Saturday, December 15, 2012

በዋልድባ ስቃዩ እና እንግልቱ እንደቀጠለ እንደሆነ ይነገራል



በዛሬው ታሕሳሥ ፭ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም. በESAT Radio ዘገባ መሰረት በዋልድባ ገዳም አካባቢ መንግሥት የተለያየ ሙከራዎችን እያደረገ እንደሚገኝ እና በገዳማውያኑ ላይ ስቃዩን እንደቀጠለ ይነገራል። ባለው ወር ላይ የገዳሙን አባቶች ጥቂት የመንግሥት ባለሥልጣናት ሰብስበው እንዳነጋገሯቸው እና ለጥር ፬ ቀን ቀጠሮ ሰጥተዋቸው እንደተበተነ ይታወሳል። በመጪው ጥር ፬ ቀን ምን ሊመጣ እንደሚችል በገዳማውያኑ ላይ ሊደርስባቸው የሚችሉትን፣ እንደ መንግሥት ባለሥልጣኖች አባባል በጥር ፬ ቀን በሚደረገው ስብሰባ ላይ የመንግሥት ተወካዮች ለገዳሙ አባቶች “ለቦታው ካሳ ተቀበሉ አለበለዚያ ሌላ ነገር ይመጣል” በማለት ገዳማውያኑን ለማስፈራራት ቢሞክሩም፥ ገዳማውያኑም “ሞትም ቢመጣ እኛ የአባቶቻችንን ርስት አሳልፈን አንሰጥም፣ እኛን ገላችሁ ሥራችሁን መስራት ትችላላችሁ” በሚል ሁኔውን እየተጠባበቁ ይገኛሉ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ መንግሥት የገዳሙን ይዞታ የቋርፍ (የገዳማውያኑ ምግብ) የሚመረትበትን ቦታ ወስዶ ስላረሰው ገዳማውያኑ በከፍተኛ የረሃብ አደጋ ተጋልጠዋል፥ ከዚህ በተጨማሪ የገዳማውያኑ የሳር ቤት ክዳን ባለው ቤት ላይ ተባይ በማፍራቱ ገዳማውያኑን ለተጨማሪ አደጋ ተዳርገዋል። ከዋልድባ ዳልሻህ ኪዳነ ምሕረት የአንድነት ገዳም ሦስት የመነኮሳይት ቡድን ወደ አዲስ አበባ ተልኮ የአስቸኳይ የምግብ እርዳታ ለመጠየቅ መጥተው እንደነበር እና ነገር ግን ከቤተክህነቱም ምንም ዓይነት ድጋፍ ሳይደረግላቸው መነኮሳይቱ ወደ ባዕታቸው ለመመለስ ችለዋል።
ዋልድባን ለመታደግ የተቋቋመው ኮሚቴ በወቅቱ ለነበረው ችግር በጊዚያዊነት ለገዳማውያኑ መጠነኛ የገንዘብ እርዳታ እና የመነኮሳይቱን ቡድን ወደ ባዕታቸው የሚመለሱበትንም የትራንስፖርት ሁኔታ አመቻችቶ ወደ ባዕታቸው ለመመለስ ችለዋል።
እግዚአብሔር አምላክ መናንያኑን በገዳም ያጸና፥ እኛንም በሃይማኖት ያጽናን አሜን።
ራዲዮን ፕሮግራሙን ለማዳመጥ ይጫኑ

No comments:

Post a Comment