Monday, February 24, 2014

በባህር ዳር ከተማ የተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ እንድምታ (በገዛኸኝ አበበ ኖርዌይ )


እባካችው እናንተ የፖለቲካ መሪዎች አንድ ሆናችው ሕዝቡን  ለለውጥ አነሳሱት



























ይቼን  አጠር ያለች ጹሁፍ እንድጽፍ ያነሳሳኝ በትናትናው እለት የካቲት 16 2006 ዓመተ ምህረት  የአማራ ክልል በሆነችው በባህር ዳር ከተማ  አንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ (አንድነት) ፓርቲ እና መላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) በቅርቡ የብአዴን/ኢህአዴግ ዋና ፀሐፊ እና የአማራ ክልል ምክትል ፕሬዘዳንት አቶ አለምነው መኮንን የአማርን ሕዝብ በማዋረደ እና በማናናቅ በአማራ ሕዝብ ላይ የተናገሩትን ስነ ምግባር የጎደለው ንግግራቸውን በመቃወም የጠሩትን  በደማቅ ፣ ደስ በሚል እና በሚያኮራ ሁኔታ የተጠናቀቀውን ታላቅ ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ በቪዲዩ ከተመለከትኩኝ በኋላ ነው::

ይህ በትናትናው እለት ተካሂዱ በነበረው  የሰላማዊ ተቃውሞ ሰልፍ ላይ የባህር ዳር ከተማ ሕዝብ በተለይም ወጣቱ የህብረተሰብ ክፍል ሆ ብሎ በነቂስ በመውጣት እልህና ወኔ በተሞላበት ትህይንት ማንነቱን በገሀድ ያስመሰከረበት የተቃውሞ ሰልፍ እንደነበር ተመልክቻለው::  ወጣቱ ትውልድ ላይ ቁጭት ፣ ንዴት፣ እልህ እና ወኔ ይታይበታል የወያኔ የጭቆና እና የዘረኝነት አገዛዝ አማሮታል፣ ለውጥንም እንደሚፈልግ በአደባባይ በመጮህ  እየተናገረ ይገኛል:: የመለው የኢትዮጵያ ሕዝብ ምሬት እና ብሶት ኢህአዲግ እና የኢትዮጵያ ሕዝብን ሆድ እና ጀርባ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል:: ሕዝቡም ከምሬቱ እና ከብሶቱ ብዛት የተነሳ ወኔን እና ድፍረትን በተላበሰ መንገድ ነበር የተቃውሞ ድምጹን ሲያሰማ የዋለው ::

ሕዝቡ በነቂስ ወቶ በድፍረት የተቃውሞ ድምጹን እንዲያሰማ የአንድነት እና የመኢአድ አባላትም ሆነ አመራሮች በአንድነት በመሆን የሰሩት ስራ የሚያስመሰግናቸው እና የሚያኮራ ተግባር ሲሆን ለሌሏቹም የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ትምህርት ሊሆን ይገባል  እላላው ::  የኢትዮጵያ ሕዝብ ለውጥን ይፈልጋል::ስለዚህም  ለለውጥ እና ለትግል የሚያነሳሳው ቀስቃሽ አመራርን ይፈልጋል ::ይህን ለውጥ የናፈቀውን እና ነፃነት የናፈቀውን ሕዝብ ለለውጥ ትግል ማነሳሳት የተቀዋሚ ፓርቲ ድርጅቶች ተግባር እና ኀላፊነት መሆን ያለበት ጉዳይ ይመስለኛል :: የተቃዋሚ የፖለቲካ ፖርቲ ድርጅቶች አንድ ሀሳብ ይዘው በአንድ ራዕይ እና ትግል  ወያኔን ለመጣል እና ከስልጣኑ ለማስወገድ  ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፎችንም ሆነ ማንኛውንም የሰላማዊ ትግል እንቅስቃሴዎችን ለማድረግ ቢተባበሩ እና ሕዝቡን ቢያነሳሱት ለውጥን ናፋቂው የኢትዮጵያ ሕዝብ በምንም ሁኔታ ውስጥ በማለፍን እና ትግሉ የሚጠይቀውን ማንኛውንም መስዋዕትነት ለመክፈል ባገኛው አጋጣሟ ሁሉ ቆራጥቱን እያሳየ እና እያስመሰከረ ይገኛል::

ይህንንም የወያኔ ካድሬዎችም ሆነ ባለስልጣኖች ጠንቅቀው የሚያቁት እና አሳሳቢ ጉዳይ የሆነባቸው ይመስለኛል :: ለዚህም ነው በተለያየ መንገድ በሕዝቡ ላይ የአካልም ሆነ የስነልቦና ጥቃት እያደረሱ የሚገኙት በህዝቡ ላይ እየደረሰ ያለው የአካልም ሆነ የስነልቦና ጥቃትእንዳለ ሆኖ  ወያኔዎች ወጣቱን ለመከፋፈል በተለያየ  ጥቅማጥቅም በማታለለ ለመያዝ እየሞከሩ ይገኛሉ:: ነገር ግን ለሆድ እና ለጥቅማ ጥቅም አልገዛም፣ ለወያኔም ካድሬዎች አላጎበድድም የሚለውን ወገን፤ የዚያ ድርጅት አባል የዚህ ድርጅት ደጋፊ እያለ ተለጣፊ ስም በመስጠት ከትምህርት፤ ከስራ እያፈናቀሉት፤ እያሰሩት፤ እያንገላታቱ ያሉት። ወያኔዎች ምክንያትን እየፈጠሩ ወጣቱን በግፍ በመግደልና በማሰር ትውልዱ በፍርሀት እንዲርድና ከትግል ራሱን  እንዲያገል ለማድረግ እና የራሳቸውን  የስልጣን ዘመን ቋይታቸውን ማስረዘሚያ አማራጭ መንገድ ማሰር፣ መግደል እና ሕዝብን ማወከብ   ነው ብለው ያምናሉ::

ለዚህም ነው ማንኛውም የሰላማዊ ትግል እንቅስቃሴዎች እንዳይሳኩ እና ሕዝብ ተሳትፎ እና እንቅስቃሴ እንዳያደርግ ወያኔዎች ሕዝብን የሚያዋክቡት እና የሚያስሩት ሰሞኑንም የባህር ዳሩ የተቃውሙ ሰልፍ በሚገባ እንዳይካሄድ እና ሕዝቡም ወጥቶ በሰልፉ ላይ እንዳይገኝ ለማድረግ  የወያኔ ካድሬዎች እና የወያኔ ቅጥረኛ ፖሊሶች የባህር ዳር ከተማን ሕዝብ ሲያስፈራሩ፣ ሲረብሹ እና ሲያውኩ እንደነበር መረጃዎች ጠቁመዋል ::  ነገር ግን የወያኔ ወከባ ያልረበሸው  የበባህር ዳር ከተማ  የሚኖረው የአማራው ሕዝብ ፍርሃትን በመስበር   የኢትዮጵያን ስም እየጠራ እና እያወደሰ ዘረኛውን እና አንባገነኑን ፋሽስቱን የወያኔን ኢህአዲግን መንግስት እና ባለስልጣናቶችን  በድፍረት ሲያወግዝ እና ሲያዋርዳቸው ማየት በቂ እና  ኩራት ነው እያልኩኝ ለባህር ዳር ከተማና በአካባቢው ለሚኖረው ሕዝብ ምስጋናዪን አቀርባለው :: በባህር ዳር ከተማ የተደረገውን እልህ እና ወኔ የተሞላበትን አጠር ያለች የተቃውሞ ሰልፍ ቪዲዮ ይመልከቱ ::

http://www.youtube.com/watch?v=owvRnG4RWFM

Sunday, February 23, 2014

በአገሩ ሁለተኛ ደረጃ ዜጋ ሆኖ ባለሙያው እንዲበሳጭና እንዲማረር እያድረጉ የኢትዮጵያን አየር መንገድ መንከባከብና ማሳደግ ይቻላልን?

በከፍያለው ገብረመድኅን – The Ethiopia Observatory
በኢትዮጵያ አየር መንገድ ውስጥ ስለተንሰራፋው መጥፎ የማኒጅመንትና ብሄረስብ ላይ የተመሠረተ አስተዳደር ስለመኖሩ ብዙ ይነገራል። ታህሳስ 21፣ 1945 ተመሥርቶ: ረዥም ታሪክና ገና ከሥረ መሠረቱ በጥሩ የአስተዳደር ፍልስፍና ላይ የተመሠረተ በመሆኑ፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የነበረው የተመቻቸ ሁኔታ ለጥንካሬው ዋነኛ ምክንያት ሆኖታል።
የሁለተኛው የዓለም ጦርነት ማብቂያ ላይ አየር መንገዱ ሲቋቋም፡ ኢትዮጵያ በስሜንና በምሥራቅ የግዛት ክልሏ ራሱ እንኳ ገና አልተጠናቀቀም ነበር – የኤርትራ ሁኒታ አለየለትም። የዛሬይቱ ኦጋዴንም ተጠቃልላ ከእንግሊዝ ጋር በተደረገ በሕግ፡ በትሪቲ: ደንብና ድፕሎማቲክ ስምምነት ሙሉ የኢትዮጵያ አካል ለመሆን ገና ሁለት ዓመት ይቀረው ነበር።
ይህ የሚያሳየው አየር መንገዱና ኢትዮጵያ አብረው ያደጉና፡ ኢትዮጵያም ቀደም ሲል ለድህነንቷና ለግዛት አንድነቷ ታማኝነት በነበራቸው ሁለት መንግሥታት ሥር ለአየር መንገዱ የወደፊት ሕልውና እንደራሳቸው አካል ልዩ ትኩረት የሰጡት ኢንተርፕራይዝ ነበር። ባለፉት ሁለት አሥርተ ዓመታት ግን የሕወሃት የዘር ፖለቲካ አየር መንገዱንም እየተፈታተነው በመሆኑ፡ ውስጡ ያሉት ዜጎችም ሆኑ፡ ሌሎች ኢትዮጵያውንም የሚሰጉለት ድርጅት እየሆነ ነው።
ይህ ማለት ግን በእነዚህ ሁለት አሥርተ ዓመታት አየር መንገዱ አልተስፋፋም ማለት አይደለም – ብዙ ዕዳ ቢኖርበትም። ብዙ አውሮፕላኖች ተገዝተዋል፡ ብዙ የበረራ መስመሮች ተክፍተዋል። ነገር ግን የትኛውም ትክክለአኛ የማኔጅመንት ምሁር ሊያስረዳ እንደሚችለው፡ የአንድ ኢንተርፕራይዝ ጤንነትና አስተማማኝነት የሚለካው በዚህ ብቻ ቢሆንማ፡ ነገሮት ሁሉ ቀላል በሆኑ ነበር በዚህ በፉክክር በተወጠረ ኢንዱችትሪ ውስጥ።
CEO Tewolde Gebremariam during the Boeing award (Credit ENA)
CEO Tewolde Gebremariam during the Boeing award (Credit ENA)
አሁን ያለው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ማኒጅመንት የዘነጋው ዋናው ካፒታሉና ኢንቬስትመንቶቹ ሠራተኞቹ መሆናቸውን ነው – espirit de corps መጥፋት – እንደሌሎቹ የአገራችን ድርጅቶችና ተቋሞች ሁሉ! ድርጅቱ በዘር ፓለቲካ በመወጠሩ፡ ሕወሃት የሚመለክተው የራሱ ስዎች በአመራር ላይ መቀመጣቸውንና የዘር ፓለቲካቸውን ማራመዳቸውንና ድርጅቱን ጠቅመው እርስ በእርስ መጠቃቀማቸውን ነው። ይህ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ የወደፊት ተስፋውን ሰባሪ ሸውራራ አስተሳስብ እንጂ ቅንጣት ለሀገር ታስቦ የሚድረግ አይደለም።
እንደዚያ ካልሆነማ ለምንድነው ነባርና አዲስ የኛ ፓይለቶች የሚወዱትንና የሚኮሩበትን ኩባንያ እየተዉ፡ በአፍሪቃ፡ በመካከለኛው ምሥራቅና እስያ ውስጥ ለመሥራት የሚገደዱት? ይህ በመሆኑ አይደል እንዴ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባጋጠመው የማኔጅመንት ችግሮች የኢትዮጵያዊ ፓይለቶቻችን ቁጥር መመናመን (መሠረቱ በሁሉም መስክ በታጠቀ በስለላ ድርጅት የተጠናከረ ዘረኝነት ነው)። ለዚህ አይደል እንዴ: በዚህ ረገድ ራሷን ችላ የኖረች አገርና አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ለሌችም ፓይለቶችና መካኒኮች ለማሠልጠን የበቃች አገር፡ አሁን የውጭ ፓይለቶች ለመቅጥር የተገደደችው?
ዘወትር አጥሩ ዝቅተኛ በሆነበት በኩል መዝለልን ልምዳቸውና ፓለቲካቸው ያደረጉት የሕወሃት ስዎች፡ አፋቸውን አሹለው የብቃት ማንስን አንድ ጉዳይ አድርገው እንዳያነሱ፡ ደግነንቱ ዛሬም ቢሆን፡ ረዳት ካፕቴን ኃየለመድህን ስኞ ዕለት በብቃት እንዳሳየው ሁሉ፡ hኢትዮጵያውያን ፓይለቶች በሄዱበት ሁል ስመጥርና ታዋቂዎች የመሆናቸው ጉዳይ ከሕወሃትም ልደት በፊት የታሪክ ምሥክርነት አለው።
On the grass at Dar airport (Credit: Richard Bodin, via Wolfgang Thome’s Blong)
On the grass at Dar airport (Credit: Richard Bodin, via Wolfgang Thome’s Blong)
እስከአሁን በምንሰማው እስከአምስት የሚደርሱ የውጭ ሃገር ፓይለቶች እንዳሉ ይነገራል። የመረጃውን እርግጠኝነት ባላጣራም፡ ቲውተር ላይ እንዳየሁት ከሆ፡ ታህሳስ 18፣ 2013 የበረራ ቁጥር ET 815 ማረፊያውን ናይሮቢን ስቶ ዳሬስላም ሣር ውስጥር ሜዳ ቆፍሮ እግሩን የቆለፈው የኢትዮጵያ አውሮፕላን አብራሪም የውጭ ስው እንደነበረ ይነገራል።
ሌላው ችግርም እንዲሁ መካኒኮቻችንን ይመለከታል። እነርሱም አገር እየጣሉ እየሄዱ ነው። ባለፈው ዓመት ተኩል አገሩንና ሥራውን ጥሎ ጥገኝነት ለመጠየቅ ያለሁበት አገር የመጣ ከዩኒቨርሲቲ ክአሥርታት በፊት በማኒጅመንት ተመርቆ ሲሠራ የነበረ የቀድሞ የድርጅቱ ባልደረባ አንድ የኢትዮጵያውያን ማኅበራዊ ስብስብ ላይ አግኝቼው እንዳጫወተኝ፡ ባጭሩ ሁኔታው እንደሚክተለው ነው:
በሠራተኛው እይታ፡ አየር መንገዱ የድሮ ጥላውን እንጂ የዛሬ ሪያልቲውወንካራ ነው። ድሮ ለአየር መንገድ መሥራት ኩራት ነበር። ዛሬ ለአየርመንገዱ ለመሥራትና ታማኝ ነው ብሎ ለመታየት ሙያችንን ማሸነፋችን፡ሃላፊነታችንን መወጣታችንና ኢትዮጵያውያነታችን በቂ አይደለም። በሌላበኩል ደግሞ ሁለተኛ ደረጃ ዜጎች መሆናችን እንዲታወቅ ሆን ተብሎበሕወሃት ስዎች አያያዝና ተቀባይነት፡ ታማኝነት ልዩነቱ መሠመሩ ነው
“አንተ አየር መንገዱንና አገርህን ትተህ እዚህ ስትመጣ ሌላ የገፋፋህ ነገር የለም” ወይ ብዬ ስጠይቀው፡ ትክ ብሎ ተመልክቶኝ፡ “አገሪቱ ስላምና ጤና ሆና ማየትና የራሴን የወደፊት ተስፋዬን መገፈፌ ነው በተደጋጋሚ የሚሰማኝ የነበረ” አለኝ።
በእርግጠኝነት መናገር ባልችልም፡ ምናልባትም ረዳት ካፒቴን ኃይለመድህንን ያንገፈገፈውም ይህ ሊሆን ይችላል። አልያ ጤነነቱ የተረጋገጠ፡ በቆንጆ ገቢ ደህና ኑሮ ይኖር የነበረ ኢትዮጵያዊ ይህንን ትቶ ራሱን መሥዋዕት ለማድረግ ምን ያስገድደው ነበር?
ይህ ሁኔታ እንዴት ይታረማል?
እስከዛሬ ያለውን የሕወሃትን አሠራር ስመለከት፡ ጠባቡና ጎጠኛው ቡድን ትምህርት በማግኘት የሀገራችን ሁኔታ በቀላሉ መለወጡን የሚጠራጠር ስሜት በየቀኑ ይዳስሰኛል። ስዎቹ ሥልጣን በእጃችን ወይንም ማንም አይኖርም ብለው የቆረጡ ይመስላል።
ለዚህ ነው ሁሉም ሃገራችን በስላምና በብልጽግና ለልጆቻችን የምትተላፍበትን መንገድ መቀይስ የሚያስፈልገው። 95 ከመቶ የሚሆነው ሕዝባችን በሁለተኛ ድረጃ ዜግነት፡ እንዲሁም በድምሩ አምስት በመቶ የሚሆኑት የሕወሃት ደጋፊዎችና አጫፋሪዎቻቸው ከሌሎቹ ብሄረስቦች የተውጣጡትን ጭምሮ በሃገራችን ላይ የጫኑት የአፈና ቀነበር አሽቀንጥሮ መጣል አለበት።
ረዳት ካፒቴን ኃይለመድህን በወሰደው እርምጃ ዛሬ ኢትዮጵያውያን ለሶስት ተከፍለዋል። አንዱ ወገን የሕወሃት ሲሆን፡ እነርሱም እንደጠላት በመፈረጅ፡ “ከሃዲ” በማለት ረዳት ካፒቴኑን በሃገር ጠላትነንት ሲፈርጁት ይሰማሉ። ቤተስቦቹንም እያስቸገሯቸው መሆናቸው ይስማል።
ሁለተኛው ወገን፡ ሁኔታውን ሀገሪቱ ካለችበት የሥልጣን ብልግናና ከላይ እንደተገለእጽው የዘረኝነት ችግር ላይ መሆኗን ተናግረው ለፓይለቱ በጎ ይመኙለታል። ለኢትዮጵያ የነፃነት ሻማ አድርገው ይመስክሩለታል።
ሶስተኛው ወገን የሚጨነቀው፡ ለፓይለቱ ወይንም ሀገሪቱ ስላለችበት ሁኔታ ሳይሆን፡ አየር መንገዳችን ምን ዐይነት የወደፊት ሕልውና ያጋጥመው ይሆን የሚለው ሥጋት የሚያበስለስላቸው ናቸው።
ለማንኛውም፡ ለሕውሃትም ሲሉ ሳይሆን፡ የስዊስ መንግሥት ረዳት ካፒቴን ኃይለመድህን ላይ የረዥም ጊዜ እሥራት እንደሚፈርድበት አልጠራጠርም። አንዳንድ ስዎች ስለኤክስትራዲሽን ሲያወሩ ይስማሉ። በኔ እምነት፡ የሞት ቅጣትን በሃገሯ የሻረች ስዊትዘርላንድ፡ የሞት ቅጣትን የሕግ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የፓለቲካ መሣሪያ አድርጋ ለምትጠቀምበት ኢትዮጵያ ግለስቡን ለሞት አሳልፋ ትሰጠዋለች የሚል ቅንጣት ጥርጥር የለኝም።
ዋናው ጉዳይ ግን፡ ለረዥም ዓመታት ስዊትዘርላንድ ውስጥ እንዲታሰር መደረጉ ለኢትዮጵያውያን የታሪኩ ፋጻሜ ሊሆን አይገባም። በተለይም ይህንን እርምጃ አሁን እንደሚገመተው ፖለቲካ ከሆነ፡ እርሱን ያነሳሳው፡ ኢትዮጵያውያን የእርሱን የትግል አርማ ከፍ አድርገው ሕወሃትን ሊፋለሙትና የሃገር ጥፋት ፓለቲካውን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ሊገድቡት ይገባል። አለዚያማ እርሱን በቃላት ብቻ ማሞካሸቱ ከሌላው ወገን እንደሚመነጨው የጥላቻና ቂም በቀል የተለየ አያደርገውም። የእነርሱ ከሳሾች የሚሉት እኮ፡ ስዎችን አደጋ ላይ ጣልክ አይደለም – ማንም አልተጎዳምና። የእነርሱ ብሽቀት አገዛዛችንን አጋለጠ፤ ሥልጣናችንን ለአደጋ አጋለጠ ነው። የቡድን ጥቅም ቧንቧችንን ሊደፍንብን ሞከረ ነው። ይህ ደግሞ እውነትና ትክክል ነው።
የስሞኑን ጫና ለመቋቋም፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ማኔጅመንት የመረጠው የአየር መንገዱን የወደፊት ማስብ ሳይሆን፡ የዛሬዋን እሳት ማዳፈን ላይ ነው። ለምሳሌም ያህል ለመጥቀስ፡ አየር መንገዱ ከአውሮፕላን ሻጭ ኩባንያና ከሚዲያ ጋር በመተባበር፡ ለራሱ የአይዞህ መልዕክትና ምሥጋና በማስባሰብ ላይ መሠማራቱ: ከላይ እንዳመለከቱት፡ እነዚህ ስዎች እሳቱ እስኪበላቸውና ሀገራችንንም እስኪጎዳ ድረስ እንደማይቀየሩ የሚያመላክት ነው።
ስሞኑን አየር መንገዱ ብዙ ለቅሶ ደራሽች ነበሩት
ከስሞኑ ለቅሶ ፈጥኖ ደራሽች መካከል ቦይንግ ግንባር ቀደም ነበር። ይዞ የመጣውም ፋና እንደዘገበው the 2013 “GOLD Level Boeing Performance Excellence Award” ነው።
ሌላው ለቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ታቦ ምቤኪ ነፃ ቲኬት: የፕሮቶኮል ወንበር ስጥቶና በግብዣ አምነሽንሾ የኢትዮጵያ አየር መንገድን እንዲጎበኙ ማድረግ ነበር – ጥቅሙና ግንኙነቱ ገሃድ ባይሆንም። ለማንኝውም አድረጉት። ታቦ ምቤኪም የድርጅቱን ከአቪዬሽን ማሰልጠኛ አካዳሚ እና የአለም አቀፍ አየር መንገዶች አውሮፕላን የመገጣጠሚያ ክፍሎችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደዘገበው፡ ፕሬዝዳንት ምቤኪ ከጉብኝታቸው በኋላ በሰጡት አስተያዬት የአየር መንገዱ የማሰልጠኛ አካዳሚ አለም አቀፍ የአቪዮሽን ጥራትን ያሟላና በአህጉሪቱ ቀዳሚ የሆነ ተቋም ስለመሆኑ አድናቆታቸውን ገልጸዋል።
Welcoming at Ethiopian for Tabo Embeki (credit: ENA)
Welcoming at Ethiopian for Tabo Embeki (credit: ENA)
ስሞኑን ይህንን ጋጋታ በጽሞና ላዳመጠ ሰው፡ የአየር መንገዱ ዝና እንዳይጎዳ የሚወስድ እርምጃ መሆኑን መገመት ይቻላል።
አየር መንገዱ ባይጎዳ ደስ ይለኛል። ሕይወቱና ነፍሱ ተጠብቆ ከድል ወደ ድል እንዲሄድ በኢትዮጵያዊነቴ እመኛለሁ። ይህ ምኞት ግን ፋይዳ የለውም – የሕወሃት ስዎች ነገ ተመልስው የከአፕርታይድ ሊቀመኳስ Hendrik Frensch Verwoerd Verwoerd ካደረገው ባላነሰ በዘርና ጎጥ ላይ የተመሠረተ ኋላቀር ፖለቲካቸው ነገ ተመልስው የጥቅም ገበያቸውና ሌላውን ማተራመሻቸው ያደርጉታል! የዜጎችን ስሜት ሲጎዱና የሃገርን ስላምና ደህንነት መሠሪ በሆነው ፖለቲካቸው ሲመርዙት: በእነዚህ ድርጊቶቻችው፡ የሕዝቡን ምሬትም እያከረሩ፡ የታሪክ መንገድ አይታውቅምና በጥቂት የታሪክ ተጋባዦች አማካይነት በድንገት የሚቀሰቀሰው እሳት እንዲገላገለን ሁኔታውን እራሳቸው እያመቻቹት ነው!
ሃገራችን ወደፊት እንድትራመድ ከተፈለገ: በኢትዮጵያውያን እኩለነት ላይ የተመሠረተ የሁሉም ኢትዮጵያውያን አሰተዳደር መፈጠር የጊዜው ጥያቄ ነው። ይህ እስካልተቻለ ድረስ፡ በውንብድና በሃገርና ወገን ከሃዲዎች የውሸትና የተንኮል አመራር ላይ የተመሠረተ የሕወሃት አስተዳደርን ዕድሜ ለማሳጠር ብዙ ነገሮች ነገ በሌሎች ኢትዮጵያውያን ሊፈጸሙ ይችላሉ!
ይህ ደግሞ በሚገባ ተቀነባብሮ ካልተካሄደ፡ ብሽቀቱን በቀላሉ መገላገል ካለመቻሉም በላይ፡ በየቦታው በተበታተነ መንገድ የሚደረገው የአልገዛም ባይነትም በአገር ደኅንነትና ዕድገትም ላይ ጉዳት ይኖረዋል።
ነገር ግን ክትርፍ አሳድጅ የውጭ ኩብንያዎችና የውስጥ አላዛኞች ባለፍ፡ ሌላው ዓለምም አሁን የኢትዮጵያን አፓርታይድ አገዛዝ የሃገሪቱና የቀጠናው የወደፊቱ የችግር ምንጭ መሆኑን በሚገባ የተገነዘቡት ይመስላል!

የባህር ዳር ህዝብ ሆ ብሎ ወጣ!! ህዝቡ “ከባዶ ጭንቅላት… ባዶ እግር ይሻላል፡፡” አለ!

የተቃውሞ ሰልፉ መነሻ የብአዴኑ ምክትል ሊቀመንበር አለምነው መኮንን የአማራውን ህዝብ በመናቅ እና በመሳደብ የተናገሩት ቃል ነው:: አማራውን… “በባዶ እግሩ እየሄደ ሌላውን ይንቃል” ካሉ በኋላ ለአማራው የሚቆረቆሩትን ደግሞ “ለሃጫቸውን…” እና የመሳሰሉትን እዚህ ላይ ለመጻፍ የምንጸየፋቸውን ቃላቶች ጭምር በመጠቀም አሽሙር አይሉት ስድብ ሰንዝረዋል:: ነገሩ ከአንድ የአማራን ህዝብ እወክላለሁ ወይም እመራለሁ ከሚል ሰው የሚጠበቅ ባለመሆኑ ብዙዎችን አሳዝኗል፣ አናዷልም::
በመሆኑም የአንድነት እና የመኢአድ ፓርቲዎች በጥምረት ሆነው በባህር ዳር ከተማ የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ ወሰኑ:: ምክትሉ ሊቀመንበሩ ከሰልፉ በፊት እንደበፊቱ በትእቢት ተወጥረው ሳይሆን ረጋ ብለው ምን ለማለት እንደፈለጉ ቢያስረዱም ህዝቡ ግን ተቃውሞውን ቀጠለበት:: ለነገሩ በዚህ አጋጣሚ ሌሎች የሚነሱ የህዝብ ብሶቶች እንዳይነሱ በመስጋት የክልሉ አስተዳዳሪዎች አንዳንድ እንቅፋቶችን ለመፍጠር መሞከራቸው አልቀረም:: እርግጥ ነው… ተቃዋሚ ፓርቲዎቹ የተቃውሞ ሰልፉን ለማድረግ ሲዘጋጁ ብዙ እክል ገጥሟቸው ነበር:: ከተማ ውስጥ በራሪ ወረቀት መስጠት እና ቅስቀሳ ማድረግ ጭምር ተክልክለዋል:: ሆኖም ህዝቡ ራሱ ከልካዮቹን በመቃወሙ የፖሊሶቹ እገታ እና ጫና በረድ አለ:: ተቃዋሚዎቹ በባዶ እግር መሄድ ማለት ምንም ማለት እንዳልሆነ ለማሳየት ቅስቀሳ ሲያደርጉም ሆነ ዛሬ በሰላማዊ ሰልፉ ላይ… ጫማቸውን አውልቀው በባዶ እግራቸው ነበር የታዩት::
bahrdar demo13 2232014
ዛሬ እሁድ… እ.ኢ.አ የካቲት 16, 2006 ባህር ዳር ቀበሌ 12፣ ግሽ አባይ በሚገኘው የአንድነት ፓርቲ ጽ/ቤት አካባቢ ሰልፉ ሲጀመር የተለያዩ መፈክሮች እየተደመጡ ነው፡፡ በሰልፉ የፊት ረድፍ ላይ የፓርቲው ሊቀ መንበር ኢንጂነር ግዛቸው፣ ዶ/ር ኃይሉ አርአያ እና ሌሎችም አመራሮች ከህዝቡ ጋር ሆነው ታይተዋል:: ከግሽ አባይ የተነሳው ሰልፈኛ ጉዞውን በባህር ዳር ጎዳናዎች ላይ ማድረግ ሲጀምር ሌሎች በሺህ የሚቆጠሩ የከተማው ነዋሪዎች ሰልፈኛውን ተቀላቅለዋል:: የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ የያዙ ወጣቶች ከፊት ሆነው መፈክር በማሰማት ከተማዋን ከጠዋት እንቅልፏ አባነኗት:: የባህር ዳሩን የተቃውሞ ሰልፍ የአንድነት ፕሬዝዳንት ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው፣ የመኢአድ ፕሬዝዳንት አቶ አበባው መሃሪ፣ የትብብር ለዴሞክራሲ ሰብሳቢ አቶ ግርማ በቀለ እንዲሁም የአንድነት ፓርቲ ብሄራዊ ምክር ቤት አባል የሆኑት አንጋፋው ፖለቲከኛ ዶ/ር ኃይሉ አርአያ ከፊት በመምራት ላይ ይገኙ ነበር::
bahrdar demo7 2232014
ከባህር ዳር በደረሰን ዘገባ መሰረት… ህጻናት ልጆቻቸውን በጀርባቸው ያዘሉ፣ በዊልቼይር የሚሄዱ፣ አዛውንቶች፣ ወጣቶች በአንድነት ሆነው በባህርዳር ከተማ የተቃውሞ ድምጻቸውን አሰምተዋል፡፡
bahrdar demo9 2232014
ሰልፉ ከመጠናቀቁ በፊት ቁጥራቸው 15 ሺህ ያህል ሰዎች እንደነበሩ ነው ከስፍራው የተዘገበው:: በወቅቱ ከተያዙት መፈክሮች የተወሰኑት…
“የመሬት ቅርምቱ ያብቃ!”
“ህዝብን ከርስቱ ማፈናቀል ይቁም”
“ገበሬው በገዛ መሬቱ ስደተኛ አይሆንም”
“የህዝብን ክብር የደፈሩት አቶ አለምነው ለፍርድ ይቅረቡ”
“ከባዶ ጭንቅላት ባዶ እግር ይሻላል”
“ህዝብን እየሰደቡ መግዛት አይቻልም”
“ድል የህዝብ ነው”
“አቶ አለምነው የሰደቡት የአማራን ህዝብ ብቻ አይደለም”
“ብአዴን /ኢህአዴግ የአማራን ህዝብ የመምራት የሞራል ልእልና የለውም”
ከስፍራው ሁኔታውን እየተከታተለ በቀጥታ ሲዘግብ የነበረው ነብዩ ሃይሉ እንደገለጸው ከሆነ… በሰልፉ ላይ አቶ አለምነው በአማራ ህዝብ ላይ የተናገሩት የጥላቻ ንግግር ለሰልፈኛው ተለቆ ህዝቡ ንግግሩን በቁጭት በብአዴን ላይ ተቃውሞውን እያሰማ ነው፡፡
“ክብራችንን የደፈሩት የብአዴን አባላት ለፍርድ ይቅረቡ”
“ነፃነታችን በእጃችን ነው”
“ከባዶ ጭንቅላት ባዶ እግር ይሻላል፡፡”
“ብአዴን የአማራን ህዝብ ለመምራት የሞራል ልዕልና የለውም”
“መተማ የኛ ነው፣ ቋራ የኛ ነው” በሰልፉ ላይ ከተስተጋቡ መፈክሮች መሀከል ይገኝበታል፡፡ ሰልፉ በህዝብ እንደታጀበ ቀጥሏል፡፡
በመጨረሻም የየፓርቲዎቹ ተጠሪዎች ለህዝቡ ንግግር አድርገዋል:: አቶ አበባው መሃሪ
1-አቶ አለምነው መኮንን በህግ እንዲጠየቅ
2- ብአዴን የአማራ ህዝባ ወኪል ነኝ ማለቱን እንዲያቆም
3-አቶ አለምነው መኮንን የአማራን ህዝብ ይቅርታ እንዲጠይቁ አሳስበዋል፡፡
የትብብር ለዴሞክራሲ ሰብሳቢ አቶ ግርማ በቀለ በንግግራቸው… አቶ አለምነው እንዲህ እንዲናገሩ ያደረገውን አምባገነን የኢህአዴግ ስርአት ለመቀየር እንስራ ብለዋል፡፡
የሰላማዊ ሰልፉን የመዝጊያ ንግግር ያደረጉት የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ፕሬዘዳንት ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራው ናቸው፡፡ ኢንጂነሩ የመግቢያ ንግግራቸውን የከፈቱት በዛሬው እለት ደስ ካሰኙን መፈክሮች “ከባዶ ጭንቅላት ባዶ እግር ይሻላል” የሚለውን በማለት ነበር፡፡ ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው በንግግራቸው መጨረሻ ላይ አቶ አለምነው ይቅርታ ካልጠየቀና በህግ ፊት ካልቀረበ አንድነት በድጋሚ በባህርዳር የተቃውሞ ሰልፍ እንደሚጠራ አሳውቀዋል፡፡
አሁን ሰልፉ ተጠናቆ ህዝቡ በሰላም እንደወጣ፣ በሰላም ወደ ቤቱ እየተመለሰ ነው:: የሰላማዊ ሰልፉ በሰላም መጠናቀቅ የህዝቡን ጨዋነትና የአመራሩን ብስለት ያሳያል:: እርግጥ ነው… ሰላማዊ ሰልፉ ተጠናቆ ህዝቡ በሰላም ወደቤቱ ቢያመራም… ባህር ዳር ላይ የተለኮሰው የመነቃቃት ስሜት ግን በቀላሉ የሚበርድ አይመስልም:: እኛም መልካሙን ሁሉ እየተመኘን ዘገባችንን እዚህ ላይ አጠናቀናል::
ምስጋና: ሙሉውን ዘገባ ለማድረግ የቻልነው በተለይ ነብዩ ሃይሉ፣ ዳዊት ሰለሞን እና እስከዳር አለሙ ሁኔታውን እየተከታተሉ ከሚያቀርቡት የፎቶ እና የጽሁፍ መረጃ ተነስተን ነው:: በመሆኑም በኢ.ኤም.ኤፍ እና በአንባቢዎቻችን ስም ከልብ እናመሰግናችኋለን::

Friday, February 21, 2014

“ድምፁ የእኔ ነው ስድቡ ግን የእኔ አይደለም” አቶ አለምነው መኮንን (አቤ ቶኪቻው)


አቶ አልምነው“ድምፁ የእኔ ነው ስድቡ ግን የእኔ አይደለም” አቶ አለምነው መኮንን
አንድነት እና መኢአድ የተሳዳቢው ባለስልጣን አቶ አለምነው መኮንን እንጀራ እናት የሆነችውን ብአዴንን ለመቃውም እሁድ በባህር ዳር ሰልፍ መጥራታቸው እንደተስማ፤በኬኒያ የስደት “ኬዝ” ጋገራ
እኒያ የአማራ ህዝብ ምንትስ ነው… ቅብርጥስ ነው… ብለው በሞቅታ ውስጥ ያለ ሰው እንኳ የማይሞክረውን የስድብ ውርጂብኝ “በመረጣቸው” ህዝብ ላይ ያወረዱት ሰውዬ፤ ዛሬ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ቀርበው። “ድምፁ የእኔ ነው ስድቡ ግን የእኔ አይደለም… ይህ የተደረገው በኮምፒውተር ቆርጦ ቀጥል ቴክኖሎጂ ነው…” ብለው መግለጫ ሰጥተዋል መባሉን ስሰማ ሮጬ ወደ ኢቲቪ ድረ ገጥ ሄጄ ያሉትን ለመስማት ሞከርኩ።
“ድምጹ የእኔ ነው…” የሚለው ከንግግራቸው ውስጥ ተቆርጦ ውጥቷል። “ተሳደበ ይሉኛል… እንዴት እሳደባለሁ… መራጮቼን… ወላጆቼን… ዘመዶቼን… ወገኖቼን… ምን በወጣኝ እና ምን ቆርጦኝ እሳደባለሁ…???” ብለው እኛኑ ሲጠይቁ የሚያሳየው ንግግራቸውን ግን ሰማሁት።
እንግዲያስ አቶ አለምነህ፤
አንደኛ የብዙሃኑም ጥያቄ ይሄው ነው… ይሄ ህዝብ ቅጥ ባጣ ድህነት እንዲኖር የተፈረደበት አንሶ ምን በድሎ ምን አጥፍቶ ይብጠለጠላል… ምን በወጣውስ ይሰደባል…???
ሁለትኛ አዩት አይደል መቁረጫ እና መቀጠያ ቴክኖሎጂው ያለው ኢቲቪ ቤት ነው…! በአደባባይ ተናግረው ዞር ከማለትዎ “ድምጹ የእኔ ነው” የሚለው የእምነት ቃልዎ ተስረዘልዎ!
ሶሰት… አራት…አምስት…. መቶ፤ ይሄንን ለሁሉም ኢህአዴጎች ንገሩልኝ፤
ወይ ልቦና ግዙ! ንስሃም ግቡ እና ተንበርከካችሁ ይሄን ህዝብ ይቅርታ ጠይቁ፤ ወይ ደግሞ “ማስተዳደሩን” ርግፍ አድርጋችሁ ትታችሁ ማደሪያችሁን ፈልጉ!
http://ecadforum.com/Amharic/archives/11096/

“የረዳት አብራሪ ኃይለመድን እህት ታስራለች፣ ቤተሰቦቹ በግዳጅ ሊናገሩ ነው”


Tensay Abera (Co-pilot Hailemedhin's sister)
Tensay Abera (Co-pilot Hailemedhin’s sister)
ቦይንግ 767-300 ጄኔቭ አርፎ፣ መንገደኞቹ ወደየመድረሻቸው ተጉዘው አውሮፕላኑም ወደ ሀገሩ ተመልሷል። ነገር ግን የወሬው በረራ ማረፊያ ቦታ እንዳጣ ነው። የኃይለመድን ጉዳይ በየቦታው የመወያያ ርዕስ እንደሆነ ነው፣ ይቀጥላልም። የግምት ወሬዎች እዚህም-እዚያም እየተረጩ ነው። በተለይ የመንግስት ካድሬዎችን “ቢዚ” አድርጓቸዋል። በምን መልኩ የድራማውን ድርሰት እንደሚጽፉ ግራ ግብት ብሏቸዋል የአዕምሮ ሕመምተኛ ሊሉት ፈለጉ …ከዚያ ትዝ ሲላቸው አዕምሮ ታማሚ ሆኖ አየር መንገዱ መንግስት እንዴት እንዲያበር ፈቀደ፣ ለአብራሪዎቹ ምርመራ አያደርግም ወይ የሚሉት ጥያቄዎች ሊከተሉ ሆነ። ቀጥለው አባትዬው እቁብ ሰብሳቢ፣ አራጣ አበዳሪ… ተደርገው ተሳሉ። እእ..ደራሲዎቹ የቤተሰብ ጣጣ መሪ ተዋናዩ ላይ የሚፈጥረው ተጽዕኖ አልታይ አላቸው። የኃይለመድን እህት ሆነው የተዋቀረ እና የተዋቃ ጽሑፍ በፌስቡክ ላይ አከታተለው ጻፉ…በርግጥ ይሄኛው የወጭ የዜና አውታሮች ዘንድ ደርሶላቸው ተራግቦላቸዋል። ተአማኒነት ባያገኝም።
በነዚህ መጨበጫ በሌላቸው ወሬዎቹ አንድ ሊገባን የሚችል ነገር ቢኖር ካድሬዎቹ ደራሲዎች የአበራሪው ስም እና ስብዕና በአሉታዊ ጎኑ ብቻ እንዲነሳ መፈለጋቸው ነው። ከአየር መንገዱ ይልቅ የመንግስታቸው ህልውና እንቅልፍ ነስቷቸዋል። ምክንያቱም ኃይለመድን የጠየቀው የፖለቲካ ጥገኝነት ነው፣ ዝርዝር ባይኖረውም ይቺ ቃል የዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ትኩረት ስቧል። የHuman Rights Watch ዳይሬክተር ሌስሊ ሌፍኮው ስለክስተቱ ተጠይቀው የኢህአዴግ አምባገነናዊ እና ኢ-ሰብአዊነት የትኛውንም ዜጋ የሚያሰድድ እንደሆነ ሳያመነቱ ተናግረዋል። የእንግሊዙ Telegraphም በመረጃ አስደግፎ “ኢትዮጵያውን ያላማቋረጥ የሚፈልሱት በድኅነት እና በጭቆና ነው” ሲል ቁልጭ አደርጎ አስቀምጦታል። እና እንደዚህ ያሉ የኢህአዴግ መታወቂያዎች ከሀገሬው አልፈው ለተቀረው ዓለም እየደረሱ መሆናቸው ካድሬዎቹን አሰበርግጓቸዋል። አውሬ ደግሞ ሲበረግግ የሚያደርገውን አያውቅም።
አሁን የልጁን ቤተሰቦች አስገድደው እንደለመድነው ETV ላይ ድራማ ሊያሰሯቸው እንደሆነ መረጃዎች እየወጡ ነው። “ፌስቡኬ በሌሎች ሰዎች ጥቅም ላይ ውሏል” ያለችው እህቱም በእስር ላይ እንደምትገኝ ተሰምቷል።
እስኪ የሚያስብሏቸውን እንስማ መቼም ምንም ቢቧጥጡ እውነታዋ ያለችው ረዳት አብራሪ ኃይለመድን ጋ’ ስለሆነ ሊያጠፏት አይቻላቸውም። እኛም እሱ እስኪናገር ከይሆን-ይሆናል አሉባልታዎች ተቆጥበን በድርጊቱ መፈጸም በፊት ባንዲራችንን ተሸክሞ ከአድማስ አድማስ አውሮፕላናችንን እያበረረ ሀገሩን ሲያገለግል ለቆየው ኋይለመድን የምንሰጠው ክብር ይቀጥል።

አንድነት እና መኢአድ፤ በባዶ እግራቸው በመሆን በባህርዳር ቅስቀሳ እያደረጉ ነው።

andent ena mead
አንድነት እና መኢአድ፤ በባዶ እግራቸው በመሆን በባህርዳር ቅስቀሳ እያደረጉ ነው።
የአማራ ክልሉ ባለስልጣን፤ “አማራው በባዶ እግሩ ነው የሚሄደው…” ብለው እጅግ የከፋ ዘለፋ ካሰሙ ብኋላ ህዝቡ በያለበት ስለ ሰውዬው ያፈረላቸው ቢሆንም እርሳቸው ግን ሳያፈሩ ትላንት በቴሌቪዥን መስኮት ተከስተው ሲያስቁን ነበር።
ዛሬ እንደሰማነው እና እንዳየነው፤ የመኢአድ እና አንድነት አባላት እሁድ ለጠሩት ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ፤ በባዶ እግራቸው በመሆን ባደረጉት ቅስቀሳ “እኛም ጫማ የለንም፤ እኛም በባዶ እግራችን ነው የምንሄደው ቢሆንም ግን የሞራል ለዕልና አለን” የሚል ቅስቀሳ ሲያሰሙ ውለዋል።
በቅስቅሳው ወቅት ፖሊስ ጉልቤውን ሊያሳያቸው ቢሞክርም ህዝቡ ከበባ እያደረግ ሲከላከላቸው አንድነት ዛሬ ከለቀቀው ቪዲዮ አይተናል።
ድረ ገጻችን፤
…የምር ግን ህዘብ እየተዘለፈም እየተዘረፈም እንዴት ይችለዋል…. ???ብላ በትልቁ እየጠየቀች፤ አንድነት ያሰራጨውን ቪዲዮ ላላዩት 
http://www.youtube.com/watch?v=cKPuAnmzSNg



                                                               http://www.abetokichaw.com/

Tuesday, February 18, 2014

ESAT Daily News Amsterdam Feb 18 2014 Ethiopia

http://ethsat.com/video/esat-daily-news-amsterdam-feb-18-2014-ethiopia/

ኢህአዴግ ራሱ ባወጣው አፋኝ ሕግ ታፈነ

ለተፈጥሮ ሃብት የጠየቀው ዓለምዓቀፋዊ እውቅና ውድቅ ሆነ

eiti


ኢህአዴግ የተፈጥሮ ሃብትን በትክክለኛ መንገድ ለሕዝብ ጥቅም መዋሉን በመከታተል ለአገራት እውቅና የሚሰጠው The Extractive Industries Transparency Initiative (EITI) ለተሰኘ ዓለም ዓቀፋዊ ተቋም ያቀረበው የእውቅና ጥያቄ ማመልከቻ ከተገመገመ በኋላ መመዘኛዎቹን ማሟላት ባለመቻሉ መውደቁ ተሰማ። ኢህአዴግ የእውቅና ማመልከቻ በድጋሚ ማስገባቱን አስቀድሞ ያወቀው ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብት ጥበቃ ድርጅት (Human RightsWatch) ጉዳዩን ከሚከታተሉ ጋር ባገኘው መረጃ ኢህአዴግ የEITI መስፈርት የማያሟላና በሰብአዊ መብት ጥሰት የተወነጀለ ድርጅት መሆኑንን ማስረጃ አስደግፎ በመጥቀስ መሟገቻ ደብዳቤ ለድርጅቱ አስገብቶ ነበር።
EITI የዛሬ 11ዓመት አካባቢ የተቋቋመ በተፈጥሮ ሃብት ዙሪያ ዕውቅና የሚሰጥ ድርጅት ነው፡፡ ድርጅቱ የተፈጥሮ ሃብት የህዝብ መሆኑን የሚያምን ሲሆን ማንኛውም የተፈጥሮ ሃብት – ማዕድን፣ ዘይት፣ ብረታብረትና ጋዝ – ከመሬት በሚወጣበት ጊዜ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ የሚኖረውን ያህል ግልጽነትና ተጠያቂነት በሌለባቸው አገራት ድርጊቱ ለሙስና እና ግጭት በር እንደሚከፍት ይናገራል፡፡ በመሆኑንም ድርጅቱ አገራት ለሚያቀርቡት የዕውቅና ጥያቄ ማሟላት ያለባቸውን መስፈርት በዝርዝር አስቀምጧል፡፡ ልማትና እድገት በሚል ሰበብ የሕዝብ ሃብት የሆነውን የተፈጥሮ ሃብት በማውጣት የህዝባቸውን መብት ለሚረግጡ አገራት የሚያቀርቡትን የዕውቅና ማመልከቻ ውድቅ ያደርጋል፡፡
የጎልጉል የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ምንጭ እንደጠቆሙት ኢህአዴግ ያቀረበው የእውቅና ጥያቄ ውድቅ መደረጉ እውነት ነው። ምንጩ እንዳሉት ኢህአዴግ በውሳኔው በመበሳጨት ይግባኝ ለመጠየቅ በዝግጅት ላይ ነው። ድርጅቱ (EITI) አንድ አገር ለሚያቀርበው የእውቅና ማመልከቻ በመስፈርቱ መሰረት ግምገማ ካካሄደ በኋላ እውቅና እንዲሰጥ ሲያምን በራሱ ድረገጽ ላይ የዚያን አገር ስም በመመዝገብ ተጠቃሹ አገር ከተፈጥሮ ሃብት ጋር በተያያዙ ኢንቨስትመንቶች የሚገኘው ትርፍ ለህዝብ ጥቅም እንዲውል ያደርጋል የሚል እውቅና በመስጠት ምስክርነቱን ያሰፍራል፡፡
ኢህአዴግ የመጀመሪያው የማመልከቻ ጥያቄ ያቀረበው በአውሮጳውያኑ አቆጣጠር በ2009 አካባቢ ነበር፡፡ ከEITI አምስት መስፈርቶች መካከል አንዱ፤ ማመልከቻ የሚያቀርቡ አገራት ከመያዶች (መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች) ጋር ለመስራት ያላቸው ፍላጎት ተጠቃሽ ነው፡፡ በወቅቱ ኢህአዴግ በመያዶች ላይ አፋኝ ሕግ አውጥቶ የነበረ በመሆኑ እውቅና ሰጪው ድርጅት – EITI – የኢህአዴግን ማመልከቻ ውድቅ አድርጎታል፡፡ የEITI ቦርድ ይህን ዓይነት ውሳኔ ሲያስተላልፍ ያሰፈረው ነገር ኢትዮጵያ በእጩ አባልነት ለመመዝገብ በመጀመሪያ በመያዶች ላይ ያወጣችውን ሕግ ማስወገድ አለባት የሚል እንደነበር የሰብዓዊ መብት ጥበቃ ድርጅት በድረገጹ ላይ አስቀምጦታል፡፡ በወቅቱ የተሰጠው ይህ ብያኔ በEITI እውቅና አሰጣጥ ታሪክ ውስጥ የመጀመሪያ እንደሆነ ተጠቁሞም ነበር፡፡
የEITI ዕውቅናን ለማግኘት ቋምጦ የነበረው ኢህአዴግ በድርጅቱ ውሳኔ ባለመደሰት ጥቂት ዓመታትን ቆጥሮ ከአቶ መለስ ሞት በኋላ በአቶ ሃይለማርያም በመመራት በድጋሚ ዕውቅና የማግኘት ዘመቻውን ማጠናከር ጀመረ፤ በይፋም እንቅስቃሴውን ቀጠለ፡፡ የማዕድን ሚ/ር መ/ቤትም ዕውቅና ማግኘቱ በጣም የሚያስፈልግ እንደሆነ በይፋ በመናገር ዘመቻውን አጧጡፎ ነበር፡፡ ከዚህም አልፎ ለዓመታት ሲጠቀምበት የነበረውን አሠራር በዓለምአቀፉ ድርጅት ላይ ተግባራዊ በማድረግ ኢህአዴግ Ethiopia Revenue Transparency Initiative (ERTI) የሚባል “ተለጣፊ” ተቋም በመመሥረት እንቅስቃሴ ሲያደርግ እንደቆየ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ ለEITI በጻፈው ደብዳቤ ላይ ገልጾዋል፡፡
ጉዳዩን በቅርብ ይከታተሉ የነበሩ የዲፕሎማቲክ ምንጮች ኢህአዴግ በአውሮጳውያኑ አቆጣጠር 2013ዓም በድጋሚ ማመልከቻ የማቅረብ ዓላማ እንዳለው ለዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብት ድርጅት አሳወቁ፡፡ በወቅቱ ኢህአዴግ ማሻሻያ እያደረጉ ነኝ የሚል ማስመሰያ ለማቅረብ የሞከረ ቢሆንም የመያዶችና የጸረ አሻባሪነት አፋኝ ሕጎቹ በተጨማሪ በቴሌኮሙኒኬሽን በኩል በስልክና ኢንተርኔት የሚያደርውን ህዝብን የመሰለል ተግባር አጠናክሮ የቀጠለበት እንደሆነ በመጥቀስ ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ ክፍሎች EITI ዕውቅና እንዳይሰጥ መወትወታቸውን ተያያዙ፡፡
እነዚሁ ወገኖች በተደጋጋሚ ያደረጉት “የወረቀትና የፔቲሽን ትግል” እየተባለ የሚቃለለው ትግል ውጤት በማምጣት ኢህአዴግ በደጋሚ ያስገባው የአባልነት ማመልከቻ ሰሞኑን ውድቅ መደረጉ ተሰምቷል፡፡ እንደ መረጃው ከሆነ EITI ማመልከቻ በሚመዝንበት በሁሉም መስፈርቶች ኢህአዴግ ወድቋል፡፡
አነስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙና ኢህአዴግ “ልማታዊ” የሚላቸው ኢንቨስተሮች ሳይሆኑ በከፍተኛ ደረጃ የሚመደብ መዋዕለ ንዋይ የሚያፈሱ ባለሃብቶች ኢንቨስት የሚያደርጉበትን አገር ለመምረጥ የመጀመሪያው መለያቸው የEITI ድረገጽ የአባል አገራት ዝርዝር እንደሆነ ስለ አሰራሩ የሚያውቁ ይናገራሉ። ኢህአዴግም አስፈላጊውን የምዝገባና የማመልከቻ መስፈርት በማሟላት የተቋሙን እውቅና የጠየቀው በድርጅቱ ድረገጽ ላይ ለመመዝገብ ነበር። የሁለት ጊዜ ሙከራው መክሸፉ ኢህአዴግ ራሱ ባወጣው አፋኝ ህግ መታፈኑ የሚያመላክት እንደሆነ የሚጠቅሱ ክፍሎች፤ ከኢህአዴግ ከፍተኛ ፍላጎት አኳያና ሰሞኑን በተለያየ አቅጣጫ እየተወጠረ ከመምጣቱ አንጻር ሁኔታው አጣዳፊና ፋታ የማይሰጥ በሽታ ምልክት እንደሆነ በምጸት ይናገራሉ፡፡
ስለEITI ውሳኔ ባጭሩ እንዲያብራሩልን የጠየቅናቸው ባለሙያ እንዳሉት “አንድ ዩኒቨርሲቲ ህንጻ በማስገንባቱና አስተማሪዎችን በመቅጠሩ ብቻ ዩኒቨርስቲ ተብሎ ሊጠራ አይችልም። ዩኒቨርስቲው ዓለም ዓቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ስለመሆኑ በዓለም አቀፍ መስፈርት መሰረት ተገምግሞ እውቅና የሚሰጠው መስፈርቶቹን በሙሉ አሟልቶ ስለመገኘቱ ምርመራ ተደርጎበት ፈተናውን ሲያልፍ ብቻ ነው። በዚሁ መሰረት አልፎ እውቅና ያላገኘ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ገብቶ መማር የተሳትፎ ያህል ነው። መስፈርቱን አሟልተው እውቅና ካገኙት ጋር መወዳደር ስለማይችል ተመራጭ አይሆንም። በተመሳሳይ Extractive Industries Transparency Initiative (EITI) የተባለው ድርጅትም ከየአገራቱ እውቅና እንዲሰጥ የሚቀርብለትን ጥያቄ /ማመልከቻ/ የሚመዝንበት መስፈርቶች አሉት። ኢህአዴግ የተፈተነው በዚሁ አቅልጦና አንጥሮ በሚያወጣው መመዘኛ ነው ብለዋል፡፡”
ስለጉዳዩ የተጠየቀው የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ /አኢጋን/ የህዝብ ግንኙነት ግብረ ኃይል ጉዳዩን በጥልቀት የሚያውቀውና ገና ከጅምሩ ሲከታተል የቆየው መሆኑን በመግለጽ በበርካታ ፈርጆች ከሚያካሂደው ትግል አንጻር በዕቅድ ሲያከናውነው የቆየ መሆኑን አመልክቷል። የህዝብ ግንኙነት ክፍሉ ለጎልጉል እንዳለው ከሆነ “የEITI ውሳኔ ኢትዮጵያን እንደ አገር የሚጎዳ መሆኑ ግልጽ ነው፤ ሆኖም ውሳኔው ኢህአዴግ በራሱ ግትረኝነትና እብሪት ያመጣው ጣጣ በመሆኑ የራሱን ተግባር ተከትሎ የተወሰነው ውሳኔ በአገሪቱ ላይ በማንኛውም መልኩ ለሚያደርሰው ኪሳራ ተጠያቂው ኢህአዴግና ህወሃት ናቸው” ብሏል። በማያያዝም የጋራ ንቅናቄው ይህንኑ ጉዳይ አስመልክቶ መግለጫ በማውጣት አስፈላጊ ናቸው ለሚላቸው ወገኖች እንደሚበትንና ተቋሙ በውሳኔው እንዲጸና የሚቻለውን ሁሉ በማድረግ ላይ ለተሰማሩ መልዕክት እንደሚያስተላልፍ አመልክቷል።
http://www.goolgule.com/the-extractive-industries-transparency-initiative-eiti-rejected-eprdfs-application/

የረዳት አብራሪው እህት መልዕክት በግምገማ አይን…


የረዳት አብራሪው እህት መልዕክት በግምገማ አይን…397281_138042889641890_1097458037_n
የረዳት አብራሪው እህት በፌስ ቡኳ በኩል እንድ መልዕክት አስቀምጣ አግኝተናል። ይህንኑ መልእክት እንደሚከተለው በገምገማ አይን እናየዋለን!
በመጀመሪያ ይህን ጽሁፍ የምታነቡ ሰዎች በሙሉ የተዝረከረከ ከሆነባችሁ ይቅርታ እጠይቃለሁ። ከትናንት ከሰዐት በኋላ ጀምሮ እስካሁን ኢንተርኔትና ቴለቪዥን ላይ ያለማቋረጥ ተተክየ ስለቆየሁና በጥልቅ ሃዘን ስለተመታሁ አይምሮየ ትክክል ላይሆን ይችላል።
(አይዞሽ እታለም ችግርሽ ችግራችን ነውና እስቲ አውጊን እባክሽ….)
‘የኢትዮጵያ አየር መንገድን ወደ ሮም ይጓዝ የነበረ አውሮፕላን ጠልፎ ጄነቫ ላይ ያሳረፈው ረዳት አብራሪ እጁን ለስዊዝ ስጠ። ምክንያቱም ስዊዘርላንድ ውስጥ ጥገኝነት ለመጠየቅ ነው ብሏል።’ የሚለውን ዜና በርካታ የዜና ማሰራጫዎች ከየፊናቸው አስተያየት ጋር አቅርበውታል። የዜና ማሰራጫዎች ብቻ ሳይሆኑ የተለያዩ ወገኖች ያሻቸውን ብለዋል። የፖለቲካ ድርጅቶች የሰብዐዊ መብት ተሟጋቾችና እንደ አቤ ቶኪቻው ያሉ ቀልደኞች የየራሳቸውን ሃሳብ ለማስተላለፍ ተጠቅመውበታል። በጣም አሳዝኝ ነገር ነው። ሁሉም የየራሱን እምነት ለማስተላለፍ እንጂ እሱስ ምን ሆኖ ይሆን ብሎ አለማሰቡ ልብ ይሰብራል።
(ቆይ እማዬ እዝችጋ እኔም አስተያየት አለኝ፤ አንደኛ ነገር በዚህ ሁሉ መሃል እኔ ምስኪኑ እንደ ቀልድኛ የተቆጠርኩበት ምክንያት አልገባኝም።  ሁለትኛው ነገር ግን “ሁሉም የየራሱን መልዕክት ለማስተላለፍ ተጠቀመበት እንጂ እርሱ ምን ሆኖ ይሆን  ብሎ አለማሰቡ ልብ ይሰብራል ላልሽው…”  የጠላትሽ ልብ ስብር ይበልና ሁሉም ኢትዮጵያዊ እኮ ምን ሆኖ ይሆን ብሎ ሲጠይቅ ነበር። ሲጠይቅ ብቻም ሳይሆን ሲጨነቅም ነበር። በርግጥ አንዳንድ ወዳጆቻችን “መንግስታችንን አዋርደ…. ” በለው ሲቆጡ አይቻልሁ።፡በተረፈ…. እኔም የወንድምሽ እና ወንድማችን ሁኔታ ካሳሰባቸው መካከል ነኝ። እናም በእውነቱ ወቀሳሽ ፍትሃዊ አልምሰለኝም። እስቲ ለማንኛውም ቀጥይልን….)
ወንድሜ ሃይለመድህን አበራ የሰዎችን ደህንነት አደጋ ላይ ለመጣል አይደለም እንስሳትን ለመጉዳት የሚፈልግ ሰው አይደልም። ደግሞም ያንን የጨነቀውን ያክል ከፈራው ነገር ለመሸሽ ሞከረ እንጂ ማንንም ባለመጉዳቱና ሃሳብ እንኳ እንዳልነበረው ምንም አይነት ማጥቂያ መሳርያ ባለመታጠቁ አሳይቷል። በሁሉም ዘንድ የሚታወቀው ለተቸገሩ በመድረስና ባዛኝነቱ ነው። ካገር ውጪ ሄዶ ለመኖር የሚፈልግ ሰው ቢሆን ለሱ በጣም ቀላል ነገር ነው። ከጥቂት ወራት በፊትንኳ ዩኤስ ኤ ሄዶ ነበር። ከ አስር ቀናት በላይንኳ መቆየት አልፈለገም። ዝም ብሎ ካገር መውጣት ቢፈልግ ከዛ የተሻለ አጋጣሚ አልነበረም። ደግሞም በኑሮ ደረጃ ውጪ ቢኖር ያን ያክል የሚያሻሽለው ነገር አይደለም። ምክንያቱም የገንዘብ ችግር የለበትም። ከራሱም አልፎ ለብዙ ሰዎች የሚተርፍ ገቢ ነበረው።
(ይሄንን ሁላችንም እናምናለን። እንኳንስ የአውሮፕላን እርዳት እና የታክሲ ረዳትም ዛሬ ግዜ ገቢው ቀላል አይደለም።(እዘችጋ ትንሽ ቅልድ ቀላⷅያለሁ….))
ከልጅነቱ ጀምሮ ጎበዝ ሳይሆን እጅግ በጣም ጎበዝ ጭንቅላት ያለው ወጣት ነው። አብዛኛዎቹን ክፍሎች ሁለት ሁለት እያለፈ አስራ ሰባት አመት ሳይሞላው ሀይስኩል ሲያጠናቅቅ የ አስራሁለተኛ መልቀቂያ ውጤቱ ሁሉም ኤ ነበር። የጀመረውን የ አርክቴክቸር ትምህርት ትቶ ወደ ፓይለትነት የገባው ለሙያው ካለው ፍቅር የተነሳ ነው። ለኢትዮጵያ አየር መንገድም የተለየ ክብር አለው።
(ይሁን…. ይሄንንም ማመን አይቸግረንም…. ቀጥይ እታለም….)
ሃይለመድህን ሁሉንም አስታዋሽ ቤተሰቡን የሚወድና ተጫዋች ሰው ነበር እስከ ቅርብ ጊዜ። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ለኛ ያለውን ፍቅር ደህነታችንን በማረጋገጥና የሚያስፈልገንን ሁሉ በመታዘዝ ቢገልጽም ከዘመድ ወዳጆቹ ጋር መገናኘትና አቆመ። የወትሮው ጨዋታና ደስተኝነቱ ቀርቶ ብቸኝነትን የሚወድ ዝምተኛ ሆነ። ህይወቱ ደስታ የራቀው መሰለ። በሁኔታው ተደናግጠን ደጋግመን በመጠየቅ ያወቅነው ሊያጠቁት የሚከታተሉት ጠላቶች እንዳሉ እንደሚያምን ነው። ስልኩን እንደጠለፉት ያስባል፤ በላፕቶፑ ካሜራ ሳይቀር ያዩኛል ብሎ ስለሚሰጋ ካሜራውን ሳይሸፍን አይከፍተውም፤ ወጥቶ እስኪገባ ቤቱን ሲበረብሩ የቆዩ ስለሚመስለው ካሜራ ጠምዶ መሄድ ሁሉ ጀምሮ ነበር። ባጠቃላይ በታላቅ የመንፈስ ጭንቀት እየተሰቃየ ነው። የሚያሳዝነው ደግሞ ይህንን ጉዳቱን ለኛ ለቤተሰቡንኳ አብራርቶ አለመናገሩ ነው። ወንድሜ ለሰዎች እርዳታ ለመድረስና የሌሎች አዳኝ ለመሆን የማይታክት ሰውንጂ እንዲህ በሚያንገበግብ ስቃይ ውስጥንኳ ለራሱ አስቦ እርዳታን የሚጠይቅ ሰው አይደለም። ሁኔታውን በደበስባሳው በታወቀበት ጊዜንኳ የሚያስፈልገውን የህክምና በማቅረብ ስላልረዳነው ቤተሰቡ ሁሉ እንደግር ሳት ይከነክነዋል።እሱ ግን እንዲህ ባለ ጥልቅ የመንፈስ ጭንቀት ውስጥንኳ ለኛ አንድም ቀን ሳያስብ ቀርቶ አያውቅም።
(ውድ እህታችን  ይሄ ነገር አልመስልህ ብሎኛል።  ለምሳሌ ከላይ ካሰፈርሽው አንቅፅ ውስጥ “በሁኔታው ተደናግጠን ደጋግመን በመጠየቅ ያወቅነው ሊያጠቁት የሚከታተሉት ጠላቶች እንዳሉ እንደሚያምን ነው።” አልሽን። እንደሚያምን ነው ማለት፤ ….ግን ማንም የሚከታትለው የለም ለማለት ነው። ይሄንን በምን አረጋገጥሽ… እንዲህ አይነቱ ጭንቀትስ እንደምን ከባዶ ሜዳ ይመጣል… ሌላው፤ “የሚያሳዝነው ደግሞ ይህንን ጉዳቱን ለኛ ለቤተሰቡንኳ አብራርቶ አለመናገሩ ነው።” አልሽን ታድያ ወንድምሽ እና ወንድማችን አብራርቶ ያልነገራችሁን ነገር አንቺ ከየት አምጥተሽ አብራርተሽ ነገርሽን…. ?) ከዚህ በተጨማሪ አንድ አጎትሽ የሰጡት መገለጫስ ሰምተሽው ይሆን….  እሰቲ ለማንኛውም… እንስማሽ…)
ይህን የምታነቡ ወገኖች ሁሉ ዛሬ እኔ ይሄን ከምጽፍ እግዚአብሄር ምስክሬ ነው እሱ ወደነበረበት ጤናና ሁኔታ ተመልሶ እኔ ሞቼ ቢሆን እመርጣለሁ። ውሸት ከሆነ ይህንን በማድረግ የውሸቴን መልስ እንዲያሳየኝ አምላኬን እለምነዋለሁ። በኛ አገር መስሪያ ቤቶች የሰዎችን እውቀት ብቃትና ቁመና ሳይቀር ሲመዝኑ የዐይምሮ ጤንነት ሁኔታን አለመከታተላቸው እጅግ የሚያሳዝን ነገር ነው።
(እዝች ጋ ውሸት ከሆነ የምትለውንም ቃል ምን አመጣት ብዬ ማስቤን አልደብቅሽም።  በተጨማሪ ግን  እታልም፤ አንቺ ራስሽ ወንድምሽ እና ወንድማችን እንዲህ ያለ የዕምሮ ስቃይ ውስጥ መኖሩን ያወቅሽው ትላንት አወሮፕላን መጥለፉን ስትሰሚ ካልሆነ በስተቀረ… ቀደመሽ ብታውቂ ኖሮማ ሀክምና ቦታ ሳይሄድ ስራ ቦታ ሲሄድ ዝም አትይም ነበር። ስለዚህ “የተከበረውን” አየር መንገዳችንን መውቅስሽ አልተዋጠልኝም።) .
ወንድሜ ትናንት አውሮፕላኑ ውስጥ ከመግባቱ በፊት ምን አጋጥሞት ይሆን እነዛ የሚላቸው ሰዎች ሲመለስ ጠብቀው እንደሚገሉት ዝተውበት ያንን ፈርቶ ይሆን ወይም ፓይለቱ ከጠላቶቹ ጋር በመተባበር ሊይጠቃው እንደሚችል ብማመን ሰግቶ ይሆን ሲወጣ ራሱን ለመከላከል በሩን የዘጋው ከሁለቱ አንዱ ወይም ሁለቱም እንደሆነ አምናለሁ። አስቡት በዛች ቅጽበት አለሙን በሙሉ ሊያናጋ የሚችል ምንም አይነት ራሱን ሊከላከልበት የሚችል መሳርያ ሳይዝ ይህንን ድርጊት የሚያስፈጽም ምን ነገር ሊኖር ይችላል ስዊዘርላንድ ገነት አይደለችም። የዐይምሮ ህመም ሰለባ የሆኑ ሰዎችን ለዚያውም በማንም ላይ ምንም ጉዳት ባልፈጸሙበትና ሊፈጽሙም ባላሰቡበት ሁኔታ ወደስር ቤት እንዲወረወሩ ህግ የሚፈቅድ አይመስለኝም። ሃይለመድህን ለህይወቱ ሰግቶ ነበር። የሰው ልጅ ሊቋቋመው በማይችል የመንፈስ ጭንቀት ገሃዱና ሃሳባዊው አለም በተዘበራረቀበት የስቃይ አለም ውስጥ ብቻውን ሲሰቃይ ነው የቆየው። በተስተካከለ የዐይምሮ ጤንነት ላይ የሚገኝ ሰው ላይገባው ይችላል። እኔ ግን የሱን ግማሽ ባያክልም የተወሰነ ይህንን መሰል ችግር ስላለብኝ ህመሙን አውቀዋለሁ። ሁሌም በሳት እየተጠበሱ መኖር ማለት ነው
(እህቴ ሙች   እንኳ ምንም እየነገርሽን ያለው የሚያሳዝን ነገር ቢሆንም፤ ይህንንም አንቀጽ ተጠርጣሪ ሆኖ አግኝቼዋልሁ። አንደኛ ነገር ርስ በርሱ የሚምታታ ሃሳብ ይዘዋል። ቅድም የሚያሳድዱት ሰዎች እንዳሉ ያምናል ያልሽን ልጅ አሁን ደግሞ የሚያሳድዱት ሰዎች ዝተውበት ይሆናል…. ስትዪን በርግጥም የሚያሳድዱት ሰዎች አሉ ወይስ ሃሳቡ የፈጠራቸው ናቸው … የሚለውን ግራ አጋብተሽናል። ሌላው እኔም ከእርሱ ባነስ መልኩም ቢሆን ይሄው ችግር ስላለብኝ ስትዪ የነገርሽን ሃሳብ ችግሩን ቤተሰባዊ ለማድርግ እነ እንትና ሆነ ብለው ያስገቧት ቃል ትመስላለች።)
ወገኖች መልዕክቴን አንብባችሁ በምትችሉት ሁሉ ረዳት ፓይለት ሃይለመድህን አበራ ፍትህ አግኝቶ ወደ ነበረበት እንዲመለስ በመጣር እንድትተባበሩን መላ ቤተሰቡ በምታምኑት ሁሉ እንለምናችኋለን! እኛም የሚያስፈልገውን የህክምና እርዳታ አግኝቶ ወደ ቀድሞው ጤናው ከተመለሰ በኋላ ለዚች አገር ባለው አቅም ሁሉ እንዲያገለግል በማድረግ እንክሳለን!
(ይሄንን መለዕክት እኔም እጋራልሁ… ሃይለመድህን አበራ የስዊዝ መንግስት ነፃ ሊለቀው ይገባል። ችግሩ ምንም ይሁን ምንም በርካታ ጥገኝነት መጠየቂያ አማራጮች እያሉት ይህንን እርምጃ የወሰደው የከፋ ነገር ቢደርስበት መሆኑ ግልጽ ነው።)
የኔ ማጠቃለያ
በኢትዮጵያ ፍትህ ማጣት ብርቅ አይደለም። ባለስለጣኖቻችን የሚያድርሱብን በደል  ለአዕምሮ መታወክ ብቻ ሳይሆን ለሀገር መታወክም ይዳርጋል። ከሃይለ መድን እህት በተጨማሪም፤ አንድ አጎቱም፤  ”ከአንድ ወር በፊት ድንገት የሞቱ አጎቱ ሁኔታ ለከባድ የአዕምሮ መታወክ ዳርጎታል።” የሚል አስተያየት ለአሶሽየትድ ፕሪስ ሰጥተዋል። በርግጥም ይህ መሆኑን የስዊዝ ሃኪሞች ማረጋግጥ ከቻሉ ሃይለመድን ነገሩ ይቀልለታል። እኛም ደስ ይለናል።
ነገር ግን፤ እህቱ እና አጎቱ በተለያይ አገላለጽ፤ ምክትል አብራሪውን የአዕምሮ ህምምትኛ ነው ማለታቸው፤ እንዲሁም እህቱ ጽሁፏን ስትጀምር ግልጽ ባልሆን ምክንያት የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችን፣ ጋዜጠኞችን እና እኛ ቀልደኞቹን ሳይቀር አጓጉል በመተቸት መጀመሯን፤ እንዲሁም የመንግስታችንን የቀደመ ልምድ ልብ በማለት እህትም ሆነች አጎት ልጁን የአዕምሮ ህመምተኛ ያሉት በእነ አጅሬ አስገዳጅነት እንደሆን እጠርጥራልሁ።
ከዚህ በፊት የ የኔ ሰው ገብሬ ቤተሰቦች እንዲሁ አይነት መግልጫ እንዲሰጡ መገደዳቸውን ማስታውሻ የያዝን ሰዎች ነን።
(ዘግ ይቶ በደረሰን ጥርጣሬ ደግሞ እህቱም እህቱ ስለመሆኗ አጎቱም አጎቱ ስለመሆናቸውም እንጠረጥራለን!(ጠረጠሩ መባላችን ካልቀረ ደገሞ እንደ እህት እና አጎት ሆነው የሚጫወቱት አቶ ሬድዋን እና አቶ በረከት ሊሆኑም ይችላሉ))
በመጨረሻም፤
እደግመዋልሁ…
ሃይለመድህን አበራ የስዊዝ መንግስት ነፃ ሊለቀው ይገባል። ችግሩ ምንም ይሁን ምንም በርካታ ጥገኝነት መጠየቂያ አማራጮች እያሉት ይህንን እርምጃ የወሰደው የከፋ ነገር ቢደርስበት መሆኑ ግልጽ ነው። ስለዚህ ሁላችንም ከጎኑ ልንቆም ይገባል። ለኢትዮጵያ ተላልፎ ከተሰጠ ግን እንደተባለው አዕምሮው የታወከ እንኳ ቢሆን የሚለቁት አይመስልኝም! ሳስብው እኛ ይሄ ሁሉ ዘመን አዕምሯችን ታወኮ መቼ አውሮፕላን ጠለፍን… ብለው ቁም ስቅሉን የሚያሳዩት ይመስለኛል።