Monday, December 31, 2012

ሽምግልናውን ሲያካሒድ ከነበሩ አስታራቂዎች የቤተክርስትያን ኣባቶች መካከል ኣንደኛው ከኢትዮጲያ ሲባረሩ ሁለተኛው የደረሱበት ኣይታወቅም


ታህሳስ  ፳፪(ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የኣዲስ ኣበባዎቹ ተደራዳሪ ኣባቶች ባለፈው ሳምንት ያወጡት መግለጫ ተገደው የፈረሙበት መሆኑም ተገለጸ።በቅርቡ በዳካስ ቴክሳስ የረካሄደውን ሶስተኛ ዙር በሶሳንጀለሰ ካሊፎርንያ ለማካሔድ ቀጠሮ ይዘው ከተነሱት ኣባቶች ኣንደኛው የሆኑት ብጹነ ብጹነ ኣቡነ ገሪማ በገጠማቸው የጤና ችግር ኣሁንም በዮኤስ ኣሜሪካ አንደሚገኙ ለማወቅ ተችሉኣል።ቅዳሜ ታህሳስ 20/2005 ኣሜሪካ የደረሱት ሊቀ ካህናት ኃይለሰላሴ ኣለማየው ታግደው መባረራቸውን ለሾይስ ኦፍ ኣሜሪካ የአማርኛ አገልግሎት አረጋግጠዋል::
ከርሳቸው ጋር አብረው የተጎዙት ሌላው የሽምግልና ቡድን አባል ዲያቆን አንዱአለም ዳግማዊ በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኑ የታወቀ ነገር የለም ፡ ሊቀካህን ሀ/ስላሴ ከእስር ተርፈው የተባረሩት የአሜሪካ ዜጋ በመሆናቸው እንደሆነም ተመልክቶል::
ይህ በእንዲህ እንዳለም ከአዲስ አበባ ተወክለው በድርድሩ ተሳታፊ የነበሩት አባቶች ታህሳስ 13/2005 በአስታራቂ ኮሚቴው ላይ ያወጡትን መግለጫ ተገደው መፈረማቸውን ደጀሰላም ዘግቦል:: አባቶቹ ኤምባሲ መጠራታቸውን መዘገባችን ይታወሳል::
ከደጀሰላም ዘገባ መረዳት እንደተቻለው አባቶቹ የተጠሩት አስታራቂውን ቡድን በሚያወግዘው መግለጫ ላይ ፊርማቸውን እንዲያሳርፉ ነው::
ይህንን በማቀነባበር አቢይ ሚና የተጫወቱት የልኡኩ ቡድን አባል ንቡረእድ ኤሊያስ አብርሀ መሆናቸውም በዘገባው ተመልክቶል::
በሌላም በኩል የሀገር ቤቱ ልኡክ አባል ብፁእ ዶ/ር አቡነ ገሪማ በደረሰባቸው የጤና ችግር በአሜሪካ ህክምና በመከታተል ላይ ናቸው::
አቡነ ገሪማ በገጠማቸው የጤና ችግር ምእመናን ለህክምና መዋጮ እያሰባሰቡ ይገኛሉ::

    No comments:

    Post a Comment