Friday, October 24, 2014

ፓትርያርኩ: የቤተ ክርስቲያን ራስ ቅዱስ ሲኖዶስ ባልመከረበትና ‹‹ለቤተ ክርስቲያን የማይመጥን ነው›› በተባለው የመክፈቻ ንግግራቸው ተገሠጹ፤ ውሳኔም ተላለፈባቸው!

  • ቅ/ሲኖዶሱኻያ ኹለት የስብሰባ አጀንዳዎችን በማጽደቅ መወያየት ጀምሯል
  • በሕገ ቤተ ክርስቲያን ማሻሻያው ሥልጣናቸውን የማጠናከር ውጥን አላቸው
  • የማኅበረ ቅዱሳን ደንብ አጀንዳ እንዳይኾን መቃወማቸው ውድቅ ተደርጓል
  • ሊቃነ ጳጳሳቱን ባዘለፉባቸው ሕገ ወጥ ስብሰባዎች ይቅርታ ጠይቀዋል
  • የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትን በራሱ የሚመራው ሊቀ ጳጳስ ይመደብለታል
  • በደቡብና ምዕራብ ኢትዮጵያ የቤተ ክርስቲያን ጸጥታ ጉዳይና የተሐድሶ መናፍቃን የሚፈጥሯቸው ችግሮች በአጀንዳነት ተይዘዋል
  • በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የመጨረሻው ከፍተኛ ሥልጣን ባለቤትና ከማንኛውም መዋቅር ኹሉ የበላይ አካል የኾነው ቅዱስ ሲኖዶስ፣ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ለምልአተ ጉባኤው መደበኛ ስብሰባ ያሰሙትን የመክፈቻ ንግግር ‹‹ለቤተ ክርስቲያን የማይመጥን ነው›› በሚል በጥብቅ ተቃወመው፡፡ ተቃውሞው የተገለጸው፣ ምልአተ ጉባኤው የስብሰባው ቁጥር አንድ አጀንዳ ባደረገውየፓትርያርኩ የመክፈቻ ንግግር ላይ በተወያየበት ወቅት ነው፡፡
  • aba-mathias
  • በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ ፭ ቁጥር ፻፷፬ ድንጋጌ መሠረት ከጥቅምት ፲፪ ቀን ጀምሮ የሚካሔደው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የመጀመሪያ ዓመታዊ መደበኛ ስብሰባ ሲከፈት፣ ፓትርያርኩ በብዙኃን መገናኛ ፊት በንባብ ያሰሙት ንግግር፣ ከወቅታዊነቱና አግባብነቱ አኳያ ቅዱስ ሲኖዶሱ አስቀድሞ ሊመክርበት ይገባ ነበር በሚል የምልአተ ጉባኤው ተሳታፊዎች በአንድ ድምፅ አቋም እንደያዙበት ተመልክቷል፡፡
  • የምልአተ ጉባኤውን ስብሰባ በርእሰ መንበርነት የሚመሩት ፓትርያርኩ 
  • በመክፈቻ ንግግራቸው÷ በምእመናን ፍልሰት፤ በቤተ ክርስቲያን ስም ሀብትና ንብረት ይሰበስባሉ ባሏቸው ማኅበራት፤ ግልጽነትንና ተጠያቂነትን በማያሰፍን እንዲኹም በቴክኖሎጂ ባልተቃኘ የሰው ኃይል፣ የገንዘብና የንብረት አስተዳደር ችግር ምክንያት ቤተ ክርስቲያን ግልጽና አደገኛ ፈተናዎች እንደተጋረጡባት ገልጸዋል፡፡ፓትርያርኩ ከጠቀሷቸው ዐበይት ችግሮች መካከል ለማኅበራት ጉዳይ የተለየ ትኩረት የሰጠ በሚመስል ንግግራቸው÷ ማኅበራቱ፣ የሚሰጣቸውን መመሪያ ለመቀበል ፈቃደኝነቱና ቅንነቱ የሌላቸው ኾነው እንደተገኙና በአስተዳደር ሥራ በቀጥታ ጣልቃ እንደሚገቡ በመጥቀስ ‹‹የሰላም ጠንቆች›› ብለዋቸዋል፤ ቤተ ክርስቲያን በአክራሪነት የምትፈረጀው ማኅበራቱ በመንግሥትና በቤተ ክርስቲያን የማይታወቅ ሀብት ስለሚሰበስቡ እንደኾነም አመልክተዋል፡፡በክርስትናችን ትውፊት የማኅበራት ሚና ‹‹ስመ እግዚአብሔርን ጠርቶ ጸበል እየቀመሱ መኖር›› ብቻ እንደኾነ የተናገሩት አባ ማትያስ፣ በሕገ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ማኅበራትንና የምእመናን ፍልሰትን የተመለከተ ሕጋዊና ዘላቂ መፍትሔ ማስቀመጥ ‹‹ቤተ ክርስቲያንን የመታደግ ጉዳይ ነው፤›› ብለዋል፡፡የምእመናን ፍልሰትን ይኹን የሀብትና ንብረት አስተዳደርን የንግግራቸው ማጀቢያ ያደረጉት ያኽል እንደ ማኅበራቱ ጉዳይ ብዙም ያላተቱት ፓትርያርኩ፣ በነጠላ ቁጥር ወደሚጠቅሱትና ስሙን በግልጽ ወዳልጠሩት ‹አንድ ማኅበር› በመሸጋገር፣ ‹‹በሕግ ማስተካከል አለብን›› ለሚለው አቋማቸው አጽንዖት ለማስገኘት ሲጥሩ ተስተውለዋል፤ ሕዝበ ክርስቲያኑም ‹‹ማኅበሩ በቤተ ክርስቲያን ሕግ እንዲመራና በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ኾኖ እንዲያገልግልእ የተደረገ ነው፤›› ያሉትን ጥረታቸውን እንዲያግዛቸው ጥሪአቸውን አስተላልፈዋል፡፡የምእመናን ፍልሰት፣ የሰው ኃይልና የንብረት አስተዳደር ይኹን የብዙኃን መንፈሳውያን ማኅበራት ጉዳይ አሳሳቢነቱ የቱንም ያኽል ቢኾን፣ በፓትርያርኩ ንግግር ውስጥ የተጠቀሱበት መንገድ በቅዱስ ሲኖዶሱ የተመከረበትና የምልአተ ጉባኤው አቋም ያረፈበት ሊኾን እንደሚገባው የገለጹ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ ‹‹ቋንቋው የቤተ ክርስቲያን አይደለም፤ አይመጥናትምም›› በሚል በጽኑ እንደተቹት ተሰምቷል፡፡የአባ ማትያስ የመክፈቻ ንግግር ከይዘቱም አኳያ ሲፈተሽ፣ ‹‹ግልጽና አደገኛ ፈተናዎች›› በተባሉት ችግሮች ላይ ቤተ ክርስቲያን የያዘችውን አቋምና የወሰደችውን ርምጃ የማያመላክትና ወቅታዊነት የጎደለው ነው በሚል ተነቅፏል፡፡ ይኸውም በንግግራቸው ለተጠቀሱት ችግሮች መፈታት ምልአተ ጉባኤው ቀደም ሲል ጥናታዊ ውሳኔ ያሳለፈባቸው፣ የይኹንታ አቅጣጫና መመሪያ የሰጠባቸው በመኾኑና መፍትሔውም እነርሱኑ መዋቅሩን ጠብቆ ለማስፈጸም ተገቢውን ክትትልና ድጋፍ የማድረግ ጉዳይ ተደርጎ በመወሰዱ ነው ተብሏል፡፡ለብዙኃን መገናኛ መገለጽ ያለባቸው የፓትርያርኩ ንግግሮች፣ በመንፈስ ቅዱስ የሚመራውና የመንበረ ሐዋርያት ወራሽ የኾነው ቅዱስ ሲኖዶስ በበቂ ከመከረ በኋላ በመጨረሻ በሚደርስባቸው ስምምነቶች ላይ ተመሥርቶ የሚያወጣቸው መግለጫዎች ብቻ እንዲኾኑም በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ ሙሉ የጋራ አቋም እንደተያዘበት ታውቋል፡፡ በመኾኑም ከአኹኑ የቅ/ሲኖዶስ የመጀመሪያ ዓመታዊ መደበኛ ስብሰባ በኋላ ርእሰ መንበሩ ፓትርያርክ አባ ማትያስ የሚያደርጉት የመክፈቻ ንግግር፣ በቅ/ሲኖዶስ ጽ/ቤት አስቀድሞ የተመከረበትና በምልአተ ጉባኤው አባላት የ‹‹እንኳን ደኅና መጣችኁ›› አቀባበል ላይ ብቻ ያተኮረ እንዲኾን መወሰኑን የስብሰባው ምንጮች ገልጸዋል፡፡በፓትርያርኩና በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ መካከል ጠንካራ የቃላት ልውውጥ እንደነበረና ፓትርያርኩ ‹‹ወትሮም ጠላቴ›› በሚል ሊያሸማቅቋቸው የሞከሩ ብፁዓን አባቶች እንዳሉም ተሰምቷል፡፡ ይኹንና የሢመት ቅድምና ያላቸው ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትን ጨምሮ ኹሉም የምልአተ ጉባኤው አባላት ፓትርያርኩ በአመራራቸው፣ሕገ ቤተ ክርስቲያንንና የቅዱስ ሲኖዱሱን ውሳኔ በመፃረር የቤተ ክርስቲያንን ክብር እያስደፈሩና ልዕልናዋን እያዋረዱ እንዳለ በመጥቀስ በተባበረ ድምፅ በመገሠጻቸው ይቅርታ ለመጠየቅ እንደተገደዱ ተዘግቧል፡፡ፓትርያርኩ ተግሣጹን ተቀብለው ምልአተ ጉባኤውን ይቅርታ ከጠየቁባቸው መተላለፎቻቸው ውስጥ፣ በመስከረም ወር መጨረሻ ከመዋቅር ውጭ በልዩ ጽ/ቤታቸው በኩል በጠሯቸውና ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ ከማኅበረ ቅዱሳን ጋራ ተደምረው በአማሳኞች የተዘለፉባቸው ስብሰባዎችና ቅዱስ ሲኖዶሱ ያልመከረበት የመክፈቻ ንግግራቸው እንደሚገኝበት ተጠቅሷል፡፡ ፓትርያርኩ ያሻቸውን እየፈጸሙ ይቅርታ መጠየቅን እንደ ስልት መያዛቸውን የሚጠቅሱ ወገኖች በበኩላቸው፣ ከይቅርታው ጋራ የፓትርያርኩ አመራርና አካሔድ ለአማሳኞች የጥፋት ምክርና ለውጭ ተጽዕኖ ከተጋለጠበት ኹኔታ ተጠብቆ የቅዱስ ሲኖዶሱን ልዕልናና ሕገ ቤተ ክርስቲያንን ለማስከበር የሚያስችል የማስተካከያ ርምጃ እንዲወሰድበትና ቋሚ አሠራር (የጠንካራ እንደራሴ ጉዳይ እንደ አብነት ተጠቅሷል) እንዲበጅለትይጠይቃሉ፡፡የቤተ ክርስቲያን ‹‹ግልጽና አደገኛ ፈተናዎች›› በሚል በፓትርያርኩ የመክፈቻ ንግግር ለተጠቀሱት የምእመናን ፍልሰትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች መፍትሔው÷ ለመዋቅር፣ አደረጃጀትና አሠራር ለውጥ የቀረቡትንና የብዙኃኑን ካህናትና ምእመናን ተቀባይነት ያረጋገጡ ጥናቶች በትግበራ ስልት ወደ ፍጻሜ ምዕራፍ በማሸጋገርና የቅዱስ ሲኖዶሱን አቅጣጫዎችና ውሳኔዎች በማስከበር ልዕልናውን ለማረጋገጥ የሚበቃ የመሪነት ብቃትና ቁርጠኝነት ገንዘብ አድርጎ መገኘት እንደኾነ ተገልጧል፡፡ስለ ማኅበራት ጉዳይ በተመለከተም ቅዱስ ሲኖዶስ በግንቦት ፳፻፬ ዓ.ም. መመሪያው፣ የተከሠቱትና ወደፊትም ሊከሠቱ የሚችሉት ችግሮች በቀላሉ የሚታዩ እንዳልኾነ ገልጾ መንሥኤው በሕግና በሥርዐት የሚመሩበት ደንብ ስላልተሰጣቸው መኾኑንገልጧል፡፡ መፍትሔውም ማኅበራቱን ፓትርያርክ አባ ማትያስ እንዳሉት‹‹በጸበል ቀማሽነት›› መወሰን ሳይኾን ለቤተ ክርስቲያን እየሰጡ ያሉትን ታላቅ አገልግሎትና ብዛታቸውን መቆጣጠርን የተገነዘበ፣ ‹‹ራሱን የቻለና የሚያሠራ ሕግ›› ማዘጋጀት እንደኾነም አስቀምጧል፡፡ ለዚኽም ብፁዓን አባቶች፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንና የሕግ ባለሞያዎች ያሉበት ደንብ አዘጋጅ ኮሚቴ ሠይሞ ነበር፡፡ፓትርያርኩ ‹‹ኹላችኁ የምታውቁት አንድ ማኅበር፤ ማኅበሩ›› በሚል ስሙን በግልጽ ስለማይጠቅሱት ማኅበረ ቅዱሳንም ቢኾን ቅዱስ ሲኖዶሱ በዚያው መመሪያው፣ ማኅበረ ቅዱሳን በቅዱስ ሲኖዶስ የጸደቀ ደንብ ተሰጥቶት ከፍተኛ አገልግሎት እየሰጠ የቆየና አኹንም እየሰጠ ያለ መኾኑን አረጋግጧል፡፡ የተሰጠው መተዳደርያ ደንብና የአሠራር መዋቅሩ÷ የማኅበሩን ዕድገት የሚመጥን፣ ለቤተ ክርስቲያን ኹለንተናዊና የላቀ መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎት ለማበርከት የሚያስችለው ተደርጎ መሻሻል እንደሚያስፈልገው በመወሰንም የ፲፱፻፺፬ ዓ.ም. መተዳደርያ ደንቡን መርምሮ የሚያሻሽል ከብፁዓን አባቶች፣ ከሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንና ከሕግ ዐዋቂዎች የተውጣጣ ኮሚቴ ሠይሟል፡፡ ደንቡ ተሻሽሎ እስከሚጸድቅም ማኅበሩ ተጠሪነቱ ለብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ ኾኖ አመራር በመቀበል እየሠራ እንዲቆይም መመሪያ ሰጥቷል፡፡አምስት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትን፣ ሦስት የሕግ ባለሞያዎችንና ሦስት የማኅበረ ቅዱሳን አመራሮችን በአጠቃላይ ዐሥራ አንድ አባላትን የያዘው የመተዳደርያ ደንብ አጥኚ ኮሚቴም በሐምሌ ወር ፳፻፬ ዓ.ም. የጀመረውንና በተለያዩ ምክንያቶች ሲስተጓጎል የቆየውን የማሻሻያ ጥናት በ37 አንቀጾችና በ34 ገጾች አካትቶ በሚያዝያ ወር ፳፻፮ ዓ.ም. ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት አቅርቧል፡፡ይኹንና ከማኅበሩ የታወጀ ኦርቶዶክሳዊ ዓላማ ጋራ ርእዮታዊና ሃይማኖታዊ ተፃባኢነት (ተፃራሪነት) ያላቸው የውስጥ አማሳኞችና የውጭ ኃይሎች ለፓትርያርኩ ያቀበሏቸው የሚመስለውና ፓትርያርኩ አንዳችም ሳይጨመርና ሳይቀነስ በማሻሻያው ይካተት በሚል ሕጋዊነትም ምክንያታዊነትም የጎደለው የተልእኮ አስፈጻሚነት መመሪያ ሳቢያ የማሻሻያ ረቂቁ ዘግይቶም ቢኾን ጸጽቆ በሥራ ላይ መዋል ከሚገባው ካለፈው ዓመት ግንቦት የርክበ ካህናት ምልአተ ጉባኤ መደበኛ ስብሰባ አድሮ በእጅጉ ተጓትቶ ይገኛል፡፡ከማኅበሩ የአገልግሎት ፈቃድ ዕድሳት፣ ከአመራሮችና አስፈጻሚዎች ምርጫ፣ ከአባላት አያያዝ፣ ከሪፖርት አቀራረብ፣ ከገንዘብና ንብረት ቁጥጥር ጋራ የተገናኙ 24 ነጥቦችን የያዘው መመሪያው፣ የማኅበሩን የአገልግሎት ነፃነትና የአገልግሎት አቅሞች በሒደት የሚያዳክምና በመጨረሻም የሚያጠፋ እንደኾነ በመተዳደርያ ደንብ አጥኚ ኮሚቴው አብላጫ አባላት ስለታመነበት በማሻሻያው እንዳለ ይካተት ብሎ ለመቀበል አዳጋች እንደኾነ በወቅቱ ለፓትርያርኩ ተገልጦላቸዋል፡፡ ኮሚቴው በነጥቦቹ ላይ በወቅቱ ለፓትርያርኩ በሰጠው በሕግ ሞያ የተደገፈ ማብራሪያ፣ በመመሪያው ከተጠቀሱት ነጥቦች የተወሰኑት ቀድሞም በማሻሻያ ረቂቁ ያሉ መኾናቸውን የተቀሩት ደግሞ ቅዱስ ሲኖዶስ ስለ ደንቡ ዝግጅት ከሰጠው ውሳኔ ጋራ የሚቃረን መኾኑን በግልጽ አስረድተዋቸዋል፡፡

  • ባለፈው ዓመት ግንቦት፣ ቅዱስ ሲኖዶሱ የማሻሻያ ረቂቁን በአጀንዳነት ይዞ በተወያየበት ወቅት ይህንኑ የአጥኚ ኮሚቴውን ሐሳብ የተቀበሉት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ፣ የፓትርያርኩን የእልከኝነትና ግትርነት አካሔድ ተቃውመዋል፤ ‹‹24ቱን ነጥቦች ሳይጨምር ሳይቀነስ ካላስገባችኁ ውይይቱ አይቀጥልም፤ ስብሰባውንም አልመራም›› ያሉት ፓትርያርኩም ለብዙኃኑ ውሳኔ ባለመገዛታቸው የስብሰባው ሒደት እግዳት ውስጥ ገብቶ በዚያው ተቋጭቷል፡፡ ምልአተ ጉባኤው በመነጋገርያ አጀንዳዎች ላይ በተወያየበት በትላንቱ የቀትር በፊት ውሎውም ፓትርያርኩ ካለፈው ዓመት ግንቦት ለዘንድሮው ጥቅምት ያደረው የማኅበሩ የመተዳደርያ ደንብ ማሻሻያ ረቂቅ በአጀንዳነት እንዳይያዝ በብዙ ታግለው እንደነበር ተገልጧል፡፡ይኹንና ፓትርያርኩ በስብሰባው መጀመሪያ ላይ ቋሚ ሲኖዶሱ ለምልአተ ጉባኤው ካቀረበው የመነሻ አጀንዳ ዝርዝር ውስጥ ረቂቁ እንዳይያዝ በማድረግ ቢሳካላቸውም ምልአተ ጉባኤው የሠየመው ሰባት አባላት ያሉበትና በጉዳዩ ላይ ጽኑ አቋም የያዘው አጀንዳ አርቃቂ ኮሚቴ እንዳያካትተው ለመከላከል ግን ሳይቻላቸው ቀርቷል፡፡ በመኾኑም የማኅበረ ቅዱሳን መተዳደርያ ደንብ ማሻሻያ ረቂቅ ከምልአተ ጉባኤው 22 ያኽል የመነጋገርያ አጀንዳዎች ውስጥ በተራ ቁጥር 14 ሊካተት ችሏል፡፡ ይህም ፓትርያርኩ በ፴፫ኛው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ ጉባኤ በማኅበረ ቅዱሳን ላይ በቅስቀሳ መልክ ያነሷቸው ጥያቄዎች በአማሳኞች ጩኸትና በውጭ ኃይሎች ግፊት ሳይኾን በቅዱስ ሲኖዶሱ ታይቶ እንዲወሰን የያዘውን አቋም ትክክለኛነትና አሸናፊነት ያሳየ ኾኗል፡፡
  • በመክፈቻ ንግግራቸው ማኅበሩን በሕግ ለማስተካከል የዛቱት አባ ማትያስ፣ በእጅጉ የተጓተተው የማኅበረ ቅዱሳን ደንብ ማሻሻያ ረቂቅ በአጀንዳ ተይዞ እንዳይጸድቅ መከላከላቸው፣ ፍላጎታቸው ላይ ላዩን እንደሚወተውቱት ማኅበሩን በሕግና በሥርዐት መምራት አለመኾኑን እንደሚያሳይእየተገለጸ ይገኛል፡፡ ለዚኽም ለአኹኑ ምልአተ ጉባኤ የመጨረሻ መልኩን ይዞ እንዲቀርብ በተወሰነው የ፲፱፻፺፩ ዓ.ም. ሕገ ቤተ ክርስቲያን ማሻሻያ ረቂቅ ከተሰጠው የእርምትና ማስተካከያ አቅጣጫ ውጭ ሥልጣናቸውን የሚያጠናክሩባቸው አግባቦች እንዲካተቱ መደረጋቸው ተጠቁሟል፡፡ቅዱስ ሲኖዶሱ ተጨማሪ እርማትና ማስተካከያ እንዲያደርጉ ከሠየማቸው ብፁዓን አባቶች፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንና የሕግ ባለሞያዎችመካከል ልዩ ጸሐፊያቸውን ያስገቡት ፓትርያርኩ÷ በተለይም በሊቃነ ጳጳሳት ምደባና ዝውውር እንዲኹም በማኅበራት ጉዳይ ላይ የወሳኝነት ሥልጣን እንዲኖራቸው እንዲኹም ከቅዱስ ሲኖዶሱ ውጭና በላይ ራሳቸውን ተጠሪ አድርገውባቸዋል የተባሉ ሌሎች የማሻሻያ አግባቦች ምልአተ ጉባኤውን በከፍተኛ ደረጃ እንደሚያነጋግሩ ይጠበቃል፤ ምናልባትም የማሻሻያ ረቂቁን ከመጽደቅ ሳያዘገየው እንደማይቀርም ተሰግቷል፡፡የመንበረ ፓትርያርኩ መቀመጫ የኾነው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የፓትርያርኩ ልዩ ሀገረ ስብከት የኾነበት ልማድ፣ በሕገ ቤተ ክርስቲያኑ እያንዳንዱ ሀገረ ስብከትበቅዱስ ሲኖዶስ በተሾመ ሊቀ ጳጳስ ወይም ጳጳስ ወይም ኤጲስ ቆጶስ እንዲመራ ከሰፈረው ድንጋጌ አኳያ ተፈትሾ ራሱን የቻለ ሊቀ ጳጳስ ሊመድብለት እንደሚችልተጠቁሟል፡፡ ይህም በአኹኑ ወቅት ከአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን እስከ ልዩ ጽ/ቤት በተዘረጋው የአማሳኞች የምዝበራ ሰንሰለት ካህናትና ምእመናን በተለይም የመዋቅር፣ አደረጃጀትና አሠራር ለውጡን የደገፉ ወገኖች፣ ‹‹ከዛሬ ነገ እንባረራለን›› በሚል ስጋት አቤት የሚሉበት አጥተው በብቀላ ዝውውር የሚንገላቱበትን አላስፈላጊ ጣልቃ ገብነት እንደሚገታው ተገልጧል፡፡
  • ከምልአተ ጉባኤው ሌሎች አጀንዳዎች መካከል÷ ምእመናን በፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ መናፍቃን በእጅጉ ስለተፈተኑባቸው፤ የቤተ ክርስቲያን መሥሪያና የመቃብር ቦታ እስከመከልከልና እስከማጣት ስለደረሱባቸው፣ አብያተ ክርስቲያን ስለተቃጠሉባቸው በክልላዊ የጸጥታ ችግሮች ምክንያት ካህናትና ምእመናን ለኅልፈት ስለበቁባቸው የሐዲያና ስልጤ፣ የምዕራብ ወለጋና ቄለም ወለጋ እንዲኹም የጋምቤላ አህጉረ ስብከትይመክራል፡፡ በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳማት አስተዳደር በብፁዕ ሊቀ ጳጳሱና በማኅበሩ መካከል ስላለው አለመግባባት፤ በሕፃናትና ቤተሰብ ጉዳይ ድርጅት የሕፃናት መርጃ ኾነው የተቋቋሙ ማእከላት ነባር ይዞታዎች መጠበቅ እንዲኹም በቤቶችና ሕንፃዎች አስተዳደርና ልማት ድርጅት ከፍተኛ የግንባታ ፕሮጀክቶች ዙሪያ በመምከር ውሳኔ እንደሚያሳልፍም ይጠበቃል፡፡
  • source: haratewahido
  • - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/35668#sthash.6KEz0Dkn.dpuf

U.K. authorities accused of ‘dodging obligations’ in the abduction of Andargachew Tsige

THE INDEPENDENT
The partner of a British father-of-three being held on death row after he was spirited into Ethiopia has accused the Government of “dodging its obligations” by insisting it has no grounds for demanding his release.
Andargachew ‘Andy’ Tsege
Andargachew ‘Andy’ Tsege
Andargachew “Andy” Tsege, 59, was arrested at an airport in Yemen in June, and vanished for a fortnight until he reappeared in Ethiopian detention facing a death sentence imposed five years ago after a trial held in his absence.
The Foreign Office is now facing legal action after it classified Mr Tsege’s arbitrary disappearance and removal to Ethiopia as “questionable but not a criminal matter” and said that despite the risk of torture and the ultimate sanction hanging over him it did not feel “entitled” to demand he be returned home to London.
Yemi Hailemariam, Mr Tsege’s partner and the mother of their three children, told The Independent she was deeply concerned that Britain was soft-pedalling on his case to preserve its relationship with an increasingly important ally in east Africa.
Mr Tsege, who came to Britain as a political refugee in 1979 and is a prominent dissident campaigning against the Ethiopian regime, is feared by Ms Hailemariam and the legal charity Reprieve to be at extreme risk of torture. Electrocution, beatings and abuse, which includes tying bottles of water to men’s testicles, have been reported by detainees, and Mr Tsege’s whereabouts has not been revealed by the Ethiopian authorities.
Ms Hailemariam said: “For anyone reading what has happened, it must be clear that Andy is the victim of a crime. He was kidnapped to Ethiopia and faces the death sentence from a trial where he wasn’t even represented. He is a political prisoner.
“The Foreign Office is dodging its obligations and it is hard to see any other reason than it is to preserve Britain’s wider relationship with Ethiopia. It is now 117 days that he has been in detention and Britain must now say enough is enough.”
Reprieve, which has taken up Mr Tsege’s case, said it was starting legal action against the Government, potentially leading to a judicial review, to force it to press for the Briton’s immediate release and repatriation.
Maya Foa, director of the Reprieve’s death penalty team, said: “Andy Tsege is now well into his fourth month of detention and, incredibly, we are no closer to knowing where he is or even whether the Ethiopians plan to execute him. The UK Government’s unwillingness to take action is simply unacceptable.”
The father-of-three was en route to Eritrea when he was arrested during a two-hour stop over in the Yemeni capital, Sana’a, at the apparent request of the Ethiopian authorities, who seem to have had foreknowledge of Mr Tsege’s travel arrangements.
The Yemeni authorities have claimed the arrest and subsequent transfer of the Briton to Ethiopia – without any opportunity to challenge the move – took place on the basis of a security agreement between the two countries.
In a letter to lawyers for Ms Hailemariam, seen by The Independent, the FCO said it accepted “due process” did not appear to have been followed in the case but said his disappearance did not amount to a “kidnapping”.
It added that it required evidence that a British national was not being treated “in line with internationally accepted standards” before it could consider approaching local authorities. The letter said: “On the information presently available, the Foreign Secretary does not consider that the United Kingdom is entitled to demand Mr Tsege’s release or his return.”
Ms Hailemariam said: “Andy has been abducted and placed on death row on the basis of a politically motivated trial. It is difficult to think of circumstances that would fall further below ‘internationally-accepted standards’. What will it take for Britain to demand the return of one of its citizens?”
A FCO spokesman said: “The British Embassy in Ethiopia remains in contact with the Ethiopian authorities about regular consular access to Mr Tsege in the future so we’re able to continue to monitor his welfare. We also continue to press for reassurances that the death penalty imposed in absentia will not be carried out.”
The Independent revealed earlier this month that public money is being used to train security forces in Ethiopia under a £2m programme run by the Department for International Development (DfID) to fund masters degrees for 75 Ethiopian officials on improving the accountability of security services.
Material on the DfID website explaining the scheme has since been removed, prompting Reprieve to write to International Development Secretary Justine Greening asking whether the policy is under review or has been erased “to avoid embarrassment”.
DfID admitted it had cancelled the masters courses due to “concerns about risk and value for money”. A source said the decision was not linked to the case of Mr Tsege.
http://www.zehabesha.com/u-k-authorities-accused-of-dodging-obligations-in-the-abduction-of-andargachew-tsige/

Wednesday, October 22, 2014

ችግር ፈጣሪ በተባሉ የግንባታ ግብዓት አቅራቢዎች ላይ ዕርምጃ እንደሚወሰድ ማስጠንቀቂያ ተሰጠ


  • 73
     
    Share
addis-ababa-realethiopia-141የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለመኖሪያ ቤት ግንባታ ደካማ የሥራ አፈጻጸም ከፍተኛ አስተዋጽኦ አላቸው ያላቸውን ጠጠር አምራቾች አስጠነቀቀ፡፡ አስተዳደሩ ጠጠር አምራቾቹ በሕጋዊ መንገድ ሥራቸውን የማያካሂዱ ከሆነ ዕርምጃ እወስዳለሁ ብሏል፡፡
አስተዳደሩ ይህንን ማስጠንቀቂያ የሰጠው በጠጠር አቅርቦት ላይ የተከሰቱ ችግሮችን ለመፍታት፣ ጥቅምት 11 ቀን 2007 ዓ.ም. በጠራው ስብሰባ ላይ ነው፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ አባተ ስጦታው በስብሰባው ላይ እንዳሉት፣ በጠጠር አቅርቦት ላይ እየተፈጠሩ ባሉ ችግሮች እጃቸው ያለበት አካላት ወደ ሕጋዊ መስመር መግባት አለባቸው፡፡ አቶ አባተ አስተዳደሩ የማጣራት ሥራ ሠርቶ አፋጣኝ ዕርምጃ እንደሚወስድ አስገንዝበው፣ በዚህ ተግባር የተሰማሩ የአስተዳደሩም ሆነ አቅራቢ ኩባንያዎች ወደ ሕጋዊ መስመር እንዲገቡ አሳስበዋል፡፡
‹‹በእኛ ሠራተኞች ጭምር ማጭበርበርና ሌብነት አለ›› በማለት አቶ አባተ የጉዳዩን አደገኝነት አስታውቀዋል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 200 ኩባንያዎች የማዕድን ፈቃድ በማውጣት 370 ሔክታር መሬት ለጠጠር ማምረቻ ወስደዋል፡፡ አስተዳደሩ ለእነዚህ ኩባንያዎች በቂ መሬትና የኮንስትራክሽን ማሽኖችን ጨምሮ ለተለያዩ ሥራዎች ብድር አመቻችቶ መስጠቱን ገልጿል፡፡
አስተዳደሩ እነዚህን ድጋፎች ለአምራቾቹ ያቀረበው በከተማው እየተካሄዱ ላሉት ሦስት የመኖሪያ ቤት ፕሮግራሞች የሚያስፈልገውን ጠጠር ለማግኘት መሆኑን ገልጾ፣ ነገር ግን ይህ ዕቅድ በሕገወጦች ምክንያት እየተስተጓጎለ መሆኑን አስረድቷል፡፡
ስብሰባውን የመሩት አቶ አባተ እንደገለጹት፣ ከእነዚህ ኩባንያዎች ውስጥ አብዛኛዎቹ የወሰዱትን የማምረቻ ቦታ ለሦስተኛ ወገን አሳልፈው ሰጥተዋል፡፡ አምራቾቹ ለቤቶች ግንባታ ጠጠር ማቅረብ ሲገባቸው ለሌሎች ፕሮጀክቶች ቅድሚያ እንደሰጡና ‹‹በተለይም ሰው ሠራሽ ዋጋ በመፍጠር የዋጋ ንረት እንዲከሰት አድርገዋል፤›› ሲሉ ወቅሰዋል፡፡
በዘርፉ ወደ ሦስተኛ ወገን ማስተላለፍ፣ ከወሰዱበት ዓላማ ውጪ ለሆነ ተግባር ማዋል አስተዳደሩ ያነሳቸው ችግሮች ሲሆኑ፣ ከተሰብሳቢዎች ውስጥ ‹‹መሬትን ከነግዳጁ ለሦስተኛ ወገን ማስተላለፍ ችግሩ ምንድነው?›› የሚል ጥያቄ ቀርቧል፡፡
አቶ አባተ እንዳሉት መሬት እየያዙ ወደ ሦስተኛ ወገን ማስተላለፍ በፍፁም አይቻልም፡፡ ‹‹እኛ የምንፈልገው ኪራይ ሰብሳቢ ሳይሆን ልማታዊ ባለሀብት ነው፤›› በማለት ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ የአስተዳደሩ መሥሪያ ቤቶች በመቀናጀት የወሰዱትን መሬት ላልተገባ ተግባር ያዋሉ አምራቾች ላይ ዕርምጃ እንዲወሰዱ አቶ አባተ መመርያ ሰጥተዋል፡፡
በተሰብሳቢዎቹ ሥራቸውን ለማካሄድ የመሠረተ ልማት አለመሟላት ችግር እንደሆነ ተነስቷል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም አስተዳደሩ ግዥ የሚፈጽምበት ዋጋ ከማምረቻ ዋጋ ንረት ጋር እንደማይገናኝ የሚጠቅሱም አሉ፡፡ ይህንን የዋጋ ንረት ለመቀነስ የትራንስፖርት ሥራ ውስጥ ለመግባት እንዲፈቀድላቸው ጥያቄ አቅርበዋል፡፡ የመሠረተ ልማት ችግሮች ተብለው ከቀረቡት ውስጥ የመንገድ አውታር፣ የኤሌክትሪክና የውኃ መስመር አለመኖር ተጠቅሰዋል፡፡
በተለይ በኤሌክትሪክ በኩል ያለው ችግር ጎልቶ የወጣ ሲሆን፣ ባለሀብቶቹ ከሁለት ዓመት በፊት ክፍያ ፈጽመው የኤሌክትሪክ ኃይል ይለቀቃል ብለው ቢጠብቁም አለመለቀቁን ተናግረዋል፡፡
አስተዳደሩ በኤሌክትሪክ ኃይል በኩል ያለውን ችግር ለመፍታት ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጋር እየሠራ መሆኑን ጠቅሶ፣ ውኃና መንገድ ግን በተቻለ መጠን ባለሀብቶቹ ራሳቸው መሥራት እንደሚኖርባቸው አስገንዝቧል፡፡
የአዲስ አበባ አስተዳደር በተያዘው የበጀት ዓመት 125 ሺሕ ቤቶችን እየገነባ መሆኑን ገልጾ፣ ለእነዚህ ግንባታዎች 1.3 ሚሊዮን ሜትር ኩብ ጠጠር እንደሚያስፈልግ አስታውቋል፡፡
ባለሀብቶቹ ይህንን ጠጠር ማቅረብ የማይችሉበት አሠራር ከቀጠለ፣ የራሱን ማሽኖች በመግዛት ወደ ሥራ ሊገባ እንደሚችል አስተዳደሩ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል፡፡ የአዲስ አበባ ኮንስትራክሽንና ቤቶች ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌታቸው ኃይለ ማርያም እንደገለጹት፣ አስተዳደሩ ወደ ጠጠር ምርት የሚገባው የባለሀብቶች የሥራ አፈጻጸም ደካማ ከሆነ ብቻ ነው፡፡
Source:: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/35617

Rotary announces US$2 million in grants to fight polio in Ethiopia

By Rotary International
240x_mg_bfv2ylk88s_rotaryADDIS ABABA, Ethiopia, October 22, 2014/African Press Organization (APO)/ — In advance of the Oct. 24 observance of World Polio Day 2014, Rotary (http://www.rotary.org) announces US$2 million in grants to combat polio in Ethiopia. The funds – part of Rotary’s broader contribution of $44.7 million to end the paralyzing disease worldwide – will be used by UNICEF to support high quality polio immunization campaigns.
Logo: http://www.photos.apo-opa.com/plog-content/images/apo/logos/rotary.png
For the second year in a row, Rotary will mark World Polio Day with a livestream event featuring a global status update on the fight to end polio as well as an array of guest speakers and performers. The event, which will stream live from Chicago, Ill., can be viewed at endpolio.org.
In Ethiopia, Rotary’s PolioPlus program will celebrate World Polio Day by hosting a commemoration ceremony in conjunction with the World Health Organization, UNICEF and the Ethiopian Ministry of Health. The PolioPlus program will also host a World Polio Day march to mark the occasion and raise awareness of the disease.
Polio is set to become the second human disease ever to be eliminated from the world (smallpox is the first). To date, Rotary has helped 193 countries stop the transmission of polio through the mass immunization of children. Rotary’s new funding commitment targets countries where children remain at risk of contracting this incurable, but totally vaccine-preventable disease.
There are only three countries in the world where the wild poliovirus has never been stopped: Nigeria, Pakistan and Afghanistan. However, the virus from these countries can travel and lead to outbreaks in other parts of the world. In fact, last year the majority of the world’s polio cases stemmed from outbreaks in countries that had previously been polio-free. In particular, an outbreak in the Horn of Africa resulted in 217 cases in 2013, including nine in Ethiopia.
“We are pleased it appears we have halted the polio outbreak in Ethiopia,” said Tadesse Alemu, Rotary’s National PolioPlus Chair for Ethiopia, referencing the country’s only case this year, recorded more than nine months ago on 14 January. “However, given the mobility of our global society, until polio is gone from Africa – and the world – Ethiopian children will remain at risk for this disease.”
Rotary provides grant funding to polio eradication initiative partners UNICEF and the World Health Organization, which work with the governments and Rotary club members of polio-affected countries to plan and carry out immunization activities. Mass immunizations of children via the oral polio vaccine mustcontinue until global eradication is achieved.
Approximately $18.5 million will go to the three remaining polio-endemic countries: Afghanistan, Nigeria and Pakistan. An endemic country is one where the wild poliovirus has never been stopped. Another $9.5 million is marked for previously polio-free countries currently reporting cases “imported” from the endemic countries: Cameroon, Ethiopia, and Somalia. And $10.4 million will go to polio-free countries that remain at risk of reinfection: Democratic Republic of Congo, India, Niger, South Sudan, and Sudan.
The remaining $6.3 million will go toward polio eradication research.
Funds for these countries will be used to fight existing polio outbreaks, or to conduct campaigns to protect against the high risk for reinfection. Countries experiencing conflict, like Ethiopia’s neighbor Somalia, are at particular risk for polio outbreaks.
To date, Rotary has contributed more than $1.3 billion to fight polio. Through 2018, the Bill & Melinda Gates Foundation will match two-to-one every dollar Rotary commits to polio eradication (up to $35 million a year). As of 2013, there were only 416 confirmed polio cases in the world, down from about 350,000 a year when the initiative launched in 1988.
Distributed by APO (African Press Organization) on behalf of Rotary International.
Contact:
Stephanie Tobler Mucznik
+41 (0)44 387 7116
Stephanie.ToblerMucznik@rotary.org
About Rotary
Rotary (http://www.rotary.org) brings together a global network of volunteer leaders dedicated to tackling the world’s most pressing humanitarian challenges. Rotary connects 1.2 million members of more than 34,000 Rotary clubs in over 200 countries and geographical areas. Their work improves lives at both the local and international levels, from helping families in need in their own communities to working toward a polio-free world. In 1988, Rotary was joined by the WHO, UNICEF and the CDC to launch the Global Polio Eradication Initiative. Visit http://www.rotary.org and http://www.endpolio.org for more about Rotary and its efforts to eradicate polio. Video and still images will be available on the Rotary Media Center (http://goo.gl/DS86iD).
http://www.zehabesha.com/rotary-announces-us2-million-in-grants-to-fight-polio-in-ethiopia/

Friday, October 17, 2014

Gunmen kill three Ethiopian peacekeepers in Sudan’s Darfur

(Reuters) – Gunmen killed three Ethiopian peacekeepers who were guarding a water hole in Sudan’s strife-torn Darfur region on Thursday, their force said.
Two of the soldiers died at the scene in Korma, north Darfur, and a third died later from his wounds in Khartoum, said the joint U.N./African Union UNAMID peacekeeping mission. The attackers stole the Ethiopians’ patrol vehicle, it added.
news
“This has been a bloody October for UN Peacekeeping,” UN Secretary-General Ban Ki Moon told reporters in New York.
“In Darfur, Mali and the Central African Republic, we have lost 14 peacekeepers in hostile acts – nearly one per day.”
A total of 61 UNAMID peacekeepers have been killed in action since their force was set up in 2007 to stem violence in Sudan’s western region.
Darfur was plunged into turmoil in 2003 when mostly non-Arab rebels took up arms against the government, accusing it of neglecting the arid region, and Khartoum mobilised mostly Arab militias to crush the uprising.
The situation has since subsided into chaos with skirmishes involving bandits, rival insurgent splinter groups, warring tribes and lawless militias.
UNAMID’s joint U.N./African Union Special Representative Abidoun Bashua called on Khartoum to bring Thursday’s attackers to justice.
“An attack on peacekeepers constitutes a war crime and is punishable under international criminal law,” Bashua said.
(Reporting By Khalid Abdelaziz; Writing by Shadi Bushra; Editing by Andrew Heavens and Ken Wills)http://www.zehabesha.com/gunmen-kill-three-ethiopian-peacekeepers-in-sudans-darfur/


ሰማያዊ፣ መኢዴፓና ኢብአፓ የምርጫ ቦርድን ስብሰባ ረግጠው ወጡ

eth election

ምርጫ ቦርድ በጊዜ ሰሌዳ ላይ ለመወያየት በጊዮን ሆቴል የጠራውን ስብሰባ “ጥያቄዎቻችን የሚመልስ አይደለም” በሚል የሰማያዊ ፓርቲ ተወካዮች ስብሰባውን ረግጠው መውጣታቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ ከሰማያዊ ፓርቲ በተጨማሪም የመላው ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (መኢዴፓ) እና የኢትዮጵያ ብሄራዊ አንድነት ፓርቲ (ኢብአፓ) ተወካዮች ስብሰባውን ረግጠው ወጥተዋል፡፡ ፓርቲዎቹ በትናንትናው ዕለት ከምርጫ 2007 ዓ.ም በፊት ውይይት ሊደረግባቸውና ሊፈቱ ይገባል ያሏቸውን ጥያቄዎች ለምርጫ ቦርድ ያስገቡ ቢሆንም በዛሬው ስብሰባ በደብዳቤ ካሳወቋቸው ችግሮች ይልቅ የጊዜ ሰሌዳ ቅድሚያ የተሰጠው በመሆኑ የምርጫ ምህዳሩን ላይ የሚያመጣው ለውጥ የለም ብለው ስብሰባውን ረግጠው መውጣታቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
ስብሰባውን ረግጠው ከወጡት መካከል የኢትዮጵያ ብሄራዊ አንድነት ፓርቲ (ኢብአፓ) ዋና ጸኃፊ ወ/ት መሊሃ ጀሃድ “ትናንትና 12 ፓርቲዎች ሆነን ፈርመን ያስገባነው ደብዳቤ ነበር፡፡ በዚህ ደብዳቤ ባነሳናቸው ጥያቄዎች ላይ መልስ ካልተሰጠን በረቂቅ የጊዜ ሰሌዳው ላይ እንደማንነጋገር ገልጸን ነበር፡፡ ቦርዱ ደግሞ ትናንትና ባስገባነው ደብዳቤ ላይ ከመነጋገርና ለጥያቄዎቹ መልስ ከመስጠት ይልቅ በጊዜ ሰሌዳው ላይ ነው የምንነጋገረው አለን፡፡ ምርጫ ቦርድ ኃላፊዎች ስለ ጊዜ ሰሌዳው እንድንነጋገር ሲያደርጉ እኛ በአካሄድ ጥያቄዎቻችን መልስ እንዲሰጥ ጠየቅን፡፡ የቦርዱ ተወካዮች እሱን በሌላ ጊዜ ስብሰባዎች ላይ እንፈታዋለን፣ ዛሬ ስለ ጊዜ ሰሌዳው እንነጋገር በማለታቸው ስብሰባውን ረግጠን ወጥተናል” ስትል ረግጠው የወጡበትን መነሻ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጻለች፡፡
eth electionበተመሳሳይ የመኢዴፓ ሊቀመንበር አቶ ኑሪ ሙደሂር “ምርጫ ቦርድ ነጻና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ አደርጋለሁ የሚለው አባባሉ ተግባራዊ እንዲሆን ጥያቄዎችን አቅርበን ነበር፡፡ ይህን ጥያቄ የዛሬ 5 አመትም ጠይቀናል፡፡ ትናንትም በጋራ በደብዳቤ አስገብተናል፡፡ ገዥው ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ ከጀመረ 5 አመቱ ነው፡፡ ይህን ቅስቀሳ የሚያደርገው በመንግስት ገንዘብ ነው፡፡ የእኛ ጥያቄ የምርጫ ምህዳሩ መስፋት አለበት ነው፡፡ ትርጉም ያለው ምርጫ መደረግ አለበት ነው የእኛ እምነት፡፡ ይህን ለማድረግ የሚያስችሉ ጥያቄዎችን ለመመለስ ፈቃደኛ ስላልሆኑ ነው እኛ ስብሰባውን ረግጠን የወጣነው” ብለዋል፡፡
ሌላኛው የመኢዴፓ ተወካይና የፓርቲው ዋና ጸኃፊ አቶ ዘመኑ ሞላ በበኩላቸው “እነሱ ካቀረቡት የጊዜ ሰሌዳ ይልቅ የሚቀድመው ሜዳውን ማስፋት ነው፡፡ ትናንትና 12 ፓርቲዎች ተፈራርመን ያስገባነው ደብዳቤ ነበር፡፡ እኛም ቀድመን በተነጋገርነው መሰረት የጊዜ ሰሌዳው ጉዳይ ቀዳሚ አጀንዳ መሆን የለበትን የሚል አቋም ይዘናል” ሲሉ ስብሰባውን ካዘጋጀው ምርጫ ቦርድ ጋር ያላቸውን ልዩነት ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
ምርጫ ቦርድ በሚቀጥለው ስለ ችግሮቻችሁ ቁጭ ብለን እንወያያለን በሚል የማባበል ስራ እንደያዘ የገለጹት አቶ ዘመኑ “የ2002ትን ምርጫን ገምግመናል፡፡ ፓርቲዎች ያስገባነው ደብዳቤ አለ፡፡ አሁንም ገዥው ፓርቲ ከመቼውም ጊዜ በባሰ ሜዳውን እያጠበበና ራሱ ብቻ እየተጫወተበት ይገኛል፡፡ ትክክለኛ ምርጫ ለማድረግ ከታሰበ እናንተም ከገዥው ፓርቲ ጋር ያላችሁን ግንኙነት ቆም ብላችሁ አስቡበት ብለናቸዋል፡፡ ያቀረብናቸው ጥያቄዎች ቅድሚያ ስላልተሰጣቸው ስብሰባውን ረግጠን ለመውጣት ተገደናል” ብለዋል፡፡
ዘግይቶ በደረሰን መረጃ የኢትዮጵያ ማህረ ዴሞክራሲ ደቡብ ህብረት አንድነት ፓርቲ ተወካይ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስም ስብሰባውን ረግጠው መውጣታቸው ተግልጾአል፡፡
በትናንትናው ዕለት 12 የፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ ከምርጫ ከጊዜ ሰሌዳው በፊት በውይይት መፈታት አለባቸው ብለው ያመኑባቸውን ጥያቄዎች ለምርጫ ቦርድ በደብዳቤ መጠየቃቸው ይታወሳል፡፡ (ምንጭ፤ ነገረ ኢትዮጵያ)http://www.goolgule.com/ethiopian-parties-walked-out-of-election-board-meeting/


Wednesday, October 15, 2014

በግል ፕሬሶች ላይ የተከፈተው ዘመቻ ለነፃነት የቆሙ ዜጎችን አንገት የሚያስደፋ አይሆንም !!!



ከአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) የተሰጠ መግለጫ

******************
በግል ፕሬስ ጋዜጠኞች ላይ እየደረሰ ያለው እስር ሀገር ለቀው እንዲሰደዱ የሚደረገው አሰተዳደሪዊ ጫና እንዲሁም የግል ሚዲያው ዘርፍ ላይ እየተፈፀመ ያለው ሴራ ገዢው ፓርቲ በህገ ወጥ መንገድ በስልጣን ለመቆየት ከሚወሰዳቸው እርምጃዎች አንዱ እንደሆነ እንረዳለን፡፡ ገዥው ፓርቲ በሚከተለው ከዴሞክራሲያዊ አስተሳሰብ ያፈነገጠና ሴራን ማዕከል ያደረገው ፖለቲካ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ ከመሄዱም ባሻገር በአደባባይ የሚከወን አሳፋሪ ድርጊት ሆኗል፡፡ ይህም የሚያሳየው ገዢው ፓርቲ በስልጣን የሚቆየው በሃሳብ የበላይነት ሳይሆን ለጊዜው በቁጥጥሬ ስር ናቸው በሚላቸው የመንግሰት መዋቅሮችን በመጠቀም መሆኑ ይታወቃል፡፡
ፓርቲያችን የኢህአዴግ የ2007 ዓ.ም ሀገር አቀፍ ምርጫ ዘመቻ አካል እንደሆነ የሚያምነው ማሳደድና ማሰር በጋዜጠኞች ላይ ተጠናክሮ መቀጠሉ ገዢው ቡድን አሁንም መግባባት የተሞላበት ምርጫ እንዲከናወን ፍላጎት እንደሌለው ያረጋግጣል፡፡ የዚህ ዓይነት ድርጊትን የኢትዮጵያ ህዝብ ብሶት ከማባባስ ውጭ የሚጨምረው ፋይዳ ይኖራል ብለን አናምንም፡፡ በዚህ የተነሳ ለነፃነት የቆሙ ዜጎች አንገት ያሰደፋል ብለንም አናምንም፡፡
በዓለማቀፍ ደረጃ አንገታችንን እንድንደፋና እንደ ዜጋ እንድንሸማቀቅ በሚያደርግ መልኩ በተወሰደው አማራጭ የግል ፕሬስ የማጥፋት እርምጃ በርካታ ጋዜጠኞች ለሚወዷት ሀገራቸው ጀርባቸውን ሰጥተው ስደትን ምርጫቸው አድርገዋል፡፡ በቅርቡ ያለወገን ድጋፍና ያላስታማሚም የስደት ሰለባ የሆነው የግል ፕሬስ ባልደረባ ጋዜጠኛ ሚሊዮን ሹሩቤ በተሰደደ በጥቂት ጊዜያት ውስጥ ህይወቱ ማለፉ አሳዛኝ ክሰተት በመሆኑ ፓርቲያችን ለቤተሰቦቹና ወዳጆቹ አዘኑን ይገልፃል፡፡ ለዚህም ሃላፊነት በጎደለው ሁኔታ ጋዜጠኞች በሀገራቸው ላይ የመስራት መብታቸው ተገፍፎ በሚደርስባቸው ወከባ ከሀገር እንዲሰደዱ ያደረገው መንግስት ሃላፊነቱን መውሰድ አለበት፡፡ ገዢው ቡድን የሚሊዮንን ሞተ አስመልክቶ ለሚነሳ የህዝብ ጥያቄ መልስ እንዲሰጥ እንፈልጋለን፡፡
በተሰደዱ ጋዜጠኞች ላይ የሚደርሰውን እንግልት ሰምተን ሳናበቃም አልሰደድም ባሉ ጋዜጠኞች ላይ የሚደርሰው ጥቃት ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ የገዥውን ፓርቲ አምባገነንነት ሳይታክት በግልፅ የሚተቸው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በሀገራችን ህገ መንግሰት አንቀፅ 29 በተደነገገው መስረት ሃሳቡን በነፃነት ስለገለፀ ብቻ ህግን ተገን ተደርጎ በተከፈተበትና ለአመታት ፍርድ ቤት ሲመላለስ በኖረበት ክስ ወቅቱን ጠብቆ እንደሚፈነዳ ፈንጂ የምርጫ ወቅቱን ጠብቀው ጥፋተኛ በማለት ወደ ወህኒ ቤት ማውረድ ፖለቲካዊ እርምጃ መሆኑን አንጠራጠርም፡፡ ፓርቲያችን ይህን በህግ ሽፋን የሚፈፀም የፖለቲካ ሸፍጥ በቁርጠኝነት መታገሉን እንደሚቀጥልና እንደዚህ አይነቱ ግፍ ሊቆም የሚችለው ህዝቡን በማስተባበር በሰላማዊ ትግል አምባገነኑን ስርኣት መቀየር ሲቻል እንደሆነ ያምናል፡፡ ስለዚህ የኢትዮጵያ ህዝብ ከጎናችን በመቆም የዜጎች የመከራ ዘመን እንዲያጥርና ፍትሃዊነት እንዲሰፍን እንድናደርግ ሃገራዊ ጥሪ እናስተላልፋለን፡፡
በግፍ የታሰሩ ጋዜጠኞች፤ ጦማሪያንና ፖለቲከኞች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱም እንጠይቃለን፤ ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ከገዥዎች በችሮታ የሚሰጥ እንዳለሆነ ህዝቡ የሚገነዝብና መንግስት በሚወሰደው እርምጃ የተነሳም አንገቱን የሚደፋ አንድም ነፃነት ወዳድ ዜጋ እንደማይኖር እናረጋግጣለን፡፡
በመተባበር የኢትዮጵያውያንን መከራ ዘመን እናሳጥር!!
UDJ














http://www.zehabesha.com/amharic/archives/35435








Kenya: Embu Court Sends 11 Illegal Ethiopian Immigrants to Jail for Three Months

ELEVEN Ethiopians who were arrested in Mbeere South recently leading to protests which led to the shooting of two residents were yesterday jailed for three months.
After their arrest at Kiritiri market on October 8, locals wanted them to be released so they could lynch them as they suspected they were robbers.
Acting chief magistrate Alfred Kibiru said the 11, who pleaded guilty to being in Kenya illegally, will be jailed at the Embu GK Prison.
He said once they finish their sentence they should be deported. Kibiru summoned the owner of the car on which the Ethiopians were being ferried to explain why the court should not take it away. He issued a warrant of arrest for Ahmed Mur Amir who was driving the car. Amir failed to appear in court yesterday.
Since the Ethiopians were arrested the court has been looking for an interpreter who understands Amharic and English or Kiswahili.
The interpreter was available yesterday. The Ethiopians told the court that they were going to Nairobi where they had been promised good jobs after suffering in their country for many years. Kibiru said they should have followed the law if they wanted to work in Kenya.
http://www.the-star.co.ke/
http://www.zehabesha.com/kenya-embu-court-sends-11-illegal-ethiopian-immigrants-to-jail-for-three-months/

Monday, October 13, 2014

Breaking News – Independent Ethiopian Journalist Temesgen Desalegn Arrested

Breaking News – Independent Ethiopian Journalist Temesgen Desalegn Arrested


ተመስገን ደሳለኝ
ተመስገን ደሳለኝ
Ethiopian journalist Temesgen Desalegn has been arrested by Ethiopian police today, October 13, 2014 for articles he wrote before 2013.
Temesgen was the editor in chief of the critical newspaper, Feteh, which was closed by government order. The Ethiopian government filed over 100 lawsuits against him, some of which he is still fighting. He has also been arrested briefly in 2013. He worked as the editor in chief of another critical magazine, Addis Times before it also got closed by the government. 
Temesgen becomes raises the number of Ethiopian journalists and publishers charged and detained over 11 this year alone.
His next appointment is on October 27, 2014; the date he will be sentenced.
Source:: Debirhan