ታህሳስ ፮(ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:- ታህሳስ 4 ቀን 2005 ዓም ማንነቱ ያልታወቀው ግለሰብ የተገደለው በወንጀል ተጠርጥሮ ከተያዘ በሁዋላ ነው። ግለሰቡን ተኩሶ የገደለው ፖሊስ በስም አልታወቀም። ይሁን እንጅ የወረዳው ፖሊስ ግለሰቡ ሊያመልጥ ሲል ተገደለ የሚል ምክንያት መስጠቱን ለማወቅ ተችልኦል።
የተርጫ ዞን የፖሊስ አዛዥ የሆኑት ኮሚሽነር አለማየሁ ጦፉ ግድያ መፈጸሙን ባይሸሽጉም ፣ ዝርዝሩን ከስብሰባ እንደወጡ እንደሚሰጡ ቢገልጹም ስቱዲዮ እስከገባንበት ጊዜ ድረስ ልናገኛቸው አልቻልንም።
በማረቃ ወረዳ የሚፈጸመው የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ከፍተኛ ደረጃ በመድረሱ ህብረተሰቡ በተደጋጋሚ ሲያማርር ይሰማል። መምህር የኔሰው ገብሬ ፍትህና ዲሞክራሲ በሌለበት አገር አልኖርም በማለት ራሱን አቃጥሎ ከገደለ ወዲህ ፣ ከ6 ያላነሱ ሰዎች ራሳቸውን በመስቀል እና ወደ ገደል በመወርወር መግደላቸው ይታወሳል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በአራት ኪሎ አካባቢ ቤታችሁን ልቀቁ በሚል ሰዎች መደብደባቸውን ነዋሪዎች ገልጸዋል። ከአሰብ አካባቢ ተፈናቅለው በአራት ኪሎ አካባቢ የሰፈሩ አንድ 70 አመት አዛውንት መደብደባቸውን የአይን እማኞች ገልጸዋል።
No comments:
Post a Comment