Monday, December 31, 2012

አቶ ጁነዲን ሳዶ ያለመከሰስ መብታቸው እንዲነሳ የሚጠይቅ ደብዳቤ ለፓርላማ መቅረቡ ተገለጠ


ታህሳስ  ፳፪(ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ከሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትርነታቸውና ከኢህአዲግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልነታቸው የተባረሩት አቶ ጁነዲን ሳዶ ያለመከሰስ መብታቸው እንዲነሳ የሚጠይቅ ደብዳቤ ለፓርላማ መቅረቡ ተገለጠ::
ሪፖርተር ጋዜጣ በሮብ እትሙ የምክር ቤቱ የቅርብ ምንጮቹን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው አቶ ጁነዲን ሳዶ በፓርላማ የስነስርአት ደንብ መሰረት ሊጠየቁበት የሚችል የህግ ጉዳይ ሊኖር ስለሚችል በም/ቤቱ አባልነታቸው ያገኙትን ያለመከሰስ መብት ም/ቤት እንዲያነ ሳ በመንግስት ተጠይቆል::
ም/ቤቱ ሀሙስ እለት ባካሄደው ስብሰባ በአምስት አጀንዳዎች ለመወያየት አቅዶ እንደነበር ያመለከተው ሪፖርተር በአራቱላይ ብቻ ተወያይቶ የምክር ቤት አካልን የህግ ከለላ ስለማንሳት የቀረበ የውሳኔ ሀሳብን መርምሮ ማጽደቅ የሚለውን አጀንዳ በቀጣይ ስብሰባ እንመለከታለን በሚል መዝለሉን አስረድቶል::
የምክር ቤቱ አባላት ለጉባኤው የሚቀርቡ አጀንዳዎችን ቀደም ብሎ በማወቅና ሰነዶች ካሉ ሰነዶቹ ከውይይት ሶስት ቀን በፊት እንዲደርሳቸው የምክር ቤቱ ደንብ ያዛልያለው ዘገባ የህግ ከለላን ስለማንሳት ቀርቦ የስለነበረው አጀንዳ የቀረበላቸው ምንም ነገር እንደሌለ ገልጠዋል::
የህግ ከለላው እንዲነሳ ጥያቄ የቀረበበት አባል ስም በይፋ አለመገለጡን ያመለከተው ሪፖርተር ምንጮቹ ግን የአቶ ጁነዲን ሳዶ ስለመሆኑ መግለጻቸውን ጽፎል:፡
የአቶ ጁነዲን ሳዶ ባለቤት በአሸባሪነት ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙ ሲሆን አቶ ጁነዲን ሳዶ ከመንግስትም ከፓለቲካም ስልጣናቸው መነሳታቸው እታወቃል::

No comments:

Post a Comment