Friday, November 30, 2012

ESAT Daliy News-Amsterdam Nov. 30 2012 Ethiopia


ኢትዮጵያ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ምርት እድገት አሳየች!


አቶ ሃይለማም ሲፈሩ ሲተቡ ቆይተው ዛሬ የካቢኔ ሹመት ለማደረግ ፓርላማ ብቅ ብለው ነበር አሉ። ይዘዋቸው ከመጡዋቸው ካቢኔዎቻቸው መካከል ሌላ ሁለት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮችን ይገኙበታል።
አቶ ሃይለማሪያም ሲያስቡት ሲያስቡት ለአቶ ደመቀ ብቻ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርነቱን መስጠት አይችሉትም ብለው ሰጉ መሰለኝ…(መሰለኝ ነው ያልኩት) ዛሬ አቶ ሙክታር ከድር እና አቶ ደብረ ፅዮን ገብረሚካኤልን ደጋፊ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አድርገው አሹመዋል። በጥቅሉ በአሁኑ ሰዓት ሀገራችን ሶስት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮች አሏተው።
እኛ  ሹመቱን ከላይ ከላይ የምናየው የመንግስታችን አድናቂዎች “እሰይ ሀገራችን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እድገት እመርታ አሳየች” ብለን ካገኘን ፅዋ ካጣን ደግሞ ግንባራችንን እያጋጨን ደስታችንን  እንገልፃናል።
የምር ግን አቶ ሃይለማሪያም ያኔ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ይሰሩ የነበረ ጊዜ እንደው ሰውየው መለስ ሆነውባቸው “ተሸከሙ” ያሏቸውን ሁሉ “እሺ ጌታዬ” ይሏቸው ነበር እንጂ፤ የጫኑባቸው ሸክም በእጅጉ ከብዷቸው ነበር ማለት ነው!? አዎና ይኸው አቶ ደመቀ ሸክሙን አይችሉትም ብለው የጠረጠሯቸው ከራሳቸው ልምድ ተነስተው አይመስልዎትም!?
ሌላው ጥርጣሬ የኢህአዴግ “ፈላጭ ቆራጮች” (ይሄ “ፈላጭ ቆራጭ” የሚለው ቃል ኢህአዴግ ይፈልጣል ይቆርጣል ብሎ ለማሽሟጠጥ ታስቦ የገባ ቃል አለመሆኑን በቅንፍ አሰውቀን እንቀጥል)  እና የኢህአዴግ ፈላጭ ቆራጮች አቶ ሃይለማሪያምን ለአንድ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ብቻ አምነው መተው ምቾት አልተሰማቸውም ይሆናል!
ለማንኛውም ዶክተር ቴውድሮስ አድሃኖምን ውጪ ጉዳይ ሚኒስትርነት ማዕረግ ተሰጥቷቸዋል። ዶክተሩ ከጤና ጥበቃ የተነሱት ጤና ስለነሱ ይሁን ወይስ የውጭ ጉዳዩ ስራ ህክምና ስለሚያስፈልገው አልታወቀም። ሲታወቅ እናወጋዋለን!

የደሴ ሙስሊሞች በፊድራል ፖሊስ ሲጨፍጨፉ


ESAT Daliy News-Amsterdam Nov. 30 2012 Ethiopia


Thursday, November 29, 2012

በጉዲፈቻ ወደ ዴንማርክ የመጣች ህጻን ለከፍተኛ የስነ አዕምሮ ችግር መዳረጎን ከዴንማርክ የደረሰን ዘገባ አመለከተ


ኢሳት ዜና:-የዛሬአራት አመት ከወላጅ እናቷና አባቷ ተረክበው ህጻኗን ከወንድሟ ጋር የወሰዳት የዴንማር ሰዎች ህጻኗ ለቤተሰቦቿ ያላትን ናፍቆት በየአጋጣሚው በመግለጽ እናቷ ጋር እየዲወስዷት በመጠየቅና ያልተለመደ በሀሪእያሳየች ደስታ በማጣቷ ለህጻናት ማሳደጊያ እንደሰጧት የኢሳት ምንጮች ከዴንማርክ ገልጣለች::
ከዴንማርክ የደረሰን ይሀው መረጃ እንደሚያመለክተው የህጻኗ ማእሾ ታሪክ በዴንማርክ ከፍተኛ መነጋገሪያ የሆነ ሲሆን ቤተሰቦቿን ያነጋገረና የህጻኗን ወደ ሀገር ቤት በመመለስ ጽኑ ፍላጎት ያሳየ ዶክመንተሪ ፊልም ተሰርቶ በቴሌቭዥን መሰራጨቱን ለምንጮቻችን ገልጻለች::
በህጻኗና በወላጆቿ ፍላጎት ወደ ሃገር ቤት መመለስ በሚለውና የለም መመለስ የለባትም በሚለው ላይ የዴንማርክ ህዝብ ድምጽ እንዲሰጥ ተደርጎ 67 ከመቶው ህጻኗ ወደ ሀገሯ ትመለስ በማለት ድምጽ መስጠቱን ምንጮች አረጋጠዋል::
17 ከመቶየአፍ መፍቺያ ቋንቋዋን ረስታለችና መመለስ የለባትም ሲሉ 20 ከመቶዎቹ ድምጽ ከመስጠት መቋጠባቸውንም ለማወቅተችሏል::
በህጻኗህይወት ታሪክ ዙሪያ ተሰርቷ በተሰራጨው ዶክመንተሪ ፊልም የህጻኗ ወላጆች ልጃቸው እንድትመልስ እያለቀሱ ሲለምኑ የሚታይ ሲሆን  የህጻኗ ጤናን ያሳባ የስነ አእምሮ ችግርም ህጻኗ እንዳጋጠማትም ፊልሙን የተመለከተው ምንጫችን ከዴንማር በስልክ ገልጻለች::
የደን ማርጥ ዜጋ አንድ ህፃን ወደ ሃገሩ ሲያመጣ ከ450 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ እንደሚከፍል የምንጮቻችን ዘገባ ያመለክታል::

አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ የተጠበቁ የስልጣን መሸጋሸጎችን አደረጉ


ኢሳት ዜና:-አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ዛሬ ይፋ ባደረጉት ሹመት 2 ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮችን እና ሁለት ሚኒስትሮችን ብቻ በመሾም አቶ መለስ የመሰረቱትን ካቢኔ ይዘው እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል።  አስቀድሞ እንደተጠበቀው የኦህዴዱ አቶ ሙክታር ከድር በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርነት ማእረግ የሲቪል ሰርቪስ ሚኒሰትር በመሆን የአቶ ጁነዲን ሳዶን ቦታ ተክተዋል። የህወሀቱ ዶ/ር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል ደግሞ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማእረግ የፋይናንስና ኢኮኖሚ ዘርፍ አስተባባሪ በመሆን ቀደም ብለው በያዙት የመገናኛ እና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ስልጣን  ላይ እንዲቆዩ ተደርጓል።
አዲስ ሹመት የተሰጠው ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ቦታ ሲሆን፣ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር የነበሩት አቶ ቴዎድሮስ አድሀኖም  የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በእርሳቸው ቦታ ደግሞ ዶ/ር ከሰተ ብርሀን አድማሱ የጤና  ጥበቃ ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል።
የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትሩ አቶ በረከት ስምኦን፣ የመከላከያ ሚኒስትሩ፣ አቶ ሲራጅ ፈርጌሳ፣ የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር ዶ/ር ሽፈራው ተክለማርያም፣ የፍትህ ሚኒስትሩ አቶ ብርሀነ ሀይሉ፣ የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ ሶፍያን አህመድ፣ የግብርና ሚኒስትር አቶ ተፈራ ደርበው፣ የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መኮንን ማንያዘዋል፣ የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር አቶ ደሴ ደለቀ፣ የትራንስፖርት ሚኒሰትሩ አቶ ድሪባ ኩማ፣ የኮሚኒኬሽን ሚኒሰትሩ አቶ ደብረጺዮን ገብረሚካኤል፣ የከተማ ልማት ሚኒስትሩ አቶ መኩሪያ ሀይሌ ፣ የውሀ እና ኢነርጂ ሚኒስትሩ አቶ አለማየሁ ተገኑ፣ የማእድን ሚኒስትሯ ወ/ሮ ስንቅነሽ እጅጉ፣ የትምህርት ሚኒሰትሩ አቶ ደመቀ መኮንን፣ የሰራተኛና ማህበራዊ ሚኒሰትሩ አቶ አብዱላጢፍ አብዱል አህመድ ፣ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሩ አቶ አማን አብዱልከድር፣ የሴቶች ፣ ልጆችና ወጣቶች ሚኒስትር ወ/ሮ ዘነቡ ታደሰ ባሉበት ስልጣን እንዲቀጥሉ ተደርጓል። አቶ መለስ ባባረሩዋቸው የንግድና እንዱስትሪ ሚኒስትር ቦታ አቶ ሀይለማርያም ሚኒሰትር ዲኤታ የነበሩትን የብአዴኑን አቶ ከበደ ጫኔን ሚኒስትር አድርገው ሾመዋል።
አቶ ሀይለማርያም ለካቢኔዎቹ አስተባባሪዎች ሁለት ጠቅላይ ሚኒሰትሮችን ከመሾም በስተቀር 98 በመቶ የሚሆነውን የአቶ መለስን ካቢኔ ሳይነኩ መቀጠሉን መርጠዋል። ኢሳት በሰሞኑ ዘገባው በአቶ ጁነዲን ቦታ አዲስ ሹመት ከመኖር በስተቀር መሰረታዊ የሚባል የካቢኔ ለውጥ እንደማይኖር ዘግቦ ነበር።
በዛሬው ሹመት ህወሃት የምክትል ጠ/ሚኒስትርነት እና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትርነት ቁልፍ ቦታዎችን አግኝቷል፡፡
ሹመቱ የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች በተለይም በኦህዴድ እና በህወሃት በተገቢው ሁኔታ አልተወከሉም የሚሉ ቅሬታዎችን
ለማርገብ የታሰበ ሳይሆን እንደማይቀር ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ ወ/ሮ አዜብ መስፍን በካቢኔው ውስጥ አለመካተታቸው አስገራሚ ሆኗል።
ሟቹ ጠ/ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ መስከረም 25 ቀን 2003 ኣ.ም በሰጡት ሹመት በመንግስት ሥልጣን ላይ
ለረዥም ጊዜ የቆዩትን ባለስልጣናት በመተካካት ስም ዞር ማድረግ ችለዋል፡፡ከነዚህ ባለስልጣናት መካከል ምክትል
ጠ/ሚኒስትር የነበሩት አቶ አዲሱ ለገሰ፣የአቅም ግንባታ ሚ/ር የነበሩት አቶ ተፈራ ዋልዋ፣የንግድና ኢንዱስትሪ
ሚ/ር አቶ ግርማ ብሩ፣የባህልና ቱሪዝም ሚ/ር አምባሳደር መሐመድ ድሪር፣የስራና ከተማ ልማት ሚ/ር የነበሩት
ዶ/ር ካሱ ኢላላ፣የውሃ ሃብት ሚ/ሩ አቶ አስፋው ዲንጋሞ፣የሴቶች ጉዳይ ሚ/ር ወ/ሮ ሙፍረሂት ከሚል፣የሰራተኛና
ማህበራዊ ጉዳይ ሚ/ር የነበሩት አቶ ሐሰን አብደላ የሚገኙበት እንደነበር ይታወሳል፡፡

የሁለት ምክትል ጠ/ሚኒስትሮች ሹመት ሕገ መንግስታዊ ድንጋጌን የጣሰ ነው ተባለ


ኢሳት ዜና:-በዛሬው ዕለት የኢትዮጵያ ፓርላማ የሰጠው ተጨማሪ የሁለት ምክትል ጠ/ሚኒስትሮች ሹመት ሕገመንግስታዊ ድንጋጌን
የጣሰ መሆኑን የሕግ ባለሙያዎች አስታወቁ፡፡
በሕገመንግስቱ አንቀጽ 75 ለአንድ ጠ/ሚኒስትር ብቻ ዕውቅና እንደሚሰጥ ያስታወሱት ባለሙያዎቹ በዚሁ አንቀጽ
75(1)ለ ላይ የተመለከተው ጠ/ሚኒስትሩ በማይኖርበት ጊዜ ምክትል ጠ/ሚኒስትሩ ተክቶት ይሰራል የሚለው ንኡስ አንቀጽ አንድ ምክትል ጠ/ሚኒስትር ብቻ  እንደሚኖር የሚያሳይ ነው ይላሉ፡፡በአሁኑ ወቅት ቀደም ሲል የተሾሙትን ጨምሮ ሶስት ምክትል ጠ/ሚኒስትሮች መሾማቸውን ባለሙያዎቹ አስታውሰው ይህ ሕገመንግስታዊ ድንጋጌን የጣሰ አካሄድ ነው ብለውታል፡፡
ጠ/ሚኒስትር ሀይለማርያም እንዲህ ዓይነት ሹመት ለመስጠት ከሕገመንግስቱ በተጨማሪ በአሁኑ ወቅት በስራ ላይ ያለው
የአስፈጻሚ አካላትን እንደገና ለማደራጀት የወጣው አዋጅ ቁጥር 691/2003 ያግዳቸዋል ብለዋል፡፡በዚህ አዋጅ
ክፍል ሁለት አንቀጽ 6 ላይ የሚኒስትሮች ም/ቤት አባላት በሚል የዘረዘራቸው ጠ/ሚኒስትሩን፣ምክትል /ጠ/ሚኒስትሩን፣የሚኒስትር መ/ቤቶችን የሚመሩ ሚኒስትሮች እና በጠ/ሚኒስትሩ የሚሰየሙ ሌሎች ባለስልጣኖች መሆናቸውን ደንግጓል፡፡
ይህው አስፈጻሚ አካላትን እንደገና ለማዋቀር የወጣው አዋጅ አንቀጽ 4 የምክትል ጠ/ሚኒስትሩ ሥልጣንና ተግባር
በሕገመንግስቱ በአንቀጽ 75 የተመለከተው እንደሚሆን በግልጽ አስቀምጧል፡፡
ባለሙያዎቹ ሹመቱ በተለይ ሕገመንግስቱን የጣሰ መሆን እንዳልነበረበት አስታውሰው በዚህ ሹመት መሰረት ጠ/ሚኒስትሩ
በማይኖሩ ጊዜ ማን ይተካቸዋል የሚለው ግልጽ የሆነ ምላሽ የለውም ሲሉ ተችተውታል፡፡
ጠ/ሚኒስትሩ የዚህን ዓይነት ሹመት መስጠት አይችሉም ያሉት ባለሙያዎቹ መስጠት ቢፈለግ እንኳን በቅድሚያ
ሕገመንግስታዊ ማሻሻያ መቅደም ነበረበት በማለት አካሄዱን ነቅፈዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ሹመቱ በዛሬው እለት እንዲሰጥ የተፈለገው በነገው እለት በኦሮሚያ ምክር ቤት ውስጥ ይነሳል ተብሎ የሚጠበቀውን ውዝግብ ከአሁኑ ለማብረድ መሆኑን ምንጮች ጠቁመዋል።
የኦህዴዱን አቶ ሙክታር ከድርን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር በማድረግ በኦሮሚያ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ነገ ይነሳል ተብሎ የሚጠበቀውን ውዝግብ ለማብረድ ታቅዶ በዛሬው እለት አዲሱ ሹመት ይፋ እንዲሆን መደረጉን የኢህአዴግ ኦህዴድ ምንጮች ገልጸዋል።
ዛሬ በሚጀመረው የኦሮሚያ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ፣ የምክር ቤት አባላቱ በአቶ ሀይለማርያም ሹመትና ኦህዴድ ከጨዋታ ውጭ  ሆኗል በሚለው ዙሪያ ከፍተኛ ውዝግብ ይነሳል ተብሎ ይጠበቃል። አዲሱ ሹመት በኦህዴድ ውስጥ ተፈጥሮ የነበረውን ውዝግብ ያርግበው አያርግበው የታወቀ ነገር የለም። ይሁን እንጅ አቶ ደመቀ ምክትል ጠቅላይ ሚኒሰትር ተብለው ከተሾሙ በሁዋላ ሌሎች ተጨማሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒሰትሮች እንዲሾሙ መደረጉ በአራቱ ድርጅቶች ውስጥ ያለውን ፍትጊያ የሚያመላክት መሆኑን ተንታኞች ይናገራሉ።

በአየር መንገድ ውስጥ በጉልበት ስራ ላይ ይሰሩ የነበሩ ከ500 በላይ ሰራተኞች በኢህዴግ ፎረም አባላት ከነገ ጀምሮ ሊተኩ ነው


ኢሳት ዜና:-ስማቸው እንዳይገለጥ የፈለጉ የአየር መንገድ ሰራተኞች ለኢሳት እንደገለጡት ከነገ ጀምሮ ከ500 እስከ 700 መቶ የሚጠጉ የጉልበት ሰራተኞች ስራቸውን ይለቃሉ። በተለያዩ ቀታሪ ኤጀንሲዎች ውስጥ ከ4 አመታት ላለነሰ ጊዜ በጉልበት ስራ ላይ ተሰማርተው የነበሩ ሰራተኞች የሚባረሩት የኢህአዴግ ፎረም አባላት አይደላችሁም ተብለው ነው። ሰራተኞች እንደገለጡት በፎረም ተጠናክረው ሲመጡ ተመልሰው ሊቀጠሩ እንደሚችሉ ቃል ተገብቶላቸዋል። በሚባረሩት ወጣቶች ቦታ በስልጠና ላይ አሉ በሺ የሚቆጠሩ የወጣት ፎረም አባላት ከነገ ጀምሮ ስራ ይጀምራሉ።
ኢህአዴግ በወሰደው እርምጃ ያዘኑ ሰራተኞች እንደገለጡት፣ የኢህአዴግ ፎረም አባላት አይደላችሁም በሚል ከስራ መባረራቸው ህገመንግስቱን የሚጥስ ብቻ ሳይሆን ሳንወድ በግድ ለእንጀራ ብለን ኢህአዴግን እንድንደግፍ የሚያደርግ ነው።
ኢህአዴግ በቀጣዩ የወረዳና የከተማ ምርጫ አሸናፊ ሆኖ ለመውጣት ያስችለው ዘንድ የወጣት ፎረም አባላትን በጊዜያዊ ስራ እየሸነገለ ነው በማለት ተቃዋሚዎች በተደጋጋሚ ወቀሳ ያቀርባሉ።
በተያያዘ ዜናም ኢህአዴግ አንዳንድ አባላቱን ከድርጅት አባልነት ያስወጣ በማስመሰል በወረዳዎች ውስጥ በሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች አስመራጮች አድርጎ ሊያሾም መሆኑን ከድርጅቱ የተገኘው መረጃ አመልክቷል።
በይፋ የማይታወቁ የድርጅቱ አባላት በገለልተኛ ስም በምርጫ አስፈጻሚነት ለማወዳደርና ለማሰራት መታቀዱን ነው ለማወቅ የተቻለው።

ethiopians chilldren adoption ! Gudifecha


ESAT DC Daily News November 28 2012


Monday, November 26, 2012

ESAT Tikuret Ethiopia London Ato Mohamed 23 November 2012


ኢሳትን አያችሁ የተባሉ ወታደሮች ታሰሩ፤ ሠራዊቱ ዉስጥ የተፈጠረዉ መከፋፋል አሁንም እንደቀጠለ ነዉ


[ግንቦት 7 ዜና] ሰሜን ኢትዮጵያ ዉስጥ በባድሜ ግንባር ወታደራዊ ክበባቸዉ ዉስጥ ቁጭ ብለዉ በናይልሳት የሚተላለፈዉን የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥንን ሲከታተሉ የተገኙ በርካታ ወታደሮች ለሁለት ሳምንታት ታስረዉ በከባድ ማስጠንቀቂያ መለቀቃቸዉን ትግራይ ዉስጥ የሚገኙ ወታደራዊ ምንጮቹን በመጥቀስ የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ኢሳት ዘገበ። አንድ ስማቸዉና ማዕረጋቸዉ እንዳይጠቀስ የጠየቁ ከፍተኛ መኮንን በስልክ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ እንደገለጹት ወታደሮቹ የታሰሩት በክበባቸው ውስጥ ቁጭ ብለዉ የኢሳትን ዝግጅት ሲከታተሉ ሲሆን ከ 14 ቀናት እስርና እንግልት በኋላ የተፈቱት የዲሻቸውን አቅጣጫ ወደ ናይል ሳይት ያዞሩት ሳያዉቁ በስህተት መሆኑን ለበላይ አለቆቻቸው ተናግረዉ ዳግመኛ ኢሳትን እንደማይመለከቱ ቃል ከገቡ በኋላ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከዚያዉ ከባድሜ ግንባር አንድ ሌላ ከፍተኛ የጦር መኮንን ለኢሳት በሰጡት መረጃ መሠረት በመከላከያ ሠራዊቱ ዉስጥ ከፍተኛ የሞራል ዉድቀት የሚታይ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ በሠራዊቱ ዉስጥ ይህ ነዉ የማይባል የኤኮኖሚ ችግር፤ ሰር የሰደደ የዘር ልዩነትና ከፍተኛ የአስተዳደር በደል በየቦታዉ ተንሰራፍቶ ይታያል ብለዋል። መኮንኑ ንግግራቸዉን በመቀጠል አብዛኛው የኢትዮጵያ ወታደር የመከላከያ ሠራዊቱን የሚቀላቀለዉ በኢኮኖሚ ችግር ምክንያት ቢሆንም የሰራዊቱ አባላት በአገሪቱ ከሚታየዉ የኤኮኖሚ ችግር ማምለጥ አልቻሉም ብለዋል። እንደ መኮንኑ አበባል ከኮሎኔልነት በታች ማዕረግ ያላቸው መኮንኖች ገቢያቸዉ ከተራው ወታደር ብዙም እንደማይለይና ተደማጭነትም እንደሌላቸው ለማወቅ ተችሏል።

በወያኔ ሠራዊት ዉስጥ ኮሎኔልና ከኮሎኔል በላይ ሹመት ካላቸዉ መኮንኖች ዉስጥ ከ95 በመቶ በላይ የሚሆኑት የህወሀት አባል የሆኑ የትግራይ ተወላጆች ሲሆኑ የእነዚህ መኮንኖች ኑሮ ከበታቾቻቸው ጋር ሲነጻጻር ሰማይና ምድር መሆኑን ተራው ወታደር ጭምር የሚያዉቀዉ ጉዳይ ነዉ።በኢትዮጵያ ዋና ዋና ከተሞች ዉስጥ ህንፃና ዘመናዊ ቤቶችን ሰርተው የሚያከራዩት አነዚሁ የህወሀት መኮንኖች ናቸዉ።ለምሳሌ አዲስ አበባ ዉስጥ በወረዳ 17፣ በቦሌ መድሀኒአለም አካባቢ ጄኔራል ወዲ አሸብር የ55 ሚሊዮን ብር ህንፃ ያሰራ ሲሆን  ኮሎኔል ታደሰና ጄነራል ዮሀንስ የሚባሉ የህወሀት መኮንኖቸች ደግሞ የ12 ሚሊዮንና የ45 ሚሊዮን ብር ህንፃ አሰርተዉ በማከራየት ላይ ናቸዉ።

ESAT Kignit Sewyew Drama November 2012 Ethiopia


ESAT Daliy News-Amsterdam Nov 26 2012 Ethiopia


Sunday, November 25, 2012

አጫጭር የሀገር ቤት ወሬዎች (ከአዲስ አባባ) ቁጥር 2


ይነጋል በላቸው
ከአዲስ አባባ
ባለፈው የዜና ዕወጃችን ይህን መሰል የሀገር ውስጥ አጫጭር ወሬዎች ዘገባ ቢያንስ በሣምንት አንድ ጊዜ እናቀርባለን ብለን ቃል ባልገባነው መሠረት ከመጀመሪያው የቀጠለውን የዛሬውንAddis Ababa is the capital city of Ethiopia. ዝግጅት ቀጥለን የምናቀርበው በታላቅ  የደስታ ስሜት ነው፡፡ እነዚህ ወሬዎች በምናባዊ የአቀራረብ ፋሽን በመዋዛታቸው የአንዳንዶችን አመኔታ በቀላሉ ላያገኙ እንደሚችሉ ቢጠረጠርም ሀሰት እንዳልሆኑ ግን ለተከታታዮቻችን በዚህ አጋጣሚ ልናስታውስ እንወዳለን፡፡ የዜና ማዕከሉ ውሸትን በመዘገብ የሚያገኘው ቅንጣት ትርፍ አለመኖሩን በሚገባ ስለሚገነዘብ ጥቂቶቹን የሥነ ጽሑፍ አላባውያንና ነገር ማስዋቢያ ግብኣቶችን(literary flavors) ከመጠቀም ውጪ ያልተሰማና ያልተደረገ ወይም ከነአካቴው ‹ይህን ዓይነቱ ነገር ሊደረግ አይችልም!› ተብሎ የሚገመትን ክስተት በዜና ፋይል ውስጥ እንደማያካትት በትህትና ያስታውቃል፡፡ ሃሳብን በተፈለገው መንገድ ማቅረብ ይቻላል፤ ማንበብና ማስነበብ ደግሞ የአስነባቢዎችና የአንባቢዎች ድርሻ ነው፡፡ መንገደኞች ይለያያሉ – ተፈጥሯዊ ነው፡፡ የመንገዱ መለያየት ግን የግድ ያህል አይደለም፡፡ መቃወም ጥሩ ነው፤ መቃወምን የባሕርይ ያህል መላበስ ግን ተፈጥሯዊ አይደለም፡፡
የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ሠራተኞች በሥራቸው መሰላቸታቸው ተገለጠ
በአንዳንድ ነገር ጎንጓኞች ‹የስዬ ኮሚሽን› በመባል የሚታወቀው የፀረ-ሙስና ኮሚሽን አንዳንድ ሠራተኞች በመሥሪያ ቤታቸው የአሠራር ወጥነት መጥፋት የተነሣ ክፉኛ እየተበሳጩና እየተናደዱ መሥሪያ ቤታቸውንም ጥለው በመውጣት ወደሌላ ኅሊናን የማይፈታተን ሥራ ለመግባት እያሰቡ እንደሆነ ከሥፍራው የደረሰን ጥቆማ ይፋ አድርጓል፡፡ ዝርዝሩ እንደሚከተለው ይቀርባል፡፡
“እኔ ከተቀጠርኩ ይሄውና አሥር ዓመት አለፈኝ፤ ነገር ግን የሠራሁት ሀገርንና ሕዝብን ሊጠቅም የሚችል ተጨባጭ ነገር የለም፡፡ በሙስና የተጠረጠረን ሰው ልንመረምር እንላካለን፤ በአዲስ አበባም ከአዲስ አበባም ውጪ፡፡ ነገር ግን ምርመራው ተጣርቶ ተጠቋሚው ግለሰብ አንዳች እንከን ሲገኝበት ባላሰብነው ወቅት ከበላይ አካል በሥልክ ለአለቃችን ይነገርና ‹ያን የእገሌን(የነእገሌን) ጉዳይ ተውት፤ ፋይሉ ይዘጋ› እንባልና ልፋታችን ሁሉ ዜሮ ይሆናል፤ ፋይሉም ተዘግቶ ሰውዬው በጀመረው የሙስና መስመር መንጎዱን ይቀጥላል፡፡ ሕግ የማይገዛቸው ብዙ ምርጥና ዕንቁ ዜጎች አሉ፤ ሀገሪቷን እንዳለ ቢሸጧት ዝምባቸውን እሽ የሚል የመንግሥት አካል የለም፤ ዘበናዮች ናቸው፡፡ እንዲህ እንዳፈለገው የሚሆን ሰው ግን በዘርም በዓላማም የነሱው ሰው ከሆነ ወይም በፖለቲካ የማይፈለግ ከሆነ ወይም በልዩ ልዩ ነገሮች ደጋፊያቸውና የሥርዓታቸው ታማኝ ከሆነ ነው፡፡ መሥሪያ ቤቱ የራሱ አቋምና የአሠራር ነጻነት ብሎ ነገርም የለውም፡፡ የወያኔው ቱባ ባለሥልጣናት የሚፈልጉትን ሰው ሀብት ለመቀማትና ሙልጭ ድሃ ለማድረግ ወይም ዘብጥያ ለማውረድ የሚጠቀሙበት እንደግል አሽከራቸው በሥልክ ወይ በቁራጭ ወረቀት ‹የእከሌን ነገር ባፋጣኝ አሳዩን› ሲባል ብቻ የነሱን የበቀል ጥማት ለማስታገስ የቆመ መሥሪያ ቤት ነው፤ የሚያሳዝነው የሕዝብ ከፍተኛ ሀብትና ሁለንተናዊ ፈሰስ ለዚህ ምንም ዕርባና ለሌለው መሥሪያ ቤት እየተመደበ በከንቱ መባከኑ ነው፡፡ ስሜ በዚህ መሥሪያ ቤት የሠራተኞች ዝርዝር ውስጥ ተካትቶ መገኘቱ በውነቱ በጣም ያሳፍረኛል፤ያንገበግበኛልም፡፡ እርግጥ ነው ደመወዙ ከሌሎች የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ስለሚሻል ለቅቆ መሄዱ በተለይ የተሻለ ሥራ ባልተገኘበት ሁኔታ ቤተሰብን ለኑሮ ችግር መዳረግ ነው፡፡ እንጂ እንደአሠራሩ አንድ ቀንም የሚውሉበት አይደለም፤ የብዙው ሠራተኛ ልብቡ እንደሸፈተ መረዳት አይከብድም፤ መድረሻ በማጣት እንጂ፡፡” በማለት ለዘጋቢያችን ያብራራው ስሙ እንዳይገለጥበት በ44ቱ ታቦት የተማጠነ የኮሚሽኑ አንድ ሠራተኛ በመቀጠልም ይህ መሥሪያ ቤት እንደሌሎች የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ሁሉ ከከፍተኛ እስከዝቅተኛ የኃላፊነትና የሥራ ቦታዎች ላይ የተመደቡትና የሚመደቡት ሠራተኞች በትምህርትና በልምድ ሳይሆን በታማኝነታቸውና የገዢው መደብ የዘር ሐረግ ያላቸው በመሆናቸው በልዩ ትዕዛዝ የሚላኩ ዜጎች መሆናቸውን፣ ከጠቅላላው የሠራተኞች ቁጥር ሌሎቹ ብሔር/ብሔረሰቦች 20 በመቶ ገደማ ቢሆኑ እንጂ የተቀረው ሙሉ በሙሉ ወይም አንድ ሁለተኛው ወይም ሦስት አራተኛው ወይም ቢያንስ አንድ ስምንተኛው በጥናት የተረጋገጠ የአንደኛ ደረጃ ዜግነት ካለው የገዢ መደብ መሆኑን ለዘጋቢያችን የእምነት ክህደት ቃሉን የሰጠው ይህ ሠራተኛ ገልጧል፡፡ ወጣቱ የቢሮ ኃላፊ ሲያጠቃልልም “ እኔ በውነቱ ይህ መሥሪያ ቤት እጅ እጅ ብሎኛል፤ልቀቅ ልቀቅ ብሎኛል፡፡ ወደዚህ የመጣሁት ባለችኝ ትንሽ የደም መጠጋጋት ቢሆንም በትግሬነቴ የሚመጣ ጥቅም ጥንቅር ብሎ ይቅር፤ ወያኔዎች ስልችት ብለውኛል፤ መድረሻ ማጣት እንጂ የነሱ ቀረቤታ በጭራሽ አያስፈልግም፡፡ የማየው የዘረኝት በሽታም አንገሽግሾኛል፡፡ ‹ዓለማቀፉን ማኅበረሰብ› ለማታለልና ስዬ አብርሃን መሰል ተቃዋሚዎችን ለማሰር በአንድ ቀን በመለስ ተጠፍጥፎ በአንድ ቀን አዳር ፀድቆ በአንድ ቀን አዳር በተመሠረተ የውሸት ኮሚሽን ለእንጀራ ስል ብቻ ‹መሥራቱ› ቋቅ እስኪለኝ አስጠልቶኛል፡፡ ለተግባራዊ ክንውን ሳይሆን ለማስመሰያነት ለተቋቋመ መሥሪያ ቤት ይህን ያህል በጀትና የሰው ኃይል መባከኑ፣ ይህን ያህል ሰፊ ቢሮ ለቲያትርና ለቧታይ ድንቃይ ድራማ ሲባል ካለጥቅም ለገሀር እምብርት ላይ መጎለቱ በእጅጉ ያሳዝነኛል፡፡ ስለዚህ ጡረታ ለመውጣት የቀረችኝ ጊዜ አንድ ሃያ ዓመት ብቻ ስለሆነች ያቺ ስታልቅልኝ ጡረታ ወጥቼ የግል ሥራየን እሠራለሁ፡፡” በማለት በከፍተኛ መንገፍገፍ ብሶቱን ገልጧል፡፡ ምኞቱ እንዲሠምር የዝግጅት ክፍላችን ይመኛል፡፡
በሌላ ዜና የዚህን መረጃ ትክክለኝነት ለማረጋገጥ ዋና ኮሚሽነሯን እንወይ ገ/መድኅንን በሥልክ አግኝተን ለማነጋገር ያደረግነው ጥረት ሴትዮዋ ከለቀቀች ብዙ ዓመታትን በማስቆጠሯ ምክንያት ሊሳካልን አልቻለም፡፡ የአሁኑ ኮሚሽነር ግን ‹እኔ ለማላዝበት መ/ቤት ምን አዳረቀኝ?እኔ ምን ቤት ነኝና?› በሚል ደመወዝና አበል ለመቀበል  ብቻ በወር አንዴ ወይ ሁለቴ ወደመ/ቤት እንደሚመጡና እንደማይመጡ ከውስጥ ዐዋቂ ምንጮች ለማጣራት ያደረግነው ጥረት አሁንም አልተሳካም፡፡
ፍርሀትና ትግስት ውሕደት መፍጠራቸው ተነገረ
እስከቅርብ ዓመታት ድረስ በኢትዮጵያ ውስጥ በተናጠል በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ይታወቁ የነበሩት አቶ ፍርሀትና ወይዘሮ ትግስት በመካከላቸው ነበረ የተባለው የልዩነት ክፍተት ከጊዜ ወደጊዜ እየጠበበ መጥቶ አንዳቸውን ከሌላኛቸው ለመለየት የማይቻልበት ወቅት ላይ በመደረሱ በአቶ መኖር በዘዴ አደራዳሪነት በቅርቡ ውሕደት መፍጠራቸውንና ከዚያም ባለፈ በትዳር ተቆራኝተው ልጆችን ለማፍራት ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ወገኖች ለንጋት የዜና ወኪል ሰሞኑን አስታወቁ፡፡ ትዳራቸው ሠምሮ ልጆችን ማፍራት ቢችሉ ለልጆቻቸው ምን ዓይነት ስሞችን ለመስጠት እንደሚፈልጉ የተጠየቁት አቶ ፍርሀትና ወይዘሮ ትግስት ሲመልሱ “በቅድሚያ ስለተሰጠን ዕድል ልናመሰገን እንወዳለን፡፡ በመሠረቱ እኛ በተፈጥሯችን እንኳንስ ለጋብቻና ለዘር ሐረግ ጥምረት ይቅርና ለጉርብትናም ልንበቃ የማንችል በጣም የተለያየን ፍጡራን ነበርን፡፡ ነገር ግን ዕድሜ ለትውልድ ሞራልና ሃይማኖት መላሸቅ ይሄውና በየፊናችን ተከብረንና ተፈርተን እንዳልኖርን ሁሉ ዛሬ አዳሜ እየተነሣ ‹ታግሼህ እንጂ ፈርቼህ እንዳይመስልህ! ‹ትግስት መራራ ብትሆንም ፍሬዋ ጣፋጭ ነው›፣ ቆይ ብቻ! አሳይሃለሁ!› እያለ በውስጡ ግን በፍርሀት እየራደ ለመኖር ሲል ብቻ የዛሬ እስትንፋሱን ለነገ ለማሳደር ሲዋረድ፣ በገዛ ቀዬው በሕዝብ ፊት ሳይቀር ቆለጡን በገመድ እየተጎተተ አውሮፓና አሜሪካ ላይ ያለ ይመስል የምሽቱን እንትን በአደባባይ እንትን እንዲል ሲገደድ፣ በስማም እንደተባለበት ሰይጣን በፍርሀት ቸነፈር የእኖርባይነት ጋግርት እጁና አንደበቱ ተለጉሞ በቁም ለሞተበት የመከራ ሕይወት ቀጣይነት ሲል የላም አለኝ በሰማይን የነገ ውሎ ለማየት ሲጓጓ፣ ወዘናው ተንጠፍጥፎ ሁሉም ነገር ያለቀበት ዛሬ ለሚያከናንበው ውርደት አንገቱን ደፍቶ  ሲልመጠመጥ ስታየው …› በማለት ወዳልተጠየቁት ጥያቄ መልስ ውስጥ ሲገቡ ያቋረጣቸው ዘጋቢያችን እንደገለጸው ከሆነ ሁለቱ ለሚወልዷቸው ልጆች ከሚሰጧቸው ስሞች መካከል ‹ጉድሠራኝ፣ አቀለለኝ፣ አዋረደኝ፣ባዶአስቀረኝ፣› እና ‹ባገርናኘ› ጥቂቶቹ መሆናቸውን እንደገለጹለት አስታውቋ፡፡ አቶ ፍርሀት አክለውም ‹ከእንግዲህ ሰውም ጉድ ይበል፤ ዓለምም ሲፈልግ ተወቅሮ ይሳቅ፤ በኢትዮጵያ ምድር ፍርሀትና ትግስት ተጋብተዋል፤ አንድ ሆነዋል፤ ለዚህ ደረጃ ያበቁንን ደርግንና ወያኔን ደግሞ ከልብ እናመሰግናለን፡፡ ደርግ በጠራራ ጠሐይ ትውልድን በመትረየስ እየጨፈጨፈ በሕዝቡ ውስጥ ፍርሀትን አነገሠ፣ የትዕግሥትንም ዋጋ አኮሰሰ፡፡ በዚያም ሳቢያ በሁለታችን መካከል የነበረው ልዩነት ሲጠፋ  ተቀላለቅልን፡፡ በኛ ማን ሊፈርድ ይችላል?› በማለት ሁለት የማይገናኙ ነገሮች እንዴት ሊገናኙ እንደቻሉ ገልጸዋል፡፡
የአዲስ አበባ መንገዶች መጨናነቅ ችግር ማስከተሉ ይፋ ሆነ
አዲስ አበባ ከየት መጡ በማይባሉ ዘመናዊ መኪኖችና ተሸከርካሪዎች እየተሞላችና ለእግረኞች መሄጃ መንገድ እየጠፋ መምጣቱ ታወቀ፡፡ በኑሮ ውድነቱ ሳቢያ አብዛኛው ሕዝብ ይልሰውንና ይቀምሰውን አጥቶ በርሀብና በችግር እየተንጠራወዘ በሚገኝበት በዚህ ዘመን በአውሮፓ እንኳን በብዛት የማይታዩ ሀመርንና ራቭ6ን የመሳሰሉ ዘመናዊ አውቶሞቢሎች እንዴት በአዲስ አበባ አውራ ጎዳናዎች ሊርመሰመሱ ቻሉ የሚለው ጥያቄ ሃሳብ የሆነባቸው አስተዋይ ዜጎች እንደሚሉት ወያኔን የተጠጉ መዝባሪና ሙሰኛ ዜጎች እየተበራከቱ በመምጣታቸው በሀገር ሲወረር አብረህ ውረር ፈሊጥ በለየለት ዘረፋ ወስጥ ተሠማርተው የሚገኙ ብዙዎች ዜጎች መኖራቸውን ጠቁመዋል፡፡ ‹ደመወዙ በጣም አነስተኛ ከመሆኑ የተነሣ የቤተሰቡን ነፍስ ቢያውል እንደማያሳድር የሚታወቅ ሰው ሽንጣም አውቶሞቢል ይዞ ብታየው ኢትዮጵያ ውስጥ ስላለህ ሊገርምህ አይገባም› በማለት የሙሰኛ ባለሥልጣናትንና ሠራተኞችን እንዲሁም ከቀረጥ ነጻ ዕቃዎችን ወደሀገር በማስገባት በአንድ ቀን አዳር የሚከብሩ ባለጊዜዎችን ገመና ያጋለጠው አንድ ስሙ እንዳይገለጥ የተማጠነ ታዛቢ ‹ ይህች ሀገር የዕንቆቅልሽ ሀገር ናት፡፡ ሰው እንዴት እንደሚኖር አታውቅም፡፡ የሁሉም ነገር ዋጋ ተሰቅሏል፡፡ ጥሩ ደመወዝ የሚያገኙ ሰዎች ራሳቸው ከሥጋና ከወተት እንዲሁም ከአትክልትና ፍራፍሬ ተፋትተው አንጀታቸው በሽሮና በበቆልት ምግብ እየተቆዘረ ባለበት ሁኔታ ጥቂት የማይባሉ የሀገሪቱ ምርጥ ዜጎች የሀገሪቱን ሀብት ለብቻ ተቆጣጥረው እንዲህ የተቀማጠለ ኑሮ መኖራቸው መጨረሻው የማያምር ከመሆኑም በተጨማሪ – ከምላሴ ፀጉር ይነቀል – የከፋ ቀን ሲመጣ ከፍተኛ መተላለቅን የሚያስከትል ይሆናል፡፡ መኪናው ግድ የለም፤ ይንዱ፡፡ ይፏሉበት፡፡ ነገር ግን ለተራው ዜጋ ቢያንስ በቀን አንዴ ቀምሶ እንዲያድር ሊፈቅዱለት በተገባ ነበር፡፡ባለሥልጣኑና ነጋዴው እየተመሣጠረ ሀገሪቱን ለራሱ ምድረ ገነት ሲያደርጋት ለአብዛኛው ሕዝብ ግን ከሲዖልም የባሰች ዘግናኛ ሲዖል አደረጋት፡፡ ግዴለም፤ የበደል ቋቱ ሲሞላና እግዚአብሔር የቁጣ ጅራፉን ሲያነሳ በሠፈሩት ቁና መሠፈራቸው አይቀርም፡፡እነሱ እያሉ ስደቱም ሆነ ስቃዩ አይቆምም፡፡ የጀመራቸው እሳት አቃጥሎና ለብልቦ እስኪፈጃቸው ድረስ ለጥቂት ጊዜ እንቸገራለን እንጂ እንዲህ ላያችን ላይ እንደተጎመሩብን የሚቀሩ እንዳይመስላቸው፡፡› በማለት በቁጭት ተናግሯል፡፡
በተያያዘ ዜና በአዲስ አበባ ብዙ ሥፍራዎች መንገዶች እየታደሱ ወይም እየተስፋፉ በመሆናቸው በሰዓት ወደ ሥራ መግባትና ከሥራ ወጥቶም በጊዜ ወደቤት መግባት አስቸጋሪ እየሆነ መምጣቱ ታውቋል፡፡ እንዲያውም በአሁኑ ወቅት በትራፊክ እንቅስቃሴ መጨናነቅ የተነሣ በመኪና ከመሄድ ይልቅ በእግር መሄድ እንደሚሻል ጓደኛው ሊፍት ሊሰጠው መኪና አቁሞለት ሲያበቃ እንዲሣፈር ግባ ሲለው ‹አይ፣ ሂድ ግዴለም፤ እቸኩላለሁ› በማለት አስቆ ግብዣውን ያልተቀበለውን አንድ ሠራተኛ  በመጥቀስ ለዚህ ዘጋቢ የገለጸ አንድ ታዛቢ አስታውቋል፡፡ ይህ የመንገዶች መጨናነቅ እንደወትሮው በሥራ መግቢያና መውጫ ብቻ የተወሰነ ሳይሆን እሁድንና ቅዳሜን የበዓላት ቀናትንም ጨምሮ ሁልጊዜ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ቀን እንደጅብ እየተኙ ወይም ቅጠላ ቅጠል እያመነዠኩ የሚውሉ ገንዘብ በመተት መሰል ነገር የሚያገኙ የሚመስሉ ዜጎች  ለጭፈራና ለቢስነስ ሥራ ሌሊቱንም በመኪኖቻቸው ሲዘዋወሩ ስለሚያድሩ የሌሊቱም መጨናነቅ በተለይ በካዛንቺስና በዑራኤል አካባቢዎች ከቀኑ ብዙም እንደማይለይ አንዲት ለጉዳዩ ቅርበት ያላት ኮረዳ አስታውቃለች፡፡
የመኪና መንገድ ሥራን በተመለከተም አንድ የአውራ ጎዳና ሠራተኛ እንደገለጡት ‹መንግሥት የመንገድ ሥራዎችን ለቻይኖቹና ለግል ተቋራጮች እንደመሥጠት ለዳተኛው የመንግሥት አውራ ጎዳና ባለሥልጣን እየሰጠ አንድ ኪሎ ሜትር ሠርቶ ለማጠናቀቅ ከሁለት ዓመት በላይ እየፈጀ ያለበት ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡ ለምሳሌ ከላምበረት መገናኛ አደባባዩ ድረስ ያለው የሦስት ኪሎ ሜትር አስፋልት መንገድ ሥራ ይሄውና በሁለተኛ ዓመቱ እንኳ ገና ከቁፈራ አልወጣም፡፡ የግሎቹ ቢይዙት ኖሮ እስካሁን አልቆ ነበር፡፡ በጀት ለማስያዝ ሲሆን ቀና ደፋ ይላሉ፤ ከፀደቀ በኋላ ሥራው ምንም አይሠራም፡፡ የሀገር ፍቅርና የሥራ ፍቅር ጠፍቷል፡፡ ብዙዎቹ የሥራ ኃላፊዎች ዘመዳቸው ሙስናና ገንዘብ ብቻ ነው፡፡ ተራው ሠራተኛም ተገትሮ ነው የምታየው፡፡ ተግቶ እንዲሠራ ንቁ ኃላፊና ጥሩ ክፍያ የለውም፡፡ ስለዚህ በምንቸገረኝነት አካፋውን ተደግፎ ከጧት እስከማታ በወሬ ተጠምዶ ታየዋለህ፡፡ ዛሬ ዛሬ ሥራ በግል እንጅ በመንግሥት ቤት ቀርቷል ወይም ተዳክሟል ማለት ይቻላል፡፡ ማን ማንን ይቆጣጠራል? አለቃና ምንዝር ሁሉም ተፈራርቶ ዝም ብሎ ነው እንደበግ እየተጋፋ የሚኖር፡፡
የሀገሪቱ የአሁንና መፃዒ ዕድል በአሳዛኝ ሁኔታ ላይ ይገኛል፡፡ የኔ የሚላት ዜጋ ባለመኖሩ በየመስኩ ሥራ እየተበደለ፣ የምንቸገረኝነት መንፈስም ዜጎችን እየበከለ ሀገሪቱ አደገኛ ሁኔታ ላይ ትገኛለች፡፡ በዚያ ላይ ወያኔ ሊያዛምተው የሞከረው የዘረኝነት ልክፍት ብዙውን ዜጋ እየተፈታተነው መጥቶ አንጎሉን በወንዘኝነት ልምሻ እየበከለው ይገኛል፡፡ መሬትን በዘርና በአጥንት የመከፋፈል አባዜም እየተንሰራፋ ሄዶ መኪናና ሕንፃ ሳይቀሩ በዘርና በጎሣ ታፔላ እየወጣላቸው ሁሉ ነገር የተመሰቃቀለበት ጊዜ ላይ ደርሰናል – ትግሬ ስካይባስ፣ አማራ ሚኒባስ፣ ኦሮሞ ስካኒያ፣ ደቡብ ሕዝቦች አይሱዚ…ይባልልሃል – ዱዳዎቹ ተንቀሳቃሾችና ግዑዛኑ ዕቃዎች አለዘራቸው አማራ ኦሮሞ እየተባሉ እነሱም ዘረኛ እንዲሆኑ እየተደረገ ነው፡፡ በዚህ ብቻም ሳይበቃ ለአንድ ቦታ ሁለትና ሦስት ስም በመስጠት ባቢሎንን መልሰው በኢትዮጵያ ላይ ነፍስ ዘርተውበታል፡፡ የጉልቻ መለዋወጥ ወጥን እንደማያጣፍጥ ሁሉ በስም መለዋወጥ የሚመጣ ከሥነ ልቦና የዘለለ ጉልህ ምጣኔ ሀብታዊና ቁሣዊ ጥቅም እንደማይኖር መገንዘብ አቅቷው ሕዝቡን ያወናብዱት ይዘዋል፤ ስም ደግሞ መጠሪያ እንጂ ይህን ያህል አቅልን ሊስቱለት የሚገባ ነገር  አይደለም፡፡ እስኪ እንዲያው ለመሆኑ ግን – እግዜር ያሳያችሁ – ንብረት እንዴት በዘር ሐረግ ይጠራል? ለነገሩ ሁሉም በየዘር ቋጠሮው – በየከረጪቱ ሲከት ሀገሪቱ የኔ የሚላት አጥታ መለመላዋን እንድትቀርና ጠላቶቿም የዘመናት ዕቅዳቸው ባሰየጠኗቸው የገዛ ልጆቿ አማካይነት እንዲሣካላቸው  በመታቀዱ ነው፡፡  በዚህም ተባለ በዚያ ባጭሩ ሀገሪቱ ባለቤት አጥታለች፡፡ የሰው ያለህ እያለች ነው፡፡› በማለት አሳዛኙን የሀገር ገጽታ አስረድተዋል፡፡
የአምልኮ ሥፍራዎች ለድምፅ ብክለት ተጠያቂ ናቸው ተባለ
አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የኦርዶክስ እምነት ተከታይ እንደገለጡት ‹ ማንኛቸውም የአምልኮ ሥፍራዎች ይሄን በተለይ ሌሊት ሌሊት የሚከፍቱትን የድምጽ ማጉያ ቢተውት ይሻል ነበር፡፡ ታሞ የሚተኛ አለ፤ በአካባቢው ሐኪም ቤት ሊኖር ይችላል፤ አዳሪ ትምህርት ቤት ይኖራል፤ ቀኑንና ምሽቱን በሥራ ሲደክም ቆይቶ ቤቱ ገብቶ ማረፍ የሚፈልግ ሰው አለ፤ ከነአካቴውም ሃይማኖት የሌለው ነገር ግን በሰላም ተኝቶ የማደር መብቱ ሊነፈገው የማይገባ ዜጋ አለ፤… ስለዚህ በቀን እንደፈለጉ ቢያደርጉም በሌሊት ግን በእልህ በሚመስል ሁኔታ ወደውጭ የሚለቁትን ከፍተኛ የድምጽ ሞገድ ማቆም አለባቸው፡፡ የሃይማኖት ተቋማቱ የአመራር አካላትም ይህን ችግር በቀናነት ተረድተው አንዳችም ሕግና መመሪያ ሳይጠብቁ ቢያንስ ሰማይና ምድር እስኪላቀቁ ድረስ ይህን ጩኸት ቢያስቆሙ መልክም ነው፡፡ ይህን መናገር ደግሞ በፀረ-ሃይማኖተኝነት ሊያስፈርጅ አይገባም፡፡› በማለት ለዚህ ዘጋቢ ገልጠዋል፡፡
ተዘዋውረን የሕዝብ አስተያየት ለመቃረም እንደሞከርነው በርግጥም ብዙ ነገሮች እየተደረጉ ያሉት ከመጻሕፍቱ በተቃራኒ እንደሆነና የሃይማኖት ሰዎች ቅዱሳት መጻሕፍታቸውን ቢመረምሩ እንደሚሻላቸው  ብዙዎች አስተያየት ሰንዝረዋል፡፡ በክርስትናው ሃይማኖት ለምሳሌ የሃይማኖቱ የማዕዘን ራስ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ በሕይወት በነበረበት ወቅት እንደመከረው ሰዎች መንግሥተ ሰማይን ሊወርሱ የሚችሉት በጸሎት ርዝመት ሳይሆን በእምነታቸው ጥብቀትና በሥራ በሚገለጽ ፍቅር እንደሆነ በመግለጽ ‹አባታችን ሆይ …›ን ከልብ መጸለይ ብቻውን በቂ እንደሆነ አስተምሯል፡፡ ‹ስለዚህ› ይላሉ አንድ አስተያየት ሰጪ ‹ስለዚህ እንደክርስቶስ ከሆነ በአሁኑ ዘመን ያሉት ካህናትና ቀሳውስት የድምጽ ብክለት ብቻ ሳይሆን የጸሎት ብክነትም እያደረሱ ነው ቢባል ከክርስቶስ አስተምህሮ አኳያ ትክክል ነን ማለት ይቻላል› ሲሉ ይህ ጉዳይ በከፍተኛ ደረጃ ትኩረት ተሰጥቶበት መንግሥትም የሃይማኖት ተቋማትም እንዲያስቡበትና በተለይ የሌሊት የማጉሊያ ጩኸቶች ገደብ እንዲበጅላቸው አበክረው አሳስበዋል፡፡ በማጉሊያ ከሚሰሙና ቤተ ክርስቲያንን ወይም መስጂዶችን በየመኝታ ቤታችን ካለሰዓቱ ከሚያመጡ የጸሎት ዓይነቶች መካከል ጥቂቶቹ የሌሊት ማኅሌቶች፣ የአዛን ጥሪዎችና በከፍተኛ የሰውና የሙዚቃ መሣሪያ ድምፅ የታጀቡ የመዝሙር ሽብሸባዎች መሆናቸውም ተገልጾኣል፡፡ ስለሆነም ዘመናዊ የኤሌክትሮኒክስ የጩኸት ማስተጋቢያ ባልተሠራባቸው ጥንታዊ ዘመናት የተደነገጉና ከአንድ ሰው የመጮህ አቅም በላይ ሄደው አካባቢን ያውኩ ያልነበሩ ጸሎቶች ዛሬ በከፍተኛ ቴክሎጂ ታግዘው የሕዝብን በሰላም የመተኛትና የማረፍ መብት በባህልና በሃይማኖት ሽፋን እንዳይጋፉ ያስፈልጋል ሲሉ ብዙዎች አስተያየታቸውን በምሬት ገልጠዋል፡፡
ከዚሁ በተያያዘም በየአካባቢው በተለይ ሐሙስና ቅዳሜ በየቃልቾችና ጠንቋዮች ቤት በሚደረገው የዛር ድልቂያና የአውሊያ ዳንኪራ ብዙ ዜጎች ቅሬታ እንዳደረባቸው ተዘግቧል፡፡ አንዳንድ የአዲስ አበባ ዳርቻዎች ነዋሪዎች ለሪፖርተራችን እንደገለጡት እነዚህ ሰይጣናዊ የዛር መንፈስን ለመጥራትና በፈረሱ – ሰው ላይ ተሹሞ የመጡበትን ፍርድና ቅድ ለማግኘት የሚጥሩ ወገኖች ዛሩ ገብቶ እስኪወጣ በሚያሰሙት የድቤና የከራማ መጥሪያ መንዙማ እንዲሁም የበሽተኞች ጉሪያ ምክንያት ስለሚረበሹ እንቅልፍ የሚባል ነገር ሳያዩ እንደሚያድሩና ከዛሩ ቤት በሚወጡ ጢሳ ጢሶችም ለአስም ህመም እንደሚዳረጉ ጠቁመዋል፡፡ አንድ በዚህ ችግር የተበሳጨ ሰው እንደተናገረው ‹ እርግጥ ነው  ሰው ሲቸገር ጠንቋይ ቤት ቀርቶ ገመድ ይዞ ወደሚቀርበው ዛፍ ሊሄድና ሊሰቀልም ይችላል፡፡ ነገር ግን ሰዎች ማወቅ ያለባቸው ነገር ችግር ባጋጠማቸው ጊዜ ወደፈጣሪ እንደመጮህና መልሱን በትግስት እንደመጠባበቅ የራሱን ችግር መፍታት ወደማይችል የሰው ልጅ ዘንድ በመሄድ ለዛርና ለአውሊያ ማፈንደድ በፍጹም ተገቢ አለመሆኑን ነው፤ ከጤናማ ሰውም አይጠበቅም፤ ለምታልፍ ዓለም ለሚያልፍ የስደት ዓለም ፈጣሪን ማሳዘን አይገባም፡፡ ብዙ ዜጎች በዚህ የተሳሳተ ጎዳና ሲነጉዱ ይታያል፡፡ በዚህ የማያዋጣ ሙከራቸው ነፍሳቸውንም ሥጋቸውንም ለሚያቆሽሽ የአጋንንት ተግባር ይጋለጣሉ – ለጊዜው ሰይጣን ማስመሰልና መማረክ ያውቅበታልና የተወሰነ ሥጋዊ ድሎትና ምቾት ሊሰጣቸው ይችላል፤ አሁን ዓለምን እየገዛ ያለውም እርሱ ነው – ቀድሞ ቃል ተገብቶለታልና፤ ዘመኑ ግን እያለቀች እንደሆነች አበቅቴው ይናገራል፡፡ ይሁንና ሰይጣን የሚናቅ ኃይል አይደለምና እያዋዛ ወደግዛቱ አስገብቶ ለመከራ ነፍስና ለመከራ ሥጋም ይዳርጋል፤ ብዙ አይተናል፡፡ እርሱን ለማሸነፍ ብርቱ የመንፈስ ጥንካሬና የጸሎት ጥሩር መታጠቅ ይገባል፤ ፈሪ ነው – በአንዲት ‹በስማም› 40 ሜትር የሚሸሽ ድንጉጥ ነው፡፡ ያቺ ‹በስማም› ግን ጠንካራ እምነት ካለው ግለስብ የምትወጣ መሆን አለባት፤ ‹ሲሞቅ በማንኪያ ሲቀዘቅዝ በእጅ› በእግዜር ቤት አይሠራም፡፡ የሰይጣን ስጦዎች በሬን ጨው እያላሱ ወደመታረጃው እንደመውሰድ ያህል ናቸው፡፡ የሃይማኖት መምህራንም በዚህ ረገድ ኃላፊነታቸውን የተወጡ አይመስሉኝም፡፡ እንዲያውም ከነሱም መካከል ወደነዚሁ የአጋንንት ሰዎች የሚሄድ እንደማይጠፋና በጥንቆላው ውስጥም የሚሳተፉ ደብተራዎችና መሪጌታዎች እንዳሉ በማኅበረሰቡ ዘንድ በስፋት ይታወቃል – ደንበኛቸው ማን ሆነና? ኮከብ እቆጥራለሁ – ዓይነጥላሽን እገፍልሻለሁ፤ ጠላትህን በአንደርብ እመታልሃለሁ፣ ዐውደ ነገሥቱን ቆጥሬ የምታገባትን ሴት እለይልሃለሁ … የሚለው ቀጣፊ የአጋንንት ውላጅ ደብተራ ሁሉ ይህን ዕኩይ የሰይጣን ሥራ የሚያከናውነው ቤተ ክርስቲያንን ተጠልሎ መሆኑን እናውቃለን፡፡ ብቻ ችግራችን የተወሳሰበ ነው፡፡…› በማለት የተሰማውን ስሜት በምሬት ገልጾኣል፡፡
በአዲስ አበባ ያገለገሉ ዕቃዎችን መሸጫ ሱቆች እየተበራከቱ መሆናቸው ተገለጸ
አዲስ አበባን ከራስጌ እስከግርጌ የሚጎበኝ ሰው በየሥፍራው ያገለገሉ የቤትና የቢሮ ዕቃዎች ለዳግመኛ ሽያጭ ከየቸገረው ሰው በቅናሽ ዋጋ እየተገዙ እንደሚሰባሰቡ መረዳት ይቻለዋል፡፡ እንዳንዳንዶች አስተያየት ከሆነ ባልተለመደ ሁኔታ ይህን ያህል የአሮጌ ዕቃዎች ሽያጭ ደርቶ ሊታይ የቻለው የድህነቱ መባባስ ያስከተለው የነበረን ጥሪት እያወጡ በመሸጥ ጊዜ የማይሰጠውን የቤተሰብን ወስፋት ለመሸንገል መሆኑን ብዙዎች ይስማሙበታል፡፡ በዚያ ላይ ልጆችን ለማስተማር፣ ለመመገብና ትምህርት ቤት ለመላክ ገንዘብ ስለሚያስፈልግ ቤትን ባዶ እያደረጉ በደህናው ቀን የተገዛን ዕቃ ለመሸጥ የሚገደዱ ዜጎች ቁጥር እየተበራከተ መምጣቱ ታውቋል፡፡ በአንድ በኩል የወቅቱ ማይማን ሀብታሞች ለአንድ የቤት ዕቃ በመቶ ሺዎች የሚገመት ብር እያወጡ ቤታቸውን ሲያሸበርቁ ቤላ በኩል ደግሞ ብዙዎች ለዕለት ጉርስ ሲሉ የዘመናት አንጡራ ጥሪታቸውን እያወጡ በርካሽ ሲሸጡ ሲታይ ኑሮ በኢትዮጵያ የመጨረሻው ዕንቆቅልሽ ደረጃ መድረሱን ያሳያል የሚሉ ወገኖች ሞልተዋል፡፡ አዲስ አበባ ውስጥ በመንገዶች ዳርና ዳር የሚታዩ ያገለገሉ ዕቃዎች ሽያጭ የሚያሳየው የሕዝቡን መደኽየት ሲሆን በሌላ ቀጭን መስኮት በኩል ደግሞ ባለጊዜዎቹ በአንድ ቀን አዳር ከብረው ሲድሩ የነበራውን የቤት ዕቃ ለአሮጌ ዕቃ ተቀባዮች ስለሚያስረክቡ ከተማዋን ወደአሮጌ ዕቃ መደብርነት እየለወጧ እንደሆነ የሚናገሩ አሉ፡፡
ዘጋቢያችን ተዘዋውሮ ባደረገው የዋጋ ጥናት መሠረት በደርግ ጊዜ ከኢትሆፍ 500 ብር ገደማ ይሸጥ የነበረው ባለስድስት ወንበር የምግብ ቤት ጠረጴዛ አሁን እንደየይዞታው በአሮጌ ተራ ከአራት እስከ ስድስት ሺህ ብር እንደሚጠራ ለመገንዘብ ተችሏል፡፡ በስድስት መቶ ብር ገደማ ይገዛ የነበረው ባለሦስት ተካፋች የልብስ ቁም ሣጥንም በአሁኑ የአሮጌ ተራ የሳልቫጅ ግዢ ከሰባት ሺህ ብር በላይ እንደሚሸጥ ታውቋል፡፡ ሻጮቹ ለአትራፊዎቹ ሲሸጡ ግን ያን ያህል ጥቅም እንደማያገኙበትና የመጣል ያህል እንደሆነ ለመረዳት ተችሏል፡፡ ዕድሜ ጠገብ የቀድሞ ደህና ነዋሪ ሰዎች ምርጫ ሲያጡ ከመዶሻና ማርቴሎ አቅም እንኳን ሳይቀር ቤታቸው ውስጥ የሚገኝን ዕቃ እያወጡ በመሸጥ ለዕለት ጉርሳቸው እንደሚጠቀሙበትና ለዚህ ውርደት የዳረጋቸውም የወያኔው ሥርዓት በዜጎች መካከል የፈጠረው ዐይን ያወጣ የሀብት ክፍፍል ሥርዓት አልባ መሆን እንደሆነ አንዳንድ ምሁራን በጥናቶቻቸው ገልጠዋል፡፡ ይህን ለማረጋገጥ የሚፈልግ አንባቢ ኬኔዲ የዘፈነውን ‹አንድ ነኝ› የሚለውን ብሶተኛ የዘፈን አልበም ማዳመጥ ወይም ኬኔዲ ቤተ መጻሕፍት ገብቶ ጽሑፎችን ማገላበጥ ይችላል፡፡
በተያያዘ ዜና አዲስ አበባ ውስጥ የድሃና የሀብታም ሠፈሮችን ማወቅ ለሚፈልግ አዲስ ግኝት መዘገቡ ታወቀ፡፡ ይሄውም አዲስ ግኝት በሀብታሞች ሠፈር ውስጥ የሚገኙ የመንገድ ላይ ነጋዴዎች የሚይዟቸው ዕቃዎች ኬክ፣ የአውሮፓ ብስኩቶች፣ ሀምበርገር፣ የታሸገ ውኃ፣ ፖም፣ ሙዝና ብርቱካን፣ የፊልም ሲዲዎች፣ ብላክቤሪና አይፎን የእጅ ስልኮችና የመሳሰሉት ሲሆኑ በኛ ሠፈር የሚገኙ አዟሪዎች ደግሞ ሎተሪ፣ ሸንኮራ አገዳ፣ቆሎ፣ መፋቂያ፣ የቻይና የሚያቃጥል ካልሲ፣ ኮቸሮ፣ እዛው በላች እዛው ሞተች የዐይጥ መርዝ፣ መርፌና ክርና መርፌ ቁልፍ፣ የቻይና ተማሪ በቤት ሥራ ታዝዞ የሚሠራት ፎርጅድ ኖኪያ የእጅ ስልክና የመሳሰሉ እንደሸንኮራው አላቂና እንደመርፌዋ ቋሚ ዕቃዎችን ነው፡፡
በሌላ ዜና እስከምንገናኝ ቸር እንሰንብት፡፡

ESAT WAZA ENA KUMENRGER 25 NOVEMBER 2012 ETHIOPIA


ብዬ ሰሚ አገኛለሁ፣ ቅሬታ አቅርቤ ይፈታልኛል የሚል ዜጋ የለም!



የሕግ የበላይነት እንዲኖር፣ ሰብዓዊ መብት እንዲከበር፣ የፕሬስ ነፃነት እንዲረጋገጥ፣ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት እውን እንዲሆን የሚያደርጉ ሕገ መንግሥትና ሕጎች አሉን??????
ከድህነት የሚያላቅቅ፣ መካከለኛ ገቢ ወዳላት አገር የሚያሸጋግር፣ የቤት፣ የጤና፣ የትምህርት፣ የትራንስፖርት፣ ወዘተ ችግሮችን የሚፈታ ዕቅድም አለን???????
እነዚህ አሉ ማለት ግን ዲሞክራሲ ተረጋገጠ፣ ልማት እውን ሆነ ማለት አይደለም፡፡ በመርህ ደረጃ ተግባር ላይ ካዋልናቸው ይጠቅማሉ፡፡ ካላከበርናቸው፣ ከረገጥናቸውና ከጣልናቸው ደግሞ ገጠመኝ ይሆናሉ፡፡ በዚህ ምክንያት አለማደግና ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት አለመገንባት ብቻ ሳይሆን፣ ወደኋላ መንሸራተትም ሊያጋጥም ይችላል፡፡

ምርጫ! መርህ ወይስ ገጠመኝ? 

ፍርድ ቤቶች ራሳቸውን የቻሉ ነፃ የሕግ ተርጓሚ አካላት እንደሆኑ ሕገ መንግሥታችንም ሕጎቻችንም በግልጽ ያስቀምጣሉ፡፡ ስለሆነም በሕግ አንፃር ሲታይ ፍትሕ ማግኘት በመርህ ደረጃ ዘወትር በየትም ሥፍራ መረጋገጥ ያለበት እንጂ፣ ፍትሕ ዘወትር እየተረገጠ አልፎ አልፎ ሊገኝ የሚችል ገጠመኝ መሆን የለበትም፡፡

በተግባር ሲታይ ግን ፍትሕ ገጠመኝ እየሆነ ነው፡፡ የፍትሕ መጓደል በሚያሳስብ ሁኔታ እየታየ ነው፡፡ በፍትሕ አካላት ውስጥ በአቅምና በአመለካከት ድክመት አለ፡፡ የሥነ ምግባር ጉድለት በትልቁ እየታየ ነው፡፡ በጠበቆች፣ በዳኞችና በዓቃቢያነ ሕግ በኩል አሳሳቢ የሥነ ምግባርና የአቅም ችግር እየተስተዋለ ነው፡፡ በአጠቃላይ የፍትሕ አካላት መጠናከር እያሳዩ ከመጓዝ ይልቅ እየተልፈሰፈሱና እየተንገዳገዱ ናቸው፡፡ በዚህ ምክንያት ፍትሕ ማግኘት መርህ መሆኑ ቀርቶ ገጠመኝ እየሆነ ነው፡፡ ጉቦ የአንቀጾች ሁሉ የበላይ አንቀጽ እየሆነ መጥቷል፡፡ 

መልካም አስተዳደር በሕግና በመርህ ደረጃ መከበር አለበት ተብሎ የታወጀ፣ የተነገረ፣ የተለፈፈለት ነው፡፡ በተግባር ደግሞ አቤት ብዬ ሰሚ አገኛለሁ፣ ቅሬታ አቅርቤ ይፈታልኛል የሚል ዜጋ የለም!!!! በዚህ ዙሪያም ጉቦና ጥቅማ ጥቅም የበላይነት እየያዙ ነው፡፡ የአቅም ማነስ ችግር ትልቅ እንቅፋት ነው፡፡ ስብሰባዎችና ሥልጠናዎች የችግር መፍቻ መድረኮች መሆናቸው ቀርቶ መደበቂያ እየሆኑ ነው፡፡ ‹‹በስብሰባና በሥልጠና ምክንያት ኃላፊ የለም›› የሚል ማስታወቂያ መለጠፍ ነው የቀረው፡፡ ኃላፊ ቢሮው ገብቶ አቤቱታ አንብቦ ችግር መፍታት መርህና ግዴታው መሆኑ ቀርቶ ገጠመኝ እየሆነ ነው፡፡

በዚህ ቀን የቢዝነስ ወይም የኢንቨስትመንት ላይሰንስ አውጥቼ፣ በዚህ ሳምንት መሬት አግኝቼ፣ በዚያኛው ሳምንት ግንባታ ጀምሬ፣ በዚህ ወር የባንክ ብድር አግኝቼ፣ በዚህ ዓመት ሥራ ጀምሬ ይህን ያህል አተርፋለሁ እያሉ ማሰብ መርህ የሚደግፈው ሒደት መሆን ሲገባው አጋጣሚ እየሆነ ነው፡፡

‹‹ሰው ያስባል እግዚአብሔር ይፈጽማል›› ተብሎ የሚገባበት እንጂ፣ ሰው ያመለክታል አስተዳደሩ ወይም ኃላፊው ይፈጽማል የሚባልበት ማስተማመኛ የለም፡፡ አዲስ ለመጀመርና የተቋረጠ ካለ ለመቀጠል ዕድሉ ገጠመኝ ነው፡፡

ይህም በእጅጉ እየጎዳን ነው፡፡ ጥርጣሬ እየበዛ በውጭ ኢንቨስተሮች ላይ ፍርኃት እያስከተለ ነው፡፡ ችግር አይኖርም፣ ሕግ አለ፣ መመርያ አለ፣ ተብሎ በእምነት የሚገባበት መሆኑ ቀርቶ፣ የደም ግፊትና የስኳር ኪኒኖችን በመያዝ የሚገባበት ጉዳይ እየሆነ ነው፡፡

የበደለ፣ የአገር ሀብት ያባከነ፣ ሕገ የረገጠ ግለሰብ ማጥፋቱ እየታወቀ ይቀጣል ወይስ አይቀጣም ለሚለው ጥያቄ ወሳኙ ማስረጃ መሆኑ እየቀረ ነው፡፡ ገጠመኝ ሆኗል፡፡ ይታሰራል የተባለው ሊሾም፣ ተጠያቂ ይሆናል የተባለው ጠያቂ የሚሆንበት ሁኔታ አለና፡፡ ገጠመኝ!

የባንክ ብድር አግኝቶ መሥራት ይቻላል? አዎ! ነገር ግን ዛሬ ተችሎ ነገ ሊቆም ይችላል፡፡ ኤልሲ በመክፈት ከውጭ ዕቃ እያመጡ መነገድ ይቻላል? አዎን! ግን ኤልሲ ሊከለከል ይችላል፡፡ መርህ መሆኑ ቀርቶ ይህም ገጠመኝ እየሆነ ነው፡፡

መንግሥት በሚያወጣቸው ጨረታዎች ሕግ ተከትሎና አክብሮ ተጫርቶ ማሸነፍ ይቻላል? አዎን! ግን በመርህ ደረጃ ይህ ሀቅ ቢሆንም በተግባር ግን ጨረታው ቀርቶ በቀጥታ ለግለሰብ ወይም ለድርጅት ተሰጥቷል ሊባልም ይችላል፡፡ በቴክኒክ ብቃትና በሚጠየቀው ገንዘብ የማይጠቅመው አሸንፎ፣ የሚጠቅም ነገር ያቀረበው ሊሸነፍ ይችላል፡፡ በብዛት የጨረታ አካሄድ መርህ መሆኑ ቀርቶ ገጠመኝ እየሆነ ነው፡፡

ብዙ ብዙ መጥቀስ ይቻላል፡፡ እያልን ያለነው በአጭሩ ሲቀመጥ ግን ሕገ መንግሥት ይከበር፡፡ ሕገ መንግሥትን ማክበርና ሁሌም ሁሉንም በሕጋዊ መንገድ ማስተናገድ ይቅደም፡፡ ይህንን በመርህ ደረጃ አምነን የምንፈጽመው እንጂ፣ ለእከሌ ሌላ ለእከሊት ሌላ እያደረግን በዘፈቀደ በጥቅም የምንሠራው መሆን የለበትም ነው፡፡

ሕጎች፣ አዋጆች፣ ደንቦች፣ መመርያዎችና አሠራሮች ለሁሉም እኩል የሚያገለግሉ እንጂ ገመጠኞች አይደሉም፡፡ ላይ ያለው ባለሥልጣንም፣ ታች ያለው ባለሥልጣንም፣ እዚህና እዚያ ያሉ ሠራተኞችም ሁሌም ሕገ መንግሥትን፣ ሕግን፣ አዋጅን፣ ደንብን፣ መመርያን ተንተርሰው ይሠራሉ እንጂ፣ ‹‹እንደ ሰውና እንደ ገንዘቡ እናስተናግዳለን›› የሚል አጉል ድርጊት መፈጸም የለባቸውም፡፡ ሁሉም በሕግ ፊት እኩል ሆኖ ይስተናገድ፡፡ ሁሉም ኃላፊ፣ ሁሉም ሹም ሕግን መሠረት አድርጎ ይሥራ ያገልግል ነው ቁምነገሩ፡፡

በሚገባ እናስብበት፤ መርህ በገጠመኝ እየተተካ ነው፡፡ ቀስ በቀስ ሰላማችን፣ ሉዓላዊነታችን፣ አንድነታችንና ህልውናችን በመርህ ደረጃ ዋስትና ያላቸው መሆናቸው ቀርቶ ገጠመኝ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ህልውና ገጠመኝ ሲሆን ደግሞ የዛፍ ላይ እንቅልፍ ነው፡፡
ስለዚህ መርሆች ገጠመኞች እንዳይሆኑ ጠንቀቅ!

Saturday, November 24, 2012

ተሃድሶ ... ተሃድሶ .... ተሃድሶ ..... ተሃድሶ .......



በኢትዮጵያ ባለፉት ሃያ አንድ ዓመታት የድርጅት እጥረት አላጋጠመንም። ለቁጥር የሚታክቱ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ተቋቁመዋል። ከመንደር እሳቤ ጀምሮ እስከ ብሄራዊ ደረጃ ከተዋቀሩት የተቃዋሚ ፓርቲዎች መካከል ምን ያህል እንደተሳካላቸው በውል ባይታወቅም ህዝብ አደራጅተናል የሚሉ አሉ። መቋቋማቸው ሳይሰማ “እንደወጡ” የቀሩ ብዙ ናቸው። እንደው ለወጉ ያህል ስያሜያቸውን እያሰሙ በመግለጫና በዘለፋ “አልጠፋንም” የሚሉም አሉ። ለዓመታት ጎረቤት አገር መሽገው ከዛሬ ነገ “መጣን” የሚሉን አሉ። መኖራቸውም መሞታቸውም ልዩነት በሌለው መልኩ የሚንከላወሱ “ሙት” ነዋሪ ፓርቲዎችም አሉ። የፖለቲካ ዓላማቸው ሌሎችን በሾኬ መጣል፤ የኢኮኖሚ ፕሮግራማቸው ሌሎቹን ማክሰር፤ የማኅበራዊ ፖሊሲያቸው ማበጣበጥ፤ የሃይማኖት አመለካከታቸው “እኛ ካልባረክነው ዉጉዝ ነው” የሚል ፕሮግራም ያላቸው የሚመስሉም አሉ፡፡ ኢህአዴግ ጥብቆ አልብሶ ያደራጃቸው “ተለጣፊ” የሚባሉትም አሉ። ቤተሰብ ሰብስበው ቃለ ጉባኤ እያጸደቁ አገርና ህዝብ ነጻ እናወጣለን የሚሉም አሉ። አጋነናችሁ ካላላችሁን ከእቁብና ከእድር ባነሰ አደረጃጀት አገር ለመምራት ተነስተናል የሚሉ እፍረት ያልፈጠረባቸውም አሉ። እየተሰነጠቁና እየተሰነጣጠሩ ኤ፣ ቢ፣ ሲ፣ ዲ፣ ኢ፣ ኤፍ፣ … የሚባሉትና ሌላም ሌላም ዓይነት፡፡ ለምን እንዲህ ይደረጋል ሲባሉ “ለአንድ ኢትዮጵያችን ብለን ነው” ይሉናል!
ታግለው የሚያታግሉ አመራሮች አሉ። ስብዕናቸው የሚወደድ መሪዎች አሉ። ከሃሳብ እንጂ ከድርጅትና ከግለሰቦች ጋር ጸብ እንደሌላቸው በማስተጋባት ያመኑበትን የትግል አቅጣጫ የሚከተሉ አሉ። በርካታ ደጋፊና ተንከባካቢ ያላቸው ዘወትር ስለመቀራረብና ስለመተባበር አስፈላጊነት የሚሰብኩ አሉ። በሌላ በኩል ደግሞ ድርጅት ባቋቋሙ ማግስት በትዕዛዝ የሚወገዙ፣የሚሰደቡና ቀጠሮ ተይዞ በደቦ የጥላቻ ዘመቻ የሚከናወንባቸው አመራሮችም አሉ። ደረጃ የሚወጣላቸውና የሚፈረጁም ጥቂት አይደሉም። ይህም የሚሆነው ለኢትዮጵያ ሲባል ነው ይባላል።
ድርጅት ባቋቋሙ ማግስት ሌሎች ድርጅቶችን በማውገዝ ራሳቸውን የሚያስተዋውቁ አመራሮች አሉ። በሚያራምዱት ያረጀና የነተበ ፖለቲካ ስንዝር መራመድ ሳይችሉ ቀርተው ሌሎችን በማወገዝ የተጠመዱ አመራሮች አሉ። ፓርቲን ከፖለቲካ ስራ ይልቅ ወደ ግል ማህበር በመቀየር ሲሳደቡና ሌላውን ሲያወግዙ ኖረው ለመሞት የወሰኑ አመራሮች አሉ። ምን እየሰሩ እንደሆነ የማናውቃቸው አመራሮች አሉ። እነዚህና ሌሎች ሁሉም የሚናገሩት ግን ስለ አገርና ህዝብ ነው። “ነጻ አውጪ” ስለ መሆናቸው!!
ብዙ አይነት የተቃዋሚ ድርጅቶች ደጋፊዎች አሉ። ያለአንዳች መታከት በችግርና በተስፋ መቁረጥ ውስጥ እያለፉ የሚታገሉ አሉ። ዳር ሆነው የሚያሽሟጥጡ፣ በሌሎች መስዋዕትነት የድል ክሬም ለመላስ የሚመኙ አሉ። በስድብና በዘለፋ መንግስት መቀየር እንደሚቻል አድርገው የሚናደፉ፣ ነገር ግን በተግባራዊ ድጋፍ ሲመዘኑ መስፋሪያ የማይሞሉ አሉ። አስር ዶላር በማዋጣት የሚደግፉትን ፓርቲ ሚስጥርና እንቅስቃሴ በዝርዝር በአድራሻቸው ሪፖርት እንዲቀርብላቸው የሚጠይቁ አሉ። ከሁሉም በላይ ወዴት እንደሚያዘሙ ግራ ተጋብተው ዝምታ የመረጡ አሉ። እነዚህ ዝም ያሉ ብዙሃን (silent majority) ተብለው የሚጠቀሱት ክፍሎች ትልቁን ቁጥር ስለሚይዙ ወደ ትግልና “እኔም ያገባኛል” መንፈስ ሊዛወሩ የግድ ነው። እንዴት? በእውቀት ተሃድሶ!!
ከተሃድሶዎች ሁሉ የእውቀት ተሃድሶ ካልቀደመ መሪው፣ ተመሪውና ድርጅቱ ሁሉም ተያይዘው ሲጓተቱ 21ኛው ክፍለ ዘመን ይጠናቀቃልና የሚቀድመውን ማወቅ ብልህነት ይሆናል። ለሁሉም የእውቀት ተሃድሶ በቅድሚያ! ለዲያስፖራው ሆነ ለአገር ቤቱም ወገን የእውቀት ተሃድሶ በቅድሚያ!! የእውቀት ተሃድሶ ባስቸኳይ፣ የእውቀት ተሃድሶ የዘለቀው ደጋፊና ዜጋ ሲነፍስ አብሮ በነፈሰበት አይነፍስምና!!

ESAT Daliy News-Amsterdam Nov 24, 2012 Ethiopia


አንዲት እናት ከሁለት ልጆቿ ጋር በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደለች


ህዳር ፲፭ (አስራ አምት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:- በሻሸመኔ ከተማ ሀይማኖት ደሳለኝ የተባለች የቤት እመቤት ከትናንት በስቲያ ማንነቱ ባልታወቀ ግለሰብ በተኛችበት ከሁለት ልጆቿ ጋር በመጥረቢያ ተቆራርጠው መገደላቸው ተዘገበ።
የእናትየውና የልጆቹ ምላሶች መቆረጣቸውን፣ አይናቸውም መውጣቱን የአይን እማኞች ለኢሳት ገልፀዋል። የአካባቢው ነዋሪዎች በነቂስ በመውጣት በዛሬው እለት ሟቾቹን የቀበሩ ሲሆን፣ ከቀብር በሁዋላም የተቃውሞ ሰልፍ አድርገዋል። .
የቤት ሰራተኛዋ ወንጀሉን በመፈጸም በኩል የመጀመሪያዋ ተጠርጣሪ ሆናለች።

የሰማዕቱ የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት ለባቡር ሀዲድ ግንባታ ሲባል ይፈርሳል መባሉ ከፍተኛ ህዝባዊ ቁጣ ቀሰቀስ



ህዳር ፲፭ (አስራ አምት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-መንግስት በበኩሉ  ሐውልቱ ለደህንነቱ ሲል ከተነሳ በሁዋላ ወደነበረበት ስፍራ ይመለሳል እያለ ነው።
በአዲስ አበባ ውስጥ ሊሠራ በታቀደ የ ከተማ ውስጥ የባቡር  ሀዲድ ሥራ ምክንያት  የዓፄ ምኒልክና የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት ሊፈርሱ የመቻላቸው ወሬ  አስቀድሞ የሾለከው ፤ለምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ቅርበት ካላቸው  ምንጮች  ነው።
እነዚህ የዘርፉ ሙያተኞች በ አምስት ዓመቱ የልማትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ መሰረት በ አዲስ አበባ ውስጥ ሊዘረጋ የታሰበው የባቡር ሀዲድ ፕላን  የዳጋማዊ አፄ ምኒልክንና የ አቡነ ጴጥሮስን ሐውልት እንደሚነካ በመጥቀስ፤ በተለይ የጣሊያንን ወረራ አልባርክም በማለታቸው ሳቢያ በመትረየስ ተደብድበው የተገደሉት የ አቡነ-ጴጥሮስ  ሐውልት ሙሉ በሙሉ እንደሚፈርስ ተናግረዋል። ዜናውን የሰሙ እጅግ በርካታ ኢትዮጵያውያንም በተለያዩ ማህበራዊ ገፆች ተቃውሟቸውን ማሰማት ጀምረዋል።
በጽሁፍ የተቃውሞ ሀሳባቸውን ከገለጹት መካከል ዲያቆን ዳንኤል ክብረት አንዱ ነው።
“ስለ ባቡር በመዝፈን ከመቶ ዓመት በላይ ያሳለፍን ሕዝቦች የከተማ ባቡር ማግኘታችንን በዕልልታ የምንቀበለው ነገር ነው”ያለው ዳንኤል፤” ዘግይተን ይሆናል እንጂ አልቸኮልንም፡፡ ሥራው በቁርጠኝነት መጀመሩና ከወሬ አልፎ ሲተገበር ማየታችንም እሰዬው የሚያሰኝ ሆኗል”ብሏል።
“ግን ደግሞ ጥያቄ አለን..”በማለት ጽሁፉን የቀጠለው ዳንኤል፦ “ይህ የባቡር መሥመር የአቡነ ጴጥሮስንና የዐፄ ምኒሊክን ሐውልት እንዲነሡ ያደርጋል?
ለዚህ ጥያቄ ምላሹ ‹አዎን› ከሆነ ስለ ባቡሩ የሚኖረን ግምት ይለያል፡፡ ኢትዮጵያን እናሳድጋለን ስንል ያሳደጓትን እየዘነጋንና መታሰቢያቸውን እያፈረስን መሆን የለበትም”ብሏል።
‹በማን ላይ ቆመሽ እግዜርን ታሚያለሽ› አለ ያገሬ ሰው ” በማለት የቀጠለው ዳንኤል ፦”የምናመጣው አዲስ ነገር- ባለን ላይ የሚጨመር እንጂ ያለንን የሚያጠፋ መሆን የለበትም፡፡ መኪና ያስፈልገናል፣ ግን እግር የሚቆርጥ መሆን የለበትም፡፡ ወደድንም ጠላንም ይህች ሀገር የታሪክና የቅርስ ሀገር ናት፡፡
ይህ ታሪኳና ቅርሷ ደግሞ የህልውናዋም ምንጭና መሰንበቻም ጭምር ነው፡፡ ይህን ታሪክና ቅርስ እያጠፉና እያበላሹ የሚመጣ ለውጥ አንገት ቆርጦ ፀጉርን እንደማስተካከል ነው የሚቆጠረው፡፡ እናም የሚመለከታቸው ሁሉ ወደ ርምጃ ከመግባታቸው በፊት ሦስት ጊዜ ሊያስቡ ይገባል፡፡” ብሏል።
ሌሎችም በርካታ ኢትዮጵያውያን ጠንካራ ተቃውሞዋቸውን በማሰማት ላይ ይገኛሉ።
መንግስት በበኩሉ   በባቡር ሀዲድ ምክንያት የዳግማዊ አጼ ምኒልክና የ አቡነ-ጴጥሮስ ሐውልት ይፈርሳል የሚለው ወሬ ከ እውነት፡የራቀ ነው በማለት መግለጫ አውጥቷል።
የሀዲዱ ግንባታ የምኒልክን ሐውልት ጭራሽ አይነካውም ያለው የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን  የ አቡነ-ጴጥሮስ ሐውልት ግን ለደህንነቱ ሲል ከተነሳ በሁዋላ እንደገና በነበረበት ስፍራ ይቀመጣል ብሏል።
የኮፖሬሽኑ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ አበበ ፤የባቡር መተላለፊያ ዋሻ ከሃውልቱ ስር ስለሚገነባ ፤ ግንባታው እስኪያልቅ ድረስ ሃውልቱ ለጥቂት ጊዜ ይነሳና ከዋሻው መጠናቀቅ በኋላ ወደ ቦታው ይመለሳል ብለዋል-ራዲዮ ፋና እንደዘገበው።
“መቼም የመጀመርያውን ባቡር ያስገቡትን የዐፄ ምኒሊክን ሐውልት አፍርሶ ባቡር እናስገባ ማለት የታሪክ ምጸት ነው፡፡ ለነጻነት የተሠውትን የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት ነቅሎ በባቡር ላይ በነጻነት ለመሄድ መከጀል ግፍ መሥራት ነው የሚሆነው” ያለው ዳንኤል ክብረት፤ምላሹ ‹አይደለም› ከሆነ ደግሞ እሰዬው፡፡ ግን አሁን በሐውልቶቹ አጠገብ የሚከናወነው ቁፋሮ ወደ መሠረታቸው እየሄደ ነው፡፡ እንደሚሰማውም የባቡሩ መሥመር በሐውልቶቹ ሥር የሚዘረጋ ነው፡፡ ታድያ የሐውልቶቹ ዕጣ ፈንታ ምንድን ነው? ለሕዝቡስ ግልጽ ማብራርያ የማይሰጠው ለምንድን ነው? ‹ለጊዜው ተነሥተው በኋላ ይመለሳሉ› የሚል መረጃም እየተሰማ ነው፡፡ ለጊዜውስ ተነሥተው የት ነው የሚሄዱት? በኋላስ በምን ሁኔታ ነው የሚመለሱት? ታሪካዊ ቦታቸውንስ ይለቃሉ?ግልጽ መልስ ያስፈልጋል፡፡>>በማለት መንግስት በጉዳዩ ዙሪያ ለህዝቡ ግልጽ ማብራሪያ    እንዲሰጥ ጠይቋል

በሙስሊም ኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርሰው ሰቆቃ እየጨመረ ነው ተባለ



ህዳር ፲፭ (አስራ አምት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-መንግስት ሙስሊሙ ላነሳው ጥያቄ ተገቢውንና ሰላማዊ የሆነ መፍትሄ ከመስጠት ይልቅ የሀይል አማራጭ መጠቀሙ፣ በሙስሊሙ ላይ የሚደርሰው በደል እየከፋ እንዲሄድ አድርጎታል።
የአካባቢው ነዋሪዋች እንደተናገሩት  ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በአማራ ክልል የኦሮሚያ ዞን ዋና ከተማ በሆነችው ከምሴ የፌደራል ፖሊስ አባላት ቤት ለቤት በመግባት ከ60 በላይ ሙስሊም ኢትዮጵያውያንን በመያዝ አስረዋል።
በተያዙት ወጣቶች ላይ የሚደርሰው እንግልት እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎ በርካታ ወጣቶች ቀያቸውን ለቀው ወደ ጂቡቲና ሱዳን ተሰደዋል።
ከደጋንና ከሀርቡ አካባቢዎች ተነስተው ሱዳን ድንበርን እያቋረጡ የነበሩ ሙስሊሞች ለኢሳት በመደወል “    እኛ በአገራችን በነጻነት መኖር ስላልቻልን በመንገድ ስንጓዝ ጅብ ይብላን ብለን ጥለን እየሄድን ነው። የሱዳንንና የኢትዮጵያን ድንበር እያቋረጥን ነው፣ እንግዲህ አገራችንን አደራ፣ ሱዳን በሰላም ከገባን ድምጻችንን ታሰሙልናላችሁ፣ ያለበለዚያ ግን መንገድ ላይ ከተያዝን እንደማስረጃ አድርገው ስለሚያቀርቡብን መልእክታችንን ብቻ አቅርቡልን ” በማለት ተናግረዋል።
በተመሳሳይ በትናንትናው እለት  በኢሊባቦር ዞን በመቱ ከተማ ከ400 በላይ ሙስሊሞች  የተቃውሞ ድምጽ ማሰማታቸውን ተከትሎ እስከ ምሽቱ 10 ሰአት ታግተው ውለዋል።
የተወሰኑ ሙስሊሞችን ለማሰር ሙከራ ተደርጎ የነበረ ቢሆንም ፣ ህዝቡ ባሰማው ተቃውሞ ወዲያውኑ ሊፈቱ ችለዋል።
የአሜሪካን መንግስት ጨምሮ የተለያዩ አለማቀፍ ድርጅቶች መንግስት የሙስሊሞችን ጥያቄ ለመፍታት እየተከተለ ያለው መንገድ ለኢትዮጵያ ህልውና አደጋ ይፈጥራል በማለት እያስጠነቀቀ ነው።

በሀረር ከተማ ከ500 በላይ ሱቆች ይፈርሳሉ መባሉን ተከትሎ አለመረጋጋት መፈጠሩ ተሰማ


ህዳር ፲፭ (አስራ አምት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-በሀረር ከተማ ሸዋ በር እየተባለ በሚጠራው  የገበያ ማእከል የሚገኙ ከ500 ያላነሱ ሱቆች ይፈርሳሉ በመባሉ በዛሬው እለት አለመረጋጋት ተፈጥሮ እንደነበር ዘጋቢዎቻችን ከስፍራው ገልጸዋል።
አብዛኞቹ ሱቆች ካለፉት 30 አመታት ጀምሮ በጉራጌ ተወላጆች የተያዙ ሲሆን፣ ክልሉ ነጋዴዎችን በማስወጣት ለአካባቢው ተወላጆች ለመስጠት  እንዳቀደ መነገሩን ተከትሎ ነው አለመረጋጋቱ የተፈጠረው።
ተገቢው ካሳ እና ምትክ ቦታ ሳይሰጥ ሱቆችን ለቀው እንዲወጡ ትእዛዝ መተላለፉ፟ ነጋዴዎችን ግራ አጋብቷል።
ሸዋ በር የገበያ ማእከል ከ2 አመት በፊት ሆን ተብሎ እንዲቃጠል ተደርጓል በሚል ከፍተኛ ውዝግብ ተፈጥሮ እንደነበር ይታወሳል።

Friday, November 23, 2012

አቶ በረሃነ ገ/ክርስቶስ የኢሕአዲግ አባላት ከሆኑት ዲፕሎማቶች ጋር ተወዛገቡ


አቶ በረሃነ ገ/ክርስቶስ የኢሕአዲግ አባላት ከሆኑት ዲፕሎማቶች ጋር ተወዛገቡ

ህዳር ፲፭ (አስራ አምት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተጠባባቂ ሚኒስትር አቶ በረሃነ ገ/ክርስቶስ የኢሕአዲግ አባላት ከሆኑት ዲፕሎማቶች ጋር መወዛገባቸውን የቅርብ ምንጮችን የጠቀሱ ዘገባዎች ይፋ አድርገዋል የውዝግቡ መነሻ የኢሕአዲግ አባላት ያልሆኑ ዲፕሎማቶች ለስራ በመታጨታቸው ነው።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተጠባባቂ ሚንስትር  አቶ በረሃነ ገ/ክርስቶስ ከምክትላቸው ከአቶ ነጋ ፀጋዬ ጋር በመሩት ሥብሰባ ላይ ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚቻል ደረጃ የኢሕአዲግ አባላት የሆኑ ዲፕሎማቶች የተገኙበት መሆኑም ተመልክቷል። ለውዝግቡ መነሻ የሆነው የአፍሪካ ሕብረት የወቅቱ ለቀመንበርነት ተረኛ ኢትዮጲያ ከመሆኗ ጋር የተያያዘ ነው ተብሏል።ኢሳት ዜና:-የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተጠባባቂ ሚኒስትር አቶ በረሃነ ገ/ክርስቶስ የኢሕአዲግ አባላት ከሆኑት ዲፕሎማቶች ጋር መወዛገባቸውን የቅርብ ምንጮችን የጠቀሱ ዘገባዎች ይፋ አድርገዋል የውዝግቡ መነሻ የኢሕአዲግ አባላት ያልሆኑ ዲፕሎማቶች ለስራ በመታጨታቸው ነው።

የአፍሪካ ሕብረት የወቅቱ ለቀመንበርነት ቦታ በመጪው ጥር ኢትዮጲያ እንደምትቀበል በመረጋገጡ ይህንን ኋላፊነት ለመወጣት የማስተባበሩን ሥራ የሚሰሩት አንጋፋዋ ዲፕሎማት ቆንጂት ሥነ ጊዮርጊስ ረዳት እንዲሆኗቸው ሦስት ዲፕሎማቶችን ይጠቁማሉ አምባሳደሯ የጠቆሟቸው ሦስቱ ግለሰቦች የፓርቲ አባላት አለመሆናቸው የኢሕአዲግ አባላት የሆኑ ዲፕሎማቶችን አስቆጥቷል።
አምባሳደር በረሃነ ገ/ክርስቶስ የአንዳፋዋን ዲፕሎማት አስተዋፅኦ በመዘርዘር ስለ አስፈላጊነታቸው ሲያነሱ ይበልጥ ተቃውሞ እንደገጠማቸው ስብሰባውን በፈለጉት ሠዓት ለመጨረስ እንኳን ከተሰብሳቢው እንዳልተፈቀደላቸው የተገኘው ዜና ያብራራል መስሪያ ቤቱን የመምራት ብቃት የለህም እስከመባል መድረስም ተመልክቷል።
ከምርጫ 97 በኋላ ልምድና ዕውቀት ያላቸው ዲፕሎማቶች መስሪያ ቤቱን ጥለው በመሄዳቸው ከ 200 በላይ የኢሃዲግ አባላት ሥልጠና ተሰጥቷቸው ውጭ ጉዳይን መቀላቀላቸውን መረዳት ተችሏል።
አምባሳደር ቆንጅት ሥነ ጊዮርጊስ በአፍሪካ ህብረት እንዲሁም በተባበሩት መንግስታት ኢኮኖሚክ ኮሚሽን የኢትዮጲያ አምባሳደር ናቸው ከንጉሡ ግዜ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ውስጥ በማገልገል ላይ ይገኛሉ።

አቶ በረከት ስምዖን በኢትዮጲያ ፖለቲካ ውስጥ ያላቸው ሚና እየጎላ መምጣቱ እየተነገረ ነው


ህዳር ፲፭ (አስራ አምት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር አቶ በረከት ስምዖን በኢትዮጲያ ፖለቲካ ውስጥ ያላቸው ሚና እየጎላ መምጣቱ በሕወሐት ሰዎች ዝንድ ቅሬታ መቀስቀሱና በአንዳንዶችም ዝንድ ቁጣ ማስከተሉ እየተሰማ ነው አቶ በረከትም ከጀርባ ሆነው ከሚያደርጉት እንቅስቃሴ ወጥተው የፊት መስመር ላይ በግልፅ መታየት ጀምረዋል።
በጠ/ሚ/ር ኋ/ማርያም ደሳለኝ የተመራ የልዑካ ቡድን ወደ ኬንያ ናይሮቢ በተጓዘበት ወቅት የልዑኩ 2ኛ ሰው ሆነው ከኬንያው ጠ/ሚ/ር ጋር ሲፈራረሙ የታዩት አቶ በረከት ስምዖን ናቸው።አቶ በረከት ስምዖን ያላቸው ይፋዊ ስልጣን በሚንስትር ማዕረግ የኮሚኒኬሽን ፅ/ቤት ኋላፊ ሲሆን ይህም ከሁሉም የሚንስትር መስሪያ ቤቶች ዝቅ ያል ስፍራ መሆኑም ታውቋል። ሆኖም አቶ በረከት ሥምዖን በሐገሪቱ ፖለቲካ ውስጥ ያላቸው ሚና እጅግ እየገዘፈ መጥቷል።
ጠ/ሚ/ር ኋ/ማርያም ደሳለኝ ለተባበሩት መንግስታት ጉባኤ ወደ አሜሪካ ኒውዮርክ ባቀኑበት ወቅት በሐገር ቤት በሁለቱ ሱዳኖች መካከል በተካሄደው ድርድርና ሥምምነት የኢትዮጲያን ምንግስት ወክለው የተገኙት አቶ በረከት ሥምዖን ነበሩ ምክትል ጠ/ሚ/ር ሆነው የተሾሙት አቶ ደመቀ መኮንን በሐገር ቤት የነበሩ ቢሆንም በስፍራው አልታየም።
ሠሞኑን ወደ ኬንያ ከተጓዘው የኢትዮጲያ ልዑካን ቡድኑ ጋር አብረው ናይሮቢ የደረሱት አቶ በረከት ሥምዖን ከኬንያው 2ኛ ሰው ጋር ሲፈራረሙ ታይተዋል።
አቶ ኋ/ማሪያም ደሳልኝ ከሐገሪቱ ፕሬዝዳንት ሞዋይ ኪባኪ ጋር ሲፈራረሙ የኬንያው 2ኛ ሰው ጠ/ሚ/ር ራይላ ኦዲንጋ ከአቶ በረከት ሥምዖን ጋር ተፈራርመዋል።
ሚኒስቴር መስሪያ ቤት የሚመሩት የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አቶ ብርሃነ ገ/ክርስቶስ የገንዘብ ሚንስትሩ አቶ  ሦፍያን አህመድ በስፍራው የነበሩ ቢሆንም የፅ/ቤት ኋላፊው አቶ በረከት ሥምዖን ከፊታቸው ቀድመው ተገኝተዋል።
አቶ በረከት ሥምዖን በኢትዮጲያ ፖለቲካ ውስጥ እየጎሉ መምጣታቸው ከስርአቱ በተለዩትም ሆነ ከስርአቱ ጋር አብረው በዘለቁት የሕወሐት ሰዎች ዝንድ እንዳልተወደደ እየተሰማ ነው የሕወሐት ሠዎች የፊት መስመሩ ላይ በግልፅ ቁጥር አንድ ላይ ባይታዩም በፖለቲካው በኢኮኖሚውም ሆነ በፀጥታውም ያላቸው ጉልህ ሚና መጠቀሱም ታውቋል።

ESAT Daliy News Amsterdam Nov 23 2012 Ethiopia


በቤት ውዝግብ የተነሳ በሀረር አንድ አዛውንት ራሳቸውን ሰቅለው ገደሉ Email ThisBlogThis!Share to TwitterShare to Facebook Posted by yared elias brehane

ህዳር ፲፭ (አስራ አምት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:- ድርጊቱ የተፈጸመው ትናንት ህዳር 13 2012 ዓም ነው። በተለምዶ ጀጎል እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ለረጅም ጊዜ በቀበሌ ቤት ውስጥ ይኖሩ የነበሩት የጥበቃ ሰራተኛው ባሻ ስዩም ተፈራ ባለፈው ዓመት ቤታቸውን ለቀው እንዲወጡ የቀበሌው ሹማምንት ይጠየቁዋቸዋል። ባሻ ስዩምም ዘመኔን በሙሉ የኖርኩበትን ቤት ትቼ መውደቂያ ሳይኖረኝ አልወጣም በማለት መልስ ሰጥተዋል። የክልሉ ባለስልጣናትም በቅርቡ ቤታቸውን ብቻ ትተው በቤቱ ቅጥር ግቢ የሚገኘውን ቦታቸውን በመውሰድ በባሻ ላይ የመጀመሪያ ምታቸውን ሰንዝረዋል።
ህዳር 12 ተከብሮ በዋለው የሀረር ሚካኤል የንግስ በአል ላይ በሰላም ታቦት አንግሰው ወደ ማረፊያ ቤታቸው የተመለሱት አዛውንቱ ባሻ ስዩም ወደ ቤታቸው ሲቀርቡ ግን የተመለከቱት ነገር ሁሉ ግራ የሚያጋባ ነበር። የቀበሌው ባለስልጣናት ቤታቸው ሰብረው በመግባት፣ እቃቸውን ሜዳ ላይ በትነውታል። ቤታቸውንም አሽገው ሄደዋል። ባሻም ገብተው የሚያርፉበት ቤት ያጣሉ፣ ድርጊቱ አበሳጫቸው፣ ለዘመናት የኖሩበትን ቤት ያለምንም ምትክ ቤት በባለስልጣናት ተቀሙ። አዛውንቱ ባሻ ስዩም ሙሉ በሙሉ ተስፋ በመቁረጥ ህዳር 13 ራሳቸውን ሰቅለው ከዚህ አለም ጣጣ ተሰናበቱ።
በሌላ በኩል ደግሞ አንድ የባጃጅ ሹፌር በትራፊክ ፖሊሶች ተገድሏል። ሾፌሩ የተገደለው ከሰአት ውጭ እየሰራህ ነው በሚል ምክንያት ነው። ሾፌሮች ለኢሳት እንደገለጹት ሹፌሩ የተገደለው ባህር እድሪስ በተባለ ፖሊስ ትእዛዝ ነው። ግለሰቡም በቁጥጥር ስር መዋሉን ሾፌሮች ተናግረዋል።
በሀርረና በጅጅጋ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ግፉ በዛብን በማለት በተደጋጋሚ በኢሳት ላይ ሲናገሩ መደመጣቸው ይታወሳል።
በሌላ ዜና ደግሞ በአምቦ ከመሰረታዊ አግልግሎት እጥረት ጋር በተያያዘ በምሽት ወንጀሎች እየተሰሩ ነው ተባለ።
የከተማዋ ነዋሪዎች ለኢሳት እንደገለጹት የከተማዋ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች መብራት የሌላቸው በመሆኑ ሰዎች በሌሊት ይገደላሉ። ባለፈው ሳምንት በአንድ መንደር ውስጥ የተለያዩ ሰዎች ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ተገድለዋል

አፋኝ ልዩ የኮማንዶ ሃይል በምስጢር ተመረቀ!!!

አፋን ልዩ የኮማንዶ ሃይል በምስጢር ተመረቀ!!!

 የወያኔ የመከላከያ ምንጮች እንደገለጡት ወያኔ ህዝብን ለማሳፈን ከየገጠሩ የሰበሰባቸዉን አዳዲስ ምልምል ልዩ የኮማንዶ ሃይሎችን በምስጢር አሰልጥኖ አስመረቀ::

በልዩ ሃይሎች ማሰልጠኛ ካምፕ ዉስጥ ላለፉት ስድስት ወራት ልዩ የኮማንዶ ሃይሎች የተመረቁት የህንን የአፈና ቡድን በበላይነት እና በተናጠል በሚመራው በሌ/ጄነራል ሳሞራ የኑስ ነው::
ይህንን የልዩ ሃይል የኮማንዶ ጦር በከፍተኛ ወጪ ከዉጪ አገራት በመጡ አሰልጣኞች በምስጢር አሰልጥኖ ያስመረቀው ወያኔ የሕወሓቱን የጦር ኣለቃ አብርሃ ተስፋይን የልዩ ሃይሉ አዛዥ አድርጎ የሾመ ሲሆን ጦሩ በአዲስ አበባ እና ለአዲስ አበባ ቅርብ በሆኖ የጦር ካምፖች ዉስጥ እንዲሰፍር ተደርጉዋል::

በኑሮ ዉድነት..በመልካም አስተዳደር እጦት..በግዴታ መዋጮ...እየተንገላታ ያለው ሰፊው ኢትዮጵያ ህዝብ በወያኘ አምባገነን ቡድን እና በሙስና በተጨማለቁ አመራሮቹ ላይ ተቃውሞ ቢያነሳ ምላሽ ሊሰጥ የሚችል ጦር የለም በሚል ጥርጣሬ ይህንን ልዩ ሃይል ያሰለጠኑ እና ለብቻው እየተቀለበ እንዲቀመጥ በምስጢር ትእዛዝ ተሰጥቱዋል::

ጦሩ ከተመረቀ  በሁዋላ የተወሰነው በቀድሞው አይሮፕላን ማረፍያ አቅራቢያ የሰፈረ ሲሆን ይህ ተወርዋሪ ጦር በዘመናዊ መሳርያ እና ትጥክ የተደራጀ መሆኑን የ አይን እማኞች ተናግረዋል ::
የምንሊክ ሳልሳዊ ምንጮች እንዳሉትበወሓቱ አብርሃ ተስፋይ የሚመራው ይህ ልዩ ሃይል ቀጥታ ከሳሞራ የኑስ የሚሰጠውን ትዛዝ ብቻ የሚተገብር ሲሆን በወያኔ ባለስልጣናት መካከል ለሚነሳው ይፋዊ የስልጣን ሽኩቻ ሕወሓትን ወግኖ እንዲሰለፍ የተዘጋጀ ጦር ነው::

የሁለት ሐውልቶች ዕጣ



click here for pdf 
ሰሞኑን የኢትዮጵያ ሕዝብ የመነጋገርያ አጀንዳ የሆነ አንድ ጉዳይ አለ፡፡ የአቡነ ጴጥሮስና የምኒሊክ ሐውልትና የባቡሩ መሥመር ያላቸው ዝምድና፡፡ ስለ ባቡር በመዝፈን ከመቶ ዓመት በላይ ያሳለፍን ሕዝቦች የከተማ ባቡር ማግኘታችንን በዕልልታ የምንቀበለው ነገር ነው፡፡ ዘግይተን ይሆናል እንጂ አልቸኮልንም፡፡ ሥራው በቁርጠኝነት መጀመሩና ከወሬ አልፎ ሲተገበር ማየታችንም እሰዬው የሚያሰኝ ሆኗል፡፡
ግን ደግሞ  ጥያቄ አለን፡፡

ይህ የባቡር መሥመር የአቡነ ጴጥሮስንና የዐፄ ምኒሊክን ሐውልት እንዲነሡ ያደርጋል?
ለዚህ ጥያቄ ምላሹ ‹አዎን› ከሆነ ስለ ባቡሩ የሚኖረን ግምት ይለያል፡፡ ኢትዮጵያን እናሳድጋለን ስንል ያሳደጓትን እየዘነጋንና መታሰቢያቸውን እያፈረስን መሆን የለበትም፡፡ ‹በማን ላይ ቆመሽ እግዜርን ታሚያለሽ› አለ ያገሬ ሰው፡፡ የምናመጣው አዲስ ነገር ባለን ላይ የሚጨመር እንጂ ያለንን የሚያጠፋ መሆን የለበትም፡፡ መኪና ያስፈልገናል፣ ግን እግር የሚቆርጥ መሆን የለበትም፡፡ ወደድንም ጠላንም ይህች ሀገር የታሪክና የቅርስ ሀገር ናት፡፡ 

ይህ ታሪኳና ቅርሷ ደግሞ የህልውናዋም ምንጭና መሰንበቻም ጭምር ነው፡፡ ይህን ታሪክና ቅርስ እያጠፉና እያበላሹ የሚመጣ ለውጥ አንገት ቆርጦ ፀጉርን እንደማስተካከል ነው የሚቆጠረው፡፡ እናም የሚመለከታቸው ሁሉ ወደ ርምጃ ከመግባታቸው በፊት ሦስት ጊዜ ሊያስቡ ይገባል፡፡ መቼም የመጀመርያውን ባቡር ያስገቡትን የዐፄ ምኒሊክን ሐውልት አፍርሶ ባቡር እናስገባ ማለት የታሪክ ምጸት ነው፡፡ ለነጻነት የተሠውትን የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት ነቅሎ በባቡር ላይ በነጻነት ለመሄድ መከጀል ግፍ መሥራት ነው የሚሆነው፡፡
ምላሹ ‹አይደለም› ከሆነ ደግሞ እሰዬው፡፡ ግን አሁን በሐውልቶቹ አጠገብ የሚከናወነው ቁፋሮ ወደ መሠረታቸው እየሄደ ነው፡፡ እንደሚሰማውም የባቡሩ መሥመር በሐውልቶቹ ሥር የሚዘረጋ ነው፡፡ ታድያ የሐውልቶቹ ዕጣ ፈንታ ምንድን ነው? ለሕዝቡስ ግልጽ ማብራርያ የማይሰጠው ለምንድን ነው? ‹ለጊዜው ተነሥተው በኋላ ይመለሳሉ› የሚል መረጃም እየተሰማ ነው፡፡ ለጊዜውስ ተነሥተው የት ነው የሚሄዱት? በኋላስ በምን ሁኔታ ነው የሚመለሱት? ታሪካዊ ቦታቸውንስ ይለቃሉ?
ግልጽ መልስ ያስፈልጋል፡፡
እንዲያውም ሕዝቡ በመንገድ ምክንያት ቤት የፈረሰባቸው ሰዎች ኮንደሚንየም እንደሚሰጣቸው ሁሉ እነርሱም ከዚያ ቦታ ተነሥተው ኮንደሚንየም ሊሰጣቸው ይችላል እያለ መቀለድ ሁሉ ጀምሯል፡

የቀድመዋ እመቤት ጋሻ አነሱ!


ባትወጋ ፡ እንኳን፡ በል፡ እንገፍ፡ እንገፍ፤
የአባትህ፡ ጋሻ፡ ትኋኑ፡ ይርገፍ።

ይህ ለዳተኛ ልጅ የአባቱን ጅግንነት ላልተከተለ ጋሻውን ለማንሳት ላልደፈረ የተዜመ ዜማ ነበረ። የቀድመዋ ቀዳማዊት እመቤት ባለቤት አቶ መለስ ዜናዊ አዜብ መስፍንን በፓራላማቸውAzeb Mesfin former first lady of Ethiopia ላይ ‘ቆራጥ ታጋይ’ ሲሉ አወድሰዋቸው ነበር።የዳኛ ብርቱካን መዴክሳ  በታጋይነታቸው ሰማቸው በኢትዮጵያዊያ ዘንድ እየገነነ መምጣቱ፤ የባለቤታቸውን ታጋይነት ሰለአጠላበት ነው በቁጭት የተናተሩት ያሉም ነበሩ። የወያኔ ተጋዳዮችም ቀዳማዊት እመቤትን እንደ ( Popular Front  for Liberation of Palestine) ‘የፍልስጤም ሕዝባዊ ነፃነት ግንባር’  አባል የሆኑትን የእውቋንና ዝነኛዋን ሌዕላአ ካህሌድ (Leila Khaled) እንደ አስራ አምስተኛው ምዕተ ዓመት ዝነኛ ፈረሳዊት ጅግኒት የካቶሊክቱ ቅድስት ጆኖ ኦፍ አርክ (Joan of Arc) ጋር ያመሳስሏቸዋል። በተለይ ራሳቸው ላይ ጣል  የሚያደርጓት ሻሽ መሰል ኮታ ቁርጥ ሌዕላአ ካህሌድን አስመስሏቸዋል። (AK 47) ክላሽስኮብ ይዘው ፎቶ ተነሰተው በኢቲቪ  ባለመቅረባቸው ጅግንነታቸው አልታወቀም።አፈሩን ገለባ ያድርግላቸውና ባለቤታቸው ቢሆኑ የአርጀቲናዊን ማርክሲስት ቼ ኮቬራ (Che Guevara) መለያው የሆነችውን ቆብ ደፋ ያደርጉ ነበር። ይህ ከውጪ የተጨለፈ የትግል ስልት ‘የትግራይ ሕዝብ ነፃነት ግንባር’ (ሕውሃትን) ፈጥሮልናል። በቅርቡ የድርጅቱ  መስራች አቦ ሰባት ነጋም እንደነገሩን ትግራይን ለማስገንጠል ሣይሆን  የአማራውንና የኦርቶዶክ ሃይማኖት  ተከታዩን የኢትዮጵያ ሕዝብ አከርካሪ ለመስበር መሆኑን ነው።
ይህ ሁኔታ በልጅነቴ የሚነገር ተረት አስታወሰኝ። ጦጢት  ሰው የሚያደርገውን በመኮረጅና መስሎ ለመታየት በምታደርገው  ተግባሯ ትታወቃለች ። በዕውቀት ደከም ያሉትን የሕብረተሰቡን ክፍል በማታለልም ወደር የላትም። በተለይ የገበሬውን ምርት አታላ በመብላት ሌሎች እንሰሳት አይደርሱባትም። የሚያሸንፋት ተማሪ ብቻ ነው ተብሎ ይነገራል። ከዕለታት አንድ ቀን ተማሪው ጦጢት ወደአለችበት በመሄድ ከምታየው ከፈተኛ ሥፍራ ላይ ቆሞ፣ ቢላዋ አንስቶ፣ በደነዙ በኩል ማጅራቱ ከገዘገዘ በኋላ ቢላዋውን ይወረውርላታል፤ ጦጢትም ቢላዋውን አንስታ በደመ ነፍስ በስለቱ በኩል ማጅራቷን ትገዘግዛለች ፣ ደሟ ሰዥረዥር፣ እሪ ብላ ትጮሃለች፤ ተማሪው ሊረዳት ቢሞክርም ወደ ዱሯ ትነጉዳለች ። ይህ የጦጢት ታሪክ አዲሱንም ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝንም ይመለከታል።
ወደ ዋናው ወደተነሰሁበት አርዕሰት ልመለስ፤ በተጋዳይ  አካባቢ የሚፈከረው መፈክር ‘ጓድ ቢሞት ጓድ ይተካል’ ነውና ወይዘሮ አዜብ መስፍን የሟቹን ባለቤታቸውን ጋሻ አንስተዋል። አነሳሳቸው ስዕላዊና ታሪካዊ ነው። አለባበሳቸው ጥቁር በጥቁር ነው፤ የትግል ጉዞቸውን ለማያውቁ ለባላቸው ሐዘን የለበሱት ነው ብለው በየዋህነት ሊገምቱ ይችላሉ። ጥቁሩ መስከረም( Black September) (Leila Khaled) ሌዕላአ ካህሌድ  አባል የሆነችበት የፍልስጢም ድርጅት  አርማ ነው። ታጋይቱ በዚህ ዓይነት አለባበስ ይታወቃሉ። በታጋይ ነኝ አለባበስ ቀዳማዊት እመቤት በቲቪ መስኮት ብቅ በማለት ‘መለስ የትግራይ ክልል በኢንዱስትሪ ለማሳደግ የነደፈውን ጹሑፍ ስላለ ያንን በሥራ ላይ አውላለሁ’ ብለውን እርፍ አሉት። ይታያችሁ አዜብ መስፍን የፓርላማ አባል ናቸው። ባለቤታቸውም የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር በመባል ነበር የሚታወቁት፤ መግለጫቸውን ስንሰማ የትግራይ ብቻ ተጠሪ ሆኑ ብለን አዘንን። በባለቤታቸው  የቀብር ሥነሥረዓት ላይ ‘ከኢትዮጵያ ሕዝብ ሌላ ሐብት የለንም’ ብለውን ነበር።   የጠቅላይ ሚኒስትሩን ሥልጣን ስላጡት ወደ ትግራይ ኮበለሊ ያሉም አሉ።ሌሎች እንደሚሉት የተመረጡበትን  ፓርላማና አዲስ የተሾሙትን ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝን ላይ ጦርነት ማወጃቸው ነው የሚሉም አልጠፉም።
ያም ሆነ ይህ አዋጃቸውን በቁምነገር ወስደነው የትግራይ ክልል በኢንዱስትሪ አድጎ ‘በትግራይ የተሠራ’ የሚል ዕቃ  በገዛን ባልከፋን ነበር። ከሃያ ዓመት ቀደም ብሎ ቢያንስም  ቢያድግም ለፍጆታ የሚስፈልጉንን ቁሳቁሶች ማምረት ችለን ነበር። ዛሬ ግን ለወጥ ማማሳያ፣ ለቡና መቁያ፣ ለምግብ ማብሰያ፣ የምንለብሳቸው ልብሶችና ጫማዎች ሳይቀሩ  በቻይና የተሠሩ ናቸው። ይህን ያየ  በአገራቸን በሆነ ክልል ውስጥ ዕቃዎች ቢመረቱ፣ ጥጃ ጠባ ሆድ ገባ ነበር።ግን ቁምነገሩ ያ! አይደለም። ለትግራይ ሕዝብ ሲዋሽለት የነበረውን የመገንጠል አጀንዳ ፉርሽ መሆኑ ነው። በትግራይ ማስገንጠል ስም ለኤርትራ መገንጠል፣  በመቶ ሺ የሚቆጠር የትግራይ ወጣት አውደ ጦርነት  ላይ ተማግዷል። አቶ
ስባት ነጋ ‘አማራውንና የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታዩን አኮታኩተነዋል’ እንደሉትም አይደለም። በመቶ ሺዎች ያለቁበትም ባድሜ የትግራይ ክልል ሆኗል ሲባል፤ ሐቁ የኤርትራ መሆኑ ነው። በሕውሃት ወያኔ መሪነት ያጣነው የባሕር በር  እስከዘለቄታው እንደማናገኘው በቅርቡ በረከት ስምዖን በአደባባይ  ግልጽ አድርጎታል። ትግራይን   በኢንዱስትሪ  የማሳደጉ ውዥንብር  ይህን ሁሉ ጥፋት ይሸፍነው ይሆን?   የአልሞት ባይ ተጋዳዮች የጥቂት የትግራይ ጉጄሌዎች ማወናበጃና ጊዜ መግዣ እንጅ  ፋይዳ ያለው ነገር አይደለም። ኢንዱስትሪ  በትግራይ ውስጥ ለምን ተገነባ ብሎ እንቅልፍ አጥቶ የሚያድር ኢትዮጵያዊ የለም።
በትግራይ ሕዝብ ነፃነት ግንባር ስም  በመላው ሃገሪቱም ሆነ በትግራይ ሕዝብ የተፈጸመው ግፍ ታሪክ ሲያወሳው የሚኖር ነው።ዙሪያ ጥምጥም ከሚሄድ ይልቅ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ያቆራረጡትን ቆምንለት የሚሉትን የትግራይን ሕዝብ በአደባባይ ይቅርታ ይጠይቁት።
ኢንዱስ ትሪው ይቋቋም ቢባል እንኳን ወይዘሮ አዜብ መስፍን ከኢፈርት ገንዘብ ወጪ፣ አድርገው ነው ወይስ ከክልሉ ግብር አስከፍለው? ከመላውየኢትዮጵያ ሕዝብ እንደይሉ ፓርላማው አልመከረበትም፤  ያም ግልጽ አልሆነም። እያደር እንደሚታየው ወይዘሮ አዜብ በዋናነት የሚቆጣጠሩትን የኢፈርት ንብረት የራሳቸው አድርገው ከሆነ ያ ሌላ ነው። ወታደር ሊቀጥሩበት ይችላሉ። ኢንዱስትሪ የተባለው ሽፋን ነው። በአሁን ጊዜ በወያኔ አምባ የሚታየው መደነባበር እንጂ ልማት አይደለም። ወይዘሮ አዜብስ ቢሆኑ የትኛው ብቃታቸው ነው? ኢንዱስትሪ ለማቋቋም የሚረዳቸው? ከአጥፍቶ መጥፋቱ አዝማሚያ ተቆጥበው፣ የባለቤታቸውን  ሐዘን በወግ ቢወጡት ይሻላል።በለቅሷቸው ላይ  ‘አልጋው ባዶ ነው’ እንደሉት የሉምና  ካልጋዎ ወርደው ሰሌን አንጥፈው ማቅ ለብሰው  መጸለዩ ባህላዊም  ሃይማኖታዊም ነው። ከእንግዲህ ምን ዓለም አሎት? ግማሽ አካሎን አተዋል፤ ከዋልድባ ገዳም ቆብ ደፍተው መመልኮሱ ይብዛቦ? ወልቃይት  ጤገኔም ቢሆን የአባቶ ሃገር ነው፤ግን ‘ ሰው ከሚጠጣው ወኃ ምራቁን አይተፋም’ በማለት ያማርሮታል፤ የዋልድማው ገዳም ጉዳይ ገና አልተቋጨም።የኢትዮጵያ ሕዝብም ቢሆን አዝኖቦታል። ከገንዘብ ዘረፋው እስከ  ቡቃቅላ ወጣት ሴት ልጆቹን ለአረብ አገር ማሻገሩን እንደባሪያ ፈንጋይነት ቆጥሮታል።
የሚያነሱት ጋሻ የገንዘብ ፍቅርን፣ የእርኩስ መንፈስን፣ የሥልጣን ጥማትን የሚመክት መሆን አለበት።
ኢትዮጵያንና ልጆቿን ዓምላክ ይታደጋቸው። አሚን!

የ ኢህአዲግ ኢ-ሳይንሳዊ የ ልማት ፖሊሲ- የ አቡነ ጴጥሮስን እና የ አፄ ምኒልክን ሃውልት ማፍረስ የ ኢህአዲግ የ አዲስ አበባ 125ኛ አመት በዓል ስጦታ!


የ ኢህአዲግ ኢ-ሳይንሳዊ የ ልማት ፖሊሲ
  • የ አቡነ ጴጥሮስን እና የ አፄ ምኒልክን ሃውልት ማፍረስ የ ኢህአዲግ የ አዲስ አበባ 125ኛ አመት በዓል ስጦታ!

ልማት (development) የ አለም አጨቃጫቂው ፖለቲካዊ ቃና የተላበሰ ጉዳይ መሆኑ ይታወቃል። የ አለማችን ፖለቲካዊም ሆኑ ማህበራዊ ኩነቶች የተቀየሩት በ ልማት ዙርያ ከተነሱ የ ፍልስፍና አስተሳሰቦች መሆናቸውን ምንጊዜም መዘንጋት የለብንም። ከኢንዱስትሪው አብዮት በሁዋላ የተነሱት የ ካፒታሊስቱ እና የ ሶሽያልስቱ ጎራዎች የ ሀገሮችን ጆግራፊ የቀየሩት፣አዳዲስ ሃያላን መንግስታትን ያወጡት ከ ልማት ጋር በሚነሱ ፍልስፍናዎች ተሞክሮዎች እና የ ልማቱ ፍልስፍና የሚወልደው የ ፖለቲካ ስርዓት ሳብያ ነበር።የ ካፒታሊስቱ አለም የ ግል ሃብትን መሰረት ያደረገ የ ኢኮኖሚ መንገድን ሲያበረታታ ከ ጎን ዲሞክራስያዊ አሰራሮችን ይሆናል ባለው መልኩ እያደራጀ ነበር። አሁን በምንኖርበት አለም የ ምዕራቡ አለም አንድ አይነት የ ካፒታሊስት ፖለቲካ የሚከተል ከመሰለን ተሳስተናል። የ ግራ ዘመሙ፣የሶሻል ዲሞክራቱ፣ሙሉ ሊበራሉ ወዘተ መጥቀስ ይቻላል። በ ልማት ስም ህዝቦች ነፃነታቸውን አጥተዋል ፣ ለ እጅ አዙር ቅኝ ግዛት ተዳርገዋል፣የረቀቀ ደባ ተሰርቶባቸዋል። በ አለም ባንክ እና በ ታዳጊው ዓለም በ 1980ዎቹ እና 1990ዎቹ ተነስቶ የነበረው ውዝግብ ተጠቃሽ ነው። የ አለም ባንክ የ ታዳጊውን አለም የልማት መርሃግብር ከመቅረፅ ጀምሮ እስከ ማከናወን ድረስ በኃላፊነት ካልሰራሁ ያለባቸው፣ ይህንኑ ተከትሎ ብዙ የማህበራዊ እና የ ኢኮኖሚ ቀውሶች መከተላቸው ይታወሳል። በተለይ ከ ልማት ድርጅቶች የ መዋቅር ለውጥ (Structural Adjustment Policy) ጋር በተያያዘ ብዙ ሰራተኞች ከስራ እየተፈናቀሉ ለ ከፍተኛ ችግር ተዳርገው የነበረ መሆኑ አይዘነጋም።በተቃራኒው ግን በ አደጉት ሀገሮች መንግሥታት ለ ዜጎቻቸው የ ሥራ ዋስትና ለመስጠት ብዙ ሲጥሩ ይስተዋል ነበር። ሥራ ያላገኙቱ የ ማህበራዊ ዋስትና ስለተዘጋጀላቸው በ እዚሁ እንዲረዱ ይደረግ ነበር። አሁንም እየተሰራበት ነው። የ ፕሬዝዳንት ኦባማ ካፒታሊዝምም በ ምርጫ ውድድሩ አሸናፊ የሆነው የ እሳቸው የ ልማት እቅድ በ መካከለኛ እና በ ዝቅተኛ ኑሮ ላይ የሚገኘውን ሕብረተሰብ የሚደግፍ ለምሳሌ የ ጤና ዋስትና እና የ ታክስ ማሻሻያዎችን የያዘ ስለነበር ነው። ልማት ከ እቅዱ ጀምሮ እንዲህ ያነጋግራል፣ያፋትጋል። ምክንያቱም ልማት ልማት በ መሆኑ ብቻ ሊደገፍ አይችልም። ይዞ የሚመጣው ቀውስ አብሮ ተመዝኖ ብቻ ይፀድቃል።ለምሳሌ ልማቱ የ ሕዝቡን ማህበራዊ፣ሃይማኖታዊ እና ቁሳዊ መብቱን እና መገለጫዎቹን ከ ጎዳ ልማት ሳይሆን ለጊዜው የተሻለ ቃል ባላገኝለትም ጥፋት የሚለው ስም ግን ይስማማዋል።

ሁለቱሳይንሳዊልማትመሰረታዊመርሆዎች ልማት ከ ስር ወደ ላይ መከናወን አለበት (development from bottom to top ) ከስር የ ልማቱን ችግር የሚያውቀው ሕዝብ የ ልማቱ ሃሳብ አመንጪ መሆን አለበት። ኤክስፐርቶች ቢሮ ቁጭ ብለው የሚቀርፁት ልማት እታች ካለው ማህበረሰብ ጥያቄ ጋር የማይገናኝ የሚሆንበት ብዙ አጋጣሚ አለ። በመሆኑም ልማት ሲታቀድ ቢቻል ከ ህዝቡ ጋር የተለያዩ መድረክ አዘጋጅቶ ከ እቅዱ ጀምሮ እንዲያውቀው ማወያየት እና እቅዱ መስተካከል ካለበት እየተስተካከለ እንዲሄድ የ ልማት ሳይንሱ ያዛል። ”የ ልማት ሂደት ከ ስር ወደላይ የሚመጣ ግብአት አለው።ከ ታች ከ ህዝቡ የሚገኘው ግብአት እና መረጃ ለ ልማት ስትራቴጂው አስፈላጊ ነው።” (Develop process which has bottom up input – The information and input from the people on the ground are important to the development of the strateg) ‘Economic Theory and Sustainable Development, by Vincent Martinet,April 2012.
ልማት ሕዝቡን ማሳተፍ አለበት(Participatory development ) ልማት የምሰራው ሕዝብ ነው ። የ ሕዝብ አዎንታ የሌለበት ልማት ዛሬ ቢሰራ ነገ እንክብካቤ በማጣት ወይም ሆን ተብሎ በ ህዝቡ እንዲፈርስ ይደረጋል።ታንዛንያ ውስጥ አንድ ግብረ-ሰናይ ድርጅት የሰራው ሥራ ብዙ ጊዜ በ ልማት ባለሙያዎች ይነገራል። ድርጅቱ በ አንድ ገጠራማ የ ታንዛንያ መንደር የ ውሃ ጉድጉአድ ለመቆፈር ያቅድ እና ከ ነዋሪዎቹ የ 10 ደቂቃ እርቀት ላይ ውሃውን ለማውጣት በ አካባቢው ያለውን ትልቅ ዛፍ ይቆርጣል፣ ቀጥሎም ውሃው ይቆፈር እና ይወጣል። ከ እዚህ በፊት የመንደሩ ነዋሪ ውሃ የሚያገኘው ከ አንድ ሰዓት በላይ ተጉዞ ነበር እና በ ሪፖርቱ ላይ ትልቅ ስኬት መስራቱን ለዋናው ቢሮ ይነግራል። ውሃው ከተመረቀ ቀጥሎ ባሉት ቀናት ግን አሁንም የመንደሩ ሰዎች በቅርባቸው ያለውን ውሃ ትተው ድሮ ይጠጡት የነበረውን ቆሻሻ ውሃ ከ አንድ ሰዓት በላይ ሄደው መቅዳታቸውን ቀጠሉ። ጉዳዩ ሲጠና ለካ ድርጅቱ የቆረጠው ዛፍ ከ አያቶቻቸው ጀምሮ ያመልኩበት የነበረ እና አሱ ተቆርጦ የምንጠጣው ውሃ ‘ቅስፈት’ አለው ስለሚሉ ነብር። ለምን መጀመርያ አልተናገራችሁም ሲባሉ መልሳቸው ”ማን አማከረን? ባለሙያዎቹ ቀን ሲሰሩ ውለው ማታ ወደ ከተማ ሄደው ነው የሚያድሩት።” ብለው መለሱ። ልማት የ ህብረተሰቡን መልካም እሴቶች፣ሃይማኖት፣ታሪክ እና ባህል ካላከበረ ልማት ሊባል አይችልም። ኢህአዲግ-ሳይንሳዊልማትፖሊሲ ከላይ ለማውሳት አንደሞከርኩት የ አለማችን ታሪክ በ ልማት እና እድገት ዙርያ (እዚህ ላይ ልማት የሚለው ፅንሰ ሃሳብ እንደየዘመኑ የተለያየ ስም የነበረው መሆኑን ሳንዘነጋ) ፖለቲካዊ ፍልስፍናዎችን እየፈጠረ ይኑር እንጂ በተለይ አሁን ባለንበት ዘመን የ ልማት ስራዎች አተገባበር በተለይ የ ፕሮጀክት አቀራረፅ እና ማሟላት የሚገባቸው ነጥቦች ላይ ብዙም ክርክር የለም።ምክንያቱም ሳይንሳዊ መልክ በመያዙ እና አንዱ ካንዱ ተሞክሮ እያገኘ በመሆኑ ነው።በተለይ ልማት ከ ታች ወደ ላይ እና ህዝብን ያሳተፈ የሚሉት መሰረታዊ እና ቁልፍ ተግባራት ምሁራን የሚስማሙበት ፅንሰ ሃሳብ ነው። የ ኢህአዲግ ኢ-ሳይንሳዊ የ ልማት ፖሊሲን ከ አንድ የ ልማት ፕሮጀክት አተገባበር ጋር እንዴት አንደሚጣረስ እንመልከት። ኢህአዲግ ”ልማቱን እኔ አውቅልሃለሁ ” የሚል መንገድ ከመቀጠሉ እና የሚሰራው ሥራ ሁሉ በ ቢሮው ካድሬዎች እና ”እበላ ባይ ምሁራን ” በሚቀርፃቸው ፕሮጀክቶች ሀገሪቱን ወደ አደገኛ መንገድ እየመራት ይገኛል።”ዋናው ነገር ይልማ” የማይባልበት ዘመን ላይ መሆናችንን ማወቅ አለብን። የ ልማት ፕሮጀክቱ ልከለስ፣ሊስተካከል ወይንም የ ህዝብን ይሁንታ ማግኘት መቻል አለበት። ኢህአዲግ የልማት አጠገባበሮችን በ ሳይንሳዊ መንገድ መስራት ቀርቶ የሚከተሉትን የ አንድ ፕሮጀክት መገምገምያ ሰነድ ያላሟላ አሰራር ይታይበታል። -ልማቱ ህዝብን ያከበረ ልማት ነው? -ዘለቀታነት አለው ? -የሀገሪቱን ጥቅም ለ ጉዳት ይሰጣል? -ሕዝብ ተወያይቶበታል? -የ ሕዝቡን ባህል፣ታሪክ እና የ ሀገሪቱን አሻራ ያፈርሳል? እና ሌሎችም ጥያቄዎች የ ኢህአዲግ የ ልማት ፕሮግራም ለመመለስ ሞራላዊ ብቃት የለውም። ለ እዚህም ማስረጃ የሚሆነው ለ ልማት ሥራ እያለ በ ዋልድባ ገዳም ይዞታ ላይ ፣በ አፋር ሕዝብ ይዞታ ላይ፣በ ጋምቤላ ገበሬዎች፣በ አዲስ አበባ በ ሺህ የሚቆጠሩ ነዋሪዎችን ከመኖርያቸው በ ህገወጥ ስም ማፈናቀል ወዘት የተፈፀሙት ግፎች የ ልማትን መሰረታዊ ሳይንስ የጣሰ ድርጊት ብቻ ሳይሆን የ ልማቱን ግብ እና ፍላጎት በደንብ ለመጠየቅ የሚያስገድድ ወቅት ላይ መሆናችንን የሚያመለክት ነው። አንድ የ ልማት ፕሮጀችት ትክክለኛ ነው ተብሎ የሚረጋገጠው ውጭያዊም ሆነ ውስጣዊ አካባቢያዊ ሁኔታዎችን ያስማማ ሲሆን ብቻ ነው።ከ እዚህ ውጭ ፕሮጀክት ሌላ ተልኮ ከሌለው በስተቀር ፕሮጀክቱ ወደ ሥራ ሊቀየር አይችልም። የ ጉልበት ፕሮጀክት የሚሰራው በ ጦር ሜዳ ብቻ ነው። የ ልማት ፕሮጀችት የ ሁሉንም ይሁንታ እስኪያገኝ ይቆያል።

Thursday, November 22, 2012

እነ እስክንድር ነጋ በዛሬው ዕለት ፍ/ቤት ቀርበው ያለምንም ውጤት ተመለሱ



ህዳር ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ታዋቂው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እና የአንድነት ፓርቲ ም/ሊቀመንበር ወጣቱ ፖለቲከኛ አቶ አንዱዓለም አራጌን ጨምሮ በአሸባሪነት የተከሰሱ ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞች በዛሬው ዕለት ፍ/ቤት ቀርበዋል፣ ያለምንም ውጤትም ወደ እስር ቤት ተመልሰዋል።
ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ፣ አቶ አንዱዓለም አራጌ ፣ አቶ ናትናኤል መኮንን እንዲሁም አቶ ክንፈ ሚካኤል ደበበ እና ሌሎች በአሸባሪነት ተከሰው እስራት የተፈረደባቸው ኢትዮጵያውያን በዛሬው ዕለት ፍ/ቤት የቀረቡት የፍ/ቤቱን ውሰኔ ተቃውመው ለጠቅላይ ፍ/ቤት ባቀረቡት ይግባኝ ነው።
ከፍተኛ ፍ/ቤት በወጣቱ ፖለቲከኛ አንዱዓለም አራጌ ላይ የእድሜ ልክ እስራት ሲወስን ፣ በጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ላይ የ18 ዓመት እስራት ፣ እንዲሁም በሌሎች ላይ በየደረጃው የእስራት ውሳኔ መስተላለፉ ይታወሳል።
በዛሬው ዕለት ጠቅላይ ፍ/ቤት ለይግባኝ የቀረቡት እነ እስክንድር ነጋ ፍ/በቱ መዝገቡን ለመመርመር በቂ ግዜ ያስፈልገኛል በማለቱ በቀጠሮ ወደ እስር ቤት ተመልሰዋል ፣ ለታህሳስ 10/2005 ቀጠሮ መሰጠቱንም ለማወቅ ተችሎዋል።