Monday, December 31, 2012

የጎንደር ዩኒቨርስቲ የተማሪዎች ዲን ተማሪዋን አስገድደው ደፈሩ


ታህሳስ  ፳፪(ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የተማሪዎች ዲን የሆኑት አቶ ናትናኤል ህዳር 27 ቀን 2005 ዓ,ም የሚያስተምሯትን ተማሪ ስልክ በመደወል ከምሽቱ 1፡30 ገዳማ ቢሯቸው ድረስ ካስጠሩ በኋላ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል እንደፈጸሙባት ከጎንደር ያገኘነው ዜና ያስረዳል።
የተደፈረችው ተማሪ በግሏ ጥረት ወደ ዩኒቨርስቲው ሆስፒታል በመሄድ አስፈላጊውን የህክምና ምርመራ ያደረገች ሲሆን የምርመራው ውጤትም ተማሪዋ የአስገድዶ መደፈር ሰላባ መሆኗን የሚያረጋግጥ ነው።
ተማሪዋን አስገድደው የደፈሩት ግለሰብ ያላቸውን የኃላፊነት ቦታ እንዲሁም የዩኒቨርስቲው ከፍተኛ አመራር የሆኑ ወዳጆቻቸውን በመጠቀም የምርመራ ውጤቱን ማስረጃ ከዩኒቨርስቲ ሆስፒታሉ ደብዛውን ለማጥፋት ቢሞክሩም ተጠቂዋ የህክምና ምርመራ ውጤቷን አስቀድማ በመውሰዷ ሳይሳካላቸው ቀርቷል።
የተጠቃችው ተማሪ የህክምና ውጤቱን ማስረጃ በመያዝ ታህሳስ 12 ቀን 2005 ዓ,ም ለጎንደር ከተማ አስተዳደር 6ኛ ፖሊስ ጣቢያ ያመለከተች ቢሆንም ፖሊስ መረጃውን ተቀብሎ ምንም አይነት እርምጃ ሳይወስድ የቆየ ሲሆን የተጠቂዋ ተማሪ ቤተሰቦችና አንዳንድ መምህራን ባደረጉት ከፍተኛ ጥረት እና ጫና ታህሳስ 20 ቀን 2005 ዓ,ም ከቀኑ 9፡00 ገዳማ ተጠርጣሪው አቶ ናትናኤል በፖሊስ ተይዘው እንዲታሰሩ ተደርጓል።
ይህ ከሆነም በኋላ የ6ኛ ፖሊስ ጣቢያ ፖሊስ አባላት ከጎንደር ዩኒቨርስቲ የአስተዳደር ም/ፕሬዝዳንት ከሆኑት አቶ ሰለሞን አብርሃ ጋር በመሆን ወንጀሉን ለማድበስበስ እና ተጠቂዋ ተማሪን በተደጋጋሚ ስልክ እየደወሉና እየተገናኙ ጫና በመፍጠር ልጅቷ ክሷን እንድታቆምና ነገሩን በእርቅ አሳበው የወንጀሉን ዱካ ለማጥፋት እየተሯሯጡ ይገኛሉ።
የልጆቿን ሁኔታ በቅርበት የሚከታተሉ ግለሰቦችም ደፍረዋል የተባሉት ግለሰብ ያላቸውን ፖለቲካዊ ተሳትፎ እና መንግስታዊ ስልጣን ተጠቅመው ወንጀሉን በቀላሉ እንዲጠፋ ሊያስደርጉ ይችላል የሚል ስጋት እንዳላቸው ገልጸዋል።
አስገድደው ደፍረዋል ተብለው የተጠረጠሩት የተማሪወች ዲን የሆኑት አቶ ናትናኤል ልጅና ሚስት ያላቸው ሲሆን ወደ ጎንደር ዩኒቨርስቲ ከመግባታቸው በፊት በደቡብ ጎንደር ዞን ውስጥ በወረዳ ካቢኔነት አገልግለዋል።
ለገዢው ፓርቲ ባላቸው ታማኝነትና አገልጋይነት በቀላሉ የዩኒቨርስቲ መምህር መሆን የቻሉ ሲሆን ግለሰቡ ለገዢው ፓርቲ በዩኒቨርስቲው ውስጥ በሚሰሩት የፖለቲካ ስራ ያለ ትምህርት ዝግጅታቸው እና ያለ ብቃታቸው የተማሪወች ዲን መሆን ችለዋል።
በጎንደር ዩኒቨርስቲ ውስጥ በዩኒቨርስቲው አመራሮች የሚፈጸመው ሙስና ከልክ እያለፈ መምጣቱን የግቢው ሰራተኞች ይናገራሉ።

አቶ ጁነዲን ሳዶ ያለመከሰስ መብታቸው እንዲነሳ የሚጠይቅ ደብዳቤ ለፓርላማ መቅረቡ ተገለጠ


ታህሳስ  ፳፪(ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ከሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትርነታቸውና ከኢህአዲግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልነታቸው የተባረሩት አቶ ጁነዲን ሳዶ ያለመከሰስ መብታቸው እንዲነሳ የሚጠይቅ ደብዳቤ ለፓርላማ መቅረቡ ተገለጠ::
ሪፖርተር ጋዜጣ በሮብ እትሙ የምክር ቤቱ የቅርብ ምንጮቹን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው አቶ ጁነዲን ሳዶ በፓርላማ የስነስርአት ደንብ መሰረት ሊጠየቁበት የሚችል የህግ ጉዳይ ሊኖር ስለሚችል በም/ቤቱ አባልነታቸው ያገኙትን ያለመከሰስ መብት ም/ቤት እንዲያነ ሳ በመንግስት ተጠይቆል::
ም/ቤቱ ሀሙስ እለት ባካሄደው ስብሰባ በአምስት አጀንዳዎች ለመወያየት አቅዶ እንደነበር ያመለከተው ሪፖርተር በአራቱላይ ብቻ ተወያይቶ የምክር ቤት አካልን የህግ ከለላ ስለማንሳት የቀረበ የውሳኔ ሀሳብን መርምሮ ማጽደቅ የሚለውን አጀንዳ በቀጣይ ስብሰባ እንመለከታለን በሚል መዝለሉን አስረድቶል::
የምክር ቤቱ አባላት ለጉባኤው የሚቀርቡ አጀንዳዎችን ቀደም ብሎ በማወቅና ሰነዶች ካሉ ሰነዶቹ ከውይይት ሶስት ቀን በፊት እንዲደርሳቸው የምክር ቤቱ ደንብ ያዛልያለው ዘገባ የህግ ከለላን ስለማንሳት ቀርቦ የስለነበረው አጀንዳ የቀረበላቸው ምንም ነገር እንደሌለ ገልጠዋል::
የህግ ከለላው እንዲነሳ ጥያቄ የቀረበበት አባል ስም በይፋ አለመገለጡን ያመለከተው ሪፖርተር ምንጮቹ ግን የአቶ ጁነዲን ሳዶ ስለመሆኑ መግለጻቸውን ጽፎል:፡
የአቶ ጁነዲን ሳዶ ባለቤት በአሸባሪነት ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙ ሲሆን አቶ ጁነዲን ሳዶ ከመንግስትም ከፓለቲካም ስልጣናቸው መነሳታቸው እታወቃል::

ሽምግልናውን ሲያካሒድ ከነበሩ አስታራቂዎች የቤተክርስትያን ኣባቶች መካከል ኣንደኛው ከኢትዮጲያ ሲባረሩ ሁለተኛው የደረሱበት ኣይታወቅም


ታህሳስ  ፳፪(ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የኣዲስ ኣበባዎቹ ተደራዳሪ ኣባቶች ባለፈው ሳምንት ያወጡት መግለጫ ተገደው የፈረሙበት መሆኑም ተገለጸ።በቅርቡ በዳካስ ቴክሳስ የረካሄደውን ሶስተኛ ዙር በሶሳንጀለሰ ካሊፎርንያ ለማካሔድ ቀጠሮ ይዘው ከተነሱት ኣባቶች ኣንደኛው የሆኑት ብጹነ ብጹነ ኣቡነ ገሪማ በገጠማቸው የጤና ችግር ኣሁንም በዮኤስ ኣሜሪካ አንደሚገኙ ለማወቅ ተችሉኣል።ቅዳሜ ታህሳስ 20/2005 ኣሜሪካ የደረሱት ሊቀ ካህናት ኃይለሰላሴ ኣለማየው ታግደው መባረራቸውን ለሾይስ ኦፍ ኣሜሪካ የአማርኛ አገልግሎት አረጋግጠዋል::
ከርሳቸው ጋር አብረው የተጎዙት ሌላው የሽምግልና ቡድን አባል ዲያቆን አንዱአለም ዳግማዊ በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኑ የታወቀ ነገር የለም ፡ ሊቀካህን ሀ/ስላሴ ከእስር ተርፈው የተባረሩት የአሜሪካ ዜጋ በመሆናቸው እንደሆነም ተመልክቶል::
ይህ በእንዲህ እንዳለም ከአዲስ አበባ ተወክለው በድርድሩ ተሳታፊ የነበሩት አባቶች ታህሳስ 13/2005 በአስታራቂ ኮሚቴው ላይ ያወጡትን መግለጫ ተገደው መፈረማቸውን ደጀሰላም ዘግቦል:: አባቶቹ ኤምባሲ መጠራታቸውን መዘገባችን ይታወሳል::
ከደጀሰላም ዘገባ መረዳት እንደተቻለው አባቶቹ የተጠሩት አስታራቂውን ቡድን በሚያወግዘው መግለጫ ላይ ፊርማቸውን እንዲያሳርፉ ነው::
ይህንን በማቀነባበር አቢይ ሚና የተጫወቱት የልኡኩ ቡድን አባል ንቡረእድ ኤሊያስ አብርሀ መሆናቸውም በዘገባው ተመልክቶል::
በሌላም በኩል የሀገር ቤቱ ልኡክ አባል ብፁእ ዶ/ር አቡነ ገሪማ በደረሰባቸው የጤና ችግር በአሜሪካ ህክምና በመከታተል ላይ ናቸው::
አቡነ ገሪማ በገጠማቸው የጤና ችግር ምእመናን ለህክምና መዋጮ እያሰባሰቡ ይገኛሉ::

    ESAT Daliy News-Amsterdam Dec. 31 2012 Ethiopia


    Sunday, December 30, 2012

    ESAT Weekly News 30 December 2012


    ተቃዋሚ ፓርቲዎች በምርጫ ቦርድ ላይ ሚስጥራዊ ያሉዋቸውን ሰነዶች ይፋ አደረጉ


    የቦርዱ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር የኢሕአዴግ ዕጩ ሆነው የተወዳደሩበትን ሰነድ አቀረቡ
    - የምርጫ አስፈጻሚዎች ለኢሕአዴግ የአባልነት መዋጮ የከፈሉበት ሰነድ አለን ይላሉ
    - አንድ ለአምስት አደረጃጀት ለምርጫ ቅስቀሳ እየዋለ ነው በማለት ኮነኑ
    በየማነ ናግሽ
    መድረክንና መኢአድን ጨምሮ ዋነኛ ተቃዋሚዎች የተሰባሰቡበት 33 የፖለቲካ ፓርቲዎች ያቋቋሙት ጊዜያዊ ኮሚቴ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ለፓርላማው አፈ ጉባዔ ክስ እንደመሠረቱበት ገልጸው፣ አገኘናቸው ያሉዋቸውን አንዳንድ ሚስጥራዊ ሰነዶች ይፋ አደረጉ፡፡
    በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ግንባር (መድረክ) ጽሕፈት ቤት የፓርቲዎቹ ጊዜያዊ ኮሚቴ ባለፈው ሐሙስ ለአገር ውስጥና ለውጭ ጋዜጠኞች በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፣ አንዳንድ ሚስጥራዊ ያላቸውን ሾልከው የወጡ ሰነዶችን ይፋ በማድረግ፣ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባለፈው ሳምንት ለቅሬታቸው ማስረጃ የላቸውም ማለቱን አስተባብለዋል፡፡
    “የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ላቀረብናቸው 18 ጥያቄዎች የሰጠው ምላሽ ቦርዱ የገዥው ፓርቲ ወገንተኛና ጉዳይ አስፈጻሚ ለመሆኑ ማረጋገጫ ነው፤” በሚል ርዕሰ ጊዜያዊ ኮሚቴው ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ቀጣዩ ምርጫ ፍትሐዊ እንዲሆን እንነጋገርበት በሚል ለቦርዱ 18 የቅሬታ ጥያቄዎችን ቢያቀርብም፣ “አንዳቸውም በማስረጃ የተደገፉ አይደለም” በሚል በተሰጣቸው ምላሽ ውድቅ ማድረጉን ገልጸዋል፡፡
    ምርጫ ቦርድ በተቃዋሚ ፓርቲዎች የቀረበለትን ቅሬታ ለአንድ ወር ያህል ከገመገምኩ በኋላ በሚል የሰጠው ምላሽ አሳፋሪና ነገ በሕዝብ የሚያስጠይቅ ነው ያሉ ሲሆን፣ ማስረጃ እንዲያቀርቡ ሳይጠይቃቸውና ተወካዮቻቸውን ሳያነጋግር ውሳኔውን ያሳወቃቸው ለመንግሥት መገናኛ ብዙኃን መግለጫ በሰጠበት ወቅት መሆኑን አስረድተዋል፡፡
    በምርጫ ቦርድ ምላሽና በምላሽ አሰጣጡ አግባብነት የተበሳጨው የ33 ፓርቲዎች ጊዜያዊ ኮሚቴ፣ ቦርዱን በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ በፓርላማ አፈ ጉባዔው ላይ ክስ እንደመሠረተበት አስታውቋል፡፡ በሌላ በኩል ማስረጃ ያላቸውን ለጋዜጠኞች ይፋ አድርጓል፡፡ “በታሪክም በኢትዮጵያ ሕዝብ ፊትም የሚያስተዛዝብና የሚያስጠይቅ ነው፤” ባለበት በዚሁ መግለጫ፣ “ለመሆኑ መቼ መድረኩ ተከፍቶ ተወያይተን? ማስረጃ ለማቅረብ ተጠይቀን ማቅረብ አለመቻላችን ታየና ነው እንዲህ ሊባል የተቻለው?” በማለት በጥያቄ ለተነሳው ጉዳይ የኮሚቴው አባላት ምላሽ የሰጡት ማስረጃ ያሉትን በማቅረብ ነበር፡፡
    የኮሚቴው ዋና ጸሐፊ አቶ ግርማ በቀለ መግለጫውን አንብበው ከጨረሱ በኋላ፣ “ማስረጃችሁ ምንድን ነው? ምን አዲስ ነገር ይዛችኋል?” በሚል ከሪፖርተር ለቀረበላቸው ጥያቄ ቀድመው ምላሽ የሰጡት የኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ አስራት ጣሴ፣ “አንድም ማስረጃ የሌለው ቅሬታ አላቀረብንም፡፡ ቦርዱ ግን የኢሕአዴግ ጉዳይ አስፈጻሚ ሆኗል፡፡ ፈጽሞ አላነጋገረንም፤ ማስረጃ እንድናቀርብም አልጠየቀንም፤” ብለዋል፡፡
    የኮሚቴው አባልና የመድረክ አመራር አባል አቶ ገብሩ ገብረማርያም በበኩላቸው፣ ለእያንዳንዱ ቅሬታ ማስረጃ መያዛቸውን ያረጋገጡት፣ የቦርዱ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወይዘሮ የሺ ፈቃደ በተለያዩ ሚዲያዎች እንደ ኢሕአዴግ ሆነው ሲከራከሩዋቸው ቆይተው አሁን የኢሕአዴግ አባል የሆኑበት ማስረጃ መገኘቱን በማሳወቅ ነበር፡፡
    “በወይዘሮ የሺ ላይ ግላዊ ጥላቻ ኖሮን አይደለም፡፡ ነገር ግን የኢሕአዴግ አባላት ሥራ አስፈጻሚ የሆኑበት ምርጫ ቦርድ ገለልተኛ ሆኖ ምርጫ ማከናወን አይችልም፤” ብለዋል፡፡ በኃላፊዋ ላይ ለምን እንዳተኮሩ ከኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሲሰጡ፣ ማስረጃውን ይዘዋል የተባሉት የኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ አቶ ወንድማገኝ ደነቀ ንግግራቸውን የጀመሩት በእጃቸው አንድ ሰነድ ከፍ አድርገው በማመልከት ነበር፡፡ በ1997 ዓ.ም. በተካሄደው አገራዊ ምርጫ “የክልል ምክር ቤት አባላት የምርጫ ጣቢያ የድምፅ ቆጠራ ውጤት መተማመኛ” በሚል የምርጫ ቦርድ ዓርማ ያለበት ሰነድ የዕጩ ተወዳዳሪዋ የወይዘሮዋ የሺ ፈቃደ ስም የሚገኝበት፣ በብአዴን ፓርቲ በንብ ምልክት ያገኙት የድምፅ ብዛትና ደረጃቸው የሰፈረበትና ለአማራ ክልል ምክር ቤት የደብረ ብርሃን ዕጩ ተወዳዳሪ ሆነው መቅረባቸውን የሚያሳይ ነው፡፡
    ወይዘሮ የሺ በቀረበው ማስረጃ ላይ አስተያየት እንዲሰጡን ጠይቀናቸው፣ “ይህ ማስረጃ ለምርጫ ቦርድ አልቀረበም፡፡ የምሠራው ለቦርዱ ነው፡፡ ቦርዱ ይህ ማስረጃ ቀርቦለት ጥያቄ ሲያቀርብልኝ ብቻ ምላሽ የምሰጥበት ይሆናል፤” በማለት የቀረበው ማስረጃ እውነተኛ ነው አይደለም ሳይሉ ለጥያቄው ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል፡፡
    ሌላ የኮሚቴው አባል አቶ ለገሠ ላንቃም የሲዳማ ዓርነት ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ተወካይ ሲሆኑ፣ በርካታ ማስረጃዎችን ማቅረባቸውን ተናግረዋል፡፡ ከእነዚህም መካከል በደቡብ ክልል የቦርባ ምርጫ ክልል ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ሲሠሩ የቆዩት አቶ ዮሐንስ አብርሃም የተባሉ ግለሰብ፣ የደኢሕዴን (ኢሕአዴግ) አባልነት መዋጮ የከፈሉበት ሰነድ ይገኝበታል፡፡ ብዙዎቹ ምርጫ አስፈጻሚዎች የፓርቲ አባላት መሆናቸውን ማሳያ ነው በማለት ነበር ያቀረቡት፡፡ ሌሎች ማስረጃዎች እንዳሏቸው በመጠቆም ጭምር፡፡ በምርጫ 2002 የነበረው ሁኔታ ምንም አለመቀየሩንና በተመሳሳይ መንገድ እየተካሄደ መሆኑን የገለጹት አቶ ለገሠ፣ በተለይ “በወቅቱ የአርቤጎና ወረዳ ምርጫ ሥራን ለማሳካት የወጣ አጭር ማስፈጸሚያ ቼክ ሊስት” በሚለው ሰነድ፣ የክልሉ ገዥው ፓርቲ ከወረዳ ማዕከል እስከ ቀበሌ የሚሠሩ ተግባራትን ያካተተ ነው፡፡ “ለልማት የፈጠርነውን የልማት ሠራዊት ወደ ምርጫ ተግባር አንድ ለአምስት በማዟዟር” በሚል የአንድ ሳምንት አደረጃጀት እንዴት ለቅስቀሳና ለምርጫ እንደሚውል፣ የሴቶችና የወጣቶችን የቀበሌ አደረጃጀቶች እንዴት መጠቀም እንደሚቻል፣ ትምህርት ቤቶችንና የሃይማኖት ተቋማት እንዴት ማንቀሳቀስ እንደሚቻል የሚያብራራ ጽሑፍም አሳይተዋል፡፡ ይኼው ሰነድ ፓርቲውን ሳያወላውል የሚመርጠውን “A” አቋሙ ተለይቶ ያልታወቀውን “B” በማለት፣ ፈጽሞ የለየለትን ተቃዋሚ ደግሞ “C” እንደሰጠ ገልጸው፣ ወደ “A” ለማምጣት ጠንካራ ሥራ መሥራት እንደሚያስፈልግ ያመለክታል ካሉ በኋላ፣ የማይመርጡትን ምን እንደሚሠሩ “በዓይነ ቁራኛ” የቅርብ ክትትል ማድረግ ይጠይቃል በማለት አስረድተዋል፡፡
    ሌሎች አባላትም ባለፈው ምርጫ ቤታቸው የተቃጠለባቸውን፣ ተገደሉ ያሉዋቸውን ሰዎችና ለእስር የተዳረጉትን ስም እየጠቀሱ ያቀረቡ ሲሆን፣ ይኼም እስካሁን በግልጽ እየተሠራበት መሆኑን አስረድተዋል፡፡
    “መንግሥት አንድ ፓርቲ አንድ አገር ብሎ ያውጅና ቁርጣችንን እንወቅ፤” ያሉት አቶ ገብሩ ገብረማርያም፣ “ጥያቄያችን ከ80 ሚሊዮን ሕዝብ ውስጥ ኢሕአዴጋዊያን ያልሆኑ ለምርጫ ቦርድ ይሥሩ የሚል ነው፤” በማለት፣ የኢትዮጵያ ሕዝብና ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ይኼንን የተበላሸ የምርጫ ሥርዓትና አምባገነንነት በመቃወም ከጐናቸው እንዲቆም ጠይቀዋል፡፡
    ምርጫ ቦርድ ፓርቲዎቹ ያቀረቧቸው አቤቱታዎችም ሆኑ ቅሬታዎች በማስረጃ ያልተደገፉና ብዙዎችም በ2002 ምርጫ ማግስት በፍርድ ቤት ሳይቀር መልስ የተሰጠባቸው ናቸው ይላል፡፡ ቦርዱ አሁንም የቀረቡለትን ቅሬታዎች በዝርዝር ካየ በኋላ ማጣራቱን ገልጾ፣ ፓርቲዎቹ አላነጋገረንም የሚሉት ተቀባይነት የሌለው ነው ብሏል፡፡
    ቦርዱ ሁሉንም ፓርቲዎች እኩል እያገለገለ እንደሚገኝ አስረድቶ፣ የሚተዳደርባቸው ደንቦችና መመርያዎች በፓርቲዎች ተሳትፎ የወጡ በመሆናቸው ወገንተኛ አድርጎ ማቅረብ ትክክል አይደለም በማለት አስረድቷል፡፡ ምርጫ ቦርድ ከማንም ፓርቲ ጋር የመወገን ዓላማ እንደሌለውና ሕጉም እንደማይፈቅድለት እየተናገረ ነው፡፡
    ይህ በዚህ እንዳለ ባለፈው ሳምንት “ምርጫ ለመድረክ ግንባርነት ዕውቅና ሰጠ” በሚል ርዕስ በወጣው ዜና “… መድረክን የፖለቲካ አጀንዳውንና የገንዘብ አቅሙን በመገምገም ብቁ ሆኖ በመገኘቱ ያቀረበው ጥያቄ በቦርዱ ተቀባይነት ማግኘቱን ወይዘሮ የሺ ገልጸዋል፤” የሚለው ዓረፍተ ነገር ከቦርዱ ሥልጣንና ኃላፊነት ውጪ በመሆኑ በዚህ መሠረት ተስተካክሎ እንዲነበብ እንጠይቃለን፡፡
    source : ethiopian reporter

    ሰንበት ምሳ፤ የደቡብ ኢትዮጵያ ልጆች ደቡብ አፍሪካ ምን አላቸው!?



    ዛሬም “ለአዲስ ታይምስ” (ፍትህ) አዲሳባ ተልካ የነበረችቱን ወግ ለሰንበት ምሳ እዚህ ተለጥፋለች፤ ይቋደሱልኝ እውነት ግን የደቡብ ኢትዮጵያ ልጆች ደቡብ አፍሪካ ምን አላቸው!?
    ሰላም ወዳጄ እንዴት ሰነበቱ…
    የመንገድ ቁፋሮው ነገር እንዴት አድርጎታል? በአሁኑ ሰዓት አዲሳባ ውስጥ ትራንስፖርት ከማግኘት “ፖርት” ማግኘት ይቀላል ሲሉ የሚያሽሟጥጡ ሰዎች መበራከታቸውን እየሰማን ነው።
    ኧረ “ፖርት” ብል ጊዜ ምን ትዝ አለኝ፤ ኢትዮጵያ ለጅቡቲ አዲስ ወደብ ግንባታ እያደረገችላት መሆኑን ሰምተን ደስታችን ጨምሯል። እሰይ እንዲህ ነው እንጂ ልግስና! በዚሁ አይነት ፤ ሌሎቹ ጎረቤቶቻችንም እንዳይቀየሙ ብንገነባላቸው ምን አለበት…? ለነ ሱዳን ፤ለነ ሱማሌ ኤርትራዬ እና ኬኒያስ ቢሆኑ ካለኛ ማን አላቸው…? እና ይታሰብበት… “ያስቀኛል ገንፎ ከራቴ ላይ ተርፎ” አሉ አበው!
    እና ታድያ የትራንስፖርቱ ነገር እንዴት አደርጎታል? እንደውም እንደሰማሁት ከሆነማ “ፒያሳ መሀሙድጋ ጠብቂኝ” ከሚለው የታላቁ ወዳጃችን መሃመድ ሰልማን መፅሐፍ በኋላ “ቦሌ ፒኮክ ጋ ጠብቂኝ” “መርካቶ ምዕራብ ሆቴል ጋ ጠብቂኝ” የሚሉ ተደጋጋሚ የቀጠሮ ፅሁፎች ሲወጡ የነበረውን ያህል… አሁን በቅርቡ ከወዳጆቻችን እንደ አንዱ የሆነው በሀይሉ ገብረ እግዚአብሔር “የትም አትጠብቂኝ” ብሎ መፃፉን ሰምተናል።
    ወዳጃችን ይህንን ሲፅፍ እንደሌሎቹ መቀጣጠሪያ ቦታ አጥቶ ሳይሆን፤ ብቀጥራት በምን ትራንስፖርት ትመጣለች? ብሎ ይመስለኛል። እርግጥ ይሄ የኔ ግምት ነው እንጂ፤ ሙሉ ፅሁፉን ገና አላነበብኩትም። (የት አግኝቼው…)
    የምር ግን የትራንስፖርቱ ነገር “የትም አትጠብቂኝ” የሚያስብል መሆኑን ብዙ ወዳጆቼ እያማረሩ ነግረውኛል። እኔ የምለው ግን መንገድ ገንቢው አካል ገንቢ አስተያየቶችን ለምን አይቀበልም? መንገዶቹን እስኪሰሩ ድረስ ወይ አማራጭ መንገድ መስራት ወይ ደግሞ የስራ ማቆም አድማ መጥራት አለበትኮ! አለበለዛ ሰዉ ከአለቃውና ከቀጠራት ጋር እየተጣላ ከተማዋ የድብድብ “ሪንግ” እንዳትሆን ያሰጋል…!
    ለማንኛውም ወዳጄ ዛሬም ኬኒያ እንሄዳለን… ሻንጣዎትን መያዝ አይጠበቅብዎም እንደው ደረስ ብለን መለስ ነው የምንለው።
    በነገራችን ላይ ከአዲሳባ ኬኒያ አንድ ሰዓት ከሃምሳ ደቂቃ የበረራ ሰዓት ብቻ ነው የሚወስደው። በአሁኑ ሰዓት ከሽሮሜዳ ቦሌ ለመድረስ እንኳ ስንት ሰዓት ይፈጃል? አሁን አሁንማ ምን ሰዓት “ሰው ነው የሚፈጀው እንጂ!” ብለው በጣም አያማሩ…
    እንደምንም ብለው ቦሌ ይድረሱ። ከዛም አንድ ሰአት ከሃምሳ ደቂቃ በሰማይ ላይ ተንሳፈው፤ ናይሮቢ ኬኒያ እንኳን ደህና መጡ ብላ ትቀበልዎታለች።
    በኬኒያ በተናጠል ከሚሰደዱ ኢትዮጵያውያን በተጨማሪ በአንድ ጊዜ አርባ ሰላሳ እየሆኑ እየተቧደኑ የሚሰደዱ የደበብ ኢትዮጵያ ልጆችን ማየት በጣም የተለመደ ነገር ነው። እነዚህ “ደቡቤዎች” ኬኒያ የሚመጡት ካናዳ፣ አሜሪካ፣ እና አውሮፓን ናፍቀው አይደለም። ወይ ደግሞ ፖለቲካን ነክተው መንግስት “ንኩት” (ውጡልኝ ከዚህ ቤት) ብሏቸውም አይደለም።
    በቃ ከሆነ ጊዜ በኋላ በደቡብ ኢትዮጵያ የመጣ አንድ ፋሽን አለ። አንድ ሰው ጎርመስ ካለ፤ “ደርሷል ይባላል” ለአቅመ አዳም አይደለም። ለአቅመ ስራም አይደለም። ለአቅመ ጉዞ ደበብ አፍሪካ እንጂ…!
    አንድ ሰሞን ግራ ገብቶኝ የደቡብ ኢትዮጵያ ልጆች ደቡብ አፍሪካ ምን አላቸው? ብዬ አንድ ወዳጄን ጠይቄው ነበር።
    እርሱም ሲነግረኝ፤ በአንድ ወቅት አንድ የደቡብ ክልል ሰውዬ ስማቸው ጠፋኝ (በቅንፍ እርሳቸውም ጠፍተዋል መሰለኝ። (በሌላ ቅንፍ ዘንድሮ አንደሆነ እግር ኳስ ተጫዋች ሳይሆን እንደወጣ የሚቀረው የመንግስት ባለስልጣን ሆኗል። ሁለቱም ቅንፋችን ዘግተን ስንወጣ))
    እናልዎ እኒህ የደቡቤ ባለስልጣን በደቡብ አፍሪካ አምባሳደር ተደርገው ተሹመው ነበር አሉ። ታድያ ያኔ ሰውዬው በርካታ ዘመዶቻቸውን ከደቡብ ክልል ወደ ደቡብ አፍሪካ ማስወጣት ጀመሩ። ዘመዶቻቸው ደግሞ በ “ሳውዝ” እንደምንም ብለው ተፍጨርጭረው ውጤት ላይ ሲደርሱ ሌላ ዘመዳቸውን መጥራት ጀመሩ። ከዛ እያለ እያለ አሁን አሁን የደቡብ ኢትዮጵያ ልጆች ታላቅ የተስፋ ምድር አድርገው የሚያዩዋት ደቡብ አፍሪካ ሆነች።
    ወደዛ ለመድረስ ደግሞ ኬኒያን መርገጥ፤ በኬኒያም መረገጥ ግድ ነው። እንዴት የሚለው ብዙ ነው… ዛሬ እንደው መንደርደሪያውን እንቃመሰውና እንቀጥልበታለን…
    አብዛኛዎቹ የደቡቤ ስደተኞች የሚመጡት በግሩፕ ነው ተባብለን የለ! ኬኒያ ድረስ በእግርም በአውቶብስም በምንም በምንም ተብሎ ይገባል። ከዛ በኬኒያ አንድ ቤት ውስጥ ቁጭ ብለው አርባ ወይም ሰላሳ እስኪሞሉ ይጠባበቃሉ። ምክንያቱም ለቀጣዩ የደቡብ አፍሪካ ጉዞ ትራንስፖርታቸውም የትልልቅ መኪና እቃ ማጠራቀሚያ “ኮንቴይነር” ነው። “ኮንቴይነሩ” ከሰላሳ እስከ አርባ የሚሆኑ ሰዎችን በአንዴ ይይዛል። ዋጋውም ከሌሎች መጓጓዣዎች ቀነስ ያደርጋል። ስለዚህ ብዙዎች ይመርጡታል።
    በኮንቴይነር ሲጓዙ ታድያ፤ ዋጋው ብቻ ሳይሆን ስቃዩም እርካሽ ነው። ሞቱም በሽ ነው። ምነው እንኳ ባለፈው ኬኒያን አልፈው ታንዛንያ ሲደርሱ ስንት ወጣቶች ናቸው አየር አጥሯቸው በኮንቴይነር ውስጥ የሞቱት…? እረሱት እንዴ፤ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ሁሉ ዜናውን ሰምተን አልነበር እንዴ! (ወይስ እርስዎ ያኔም ዲሽ ገዝተው ነበር…!? ትንሽ ኢቲቪን ሏሽሟጥ ብዬ እንጂ ዜናው በአለም አቀፍ ማሰራጫዎችም ተሰራጭቶ ነበር። እና በርግጠኝነት ሰምተውታል)
    ኬኒያ ቁጭ ካሉ ደግሞ እንደዚህ አይነት ዜና ብርቅ አይደለም። በተለይ ታንዛንያ ላይ በርካታ ወገኖቻችን በታጨቁበት ኮንቴይነር ውስጥ ፍፃሜያቸው ሆኗል።
    ነገር ግን እንዲህም ሆኖ ጉዞው አያቋርጥም። መጓጓዣውም አይቀየርም። ኬኒያ ለ12 አመታት የኖረው አዲስ እንደነገረኝ ከሆነ “እነኳን ሌላው ቀርቶ አጠገባቸው ጓደኞቻቸው በኮንቴይነር ውስጥ አየር አጥሯቸው ሞተው በእግዜር ታምር ተርፈው ደቡብ አፍሪካ የገቡ ሰዎች ራሳቸው፤ ሌላ ዘመዳቸውን የሚያስመጡት በኮንቴይነር ነው።” ብሎኛል።
    ደቡቤ ወዳጆቻችንም እንትና ሞተ የሚለውን ወሬ ቢሰሙትም ከልባቸው አይፅፉትም። በጣም ያስገረመችኝን አንድ ወሬ ቀጥሎ ልንገርዎትማ፤
    በደቡብ ኢትዮጵያ በተለይ ከንባታ እና ሃድያ አካባቢ የተለያዩ ቪዲዮ ቤቶች አሉ። ቪዲዮ ቤቶቹ ፊልም ያሳያሉ። የሚያሳዩት ፊልም የ “ጄኪ ቻን” ካራቴ እንዳይመስልዎ… የ “ጆቴ ጃና ህይወት በደቡብ አፍሪካ” የሚል ነው።
    እንግዲህ “ጆቴ” በአካባቢው የሚታወቅ የደቡብ ልጅ ነው አሉ። (ስሙ አፌ ላይ መጥቶ ነው አንጂ ማስታወሻ ደብተሬ ላይ ያለው እውነተኛው ስም አይደለም) እና ከደቡብ ሲወጣ “ስንጥር ነበር የሚያክለው ቀጫጫ፤ አሁን ወፍሮ ባላባት መስሏል። እቤቱ ሶፋ ላይ ሲቀመጥ፣ በሪሞት ቴሌቪዥኑን ሲያበራ እና ሲያጠፋ፤ የሆነች ነጭ የምታምር መኪና ተደግፎ፣ ደግሞ ሌላ ቀይ መኪና ውስጥ ቁጭ ብሎ “ሾፌር” ሆኖ… ብቻ በጥቅሉ የአካባቢው ወጣቶች በቅርብ የሚያውቁት “ጆቴ ጃና” ሆኗል የሚያስቀና…!
    ይህንን ቪዲዮ የአካባቢው ወጣቶች ከፍለው ነው የሚያዩት። ከዛ የስቃይ እና የሞት ወሬ ትዝ አይላቸውም። ቁጭ ብለው ያስባሉ እንደ “ጆቴ ጃና” መሆን የሚቻለው እንዴት ነው? ብዙውን ጊዜ ቪዲዮውን የሚያሳየው ሰውዬ ራሱ አማካሪ ነው። እንደውም ሳስበው ቪዲዮውን ካሳያቸው በኋላ “እንደ ጆቴ ጃና መሆን ይፈልጋሉ… እንግዲያስ መላው ቀላል ነው!” ብሎ ማስታወቂያ ሳይሰራ አይቀርም።
    ታድያ የድለላ ስራ ይራና ጠርቀምቀም ያሉ ጎረምሶችን ከመንገድ መሪ ጋር አድርጎ ኬኒያ ያደርሳቸዋል። ከኬኒያ ደግሞ ጠርቀምቀም ሲሉ በኮንቴይነር መኪና ውስጥ ተጭነው በሰላም ከገቡ “ጆቴ ጃና” ደቡብ አፍሪካ ይቀበላቸዋል።
    “መሃሉ አይነገርም” እንዲል ሰባኪው መሃሉ ግን ብዙ ጣጣ አለው። በደቡብ ኢትዮጵያ እና በደቡብ አፍሪካ መሃል ካሉት የመሃል ላይ አበሳዎች አንዱ ኬኒያ ውስጥ ያለው አበሳ ነው… በሚቀጥለው ጊዜ ቅንጭብጫቢ አበሳዎችን እናነሳለን!
    ለዛሬ ይብቃን…
    እስቲ አማን ያሰንብተን!

     http://www.abetokichaw.com/
       

    ESAT Meade Esat Ethiopia Dec 30 2012


    Saturday, December 29, 2012

    ይድረስ ለተቃዋሚዎች


    የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የሚባለውን የወያኔ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ፤ በኢትዮጵያ ውስጥ በወያኔ መንግስት የተሾመ ለወያኔ ማፊያ ቡደን የሚያገለግል እንደሆነ በረጅም አመት የማጭበርበር የስራ ልምዱ አስመስክሯል ። ይህ ድርጅት ገለልተኛ እንዳልሆነ እየታወቀ በኢትዮጵያ የሚገኙ ከ 34 በላይ የሚሆኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች ወያኔን በማይገባው ቛንቛ በሰላማዊ ትግል ታግሎ ወያኔን ለማስወገድ ውጤታማ ያልሆነ ልፋት እየለፉ ይገኛሉ ።
    እነዚህ የተሰባሰቡት ፖለቲካ ፓርቲዎች የሚከተሉት ሰላማዊ ትግል በጣም ዘመናዊ እና የሚዎደድ ቢሆንም ወያኔን የመሰለ ዘረኛ እና የተደራጁ የማፊያ ቡድኖችን ከስልጣን ለማስወገድ ትክክለኛ አካሄድ አይመስልም ። እነዚህ ድርጅቶች በ አሁኑ ሰአት በወያኔዎች የሚመራው የምርጫ ቦርድ መፍትሄ እንደማይሰጣችው እየታወቀ ለዚህ ድርጅት ጥያቄ ማቅረብ ጊዜን ከማባከን በተጨማሪ አምባገነኑን የወያኔ መንግስት በስልጣን ላይ እንዲቆይ እድሜውን ለማራዘም እድል እንደመስጠት ይቆጠራል።
    እነዚህ የወያኔ ቡድን በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የሚያደርሰው አድለዎ ፣ አፈና ፣ዘረኛነት እና አምባገነናዊ አገዛዝን በመቃዎም ብሎም የሃገራችን ህዝብ የስልጣን ባለቤት እንዲሆን ለማድረግ በሰላማዊ መንገድ እየታገሉ ያሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች አሁን በወያኔ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ወይም ምርጫ ቦርድ እየደረሰባቸው ያለውን ጫና መቛቛም ከማይችሉበት ደረጃ ላይ መድረሳቸውን እየተናገሩ ይገኛሉ ።
    እነዚህ የምርጫ ቦርድን ጥያቄ ለመጠየቅ የተሰባሰቡ እና በሃገር ውስጥ የሚገኙ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲ ሰብስብ  የኢትዮጵያ ህዝብን የስልጣን ባለቤት እንዲሆን ባላችው አቅም እየታገሉ ይገኛሉ ። ነገር ግን ገዡ ቡድን ከአምባገነንነቱ የተነሳ ተቃዋሚዎች  ህዝብን እንኳን ሰብስበው ማዋያየት የማይችሉበት ደረጃ አድርሷቸዋል ።
    ስለዚህ ተቃዋሚዎች እንታገልለታለን የሚሉትን የኢትዮጵያ ህዝብን ማዋያየት እንኳን በማይችሉበት ሁኔታ፤ የገዡ መደብ ባስቀመጠላቸው አቤቱታ የማቅረብ መብት ብቻ የኢትዮጵያን ህዝብ ከወያኔ አምባገነናዊ አገዛዝ ነጻ ለማውጣት ከመታገል ይልቅ ፤ የችግሩ ገፈት ቀማሽ የሆነውን የኢትዮጵያን ህዝብ ለመብቱ እንዲታገል አስቸኳይ ጥሪ ማቅረብ እና ህዝባዊ ትግሉ ውጤታማ እንዲሆን መምራት አማራጭ የሌለው አማራጭ ነው ።
    የምትጠሩትን ህዝባዊ እና ሰላማዊ የትግል ጥሪ የኢትዮጵያ ህዝብም ተቀብሎ የስልጣን ባለቤት ለመሆን ፣ የሚጠቅመውን የመምረጥ የማይጠቅመውን የመሻር እና በሃገሩ ባይተዋር የማይሆንበት ስረዓት እንዲኖረው ወደ ትግሉ በቆራጥነት መቀላቀል ሃገራዊ ግዴታው ነው ።

    Gen. Samora Yenus in a German hospital – update


    Elias Kifle
    UPDATE – December 28, 2012: Ethiopian Review sources are reporting that armed forces chief of staff Gen. Samora Yenus is back in a Germany hospital. In August, we reported that Samora, looking frail, returned to Addis Ababa to attend dictator Meles Zenawi’s funeral, and that he will return to the hospital.
    UPDATE – August 21, 2012: Samora Yenus has been observed at Bole Airport today along with other TPLF junta officials receiving Meles Zenawi’s body. Our sources have verified that he returned to Addis Ababa two days ago from Germany, but he will return to continue his medical treatment.
    Samora YenusThe late Ethiopian dictator Meles Zenawi’s military chief of staff, Gen. Samora Yenus, is currently in Essen, Germany, receiving medical treatment.
    Doctors at Essen University Hospital have diagnosed Samora with Pneumocystis Carinii Pneumonia, which is a symptom of AIDS, according to Ethiopian Review Intelligence Unit sources.
    Samora was taken to Bole Airport by ambulance after he collapsed following a TPLF meeting last week, and flown to Germany.
    Lt. General Seare Mekonnen is now in charge of the armed forces in Ethiopia, Ethiopian Review sources in Addis Ababa reported.

    ሀገር ወዳድ መሆን እኮ ጦርነትን በሀገር ላይ ማሰብ አደለም፤ ሀገር ወዳድ እኮ መንግስት ህዝቡን ሲበድለው የራስን ኑሮ ደልቀቅ አድርጎ ማየት አደለም፤ ህዝብ ሲራብ ቆሞ ማየት አደለም፡፡ ምን አልባትም ችግርን አብሮ መጋፈጥ ትልቅ እሴት አለው



    SATURDAY, DECEMBER 29, 2012

    ሰበር ዜናሌፍተናንት ጄኔራል ታደሰ ወረደ ሌ/ጄ ሳሞራ የኑስን ይተካሉ ተብሎ ይጠበቃል::


    ሌፍተናንት ጄኔራል ታደሰ ወረደ ሌ/ጄ ሳሞራ የኑስን ይተካሉ ተብሎ ይጠበቃል::

    በ2008 ከሜ/ጄ ወደ ሌ/ጄ የተሸጋገሩት ታደሰ ወረደ የጦር ሃይሎች ኢታማጆር ሹም የነበሩትን ሌ/ጀኔራል ሳሞራ የኑስን ይተካሉ ተብሎ ይጠበቃል ሲሉ ዉስጥ አዋቂ ምንጮች ገለጡ::በኢትዮጵያ የመከላከያ ሚኒስቴር ቅድመ ተከተል መሰረት ጄኔራል ሳሞራ የኑስን ይተኩዋቸዋል የሚባሉ 4የበታች ጄኔራሎች አሉ ብለዋል ምንጮቹ ለምንሊክ ሳልሳዊ...



    እነርሱም:-
    1-ሌፍ/ጄኔራል ታደሰ ወረደ- የጦር ሃይሎች የስልጠና ሃላፊ/በአሁን ሰአት በተባበሩት መንግስታት በአቢያ የሰፈረው የኢትዮጵያ ጦር አዛዥ

    2-ሌፍ/ጄኔራል ገዛኢ አበራ- የሎገስቲክ ሃላፊ
    3-ሌፍ/ጄኔራል  ሳአረ  መኮንን የሰሜን አዝ አዛዥ
     4-ብ/ጄኔራል ገብረ ዴላ-የጦር ሃይሉ የደህንነት እና የስለላ ሃላፊ...ሲሆኑ

    ጄኔራል ታደሰ ወረደ እንደ ሳሞራ የኑስ ሳይሆኑ ትምህርታቸዉን በአሜሪካን አገር ተከታትለው የጨረሱ እና በወታደራዊ ሳይንስ የረቀቁ እንደሆኑ ምንጮቹ ሲመሰክሩ እንዲህ ይላሉ..... ያንብቡት...

     ይህ ከዚህ በታች የምትመለከቱት ደብዳቤ የተባበሩት መንግስታት
                                                                          ዋና ጸሃፊ ባንኪ ሙን  ሌፍ/ጄኔራል ታደሰ ወረደን የሾሙበት ነው::
    Secretary-General
    SG/A/1301
    BIO/4304
    PKO/285

    Department of Public Information • News and Media Division • New York
    Biographical Note

    Secretary-General Appoints Lieutenant General Tadesse Werede Tesfay of Ethiopia Head


    Of Mission, Force Commander of United Nations Interim Security Force for Abyei



    United Nations Secretary-General Ban Ki-moon has appointed Lieutenant General Tadesse Werede Tesfay (Ethiopia) as Head of Mission and Force Commander of the United Nations Interim Security Force for Abyei (UNISFA).  Lieutenant General Tesfay will be responsible for discharging the mandate of UNISFA, as contained in Security Council resolution 1990 of 27 June 2011, including monitoring and verifying the redeployment of all armed forces from the Abyei area, in accordance with the 20 June Agreement between the Government of Sudan and the Sudan People’s Liberation Movement on Temporary Arrangements for the Administration and Security of the Abyei Area.

    Lieutenant General Tesfay brings to the position extensive command and field experience gathered during his distinguished military career with the Ethiopian National Defence Forces. Lieutenant General Tesfay has most recently occupied the position of Head of the Joint Training Department and has previously held a number of important command and staff appointments within the Ethiopian National Defence Forces, including commanding the Army Corps and serving as a member of the Defence Commanders Council.

    Lieutenant General Tesfay has a Master of Business Administration and an additional master’s degree in security sector management.

    Born in Ethiopia on 13 July 1958, he is married and has four children.
     ተጨማሪ
    ጄኔራል ታደሰ ወረደ እንደ ሳሞራ የኑስ ሳይሆኑ ትምህርታቸዉን በአሜሪካን አገር ተከታትለው የጨረሱ እና በወታደራዊ ሳይንስ የረቀቁ እንደሆኑ ምንጮቹ ሲመሰክሩ እንዲህ ይላሉ..... ያንብቡት...
    General Tadesse Werede member of Ethiopia's elite, the Defense Commanders Council is considered the most accomplished military officers and the most battled field experienced general and is also considered one of the most educated military officer among the defence top brasses, with one undergraduate degree and two graduate degrees in Master of Business Administration and an additional master’s degree in security sector management from distinguished American universities. He will be heading to assume the position of chief of staff with the retirmnet of General Samora Yunis and with his mission once is complete with the UN-Interim security forces for Abyei in Sudan where currently he is the chief commander.

    In appointing Lt. General Tadesse Werede, as Head of Mission and Force Commander of the United Nations Interim Security Force for Abyei (UNISFA), United Nations Secretary-General Ban Ki-moon, the secretary said, “ Lieutenant General Tesfay will be responsible for discharging the mandate of UNISFA, as contained in Security Council resolution 1990 of 27 June 2011, including monitoring and verifying the redeployment of all armed forces from the Abyei area, in accordance with the 20 June Agreement between the Government of Sudan and the Sudan People’s Liberation Movement on Temporary Arrangements for the Administration and Security of the Abyei Area.” Speaking about Lt. General Tadesse Werede’s experience, secretary general Ban Ki-Moon said, “Lieutenant General Tesfay brings to the position extensive command and field experience gathered during his distinguished military career with the Ethiopian National Defense Forces. Lieutenant General Tesfay has most recently occupied the position of Head of the Joint Training Department and has previously held a number of important command”(Dejazmch of Tigrai  እንደመሰከሩት)
    http://www.unmultimedia.org/photo/detail.jsp?auto=1&id=480/480717&key=2277&query=*

    መንግሥት ለዕርቁ ጉዳይ የሄዱትን ሊቀ ካህናት ኀ/ሥላሴ ዓለማየሁን አስሮ ወደ አሜሪካ ላካቸው


    ኢትዮጵያ መንግሥት ዓላማውን ግልጽ አድርጓል፤ እኛው አውቀናል
    by Deje Selam on Saturday, December 29, 2012 
    የመንግሥት ደጋፊ የጡመራ መድረኮች “አስታራቂ ኮሚቴው” ላይ ዘምተዋል፤
    ከጳጳሳቱ መካከል የዕርቁ እንቅፋት የሆኑት አባቶች በግልጽ ታውቀዋል፤ ስማቸውን ከማውጣታችን በፊት አሁንም ሐሳባቸውን ይቀይሩ እንደሆነ እንጠብቃቸዋለን፤
    ጉዳዩን ያቀነባበሩት የአዲስ አበባው ልዑክ አባል የሆኑት ን/ዕድ ኤልያስ አብርሃ ናቸው ተብሏል፤
    የአዲስ አበባው ልዑክ አባቶች ዲሲ ኢትዮጵያ ኤምባሲ ከተጠሩ በኋላ ተገደው እንዲፈርሙ ተደርገዋል፤
    (ደጀ ሰላም ታኅሣሥ 20/2005 ዓ.ም፤ ዲሴምበር 29/2012)፦ በቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ጣልቃ አልገባኹም በሚል ሰሞኑን መግለጫ የሰጠው የኢትዮጵያ መንግሥት ለዕርቁ ጉዳይ ከቅ/ሲኖዶስ ጋር ለመነጋገር ወደ አዲስ አበባ የሄዱትን የሰላምና አንድነት ጉባኤውን አባል ሊቀ ካህናት ኀ/ሥላሴ ዓለማየሁን አስሮ ወደ አሜሪካ ከላካቸው ወዲህ ለዕርቁ ያለው የተስፋ ደጅ መዘጋቱ እሙን ሆኗል። መንግሥት የዕርቁ ድርድር ለይስሙላ እንጂ “ከምር” እንዲሆን አልፈለገም ነበር። ነገሩ ከምር ሲሆን ግን “የጭቃ ጅራፉን” መምዘዝ ይዟል። ለዲፕሎማሲ ይጠቅመኛል ብሎ የፈቀደው ዕርቅ መሰካት ሲጀምር ከዲፕሎማሲው ከማገኘው ትርፍ በሩን መዝጋት ይሻለኛል ያለ መስሏል። የራሱን ፓርቲ አባል በፓትርያርክነት ለማስቀመጥ በጠራራ ፀሐይ ወረራውን ቀጥሏል።
    በተያያዘ ዜና አስታራቂ ጉባኤው አውግዘው መግለጫ እንዲሰጡ የተገደዱት የአዲስ አበባው ልዑክ አባላት ሐሳባቸውን በግድ እንዲቀይሩ የተገደዱት ወደ ኢትዮጵያ ኤምባሲ ከተጠሩ በኋላ መሆኑ ሲታወቅ ደብዳቤውን ያዘጋጁት ንቡረ ዕድ ኤልያስ አብርሃ ከኤምባሲው ሰዎች ጋር በመሆን እንደሆነ ምንጮቻችን ገልጸዋል። ሦስቱ ብፁዓን አባቶች ደብዳቤውን ያለውድ በግድ እንዲፈርሙ ሲገደዱ ሐሳባቸውን ላለመቀየር ያንገራገሩት ብፁዕ አቡነ አትናቴዎስ በብዙ ማግባባት ፊርማቸውን እንዲያኖሩ ተደርገዋል ተብሏል።
    ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ መግለጫው ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ኢላማ የተደረገው አስታራቂ ጉባኤ በመንግሥት ደጋፊ የግል ጦማሪዎች ሳይቀር በመወገዝ ላይ ይገኛል። “መጀመሪያውኑም ገለልተኛ አልነበረም” የተባለው አስታራቂው ቡድን ከመ-አርዮስ የታየበት ምክንያት ዕርቁን ከግብ ለማድረስ በመቃረቡ ነው።
    ቸር ወሬ ያሰማን፣ አሜን።

      የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት መተማ ወረዳ አለንጌ በተባለ ቦታ ጥቃት ፈፀመ


      ታህሳስ  ፳(ሃያ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
      ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት ታህሳስ 18 ቀን 2005.ዓ.ም በመተማ ወረዳ ልዩ ስሙ አለንጌ በተባለው አካባቢ ከመከላከያ ሰራዊት ጋር በተካሄደው ውጊያ 8 የጠላት ወታደሮችን ገድሎ 11 በማቁሰል ከፍተኛ የህይወትና የንብረት ኪሳራ ማድረሱን ግንባሩ ገልጿል።
      ግንባሩ በርካታ የጦር መሳሪያዎችን መማረኩንም ገልጿል።
      መንግስት በጉዳዩ ዙሪያ የሰጠው መልስ የለም። ዜናውንም ከገለልተኛ ወገን ለማረጋገጥ አልተቻለም።                                      
                          

      በኢሳት እርዳታ ሳጅን ሽታየ ወርቁ ራሱን ከማጥፋት ተቆጠበ 

        ታህሳስ  ፳(ሃያ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
      ኢሳት ዜና:-ከሁለት ቀናት በፊት በደቡብ ክልል በዳዉሮ ዞን በሎማ ወረዳ ገሣ ከተማ ላይ ይደረግ በነበረዉና የሎማ ዲሣ ህዝብ የአዲስ ወረዳ አግባብነት ስብሰባ ላይ የግል አስያየቱን የሰጠዉ የፖሊስ ባልደረባ ሳጅን ሽታየ ወርቁ እራሱን ከምግብ እና ከውሀ ለ24 ሰዓታት ከልክሎ በወጣበት ዛፍ ላይ ራሱን ከማጥፋቱ በፊት ከኢሳት ጋር ተገናኝቶ አላማውን ለህዝብ ይፋ ለማድረግ በመፈለጉ የኢሳት ባልደረቦች በስልክ አግኝተው ራሱን እንዳያጠፋ በመምከራቸው፣ ከድርጊቱ ታቅቦ በፖሊስ ታጅቦ ወደ እስር ቤት ተጉዟል።
      ሣጅን ሽታዬ ወርቁ ሺበሺ ከሁለት ቀናት በፊት “ወረዳ አያስፈልም ካላችሁ ለምን ድሮ ለሲዳማ 9 ለወላይታ 5 እያለችሁ ሸንሽናችሁ ሰጣችሁ በማለት” በስብሰባ ላይ በሰጠዉ አስተያየት ምክንያት በዕለቱ ለስብሳበ የወጡ የወረዳዉ የመንግሥት ሠራተኞች የእርሱን ሀሳብ በመደገፍ ስብሰባዉን አቋርጠዉ በመዉጣታቸዉ ምክንያት ከትላንቱ ስብሰባ የወረዳዉ ፖሊስ አባላት በሙሉ እንዳይገቡ መከልከላቸዉን መግለጻችን ይታወሳል፡፡
      ሳጅን ሽታየ በእለቱ ያጋጠመውን ድርጊት በዝርዝር አስረድቷል ።
           
         
              

      የባለራእይ ወጣቶች ማህበር አባላት ጉባኤ እንዳናካሂድ ተከለከልን አሉ


             ታህሳስ  ፳(ሃያ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
      ኢሳት ዜና:-የማህበሩ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ወጣት ብርሀኑ ተግባረእድ እና ምክትል ሊቀመንበሩ ወጣት ሚካኤል አለማየሁ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ጉባኤያቸውን ለማዘጋጀት አዳራሽ ፍለጋ ቢንከራተቱም የጸጥታ  ሀይሎች በሚያደርሱባቸው ተጽእኖ ለመከራየት አልቻሉም።
      ወጣቶቹ በመጪው እሁድ ጉባኤ ለማካሄድ የተከራዩትን አዳራሽ፣ የጸጥታ ሀይሎች ባሳረፉት ጫና ሆቴሉ ፈቃደኝነቱን እንደሰረዘባቸው ገልጸዋል።
      ሀሳባችንን በነጻነት መግለጽ አልቻልንም የሚሉት ወጣቶቹ፣ ለማን አቤት እንደሚባልም ግራ እንደገባቸው ገልጸዋል
      ከወጣቶቹ ጋር ያደረግነውን ሙሉ ቃለምልልስ በትኩረት ዝግጅታችን መከታተል ትችላለችሁ።

      ESAT Daily News Amsterdam 29 December 2012 Ethiopia


      Breaking News (ሰበር ዜና)፡ 6ኛውን ፓትርያርክ ለማስመረጥ ለተሾሙት ሰዎች ከሲኖዶስ የተጻፈላቸው ምስጢራዊ ደብዳቤ እጃችን ገባ


      (ዘ-ሐበሻ) የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ታኅሣሥ 6 ቀን በዋለው ጉባኤው ለስድስተኛው ፓትርያሪክ ምርጫ ከሦስት ያላነሱ ከአምስት ያልበለጡ ዕጩ ሊቃነ ጳጳሳት ለውድድር እንዲቀርቡ ወስኗል፤ አስመራጭ ኮሚቴም ተመርጧል ስትል ዘ-ሐበሻ መዘገቧ ይታወሳል። ሆኖም ግን አዲስ አበባ ያለው ሲኖዶስ እንዲህ ያለ ውሳኔ አለመወሰኑን አስተባብሎ ነበር።አሁን ለዘ-ሐበሻ የደረሰው ከሲኖዶስ የወጣና ለፓትርያርክ አስመራጭ ኮሚቴዎች የተጻፈው ደብዳቤ ግን ማን ውሸታም እንደሆነ የሚያጋልጥ ነው ተብሏል። ግን እንዴት ይህ ሁሉ የኦርቶዶክስ ምዕመንን መዋሸት አስፈለገ? ምስጢራዊው ደብዳቤን አይታችሁ ፍረዱ።Holy-sinodHoly-sinod-1

      Gen Samora Yenus is dying


      The Horn Times Newsletter, 28 December 2012
      by Getahune Bekele
      The unschooled and uncultured top war criminal Gen Samora is dying…
      A poor peasant and a primary school dropout, who was described by senior political commentator as cold blooded murderer with thinking and reasoning capacity of a dinosaur, Gen Samora is dying…
      According to a sensitive document leaked to the Horn Times from Bella military referral hospital in Addis Ababa, the frail TPLF army chief-of-staff and top November criminal, the dastardly Gen Samora Yenus Mohamedfereja, has less than a year to live.
      And if he dies before being arrested and tried, Samora Yenus will be the fourth high profile TPLF war criminal to escape justice after the late fuehrer Meles Zenawi, former intelligence chief Kinfe G.medhin and after former army commander the late Gen Hayelom Araya, who was killed during gun fight over a prostitute in one of Addis Ababa’s brothels.
      Diagnosed with HIV AIDS in 2006 and declared a habitual defaulter for not taking his medication regularly, the illiterate and lowbrow Samora has been receiving treatment consisted of strengthening the body’s natural defense, killing bacteria and battling infection at Essen university hospital in Germany.
      However, despite the impoverished Ethiopia footing his massive medical bill including the purchase of an expensive drug called zidovudine, the bawling warlord has developed new strain known as extensively drug-resistant (XDR) tuberculosis, which resisted all 8 second line drugs.
      The intercepted document further revealed that the murderous warlord is suffering from other scourges as well; diabetes mellitus and hypertension, which complicated the costly multi-system treatments. And currently, he is not responding well to available medications both at home and abroad.
      Hence insiders said he has reached the end of his tether.
      The man who visited heartrending terrors up on the peoples of Ethiopia, Somalia and Eritrea is finally succumbing to the terror of the AIDS pandemic.

      Born to Muslim family who were eking out a hard-scrabble living from subsistence farming in poverty stricken town of Axume-Tigraye in 1955, the wanderer assassin never practiced Islam due to his secular job as TPLF killing machine for nearly 40 years.
      Samora first gained notoriety in 1977 when he executed 6 TPLF combatants for miner sexual offences and barbaricly urinated on their corpuses.
      Although holocausts of deaths from such nerve-racking terrors were common in an outdated organization like the TPLF, an equally notorious former commander of Bado-6 prisons (a network of underground cells strewn across Tigraye), who is now living in the US town of Ohio as fugitive, Bisrat Amare, once described the dying Samora “a Terror guru” after watching him commit various other atrocities.
      But most Ethiopians will remember Samora Yenus for the bloodcurdling war crimes he committed during the 2005 nationwide anti-TPLF uprising.
      The oaf teamed up with federal police boss Workeneh Gebeyehu and nonchalantly pulled off a victory for his fuehrer by using ambulances filled with obdurate Tigre hoodlum dressed as paramedics to penetrate the crowed and exterminate leaders and organizers of the peaceful demonstration.
      Nevertheless, the biggest crime of all was the use of Bella military referral hospital as army and federal police headquarter, where nonplussed and wounded protesters brought in by “ambulances” were watched bleed to death.
      “We have defeated our enemy and straighten the path for Tigre People Liberation Front, TPLF, to rule until the second coming of Jesus Christ.” The unrepentant Samora said in 2007 after the late Zenawi gave him a comparative reward by promoting him to the rank of a General.
      Furthermore, well placed sources inside the TPLF camp told the Horn Times that Samora used the promotion to amass wealth through corrupt practices and now he is the sole owner of a multi-million dollar shopping complex built in Addis Ababa’s Gofa Sefer district, next to St Gabriel orthodox church.
      “I recently visited his glittering bronze statue which is placed at the prestigious Bete Mezeker library in Addis Ababa. Samora is well prepared for life after death.” A political analyst who requested anonymity said.
      infohorntimes@gmail.com
      Fax-o866502023

      Friday, December 28, 2012

      ሰበር ዜና በቡሬ ግንባር ሰራዊቱ እርስ በእርስ ተዋጋ


       ታህሳስ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
      ኢሳት ዜና:-የኢሳት የመከላከያ ምንጮች እንደገለጡት በቡሬ ግንባር በሚገኙ የመከላከያ ሰራዊት  አባላት መካከል ማንዳ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ማክሰኞ ሌሊት የተጀመረው የእርስ በርስ ጦርነት እስከ እኩለቀን ዘልቆ እንደነበርና አሁንም ውጥረቱ እንዳለ መሆኑን ለማወቅ ተችሎአል።
      የእርስ በርስ ጦርነቱ እንደተጀመረ የአካባቢው ነዋሪ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ጦርነት ጀመሩ በሚል ቀየውን ለቆ የተንቀሳቀሰ ሲሆን፣ ከፍተኛ ወታደራዊ ባለስልጣናት በሄሊኮፕተር እየተንቀሳቀሱ ጦርነቱን ለማስቆም ጥረት ሲያደርጉ እንደነበር ምንጮቻችን ገልጸዋል።
      40 ወታደሮች መሞታቸውን እንዲሁም ከ39 በላይ ደግሞ መቁሰላቸውን ከማንዳ ሆስፒታል የተገኘ መረጃ ያመለካተ ሲሆን፣ ሆስፒታል ሳይደረሱ የሞቱ፣ ወደ መቀሌ ሆስፒታል በሄሊኮፕተር የተወሰዱ ወታደራዊ አዛዦች መኖራቸውንም ለማወቅ ተችሎአል።
      ዘግይቶ በደረሰን ዜና ደግሞ 15 ወታደሮች ወዲያውኑ መሞታቸውን ፣ 12ቱ ደግሞ ለሞት ሲያጣጥሩ በአይናቸው ማየታቸውን አንድ ስማቸውም ድምጻቸውም እንዳይተላለፍ የጠየቁ በሆስፒታሉ ውስጥ የሚሰሩ ነርስ ተናግረዋል።
      የግጭቱን መንስኤ በትክክል ለማወቅ አልተቻለም። አንዳንድ ወገኖች ግጭቱ በህወሀት ወታደራዊ ባለስልጣናት መካከል በተፈጠረ አለመግባባት የተነሳ ነው ሲሉ ሌሎች ወገኖች ደግሞ በህወሀት ደጋፊ ወታደሮችና በተቀረው ሰራዊት መካከል የተፈጠረው አለመግባባት ነው ይላሉ።  ኢሳት የግጭቱን ትክክለኛ ምንጭ ለማወቅ ጥረት እያደረገ ነው።
      ማንዳ ከቡሬ ግንባር 21 ኪሎሜትር የሚርቅ ሲሆን፣ ግጭቱ በትክክል የተነሰባት ቦታ አሊ ፉኑ ዳባ እየተባለ በሚጠራው የጎሳ መሪ ስም በተሰየመ አሊ ፉኒ አካባቢ ነው። ግጭቱ በዚሁ ስፍራ ይጀመር እንጅ ወደ አራት አጎራባች አካባቢዎች ተሰራጭቶ እንደነበር ምንጮች አመልከተዋል።
      ከትናንት በስቲያ እና ትናንት ውጥረቱ እንደነበር ለማወቅ የተቻለ ሲሆን፣ ምናልባትም ግጭቱ እንደገና ሊያገረሽ ይችላል በሚል ስጋት የአካባቢው ሰዎች ቀያቸውን እየለቀቁ ነው።
      የቡሬ ግንባር ዋና እዝ መቀሌ የሚገኝ ሲሆን፣ በሰሜን እዝ አዛዥ ጄነራል ሳእረ መኮንን እንደሚመራ ይታወቃል።
      ቡሬ ግንባር የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከባድመ ቀጥሎ ሀይሉን በብዛት ያሰማራበት ቦታ መሆኑ ይታወቃል። ኢሳት በቅርቡ በሰሜን ግንባር የተመደበን አንድ የመከላከያ ሰራዊት አባል በማናገር በሰራዊቱ ውስጥ ያለውን ችግር መዘገቡ  ይታወሳል።
      በሌላ ዜና ደግሞ በአካባቢው ለሚንቀሳቀሰው የአፋር ጋድሌ ሚሊሺያ ሀይል ወጣቶችን ትመለምላላችሁ የተባሉ የሚሊሺያው ወታዳራዊ አዛዥ የሆኑት የኮሎኔል ሙሀመድ አህመድ 4 የቅርብ ዘመዶች ተይዘው ታስረዋል። በአካባቢው ከፍተኛ ውጥረት መንገሱንና መንግስትም ካለፉት ሁለት ሳምንታት ጀምሮ በርካታ ወታደሮችን ማስፈሩን መዘገባችን ይታወሳል።

      የኢትዮጵያውያን ግጭት በሳውዲ


      በዋና ከተማዋ በሪያድ ና በሌሎችም ከተሞች በሚገኙ ኢትዮጵያውያን መካከል የሚነሳው ግጭት አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ኢትዮጵያውያን ነዋሪዎች አስታወቁ ። ነዋሪዎች ለዶቼቬለ እንደተናገሩት በህገ ወጥ መንገድ ወደ ሳውዲ የሚገቡ ኢትዮጵያውያን በብሔር ተከፋፍለው እንዲሁም በቂም በቀል በሚፈጥሩት ግጭት ለሞት ለከፋ የአካል ጉዳት እየተዳረጉ ነው ።
      በህጋዊ መንገድ ወደ ሳውዲ አረቢያ የሚሄዱት ኢትዮጵያውያን አያያዝ አሳሳቢነት ተደጋግሞ በሚነሳበት በአሁኑ ወቅት በዋና ከተማዋ በሪያድ ና በሌሎችም ከተሞች በሚገኙ ኢትዮጵያውያን መካከል የሚነሳው ግጭትና መዘዙ አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ኢትዮጵያውያን ነዋሪዎች አስታወቁ ። ነዋሪዎች ለዶቼቬለ እንደተናገሩት በህገ ወጥ መንገድ ወደ ሳውዲ የሚገቡ ኢትዮጵያውያን በጎሳ ና በብሔር ተከፋፍለው እንዲሁም በቂም በቀል በሚፈጥሩት ግጭት ለሞት ለከፋ የአካል ጉዳት እየተዳረጉ ነው ። ለዚህም ነዋሪዎቹ በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ በኢትዮጵያውያን መካከል በተፈጠረ ፀብ ሞቱ የተባለውን ኢትዮጵያውን በቅርብ ጊዜ ምሳሌነት ያነሳሉ ። የጅዳው ወኪላችን ነብዩ ሲራክ ዝርዝር ዘገባ አለዉ።
      ነብዩ ሲራክ
      ሂሩት መለሰ
      ነጋሽ መሐመድ

      Audios: http://www.dw.de/popups/mediaplayer/

      contentId_16486558_mediaId_16486552

      በኢትዮጵያ ለሚገኙ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች የቀረበ ጥሪ !


      በኢትዮጵያ ለሚገኙ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች የቀረበ ጥሪ !
      የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የሚባለውን የወያኔ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ፤ በኢትዮጵያ ውስጥ በወያኔ መንግስት የተሾመ ለወያኔ ማፊያ ቡደን የሚያገለግል እንደሆነ በረጅም አመት የማጭበርበር የስራ ልምዱ አስመስክሯል ። ይህ ድርጅት ገለልተኛ እንዳልሆነ እየታወቀ በኢትዮጵያ የሚገኙ ከ 34 በላይ የሚሆኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች ወያኔን በማይገባው ቛንቛ በሰላማዊ ትግል ታግሎ ወያኔን ለማስወገድ ውጤታማ ያልሆነ ልፋት እየለፉ ይገኛሉ ።
      እነዚህ የተሰባሰቡት ፖለቲካ ፓርቲዎች የሚከተሉት ሰላማዊ ትግል በጣም ዘመናዊ እና የሚዎደድ ቢሆንም ወያኔን የመሰለ ዘረኛ እና የተደራጁ የማፊያ ቡድኖችን ከስልጣን ለማስወገድ ትክክለኛ አካሄድ አይመስልም ። እነዚህ ድርጅቶች በ አሁኑ ሰአት በወያኔዎች የሚመራው የምርጫ ቦርድ መፍትሄ እንደማይሰጣችው እየታወቀ ለዚህ ድርጅት ጥያቄ ማቅረብ ጊዜን ከማባከን በተጨማሪ አምባገነኑን የወያኔ መንግስት በስልጣን ላይ እንዲቆይ እድሜውን ለማራዘም እድል እንደመስጠት ይቆጠራል።
      እነዚህ የወያኔ ቡድን በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የሚያደርሰው አድለዎ ፣ አፈና ፣ዘረኛነት እና አምባገነናዊ አገዛዝን በመቃዎም ብሎም የሃገራችን ህዝብ የስልጣን ባለቤት እንዲሆን ለማድረግ በሰላማዊ መንገድ እየታገሉ ያሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች አሁን በወያኔ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ወይም ምርጫ ቦርድ እየደረሰባቸው ያለውን ጫና መቛቛም ከማይችሉበት ደረጃ ላይ መድረሳቸውን እየተናገሩ ይገኛሉ ።
      እነዚህ የምርጫ ቦርድን ጥያቄ ለመጠየቅ የተሰባሰቡ እና በሃገር ውስጥ የሚገኙ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲ ሰብስብ  የኢትዮጵያ ህዝብን የስልጣን ባለቤት እንዲሆን ባላችው አቅም እየታገሉ ይገኛሉ ። ነገር ግን ገዡ ቡድን ከአምባገነንነቱ የተነሳ ተቃዋሚዎች  ህዝብን እንኳን ሰብስበው ማዋያየት የማይችሉበት ደረጃ አድርሷቸዋል ።
      ስለዚህ ተቃዋሚዎች እንታገልለታለን የሚሉትን የኢትዮጵያ ህዝብን ማዋያየት እንኳን በማይችሉበት ሁኔታ፤ የገዡ መደብ ባስቀመጠላቸው አቤቱታ የማቅረብ መብት ብቻ የኢትዮጵያን ህዝብ ከወያኔ አምባገነናዊ አገዛዝ ነጻ ለማውጣት ከመታገል ይልቅ ፤ የችግሩ ገፈት ቀማሽ የሆነውን የኢትዮጵያን ህዝብ ለመብቱ እንዲታገል አስቸኳይ ጥሪ ማቅረብ እና ህዝባዊ ትግሉ ውጤታማ እንዲሆን መምራት አማራጭ የሌለው አማራጭ ነው ።
      የምትጠሩትን ህዝባዊ እና ሰላማዊ የትግል ጥሪ የኢትዮጵያ ህዝብም ተቀብሎ የስልጣን ባለቤት ለመሆን ፣ የሚጠቅመውን የመምረጥ የማይጠቅመውን የመሻር እና በሃገሩ ባይተዋር የማይሆንበት ስረዓት እንዲኖረው ወደ ትግሉ በቆራጥነት መቀላቀል ሃገራዊ ግዴታው ነው ።

      መንግስት የኢንተርኔት ድረገጾችን እና ብሎጎችን እንደሚያፍን በይፋ አመነ


      ታህሳስ ፲፱ (አስራ ዘጠኝቀን ፳፻፭ /

      ኢሳት ዜና:-አንዳንድ የኢንተርኔት ድረገጾች እና ብሎጎች በኢትዮጽያ እንደሚታገዱ የኢንፎርሜሽን ደህንነት ኤጀንሲ ዋናዳይሬክተር ብርጋዴር ጄኔራል ተክለብርሃን ወልደአረጋይ በይፋ አረጋገጡ፡፡

      /ጄኔራሉ ሰሞኑን ለንባብ ከበቃው መንግስታዊው “ዘመን” መጽሔት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ እንዳረጋገጡት አንዳንድአስጊ ናቸው ያሏቸውን የኢንተርኔት ድረገጾችና ብሎጎችን ማገድ የኤጀንሲው  ስራ አለመሆኑን፤ ነገር ግን በመርህደረጃ መደረግ አለባቸው ብሎ ማስቀመጡን ጠቅሰዋል፡፡ለዚህ ደግሞ ቴሌ እንዲያጣራቸው አቅም የመገንባት ስራእንሰራለን፡፡ከተቻለ ደግሞ ከሃይማኖት፣ከዘር፣ከሽብርተኝነት፣ከሕዝብ ሞራል ጋር የተያያዙ ድረገጾች ወደ ኢትዮጽያእንዳይገቡ ጥረት ይደረጋል” ሲሉ ተናግረዋል፡፡

      የሃይማኖት አክራሪነት አንድ ስጋት ነው፡፡ከዚያ አልፎ ሽብርተኝነት አለ፡፡ሕዝቡ በስነልቦና እንዲሸበር
      ፍርሃት፣ጭንቀት፣አለመተማመን እንዲሰፋ፣ ወጣቱ በሙሉ አቅሙ ወደ ልማትና ዴሞክራሲ ግንባታ እንዳይገባ የሚያደርጉ ኃይሎች አሉ ” ያሉት /ጄኔራሉይህን ለመቆጣጠር ኢንተርኔትን መሰረት ያደረገ የመከላከያ አቅም መገንባት ያስፈልጋልሲሉ ገልጸዋል፡፡

      /ጄኔራሉ በዚሁ ቃለምልልሳቸው መረር ብለው “የኢትዮጽያ ቴሌኮምኒኬሽን የኀብረተሰቡን ሰላም የሚያጠፉዌብሳይቶችን የመቆጣጠር አቅም ሊኖረው ይገባል፡፡መርሁ ይህ ነው፡፡ለኀብረተሰቡ የሰላምና የልማት አጀንዳ እንቅፋትሊሆኑ የሚችሉ የመቆጣጠር ብቃት አስፈላጊ ነው” ብለዋል፡፡

      ስርዓት ያልተበጀለት ኢንተርኔት ጉዳቱ ሰፊ ነው” የሚሉት /ጄኔራል ተክለብርሃን “ሕገመንግስቱንም ሆነ የሕዝቡን ሰላም የሚጻረሩ እንቅስቃሴዎች ሊፈቀድላቸው አይገባም” ብሎ አስቀምጧል ሲሉ አስረድተዋል፡፡

      የኢትዮጽያ መንግስት በኢንተርኔት ድረገጾች እና ብሎጎች ላይ አፈና በማድረግ የዜጎችን ሀሳብን በነጻ የመግለጽ
      ነጻነት የሚጻረሩ ሕገወጥ እርምጃዎችን ይወስዳል በሚል የሚቀርብበትን ተደጋጋሚ ክሶች፤ መሰረተ ቢስ ናቸው በሚል ሲያጣጥል መቆየቱ አይዘነጋም፡፡