ታህሳስ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የአንድነት ፓርቲ ምክትል ሊ/መንበርና የህዝብ ግንኙነት ሐላፊ የሆነው አቶ አንዱዓለም አራጌ በጨለማ ቤት ውስጥ ታስሮ፣ ቀዝቃዛ መሬት ላይ እንዲተኛ መደረጉ በየጤናው ላይ ከፍተኛ ችግር እየፈጠረበት መሆኑን ትናንት ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ተናግሯል።
አቶ አንዱዓለም የመተንፈሻ ችግር እንዳለባቸው ይሁን እንጅ በጠባብ ክፍል 6 ሆነው በመታጎራቸው መታመማቸውንና ከባለቤታቸውና ጥቂት ቤተሰባቸው ውጪ ሌሎች ጓደኞቻቸውና የስራ ባልደረቦቻቸው እንዳይጠይቁዋቸው መደረጉን ተናግረዋል፡፡
የቀድሞው የፓርላማ አባል አቶ አንዷለም አያሌው በበኩላቸው ጠበቆቻቸው መጥተው ሊያናግሩዋቸው እንዳልተፈቀደለቻው ገልጸዋል።ዳኛው አቶ ዳኘ መላኩ ስርአቱን አልጠበክም በሚል የመናገር እድል ነፍገውታል፡፡ ዛሬ መንግስት ያቀረበለት ጠበቃ ቢቀርብም በጊዜ ቀጠሮ ለታህሳስ 28 ቀን 2005 ዓ.ም እንዲቀርብ ተነግሮታል፡፡
ጠበቃ ደርበው ተመስገን ይግባኙ እንኳን ሳይጠናቀቅ ከፍተኛው ፍርድ ቤት የተከሳሾችን ንብረት ለመውረስ በመጣደፍ ላይ ነው በማለት በቃል ሊያቀርቡ ቢፈልጉም ፍርድ ቤቱ በጽሑፍ ያቅርቡ ሲል አስቁሟቸዋል፡፡
ጠበቃ አበበ ጉታ በበኩላቸው ደንበኞቻችን በአንድ የክስ መዝገብ ቢከሰሱም ቃሊቲ እና ቂሊንጦ ተበትነው በመታሰራቸው ለጠበቆች ጥየቃ እንዳልተመቻቸውና በበቂ መጎብኘትና ማነጋገር አለመቻላቸውን ለፍርድ ቤት አሳውቀዋል፡፡
ፍርድ ቤቱ መዝገቡን ለውሳኔ ለጥር 10 ቀን 2005 ዓ.ም በጊዜ ቀጠሮ ያሻገረ ሲሆን ክርክሩ በጽሑፍ ተገልብጦ እንዲቀርብለት አዟል፡፡
በትናንት ዘገባችን የተከሳሾችን የመቃወሚያ ሀሳብ ማቅረባችን ይታወሳል።
No comments:
Post a Comment