስቦም የታመሙ ሌሎች ታጋዮች ነበሩና እንቅስቃሴያችን ተገድቦ ነበር፡፡ የማስታውሰው አንድ በቅሎ ነበረን፤ ስንቅ ምናምን የሚያመላልስ፡፡ ከሁሉም በጠና ታሞ የነበረው አቶ መለስ ስለነበረ በዛ በቅሎ ላይ ብቻውን ተቀምጦ መጓዝ ስለማይችል ሰው ደግፎት ጉዞ ጀመርን፡፡ ጉዞው ደግሞ በጨለማ ነው፡፡ በወቅቱ እንቅስቃሴያችን ድብቅና የተገደበ ነው፡፡ ምክንያቱም ታጋዮች ገና የሚረባ ትጥቅ እንኳ ያልታጠቁበትና ያልተጠናከሩበት ጊዜ ነውና ‹እኔን ሲጎትቱ እዚህ አካባቢ ነው ያሉት የሚል ወሬ ለጠላት ከደረሰ አደጋ ላይ እጥላቸዋለሁ፤ የእነርሱንም ሕይወት ለአደጋ እዳርጋለሁ። እነርሱ ደግሞ አደጋ ላይ ከወደቁ ትግሉ በእንጭጩ ይቆማል› የሚል ስጋት አድሮበት ታጋዮቹ ባረፉበት ምዕራብ ትግራይ ቆላማ፣ተራራማና ገደላማ አካባቢ ነበር ‹ሕይወቴን ባጠፋ የእነርሱን ሕይወት አድናለሁ› ብሎ ያሰበው። ‹የእኔ ሕይወት ቶሎ ቢያልፍ ይሻላል፣ እኔን ሲጎትቱና እኔን ሲሉ አደጋ ላይ ይወድቃሉ፣ ለእኔ ሲሉ ያልሆነ ቦታ እያደሩና እየዋሉ ነው፣ እኔ ከሞትኩ ግን እንደልባቸው መንቀሳቀስ ይችላሉ› ብሎ አስቦ ኖሮ ታጋዮቹ ካረፉበት ቦታ ተንፏቆ ገደል አፋፍ ሊደርስ ሲል አዩት። ገደል ገብቶ ራሱን ሊያጠፋ ነበር ግን ያዙት። በእዚህ ጊዜ እርሱም ያለቅሳል፣ ታጋዮቹም ተላቅሰው ደግፈውት ጉዞው ቀጠለ፡፡ በኋላ ግን ነገሩ ጥሩ ሆነ፡፡ ከከተማና ከድርጅት መድሃኒት ተላኩልንና ከተወሰኑ ሳምንታት በኋላ ዳነ። መጨረሻ ላይ የነበረውን ሁኔታ ሲያጫውተን ተስፋ መቁረጥ ሳይሆን ለሌሎች ታጋዮች ሕይወት ሳስቶ የራሱን ሕይወት ለማጥፋት ወስኖ እንደነበር ነገረን፡፡ የእነርሱ ህይወት ከጠፋ የትግሉ ጉዞ ይሰናከላል፣ በእንጭጩ ይቀጫል ብሎ ስላሰበ ነው። እንዲህ አይነት ሰው ነው መለስ። እና እነዚህ ባህሪዎቹ ብዙም የሚታወቁ አይደሉም። አቶ መለስ ሰው አይለይም፡፡ በጣም በጣም አሳቢ ነው፡፡ አዛኝ ነው። ስስ ነው፤ ለሰው። ለሕዝቡና ለአገሩ የላቀ ስሜት አለው፡፡ አገር ሲባል ሕዝብ ነው፡፡ ከሕዝብ ውጪ የሚታይ ነገር የለም ብሎ የሚያስብ ሰው ነው መለስ።
ዘመን፦ ከእርስዎ ጋር በነበራችሁ ቀረቤታ ሌላሰ የሚያስታውሱት የተለየ ነገር ይኖራል?
አምባሳደር ስዩም፦ በሥራ፣ በትግል፣ በመንግሥት ኃላፊነትም አብረን ቆይተናል። ሳንገናኝ የቀረንበትን ቀን መቁጠሩ ይሻላል። አብረን ሰርተናል። የሚያየውን ጉድለት አይደብቅም።ጉድለትህን እንድትማርበት ነው የሚያነሳው፡፡ እርሱንም ጉድለት አለብህ ካልከውና በትክክል ጉድለቱን ከጠቆምከው ከመቀበል ወደኋላ አይልም። ጉድለቱን አይቶ ይቀበላል፣ ይማራል፣ ሰውንም ያስተምራል። ጉድለትህን ይነግርሃል፣ ያስተምርሃል። ይህን የሚያደርገው እንድትታነፅበት ነው። ኢህአዴግ መለስን አንጿል፣ መለስም ኢህአዴግን አንጿል። ገንብቷል። እኛ የምናየው በመለስ እይታና በመለስ ራዕይ፣ በመለስ መስመር፣ በመለስ ፖሊሲ የታነፁ ግድቦችን፣ መንገዶችን፣ የመሰረተ ልማት አውታሮችን፣ የኢኮኖሚ ልማትንና እነዚህን ነው፡፡ ጎልተው በተጨባጭ የሚታዩት እነዚህ ናቸው።መለስ ያነፀውና የማይጠፋው ነገር ካለ የሕዝቡ አስተሳሰብ ነው፡፡ ሀብትም የሚፈጥረው፣ ትራንስፎርሜሽን የሚያመጣውና የመጪውንም ትውልድ የሚወስነው ይሄ ነው። በሕዝቡ ውስጥ ያለው አስተሳሰብ ምን አንጿል? የሚለውን ነው መለስ የሚያየው፡፡ ድህነትን እናሸንፋለን። ሥራ ክቡር ነው። ሳይሰሩ መብላት ሀጢያት ነው። ሙስናን፣ ኪራይ ሰብሳቢነትን የሚያወግዝና ይህም የልማት፣ የትውልድ፣ የትንሳኤያችንና የሕዳሴያችን ነቀርሳ መሆኑን በወጣቱም ሆነ በሁሉም ዘንድ እንዲሰርጽ አድርጓል። በድርጅቱ ቁርጠኝነትን፣ የሕዝብ አገልጋይ መሆንን፣ የራስን ጥቅም ከሕዝብ ጥቅም፣ ልማትና እድገት ጋር የማስተሳሰርን አስተሳሰብ በታጋዩ፣ በደጋፊው፣በሕዝቡ ውስጥ ሰርጾ እንዲገባ ማድረግ ችሏል፡፡ ዋስትናችን ይሄ ነው በእዚህ አስተሳሰብ እንቀጥላለን ብሎ ሕዝቡ ይሄንን ስላመነበት ነው የተቀበለው። ለምንድን ነው ሕዝቡ በመለስ ህልፈት እንደዚህ አንጀቱ ያረረውና የተቃጠለው?
ዘመን፦ አዎ እርሱን ላነሳልዎት ነበር፡፡ አሁን ሕዝቡ በጣም በሚያስደንቅ ሁኔታ ነው ኀዘኑን እየገለፀ ያለው፡፡ ይሄ ከምን የመነጨ ነው ይላሉ?
አምባሳደር ስዩም፦ ይሄ ምንን ያሳያል? ይሄን ሀሳብና ራዕይ ያመነጨ፣ወደ ተግባር ያሸጋገረው መሪ ጠፋብኝ፤ ይሄን ያስታጠቀኝን መሪዬን አጣሁት፡፡ አከብርሃለሁ፡፡ ምክንያቱም አንተ የሰጠኸኝን ይዤ ተጠቃሚ ሆኛለሁ ነው ሕዝቡ የሚለው።ወጣቱም ሥራ አልባ ነበርኩ፣ ጨልሞብኝ ነበር፣ የብርሃን መንገድ አግኝቼ መንቀሳቀስ ጀምሬያለሁ። ዳር ላይ ሳታደርሰኝ ሄድክብኝ እያለ ነው። ይሄን መገንባቱ ነው ዋስትናችን የሚሆነው። ትልቁ ያገኘነው ሀብትም ይሄ ነው። የተገነቡት ተገንብተዋል፡፡ የሚገነቡትን እንገነባለን፡፡ የመሰረተ ልማት አውታሮችን እንቀጥልባቸዋለን፣ ወደ ኋላ የሚመለሱ አይደሉም፡፡ ግን ከእዚህም በላይ አማትረው የሚሄዱና ብዙ ራዕይን መሰረት ያደረጉ የሰነቅናቸው አመለካከቶች አሉ። መለስ ሁል ጊዜ እነዚህ አመለካከቶች፣እነዚህ የልማት፣ የዴሞክራሲ፣ የሰብአዊና የእኩልነት መብቶች በሕዝቡ አስተሳሰብ ውስጥ ከነገሱ ኢህአዴግ ቢኖርም ባይኖርም ችግር የለውም ይል ነበር፡፡ አሁን ሕዝቡ እነዚህን አስተሳሰቦች የእኔ ናቸው ብሎ አቅፎ ይዟቸዋል። ይህንን ነው መለስ ያነፀው፡፡ይሄም አይመክንም፡፡
ከትውልድ ወደ ትውልድ ይሸጋገራል። መለስ ሁል ጊዜ የእኛ ትግል የማራቶን እሩጫ አይደለም ይል ነበር። አንድ ሰው ብቻውን ሮጦ የሚጨርሰው የማራቶን ሩጫ አይደለም። የዱላ ቅብብሎሽ ነው፡፡ ትውልዶች የሚቀባበሉት ነው። አንድ ትውልድ አንድ ቦታ ላይ ያደርሳል። በአንድ ወቅት የተጀመረ የሕዝብ ትግል ስለማያቋርጥ ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተሸጋገረ ነው የሚሄደው፡፡ እንደ ዱላ ቅብብሎሽ ነው ይዘነው የምንጓዘው ይል ነበር።መለስ ይህን ዱላ ተቀባይ ወጣት ፈጥሯል። ሴቱን፣ ወንዱን፣ ወጣቱን፣ አዛውንቱን፣ሁሉንም በእዚህ አስተሳሰብ አንፀነዋልና ዋስትናችን ይሄ ነው። ይሄ ደግሞ የመለስ ራዕይ ነው።ይሄ የመለስ አስተዋጽኦ ነው።ተኪ የሌለው አስተዋፅኦ ነው።ውጤት ነው። ለዚህ ነው መለስ በስጋ ቢለየንም በስራውና በያዝነው አመለካከት ሁልጊዜም አብሮን ይኖራል፡፡ መጪው ትውልድም አብሮት ይኖራል የምንለው። ሕዝቡም ይህን ጥልቅ ግንዛቤ በሚገባ ተረድቶታል ብዬ አምናለሁ።
ዘመን፦ቀጣዩ የኢትዮጵያ አመራር፣ ሕዝቡም ኀዘኑን ረስቶ ጠንክሮ ወደ ሥራ በመግባቱ ረገድ ምንድን ነው የሚጠበቅበት፤ በተለይ አመራሩ?
አምባሳደር ስዩም፦ በታሪክ አንዳንዴ የሚወሳ ነገር አለ። አዲሲቷ የቻይና ሕዝባዊት ሪፐብሊክ በፈረንጆች አቆጣጠር በ1949 ዓ.ም ነው የተመሰረተችው። በቻይና አብዮት የሕዝብ ትግል ከሚታወቁት መሪዎች አንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ቹ ዬን ላ ናቸው። በ1976 ዓ.ም በፈረንጆች አቆጣጠር ነው ድንገት ያረፉት።በድንገተኛ አደጋ ነው የሞቱት። የእዚች አገር ታሪክ አሁን ያለውን የኢትዮጵያን ሁኔታ የሚያሳይ ነገር ነው ተፅፎ የምታገኘው። አሁን በሕይወት ያሉ ታሪኩን የሚያውቁት ሲናገሩ በወቅቱ አገሪቷን በሙሉ ሽባ ያደረገ ሁኔታ ተፈጥሮ ነበር ነው የሚሉት፤ በእርሳቸው ሞት። ከእርሳቸው ሞት በኋላ ሕዝቡ በጣም ደንግጧል። አሁን የምታየው የኢትዮጵያ አይነት ሕዝቡ መንገድ ወጥቶ በማልቀስና በማዘን ወደ ሥራ መንቀሳቀስ የተሳነው ጊዜ እንደነበረ ነው የሚነገረው፡፡ ከሐዘኑ ለማገገም የወራት ያህል ጊዜ ወስዶባቸዋል። በሐዘን ምክንያት ሁኔታው የጨለመበት ነበር። በኋላም የማኦ ዘይቱንግ ሞት ተከተለ፡፡ እና በወቅቱ በአገሪቱ ያልተረጋጋ ሁኔታ ነበር ተፈጥሮ የነበረው።እኛ ዛሬ ከእዚህ መማር አለብን እላለሁ። እያዘንን ወደ ሥራ መግባት ነው ያለብን። ሀዘናችንን በሥራ ነው መግለፅ ያለብን። እየሰራን ነው መለስን ህያው አድርገን እርሱነቱ እንዲቀጥል የምናደርገው። እያዘንን ወደ ሥራ በመግባት ሀዘናችንን በሥራ ነው መግለጽ የሚገባን፡፡በእዚህ አይነት ሁኔታ ነው መለስን ህያው የምናደርገው፡፡ እርሱ የፈጠረልንን ሥራ፣ እርሱ የሰጠንን ራዕይ ይዘን የእርሱ ፍላጎት የነበረውንና የእኛንም ጥቅም የምናረጋግጥበትን ይህን ራዕይ አጠናክረን መቀጠል አለብን። ኀዘናችን ከልባችን እስኪወጣ ድረስ ጊዜ ሊወስድብን ይችላል። ሀዘናችን ጥልቅ ነው፡፡ ግን ይህን ተሸክመን በሥራ ነው መግለፅ ያለብን፡፡ መለስን በሥራ ህያው እናድርገው የሚለው ነገር አሁን የወጣቱና የአዛውንቱ ቋንቋና አስተሳሰብ ሆኗል። ቀና ደፋ እያሉና አካፋና ዶማ ይዘው እየቆፈሩ ግድቡን እየገደቡ ነው ሐዘናቸውን እየገለፁ ያሉት፡፡ ሥራ አቁመን አይደለም ማዘን ያለብን፡፡የእኛ ትልቁ መልዕክት ይህን አገሪቱ የጀመረቻቸውን ጅምሮች በዚሁ አጠናክሮ መቀጠል ነው የሚያስፈልገው፡፡ እኛ የሞት ሞት የምንሞተው ሀዘናችን ከስራ ውጪ ካደረገን ነው። በቃ መለስ አልፏል።ሁልጊዜ እናከብረዋለን፣ እንወደዋለን፡፡ ግን የእኛ ክብርና ፍቅር የሚገለፀው በስራ መሆን አለበት የሚለውን በትክክል መረዳት ያስፈልጋል፡፡
ዘመን፦አመራሩ በቀጣይ የእርሳቸውን ፈለግ ተከትሎ እንዴት ነው በጥንካሬና በብስለት መጓዝ ያለበት?
አምባሳደር ሰዩም፦ እንግዲህ ከዚህ ውጪ ሌላ አማራጭ የለውም፡፡ ሌሎች አማራጮች፣ አማራጮች አይደሉም፡፡ ህዝቡን በበሳል መስመር መምራት የተቀመጠለት መስመር ነው፡፡ አዲስ መስመር ፍለጋ ላይ አይገባም፡፡ ይህን መስመር እንዴት ተግባራዊ ላድርግ ብሎና በቁርጠኝነት ለእዚህ የሚያበቃውን አደረጃጀት አጠናክሮ እንዲሁም የተፈጠረውን የህዝብ ማዕበል ይዞ መቀጠል አለበት። ህገ መንግስታችንን በመጠበቅ የድርጅቱን መመሪያዎችና ህጎች መሰረት ያደረጉ ተቋማትን ነው መገንባት ያለብን።መለስን አንድም ሰው ባይተካውም የመንግስትና የድርጅቱ አመራርና የህዝቡ እንቅስቃሴ እንዴት ተቀጣጥሎ ይሂድ የሚለውን ማየት አለበት፡፡
ከዚህ ውጪ ሌላ አማራጭ የለም፡፡ ወደ ኋላ፣ ወደ ግራ፣ ወደ ቀኝ የሚባልበት መንገድ የለም። የአገራችንና የህዝባችን መፃኢ እድል ብሩህ ነው። በጣም ብሩህ ነው።እንዲህ አይነት ለለውጥ፣ ለትራንስፎርሜሽን፣ ለስራ የተነሳሳ የህዝብ ማዕበል ከሁሉም የሚበልጥ ሀብትና ፀጋ ነው። በዴሞክራሲ፣ በልማት፣ በመልካም አስተዳደር ዙሪያ የህዝቡን ይሁንታ ያገኘ አገር በታሪክ አጋጣሚ ጥቂት ነው። ይህን እድል አግኝተናል።ሁሉንም ሀብትና ጥበብ የሚያስጨብጠንና የሚፈጥርልን ይሄው ነው፡፡ በዚህ ይሁንታ እንዴት አድርገን ነው ህዝቡም አመራሩም በጋራ ተሳስሮ የሚሄደው የሚለውን ያያል ብዬ አምናለሁ፡፡ ከዚህ ውጪ ሌላ አማራጭ የለውም።
ዘመን፦ በዚህ ሁኔታ በቀጣይ የአቶ መለስ ራዕይ ይሳካል፣ ኢትዮጵያም ታላቅ አገርና ህዝብ ትሆናለች ብለው ያምናሉ?
አምባሳደር ስዩም፦ አልጠራጠርም። ወደ ኋላ የምንመለስበት ምንም ምክንያት የለም። ሁሉም ዕድል አለን፡፡ እንኳን አሁን ይሔን የፈነጠቀውን ብርሀንና ውጤት እያየ ይቅርና ህዝቡ በተስፋ ድርጅቱንና አመራሩን አምኖ ሲንቀሳቀስ ቆይቷል።አሁን የራሱም አድርጎ ይዞታል፡፡ ወደኋላ የሚመለስበት ምክንያት የለም።
ዘመን፦ ይህን ያነሳሁብዎት አንዳንድ ወገኖች ከአቶ መለስ ህልፈት በኋላ የፖሊሲ ለውጥ ሊመጣ ይችላል፤ለውጦች ሊኖሩ ይችላሉ የሚሉ ሃሳቦችን እያነሱ ስለሚገኙ ነው፤
አምባሳደር ስዩም፦ የጥፋት መንገድ ዕድል የለውም። ህዝባችን ተገቢ ጥርጣሬዎች ሊኖሩት ይችላሉ። መነሳት ያለባቸውን ጥያቄዎች ቢያነሳ ተገቢ ነው። መለስን የሚተካ ሰው ይገኛል? አይገኝም። የዘመናችን ትውልድ የሚያፈራቸው በጣም ጥቂት በጣት የሚቆጠሩ በዓለም ነበሩ የሚባሉ ካሉ አንዱ መለስ ነው። እንደዚህ ያሉ ሰዎች ደግሞ በታሪክ አጋጣሚ ጥቂቶች ናቸው፤ ባለንበት ዘመን፡፡ እነዚህ ሁሉም መሬት ላይ ያሉ ትውልዶች ያፈሩት የዘመናችን ብልህና አዋቂ፣ ለህዝብ አመራር የሰጠ ታላቅ መሪ ነው መለስ። እርሱ የአፍሪካም መሪ ነው፡፡ በዓለም አመራር ሲሰጡ ከነበሩት ጥቂት ከሚከበሩና አንቱ ከሚባሉ መሪዎች መካከል አንዱ ነው፡፡
ኢትዮጵያ የዚህ ባለቤት በመሆኗ ትኮራበታለች፤ ከህይወት ህልፈቱም በኋላ። እንደነዚህ አይነት ሰዎች በፈለግህበት ደረጃ የሚገኙ አይደሉም። አቶ መለስ ግን እንዲህ አይነት ሰው ቢሆንም ከድርጅቱ ውጪ ማናቸውንም ሚና መጫወት የቻለበት ሁኔታ የለም፡፡ በእርግጥ እርሱ ድርጅቱን፣ መንግስትንና ህዝቡን አንጿል። ህዝቡ፣ መንግስትና ድርጅቱም አቶ መለስን አንፀዋል። ይሔ ተሳስሮ ነው የሚሄደው።እና አመራሩና ህዝቡ አንድ ላይ በዚህ በተፈጠረው ሁኔታ አብሮ በሚሄድበት ጊዜ የሚጎድለውን እየተካ መጓዝ አለበት።ብዙ መለሶች ወደ ፊት ይወጣሉ ብለን በዚህ አስተሳሰብ ነው መሄድ ያለብን ብዬ አምናለሁ።
ዘመን፦ እንዳው በእርሶዎ ዕይታ አቶ መለስን ለየት የሚያደርጋቸው ነገር ይኖራል?
አምባሳደር ስዩም፦ እኔ ይሄንን በአንድ ቋንቋ ብገልፀው ይሻላል። አቶ መለስን መለስ ያደረገው ባለራዕይና ራዕዩን ተግባራዊ ለማድረግ በቁርጠኝነት የሚንቀሳቀስ መሆኑ ነው።ይህን ራዕይ ደግሞ ራዕይ ብሎ የሚያየው ህዝቡን እስከጠቀመና የህዝብ ነው ብሎ እስካመነ ድረስ ብቻ ነው። አንዳንድ ጊዜ ጥልቅ የሆነ ህዝባዊ ፍቅር ይዞ ራዕዩን በፈለገው መንገድ ለመተግበር የሚያቅተው ሰው አለ። አቶ መለስ ብቻ ነው ጥልቅ የህዝብ ፍቅር ያለው ማለትም አይደለም፡፡ ግን ጥልቅ የህዝብ ፍቅር ኖሮት፣ የአመራር ብቃትንና የህዝብን ፍቅር መሰረት አድርጎ ህዝቡን በልማት፣ በዴሞክራሲ፣ በፍትህና በመልካም አስተዳደር መርቶ መሄድ ላይ አቅሙ የማይኖረው ብዙ ሰው ነው ያለው፡፡ ጥልቅ የህዝብ ፍቅርን መነሻ በማድረግ ግን መለስ ባለ ራዕይ ነው፡፡ ራዕዩንም ወደ ተግባር የማሸጋገርና ሌሎችንም አደራጅቶ የመምራት ብቃት ነበረው፡፡ ይሔ የመለስ ባህሪ ነው፡፡
ዘመን፦ በህይወት ዘመናቸው ይመኙትና ይፈልጉት የነበረው ምን ነበር?
አምባሳደር ስዩም፦ አስታውሳለሁ በመጀመሪያ ጊዜ የሽግግር መንግሥት ፕሬዝደንት በነበረበት ወቅት አብረን ዋሽንግተንን ጐብኝተን ነበር። በዚያን ወቅት አንዲት ኢትዮጵያዊት በሚቀጥለው አስር አመት ለኢትዮጵያ ያልዎት ራዕይ ምንድን ነው? ብላ ጠየቀችው፡፡ የምመኘው በሚቀጥሉት አስር አመታት ውስጥ የኢትዮጵያ ህዝብ በቀን ሦስት ጊዜ እንዲበላ ነው ብሏል፡፡ የመለስ ራዕይ ድህነትን ማሸነፍ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከገባበት ውርደትና አንገቱን ካሰበረው ችግር እንዲላቀቅ ማድረግ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝቦች፣ ብሔሮችና ብሔረሰቦች እፁብ ድንቅ የሚባል ባህልና ስልጣኔ ባለቤቶች ናቸው፡፡ በሃይማኖትም ተባብሮና ተቻችሎ፣ አገር ገንብቶ የኖረ ሕዝብ ነው፤ ለብዙ ትውልዶችና ዘመናት፡፡ ነገር ግን የእነዚህ እሴት ባለቤት ሆኖም ግን አንገቱን ሰብሮና ሀፍረት ተከናንቦ የድህነት፣ የጦርነት፣ የልመናና የረሀብ ተምሳሌት ሆኖ ነው የኖረው፡፡ አገር ለቆ ወይንም ለቃ ስደት ሄዶ ወይንም ሄዳ አሜሪካ የገባ ልጅ ወይንም የገባች ልጅ ያለው ቤተሰብ እንደ ትልቅ ፀጋ የሚያይበት፡፡ልጄ ተለየኝ ወይንም ተለየችኝ ብሎ ሳይሆን ልጄ አሜሪካ ገባ ወይንም ገባች የሚል፡፡የክረምት ጐርፍና ወንዝ ሞልቶ ለያይቶት ሲከርም መቼ ነው የሚያባራልኝ ብሎ ናፍቆቱን መወጣት አቅቶት የሚጨነቅ ሕዝብ፡፡ ባህር ማዶ ተለይተውት የሄዱ ልጆቹን የሀብትና የኑሮ ምንጭ አድርጎ የሚያይበት ሁኔታ ነበር የተፈጠረው። ህፃናት ተወልደው ምን ትፈልጋለህ ? ሲባሉ አሜሪካ መሔድ እፈልጋለሁ ነው የሚሉት፡፡ አገሬን አስከብሬ እኖራለሁ አይደለም መልሳቸው። ከእዚህ የባሰ ውርደት የለም፡፡ ስደትን እንደክብር የሚያይ ሕዝብ ነበር፡፡ መለስ ታዲያ ለዚህ ውርደት የዳረገን ድህነት ነው። የሰላም፣ የመልካም አስተዳደር፣ የዲሞክራሲ እጦት ነው። ድህነትን አሸንፈን ልማትን እውን ካደረግን የመልካም አስተዳደሩንም ሥራ ከአጠናከርንና የሕዝቡን መብት ካረጋገጥን ሕዝባችን ብድግ ይላል፡፡ ለዚህ ማብቃት አለብን ይል ነበር፡፡ የመለስ የመጀመሪያውም የመጨረሻውም ራዕይ ይሔ ነው።
ዘመን፦ እርስዎ ከትግሉ መስራቾች አንዱ እንደነበሩ ይታወቃል፡፡ ያኔ ለዚህ ለአሁኑ ጊዜ እንበቃለን ብላችሁ ታስቡ ነበር?
አምባሳደር ስዩም፦ መለስ ያለው ነው፡፡ የቅብብሎሹ ታሪክ ነው።ሰው መቼ እንደሚሞት አይታወቅም፡፡ እንኳን ለዚህ እድል ልንበቃ ቀርቶ ነገን እንውላለን፣ አንውልም ማንም የሚያውቅ የለም፡፡ እንጀምረውና ወጣቱ ትውልድ ይቀጥልበታል። ሕዝቡ ትግሉን የእኔ ነው ብሎ ይሂድበት፡፡ ሕዝቡን ባለቤት እናድርገው ነው ምኞታችን። ህወሀትም ኢህአዴግም ልዩ የሚያደርጋቸውና የትግል ሂደታቸውም ሆነ ራዕያቸው የነበረው የዚህ ትግል ባለቤት ህዝቡ ነው የሚለው ነው፡፡ የኢህአዴግና የደርግ ወታደር ተብሎ በሁለት ወታደሮች መካከል የሚካሄድ ጦርነት የህዝብ ጦርነት ነው፡፡ ጦርነቱ የሕዝቡን መብትና ክብር የአገሪቱንም ህዳሴ እውን ለማድረግ የተካሄደ ነው እና ትግሉ የህዝቡ የራሱ ስለሆነ ህዝቡ ባለቤት ሆኖ ይህን ትግል መምራት አለበት። የሚፈለገውን መስዋዕትነትም በሁሉም መስክ መክፈል አለበት። እኛ ይህችን ለማስጨበጥ እድል ካገኘን ከዛ በኋላ ሚናችንን ተወጥተናል የሚል ነበር፡፡ እና ለዚህም ነው እነመለስ ለእኔ ፣ ለራሴ ክብር ሳይሆን ዛሬ ይህቺን ሰርቼና መስዋዕትነት ከፍዬ ልለፍ ይሉ የነበረው፡፡ የእዚህ ትግል ታሪክ ብዙ ነው፡፡ ተነግሮለት የሚያልቅ አይደለም፡፡ ገና አልተፃፈም። ጀግኖች ጠላት ምሽግ ገብተው ያፈራረሱበትና እንደ ቢራቢሮ የእሳት እራት የሆኑበት፡፡ ፈንጂውን በህይወት እየጠረጉና እየረገፉ የሕዝቡን ትግል ለድል ያበቁበት፡፡መስዕዋትነት ለመክፈል ዝግጁ የሆነ ፍጡር የታየበት ትግል ነበር፡፡ ይህን ደግሞ የኢትዮጵያ ሕዝብ ይኮራበታል።
ዘመን፦ አምባሳደር ዛሬ ላይ ሆነው የእርስዎ፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩና የመሰል ጓዶቻችሁ የትግልና የመከራ ጊዜ አልፎ ሲያዩት ምን ይሰማዎታል?
አምባሳደር ስዩም፦ እኛና መለስ ያየነውን፣ መለስ የፈጠረውን ሳያዩ ያለፉት የትግል ጓዶች ይታዩኛል። እኛ በጣም እድለኞች ነን እንላለን፡፡ ይህን አይተናል፡፡ መለስ ሁልጊዜ የሰጣችሁኝን አደራ ዳር ሳላደርስ አልቆምም ይል ነበር። ህይወቴ ከመሬት በላይ እስካለች ድረስ ከዚህ ድርጅት አልለይም፤ የሰጣችሁኝን አደራ ተግባራዊ አደርጋለሁ ሲል ነበር።የእርሱን ቃል፣ ራዕይና አመራር እውን ለማድረግ ሲታገሉ አልፈው ለቀበራቸውና መስዕዋትነት ለከፈሉ ብዙ ሺዎች ሲገባላቸው የነበረውን ቃል አክብሮና ፍላጐቱን አድርሶ ሔዷል። የቀረነው እንግዲህ መለስ ያላየው እኛ ያየነው አለ። የመለስና የኢህአዴግን መስመር፣ የሕዝቡንም ፍላጐትና ራዕይ አይተናል፡፡
እኔ በጣም እድለኛ ነኝ፡፡ ከታደሉት ውስጥ ነኝ፡፡ እንኳን አርባ አመት በዚህ ሁኔታ እቆያለሁ ቀርቶ በትግሉ ወቅት አርባ ቀንም እንኳ እኖራለሁ የሚለውን ሀሳብ አልሜውም አላውቅም፡፡ ለማንኛውም ከዚህ ሕዝብ አብራክ መውጣት ሁል ጊዜ እየኮራህበት የምትሔደው ጉዳይ ነው፡፡ የሚያስተምርህና የምትኮራበት ሕዝብ ነው፡፡ለእዚህ ሕዝብ ደግሞ ብትወድቅ የክብር ክብር ነው፡፡
ዘመን፦ እግዚአብሔር ይስጥልኝ አምባሳደር በዘመን መጽሔታችን ስም እግዚአብሔር ያፅናዎት እላለሁ፣ ሁላችንንም እግዚአብሔር ያፅናን፡፡
አምባሳደር ስዩም፦ አሜን ሁላችንንም ያፅናን፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ቶሎ ከዚህ ሐዘን ወጥቶና ፀንቶ የያዘውን የልማትና የመልካም አስተዳደር ትግል አጠናክሮ እንዲቀጥልበት አደራ እላለሁ። እየሰጠን ያለውን ኃላፊነትና አደራም እንሸከማለን ብዬ ላረጋግጥለት እፈልጋለሁ። አመሰግናለሁ።

ሰበር ዜና፡ አቡነ ሳሙኤል የአቡነ ማቲያስን ለፓትርያርክ እጩነት መቅረብ ተቃወሙ


የሁለቱን ሲኖዶሶች እርቀሰላም እንደፈረሰ አድርገው እንዲያነቡ የወያኔ መንግስት የተጠቀመባቸው አቡነ አብርሃም ዛሬ ያሰቡት ሳይሳካ የተለየ አቋም ይዘዋል
(ዘ-ሐበሻ) ታማኞቹ የዘ-ሐበሻ የቤተክህነት ምንጮች “መንግስት ተጠቅሞብኝ ጣለኝ” እያሉ በመናገር ላይ ያሉት አቡነ ሳሙኤልና ስደተኛውን ሲኖዶስና የተጀመረውን እርቀሰላም ባልተፈረመ ፊርማና ማህተብ የሚያወግዝ መግለጫ ከጥቂት ሳምንታት በፊት በኢትዮጵያ ቴሌቭዝን ያነበበቡት አቡነ አብርሃም የአቡነ ማቲያስን ለፓትርያርክነት ለእጩነት መቅረብ መቃወማቸውን አጋለጡ። እጩ ፓትርያርክ መሆን አለባቸው በሚል አስመራጭ ኪሚቴው በመጨረሻም፦
1ኛው ብፁዕ አቡነ ማትያስ፣
2ኛው ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ፣
3ኛው. ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ፣
4ኛው ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል
5ኛው. ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ ናቸው የሚለውን ውሳኔ አስመራጭ ኮሚቴው ካሰማ በኋላ አቡነ ማቴዎስ “በቀደመው የአበው ገዳማዊ ሥርዓት መሠረት በዕጩነት መግባት አይገባኝም። አባቶቼ ስለ እግዚአብሔር ብላችሁ እኔን ተዉኝ” በማለት እጩ ሆነው መቅረባቸውን ቢቃወሙም በሲኖዶሱ አባላት ማግባባት አቡነ ማቴዎስ በመጨረሻም እጩነቱን ተቀበለው የፓትርያርክ አሯሯጭ ለመሆን ወደ ውድድሩ ገብተዋል ያሉት የዘ-ሐበሻ ምንጮች ሌሎቹም ጳጳሳት እንዲህ ያለ አቋም በማሳየት “የሚመረጠውን ጳጳስ እያወቅን አሯሯጭ አንሆንም” ቢሉም በማግባባት ውሳኔውን ተቀብለዋል ብለዋል።
ይህን ተከትሎ በመንግስት 6ኛው ፓርትያርክ ይሆናሉ ተብለው ቃል የተገባላቸው አቡነ ሳሙኤል በመጨረሻም በመከዳታቸው እጅጉን በመሳጨት “መንግስት ተጠቅሞብኝ ጣለኝ” በማለት በመቆጨት ላይ እንዳሉ ያወሱት የዘ-ሐበሻ የቤተክህነት ምንጮች የአስመራጭ ኮሚቴው አሠራር፣ ጥቆማና ውሳኔ ትክክል አይደለም በሚል ከረር ያለ ሐሳብ ያሰሙት አቡነ ሳሙኤል እና እርቀ ሰላሙ መፍረሱን እና ዳቦ መቆረሱን በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን በማብሰር ለወያኔ ተባባሪ የሆኑት አቡነ አብርሃም ባሰሙት ንግግር በተለይ በአቡነ ማትያስ ለዕጩነት መቅረብ ላይ ያላቸውን ተቃውሞ መረር ብለው መናገራቸውን ምንጮቻችን ነግረውናል። በመንግስት መጠቀሚያ ሆነው እንደ “ማስቲካ” ተጥለዋል የተባሉት አቡነ ሳሙኤልና አቡነ ማቲያስ የአቡነ ማትያስ ዜግነት ጉዳይ ዕልባት ሳያገኝና ነገሩም በሥርዓቱ ሳይጣራ ከዝርዝሩ ውስጥ መግባታቸውን አምርረው ቢቃወሙም አጠቃላይ የምርጫው ሒደት ትክክል አለመሆኑንም ለማስረዳት ቢሞክሩም አባይ ጸሐዬ ከጀርባው ሆኖ የሚሰማው ሃይል ምንም ሊያደምጣቸው እንዳልቻለና በወያኔ የተተፉትን አባቶች እንደውም ምልዓተ ጉባዔው ይህን ጥያቄ በዚህ ሰዓት ማንሳታቸው ተገቢ አለመሆኑን፣ “ትናንት ምርጫው እንዲካሔድ ስታቻኩሉ የነበራችሁ እናንተ ናችሁ፡፡ ይዋልና ይደር፣ ጉዳዩን በጥሞና እንመልከተው ስንላችሁ አይሆንም ብላችሁ አጣደፋችሁት፡፡ አሁን ስምንት መቶ መራጭ መንገድ ከጀመረ በኋላ፣ የውጭ እንግዶች እየተጠባበቅን ባለንበት ሁኔታ እንዲህ ያለ ግርግር ማንሳት ቤተ ክርስቲያኒቱን ማዋረድ ነው” የሚል ምላሽ እንደተሰጣቸው ምንጮቻችን ነግረውናል። ይህም የሚያሳየው ሁለቱ አባቶችን ወያኔ እርቀሰላሙን እንዲያሰናክሉ ያዘጋጃቸውን እነዚህን አባቶች አንቅሮ መትፋቱን ያሳያል ሲሉ አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ።

ዘ-ሐበሻ አሁንም ይህን ጉዳይ እየተከታተለች፤ የደረሰበትን ጉዳይ ታሳውቃለች።
እውነት ያሸንፋል!!
Ze-Habesha Website is not responsible for accuracy of information or endorses the contents provided by external sources. All blog posts and comments are the opinion of the authors.

ESAT Weekly News Feb 24 2013


ESAT Ye Ehud Weg 24 February 2013 Ethiopia

Saturday, February 23, 2013

የስድሰተኛው ፓትርያርክ ምርጫ እጩዎች ይፋ ሆኑ

(Feb 23, 2013, አዲስ አበባ)--ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የካቲት 16/2005 ባካሄደው ስብሰባው ለስድስተኛው ፓትርያርክ የሚወዳደሩ ዕጩዎችን ተቀብሎ አጸደቀ። ሲኖዶሱ አስመራጭ ኮሚቴው ባቀረባቸው እጩዎች ላይ ከተወያየ በኋላ ነው ያጸደቀው።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ፓትሪያርክ(ኢሬቴድ)
በዚህ መሰረት፦
ብጹእ አቡነ ማትያስ በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳማት ሊቀ ጳጳስ፤ብጹእ አቡነ ህዝቅኤል የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሃፊና የከፋ ሸካ ቤንች ማጅ ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤ ብጹእ አቡነ ዮሴፍ የባሌ ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤ ብጹእ አቡነ ኤልሳእ የሰሜን ጎንደር ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፤ ብጹእ አቡነ ማቴዎስ የወላይታ ዳውሮ ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በእጩነት ቀርበዋል ብለዋል የአስመራጭ ኮሚቴው የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ባያብል ሙላቴ ።
 

የፊታችን ሐሙስ የካቲት 21 አዲስ አበባና ድሬደዋን ጨምሮ ከሁሉም አህጉረ ስብከት የተወከሉ ሊቃነ ጳጳሳት ፤ የአህጉረ ስብከት ስራ አስኪያጆች ፣ ካህናት ፣ ምዕመናንና የሰንበት ትምህርት ቤት ተወካዮች በእጩዎቹ ላይ ድምጻቸውን ይሰጣሉ። ድምጽ ሰጪዎቹ ቁጥር ስምንት መቶ እንደሆነ ነው አቶ ባያብል የተናገሩት ።
 

በዚሁ ዕለት ምሽት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ስድስተኛው ፓትርያርክ ማን ይሆናል የሚለው ምላሽ እንደሚያገኝ ፋና ዘግቧል ። የሚመረጡት ፓትርያርክ እሁድ የካቲት 24/2005 በቅድስት ስላሴ ካቴድራል በሚደረግ ስነ ስርዓት በዓለ ሹመታቸው ይፈጸማል 

ከኢሬቴድ
http://ethionetblog.blogspot.no/2013/02/blog-post_5738.html?spref=fb

ወጣቷን ማን ገደላት?

መስከረም 2 ቀን 2000ዓ.ም ነው፤ በድንገት መተንፈስ አቅቶኝ በጣም ታመምኩ፤ ፈረንሳይ አካባቢ በሚገኘው < ቅድስተ ማሪያም ከፍተኛ ክሊኒክ> ተወሰድኩ፤ በአስቸኳይ መተኛትና ኦክሲጅን ከስታብላይዘር ጋር መውሰድ እንዳለብኝ..ዶ/ር ገለፀ። የመኝታ አንድ ሺህ ብር ተያዘ።..አልጋ ይዤ አንድ ሰዓት እንኳ ሳይሞላኝ …የክሊኒኩ ነርስ መጥታ « ይቀርታ ኦክሲጅን የለንም..ስለዚህ ወደ ጳውሎስ ሆ/ል ሪፈር ተብለሃል» ብላ ወረቀት ሰጠችኝ። ምንም ህክምና ሳላገኝ 500 ብር ቆርጠው ግማሹን ሰጡኝ። ወደ ጳውሎስ ተወስጄ በድንገተኛ ክፍል ያለአንዳች ህክምና እርዳታ ለ10 ሰዓታት ቆየሁ፤ ስቃዬ ጨምሮዋል፤ ከምሽቱ 4ሰዓት ሲሆን በጣም ስለደከምኩ ኦክሲጅን ተሰጠኝ፤…ከአጠገቤ 3 ሰዎች ተኝተዋል፤ አንዷ ወጣት አስቸኳይ ደም ያስፈልጋት ነበር፤ ቤተሰቦቿ የታዘዘውን አደረጉ፤….ከሌሊቱ 9፡00 ሰዓት ድረስ ደም ስላልተሰጣት በጣም ደከመች፤ ቤተሰቧ ተረብሸው ተረኛው ነርስ የተኛበት ክፍል ሄደው ለረጅም ሰዓት ተማፀኑት፤ እየተጨናበሰ « ምን ከእንቅልፌ ትበጠብጡኛላችሁ..» እያለ መጣ፤ ከዛ ለተዳከመችው ወጣት ደም ቀጠለላት፤ ወዲያው ነርሱ ሲደናገጥ አየሁት….የወጣቷን አስታማሚዎች ጨምሮ..የኔን እንዲሁም የሌላውን ከክፍሉ እንዲወጡ አደረገ፤…በደረብኩ ጋቢ አሸንቁሬ ሂደቱን እከታተላለሁ፤…ወዲያው,….ወዲያው.. የወጣቷን የደም ግፊት ይለካል። አንዲት መለከ መልካም ዶ/ር መጣች፤ ሃዘን በተቀላቀለበት የለሆሳስ ድምፅ « እንዴት?…እንዴት እንዲህ አይነት ስሀተት?…» አለችው ለነርሱ ..እንባዋን እያፈሰሰች፤ ወጣቷ ላትመለስ በሞት አንቀላፍታለች፤ የታዘዘው ደምና የተሰጣት ልዩነት ስለነበረው ለሞት ዳረጋት፤ ሴቷ ዶ/ር ያለችውም ይህንኑ ነው « ከመስጠትህ በፊት ለምን ቼክ አላደረክም?» የሚል፤…ያቺ ወጣት በዛ አይነት ስህተት መሞትዋን ቤተሰቧ አያውቅም። ያው « እ/ር ፈጠራት..እራሱ ወሰዳት » እንደሚሉ አያጠራጥርም። ግን ወጣቷን የገደላት ነርሱ ነው፤ ቀይ መስቀል ነው!!.. ያን ከወንጀል ያልተናነሰ ድርጊት የምናውቅና ያየን ደግሞ ፥ ዶ/ሯ፣ነርሱ እንዲሁም እኔ ነን። የዚህን አገር ህክምና አሰጣጥ ስመለከት…ከሕሊናዬ የምትጠፋው ይህቺ ሟች ወጣት ድቅን አለችብኝ። ..አወይ አገሬ፥ ዳቦ፣ የፍትህ እጦት፣ የህክምና ችግር….መከራ በመከራ የተደራረበባት….መቼ ይሆን ወገኔ ከዚህ ሁሉ የሚላቀቀው?…እንባዬን ጨምቄ የማነሳው የዘወትር ጥያቄ ነው!!