Tuesday, December 25, 2012

አዲስ ራዕይ የተሰኘ መጽሄት በሁሉም የመንግስት መ/ቤት ሰራተኞች ዘንድ በግዳጅ እየተሸጠ ነው


ታህሳስ ፲፭(አስራ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-በሟቹ የቀድሞ ጠ/ሚ/ር መለስ ዜናዊ የስራ ታሪክ ዙሪያ የሚያጠነጥን አዲስ ራዕይ የተሰኘ መጽሄት በሁሉም የመንግስት መ/ቤት ሰራተኞች ዘንድ በግዳጅ በ 100 ብር እየተሸጠ መሆኑ ተገለጸ::
ከሀገር ቤት የኢሳት ምንጮች እንደገለጡት በጠ/ሚሩ ህይወት ዙሪያ የሚያጠነጥነውን አዲስ ራዕይ የተሰኘ መጽሄት ከ 2000 ብር በላይ ደሞዝተኛ የሆነ በአንድ ክፍያ 100 ብር ለመግዛት ይገደዳል ከ2000 ብር በታች ደመወዝ ያለው እንደደሞዙ ልክ በየወሩ ይቆረጥበታል::
የተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤት ሰራተኞች በስብሰባ ተነግሯቸውና ሳያቁ እንዲፈርሙ ተደርጎ ከደመወዛቸው ለአዲስ ራዕይ መጽሄት 100 ብር መወሰዱን ቢቃወሙም ሰሚ እንዳላገኙ አስታውቀዋል::
የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር በህይወት ዘመናቸው የሰሩትን ስራ አጉልቶና አኩርቶ ይተርካል በተባለው መጽሄት የግዢ  ድርድር የሚባል ነገር የለም ሁሉም ሰራተኛ በአንድ መቶ ብር የመግዛት ግዴታ እንዳለበት በግልጽ ተነግሯል እንደ ምንጮቻችን ዘገባ

No comments:

Post a Comment