Thursday, December 20, 2012

የባለስልጣናት የሃብት ምዝገባ መረጃ ከሕዝብ እንደተደበቀ ነው


ታህሳስ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-በፌዴራል የሥነምግባርና ጸረሙስና ኮሚሽን ሥር የሚገኘው የባለሥልጣናት የመንግስት የሥራ ኃላፊዎችን ሃብትና
ንብረት ለመመዝገብ የተቋቋመው ቢሮ እስካሁን የ50ሺ ባለስልጣናትን ሃብት መመዝገቡን ሰሞንን በመንግስት መገናኛ
ብዙሃን ቢገልጽም የአንዳቸውንም የሃብት መረጃ ለሕዝብ ይፋ እንዳላደረገ ምንጮች አስታወቁ፡፡
በሃብት ማሳወቅና ምዝገባ አዋጅ ቁጥር 668/2002 መሰረት የተቋቋመው ይህው ቢሮ የመንግስት ባለስልጣናትና ተሿሚዎችን ሃብትና ንብረት በመመዝገብና በማደራጀት ለሕዝብ ይፋ ማድረግና ባለስልጣናቱም ከገቢያቸው በላይ ሃብት አፍርተው ሲገኙ ለፍርድ ማቅረብ ከተልዕኮዎቹ መካከል ይገኙበታል፡፡
ሆኖም ከአንድ ኣመት በፊት ምዝገባው ሲጀምር የባለስልጣናቱን ንብረትና ሃብት ዝም ብሎ ከመመዝገብ ባለፈ ከየት አመጣህ ብሎ የመጠየቅ ኃላፊነት(ማንዴት) እንደሌለው ማስታወቁ የምዝገባውን ፋይዳ ጥያቄ ምልክት ውስጥ ከማስገባቱም በላይ፣በሌብነት የሚጠረጠሩ ባለስልጣናት የድርሻቸውን ከወሰዱ በኃላ የሰረቁትን ማስመዝገብ እንዲችሉ አድርገው ሕጉን አወጡ የሚል ትችትን አስከትሎበታል፡፡
በአዋጁ መሰረት የቀድሞ ጠ/ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊን ጨምሮ ሚኒስትሮች፣አምባሳደሮች፣የፓርላማ አባላትና ሌሎች
ባለስልጣናት ሃብታቸውን ያስመዘገቡ ሲሆን ፣ ሰዎቹ ያስመዘገቡት ሃብት ምን ያህል ከገቢያቸው ጋር የተመጣጠነ ነው?
የሃብት ምንጩስ ምንድነው የሚለውን ለሕዝብ ይፋ ማድረግ የነበረበት ቢሆንም እስካሁን ይፋ ሳያደርግ መቆየቱ
የመዝጋቢውን አካል ነጻነት ጥያቄ ውስጥ ጥሏል፡፡
በአዋጁ ላይ በኮሚሽኑ እጅ የሚገኝ የማንኛውም የተሿሚ፣የተመራጭ፣ ወይም የመንግስት ሰራተኛ የሃብት መረጃ ምዝገባ ለህዝብ ክፍት እንደሚሆን ቢደነግግም የቤተሰብ ሃብትን የሚመለከት መረጃ በሚስጢር እንደሚያዝ በመደንገጉ የምዝገባው አስፈላጊነት ገና ከጅምሩ ጥያቄ ላይ የጣለ ጉዳይ ነበር፡፡ ይህም ሆኖ የባለስልጣኑ የራሱ የምዝገባ መረጃ እንኳን ለህዝብ ይፋ አለመሆኑ ምዝገባው የይስሙላ ነው የሚለውን የሚያጠናክር መሆኑን ምንጫችን ጠቅሷል፡፡
በአሁኑ ወቅት ጥቂት የማይባሉ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት በራሳቸውና በዘመዶቻቸው ስም ከፍተኛ ሃብት ያካበቱ
ሲሆን በሚኒስትር ደረጃ የተቀመጡ ሹማምንት ሳይቀሩ በመንግስት ቤት እየኖሩ የግል መኖሪያ ቤታቸውን በከፍተኛ
ገንዘብ በአደባባይ በማከራየት በመነገድ ላይ መሆናቸው ይታወቃል፡፡
ጥቂት የማይባሉ ባለስልጣናት የገቢ ምንጫቸው እንኳን በትክክል በማይታወቅ መንገድ ከፍተኛ ገቢ የሚያገኙና ልጆቻቸውን በአገር ውስጥና በውጪ አገር በከፍተኛ ወጪ የሚያስተምሩ መሆናቸው የሚታወቅ ነው፡፡
የፌዴራል የስነምግባርና ጸረሙስና ኮሚሽን ሃብት እየመዘገብኩ ነው ቢልም ይህንን ዓይን ያወጣ ሙስናና በስልጣን መባለግ ደፍሮ ለማጋለጥ ባለመቻሉ ዛሬም ጥርስ የሌለው አንበሳ የሚለውን ስሙን ማደስ

    No comments:

    Post a Comment