Monday, December 29, 2014

ሂጃብ በማረሚያ ቤት ለብሶ መግባት /መዘየር/ ተከለከለ

(ልብ ይበሉ ሂጃብ ነው!! ኒቃብ ብቻ አይደለም!!)
ከ 2001 ጀምሮ የፌድራል ጉዳዩች በሚኒስተርነት እየመሩ የሚገኙት ዶ/ር ሽፈራው ከዚህ ቀደም ከ 18 አመት በታች ቁርአን መቅራት የላባቸው ጽንፈኛና አክራሪ ይሆናሉ ማለታቸው ይታወቃል:: አሁን ደግሞ እሳቸው በበላይነት የሚመሩት የማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ሙስሊም ሴቶች ሂጃብ ለብሰው ወደ ማረሚያ ቤት ቤተሰቦቻቸውን ገብተው እንዳይጠይቁ አግዶል::
ፎቶ ከፋይል
ፎቶ ከፋይል
ሂጃባቸውን አናወቅልቅም ያሉቱን ለማሽማቀቅ ከፍተና ጥራት በማድረግ ላይ ይገኛሉ::በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ታስረው የሚገኙ ንፁሃን እስረኞችን ለመጠየቅ ወደ ማረሚያ ቤቱ የሚጓዙ ሙስሊም እህቶቻችን ሂጃባቸውን በወንድ ፊት አውልቀው ፀጉራቸውን ሳያሳዩ ወደ ማረሚያ ቤቱ መግባት እንዳይችሉ አሁንም እየተደረገ መሆኑ ተገለፀ፡፡
የኮሚቴዎቻችን እና የወንድሞቻችን ባለቤቶች፣እህቶች እና እናቶች በማረሚያ ቤቱ ጠባቂ ፖሊሶች ፀጉራችሁን ክፈቱ፣ ሂጃባችሁን አንገታቹ ላይ አድርጉ፣ ሻሻችሁን አውልቃችሁ በእጃቹ ያዙት አለበለዚያ መግባት አትችሉም እየተባሉ ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ሳይገቡ እየተመለሱ እንደሚገኙ ታውቋል፡፡
የተወሰኑ የማረሚ ቤቱ ፖሊሶች በራሳቸው ተነሳሽነት ሙስሊም ሴቶችን ከዚህ ቀደሙ እንደሚፈትሹት በመፈተሽ እንዲገቡ አድረገው የነበረ ቢሆንም መልሰው መከልከላቸው ታውቋል፡፡
ማረሚያ ቤቱ አቃቂ እንደመገኘቱ ከከተማዋ ራቅ ያለ ሲሆን ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ድረስ ስንቅ እና አልባሳትን ተሸክመው ሴት እህቶቻችን ቢሄዱም ሂጃባችሁን ካላወለቃችሁ አትገቡም በሚል ደክመው ወደ ቤታቸው ሳይገቡ እየተመለሱ እንደሚገኙ ታውቋል፡፡
በትላንትናው ዕለት ቅዳሜም ቤተሰባቸውን ሳይጠይቁ በማረሚያ ቤቱ በር ላይ ፖሊሶች እንዳስመለሷቸው ተገልፆል፡፡በማረሚያ ቤቱ እየተፈጸመ የሚገኘውን የሂጃብ ገፈፋ በደል የኮሚቴዎቻችን እና የወንድሞቻችን ቤተሰቦች ብቻ የሚሸከሙት ሳይሆን መላው ሙስሊም ማህበረሰብ በደሉን በጋራ ሊጋፈጥ እና ሂጃባቸውን እንዲከበርላቸው ጥረት ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡
Source: FITH RADIO [ፍትህ ሬዲዮ]

Saturday, December 20, 2014

ድንቄም ጠቅላይ ሚኒስትር!

(ወንድሙ መኰንን፣ ከብሪታኒያ)

hailemariam pm


ብዙ ተብሏል። እኔም አንድ ነገር ልጨምርና ልገላገለው። “የጊዮርጊስን መገበሪያ የበላ ሲለፈልፍ ይኖራል” ነው የሚባለው? ተናግሮ ከሚያናግር ይሰውራችሁ! ውሀን ምን ነበር የሚያናግረው? ድንጋይ! የሰውም ድንጋይ እራስ አለ! ይቅርታ አንጀቴ አርሮ ነው!
ሦስት መንግስታትን የማየት ዕድል አጋጥሞኛል። ተወልጄ፣ አድጌ፣ ተምሬ ለዩኒበርሲቲ የበቃኹት በንጉሠ ነገሥቱ ዘመነ መንግሥት ነበር። ዕውነቱን እንናገር ከተባለ፣ ንጉሡ ሲናገሩም ሆነ ሲራመዱ፣ የርዕሰ ብሔርነት ግርማ ሞገስ ነበራቸው። “በንጉሥ መገዛቱ ጊዜ ያለፈበት፣ ያረጀ ያፈጀ፣ ገበሬውን በገባርነት ጠፍንጎ የያዘ፣ አገሪቱ በዕድገት ወደፊት እንዳትራመድ ያገዳት፣ ኋላ ቀር የፊውዳል ሥርዓት ነውና ወደሶሻሊዝም እንለውጣት” የሚሉ ድምጾች ከተማረው ክፍል አካባቢ እያየሉ መጡና እኛንም እንደጎርፍ ይዘውን ነጎዱ። ተከተልናቸው። “መሬት ለአራሹ እያልን” ተማሪዎች በጠበጥን። እንዳጋጣሚ ሆኖ በ፲፱፷፮ ዓ/ም የጠና ረሀብ በወሎ በመከሰቱ ሕዝብ በረሀብ እየረገፈ ፹ ዓመታቸውን “ድል” ባለ ድግስ አከበሩ የሚል በተማሪዎች የተጀመረው ርብሻ በመምሕራን (ሴክተር ርቬው)፣ በታክሲዎች እና በሠራተኞች ሥራ ማቆም አድማ ተቀጣጥሎ ለወታደሩ “መንግሥት የመገልበጥ” እድል ተፈተለት። የሥርዓቱ ጠባቂ የነበረው የወታደሩ ክፍል አመጸና የንጉሡን መንግሥት አፈረሰው። አዝጋሚ ዕድገት ላይ የነበረች ኢትዮጵያ የባሰውኑ በወታደራዊ ደርግ ተጠፈነገችና ወደ ኋላ ተወረወረች። የንጉሡ ሥርዓት በአምባገነን ወታደሮች ሲተካ፣ ሶስት መኰንኖች ተፈራረቁባት። ርዕሰ ብሔርነቱም መጀመሪያ ለጥቂት ወራትም ቢሆን (ከመስከረም እስከ ኅዳር ፲፱፻፷፯) ሌፍትናንት ጀኔራል አማን አንዶም፣ ቀጥሎም ትንሽ ውረድ ብሎ ለጥቂት ዓመታት (ከኅዳር ፲፱፻፮፯ – ጥር ፲፱፷፱) ብርጋዴር ጄኔራል ተፈሪ በንቲ፣ ቀጥሎ በጣም ወርዶ-ወርዶ፣ ለብዙ ዓመታት (ጥር ፲፱፻፷፱ – ግንቦት ፲፱፻፹፫) ሻለቃ መንግሥቱ ኃይለማርያም (በኋላ ኮሎኔል) በመጨራረስ ተተካኩ። ሲምሩ በሰደፍ፣ ከፈለጉም በእሥራት፣ ከጨከኑም በጥይት ሕዝቡን በጅምላ እየረሸኑ፣ ለአሥራ ሰባት ዓመታት በወታደር ፌሮ ጭንቅላታችን ላይ ቁመው ወታደሮቹና ጀሌዎቻቸው ቀጠቀጡን።  ግድያው እሥራቱ ያደነዘዘው ሕዝብ፣ “የባሰ አይመጣም” በማለት፣ ገንጣይ አስገንጣይ ዘረኞች ወደ አዲስ አበባ ሲገሰግሱ፣ ዝም ብሎ አያቸው። እንዲያውም አንዳንዱ መንገድ እየመራ ወደ አዲስ አበባ አደረሳቸው። ይኸውና በወያኔ የሚመራው የዘረኞች ቡድን ከዚያች ከተረገመች ከግንቦት ፳ ቀን ፲፱፻፹፫ ዓ/ም ጀምሮ፣ ያላንዳች ርኅራሔ፣ ቀጥቅጦ እየገዛን ነው። ያም ብቻ አይደለም። መሬታችንን እየሸነሸነ፣ ነዋሪውን እየፈነቀለ በርካሽ እየቸበቸበው ነው። ዛሬ ኢትዮጵያ ንጉሡ ለደርግ ከአስረከቧት እጅግ አንሳ ትገኛለች። መሪዎቹም፣ ከበፊተኞችም እጅግ ወርደው የወረዱ ቀትረ ቀላሎች ሆኖብን። መጀመሪያ መለስ ዜናዊ ለሀያ አንድ ዓመታት (ከግንቦት ፳ ቀን ፲፱፻፹፫ – ከግንቦት ፳ ቀን ፳፻፬)፣ ፏልለውብን ሞት ገላገለን። መለስ ዜናዊን የተኩት ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ ድቄም ጠቅላይ ሚኒስቴር ናቸው።
እንግዲህ እኔ እስካሁን የኖርኩት ከግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ እስከ ኃይለማርያም ደሳለኝ መሆኑን ተገንዘቡልኝ። ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በ፲፱፻፳፰ ዓ/ም በሊግ ኦፍ ኔሺን ላይ ያደረጉትን[i] ንግግር፣ ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ፣ ሰኔ ፳፪ ቀን ፲፱፻፺፱ ዓ/ም ካደረጉት አሳፋሪ ንግግር[ii] እና የአሁኑ ጠቅላይ ሚኒስቴር ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ ሰሞኑን የስልጤ ዞን ዋና ከተማ፣ ወራቤ የተመሠረተችበትን አሥረኛ ዓመት ለማክበር ተግኝተው ከተናገሩት አሳፋሪ ንግግር[iii] ብናወዳድር፣ “እንዴት ወርደን እዚህ ደረሰን” ያስብላል።
መለስ ዜናዊ ለሰው ስሜት የማይጨነቁ፣ በአራዳ አነጋገር ሁሉንም የሚዘረጥጡ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ስቃይ ነበሩ። ሙት ወቃሽ ላለመባል፣ ያሉትን አስነዋሪ አባባሎች “ሾላ ብድፍን” ብለን እናልፈዋለን። አሽቃባጮችም ነበሯቸው። ብልግና በተናገሩ ቁጥር፣ መላው የፓርላማ አባላቸው፣ የሚያቅለሸልሽ ታሪክ እንኳን ቢሆን፣ ከት ብሎ የሚስቅላቸው ሞልቷቸው ነበር። እሳቸውን የተኩት ጉድ እንደሳቸው መሆን ቢያምራቸውም፣ የተለዩ ፍጡር ናቸው። ወላጆቻቸው፣ “ኃይለ ማርያም”ብለው ስም ሲያወጡላቸው፣ ለመሆኑ ምን ታይቶአቸው ነው? በዚህ ስማቸው መጨረሻ ላይ እደምደማለሁ መልካም ንባብ።
ኃይለማርያም፣ ደሳለኝ ጠቅላይ ሚኒስትር ሳይሆኑ፣ የወያኔ ባለአደራ ሁነው የጠቅላይ ሚኒስቴርነቱ ቦታ ጠባቂ ናቸው። አልጋ ጠባቂ እንበል?! አልመሆናቸውን ገና በጠዋቱ፣ የሟቹ የመለስ ሚስት፣ ደፋሯ አዜብ ጎላ (መስፍን) አስመስክራለች። “የምኒልክን ቤተ መንግሥት አልለቅለትም” ብላ ጎዳና ተዳዳሪ ልታደርጋቸው ምንም አልቀራትም ነበር። ደንቄም ጠቅላይ ሚኒስትር!
ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ የራሳቸው ሰው ባለመሆናቸው፣ የወያኔ መሣሪያ መሆናቸውን ለማስመስከር፣ አራዳው መለስ የተናገሩትን አነጋገር ቃል በቃል፣ አንዲት ቃል ሳይጨምሩ – ሳይቀንሱ፣ እንደበቀቀን ሲደግሙት ተሰምተዋል። የእነ አቤ ቶኪቻው መሳቂያ መሳለቂያም ሁነዋል። ከኦሪጂናሌው መለስ ላለማነስ፣ ብዙ ነውሮችን ካፋቸው ዘርግፈዋል። አዪዪ! ምናለ በተማሩት የውሀ ማጣራት ሙያ ቢሰማሩ ኑሮ! ከሰውም ሞገስን፣ ከእግዚአብሔርም በረከቱን ባገኙ ነበር። ለጠማው ንጹሕ ውሀ ማቅረብ በሰማይም ባጸደቃቸው በምድርም ባስከበራቸው!
“ያለቦታው ገብቶ፣ ያለ ሰገባው
አሳዛኙ ልቤ፣ የተንገላታው”
ነበር ያለው ያ አፍቃሪ! ያለቦታቸው ገብተው፣ ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ አገር የመምራቱን ኃላፊነት አምቦጫረቁት። የቢቢስን እና የሲኤንኤንን ገዜጠኞች በሽብርተኝነት ሊያስሯቸው እንደሚችሉ አስፈራርተዋል። አራዳ ሳይሆኑ፣ እንደመለስ ጮጋ ለመሆን የሚያደርጉት መፍጨርጨር የመጨረሻው ፋራ መሆናቸውን፣ አጋልጦባቸዋል። አይ የኛ ነገር። ወርደን ወርደን እዚህ ደረስን? እንዲያው ኢትዮጵያውያን ፈጣሪን ምን ያኽል ብንበድለው ነው፣ ለእንደነዚህ ዓይነቶቹ ጉዶች አሳልፎ የሰጠን? ነገራችን ሁሉ፣ “ከድጡ ወደ ማጡ” ሆኖብናል። ሕዝባችን መገድሉ፣ መታሰሩ፣ መሰደዱ፣ መራቡ፣ መጠማቱ፣ መታረዙ ሳያንስ፣ እነዚህ መዥገሮች በየቀኑ እየተነሱ የሚመርጉበት ስድብ፣ የባሰ የሚያስመርር ደረጃ ላይ አድርሶታል። “ጠቅላይ ሚኒስቴር” ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ ድንቄም ጠቅላይ ሚኒስትር!
የታኅሣሥ ፪ቱን (11 December 2014) የኢሳት ሬዲዮ ፕሮግራም እንደኔ ያደመጠ ሁሉ መቼም ሆዱ በንዴት ድብን እንደሚልበት አልጠራጠርም። ጨጓራ የሚልጥ የአልሰርን በሽታ ያስንቃል። ከአንደ ጠቅላይ ሚኒስቴር ቀርቶ፣ አንድ እራሱን ከሚያከብር፣ አባትና የቤተሰብ ኃላፊ ነኝ የሚል ሰው፣ እንዲህ የወረደ ንግግር አያደርግም። ምን አለ አሁን እንዲህ ዓይነት ቅሌት ቢቀርባቸው? ኤዲያ! ኤዲያልኝ ወዲያ! ምን ዓይነቱ ለዛው ሙጥጥ ናቸው? እኔ ስለሳቸው አፈርኩ። ሰውዬው ያልበላቸውን ነበር የሚያኩት። ወራቤ፣ የስልጤዋ ዋና ከተማ፣ ጠቅላይ ሚኒስቴር መስለዋት አሥረኛ ዓመቷን ልታከበር፣ የወያኔ ባላደራውን ጠርታ፣ መከበሯ ቀርቶ ተዋረደች። ጠቅላይ ሚኒስቴር ተብዬው፣ እንዲህ ነበር ያሉት፣ ዲንቄም ጠቅላይ ሚኒስትር!
፩ኛ፡ አሜሪካ ተሰደው ስለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን
“አንዳንድ ጌዜ አሜሪካን አገር ውስጥ የሆነ መርቸዲስ፣ ማለት፣ መኪና ተደርድሮ ባለበት ፎቶግራፍ ይነሱና ከዚያ በኋላ ወደቤተሰብ ይልኩና፣ ይኼ የኔ መኪና ነው ይላሉ። ማንን እንድሚያታልሉ ግን አይገባም።”
ያጣ ወሬ! እንዴ! ጠቅላይ ሚኒስቴር ተበዬው እኮ በሥፍራው የተገኙት የወራቤን ከተማን አሥረኛ ዓመት ምስረታ ለማክበር ነበር። አሜሪካ የሚኖሩት ስደተኞችናና የወራቤ ከተማ ምን አገናኛቸው? ከተደረደሩት መኪናዎች ጋር ተደግፈው የተነሱትን ፎቶ የት ቁመው ያዩት? ሰውዬው ለምን ያልበላቸው ቦታ ያካሉ? ለመሆኑ፣ አሜርካን ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ አንቱ የተባሉ ስንት ኢትዮጵያውያን ምሑራን እንዳሉ ያውቁ ይሆን? አሜሪካን ሆስፒታሎች ውስጥ ስንት እውቅ ኢትዮጵያውያን የሕክምና ባለሙያዎች እንዳሉ ማን በነገራቸው። አሜሪካ የምርምር ማዕከላት ውስጥ፣ ናሳ ሳይቀር፣ ስንት ኢትዮጵያውያን ሳይንቲስቶች እንዳሉ የሚያስብ ጭንቅላት አላቸው ልበል? ኢትዮጵያን ለማንቋሸሽ እራሳቸው ቆሽሸው አረፉት! ይሁን! ይህቺ ቀን እኮ ታልፋለች። ማርቸዲስ ለኃይለማርያም ብርቅ ይሆን ይሆናል እንጂ፣ ወጪ አገር ማርቸዲስ ታክሲ ነው። ፈራሪም፣ ሎተስም፣ ቤንትሌይም፣ ሮልስ ሮይም ማለት እኮ አንድ ነገር ነበር። ድንቄም ጠቅላይ ሚኒስትር!
፪ኛ፤ በጀርመን ተሰደው ስለሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን በተመለከተ
“… ለልጆቼ ዶሮ ይዘህ ሂድ አሉኝ። እሺ ብዬ ጀርመን አገር ዶሮ ወጥ ተሸክሜ ሄድኩኝ። ከሄድኩ በኋላ፣ በተሰጠኝ ስልክ ብደውል፣ ብደውል፣ ልጆቹን ማግኘት አቃተኝ። ምንድነው ሲባል፣ ስልኩን ለጓደኞቼ፣ ለጀርመናዊ ለጓደኞቼ አሳየኹዋችወ፣ ኧረ! ይኸማ ሀይም(?) ውስጥ እኮ ነው አሉኝ። ምንድነው ሀይም አልኳቸው። ሰው የሚሰቃይበት እስር ቤት ዓይነት ነገር ነው አሉኝ። ዶሮ ወጡን ይዤ እዚያ ሀይም ሄድኩ። ስደርስ ኮንቴነር ውስጥ ነው ያሉት። እዚያ ዱቄት ይሰጣሉ፣ ዱቄቱን እያቦኩ፣ ዱቄት ብቻ ነው የሚበሉት። እቃውን አስረከብኩላውና፥ “ታዲያ ያ ሁሉ ፎቶግራፍ የላካችሁት፣ ከየት የመጣ ነው?” አልኳቸው። ብዙዎቻችን እናውቃለን፣ ውጭ አገር ሰው እንዴት እንደሚኖር።“
ደግሞ “ጀርመናዊ ጉደኞቼ ይላሉ! አያፍሩም? ለመሆኑ፣ የማን ደፋር እናት ናት፣ እንደተራ ሰው፣ ክቡር ጠቅላይ ሚኒቴራችንን ዶሮ አሸከማ ጀርመን አገር ድረስ የምትልክ? “የማይመስል ወሬ፣ ለሚስትህ አትንገር” ነው የሚባለው? እንዴ! የወራቤ ነዋሪ ላለፉት አሥር ዓመታት ያደረገውን ጉዞ እንዲገመግሙለት እንጂ፣ ጀርመን ውስጥ ስለሚኖር ስደተኛ ወሬ ጠምቶአቸው ነው እንዴ የጋበዟቸው? በነገራችን ላይ፣ ጀርመን አገር አዲስ የመጡት ስደተኞቹ፣ ምናልባት ጉዳያቸው እስከሚጠናቀቅ በዚያ ዓይነት አኗኗር ለጊዜው ይኖሩ ይሆናል፣ ለመሆኑ፣ አዲስ አባባ ስንት የጎዳና ተዳዳሪዎች እንዳሉ የሚያይ አይን ተተክሎላቸው ይሆን?
፫ኛ፣ በአረብ አገር ተሰደው ስለሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን በተመለከተ
“እኛ እህቶቻችንን ለማየት አቻልንም። ሳውዲ ሂደን፣ ማየት አልቻልንም።… ይኸ የዚያ አካባቢ የሀይማኖትዊ ሥነ ሥርአት ሊኖር ይችላል። ነገር ግን ሂጄ ማየት ስላልተቻለኝ፣ የፈቀዱልኝስ እንድሄድ ነበር። ለምንድነው፣ ማየት የማይፈቀድልኝ፣ የሀይማኖታዊ ሥነ ሥርዓት ሊሆን ይችል ይሆናልግን በእዚያ ደግሞ ቦታ ስንሄድ፣ መንገድ ላይ እንደአበደ ውሻ የሚኖሩ እህቶቻችን አየን። ከዚያ ቦታ ስንሄድ፤ በምባሲ በራፍ፣ ወደ ሺ የሚጥጉ፣ አንድ ላይ ተኰልኵለው  በዚያ ሙቀት ውስጥ ኤር ኮንዲሺነር በሌለበት ታጭቀው ሲሰቃዩ አየሁ። ከዚያ በኋል ግን፣ ምን ትዝ ይለኛል፣ ቢያንስ እዚህ ገጠር ውስጥ በእግራቸው ተጉዘው በልተው ጠግበው እኮ ይኖራሉ።
ድንቄም ጠቅላይ ሚኒስትር! ወያኔ አገሪቱን መቀመቅ ውስጥ በመጨመሩ፣ ኢኮኖሚዋን ማድቀቁ፣ እና እንደ ኃይለማርያም ደሳለኝ ያሉ አሽከሮቻቸው በልተው በልተው ሆዳቸው ተወጥሮ ሲነፋፋ፣ ቤተሰቦች የሚበላ የሚቀመስ ሲያጡ፣ ወጣት ሴቶቻችን ገና በሎጋ ዕድሜአቸው፣ትምሕርታቸውን አቋርጠው፣ ሴተኛ አዳሪ ከመሆን፣ በጉልበታቸው ሠርተው ቤተሰቦቻቸውን ለመርዳት የሚያደርጉትን መፍጨርጨር፣ ከእብድ ውሾች ቆጥረዋቸው አረፉ? ደግሞ ሰለ አረቦች ግርድና አፋቸውን ሞልተው ተናግረዋል። ለመሆኑ የግርድና ንግዱን የሚያካሄዱት የሕወሀት አባላት መሆናቸውን የሚረዳ ጭንቅልታ ማን ባዋሳቸው! አፋቸው ተበላሽቷል። ታዲያ ምን ያደርጋል! በቅቤ አሽተው አይመልሱት ነገር። ድንቄም ጠቅላይ ሚኒስትር!
፬ኛ፣ ድንጋይ ይወረውራሉ ስለሚሏቸው የስልጤ ወጣቶች
“አንድ እኛ እዚህ ግድም የሚያሳዝነን፣ አብዛኛው እዚያ መርካቶ አካባቢ ደንጋይ የሚወረውረው ወጣት የዚህ ዞን ወጣት መሆኑ ነው። በሙስሊምነት ከሆነ፣ ትልቁ ሙስሊም፣ ኦሮሞ ነው፣ ኦሮሚያ ነው። ነገር ግን ድንጋይ የሚወረውረው ግን የሥልጤ ወጣት ነው። ምን ማለት ነው ይኼ? ምን ማለት ነው? አባቶች በተለይ እስቲ ይታያችሁ የናንተ ልጆች ድንጋይ ሲወረውሩ፣ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ መስኮት ሲሰብሩ፣ መኪና ሲሰብሩ፣ እናንተ እዚህ ሁናችሁ ሲታዩ እንዲያው በአጠቃላይ፣ ይኸ ምን ማለት ነው? ይኸ አደብ መግዛት አለበት። ትላንት ከዚህ ሞባይል ገዝቶ፣ መርካቶ የገባ ሰው ድንጋይ እያነሳ ንብረትና ኃብት ማውደም ማለት፣ ይኽ ንቀት ነው። በምንም ምልኩ! ድንጋይ ወርውሮ መስኮት ሰበረና መኪና ከሰበረ በኋላ ሲታሰር ደግሞ በኃይማኖት ምክንያት ታሰርኩ ካለ፣ ድንጋይ የሚያስወረውር ሀይማኖት የለም። እንደዚያ ነገር ድንጋይ የሚያስወረውር ሀይማኖት የለም …።”
ለዛው ሙጥጥ! ወይ ጉድ! ከክብር እንግዳ ተሳዳቢ እግዚአብሔር ይሰውራችሁ። የሥልጤ ሕዝብ የጋበዛቸው፣ የወራቤን ከተማ መቆርቆር አሥራኛ ዓመት ሲያከብሩ፣ ከጠቅላይ ሚኒስቴራቸው ጋር አብረው በክብር ተደስተው ቀኑን ለማሳለፍ ነበር እንጂ፣ ሊሰደቡ፣ ሊዋረዱ፣ ልጆቻቸው ላይ የሚቃጣውን ማስፈራሪያ ሊያዳምጡ ነበር እንዴ! የስልጤን ሕዝብ አዋረዱት! ምንኛ ሕዝቡ ልቡ ይቁሰል! ድንቄም ጠቅላይ ሚኒስትር!
፭ኛ፣ ስለሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊ ኮሞቴ
አፋጣኝ የፍርድ ውሳኔ ለምን አይሰጥም ተብሎ የተጥየቁ ግለሰቦችን በተመለከተ በመጀመሪያ ደረጃ እኛ ሰዎቹ የሙስሊሙ ኮሚቴ ተወካዮች ነን ሊሉ ይችላሉ። ይኸ መብታቸው ነው። ማንም አይከለክላቸውም።  ግን መንግሥት ተወካይ ለመሆናቸው ምንም ማስረጃ የለውም። ሙስሊሙን እነሱን እንዴት እንደወከለ አናውቅም። ስለዚህ ስለማናውቅ ጉሕጋዊ ወኪሎች ስለመሆናቸው ማስረጃ የለንም ነው የምንለው። ሕጋዊ ወኪሎች አይደሉም። እነዚህ ግለሰቦች ላረጋግጥላችሁ የምፈልገው በሀማኖታቸው ምክንያት ወይም ዕምነታቸው ምክንያት ወይም በሚያራምዱበት ዕምነት ምክንያት አይደለም የታሰሩት። የታሠሩት ሀይማኖታቸውን እና እምነታቸውን ሕገ መንግሥቱ በሚፈቅደው መሠረት ከማካሄድ አልፈው ሂደው ከምንግሥትና ከሕዝብ ጉዳዮች ላይ ወንጀል በመፈጸማቸው ነው የታሰሩት።
ምን ወንጀል? ሰው ገደሉ? ዕቃ ሰበሩ? በቃ ወያኔ አስተዳዳሪአቸው “ወንጀለኞች” ናቸው ካለ እንደበቀቀን ተከትለው፣ የኛ “ጠቅላይ ሚኒስቴር” ፈረዱባቸው ማለት ነው? ወያኔ ከሳሽም፣ ምስክርም፣ ዳኛም ነው። አገሪቱን ጠፍንጎ ይዞአል። ምን ዓይነት ጭንቅላት ቢኖራቸው ነው፣ ወያኔ እንዲህ የሚጫወትባቸው? አይ ሆድ! ለሆዱ ያደአንጎሉ አይሠራም። ይህቺን አጥብቃችሁ ያዙልኝ! ሕግ የሚሠራው ሁሉም ሲገዛለት ነው። ወያኔ ሕግን የሚጠቀመው ሌላውን ጠፍንጎ ለመያዝ ነው። ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ ዕውቀታቸው ወሀ ማጣራት ነው አንጂ ሕግ አይደልምና የተማሩት፣ የሕጉን ነገር ባያጨማልቁት ጥሩ ነበር።  ከዚያ አልፈው ተርፈው፣ እስካሁ ፍርድ ያልተሰጠበትንም ምክንያት ሲደረድሩ፣ የተከሳሾቹ ጥፋት እንደሆነ ሊነግሩን ከጅሎአቸዋል። ኧረ ምን ከጀላቸው፣ ወንጀሏቸው እንጂ! ጥፋተኛ ላለመሆናቸው፣ አራት መቶ ገደማ ምስክሮች በማቅረባቸው፣ ያንን ለማዳመጥ የዘገየ ፍርድ ነው ብለውን አርፍዋል። ድንቁርና አንዳንዴ ጡሩ ነው። ከሒሊና ወቀሳ ያድናል።በድፍኑ፣ ወያኔ ወንጀለኛ ነው ብሎ የፈረጀው ሁሉ ወንጀለኛ መሆን ስላለበት፣ እራሱን መከላከል የለበትም ሊሉን ምንም አልቀራቸውም! በቃ! ወያኔ ከእግዚአብሔር በታች ትልቁ አማላካቸው ነው። ድንቄም ጠቅላይ ሚኒስትር።
፮ኛ፣ የወላይታን ሕዝብ በጅምላ ሰድቡ
“እኔ የተወለድኩበት ብሔር፣ ብዙ ሰው ነው እዚህ ጋ የሚያሰፋው። ያኛውን ለመምሰል ሲል ነ። ትንሽ ቀላ ካለ፣ ያኛውን እመስላለሁ ለማለት ይኸንን አሰፍቶ፣ እራሱን ለውጦ፣ እራሱን ለመሸ የምንሸቃቀጥበት ነው የኛ ትውልድ።
ኧረ በሕግ አምላክ! እኚህን ሰው አንድ በሉልን! የወላይታ ሕዝብስ እራሱን እንደሸቀጥ አልሸጠም። ይልቁንስ ከኩሩውና ከርህሩሁ የወለይታ ሕብረተሰብ ተፈጥሮ ሒሊናውን ለቁራሽ እንጀራ የሸጠ ማን እንደሆነ እናውቃለን። የሥነ አዕምሮ ሐኪም ጋ የሚወስዳቸው ዘመድ የላቸውም? ወያኔ ምንኛ ጭንቅላታቸውን ብታዞራቸው ነው ጃል፣ እራሳቸውን እንዲሰድቡ የለወጠቻቸው? ደግሞ የወላይታን ባሕላዊ ጠባሳ ለመሸፈን መሰፋትን፣ ከወራቤ አሥረኛ ዓመት የምሥረታ በዓል ጋር ምን አገናኛቸው? ስድብ ርቦአቸዋል? ስድብ ጠምቶአቸዋል? የእሳቸውን አዕምሮ ነው ወያኔ ግጥም አድርጋ የሰፋችባቸው እንጂ፣ እኔ የማውቀው የወላይታስ ሕዝብ ባሕሉን አክባሪ ኩሩ ኢትዮጵያዊ ነው። ድንቄም ጠቅላይ ሚኒስትር!
በመጨረሻ፣ ጠቃላይ ሚኒስትሩ፣ ለምንድነው ዲያስፖራውን የሚጠሉት? ምክንያት አላቸው! በፈረጆቹ አቆጣጠር፣ 2011 ላይ ወያኔ ገንዘብ ከዲያስፖራው ለመለምን ወሰነች። እሳቸው የአሜርካውን ልዑክ እንዲመሩ ተላኩ። ሁሉም በሄዱበት ተመሳሳይ ዕድል ገጠማቸው። ከሄዱበት ሁሉ ዲያስፖራው ምድረ ወያኔን ባዶ እጃቸውን ስደዳቸው። ለንደን ላይ ለምሳሌ፣ ከኢምፔሪያል ኮሎጅ አሳደናቸው አባረን፣ እምባሲ ከተናቸዋል[iv]፣ አንዲት ሳንቲም ሳይሰበስቡ ተመለሱ። አሜርካ ላይ እንዲሁ አዳራሻቸው ተረብሾባቸው፣ ኪሳራ በኪሳራ ሆነው፣ ቤሳ ቤሲትን ሳይሰብበሰቡ ተመለሱ። ታዲያ በዚህ የበሸቁት ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ ሚያዝያ ፲፭ ቀን ፳፻፫ (23 April 2011) በወጣው ሪፖርተር ጋዜጣ ላይ፣ እንዲህ እያሉ ነበር የተሳደቡት!
“ከሁለት ሺ በላይ ሕዝብ በሚሰበሰብበት አካባቢ፣ ከ20 እስከ 150 ሰዎች፣ የተቃውሞ ሰልፍ ቢወጡ፣ ምንም የሚገርም አይደለም። እነሱም፣ የቀደሞ የደርግ ሥርዓት ርዝርዦችና፣ በሽብር ተግባር ላይ የተሰማሩ የአማጺ ቡድኖች አባላት ናቸው። እነዚህ ሰዎች፣ በበርካታ ዓመታት ሲጮሁ ኑረዋል። ኢትዮጵያ ግን ወደፊት እየገሰገሰች ትገኛለች። እነሱ እየጮሁ ይኖራሉ፣ ምናልባትም፣ አርጅተው እስኪሞቱ ድረስ የሚጮሁ ይኖራሉ።ሬሳቸው አገር ቤት ሊቀበር ይመጣል… እኛም እንቀጥላለን። ይልቁንስ፣ በዚህ ታሪካዊ ወቅት እራሳቸውን በእሳት ባያስለበልቡ የሚሻል ይሆናል”።
“አርጅተው እስኪሞቱ ድረስ የሚጮሁ ይኖራሉ። ሬሳቸው አገር ቤት ሊቀበር ይመጣል” ነበር ያሉት? ይኸንን የተናገሩት ሚያዚያ ፲፭ ነበር። ከነዚያ ሰላማዊ ሰልፈኞች እስከአሁን ሙቶ ወደ አገር ቤት የተመለሰ ሬሳ የለም። እግዚአብሔር ይመስገን። ዳሩ ግን እንደ ጣዖት የሚያመልኳቸው አሳዳሪ ጌታቸው፣ መለስ ዜናዊ፣ ነሐሴ ፲፭ ቀን 2004 ዓ/ም ብራሴልስ ሆስፒታል ሙተው ወራት ከከረሙ በኋላ ለቀበር፣ አዲስ አበባ ሬሳቸው ገብተውላቸዋል። በእግዚአብሔር የሚያምን ሰው ግፍ አይናገርም። አንዳንዴ እግዚአብሔር ቅርብ ነው። ስሙ የተመሰገነ ይሁን!
ሰውዬው የዞረባቸው ናቸው። ጠቅላላ ሰብዕናቸው፣ ውጥንቅጡ የወጣባቸው የሚናገሩትንም ሆነ የሚያደርጉትን የማያውቁ ጉድ ናቸው። ወይ አያምሩ ወይ አያፍሩ! እንኳን ለጠቅላይ ሚኒስቴርነት፣ የአንድ መስሪያ ቤት ዴፓርትመንት እንኳን ለመምራት ብቃት ያንሳቸዋል። እንኳን ሠርተው፣ ተናግረው ስሜት የማይሰጡ አሳፋሪ ሰው ናቸው። ለወያኔ መሣሪያነት ያበቃቸው ይኸው ቅደመ ሁኔታ ነው።
አንድ ለብዙ ጊዜ አምቄው እስከዛሬ ያቆየሁትን ልበልና ልሰናበታችሁ።
ደንታ-ቢስ ከሀዲ፣ አድር-ባይ ሆድ-አደር
ወገኑን የሸጠ፣ የወያኔ አሽከር፣
ስብዕናውን ገድሎ፣ ከሒሊናው የራቀ
ስሙ ኃይለ-ማርያም፣ እሱ ጸረ-ማርያም፣ የተዘባርቀ

ኢህአዴግ በባህር ዳር ግድያ ፈጸመ!

በባህርዳር ዋይታ ሆነ!

bahirdar


በእምነት ቦታ ይገባኛል ነዋሪዎች ባሰሙት ጥያቄ ኢህአዴግ የጥይት መልስ ሰጠ፡፡ ድርጊቱን በምስል በማያያዝ በተለያዩ ማኅበራዊ ገጾች ያሰራጩት ክፍሎች አዛውንትና መነኮሳት ሳይቀሩ መደብደባቸውንና መቁሰላቸውን በምስል አስደግፈው አመልክተዋል፡፡
አኻዙ በትክክለኛው ባይታወቅም አምስት የሚደርሱ ሰዎች ሕይወታቸው እንዳለፈ በማኅበራዊ ገጾች የተበተኑት መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ አንዳንድ የድረገጽ ዜናዎችም በአኻዝ ከመለያየት በስተቀር የግድያውንና የድብደባውን መጠን በመግለጽ ዜናቸውን አስፍረዋል፡፡
ድርጊቱን የፈጸመው ኢህአዴግ ስለሞቱትና ስለተደበደቡት መነኮሳትና አዛውንት እንዲሁም ሌሎች ወገኖች ይህንን መረጃ እስካጠናቀርንበት ጊዜ ድረስ ይፋዊ ማስተባበያ አልሰጠም፡፡ ይልቁንም ከሁለት ሳምንት በፊት ኢህአዴግ የፌዴራል ምክትል ሚ/ሩን በፖሊስ ፕሮግራም በማቅረብ የፌስቡክ ዜናዎችን አትመኑ በማለት ማሳሰቢያ ሲሰጥ ነበር፡፡
ነገረ ኢትዮጵያ” የተሰኘው የፌስቡክ ገጽ ቀበሌ፣ ወሰንና የምክርቤት ስም ጠቅሶ የተፈጠረውን ሁኔታ ከዚህ እንደሚከተለው አስፍሮታል፡፡
“የአማራ ክልል አስተዳደር የቤተ ክርስቲያን ንብረት የሆነውን የታቦት ማደሪያ ለመንገድና ለጥቃቅንና አነስተኛ ሱቆች መስሪያ እንዲነጠቅ ማዘዙን ተከትሎ በቤተ ክርስቲያን የተጠራው ተቃውሞ አሁንም ድረስ እንደቀጠለ መሆኑን የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገልጸዋል፡፡ ከታቦት ማደሪያው 9 ሜትር ገብቶ መንገድ እንዲሰራ እንዲሁም ቀሪው ለጥቃቅንና አነስተኛ ሱቆች እንዲሰጥ አስተዳደሩ ማዘዙን ተከትሎ ታቦት ማደሪያውን ከነገ ህዳር 10/2007 ዓ.ም ጀምሮ ሊፈርስ እንደነበር መረጃው የደረሳት ቤተ ክርስቲያን ለህዝበ ክርስቲያኑ አስቸኳይ ጥሪ ማስተላለፏ ታውቋል፡፡ ህዝቡም “በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ተገናኝተን በእግዚያብሄር ስም በአስቸኳይ ጠርተንዎታል” በሚል በቀረበለት ጥሪ መሰረት ዛሬ ጠዋት ተቃውሞውን የጀመረ ሲሆን አሁንም ድረስ እንደቀጠለ ተገልጾአል፡፡ ህዝቡ ቀበሌ 10 በሚገኘው አዲሱ ምክር ቤት እንዲሁም በዚሁ ቀበሌ በሚገኘው የቀድሞው ምክር ቤት በመገኘት ተቃውሞውን እየገለጸ ይገኛል፡፡ በተለይ በአዲሱ ምክር ቤት ተገኝቶ ተቃውሞውን እያሰማ የሚገኘውን ህዝብ በኃይል ለመበተን ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝ ከቦታው የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡”
ግድያውንና ድብደባውን በተመለከተ “የክልሉ መስተዳድር ድርጊቱን እንደፈጸመ አድርገው የሚወጡት ዘገባዎች ትክክል አይደሉም፤ መስመርም ያስታሉ፤ ዋንኞቹን ወንጀለኞች ከደሙ የነጹ ያደርጋቸዋል” በማለት ቅሬታቸውን ለጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ የሰጡ ወገኖች “በየትኛውም የአገሪቱ ክልሎችም ሆነ ከተሞች ለሚፈሰው ደምና ለሚጠፋው ሕይወት ግምባር ቀደም ተጠያቂው ህወሃት/ኢህአዴግ እንደሆነ ሊሰመርበት ይገባል” ሲሉማሳሰቢያ ሰጥተዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ “በቁጥጥር ሥር ውሏል” የተባለው የሙስሊሙ ተቃውሞ በድንገት መካሄዱ ታውቋል፡፡ በአዲስ አበባ ኑር መስጊድ የተካሄደውን ተቃውሞ አስመልክቶ የተለያዩ የማኅበራዊ ገጾች በተለይም የሙስሊሙን ጉዳይ በመከታተል ይፋ የሚያደርጉ መገናኛዎች እንዳስታወቁት ተቃውሞው የተካሄደው ኢህአዴግ ከሚጠብቀውና ከሚገምተው ውጪ ነበር፡፡ እንደወትሮውም የጥሪ ማስታወቂያና ቅስቀሳ አስቀድሞ አልተካሄደም በማለት ዘግበዋል፡፡ ተቃውሞው ውጤታማ፣ ግቡን የመታና የተጠናከረ ቅንብር እንደነበረው የታዘቡ ይናገራሉ፡፡
ኢህአዴግ በእሁድ የፖሊስ ፕሮግራሙ የሚሰጠው “ልማት ተኮር” የፖሊስ ማስተባበያ “ምርመራ ውጤት በተስፋ” ይጠበቃል፡፡ ከተለያዩ የማህበራዊ ገጾች ያገኘናችው ምስሎች ከዚህ በታች ሰፍረዋል::
bahirdar3bahirdar5bahirdar10bahirdar11bahirdar7bahirdar15bahirdar16bahirdar17bahirdar14bahirdar6bahirdar8bahirdar9nur mesjid addisbahirdar1bahirdar13
http://www.goolgule.com/eprdf-killed-ethiopians-in-bahirdar/

Friday, December 19, 2014

The Role of Civil Society Organization (CSOs) in the Upcoming Elections in Ethiopia

Call for papers

crew_logo


Fourth International Conference of Ethiopian Women in the Diaspora
March 7, 2015
Washington DC, USA
The Role of Civil Society Organization (CSOs) in the
Upcoming Elections in Ethiopia
Call for papers
Civil society organizations (CSOs) flourished in Ethiopia from early 1990s to 2005 better than ever before. Some of these civil society organizations focused on service delivery, others on civil rights, gender equality and good governance, and still others on consciousness raising and the environment.
In 2009, the Government of Ethiopian enacted a new law, the Societies and Charities Proclamation. The law drastically restricted the activities of many nongovernmental organizations, prohibiting them to work on human rights and good governance. Currently, CSOs have no role in raising awareness of democracy, human rights, rule of law, and citizenship in the country. Meaningful participation of CSOs in activities related to the upcoming election is highly unlikely.
Individual initiatives through CSOs are based on the inalienable right to participate in vital political, social, economic or other issues, without belonging to political parties (in or outside government). Civil society organizations are autonomous means of participating in public life. They are systems of taking initiatives for ensuring that people follow their preferred directions to their political, economic or social lives. Without the active role of CSOs therefore, creating awareness of the rights and responsibilities of citizens and having fair and free elections is going to be impossible. That is, the 2015 elections could simply result in a one-party dominated election similar to that in 2010. Citizens will not participate freely to build a democratic society that will reflect their needs.
At its 4th annual international conference, therefore, the Center for Rights of Ethiopian Women (CREW) plans to consider the role of civil society organizations in the upcoming elections in Ethiopia. The main objective is to create an understanding of the magnitude of the negative impacts of the Societies and Charities Law on the activities of nongovernmental organizations. As a women’s civil society organization, CREW will also pay special attention to Ethiopian women’s participation in the political process. Thus, one of the major questions that the conference will address will be the role of women’s organizations in mobilizing women to use their rights towards fair and free elections.
With that in view, the conference is intended to cover the following themes:
  1. Assessment of the Societies and Charities Law and its impact on the activities of civil society organizations in the upcoming elections:
  • Lessons learned from previous elections; and
  • Challenges and opportunities for the upcoming elections
2.   Women’s participation in the political process:
  • Women’s advocacy for free and fair elections
  • Plan of action and advocacy on women’s participation in the political process
  • Strategies for encouraging women to seek political leadership positions.
3.  Encouraging the international community to promote free and peaceful elections in Ethiopia.
If you are interested in presenting papers on any of these areas, please send us a one-page proposal by January 30, 2015. The proposal should state the topic and show the pertinence of your presentation to our theme. If you have any questions, please write to us via our e-mail:  ethiowomen@gmail.com. (Click here to read the document in PDF)
http://www.goolgule.com/the-role-of-civil-society-organization-csos-in-the-upcoming-elections-in-ethiopia/

የኦባንግ ጉዞና ለዲያስፖራው ፖለቲካ ያለው አስተዋጽኦ

(ሽመልስ ወርቅነህ)

obang in israel


በቅርቡ በዋሽንግተን ዲሲ ከተማ በአቶ ኦባንግ ሜቶ በተጠራው ስብስባ ላይ የመገኘት እድል አጋጥሞኝ ነበር:: በስብሰባው ላይ ከተለያዩ የአለም ክፍሎችና ከአሜሪካ ግዛቶች የተሰባሰቡ በርካታ ኢትዮጵያውያን ተገኝተዋል::
የስብሰባው መሪ ሀሳብ “ስለ እያንዳንዳችን ከመናገር እያንዳንዳችን እንነጋገር” የሚል ድፍረትን፣ ግልፅነትን፣ መከባበርን፣ መነጋገር መቻልን ሃላፊነት በተሞላበት ስሜት ይቀርቡ በነበሩት አስተያየቶች የሚያረጋግጡ ከመሆናቸውም በላይ የተለየዩ የፖለቲካ አመለካከት፣ እምነት እንዲሁም የተለየዩ ብሄረሰቦች ዉሁድ ኢትዮጵያውያን በአንድ ጠረጴዛ ዙርያ ተቀምጠው ያነሱዋቸው የነበሩት ሃሳቦች በጥንታዊት ኢትዮጵያና በአዲሲቱ ኢትዮጵያ የፖለቲካ ገመድ ጉተታ ግራ ለተጋቡ ጥሩ አስተማሪ መድረክ ነበር::
ኢትዮጵያ የምትባል ጥንታዊት ሃገርን የሲኦል መገለጫ አድርገው ለሚስሉዋት የህወሃት ኢሃዴግ ደጋፊዎችና ተመሳሳይ አመለካከት ያላቸው የፖለቲካ ሰአሊዎች ወይም ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር ያላቸውን ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ቁርኝት በፖለቲካ ብሩሽ ለማጥፋት የሚንደፋደፉ ያሉትን ያህል አዲሲቱን ኢትዮጵያን በጎሪጥና በሃሳባቸው የተለየ ቅርፅ ሰጥተው ለሚባንኑትም ሁለቱም አካሄዳቸው ሃገራችንን መጉዳቱን የስብሰባው ተሳታፊዎች አማካይ መንገድ እንዳለ በማሳየት ለዚህም ብቸኛ መንገዱ እውነትን መጋፈጥና መነጋገር ብቻ እንደሆነ ያሰመሩበት ጉዳይ ነው::
ስለ ዲሞክራሲ ማውራትና በዲሞክራሲ ህይወት ውስጥ መኖር ያለውን ልዩነት በተሳታፊዎቹ አቀራረብና በመድረኩ አመራር ያለው የዳበረ የፖለቲካ ግንነት አመላካች ነበር::
ይህ ወቅቱ የጠየቀውና አብዛኛው መድረክ ያጣና የታፈነ ኢትዮጵያዊ ድምፅ በመሆኑ ወንድማችን ኦባንግና ሶሊዳሪቲ ይህን መድረክ በመክፈታቸው ከፍተኛ ምስጋናና ድጋፍ ሊደረግላቸው ይገባል:: ከተለያዩ ክፍለ አለማትና ከአሜሪካ ስቴቶች በስፍራው ተገኝታችሁ አሁን በሀገራችን የሚታየውን ችግር ለመፍታት የሚያስችሉ የበሰሉ ሃሳቦችን ላቀረባችሁ ምሁራን የሃይማኖት አባቶችና እናቶች ታላቅ አክብሮትና ምስጋና ይድረሳችሁ::
ኢትዮጵያውያን ዝርዝር ሂደቱን ክፍል 1፣ ክፍል 2 እና ክፍል 3 ከዚህ ማግኘት ትችላላችሁ::
በተለይም በዲያስፖራው የሚታየው ጫፍና ጫፍ ቆሞ በስልጣን ላይ ካለው አምባገነን የህወሃት ኢሃዴግ መንግስት ባልተናነሰ ሁኔታ ባለፉት አመታት ኢትዮጵያውያንን እየከፋፈሉ ያሉት ጥቂት የፖለቲካ ሃይሎችና በስመ ደጋፊነት የተሰለፍን ወገኖች አካሄድ ትግሉን ወደ ሁዋላ ከማስኬድ በስተቀር ያስገኘው ፋይዳ እንደሌለውና አሁንም መፍትሄው ድፍረትና የመቻቻል ፖለቲካ ብቻ እንደሆነ ከምንም በፊት ለእውነት እራስን ም ማስገዛት ተቀዳሚ ተግባር ና የፖለቲካው ወሳነ ሃይል ህዝብን ማእከል ያደረገ ትግል ብቻ መ ሆኑን ከዚህ ስብሰባ መገንዘብ ይቻላል::
ዲያስፖራው የኢትዮጵያን ፖለቲካ በአብዛኛው የሚገመግምበት መድረኩ የፓልቶክ ክፍሎች በመሆናቸው በአካል ተገናኝቶ በመነጋገርና በኮምፒዩተር ጀርባ ሃሳብንም ሆነ ልዩነትን ማስተናገድ ያላቸውን ልዩነት በመገንዘብ ለአካላዊ ግንኙነት ትኩረት በመስጠት መሰባሰቡ ያለውን ፋይዳ መገንዘቡ የወቅቱ ጥያቄ ይመስለኛል::
በፓልቶኮች የሚደረጉ ውይይቶች በአብዛኛዎቹ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻሉና ዲሞክራሲያዊ ባህርያቸውም እያደገ የመጣና የትግላቸውም ማእከል በሃገር ቤት ያለው ትግል መሆኑ የሚያበረታታ ሲሆን የሶሊዳሪትና የአቶ ኦባንግ አካሄድ ለዲያስፖራው ፖለቲካ መጎልበት አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ተስፋ አለኝ::
http://www.goolgule.com/obangs-contribution-to-the-diaspora-politics/

Saturday, December 13, 2014

አገር ውስጥ እየኖሩ መሞት፣ በስደት ጉዞ መሞት፣ በስደት እየኖሩ መሞት!

“መጪው ጊዜ ከኢህአዴግ ጋር ብሩህ ነው!”
ethiopians and their plight

* አገር ውስጥ “ባርነት”፤ ከአገር ተሰድዶ “ባርነት”

ከጥቂት ቀናት በፊት በአገራቸው መኖር ያቃታቸው 70 ኢትዮጵያዊያን ቀይ ባህርን በጀልባ አቋርጠው ወደ የመን ሲያመሩ በደረሰ አደጋ ሁሉም መሞታቸው ተገልጾዋል። ኢህአዴግ እነዚህ በእርግጥ ኢትዮጵያውያን ለመሆናቸው ማስረጃ እንደሌለውና “እያጣራ” መሆኑን በቃል አቀባዩ በኩል ተናግሯል፡፡
በዚህ ዓይነት ሁኔታ ከአገራቸው እየተሰደዱ ለባህር፣ ለአውሬ፣ … የተዳረጉት ወገኖቻችን ብዛት ተቆጥሮ አያልቅም፡፡ ይህንን ሁሉ አልፈው ወዳሰቡት የደረሱት ደግሞ በስደት የሚኖሩባቸው በተለይ የአረብ አገራት ይህ ነው የማይባል ሰቆቃ ይደርስባቸዋል፡፡ ይህንን ሁሉ የሚሰማው ወገን አሁንም በየኤምባሲው ቪዛ ለማስመታት በተገኘው ቀዳዳ ከአገሩ ለመውጣት ይጥራል፡፡ በዚህ በኩል ያልተሳካለት ድንበር በማቋረጥ አስጨናቂውንና አስፈሪውን ጉዞ ይጀምራል፡፡
“አገር እየለማች” ነው ለሚለው ኢህአዴግ ይህ ምንም ዓይነት ምላሽ የሚሰጥበት ባይሆንም አሁንም “ለጊዜው የምጠብሰው ትልቅ አሣ አለና ጊዜ የለኝም” በማለት መስማት የተሳነው መሆኑን ይናገራል፡፡ አሽቃባጭ ካድሬዎቹም በየማኅበራዊ ድረገጾችና መገናኛ ብዙሃን “መጪው ጊዜ ከኢህአዴግ ጋር ብሩህ ነው” ይሉናል፡፡
በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ የስደት ህይወት ለመምራት እየወሰኑ የሚሄዱት ወገኖቻችን ከሚያስቡበት አገር ሲደርሱ ስለሚሆነው ሰሞኑን የወጣው የ2014 “የባርነት መለኪያ ዘገባ” በዘመናዊ ባርነት ውስጥ የሚገኙት ኢትዮጵያውያን ቁጥር 390ሺህ እንደሚገመት ተናግሯል፡፡ (የጎረቤት ኬኒያ65ሺህ እንኳን አልደረሰም)
ከአረመኔ የባህር ላይ አስተላላፊዎች ያመለጡት ወይም “በልማት እየተመነደገች” ካለችው አገራቸው ኑሮን ማሸነፍ እያቃታቸው ወደ አረብ አገራት “በቪዛ” የሚወጡት በ“Global Slavery Index” መለኪያ መሠረት ለዘመናዊ ባርነት የሚጋዙ ናቸው፡፡
አገር ውስጥ ያለው “ዘመናዊ ባርያ” ኑሮን ማሸነፍ ያቃተውና የሰው ልጅ ሊሰራው የማይገባውን ሥራ የሚሠራ እንደሆነ ዘገባው ጠቆሟል፡፡ ከገጠር ወደ ከተማ የሚሰደደውና እዚያም በኑሮ ስቃይ ውስጥ የሚገባው ወላጅ ልጆቹን ለጎዳና ተዳዳሪነት፣ ለልመናና ለወሲብ ንግድ አሳልፎ ይሰጣል፡፡ ወደ ት/ቤት መላክ የሚገባቸው ህጻናት ሊሠሩት ቀርቶ ሊያስቡት የማይገባ እጅግ ዘግናኝና ሰቅጣጭ ሥራዎችን እንዲሰሩ ይገደዳሉ፡፡refugees and their boat
በአፍሪካ ቀዳሚውን ሥፍራ የያዘው የመርካቶ አካባቢ የመሸታና የሴተኛ አዳሪ ቤቶች ክምችት እንደሆነ የጠቆመው ዘገባ የዘመናዊ ባርነቱን ሁኔታ ይዘረዝራል፡፡ በዚህ ሁኔታ ከአገር ውስጥ “ዘመናዊ ባርነት” ያመለጡት ወደ አረብ አገራት “ለውጭ አገር ዘመናዊ ባርነት” ገንዘባቸውን እየከፈሉ ራሳቸውን በፈቃደኝነት ይሰጣሉ፡፡
በዚህ የባርነት ንግድ ያልጠገበው ኢህአዴግ በቅርቡ በሳውዲ የሆነውን የወገን ሰቆቃ ቸል በማለት የተቋተረጠበትን ገቢ እንደገና ለመጀመር “ሕግ እያረቀቀ” መሆኑ ተሰምቷል፡፡ ባርነቱን በመቀጠል ሽያጩን ለማጧጧፍና ትርፉን ለማጋበስ ረቀቅ ባለ ሁኔታ ዝግጅቱን አድርጓል፡፡ ባለሥልጣናቱም የአረቡን አገራት ጎብኝተው “በባርነት ንግዱ” ላይ ተስማምተው መጥተዋል፡፡ ይህንን “መልካም ዜና” የሰሙት “ተስፈኛ ዘመናዊ ባሪዎችም” ዓይናቸውን ጨፍነው ወደ ጭለማው ለመግባትና ህይወታቸውን ለባርነት አሳልፈው ለመስጠት ሙሉ ዝግጅት እያደረጉ ነው፡፡ እስከዚያው ለመጠበቅ ያልቻሉትና “ከአገር ውስጥ ዘመናዊ ባርነት” ሞትን የመረጡት አሁንም ድንበር እያቋረጡ ወደ ባህር ይጓዛሉ፡፡
ባለፉት የመጋቢትና የሚያዚያ ወራት ቁጥራቸው ከመቶ የሚያልፍ በተመሳሳይ አደጋ ሰጥመዋል፤ ለቀብር ሳይበቁ በውሃ ተበልተዋል፡፡ ያገራቸው “ህዳሴና ልማት” ሊያኖራቸው ያልቻለው አውሮጳን አልመው እስከዚያው የአረቢያ ምድርን ተስፋ አድርገው በምድርና በባህር የሚሰደዱት ኢትዮጵያውያን ቁጥር እየጨመረ ከመሄድ በቀር የመቀነስ ሁኔታ አይታይበትም፡፡ አውሮጳን ሳያልሙ “ለዘመናዊ ባርነት” ወደ አረቢያ የሚሰደዱት ምንም ተስፋ በሌለበት ሁኔታ እንኳን ከእነርሱ በፊት ሄደው የተሳካላቸውን ሰዎች በማሰብ እነርሱም ከእነዚያ መካከል እንደሚሆኑ በመገመት ጉዞ ያደርጋሉ፡፡ ከደረቁ ምድር ገና ለመሳፈር ሲነሱ ለባህር ወንበዴዎች ገንዘባቸውን ይከፍላሉ፤ ከዚያም ሲያልፍ የአካል ክፍላቸውን እያወጡ ይሸጣሉ፤ እዚያው በኢንፌክሽን ይሞታሉ፤ ከዚህ ያመለጡትና “ባርነትን” ተስፋ ያደረጉት ደረቅ ምድር ሳይደርሱ በባህር ይሰጥማሉ፡፡ ከዚህ ሁሉ የተረፉት ጥቂቶች ከባህርና ከአጓጓዥ አውሬዎች አምልጠው “ለዘመናዊ ባርነት ብቁ” ይሆናሉ፡፡ በባርነት “ያተረፉትን” ገንዘብ ወዳገራቸው ይልካሉ፤ ያገራቸውን “ኢኮኖሚ በድርብ አኻዝ” ያሳድጋሉ፤ “በልማቱ መስክ” ይሳተፋሉ፤ … “መጪው ጊዜ ከኢህአዴግ ጋር ብሩህ ነው!”
http://www.goolgule.com/life-of-ethiopians-and-the-global-slavery-index/

የኢትዮጵያ መንግሥት ገመና (ተመስገን ደሳለኝ)

ተመስገን ደሳለኝ  (ከዝዋይ እስር ቤት)
Temesgen Desalegn behindbarመሐሙድ የሱፍ የተወለደው በ1980ዓ.ም ከሶማሌ ክልል ርእሰ-መዲና ጅጅጋ 500 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በምትገኘውዶሀን ከተማ ነው፡፡ ለቤተሰቡ ሰባተኛ ልጅ ሲሆን፤ አምስት እህቶችእና ሦስት ወንድሞች አሉት፡፡ በጅጅጋ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት እስከ አስረኛ ክፍል ድረስ መዝለቁቢሳካለትም፤ ከዚህ በላይ ግን ሊቀጥል አልተቻለውም፡፡ ምክንያቱ ደግሞ የኢትዮጵያመንግስት የደህንነት ሠራተኞች የ1999ዓ.ም የግንቦት ሃያ በዓል በጅጅጋ ከተማ ስታዲዬም በተከበረበት ዕለት፣ የኦጋዴን ነፃአውጪ ግንባር (ኦብነግ) በሰነዘረው የቦንብ ጥቃት ተሳትፈሃል በሚል ለእስር በመዳረጉነው፡፡ ይህንን ተከትሎምከምድራችን አስከፊ ማሰቃያዎች መካከል ግንባር ቀደም በሆነውና የክልሉ
ነዋሪ “ጄል-አዳብ” (የገሃነም እስር ቤት) እያለ በሚጠራው ማጎሪያ ውስጥ እጅግ በጣም የከፋ ምድራዊ መከራ እንደተቀበለሀዘን በተጫነው ድምፅ ይናገራል፡፡ በሠውነቱ የተለያዩ ክፍሎች ላይ እንደ ፍም ቀልተው የሚታዩት ጠባሳዎቹም ያሳለፈውንሥቃይ አፍ አውጥተው ይመሰክራሉ፡፡ ለአራት ወራት ያህል አንድ ክፍል ውስጥ ለብቻው ተቆልፎበት፤ ሃያ አራት ሠዓታትሙሉ እጆቹ በካቴና ተቀፍድደው፣በቀን ከአምስት ጊዜ በላይ ለምርመራ እየተጠራ ያለዕረፍት ከባድ ስቅየት (ቶርቸር)ሲፈፀምበት ቆይቷል:፡ በመጨረሻም ለአንዲትም ቀን የፍርድ ቤት ደጅ ሳይረግጥ፣ ለኦብነግ አባላት አንድ ፓኬት ሲጋራሲያቀብል እጀ-ከፈንጅ ተይዟል በሚል ክስ የጅጅጋ ዞን ፍርድ ቤት በሞት እንዲቀጣ መወሰኑን እዛው እስር ቤት ሆኖከኢትዮጵያ ሬዲዮ የዜና እወጃ  እና ከቪኦኤ ሶማሊኛ ፕሮግራም ሠምቷል፡፡
ከፍርዱ በኋላም በተመሳሳይ ወንጀል ከተከሰሰ አንድ እስረኛ ጋር በካቴና ተጠፍሮ በቀን አንድ እንጀራ ለሁለት ተካፍሎእንዲበላ እንደ ውሻ እየተወረወረለት 60 ቀናትን አሳልፏል፡፡ መሐሙድ በተለይም በእንቅልፍ ወቅት እርሱ ወይምየሰንሰለት ደባሉ የተገላበጠ እንደሆነ ካቴናው የሚያደርስበትን የመለብለብ ቃጠሎ ሲያስታውስ ዓይኖቹ በእንባ ይሞላሉ፡፡በአሁኑ ወቅት በዝዋይ ማጎሪያ ከባድ ጥበቃ ለሚደረግባቸው ብቻ በተመደበ ‹‹ዘጠነኛ ቤት›› ውስጥ አስራ አንድ ሶማሊኛተናጋሪዎችን ጨምሮ በድምሩ ሰላሳ አራት ሰዎች ጋር ከዛሬ ነገ የግፍ ፍርዱ ተፈጻሚ ሊሆንብኝ ይችላል በሚል ሰቀቀንእየባነነ በስጋት ተጠፍንጎ መኖር ከጀመረ እነሆ ሰባት ዓመት ሊደፍን ሦስት ወራት ብቻ ቀርተውታል፡፡
የተዋረደው የፍትሕ ሥርዓት!. . .
ርግጥ ነው ይህ በጨረፍታ ያቀረብኩት አሳዛኝ ታሪክ የመሐሙድ የሱፍ ብቻ አይደለም፡፡ ሌሎች ሰባት ‹‹አባሪዎቹ››ስቃዩንም ሆነ የሞት ፍርዱን ይጋሩታል (በነገራችን ላይ በአንድ መዝገብ የተወነጀሉት እነዚህ ስምንት የሞት ፍርደኞች፡-መሐድ ኢብራሂም፣ አረብ ሰዋኔ ዱልባንቲ፣ ሐሰን መሐመድ ዑስማን፣ ሐሰን መሐመድ ዓሊ፣ ሙክታር መሐመድ ዓብዱላሂ፣ከድር ሽኩር ሙሳ እና ካሚል ዓብዱልናስር እንኳን በጋራ መንግሥት ላይ ሊያሴሩ ቀርቶ እርስ በርስም የተዋወቁት እስር ቤትውስጥ ነው፡፡ ከጅጅጋ ወደ ዝዋይ ‹‹ዘጠነኛ ቤት›› ተዘዋውረው በርካታ ዓመታትን ያሳለፉትም በጭካኔው ወደርእንደማይገኝለት የሚነገረው የክልሉ ፕሬዚዳንት አብዲ
በአደራ እንዲቀመጡ በመተላለፋቸው መሆኑን ነግረውኛል፡፡) እንደ መሐሙድ ሁሉ እነርሱም ፍርድ ቤት ቀርበውአያውቁም፤ ምንም ዓይነት የሰውም ሆነ የሰነድ ማስረጃ አልተቆጠረባቸውም፡፡ እዚህ ጋ የማነሳው አሳዛኝ ገጠመኝከመካከላቸው አንዳቸውም ራዲዮ ስላልነበራቸው የተጣለባቸውን የሞት ፍርድ ውሳኔ የሠሙት፣ ዜናው ከተላለፈ ከበርካታቀናት በኋላ ሬዲዮ ካላቸው እስረኞች መሆኑ
ነው፡፡ ይህ እጅግ አሳፋሪና አስደንጋጭ መንግሥታዊ ውንብድና በደንብ ይብራራ ዘንድ ለተከሳሶቹ ከተሰጣቸው ባለ አንድገፅ የክስ ቻርጅ የሁለቱን ብቻ በአዲስ መስመር እጠቅሳለሁ፡-‹‹በሶማሌ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ አቃቤ ሕግና ፍትሕቢሮ በሶማሌ ክልላዊ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት
ጅጅጋ
የዐ/ሕግ/መ/ቁ 90/2000
ዝዋይ እስር ቤት ያለው
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከሳሽ፡- ዐ/ሕግ
ተከሳሽ፡- ሐሰን መሐመድ ዑስማን (ሐንን መድቤ)
ዕድሜ፡- 21
ሥራ፡- ተማሪ
አድራሻ፡- ጅጅጋ ከተማ፡- 06 ቀበሌ
ወንጀል
በ1996ዓ/ም የወጣውን የኤ.ፌ.ዴ.ሪ የመ.መ.ሥ.ሥ.ህ.ቁ. 240(3) እና 251(መ) ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ፣
የወንጀል ዝርዝር
ተከሳሽ ከመስከረም 1999 ዓ.ም. ጀምሮ እራሱን ኦ.ብ.ነ.ግ. እያለ ከሚጠራው ተቃዋሚና አሸባሪ ድርጅት ጋር በራሱፈቃድ
በዚሁ በጅጅጋ ከተማ ከላይ በተጠቀሰው ዓመተ-ምህረት አባል በመሆን በጫካ በዚሁ አካባቢ ከሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ጋርበከተማም
ሆነ በጫካ በመገናኘት በኢኮኖሚ ረገድ የሚያስፈልጋቸውን፡- ጫማ፣ ልብስ የመሳሰለውን እዚያው ድረስ ሄዶ በማቀበልአብሮ
ሲንቀሳቀስ በመቆየቱ ተከሶ ቀርቧል፡፡››
ሁለተኛው የክስ ቻርጅ ደግሞ እንዲህ ይነበባል፡-
‹‹በሶማሌ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ አቃቤ ሕግና ፍትሕ ቢሮ
በሶ/ክ/መ/ ጅጅጋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት
ጅጅጋ
የዐ/ሕ/መ/ቁ 90/2000
ከሳሽ፡- ዐ/ሕግ
ተከሳሽ፡- መሐድ ሼክ ኢብራሂም
ዕድሜ፡- 28
ሥራ፡- የለውም
አድራሻ፡- ጅጅጋ ከተማ፡- ቀበሌ 05
1ኛ ክስ
ወንጀሉ
በ1996 ዓ/ም የወጣውን የኤ.ፌ.ዴ.ሪ የመ/መ/ህ/ ቁ. 241 እና 251(መ) ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሹ በ1998 ዓ.ም. ወራትና ቀኑ በውል ካልታወቀ ጊዜ ጀምሮ እራሱን ኦ.ብ.ነ.ግ. እያለ ከሚጠራው ተቃዋሚ የፖለቲካ
ድርጅትና አሸባሪ ጋር በራሱ ፈቃድ አባል በመሆን ከዚህ ሕገ-መንግሥቱን ከሚፃረር ድርጅት በቀጥታ ፌዴሬሽኑእንዲከፋፈል፣ ክልሉን
የመገንጠል ዓላማ ለማሳካት ይህንኑ ድርጅት ከዚሁ በጅጅጋ ከተማ ለጊዜው ካልተያዘ ግብረ-አበሩ ጋር በመሆን ይህንኑአሸባሪ ድርጅት
በሚያስፈልገው ማቴሪያል ሁሉ፡- ጫማ፣ የፖሊስ የደንብ ልብስ፣ መድሃኒት. . . የመሳሰለውን በማቀበሉ፡፡
2ኛ ክስ
ወንጀሉ
በ1996ዓ/ም የወጣውን የኤ.ፌ.ዴ.ሪ የመ/መ/ህ/ ቁ. 36 (ለ) ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሹ ከ1996 ዓ.ም. ጀምሮ የተለያዩ መ/ቤቶች ማለትም፡- የክልሉ ት/ቢሮን፣ የቀብሪ-ደሐር ት/ቢሮን፣ እንዲሁም የMSF
እና የተለያዩ መሥሪያ ቤቶችን እና የትምህርት ተቋማትን ማህተም በማስመሰል አትሞ እና የኃላፊዎችን ፊርማ ዓይነትአስመስሎ
በማስፈር ሐሰተኛ ሰነድ አዘጋጅቶ በመገኘቱ ተከሶ ቀርቧል፡፡››
(ሁሉም የክስ ቻርጆች ማኅተም እና አንጋው አፈወርቅ ምንተስኖት የተባለ የክልሉ ዐቃቤ ሕግ ፊርማ አላቸው)
እነሆም ያለአንድ ምስክር፣ ያለምንም የሰነድ ማሰረጃ፣ አንድም ቀን ችሎት ቀርበው የእምነት ክህደት ቃል ሳይጠየቁ እና
ሳይከራከሩ (ያውም የዞን ፍርድ ቤት) በነዚህ በስም በጠቀስኳቸው በስምንቱ ኢትዮጵያውን ላይ የሞት ቅጣትን የመሰለየመጨረሻ
ውሳኔ እንደቀልድ አስተላልፎባቸዋል፡፡ (በነገራችን ላይ ሌሎች 13 የኢትዮጵያ-ሶማሌ ተወላጆችም በተመሳሳይ የሐሰትውንጀላ የዕድሜ
ልክ እስር ተፈርዶባቸው ዝዋይ ይገኛሉ፡፡ የሚገርመው ጉዳይ ደግሞ ም ቢሆኑ መጀመሪያ ተጠርጥረው በተያዙበት ወንጀልአይደለምየተጠየቁት፡፡ ጉዳዩ ጭራሽኑ በምርመራም ወቅት አልተነሳም) መቼም በዚህ መልኩ በተቀናበረ የውሸት ክስ ከ20-27 ዓመት የሚገኙ
ወጣቶችን በሲኦላዊ እሳተ-ነበልባል ስቅየት ውስጥ እንዲያልፉ ከማድረግም በዘለለ፣ ብሩህ ቀናቸውን አጨልሞ ላይመለሱወደመቃብር
የሚሸኝ ቅጣት ሲጣል ከመመልከት የበለጠ የትኛውንም ዜጋ የሕሊና ስቃይ ውስጥ ከትቶ፣ አንገት አስደፍቶ፣ በቁጣ ቀስቅሶ
ወደአደባባይ የሚያወጣ ገፊ-ምክንያት አለ ብዬ አላምንም፡፡

ማነው ተጠያቂው?
በእነዚህ ንፁሃን ኢትዮጵያውያን ላይ ‹በጄል-አደብ› የደረሰባቸው በነውረኝነት የታጀለ ኢ-ፍትሐዊ ፍርድ እና ስቅየት፣
የሥርዓቱን እውነተኛ ማንነት ገሃድ የሚያወጣ ተጨባጭ ተግባር መሆኑ ባይካድም፡ ይህንን አረሜናዊ ድርጊት በፊት-አውራሪነት
የመሩት፡- ኮሎኔል ሞኒ መንገሻ በጊዜው የክልሉ የፀረ-ሽብር ግብረ-ኃይል ዋና ኃላፊ የነበረ አሁን ወደአዲስ አበባ ተቀይሮ‹ሕገ-ወጥ
የሠው ዝውውር ወንጀል መከላከል› ኃላፊ፣ ቢኒያም የተባለ የክልሉ የደህንነት ኃላፊ፣ ሻለቃ ዘገየ በክልሉ የፌዴራል ፖሊስኃላፊ፣
ወልደአራዌ የክልሉ ፖሊስ ም/ኮሚሽነር፤ እንዲሁም ሻለቃ ወንድሜ፣ ሻለቃ በለጠ እና ታሰረ የተባሉ ኃላፊነታቸውንለይተው
የማያስታውሷቸው ግለሰቦች መሆናቸውን ግፉአኖቹ በተሰበረ ልብ፣ ምሬት በሞላው ድምፅ፣ ተስፋ በቆረጠ ስሜትሲተርኩልኝ ዓይኖቼ
ላይ የተቋጠረው የእንባ ከረጢት ገንፍሎ እንዳይፈስ ብርቱ ትግል ማድረጌን አልሸሽግም፡፡
የሆነው ሆኖ እነዚህ የሥርዓቱ ሹማምንት የፍርድ ቤት ደጅ ሳይረግጡ፣ የሞት ቅጣት እንዲተላለፍባቸው ባደረጓቸው
ምስኪኖች ላይ የማሰቃያ ጥበቦቻቸውን በሙሉ ከሞከሩባቸው በኋላ፡- ‹‹ሞት እንፈርድባችኋለን!!›› እያሉ ያስፈራሯቸውናይዝቱባቸው
ነበር፤ እነርሱም፡- ‹‹እናንተ ፍርድ ቤት ናችሁ እንዴ?›› ብለው በግርምትና ባለማመን ሲጠይቋቸው፣ ማናአህሎኝነትያሳበጣቸው የፀጥታ
ኃላፊዎች እንዲህ በማለት አስረግጠው መልስ መስጠታቸውን ሰምቻለሁ፡-
‹‹አዎን! ፍርድ ቤት ማለት እኛ ነን!!››
በርግጥ ከዚህ ሁሉ መከራ በኋላ የተላለፈባቸው ውሳኔ፣ ያውም በሞት እንዲቀጡ የሚል መሆኑን ስናስተውል የዛቻውን
መነሾ መረዳቱ አዳጋች አይሆንብንም፡፡ በአናቱም በምርመራ ወቅት ዕድል ፊቷን ያዞረችበትን ተጠርጣሪ እዛው እስረኛ ፊትበሽጉጥ
ግንባሩን በርቅሰው እንደ መናኛ ነገር ሜዳ ላይ ይዘረጉት እንደነበረ የዓይን እማኞች ይመሰክራሉ፡፡
በጥቅሉ ይህ ሁነት በሀገሪቱ አለቅጥ የተንሰራፋውን የፍትሕ እጦት፣ የሠብአዊ መብት ጥሰት፣ ዳኞች ከሕግ ይልቅ ከቤተ-
መንግሥት በሚላክላቸው የፍርድ ውሳኔ ንፁሃኑን ለምድራዊ ስቃይ ከመዳረግም አልፈው ተርፈው በጭካኔሕይወታቸውንም
እንደሚነጠቁ በቂ ማስረጃ ይመስለኛል፡፡

‹‹ጄል-አዳብ››
የክልሉ ኗሪዎች ‹‹ጄል-አዳብ›› (የገሃነም እስር ቤት) እያሉ የሚጠሩት የጅጅጋው ማሰቃያ ቤት ክፍሎች የተሠሩት አራትመቶ
ታሳሪዎችን እንዲይዙ ታስቦ ቢሆንም፣ አብዛኛውን ጊዜ ከአራት ሺህ በላይ ታሳሪዎች እንደሚታጎሩበት አረጋግጫለሁ፡፡ይህም አንድ
ሰው ከአንድ ሰዓት በላይ በእንቅልፍ ማሳለፍ እንዳይችል አድርጎታል፡፡ ምክንያቱም ቦታውን ለተረኛው የመልቀቅ ግዴታአለበትና፡፡
ምናልባት እንቅልፍ ቢጥለው እንኳ ተረኞቹ ቀስቅሰው (ጎትተው) ያስነሱታል፡፡
ከ‹‹ጄል-አዳብ›› በሕይወት ተርፎ የሚወጣ ሰው ዕድለኛ ተደርጎ ይቆጠራል፡፡ በዚህ ቦታ ከቤተሰብ ጋር መገናኘት ጭራሽ
አይሞከርም፡፡ ማሰቡ እንኳ እንደ ቅንጦት ነው የሚታየው፡፡ በእስር ቤቱ አጥር ሦስት መቶ ሜትር ክልል ርቀት ዙርያ ውስጥመገኘትም
ለከባድ ስቃይ (አንዳንዴም ለሞት ቅጣት) ይዳርጋል፡፡ በሃያ አራት ሰዓት አንዴ፣ አንድ እንጀራ ለሦስት እየተቃመሱለአምስት ዓመት
በዛ እስር ቤት ያሳለፈ ምስኪን አጋጥሞኛል፡፡ ይህ ወጣት በ2004ዓ.ም መጨረሻ አካባቢ ሦስት ዓይነት ተላላፊ በሽታ(ተቅማጥ፣
ሰውነትን የሚያሳክክና ጉሮሮን አሳብጦ ለአዕምሮ መቃወስ የሚዳርግ) ተከስቶ በቀን እስከ አስራ አራት ሰው ድረስ ይሞትእንደነበር
ያስታውሳል፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን ሕክምና ብሎ ነገር አልነበረም፡፡ እንዲያውም በግልባጩ የክልሉ አስተዳዳሪዎችጭካኔያቸውን (ኢ-
ሠብአዊነታቸውን) ወለል አድርገው የሚያሳብቁ ድርጊቶች መፈፀማቸውን አላቋረጡም፡፡ ለማሳያ ያህልም እስረኛው ከሌሊቱስድስት
ሰዓት ላይ በአንድ ድምፅ እንዲህ የሚል መፈክር እንዲያሰማ መገደዱን እዚህ ጋ መጠቀስ ይቻላል፡-
‹‹መለስ ዜናዊ ሐኖላዶ!›› (መለስ ዜናዊ ለዘላለም ይኑር!)
‹‹አብዲ ሑመድ ዑመር ሐኖላዶ!››
‹‹ኢትዮጵያ ሐኖላዶ!››
ኦብነግ ሐዳኦዶ!›› (ኦብነግ ይውደም!)ሌላው አስገራሚ ጉዳይ ቤተሰብ ታሳሪ ልጁ በሕይወት ይኑር ይሙት የሚያውቀውከማጎሪያው በስንት ጊዜ አንዴ የሚፈታ
ሰው ሲገኝ ብቻ የመሆኑ እውነታ ነው፡፡ እናም ድንገት በአንዲት ‹ዕድለኛ› ቀን አንድ ታሳሪ ከ‹‹ጄል-አዳብ›› የተለቀቀእንደሆነ ወሬው
ከመቅጽበት ይዛመትና ለሳምንታት አሊያም ለወራት የእስረኛው ቤት በእንግዶች እስከ አፍ-ገደፉ ጢም ብሎ ይውላል፡፡የተለመደ
ነውና እሱም ያለመታከት የቀረበለትን ጥያቄ በሚከተለው መልኩ ሲመልስ ይከርማል፡-
‹‹ኦ!… እገሌ ከሞተ እኮ ሁለት ዓመት አለፈው›› ፤ “እገሌማ ሲያሳዝን! ካረፈ ገና አንድ ወሩ ነው”፤ “ኦ! እገሌ ለወደፊቱ
እግዜር ይጠብቀው እንጂ እስካሁን በሕይወት ይገኛል…” ወዘተ ወዘተ. . .