Tuesday, December 25, 2012

ሰብአዊ መብትና: መንግሥታዊ ግፊት በኢትዮጵያ (2012)


ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ
በዲሴምበር 2008 ላይ በኢትዮጵያ የ‹‹ለውጥ የሌሽ ዓመት›› በማለት እንጉርጉሮ መሰል መልእክት ጽፌ ነበር፡፡
2008 የ2007፤2006፤2005፤2004 ቅጂ ነበር… በየቀኑ ኢትዮጵያዊያን ሲነቁ ልክ እንደተሰበረ የሙዚቃ ሸክላ ባለፈው የሕይወት ስቃያቸውድግግሞሽ መከራ ውስጥ በመዳከር ነበር የሚገኙት፡፡ እያንዳንዱ አዲስ ቀን ካለፈው የወረሰውን ይዞ ነበር የሚመጣው፡፡ ጫና፤ማስፈራራት፤ ንቅዘት፤እስራት፤ ማጭበርበር… ጭካኔና የሰብአዊ መብት ገፈፋ… ከዚህ ክፉ ከሆነው የስቃይ፤ የጣረሞት ግርዶሽ፤ አዙሪት፤የተስፋ እጦት፤ ውጣ ውረድ መከራ እንዴት እንደሚገላገሉ መንገዱን አያውቁትም፡፡ ስለዚህም ከዚህ መዓት ለመገላገል ያላቸው አንድተስፋ መጸለይ፤ መጸለይ፤ ደሞ መጸለይ ብቻ ነበር::አሁን 2012 ዲሴምበር ነው::ኢትዮጵያዊያኖች በ 2008፤ 2009፤ 2010፤ 2011፤ ከነበሩበት ሁኔታ አሁን የተሸለ ላይ ናቸው?የጤፍ ዋጋ በ2008 ከነበረው ዋጋ ቀነሳል? አምና ከነበረው?የምግብ ዘይት፤ የምርት ውጤቶች፤መሰረታዊ የምግብ አቅርቦት፤ ሥጋ፤ ዶሮ፤ እንቁላል፤ ቤት፤ ውሃ፤ መብራት፤ የምድጃ ጋዝ፤ ናፍጣ…..?ዛሬ በኢትዮጵያ በ2008 ከነበሩት ድሆች ቁጥራቸው ጨምሯል? የባሰ ችጋር፤ ቤት አልባነት፤ ሥራ አጥነት፤ የጤና ችግር፤ አንስተኛ የትምህርት እድልለወጣቶቹስ?በ2008 ከነበረው ያነሰ ሙስና አለ? ድብቅነት: ያነሰ ግልጽነት ተጠያቂነት በ2012 አለ?በ2008 ከታየው የምርጫ ነጻነትና ፍትሃዊነት በ2012 አለ?በ2008 ከነበሩት የፖለቲካ እስረኞች ቁጥር አሁን ቁጥራቸው የበዛ ይገኛሉ?በ2008 ከነበረው የፕሬስ ነጻነት ያነሰ እና ካለፈው በጣም የበዙ ጋዜጠኞች በወህኒ ቤት በ2012 ይገኛሉ?በ2012 ኢትዮጵያ ለዜጎቿ ምግብ አቅርቦት ከውጭ በሚቸር ምጽዋት ላይ በ2008 ከለመነችው የበለጠ ትጠይቃለች?ኢትዮጵያ አሁንም በሰብአዊ መብት መድፈር በተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት መዝገብ ላይ በመጨረሻው ደረጃ ላይ ነች?በ2012 የኢትዮጵያ መንግሥት የስርአት ግፊቶች ማስረጃዎችአሁንም በተባባሰ ሁኔታ በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ደፈራ ሁኔታ፤ በማያቋርጥ መልኩ በዋናነት ከሚጠቀሱ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችና እናከሌሎች ከሚመለከታቸውና ከሚያሳስባቸው፤ አካላት ያለው አገዛዝ ውግዘቱ እየደረሰበት ነው፡፡ በ2012 ገዢው ፓርቲ፤ በባሰ ሁኔታከማይስማሙትና ከተቃዋሚዎች ጋር በመግባባትና መቻቻል ፈንታ በመታበት ጨቋኝና አዳዲስ አመለካከቶችን ለመቀበል የማይሻ ሆኗል፡፡ ይሄአገዛዝ የራሱን ሕገ መንግሥት መናድ፤ ውል የገባበትን ዓለም አቀፍ ድንጋጌዎች መጣስ እና ነቃፊዎቹ ላይ ተጸኖ ማድረጉን አላቆመም:: አንዳንድሰዎች መለስ ካለፈ በሆላ የተሻለ ሊሆን ይችላል ብለው ቢያስቡም፤ የተቃዋሚዎችን አንዳንድ ሃሳቦች መቀበል፤የሰብአዊ መብት ወንጀሉንምበመጠኑም ቢሆን ለማስመሰልና በማለባበስ፤ የመሻሻል ቀን ቢጠበቅም ከራስ ጸጉራቸው እስከ እግር ጥፍራቸው ድረስ ስብእናቸውን ወደ መለስግልባጭነት ለመለወጥ በሚጣጣሩት በኩል ያለው ሁኔታ፤ ‹‹ወይ ፍንክች ያባ ቢላ ልጅ›› ከመለስ መርህ ሌላ ብለዋል፡፡ በእውር ድንብራችንም ቢሆንየመለስን ራእይ እንከተላለን፤ ማለትም 2013፤ 2014፤ 2015… ከ20012 ወይም ከ2008 አንዳችም ለውጥ አይኖርም ባይ ናቸው፡፡በኢትዮጵያ የሚታየው ሥልጣንን መከታ ያደረገ ግፋዊ የሰብአዊ መብት መደፈር እንደሚያረጋግጠው እጅጉን የከፋ ለመሆኑ ማስረጃው በራሱይመሰክራል፡፡የዩ ኤስ ስቴት ዲፓርትመንት የሰብአዊ መብት እንቅስቃሴ መንግስታዊ ድፍረት በኢትዮጵያ (ሜይ 2012) ድምዳሜ፡-በኢትዮጵያ ጉልሁ የዜጎች ሰብአዊ መብት መደፈር 100 የፐለቲካ ተቃዋሚ አባላት፤ ንቁ የፖለቲካ ተሳታፊዎች፤ ጋዜጠኞች፤ ብሎግአድራጊዎች በመንግስት ለእስር መዳረጋቸው ነው፡፡……. መንግሥት የፕሬስ ነጻነትን ገድቧል፤የእስርና የእንልት ፍርሃት ጋዜጠኞችንእራሳቸውን ሳንሱር እንዲያደርጉ አድርጓቸዋል፡፡ የችሮታና የማሕበረሰቦች አዋጅ (ሲ ኤስ ኦ ሕግ) መንግስታዊ ያለሆኑ ድርጅቶችእንቅስቃሴና ተግባርና ሌሎችም የሰብአዊ መብት መደፈር ድርጊቶች፤ስቃይን፤ድብደባን፤ጉስቁልናንና ማዋረድን፤በደህንነት ሰዎችመንገላታትን፤ሕይወትን የሚፈታተንና ለሞትም ሊያደርስ በሚችል የወህኒ ቤት ሁኔታ መታሰርን፤ ያለ ፍርድ ቤት ትእዛዝ መያዝንናከእስርም በኋላ በማያልቅ ቀጠሮ መቸገርን፤ ሕገ ወጥና ማስረጃ ያለቀረበበት በሶማሌ ግዛት በሚካሄደው ግጭት ላይ በሚመሰረት መሰረተቢስ ክስ ለስቃይ መዳረግ፤የመሰብሰብ ነጻነትን፤ የማሕበራት መደራጀትን፤ ማገድ፤ የፖሊስ አባላትና አመራሩ፤የመስተዳድሮች፤ የፍትህአካላት በሙስና መዘፈቅ…ላይ ይገኛል ሲል አተቶል::የሁማን ራይትስ ዎች ድምዳሜ:የኢትዮጵያ መንግስት ሃሳብን በነጻ የመግለጽን የማህበራትን በነጻ የመደራጀትን፤የመሰብሰብን፤መከልከልን በባሰ ሁኔታ ቀጥሎበታል፡፡በ2011በመቶ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ከሕግ ውጪ ተይዘው በወህኒ ይገኛሉ፤እስካሁንም ድረስ በስቃይና በሚጎዳ እስር ውስጥ ስቃያቸውእንዳለ ነው፡፡ሴፕቴምበር 2011 ድረስና ከዚያም በኋላ፤ የኦሮሞ ተወላጆችን በገፍ ማሰር፤የተቃዋሚውን የኦሮሞ ነጻ አውጪ ድርጅትንአባላት ጨምሮ በማርች ጋዜጠኞችን፤የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትን፤ከጁን እስከ ሴፕቴምበር ድረስ አፈናውን በማጠናከር የጸረ ሽብርተኛአዋጅን መሳርያ በማድረግ ብዙዎች ለግፍ ወህኒ ተዳርገዋል፡፡የፍሪደም ሃውስ ድምዳሜ:የፖለቲካ መብትንና የሲቪል ማሕበረሰቡን መብት በመድፈር ረገድ አሁን ኢትዮጵያ በ2012 በዓለም አሁንም ዝቅ ብላ 6ትገኛለች::በኢትዮጵያ ያለው የፖለቲካ ሕይወት አሁንም በአቶ መለስ ዜናዊ ከ1995 ጀምሮ እስከ ህልፈታቸው ድረስ ይመራ በነበረው በገዢው ፓርቲኢ ፒ አር ዲ ኤፍ መዳፍ ስር ነው፡፡ የሜይ 2011 የፌዴራልና የክልል ምርጫዎች፤በጥብቅ በኢ ፒ አር ዲ ኤፍ ቁጥጥር ስር ነበረ:: ገዢውንፓርቲ ያልደገፉ መራጮች ዛቻና ማስፈራሪያ ይደረግባቸውና ገዢውን ፓርቲ እንዲመርጡ ይገደዱ ነበር፡፡ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ስብሰባበደህነነቶችና በፖሊስ ሃይል ይበተኑና መሪዎችም በቁጥጥር ስር ይውሉ ነበር፡፡ ኢ ፒ አር ዲ ኤፍ የጸረ ሽብርተኝነት አዋጁን፤ተቃዋሚዎችንናየነጻው ፕሬስ አባላትን ለማሰርና ለማንገላታት የሚጠቀምበት መሳርያ ነው፡፡ ፓርላማው በርካታ ተቃዋሚዎችን ሽብርተኞች በማለትየተቃዋሚዎችንም ዘገባ የሚያትሙትን የነጻው ፕሬስ አባላት በሽብርተኝነት ፈርጇል፡፡ ለእስር ዳርጓል፤ ለስደት አብቅቷል፡፡ ሚዲያውየተያዘው በመንግስትና መበንግስት ቁጥጥር በሚንቀሳቀሱ ጣቢያዎችና ሰራተኞቻቸው ሕትመቶችና የመንግስት ተቀጣሪ ሰራተኞች ነው፡፡በ2009 የወጣው የመንግስታዊ ያልሆኑ መጽዋች ድርጅቶች ሕግ ድርጅቶቹ በሰብአዊ መብት ጉዳይና በፖለቲካ የፋይናንስ አርድታ ላይእንዳይንቀሳቀሱ አግዷቸዋል፡፡ ማንኛውም ሃገራዊ ድርጅትም ከውጪ ለጋሽ ድርጅቶች ሊያገኝ የሚገባውን መጠን ገድቦታል፡፡ ይህም ሕግመንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን እንዳይንቀሳቀሱ ግዑዝ አድርጓቸዋል፡፡ የፍትሕ አካሉ ለይስሙላ ነጻ ነው ይባላል፤ ውሳኔውም በአብዛኛውመንግስታዊ ሃሳብን ብቻ የሚደግፍ ነው፡፡አምነስቲ ኢንተርናሽናል ‹‹የኢትዮጵያ መንግሥት የመለስን መተካት እንደ አለፈው ማረሚያና ማስተካከያ በመውሰድ ካለፈው በተለየሁኔታ፤በመንቀሳቀስ ተቃዋሚ የሆነን ማንንም ከመያዝና ማንም ለእስር እንዳይደረግ›› መሆን አንዳለበት ገልጻል፡፡የማጣራያ ባለሙያዎች የሆኑትና በተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ካውንስል እውቅናና ይሁንታ የተሰጣቸው ልዩ ራፖርተ ማዕና ኪያይበ2012 ይፋ የውግዘት መግለጫ በማውጣት ገዢው ፓርቲ የጅምላ ክስ በጸረ ሽብርተኝነት አዋጁ በመታገዝና አዋጁን ለራሱ በሚጠቅም መልኩመጠቀሚያ በማድረግ፤ ነጻነትን በመግፈፍ፤ በሚያሳዝንና በዓይነ ደረቅነት፤ቀጣይ እንዲሆን እያደረገ፤ የሰብአዊ መብትን መድፈሩን ቀጥሎበታል፡፡በሰላማዊ መንገድ የመሰብሰብና የሙያ ማሕበራት መደራጀት ልዩ የተባበሩት መንግስታት ባለሙያ ራፖርተር፤ ሲደመድም፡-በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ባሉ ማሕበራት ላይ ታላቅ ችግር በመፍጠር እንቅስቃሴያቸውን እያገደ ያለው፤ በሃገሪቱ ላይ የተጫነው የጸረሽብር አዋጅነው፡፡ ገዢው መንግስት በሁሉም ዘርፍ ያሉትን በተለይም የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችን እንቅስቃሴ የነጻነት ዋስትና ሊሰጥ የግድ ነው፡፡የተባበሩት መንግሥታት በጸረሽብርና ሰብአዊ መብት ድንጋጌ ልዩ ራፖርተር ቤን ኤመርሰን፤ ሲናገሩ የጸረሽብርተኝነቱ አዋጅ ለመጉጃነት ሊውልስለማይገባ በኢትዮጵያ የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ላይ የዓለም አቀፉን የሰብአዊ መብት ድንጋጌ የማይጥስና በተቃርኖ የማይጓዝ መሆኑ ሊረጋገጥ ተገቢነው ብለዋል፡፡ማርግሬት ስካግያ፤ የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ድፍረት መከላከያ ራፖርተር ጋዜጠኞች፤ ብሎገርስ፤እና ሌሎችም ስለሰብአዊ መብትመከበር የሚሟገቱ ገና ለገና ሃሳባቸው ከኢትዮጵያ መንግስት አስተሳሰብና አካሄድ ጋር ስለማይስማማ ብቻ ጫና ሊፈጠርባቸው አይገባም ብለዋል፡፡ገብሪየላ ናውል የተባበሩት መንግስታት በዳኞችና በጠበቆች ነጻነት ልዩ ራፐርቱዋር በወንጀል ፍርድ ሂደት ተከሳሾች ማስረጃ በማያጠራጥር መልኩእስካልቀረበባቸውና ወንጀለኛነታቸው እስክላተረጋገጠባቸው ድረስ በኢትዮጵያ ሕገ መንግስት ላይ በሰፈረው አይነት ንጽህናቸው በተግባርሊረጋገጥላቸው ተገቢ ነው:: እንዲሁም ተከሳሾች የሕግ ጠበቃቸውን ከችሎት ቀጠሯቸው አስቀድሞ የማነጋገር መብታቸው ሊጠበቅና የመከላከያሃሳባቸውን ለማቅረብ እንዲችሉ ሊመቻችላቸው ይገባል16 የአውሮፓ ፓርላማ አባላት በዲሴምበር 18/2012 አንድ ግልጽ ደብዳቤ ለጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ አቅርበዋል፡፡ ደብዳቤውምጋዜጠኛና ብሎገር እስክንድር ነጋ በእስር መንገላታቱን የሚያሳስብ ነበር›› በደብዳቤያቸው ላይ ሲፅፉ የፓርላማ አባላቱ አንዳሉት የአቶ ሃእለማርአምመንግስት ኢትዮጵያ በፈረመችውና ልታከብረውም ቃል በገባችው በዓለም አቀፍ ድንጋጌው እንደሰፈረው በአርቲክል 19 ላይ በተቀመጠውመሰረት፤ኢትዮጵያ ቃሏን ማክበርና ለሕጉም ተገዢ የመሆን የአባልነት ግዴታ አስገንዝበዋል፡፡ገዢው መንግሥት በሃይማኖት ተቋማት ላይ የሚያካሂደውን ሕገ ወጥ ጣልቃ ገብነት መተው፤ ጉዳዩን ለባለቤቶቹ መልቀቅ አለበትየኢትዮጵያ ሕገመንግስት አንቀፅ 11 ‹‹የሃይሞኖትንና የመንግስትን ልዩነት›› በሚገባ አስቀምጧል፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት ዓለማዊ መንግሥት ለመሆኑዋስትና ስለሚሰጠው ‹‹ሃይማኖታዊ መንግሥት የለም››:: አርቲክል 27 ማንም ሰው በፍላጎቱና በምርጫው ያሻውንና ይሆነኛል ያለውን ሃይሞነትየመከተል መብቱ በራሱ ፈቃድ ላይ የተመሰረተና ማንም በጫናና በእዝ ሊያሳምነው እንደማይችል በግልጽ ሰፍሯል፡፡ በግልጽ የተቀመጠውንየሃይሞነት ተቋማትንና አማኞቹን የዜግነት ነጻነት በኢትዮጵያ ያለው ገዢ መንግሥት በሙስሊም አማኞች ላይ ሕጉን በሚጥስ መልኩ የራሳቸውንየሃይሞኖት መሪዎች በነጻ እንዳይመርጡ ጣልቃ በመግባት ችግር ፈጥሮባቸዋል፡፡ የራሱን ሕገመንግስትም እያፈረሰው ነው፡፡ እንደ አሜሪካውየሃይሞኖት ነጻነት ኮሚሽን በኮንግሬስና በአሜሪካ ፕሬዜዳንት የተዋቀረ ነጻ አካል በዓለም አቀፍ ደረጃ የሃይሞኖትን ነጻነት የሚቆጣጠር ሲገመግም: -ከጁላይ 2011 ጀምሮ የኢትዮጵያ መንግሥት በሙስሊም አማኝ ዜጎች ላይ በተለምዶ ለዘመናት ሲከተሉት የነበረውን ሱፊ የእስልምና እምነትአል-አባሽ በተባለው የአስልምና እምነት ሊተካባቸው እያስገደደ ነው፡፡ መንግስት በሌላ በኩልም የእስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ካውንስልምርጫ በራሱ ሰዎች ለመሙላት ምርጫ አካሂዷል፡፡ ቀደም ሲል እንደነጻ አካል ሆኖ ሲያገለግል የነበረው አሁን እንደመንግስት ተቋም ሆኖበመንቀሳቀስ ላይ ነው፡፡ አሁን ሽብርተኛ ተብሎ መፈረጅ መያዝ ለእስርም መዳረጉ መንግስት የኢትዮጵያን ሙስሊም አማኞች ለመቆጣጠርያደረገው ሲሆን፤ ድርጊቱ በሃገሪቱ ላይ ያለውን የሃይማኖት ነጻነት መገደብ በግልጽ ያሳያል፡፡ በሃገሪቱ በመላ የሙስሊም አማኞች ሰላማዊተቃውሟቸውን በሚያሰሙበት ጊዜ በመያዝ ላይ ናቸው:: በኦክቶበር 29 የኢትዮጵያ መንግስት 29 ተሟጋቾች በሽብርተኝነት ስምናየእስልምና መንግስት ለማቋቋም በሚል ማስረጃ ያለተሰጠበት ሰበብ አስሯል፡፡ገዢው አስተዳደር የራሱን ሕገመንግሥትና ዓለምአቀፋዊ ሕጋዊ ግዴታዎችን በማክበሩና በመተግበሩ ረገድ መታመን መቻልና የሙስሊሙንሕብረተሰብ እምነታቸውን በነጻነት እንዲከተሉ ጣልቃ ገብነቱን ሊያቆም ይገባል፡፡ ከተቃውሞው ሰላማዊ እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ በሕገወጥ መንገድየተያዙትና የሃይሞነት እምነታዊ ነጻነታቸው ተገፎ ለእስር የተዳረጉት ሁሉም በነጻ መለቀቅ አለባቸው፡፡ሁሉም የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱሰፋ ባለ አመለካከት በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ሁለት አይነት የፖለቲካ እስረኞች ይገኛሉ፡፡ የሕሊና እስረኞች አሉ፤ በገዛ ሕሊናቸው የታሰሩ ደሞአሉ፡፡ የሕሊና እሰረኞቹ የታሰሩበት ሰበብ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች እና ጋዜጠኞች በመሆናቸው የነው፡፡ ምንም አይነት ሕግ አልጣሱም ደንብአላፈረሱም፡፡ የፈጸሙት ነገር ቢኖር ለሕሊናም ሆነ ለደንቡ ትክክል የሆነውን ብቻ ነው፡፡ ስለዕውነት መስክረዋል ዕውነትን ተናግረዋል፡፡ለባለስልጣናትም እውነቱን ተናግረዋል፡፡ ፍትሕ ሲጓደል ተሟግተዋል፡፡ ስለነጻነት፤ ስለዴሞክራሲ፤ ስለሰብአዊ መብት መከበር፤የሕይወታቸውንከፍተኛ ዋጋ በመሰዋት፤በነፍሳቸውና በነጻነታቸው ተሟግተው ጠብቀዋል፡፡ በአንዲት የብዕር ጠብታ ነጻ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡በገዛ ሕሊናቸው የታሰሩት ደግሞ በሰብአዊ ፍጡር ላይ ከፍተኛውን ወንጀል በመፈጸማቸው፤ ይህንንም ሲያከናውኑ በመሃይምነት በመመራትየራሳቸውን ሕሊና ስተው ነው፡፡ እነዚህ እስረኞች በስልጣን የእ ንቅልፍ ኪኒን ደንዝዘውና ራሳቸውን ስተው ነው የሚገኙት፡፡ በአንድ ዕለት ለፍርድናበሕግ የበላይነት ተጠያቂ መሆናቸው እያባነናቸው ከራሳቸው ጋር በሙግትና ፍርሃት ላይ ናቸው፡፡ አንድ ቀን ሌሎችን በዳኙበት ሁኔታ ለፍርድቀርበው እንደሚፈረድባቸው ያውቃሉ፡፡ በሰፈሩት ቁና አንድ ቀን መሰፈር አይቀሬ ነው::በራሳቸው ሕሊና የታሰሩት የሕሊና እስረኞችን ቢለቁና ነጻነታቸውን ቢመልሱላቸው እነሱም ይፈታል ነጻም ይወጣሉ፡፡ አንድ ብቸኛ መዳኛቸውይሄው ብቻ ነው፡፡ በተቃራኒው ደግሞ የጋንዲን አደገኛውን ማስጠንቀቂያ መቀበል ነው፡፡ ‹‹ገዳዮችና ጨካኝ አምባገነኖች ነበሩ፤ ለጊዜውምየማይደፈሩ መስለው ነበር፤ በመጨረሻው ግን ዕጣ ፈንታቸው መውደቅ ነው፡፡—ምንግዜም መውደቃቸው አይቀሬ ነው:: ስለዚህ አስቡ!››የሕትመት ውጤቶችን ማፈኑ ይብቃናፖሊዮን ቦናባርት ‹‹ከሺ ጥይቶች ይበልጥ የሚያስፈሩት አራት የተቃዋሚ ጋዜጠኞት ናቸው ይል ነበር:: (ወይም ከሺ ጦረኛ 4 ጋዜጠኛ ይፈራል::)ይህ አባባል በኢትዮጵያ ላለው ገዢ ቡድን ትክክለኛ መልእክት ነው፡፡ ባለፈው ሳምንት 3 በእስር ወህኒ ቤት ያሉና አንድ ተገፍቶ ከሃገሩ የተሰደደአራት ጋዜጠኞች፤ የ2012 ን እጅጉን የተከበረውን ሄልማን/ሄሜት የሚባለውን ሽልማት ተሸላሚ ሆነዋል፡፡ ‹‹በዓለም እጅጉን በከፋ ሁኔታ ታፍኖያለውን የመናገር ነጻነትን እውን ለማድረግ ያደረጉትን ጥረት እውቅና በመስጠት ነው የተከበሩት፡፡ ተሸላሚዎቹም፤ እስክንድር ነጋ በግል የሚታገልጋዜጠኛ ብሎገርና የ2012 የኢንተርናሽናል ፔን ተሸላሚ፤ በሃገሪቱ ካሉት ጥቂት እንስት ጋዜጠኞች አንዷ የሆነችውና በጥንካሬና በአልበገር በይነትየዓለም አቀፍ የሴቶች ሚዲያ ተሸላሚዋ ርዕዮት ዓለሙ፤ ውብሸት ታዬ በመንግስት ጫና የፈረሰው የሳምንታዊው የአውራምባ ታይምስ ጋዜጣኤዲተር፤ በመንግስት ጫና የፈረሰውና አሁን በኢንተር ኔት ስራውን የቀጠለው የአዲስ ነገር ጋዜጣው መስፍን ነጋሽ ናቸው፡፡ እነዚህ የሚዲያ ጀግኖችለዚህ ታላቅ ሽልማት የበቁት ከተለያየ ሃገር ከቀረቡ 41 ጸሃፊዎች፤ ጋዜጠኞች ጋር ነው በማለት ሁማን ራይትስ ዎች ሲዘግብ:-የእነዚህ 4 የታሰሩና ለስደት የተዳረጉ ጋዜጠኞች አርአያነት በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የነጻ ጋዜጠኝነት አልበገር ባይነትና አደጋውንያሳያል፡፡ በነጻ ሃሳብን መግለጽ እንደ ክፉ ደዌ በሚቆጠርበት ዕውቀትና ነጻነት እንደጦር በሚፈሩ አምባገነኖች በምትመራ ሃገር ውስጥአደጋውና ስቃዩ የሚያሳየው ለነጻነት በቆሙና መስዋዕት ለመሆን በቆረጡ ላይ የሚያስከፍለውን መራር አበሳና ዋጋ ነው፡፡ ገዢው መንግስትበነዚህ በተሸላሚዎቹ ለስራቸውና ለቆሙለት ዓላማቸው ተግባራዊ አለመሆን ምን ያህል ጫና እንደተደረገባቸውና ነጻ እስትንፋስ ሳይቀርሊታገድ በሚሞከርበት የማያዛልቅ ጀብደኝነት የተቃጣባቸውን እንግልት እስራትና መከራ የሚያሳይ ነው፡፡እነዚህ ተሸላሚዎች በኢትዮጵያእየኖሩ እራሳቸውን ሳንሱር በማድረግ የቻሉትን ያህል ለመተንፈስ የሚሞክሩትንና ግፍና መከራው ሲበዛባቸው ሃገርን ጥሎ በመሰደድበእስራት የተንገላቱትን ሁሉ የሚወክሉ ናቸው፡፡ሁሉም ዲክታተሮችና ፈላጭ ቆራጭ ገዢዎች የነጻውን ፕሬስ የማስተማርና የማንቃት የማደራጀትና ለፍትሕ ለነጻነት መቆም ለዴሞክራሲ መታገልንእጅጉን ይፈሩታል፡፡ የሚዲያዎቹን ንብረትነት በግላቸው በመቆጣጠርና የነሱን ቱልቱላ ብቻ እንዲያስተላልፉ ሕሊናቸውን ለጊዜያዊ ጥቅምና ለራስወዳድነት ባሳደሩ ፓሮት ጋዜጠኞች ስለሚታገዙና የሃሳብን በነጻ መንሸራሸር ስላገዱ በዚህ ልክፍታቸው የሕዝቡን ልብና ህሊና ያሸነፉይመስላቸዋል፡፡ ይሄ ደሞ የቅዠት ምኞት ነው፡፡ ናፖሊዮን እንዳለው ‹‹ጋዜጠኛ ቁማርተኛ ነው፡፡ ገሳጭ ነው፡፡መካሪና የሃሳብ አጋሪ ነው፡፡ የነገስታትእንደራሴ ነው፡፡ የሕዝብ መምህር ነው›› ልክ እንደናፖሊዮን ፍርሃት የኢትዮጵያ እውቀት አልባ ዲካታተር ገዢዎችም ፍርሃት፤ የነጻው ፕሬስየማስተማር ሃይል ነው፡፡—-ማስተማር፤ ኢንፎርሜሽን ባለቤት ማድረግ፤ማስረዳት፤ ማሳወቅ፤ ሕዝቡን የዕውቀት ባለቤት ማድረግን፡፡….. የነጻውፕሬስ፤ ገዢዎች የሚፈጽሙትን ደባና ቅጥ ያጣ ድርጊታቸውን፤ በሕዝቡ ላይ የሚያሳድሩትና መከራ፤ በማጋለጥ ተጠያቂ እንደሚያደርጋቸውናየሕዝብ አጋርነቱን በሚገባ ስለሚረዱ ነው ፍርሃታቸው፡፡ ገዢዎቹ የኢትዮጵያ ባለስልጣናትም እንደ ናፖሊዮን ነጻ የፕሬስ ሰዎችን፤ ማሰቃየት፤ማሰር፤ ሳንሱር ማድረግ፤በመሳርያ ማስጨነቅን ስራዬ ብለው ተያይዘውታል፡፡ ሕዝቡን ማለቂያ የሌላቸው በሚመስሉ በሆዳቸው በሚያስቡ ሕሊናቢስ የደህንነት አባላት በመክበብ፤በመግደል በማሰር የፖለቲካ ተቃዋሚዎቻቸውን ለእስር በመዳረግ፤ በሰላማዊ መንገድ መብታቸውን ለማስከበርበባዶ እጃቸው የወጡ ዜጎችን ኢላማ እያደረጉ በመግደል ዘለአለማዊ መሆን የሚቻል ይመስላቸዋል፡፡ የነጻው ፕሬስ አባላት የሚያስተምሩትየሚያሳውቁት፤ የነጻነትን ጥቅም የሚገልጡት ለተወሰነ ማሕበረሰብ ሳይሆን ለገዢው መንግስትና በገዢው መንግስት ቁጥጥር ስር ለዋሉትም ጭምርነው፡፡ እሱም ገዢው ፓርቲ ጥፋቱን ሲረዳውና የሚያስከትልበትን ተጠያቂነት፤ የኔ በሚላቸውም አገልጋዮቹ ሳይቀር ለምን? ማለት እንደሚጀመርሲረዳው ከፍርሃቱ የተነሳ የነጻውን ፕሬስ አባላት ለግፍና መከራ መዳረጉን ያጠናክራል፡፡ እነዚህ ተሸላሚዎችም የዚህ መከራና ጫና ፍትህ እጦትሰለባ ናቸው፡፡ሁሉም ለእስር የተዳረጉ የነጻው ፕሬስ አባላት አሁኑኑ ሊፈቱ ይገባል::“ሠላማዊ ለውጥን የሚያግዱ በቁጣ የሚቀሰቀስ አመጽን ያስነሳሉ::”› ጆን ኤፍ ኬነዲ==========ፕሮፌስር ዓለማየሁ ገብረማርያም በካሊፎርኒያ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ሳን በርናርዲኆ የፖሊቲካ ሳይንስ መምሀርና የህግ ጠበቃ ናችው።*የተቶረገመው ጽሁፍ (translated from):




No comments:

Post a Comment