Wednesday, December 19, 2012

የእስራኤል ወገኖች ኦባንግን “ድረሱልን” እያሉ ነው


“ከኢትዮጵያ ስለመጣችሁ ታሰራችሁ”
የእስራኤል ወገኖች ኦባንግን “ድረሱልን” እያሉ ነው
አገር ቤት ያሉትን ወገኖች ለጊዜው መታደግ ካልተቻለ ቢያንስ ከማንም ተጽዕኖ ወጪ በስደት የሚኖሩትን ኢትዮጵያዊያኖች ለመርዳት ለሚቀርብ ጥያቄ የሚሰጠው ምላሽ የሚያሳዝን እንደሆነ አቶ ሳሙኤል አለባቸው በእስራኤል የኢትዮጵያን እናድን አንድነት ማህበር ሊቀመንበር ገለጹ። አቶ ኦባንግ ሜቶን ማህበሩ በተለይ መጋበዙን አስታወቁ።
ከሚያሳዝን መከራ ተርፈው እስራኤል ከደረሱ በኋላ እስር ቤት እንዲቆዩ የተደረጉት ታዳጊዎች መፈታታቸውን አስመልክቶ መግለጫ ያሰራጩት አቶ ሳሙኤል በተለይ ለጎልጉል እንደተናገሩት “በተለያዩ አገራት መከራ እየተቀበሉ ያሉትን ወገኖች መታደግ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ተቋማትና የፖለቲካ ፓርቲዎች ተግባር ሊሆን እንደሚገባ ጠቅሰው፣ በተግባር ግን ይህንን ማየት” እንዳልቻሉ ተናግረዋል።በእስራኤል እየደረሰ ያለውን የወገኖች ስቃይ አስመልክቶ ለቀረበ ጥሪ ምላሽ ለመስጠት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ግንባር ቀደም እንደነበር ያስታወሱት አቶ ሳሙኤል “በየአገሩ የተበተኑ ወገኖች እንደሚሉት በእስራኤል ያሉ ኢትዮጵያዊያን በአቶ ኦባንግና በድርጅታቸው አኢጋን ላይ ታላቅ እምነት አላቸው” ብለዋል።
“አቶ ኦባንግን ብቻ ሳይሆን አብረዋቸው ለሚሰሩት ሁሉ ልዩ ክብርና ፍቅር እንዳለን የምንገልጸው ዝም ብለን አይደለም” ያሉት አቶ ሳሙኤል “በጠላት ላይ ትኩረት አድርጎ በህብረት ከመስራት ይልቅ እርስ በርስ በመጠላለፍና ባለመተማመን በሚፈጥሩት ውዝግብ ጊዜያቸውን ከሚያባክኑት የተቃዋሚ ፓርቲዎች ይልቅ ኦባንግ የሚመሩት ድርጅት ውጤታማ ስራ ሲሰራ ይስተዋላል። ይህ እውነት በሁሉም ኢትዮጵያዊ ዘንድ በገሃድ የሚታወቅ ነው…” ሲሉ ተናግረዋል። ከህዝብ በቀረበ ጥያቄ አቶ ኦባንግ እስራኤል እንዲገኙ ጥሪ ማቅረባቸውንም አስታውቀዋል። ያስመዘገቡት ስኬት፣ የህይወት ተሞክሯቸውና ትምህርት ሰጪው ልምዳቸው፣ እንዲሁም የሚመሩት ድርጅት የገነባው ስም ለግብዣው ዋና ምክንያት መሆኑን አስታውቀዋል።
ለአንድ አገር ወዳድ የዜጎቹን ህይወት ከመታደግ በላይ ታላቅ ክብር የሚያሰጠው ጉዳይ እንደሌለ ያመለከቱት አቶ ሳሙኤል አድማሱ፣ “በህዝብ መወደድ እንዲሁ የሚገኝ ቀላልና ተራ ጉዳይ አይደለም። ቀናነትና መልካምነት እያደር በሁሉም ዜጎች ልብ ውስጥ የሚነደው በቀስታ ነው። ቀስ ብሎ የሚገነባ ክብር በቀላሉ አይናድም። ይህን የመሰለው ፍቅርና ክብር አቶ ኦባንግ ለሚመሩት ድርጅት አለን። ከተደረገው ነገር አንጻር ብዙ መናገር ቢገባኝም ለጊዜው ከዚህ በላይ የምለው የለም” ብለዋል፡፡
በተቃራኒው “አምላክ ይማርህ/ሽ የማይባልለት በሽታ ይዞናል። ብዙ ስራ አለብን። ብዙ ጉዳዮች ከፊታችን ተቀምጠዋል። አላማችን ኢትዮጵያ ናት ግን አንስማማም። ከመከራ፣ከግድያ፣ ከእስር፣ ልንማር አልቻልንም። ኢትዮጵያን ፊትለፊት በማሳየት ውስጥ ውስጡን ለግል ጥቅም የምንሰራ አለን። እንዲህ ያለው ድርጊት ሊያበቃ ይገባዋል” ብለዋል።

No comments:

Post a Comment