Wednesday, September 25, 2013

“ማኅበረ ቅዱሳን አክራሪ ሆኖ የገደለው ሰው የለም’ – ዲ/ን ዳንኤል ክብረት ምላሽ ሰጠ

የቀድሞው ጠቅላይ ሚ/ር መለስ ዜናዊ በፓርላማ ማህበረ ቅዱሳንን “አክራሪ” ሲሉ መግለጻቸው ይታወሳል። ከቅርብ ግዜ ወዲህ ደግሞ የአቶ ኃይለማርያም መንግስት በተለይ የጸረ ጽንፈኝነትን እና አክራሪነትን ለማጥፋት እታገላለሁ እያለ ባለበት ወቅት ማህበረ ቅዱሳንን ደግሞ አክራሪ ሲል መግለጹ ከፍተኛ ቁጣን መቀስቀሱ ይታወሳል። በአዲስ አበባ እየታተመች የምትወጣው እንቁ መጽሔት ሰሞኑን ዲ/ን ዳንኤል ክብረትን አነጋግራ ወጥታለች – በዚህ ጉዳይ። ዘ-ሐበሻ ይህን ቃለ ምልልስ እንደወረደ ለአንባቢ ግንዛቤ ሊሰጥ ይችላል በሚል መንፈስ አስተናገዳዋለች።
ዕንቁ፡- ጽንፈኝነት ምንድን ነው? አክራሪነትስ?
ዲ/ን ዳንኤል ክብረት፡- አንድን ነገር ወደ ጥግ ወይም ወደ መጨረሻው ጠርዝ ላይ መውሰድ ጽንፈኝነት ነው፡፡ በነገራችን ላይ፣ አክራሪነት ይሁን ጽንፈኝነት በጽንሰ ሐሳብ ደረጃ ብዙም ልዩነት ያላቸው ጉዳዮች አይደሉም ፡፡ ልዩነታቸው በአፈጻጸም ላይ ነው ፡፡ ጽንፈኞቹ ‹‹ይሄ እና ይሄ ብቻ!›› የማለት ጠባይ አላቸው፡፡ አክሪዎቹ ደግሞ ‹‹ይሄ እና ያ….. ካልሆነ እንዲህ እናደርጋለን›› ወደሚልና ወደ ተግባሩ ርምጃ የሚያዘሙት ናቸው፡፡ ጽንፈኝነት በየትኛውም ጠባይ ሊኖር ይችላል፡፡ በማንኛውም ጉዳይ በቅርብ ስትመጣ ለዘብተኝነት ፣ ወደ መሀል ሲሆን ወግ አጥባቂነት ፣ ወደ ዳር ሲኬድ ጽንፈኝነት ይኖራል፡፡ በባሕልም ቢኾን ለዘብተኛ ሰው አለ ፤ ማንኛውም ባህል ምንም የማይመስለው፡፡ ባህሉን የሚያጠብቅም አለ ፤ ‹‹ባሕሌን እወደዋለኹ፤ አከብረዋለኹ፤ ለምን ትነካብኛለህ? ለምንስ ትበርዘዋለህ? እንዲሁ ሳይበረዝና ሳይከለስ እንዲሁ እንዲኖርልኝ እፈልጋለኹ. . .›› ብሎ የሚያስብ ሰው አለ፡፡ ወደ ዳር ያለው ደግሞ ‹‹ከዚህ ውጭ ያለውን ፈጽሞ ማየትም ኾነ መስማት አልፈልግም!. . .›› ባይ ነው፡፡ የሌላውን ህልውና የሚክድ ነው፡፡ ይህ ለእኔ ተፈጥሯዊ ነው፡፡ ከባዱ ነገር አክራሪነት ነው፡፡ ወደ አክራሪነት ስትመጣ ‹‹ይሄኛውን ካልተቀበለ…›› ከሚል ይነሣና ርምጃ እስከ መውሰድ ጥግ ድረስ የሚሄድ ይሆናል፡፡
ዕንቁ፡- በኢትዮጵያ ውስጥ አክራሪነት አለ?
ዲ/ን ዳንኤል ክብረት ፡- በአገራችን ‹‹አክራሪነት የለም›› ብለን መደምደም አንችልም፡፡ በተወሰነ ደረጃ አለ፡፡ የሚለያየው በምን ያህል ደረጃና የት ነው ያለው? የሚለው ይመስለኛል፡፡ ምክንያቱም የመኖሩን ምልክት ሰዎች ከእምነታቸው የተነሣ ሲገደሉ፣ የእምነት ቦታዎች ሲቃጠሉ ፣ የእምነት አባቶች መቃብራትና የተለያዩ ነገሮች እንዲፈርሱ ሲደረጉ አይተናል፡፡ ጽንፈኝነትን ብቻ ሳይሆን ወደ ኃይል ርምጃው የመሄዱን ነገር አይተናል፡፡የዛሬ ሰባት ዓመት ከተመለከትነው የጅማው ድርጊት ብንነሣ እንኳ አክራሪነት መኖሩን እንረዳለን፡፡ እነዚያ የጅማ ክርስቲያኖች የተገደሉት ምንም መጥፎ ነገር አድርገው አልነበረም፡፡ ‹‹ብዙዎች ሆነው ነውጥ ፈጥረው ነው›› እንዳይባል በቁጥራቸው ትንሽ ናቸው፡፡ የነበሩትም በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ነበር፡፡ ኢሕአዴግ በገባበት ከኻያ ዓመት በፊት በነበሩት ሰሞናት በአሰቦት ገዳም እነ ጃራ አል ኢስላሚያ የፈጸሙትም በምሳሌነት ሊወሰድ የሚችል ነው፡፡ እነዚያ መነኮሳት ተራራ ላይ በነበረ አንድ ገዳም ይኖሩ የነበሩ ናቸው፡፡ ሌላ ያደረጉት ነገር የለም፡፡ የተገደሉት መነኩሴ ወይም ክርስቲያን በመኾናቸው ብቻ ነው፡፡ ይህ ሲታይ የአክራሪነት ጠባዕያት በአገራችን የለም ለማለት ያስቸግራል፡፡
ዕንቁ፡- ከመቼ ወዲህ ነው ይህ ዝንባሌ በኢትዮጵያ መስተዋል የጀመረው?
ዲ/ን ዳንኤል፡- ይህ የመገዳደል ሁኔታ ማለትም አንድ ሰው ክርስቲያን በመኾኑ የመግደል፣ ሙስሊም በመኾኑ የመግደል ወይም የሙስሊምን መስጊድ፣ የክርስቲያኑን ቤተ መቅደስ በማቃጠል የሚገለጸው ድርጊት በቅርብ ጊዜ ታሪክ ውስጥ ከ1980ዎቹ በኋላ መታየት የጀመረ ነው ፤ የተመዘገቡት መረጃዎች እንደሚያሳዩት ፣ ከ1980 ዓ.ም ወዲህ ነው፡፡ ይህም ከአካባቢያዊ ሁኔታዎችና በመላው ዓለም ከተስተዋለው የተከተለና ችግርን የመፍቻ አንድ አማራጭ አድርጎ ከመመልከት የመነጨ ነው፡፡
ዕንቁ፡- በአገር ውስጥ እንዲህ ዐይነት ነገሮች እንዳይከሠቱ ያልተሠሩ ሥራዎች አሉ?
ዲ/ን ዳንኤል፡- አንድ ከመንግሥት ፣ ሁለት ከሃይማኖት ተቋማት ፣ ሦስት ከሌሎች አካላት በኩል ያልተሠሩ ሥራዎች አሉ፡፡ መንግሥት በሕገ መንግሥቱ ‹‹ሃይማኖት እና መንግሥት የተለያዩ ናቸው›› ብሏል ፡፡ ግን ኢትዮጵያ ውስጥ የሃይማኖት ፖሊስ እንኳ የለም፡፡ ይሄ ባለመኖሩ መንግሥት ሃይማኖቶችን እንዴት ነው የሚያያቸው? ለሚለው መልስ ለማግኘት አስቸጋሪ ይኾናል፡፡ ስለዚህ በአንድ በኩል ያለው ለሌላው ያደላል፣ በሌላ በኩል ያለውም ለሌላው ያደላል እያለ እንዲያማርር ኹኔታው በር ከፍቷል፡፡ አሠራሮች ላይ የሚፈጠሩ ነገሮች አሉ፤ በምዝገባውና በሌላውም፡፡ አንዳንዶቹ የተጨቋኝነት፣ ሌሎቹ የጨቋኝነት፣ ደግሞ አንዳንዶቹ የተገላጋይነት ስሜት እንዲሰማቸው የሚያደርጉ ናቸው፡፡የሃይማኖት አስተሳሰቦች የሚመሩትን ብዙኃኑን ሕዝብ እንዴት ነው? በምን መልኩ ነው? እምነቱን ከአገሪቱ ዕድገት፣ ከአገሪቱ የፖሊቲካ አስተሳሰብ ጋራ በማይጣላበት ሁኔታ ጋር ማስኬድ የሚቻለው….. በሚለው ላይ በደንብ የተጠና ፖሊስ በአገሪቱ አልነበረም፡፡ የተሠራ ሥራ አልነበረም፡፡ አሁንም አለ ለማለት ይከብደኛል፡፡ ዛሬ በሃይማኖት ጉዳዮች አንድ የሃይማኖት ‹‹ዳይሬክቶሬት›› ነው ያለው፡፡ ግን አገሪቱ ውስጥ ትልልቅ ቦታ የሌላቸው፣ ታላላቅ ጉዳዮችን የማይወስኑ…. በትልቅ ፖሊሲ፣ በትልቅ ሚኒስቴር ደረጃ ይታያሉ፡፡ ይህ ለቦታው የተሰጠውን ግምት ያንጸባርቃል፡፡ ብዙውን ውኃ በትንሽ ኮዳ ለመያዝ የመሞከር አሠራር ነው የሚስተዋለው፡፡ ስለዚህ በእምነቱ ጉዳይ ከኮዳው አቅም በላይ ሲኾን የሚፈጠሩ ዐይነት ችግሮች እየተመለከትን ነው፡፡
ዕንቁ፡- አክራሪነትን ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ አኳያ እንዴት ታየዋለኽ?
ዲ/ን ዳንኤል ፡- በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ አክራሪነት ቦታ የለውም፡፡ ከመጽሐፍ ቅዱስ ይዘት፣ ከቀኖናው ስንነሣ ይህች ቤተ ክርስቲያን ለሌሎች ዕውቅና የመንፈግ ችግር አልነበረባትም፡፡ ዕውቅና ስትሰጥ ነው የኖረችው፡፡ የእስልምና እምነት ተከታዮች ወደ አገሪቱ ሲመጡ፣ በወቅቱ የነበሩት ካህናት፣ ዲያቆናት፣ ምእመናን ባይቀበሉት ኖሮ ንጉሡ ብቻውን ምንም ሊያደርግ ባልቻለ ነበር፡፡ የዚህ ምክንያት ኢትዮጵያ ውስጥ የነገሥታቱ ሥልጣን፣ ከእምነት አባቶች ተቀባይነት ማግኘት የሚመነጭ በመኾኑ ነው፡፡ ያ ሳይኾን ሲቀር በአገሪቱ የተፈጠሩትን ችግሮች ቀረብ ካሉት ጊዜያት በእነ ዐፄ ቴዎድሮስ፣ በእነ ዐፄ ሱስንዮስ ከኾኑት ድርጊቶች ማየት እንችላለን፡፡ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሁልጊዜ ግጭቶች ይፈጠሩ የነበሩት፣ ሌሎች ለእርሷ ዕውቅና መስጠት ሲያቅታቸው ነው፡፡
ለምሳሌ ባለፉት ሁለት ሺሕ ዘመናት ስትቀድስ፣ ስታስተምር የኖረችበትና በ6ኛው መ/ክ/ዘ በእጅ የተጻፈው ወንጌል የተገኘው በዐድዋ እንዳባ ገሪማ ገዳም ነው፡፡ ከእርሱ የቀደመ እስከ አሁን ሊገኝ አልቻለም፡፡ እንደዚህ ያለ የክርስትና ታሪክ የተገኘባትንና አስቀድማ ወንጌል ስታስተምር የነበረችን ቤተ ክርስቲያን ‹‹ወንጌል ስታስተምሪ አልነበረም›› የሚልና ለሥራዋ፣ ለአገልግሎቷ ዕውቅና የመንፈግ ችግር አለ፡፡ ይህን ኃይል በመጠቀም፣ ድንበሯን በመሻገር፣ እርሷው ቤት ድረስ ገብተው ካህናቷ ካሉበት፣ ቅኔ ማሕሌቷና መቅደሷ ውስጥ የመዝለቅ ፍላጎት ያላቸው ሲመጡ ችግር ነው የሚኾነው፡፡
በ17ኛው መ/ክ/ዘ በዐፄ ሱስንዮስ ጊዜ በካቶሊኮችና በኦርቶዶክሶች መሐል የተከሠተው ግጭት መንሥኤው አስቀድሜ የገለጸኹት ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያኒቱ ሮማ አልሄደችም፡፡ ሮም ናት እዚህ የመጣችው፡፡ እዚህ መምጣቷ ብቻ አልነበረም ችግሩ፣ ‹‹ከዛሬ ጀምሮ ከበሮው፣ ታቦቱም፣ የካህናቱ አልባሳትም ይውጣ! የዘመን አቆጣጠሩም እንደ ጎርጎሮሳውያን ይሁን! በዓላቱም ይቀየሩ! የዓመቱ መጀመሪያ መስከረም መኾኑ ቀርቶ ታኅሣስ ይሁን!›› በሚል በቀጥታ በቤተ ክርስቲያኒቱ ህልውና ውስጥ ገቡ፡፡ ይህን የመሰለው ግፊትና ዕውቅና የመንፈግ ኹኔታ ሲመጣ ወደ ጦርነት ደረጃ ታለፈ፡፡
በስተኋላ የዐፄ ሱስንዮስ ዘመን አልፎ የዐፄ ፋሲል ዘመን ሲመጣና ችግሩ ቆሞ ኢትዮጵያውያን አባቶች፣ እነዚህ ሰዎች ምን ይደረጉ ሲባሉ ‹‹ጉባኤ ይጠራና እንከራከር›› ነው ያሉት፡፡ ጉዳዩን ከጉልበት ወደ ዕውቀት አቅጣጫ ነው የወሰዱት፡፡ ‹‹የሐሳብ ክርክር እናድርግ፤ በጉባኤው የረታ ይሂድ›› አሉ እንጂ ሌላ ነገር አላሉም፡፡ ይህም የሊቃውንቱን ጠባይ የሚያሳይ ነው፡፡ ስለዚህ በቤተ ክርስቲያኒቱ ታሪክ አክራሪነትን ሊያበቅል የሚችል መሬት አይገኝም፡፡
ዕንቁ፡- በቅርቡ የመንግሥት ወኪሎችና ሌሎች የሃይማኖት አባቶች በተገኙበት አገር ዓቀፍ የሆነ ጉባኤ፣ አባ ዮናስ የተባሉ ሰው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በተለይ በማኅበረ ቅዱሳን በኩል ‹‹የአክራሪነት ችግር አለ›› የሚል ሐሳብ አቅርበዋል፡፡ ይህን መነሻ በማድረግ በርግጠኝነት በቤተ ክርስቲያኒቱ የአክራሪነት ችግር ስለመኖሩ ለማሳወቅ የደፈሩ የፖሊቲካ ሰዎችም ነበሩ፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ የአንተ አስተያየት ምንድን ነው?
ዲ/ን ዳንኤል፡- በቅድሚያ አሁን በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ ያሉትን ሰዎች በሦስት ከፍለን ማየት አለብን፡፡ አንደኛ የሌሎች መሣርያ በመኾን መሣርያ ያደረጓቸውን ወገኖች ጉዳይ የሚያስፈጽሙ አሉ፡፡ እነዚህ ሰይጣን ወደ ገነት መግባት በቻለበት ሁኔታና መንገድ ሊታዩ ይችላሉ፡፡ እንደሚታወቀው ሰይጣን ራሱ ወደ ገነት አልገባም፡፡ ወኪል ነበረው፡፡ ወኪሉም እባብ ነበር፡፡ በእባብ ውስጥ አድሮ ነው ወደ ገነት የዘለቀው፡፡ ምክንያቱም የሰይጣን ባሕርይም ጠባይዕም ስለማይፈቅደለት ራሱ ወደ ገነት አይገባምና ነው፡፡ በአባቶቻችን መጽሐፍ እንደሚነገረው፣ እባብ ተንኮለኛ፣ ውብና ትክለ መልካም ነበረች፡፡ ስለዚህ ሰይጣን ክፉ ሐሳቡንና ሤራውን በተዋበውና በማራኪው የእባብ ውበትና ተክለ ሰውነት ሸፍኖ ወደ ገነት ገባ፡፡ ሔዋንም ልትሳሳት የቻለችው የምትነጋገረው ከእባብ ጋራ ስለመሰላት ነው፡፡ ከእባብ ጀርባ ያለውንና የእባብን ሐሳብ የቀየረውን ነገር መመልከት አልቻለችም፡፡ልክ እንደዚሁ ሁሉ ገነት በኾነችው ቤተ ክርስቲያን የሌላውን ሐሳብ ይዘው የመጡ ወገኖች ገብተዋል፡፡ እነዚህ ወገኖች በምንኩስና፣ በቅስና፣ በዲቁና፣ በመምህርነት፣ በዘማዊነት አለባበስ ውስጥ ሁሉ የሚገኙ ናቸው፡፡ ግን ሐሳባቸው የእነርሱ አይደለም፡፡
ሁለተኛ፡- ቤተ ክርስቲያኒቱ ለዘመናት ስትቃወመው የነበረችውን የለዘብተኛ ማለት የሊበራል ክርስትና አስተሳሰብ ተጭነው በመምጣት ያን የሚያራምዱ ሰዎችም አሉ፡፡ ከእኒህ ጋራ ሊታዩ የሚችሉ ግን ደግሞ ለምንም ነገር ግድ የሌላቸው ሰዎችም አሉ፡፡ በአርባና በሰማኒያ ቀናቸው ከመጠመቃቸው በቀር ለምንም ሆነ ለምን ቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ ግድ የሌላቸው መኖራቸው አይካድም፡፡
ሦስተኞቹ ደግሞ ፣ ‹‹የለም፣ ይህች ቤተ ክርስቲያን የራሷ የኾነ በጣም ብዙ ጠንካራ ነገሮች አሏት፡፡ በዶግማ፣ በቀኖና፣ በትውፊት፣ በቅርስ፣ በባህል ሀብታም ነች፡፡ በዓለም ላይ የጠፉ ቅርሶችን ጠብቃና ተከባክባ የቆየች ናት፡፡ የዓለም የባህል ሙዝየም ናት. . .›› ብለው የሚያምኑ፣ የሚሟገቱላትም ናቸው፡፡
ለምሳሌ፡- ሰንበቴ ይህች ቤተ ክርስቲያን ይዛው የቆየችው የዓለም ባህል ነው፡፡ የዓለም ክርስትና ሲጀመር ሰንበቴ ነበር፡፡ ሲጠፋ ግን ጠፋ፡፡ እርሷ ዘንድ ግን አለ፡፡ ጽዋ በሌላም ቦታ ነበር፤ ግን ጠፋ፡፡ ዛሬ የአውሮፓን ካታኮምብ (ጥንታዊ ከርሰ መቃብሮች) ቁፋሮ ሲካሄድ የሚገኙ ሥዕሎች ሰንበቴ ተሰብስበው ሲበሉ፣ ጽዋ ሲጠጡ የሚታዩባቸው ናቸው፡፡ እነርሱ አሁን የድሮ ክርስቲያኖች እንዲህ ነው የሚበሉት፣ የሚጠጡት ይሉኻል እንጂ ዛሬ ህልውናው የለም፡፡ እኛ ጋራ ግን ከነሕይወቱ ተጠብቆ ታገኘዋለህ፡፡ ሌላ ምሳሌ እንውሰድ፤ መስቀል እኛ ጋራ አልነበረም የተጀመረው፡፡ ሌሎች ጋራ የነበረ ነው፡፡ ግን እኛ ጋራ ነው ሕያው ኾኖ የሚገኘው፡፡ በሌሎች ቦታዎች ታስቦ ነው የሚውለው፡፡ ጥምቀትም ታስቦ ነው የሚውለው፡፡ የግብጽን ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ስታይ፣ እስከ ስምንትና ዘጠነኛው ክፍለ ዘመን ድረስ ጥምቀትም መስቀልም በአደባባይ ይከበር ነበር፡፡ ዛሬ ግን አልኾነም፡፡ ይኸው እኛ ጋራ ግን በህልውናው አለ፡፡ ስለዚህ ነው ይህች ቤተ ክርስቲያን የራሷ ብቻ ሳትኾን የዓለም ባለ አደራ ናት የምንለው፡፡ ከዓለም ከኦሪት ታቦታቱን፣ ከሐዲስ መስቀሉን ጠብቃ በአደራ አስቀምጣ የቆየች አደራ የማትበላ ናት፡፡
‹‹ይህች ቤተ ክርስቲያን አደራዋን እንደጠበቀች፣ ሃይማኖትን እንደ አባቶቻችን፣ አሠራሩን እንደ ዘመናችን አድርጋ መሄድ አለባት›› የሚሉ ወገኖችም ያሏት በመሆኑ ፣ በእነዚህ ወገኖችና የሌላውን ሐሳብ ተጭነው በሚመጡ ሰዎች መሐል ትግል አለ፡፡ ክርክር አለ፡፡ ሰውዬውን በአካል ባላውቃቸውም ሲናገሩ ባላዳምጥም አሉ የተባለውን ሰምቻለሁ ፡፡ ምናልባት ስማቸው የተነሣው አባት የተባለውን ሐሳብ ይዘው መጥተው ሊሆን ይችላል ብዬ አምናለኹ፡፡
የሆነው ሆኖ፣ የሌላውን ሐሳብ ይዘው የሚመጡ ሰዎች ትልቁ ችግራቸው ምንድን ነው? ዘመኑን ከመዋጀት ይልቅ (መጽሐፉ ‹‹ዘመኑን ዋጁ›› ይላልና) ዘመኑን የመጠቀም ስልት መከተላቸው ነው፡፡ የኮሚዩኒስት ሐሳብ ሲራመድ ካዩ፣ ራሳቸውን ኮሚዩኒስት ሌላውን ካፒታሊስት ያደርጋሉ፡፡ የካፒታሊስት ሐሳብ በዘመኑ ሲራመድ ሲያዩ ደግሞ ራሳቸውን ካፒታሊስት ሌላውን ኮሚዩኒስትነት ፈርጀው ማስመታት ይፈልጋሉ፡፡ ይህን መሰል ተግባርም በየዘመኑ ይፈጽማሉ፡፡
ማኅበረ ቅዱሳን ከተመሠረተ ወደ ሃያ ዓመት በላይ ኾኖታል፡፡ ከመጀመሪያው ጀምሮ ይሰጡት የነበረውን ስሞች ብንመለከት የሚያስገርምና የሚያስደንቅ ነው፡፡ መአሕድ በአገሪቱ ትልቅ መነጋገርያ በኾነበት ጊዜ ‹‹መአሕድ ነው›› ተባለ፡፡ አገሪቱ ቅንጅት፣ ቅንጅት በምትሸትበት ጊዜ ደግሞ ‹‹ቅንጅት›› ተባለ፡፡
ዕንቁ፡- ለምንድን ነው እንደዚህ የሚባለው?
ዲ/ን ዳንኤል፡- ምክንያቱ አስቀድሜ ባቀረብኹት ምሳሌ መሠረት በዘመኑ የመጠቀም ፍላጎት ካላቸው ሰዎች ጠባይና ባሕርይ የሚመጣ ነው፡፡ አንተ በሐሳብ ስትሸነፍ ማስመታት መቻል አለብኽ፡፡ በእኛ አገር የተለመደ ሦስት ዐይነት አሠራር አለ፡፡ አንድን ነገር መጀመሪያ ታውቀዋለህ ፡፡ ቀጥለህ ስም ትሰጠዋለኽ፡፡ ሠልሰህ ትመታዋለህ፡፡ ስም ካላወጣህለት አይመታልህም፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን ለምን ነበር ‹‹መአሕድ›› ይባል የነበረው? የሚያደርገው እንቅስቃሴ በመታወቁ ነው፡፡ እንደዚህ የሚወነጅሉትም ሰዎች እኮ ያውቁታል፡፡ ግን ለመምታት የሚያስችላቸውን ስም ማውጣት አለባቸው፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን ግን እስከ አሁን ድረስ አክራሪ ሆኖ ያመጣው ነውጥ፣ ያስነሳው ነገር፣ የደበደበው፣ የገደለው ሰው፣ ያቃጠለው ቤተ እምነት የለም፡፡
ዕንቁ፡- ሰው ሕይወቱን፣ እምነቱን፣ ትምህርቱን፣ የዕውቀትና የኑሮ ምርጫውን በተመለከተ የራሱ ሐሳብና ከሐሳቡም የሚመነጭ ውሳኔ አለው፡፡ የሌላውን መብት እስካልተፃረረ ድረስ በራሱ ለራሱ የመመራት መብት ባለቤት ነው፡፡ ‹‹ለምንድን ነው እኛ ወዳደራጀነው ተቋም፣ ማእከል የማትመጣው›› የሚሉ ‹‹አልመጣም›› ሲል በአክራሪነት ወይም በሌላ የሚፈርጁ ሰዎችና ቡድኖች ደግሞ አሉ፡፡ ይህን ኹኔታ በጠራና የተሻለ ግንዛቤ በመፍጠር ደረጃ ለኅብረተሰቡ ማስተማር የሚቻልበት መንገድ አለ?
ዲ/ን ዳንኤል፡- አስቀድሜ ለማንሣት እንደፈልግኹት፣ ለዘብተኛው አካል መሥዋዕትነት ለመክፈል ወይም ደግሞ አንዳች ሱታፌ ለማድረግ ፍላጎት የለውም፡፡ ያኛው ደግሞ የሌላው ወኪል ነው፡፡ ምክንያቱም ይህች ቤተ ክርስቲያን እኮ በሦስት ደረጃ ማለትም ወይ ለማፍረስ! ወይ ለመጠምዘዝ (ከምትሄድበት አቅጣጫ ወደ ሌላ መሥመር ለመውሰድ) ይህ ካልኾነ ደግሞ ለማደንበሽ ብዙ ጥረት ተደርጓል፡፡ ማደንበሽ ማለት ምንም እንቅስቃሴ እንዳታደርግ፣ ዝም ብላ እንድትኖር ማድረግ ማለት ነው፡፡ ለአንድ ሰው ምግብ፣ ልብስ፣ መጠለያ ተሰጥቶት ግን በአእምሮው ምንም ዕውቀት እንዳይኖረው የማድረግ አይነት ነው፡፡ እንደዚህ አይነቱ ሰው አንድ ሰፈር ውስጥ ቁጭ ብሎ የፈለገውን ፊልም፣ የፈለገውን ሙዚቃ እያየና እያደመጠ፣ በዚህ ብቻ እየተደሰተና እየጨፈረ እንዲኖር ቢደረግ ይህ ኑሮ አይደለም፡፡ ያ ሰው ምንም የሚያስበው፣ የሚሠራው፣ የሚፈጥረው ነገር የለውም፡፡ በቃ ሰፈሩ ብቻ መኖርያው ነው፡፡ የምግብ፣ የልብስ ችግር የለበትም፡፡ እንግዲህ ይሄ ነው መደንበሽ የሚባለው፡፡
በእኒህ በሦስቱ የማጥፊያ ስልቶች ይህች ቤተ ክርስቲያን ተሞክራለች፡፡ ግን የእግዚአብሔር ኃይል፣ የቅዱሳን ጸሎት በውስጧ ስላለ የተመኙላትን ልትኾን አልቻለችም፡፡ በርግጥ የተወሰኑ ሰዎችን መማረክ ይቻል ይኾናል፤ ግን ይህች ቤተ ክርስቲያን ከማናችንም ኃይል በላይ ናት፡፡ ያልታወቀና ማንም የማይደርስበት ኃይል ያላት ነች፡፡ ባትሆን ትጠፋ ነበር፡፡ ግራኝ አንድ ዐሥረኛ ምእመኗ እስኪቀር ጭፍጨፋ አካሂዶባታል፡፡ ብዙዎቹን መቅደሶቿን አቃጥሎባታል፤ ግን አልጠፋችም! ፋሽስት ኢጣልያ ብዙ ነገር አድርጓል፡፡ የፋሽስት ኢጣልያ ወራሪ ጦር እንደገባ ወደ አራዳ ቅ/ጊዮርጊስ በመሄድ የቤተ ክርስቲያኑን ቅጽር በወታደሮች ነው ያስከበበው፡፡ ቀጥሎም የቅ/ጊዮርጊስ ታቦት ‹‹ወታደራዊ ፍርድ ቤት›› በሚለው ችሎት እንዲቀርብ በማድረግና ‹‹ሞት ሊፈረድበት ይገባል!›› የሚል ውሳኔ በማስወሰን ዙሪያውን ተኩስ እንዲከፈትበት አድርጓል፡፡ የተኩሱ አሻራ አሁንም ድረስ በቤተ ክርስቲያኑ ቅጽር ውስጥ አለ፡፡ ግን ይህ ለምን ተደረገ?….. የሚለው ነው ዋናው ጥያቄ፡፡ ታቦቱ አገር በመጠበቁ ካልኾነ ምን ወንጀል ነበረበት? ከአራዳ ጊዮርጊስ አልፈው ደብረ ሊባኖስ በመሄድ መነኮሳቱን የገደሉት ለምንድን ነው? ቅርሷንስ ጭነው የሄዱት? ያኔ ብዙ መነኮሳት ተገድለዋል፡፡ ከሞቱት መሐል እነ አቡነ ጴጥሮስ የዚህች ቤተ ክርስቲያን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ራስ ናቸው፡፡ ግን የሚጠብቃት ኃይል ስላለ ምንም ሊያደርጓት አልተቻላቸውም፡፡
ዕንቁ፡- ይህ ‹‹አክራሪ›› የሚባለው ስያሜ የመነጨው ቤተ ክርስቲያኒቱን ለማፍረስ፣ ለመጠምዘዝ ወይም ለማደንበሽ ከሚፈለገው መንፈስ ነው ማለት ይቻላል?
ዲ/ን ዳንኤል፡- ታድያስ! እርሱ እኮ ነው ‹‹ይህችን ቤተ ክርስቲያን እንጠብቅ›› የሚሉትን የሚፃረረው፡፡
ዕንቁ፡- ‹‹መንፈሱ መኖር አለበት›› በሚሉና ‹‹መንፈሱ መኖር የለበትም›› በሚሉ መካከል ነው ትግሉ ያለው?
ዲ/ን ዳንኤል፡- ነው!. . .ትግሉ እርሱ ነው፡፡ ‹‹ይህች ቤተ ክርስቲያን ተጠብቃ፣ ሥርዐቷን ይዛ ወደሚቀጥለው ትውልድና ዘመን መሻገር አለባት›› የሚሉትን አካላት ነው አሁን ‹‹አክራሪ›› ማለትና ዝም ማሰኘት የሚፈለገው፡፡ እነዚህን ሰዎች ዝም ማሰኘት ግን አይቻልም፡፡ ሃይማኖት የህልውና ጉዳይ ነው፡፡
ዕንቁ፡- ዝም ማሰኘት ካልተቻለ ግቡ ምን ሊኾን ነው?
ዲ/ን ዳንኤል፡- እርሱን በሂደት የምናየው ነው፡፡ የዚህችን ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ማንም በዕቅድ፣ በስትራተጂ፣ በምን ሊተምነው አይችልም፡፡ ታሪኳ የእግዚአብሔር ሥራ ውጤት ነው፡፡ ስለዚህ ‹‹እገሌ ነው እርሷን የሚመራት›› ሊባል አይችልም፡፡ አስተዳደራዊ አመራር ይኖራታል እንጂ መንፈሳዊ አመራሯን ከፈጣሪ የምታገኝ ቤተ ክርስቲያን ናት፡፡ ስለዚህ እኛ የተባሉት ሰው…. ይህን ዓላማ ይዘው መጥተው ተናግረውት ካልኾነ በቀር ማኅበረ ቅዱሳንን አክራሪ ለማሰኘት የሚያበቃ ምንም፣ አንድም መከራከሪያ ሊያመጡ አይችሉም፡፡ ለነገሩ እርሳቸውም ቢሆኑ ማስጠንቀቂያ ሰጡ እንጂ ይሄ፣ ይሄ፣ ይሄ ብለው በዝርዝር ያመጡት ምንም ነገር የለም፡፡ ከሳቸውም በፊት የነበሩት ሌሎች ሰዎች እንደ እርሳቸው ብለዋል፡፡ ማናቸውም ግን ማስረጃ ብለው የሚያቀርቡት ነገር የላቸውም፡፡
በበኩሌ አራት፣ አምስት ነገሮች ሲነገሩ እሰማለኹ፡፡ ‹‹አንዲት አገር አንዲት ጥምቀት››፤ ‹‹አንድ አገር አንድ ሃይማኖት›› ብለዋል የሚል፡፡ ይህን ከብዙኀን መገናኛ እሰማዋለኹ እንጂ ከየትኛውም የቤተ ክርስቲያን መጽሐፍ ላይ ተጠቅሶ አይቼ አላውቅም፡፡እንዴ ‹‹አንድ አገር አንድ ሃይማኖት›› የሚለው እኮ ከራሷ ከቤተ ክርስቲያኒቱ አስተምህሮ ጋራ የሚጋጭ ነው፡፡ በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 1 ቁጥር 8 ላይ የሚለው ‹‹በኢየሩሳሌም፣ በይሁዳ፣ በሰማርያ እስከ ዓለም ዳርቻ አስተምሩ›› ነው፡፡ አንድ አገር ውስጥ ተቀመጡ አላለም፡፡ የሚባለውን የማንቀበለው ከእኛ አስተምህሮ ጋራ ስለሚጋጭ ነው፡፡ ቢቻል ጅቡቲ፣ ሱዳን፣ ኬንያ፣ ሶማልያ፣ ታንዛንያ፣ ጋና፣ ጃማይካ ሄደን አስተምረን ክርስቲያን ማድረግ ነው የሚጠበቅብን፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታይ የኾኑ አሜሪካውያን፣ ጃማይካውያን፣ እንግሊዛውያን፣ ጀርመናውያን አሉ፡፡ እነዚህን ሁሉ እንዴት ወደ አንድ አገር መጥቅለል ይቻላል? ሊሆን አይችልም፡፡ ፈጽሞ ከቤተ ክርስቲያኒቱ አስተምህሮ ጋራ የማይሄድ ነው፡፡
ቤተ ክርስቲያኒቱ በዜግነት ኢትዮጵያውያን ያልኾኑ የእምነት አባቶች ያሏት ነች፡፡ የመጀመሪያው ጳጳስ አቡነ ሰላማ ግሪካዊ ነው፡፡ ዘጠኙ ቅዱሳን የሶርያ፣ የግሪክ፣ የሮም ሰዎች ናቸው፡፡ ወደዚህ ቀረብ ስንል አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ግብጻዊ ናቸው፡፡ የደብረ ሊባኖሱ 11ኛው ዕጨጌ አቡነ ዕንባቆም የመናዊ ነው፡፡ እንዴት ተደርጎ በአንድ አገርና በአንድ ሕዝብ መወሰንና ማስተማር የሚቻለው፡፡ በዚህች ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እኮ ዕድሉ የለም፡፡
ዕንቁ፡- ጽንፈኝነትን ይኹን አክራሪነትን የሚያበረታታ ታሪካዊ መሠረት በአገራችን ታሪክ አለ?
ዲ/ን ዳንኤል፡- ከዚህ ጥያቄ አንጻር ሦስት ነገሮችን ማየት ያለብን ይመስለኛል፡፡ አንደኛ፡- የእምነቶቹ ግንኙነት በመተዋወቅና በመግባባት እንዲኾን የተሠራ ሥራ የለም፡፡ ይሄ ባለመሠራቱ አንዳንድ ወገኖች ሁልጊዜ የተጨቋኝነት ስሜት እንዲሰማቸው የሚያደርጉ ነገሮች ይኖራሉ፡፡ ግን እነዚህን በቀላሉ ማጥፋት የሚቻልበት መንገድ፣ እርስ በርስ የሥነ ምግባር መመሪያ እንዲኖራቸው የማድረጉ ዕድል አለ፡፡
ለምሳሌ አንዱ ስለሌላው ሲናገር መሆን ስለሚኖርበት ኹኔታ ተቀራርቦ በመወያየት አንድ የሚያግባባ ነጥብ ላይ መድረስ ይቻላል፡፡ በመሠረቱ ስለሌላው እምነት ማስተማር ተፈጥሯዊ ነው፡፡ አንተ ‹‹እኔ ትክክል ነኝ›› ስትል ሌላው ‹‹ስሕተት ነው›› ማለት በፍጹም ችግር ያለበት ጉዳይ አይደለም፡፡ አንድ ሙስሊም ‹‹እስልምና ትክክለኛ የመዳን ሃይማኖት ነው›› እስካለ ድረስ ‹‹ክርስትና ስሕተት ነው›› ብሎ ስሕተት ናቸው ብሎ ስለሚያምንባቸው ነገሮች ቢያስተምር ተፈጥሯዊ ነው፡፡ ለምን ይህን አደረግኽ ልንለው አንችልም፡፡ አለበለዚያ ‹‹ክርስትናም እስልምናም ትክክል ነው›› ማለት መቻል አለበት፡፡ አንድ ክርስቲያንም ስለ እስልምና ‹‹ቁርዓን እዚህ ጋራ ተሳስቷል፤ ነቢዩ መሐመድ እዚህ ላይ ተሳስተዋል፤ አካሄዳቸው ስሕተት ነው›› ቢል ለእኔ ተፈጥሯዊ ነው፡፡ ግን እርሱ አይደለም ችግሩ፡፡ ይህን ስታስተምር ምን ዓይነት ሥነ ምግባራዊ መርሕ መከተል አለብህ፤ አንዱ ወደ አንዱ እንዲመጣ ሳይሆን አንዱ በሌላው ላይ የጥላቻ ስሜት እንዳያድርበት ማድረግ የሚቻልበት ዕድል አለ፡፡
በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ መንግሥት የሃይማኖት ተቋማትን የሚያይበት አሠራር መስተካከል አለበት ባይ ነኝ፡፡ በአንድ ሚኒስቴር ሥር የሃይማኖት ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው ያለው፡፡ ፖሊሲ የለውም፡፡ አሁን ተቋቋመ የተባለው ጉባኤ በራሱ ሲታይ ሕዝቡ በሚገባ የተረዳው አይነት አይደለም፡፡ የምንመሠርታቸው ተቋማት ለምን እንደ ሐበሻ መድኃኒት ድብቅ እንደሚኾኑ ይገርመኛል፡፡ ሲኾን እንደዚህ ዐይነቱ ተቋም መቋቋም የሚገባው በላይኛው አካል አልነበረም፡፡ ከታች ከአጥቢያ ጀምሮ አብያተ ክርስቲያንና መስጊዶች ባሉበት አካባቢ የሚገኙ ምእመናን ተሰብስበው ‹‹እንዴት ነው ሁሌ ከምንቧቀስ፣ ከምንጋጭ በጋራ በሚያገናኝን ጉዳይ ላይ የማንነጋገረው? የሚያስማማን ኹኔታ የማንፈጥረው?›› የሚለውን ጥያቄ በማንሣት መወያየት ይኖርባቸዋል፡፡ የምንለያይበት ነገር ቢኖርም የጋራችን በኾነው ጉዳይ መነጋገር፣ የተለያየንበትን በየራሳችን አስቀምጠን ጊዜ የሚፈጅ ቢኾንም የፈጀውን ያህል ጊዜ ፈጅቶ ይሄን፣ ይሄን፣ ይሄን እያልን ወደላይ መድረስ አለብን፡፡
ምንም ነገር ቢሆን ሊሰምር የሚችለው በእኛ በኢትዮጵያውያን ጠባይ ከታች ወደላይ ሲሆን ነው፡፡ እምነት ከታች ወደላይ ነው፡፡ በቤተ ክርስቲያናችን ምእመናን ያለጳጳስ ኖረው ያውቃሉ፡፡ ያለምእመናኑ ግን ጳጳሳቱ ኖረው አያውቁም፡፡ ስለዚህ ወሳኞቹ ምእመናን ናቸው፡፡ ያለ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ብዙ ሙስሊሞች ኖረዋል፡፡ የእስልምና ጉዳዮች ጠ/ም/ቤት የተቋቋመው በዐፄ ኃይለ ሥላሴ ጊዜ ነው፡፡ ከዚያ በፊት ብዙ ሙስሊሞች ነበሩ፡፡ ሙስሊሞች ባልነበሩበት ዘመን የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ኖሮ አያውቅም፡፡ ስለዚህ ወሳኞቹ ሙስሊሞቹ ናቸው፡፡ በዚህም መሠረት የእምነቱ ነገር ከታች ወደላይ እንጂ ከላይ ወደታች ኾኖ አይኾንም፡፡ በቃ አይኾንም! የኢትዮጵያ እምነት ጠባዩ እርሱ አይደለም፡፡ ይህን ጠባይ እኛ እንሻገረው ብንል ብሎኑ ጭራሽ አይገጥምም፡፡ የሚመጣው ስድስት ቁጥር ብሎን ነው፤ ማስገባት የሚፈለገው ግን አራት ቁጥር ብሎን ነው፡፡ ና ግባ፤ ቢባል እሺ አይልም፡፡ ስለዚህ ምን ይደረጋል. . . ልኬቱ መመጠን አለበት፡፡ ቀዳዳውን ላስፋው ሲሉ ግን ግጭቱ ይፈጠራል፡፡
ዕንቁ፡- በኢትዮጵያ ውስጥ ‹‹የሃይማኖት መቻቻል›› አለ ትላለህ?
ዲ/ን ዳንኤል፡- እኔ ከመቻቻል ያለፈ መገንዘብ ነበረ እላለኹ፡፡ ‹‹መቻቻል›› የሚለውን አልቀበለውም፡፡ ለምን? አሁን ባልና ሚስትን ብዙ ጊዜ ስናስታርቅ ‹‹እኔኮ ችዬው ነው የኖርኩት›› ብለው ሲሉ ተስማምቶኝ ነው ማለታቸው አይደለም፡፡ ምን ይደረግ ብዬ፤ ልጅ ለማሳደግ ብዬ፤ ችዬው፣ ተሸክሜው እያሉ ነው የተበደሉት ሚስቶች፡፡ አንደኛው ተሸካሚ ኾኖ እህህ…ብሎ የመቻል ነው፡፡ ጭነት የበዛበት ነው፡፡ የማይፈለግ ነገር ያለበት ነው፡፡ ቻለው ተብለህ የምትኖረው ኑሮ ማለት ነው፡፡ መገንዘብ ማለት ግን አንዱ የሌላውን ችግር፣ ብርታት ተገንዝቦ በዚያ ውስጥ መኖር ማለት ነው፡፡
ዕንቁ፡- ይኼ የምትለው መገናዘብስ አለ?
ዲ/ን ዳንኤል፡- ኢትዮጵያ ውስጥ በብዙ ሕዝብ ዘንድ አለ፡፡ አሁን አለና የለምን በቃላት ደረጃ ስናገረው ተግባራዊ መመዘኛው በኢትዮጵያ ውስጥ ምን ያህል የእስልምና እምነት፣ ምን ያህልስ የክርስትና እምነት ተከታዮች አሉ ብለን ስንጠይቅ በሚልዮኖች የሚቆጠሩ ናቸው፡፡ የእነዚህ ሁለት እምነት ተከታዮች ቁጥር ከኢትዮጵያ ሕዝብ አብላጫው ነው፡፡ በአብዛኛው ማኅበረሰብ ዘንድ ይኸው መገናዘብ አለ፡፡ በርግጥ በጥቂቶች ዘንድ ላይኖር ይችላል፡፡ ለምሳሌ አንድን ሙስሊም ‹‹እንኳን ለመውሊድ በዓል አደረሰኽ›› ስትለው ተገንዝበህዋል ማለት ነው፡፡ በዚያ በዓል ላይ ተስማምተህ ላይኾን ይችላል፡፡ እንደውም ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያ ብዙኀን መገናኛዎች ለሙስሊሞች ‹‹እንኳን ለዒድ አል አረፋ በዓል አደረሳችኹ››፤ ለክርስቲያኖች ‹‹እንኳን ለጥምቀት በዓል አደረሳችኹ›› ሲሉ ይደመጣሉ፡፡ ግን ለምንድን ነው እንዲህ የሚሉት? እኔ በኢትዮጵያዊነቴ የሙስሊም ወገኔን በዓል ገዝቼዋለኹ፡፡ ሙስሊሙም የእኔን በዓል ገዝቶታል፡፡ እርሱም በእኔ እምነት እድናለኹ፤ እኔም በእርሱ እምነት እድናለኹ፤ አላልንም እንጂ በባህላችን አንዳችን የሌላችንን በዓል ገንዘብ አድርገነዋል፡፡
ስለዚህ በብዙኀን መገናኛ በኩል መባል የሚኖርበት ‹‹ለኢትዮጵያውያን በሙሉ እንኳን ለዒድ አል አረፋ፤ እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በዓል አደረሳችኁ›› ነው፡፡ ለምን ሚዲያው ይለየናል? እኛ ያልተያየነውን ለምን የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት የሚለያየን እላለኹ፡፡ ብዙውን ጊዜ እኔ ጓደኛዬን ‹‹እንኳን አደረሰን›› ነው የምለው፡፡ ለምሳሌ እርሱ የመውሊድን በዓል ሲያከብር የሚያገኘው ሃይማኖታዊ በረከት እንዳለ አስቦ ነው፤ ልክ እኔ ጥምቀት በማከብርበት ጊዜ እንደማደርገው፤ ግን እርሱን እንኳን አደረሰኽ ስለው እርሱ በዓሉን ሰላማዊ ኾኖ፣ ነጻ ኾኖ፣ ደስ ብሎት የሚያከበርበትን ከባቢያዊ ኹኔታ መፍጠር ግዴታዬ ነው፡፡
ዕንቁ፡- ‹‹እንኳን አደረሰህ›› እና ‹‹እንኳን አደረሰን!›› በሚለው መሀል ልዩነት አለ እያልኽ ነው?
ዲ/ን ዳንኤል፡- ኢትዮጵያ ውስጥ ስንኾን አዎ፣ ልዩነት አለው፡፡ ለምን? እኔም አስተዋፅኦ አድርጌአለሁ፡፡ ሙስሊሙ ሃይማኖታዊ በዓሉን ደስ ብሎት፣ ነጻ ኾኖ እንዲያከብር፡፡ በዚህም ደስተኛ ነኝ፡፡ እኔም የጥምቀት በዓሌን ደስ ብሎኝ በሰላማዊ ሁኔታ ለማክበሬ የሙስሊሙ አስተዋፅኦ አለበት፡፡ ስለዚህ ኢትዮጵያውያን ‹‹እንኳን ለመውሊድ፣ እንኳን ለብርሃነ ልደቱ አደረሰን፤ አደረሳችሁ›› ማለት ወይም መባባል ነው ያለብን፡፡ የሁላችንም አስተዋፅኦ ያለበት ነገር እኮ ነው፡፡እስኪ ፈጣሪ ያሳይህ. . .ለጥምቀት፣ ለፋሲካ. . .ቀን በግ ይዞ የሚመጣውን ሰው ሙስሊም ይሁን ክርስቲያን በምን ታውቀዋለኽ? ለይተህ የምታውቅበት ልዩ ዘዴ አለህ እንዴ? እርሱ ይዞ ባይመጣ አንተ ከየት ነበር የምታገኘው? ይህ ሰው እኮ ለፋሲካ ይህን ነገር ማድረስ አለብኝ ብሎ ከሠራ ትልቅ ተግባር ነው ያከናወነው፡፡ እና የእነዚህ ወገኖቻችን አስተዋፅኦ በእኛ በዓል አከባበር ላይ አለበት፡፡ ለምን ታድያ የሥራውን ቀን ዝግ እናደርጋለን? የማይገባኝ ነገር እርሱ ነው፡፡ ጥምቀት ዕለት ሙስሊም ወገናችን ለምን ሥራ እንዲገባ አይደረግም? የመውሊድ ዕለትስ እኛ ሥራ እንዳንገባ የሚደረገው ለምንድን ነው? መገናዘቡ የለም ከተባለ፣ አንዱ ለሌላኛው ያበረከተው አስተዋፅኦ የለም አልነበረም የሚባል ከኾነ ሥራው ሲዘጋ በከፊል ነው መዘጋት የሚኖርበት፡፡ የመውሊድ በዓል ሲሆን ሙስሊም የሆናችሁ ወደ ሥራ አትምጡ፤ የስቅለት ዕለት ሲሆን ደግሞ ክርስቲያን የሆናችሁ ወደ ሥራ አትግቡ፤ ሌሎቻችሁ ግን ወደ ሥራ መግባት አለባችሁ መባል ነበረበት፤ በዓሉ የእነርሱና የእኛ ብቻ ከሆነ፤ ግን የሁላችንም ነው፡፡ በሕግ ደረጃ ብሔራዊ በዓል ነው ተብሎ ከተደነገገ በኋላ በሚዲያ በኩል ልዩነቱ ለምን ይመጣል? ይሄ ነው በተግባር መልስ ማግኘት ያለበት፡፡ ኢትዮጵያውያን ከሥር ሆነን ያዳበርነው ከወደላይ ትልቅ ችግር ይፈጠርበታል፡፡ አስቀድሜ እንደተናገርኹት በኢትዮጵያ ውስጥ እምነት ከታች ወደላይ ነው፡፡ ታች ያለው ያለ በላዩ መኖር ይችላል፡፡ በስተላይ ያለው ግን ያለ በታቹ መኖር አይችልም፡፡
ቤተ ክህነት መኖሯን ሳያውቁ የሚኖሩ ብዙ ምእመናን አሉ፡፡ ጋምቤላ፣ ጎጃም፣ አሶሳ ጠረፍ ሄደህ፣ ጎንደር ገጠር ወርደህ ፤ .ፓትርያርኩ ማን ናቸው? ብለኽ ጠይቅ፤ የት ያውቃል! የእስልምና ጉዳዮች ሰብሳቢ ማን ቸው? ብትለው እስኪ የት ያውቅልሃል! እግዚአብሔርን ፣ የአጥቢያውን ታቦት፣ ቃዲውን ነው የሚያውቀው፡፡ ወይም ደግሞ በሰፈሩ ያለውን ዑሏማ ‹‹አሏህ ወ አክበር›› የሚያሰኘውን ሰው ነው የሚያውቀው፡፡ ከእግዚአብሔር ጋራ፣ ከአላህ ጋራ የሚያገናኘው ያ በቅርቡ ያሉት የሃይማኖቱ ተጠሪ ናቸው፡፡ እርሱ ካለለት በቂ ነው፡፡ ከዚያ በላይ ያለው ትርፍ ነው፡፡ እኔ ታች ያሉት ከተግባቡ ኢትዮጵያ ውስጥ ምንም ችግር የለም ባይ ነኝ፤ የሃይማኖት መሠረቶች እነርሱ ናቸውና፡፡ ሌላው ዓለም ስንሄድ ከላይ ወደታች ነው፡፡ ለዚህም ነው ለኢትዮጵያውያን በሃይማኖታቸው ጸንተው መኖር እምነቱ ከታች መኾኑ ዋነኛው መሠረት ነው፡፡
ዕንቁ፡- እምነቱ ከላይ ወደታች ቢኾን ምን ችግር ይገጥመዋል?
ዲ/ን ዳንኤል፡- ግብጽ ስንት ጊዜ ጳጳስ ስታስቀር ምን ይውጠን ነበር? በዚህ ሁሉ ጭቅጭቅ፣ በዚህ ሁሉ ክርክር በንጉሡም በደርግ ዘመንም እንይ፤ አሁንም እንመልከት፡፡ ስለ እምነት ተቋማት የተለያየ አመለካከት ነው የነበረው፤ ያለውም፡፡ በየዘመኑ የሃይማኖት ተቋማት መሪዎች ከመንግሥት ጋራ ናቸው አይደሉም የሚለው ክርክር አለ፡፡ ይህ ክርክር ግን ታች ያለውን ሰው አይነካውም፡፡ ጥፍጣፊው አይደርስበትም፡፡ ለምን? ብለን ስንል ጉዳዩ ከላይ ነው፡፡ እርሱ ከታች አንድ የንስሐ አባት፣ አንድ ቁርዓን የሚያስቀራው ካለ በቂው ነው፡፡ ታቦቱ አጠገቡ ካለ እዚያው ሄዶ ያስቀድሳል፤ ክርስትና ያሥነሳል፤ ሲሞት እዚያው ይቀበራል፡፡ እኔ ኢትዮጵያ ውስጥ አለ የምለው መገናዘብ፣ መግባባት ይህን ነው፡፡
ዕንቁ፡- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ህልውና ለመጠበቅ፣ እሴቶቿን በነበረበት ለማቆየት የሚደረገውን መንፈሳዊ ትግል ወይም ይህን የመሰለውን ተነሣሽነትና መንፈሳዊ አስተምህሮ እንደ አክራሪነት ተግባር የሚመለከቱትን ለመከላከል ምን መደረግ ይኖርበታል?
ዲ/ን ዳንኤል፡- አንደኛ መገንዘብ አለባቸው! በደንብ ስለማውቀው ክርስትና ልናገር፡፡ ክርስትና የሚጠይቅህ አንተ አምነህ ፣ ተጠምቀህ ብቻ እንድትኖር አይደለም፡፡ ይሁዳ በመልእክቱ ቁጥር ሦስት ላይ ‹‹ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለተሰጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ እመክራችኋለኹ›› ነው ያለው፡፡ እንድትጋሉ እንጂ አምናችሁ፣ ተጠምቃችኹ እንድትቀመጡ አላለም፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ለጢሞቴዎስ በላከው መልእክት ላይ ‹‹ሩጫዬን ፈጽሜአለኹ፤ ሃይማኖቴን ጠብቄአለኹ፤ መልካሙን ገድል ተጋድዬአለኹ›› ብሏል፡፡ ስለዚህ ሃይማኖት መጠበቅ አንድ ነገር ነው፡፡ ብዙ ሰው እንደሚለው ግን ይህ ብቻ በቂ አይደለም፡፡ መልካሙን ገድል መጋደል ደግሞ ይኖርብናል፡፡ ያ መልካሙ ገድልም ደግሞ ከሦስት አካላት ጋራ የሚደረግ ነው፡፡ አንደኛ፡- ከራስ ጠባይዕ ጋራ፣ ሁለተኛ፡- ከሰይጣን ጋራ፣ ሦስተኛ፡- ከተለያዩ አካላት ማለትም ሃይማኖትኽን፣ ቤተ ክርስቲያንህን ወይም እምነትህን ለማፍረስ ከተነሡ ወገኖች ጋራ፣ ከመናፍቃን፣ ከከሐድያን፣ ከአላውያንና ከሌሎች አካላት ጋራ የምታደርገው ተጋድሎ ነው፡፡
ለምሳሌ፡- መናፍቃን ከውስጥ የሚወጡ ናቸው፡፡ አላውያን የምንላቸው ኃይልና ሥልጣን ተጠቅመው የሚመጡ ሲኾኑ ፤ ከሐድያን ደግሞ ወጥተው የሚሄዱ ናቸው፡፡ መልካሙ ገድል የሚባለውም ከእኒህ ጋራ የሚደረግ ተጋድሎ ነው፡፡ ይሄ ከሌለ ተጋድሎ አለ ሊባል አይችልም፡፡ ስለሆነም በክርስትና የመጋደል ግዴታ አለ፡፡ ስለዚህ የክርስትና ተጋድሎ በሚሰጠው ግዴታ ውስጥ አንድ ክርስቲያን አንዱን የተጋድሎ ዐይነት መምረጥ ይኖርበታል፡፡ ‹‹ቀኝኽን ለሚመታኽ ግራኽን ስጥ›› የሚል ክርስትናን የምንከተል በመኾናችን እስከ አሁን አባቶቻችን ሞተዋል እንጂ አልገደሉም፡፡
ሃይማኖትን የመጠበቅና የመጋደል ግዴታ በክርስትና አለ፡፡ በዚህ መሠረት የሚጋደሉትን አክራሪ የሚሉ ሰዎች ካሉ ያልተገነዘቡት ነገር አለ፡፡ አክራሪነት ይሄ ከኾነ በክርስትና አክራሪነት የሚጀምረው በቅዱስ ጴጥሮስ ዘመን ከነበሩት ሐዋርያት ነው ማለት ነው፡፡ እነዚያ ሁሉ አክራሪዎች ከኾኑ የምናወራው ስለ ክርስትና ነው ማለት ነው? ስለዚህ ስም በሌላው ላይ ከመለጠፋቸው በፊት ማወቅ፣ መገንዘብ ይኖርባቸዋል፡፡በተለይ ማኅበረ ቅዱሳንን በተመለከተ የሚሰነዘሩ ሐሳቦች ምንጫቸው መታየት አለበት፡፡ ለምንድን ነው ያ ሰው እንደዚያ ያለ ሐሳብ ያቀረበው፤ በምን ፍላጎት ላይ ተመርቶ ነው የሚለው መጤን ይኖርበታል፡፡ ከዚህ በፊት መንግሥት ‹‹ኪራይ ሰብሳቢነት›› የሚል ትልቅ አጀንዳ አንሥቶ በነበረ ጊዜ የሆኑ አካላት ተነሥተው ‹‹ማኅበረ ቅዱሳን ኪራይ ሰብሳቢ ነው›› ብለዋል፡፡ እንደነዚህ ያሉ አካላት ነገ ሌላ ስም ቢመጣ የመጣውን ስም ከማለት አይመለሱም፡፡
ዕንቁ፡- ማኅበረ ቅዱሳን እንደዚህ ዐይነቱን ነገር ለመከላከል ምን ማድረግ አለበት?
ዲ/ን ዳንኤል፡- የተለየ ነገር ማድረግ አለበት ብዬ አላምንም፡፡ እያደረገ ያለውን መቀጠል ነው፤ ምክንያቱም ለሚነሣው ሁሉ መልስ በመስጠት ራስን ከሠራተኛነት ወደ ተዋጊነት መለወጥ አያስፈልግም፤ እውነት ነውና የሚያሸንፈው፡፡ በአገራችን ይትበሃል ‹‹ቂጣም ከኾነ ይጠፋል፤ ሽልም ከኾነ ይገፋል›› እንደሚባለው በተያዘው ሐቅ መቀጠል ነው፡፡ አንድ ሰው እርግዝና መኾኑን ባወቀው ጉዳይ ‹‹አይ ይሄ ቦርጭ ነው›› ላሉት ሰዎች ሁሉን ለማስረዳት በመድከም ጨጓራውን መላጥ የለበትም፡፡ ሲወለድ ይታወቃል፤ ያኔ ይደርሳል፡፡
በበኩሌ አንድ የተባለ ነገር ብቻ አውቃለኹ፡፡ በዓለም ላይ ተከሥቶ ‹‹ማኅበረ ቅዱሳን አላደረገውም›› የተባለውን ነገር፡፡የመስከረም 11 የአሸባሪዎች ተግባር ማኅበረ ቅዱሳን አደረገው አልተባለም፡፡ ከዚህ ውጭ ያሉት ነገሮች ግን ተመልክተውታል፡፡ እናም ክፉ ነገር ሲመጣ መለጠፍ ለሚፈልጉ ሰዎች ሁሉ መልስ መስጠት አይቻልም፡፡ ግን የሚመለከታቸው አካላት ጊዜ ሰጥቶ፣ መዛግብቱን ይዞ ማስረዳት ይኖርበታል፡፡ እንደውም ማኅበሩ አንድ የሚጎድለው ነገር ቢኖር ማስረዳት ነው፡፡ መልስ መስጠት እንጂ ቀድሞ የማስረዳት ነገር ውስጥ ብርቱ አይደለም፡፡ ስለዚህ ቀድሞ ጉዳዮቹን የማስረዳት፣ የመንገር ሓላፊነት አለበት፡፡ የሚያስረዳውም ሰዎች እንዲገባቸው ብቻ አይደለም፡፡ መረዳት፣ አለመረዳት ግን የእነዚያ አካላት ድርሻ ነው፡፡
ዕንቁ፡- በቤተ ክርስቲያኗ ላይ ወንጃይ ጣቶች የሚቀሰሩት ለምንድን ነው?
ዲ/ን ዳንኤል፡- ቤተ ክርስቲያን ከሃይማኖታዊ ዕሴቷ በተጨማሪ ለብዙ ዘመናት ሁለት ለአገሪቱ የሚጠቅሙ ዕሴቶችን ይዛ የኖረች ነች፡፡
አንደኛ፡- የኢትዮጵያዊነት ዕሴት ማለትም አገርን የመውደድ፣ አገርን ከአጥቂዎች የመከላከል፣ የአገር ፍቅር ስሜት በደም ሥር እንዲዘዋወር የሚያደርግ፣ ለአገር የመሞት እሴትን የያዘች ነች፡፡ ይሄ በግልጽ ይታያል፡፡ በተለያየ ዘመን የመጡ የአገሪቱ ጠላቶች መጀመሪያ ማፍረስ የሚፈልጉት ይህችን ቤተ ክርስቲያን ነው፡፡ በተለያዩ ጊዜያትም አገሪቱ በጠላቶቿ ስትወረር ከግንባር ቀድማ የምትደርሰው ይህች ቤተ ክርስቲያን ነች፡፡ ለምን? ሃይማኖታዊ ብቻ ሳይኾን አገራዊ አደራንም የተረከበች ቤተ ክርስቲያን በመኾኗ፡፡
ሁለተኛ፡- የአገር፣ የታሪክ፣ የባህል፣ የእምነት፣ የቅርስ ባለአደራ ናት፡፡ ቤተ ክርስቲያኒቱን ያቃጠለውና ብዙ ምእመን የፈጀው የግራኝ መሐመድ ካባ የሚገኘው በመርጡለ ማርያም ቤተ ክርስቲያን ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን ያንን ካባ ያስቀመጠችው እርሱን በመሳምና በመሳለም በረከት ይገኛል ብላ እንዳልኾነ ይታወቃል፤ ግን የአገር ታሪክ ነው፡፡ የብዙ ነገሥታት፣ የአያሌ መኳንንት፣ የሚወዷትና የሚጠሏት ሰዎች ቅርስ ያለው በቤተ ክርስቲያኗ ነው፡፡ ባለአደራ ስለኾነች፣ እርሷን የሚመለከቱም የማይመለከቱም መጻሕፍት ይገኙባታል፡፡ በጭራሽ ከእርሷ ጋራ የማይሄዱ የእነአርስቶትል፣ የእነሶቅራጥስ የእነፕሌቶ መጽሐፎች ሁሉ አሉ፡፡ ይህችን አገር የማድከም ፍላጎት ያለው፣ በዓለም ላይ አንገቷን ቀና አድርጋና ከፍ ብላ እንድትሄድ የማይፈልግ ማንኛውም ኃይል መጀመሪያ መምታት ያለበት ይህችን ቤተ ክርስቲያን ነው፤ ምክንያቱም አገሪቱን አገር የሚያሰኟት ሁለት ትልልቅ ዕሴቶች ውስጧ ያሉ በመኾኑ፡፡
በብዙ ዓለም አገሮች ዞሬአለሁ፡፡ በኢትዮጵያ የሚደሰቱ አላየሁም፡፡ አንድ ምሳሌ ልጥቀስ፡፡ በእኛው አገር ውስጥ አንድ የውጭ ማኅበረሰብ ት/ቤት አለ፡፡ ይህ ት/ቤት ከውጭ በሚመጣ የትምህርት ቁሳቁስ እየተረዳ የትምህርት ሥርዐቱን የሚያስኬድ ነው፡፡ በታሪክ ማስተማርያ መጽሐፉ ላይ(አንድ ተማሪ አምጥቶ እንዳሳየኝ) ስለ አፍሪካ በሚገልጸው ክፍል ‹‹ኢትዮጵያና ላይቤሪያ ቅኝ አልተገዙም›› ይልና ምክንያቱን ሲያብራራ ‹‹ላይቤሪያ በአሜሪካ የበላይ ጠባቂነት ሥር ስለነበረች ሲኾን ኢትዮጵያ ደግሞ መሬቷ አስቸጋሪ ስለኾነ ነው›› ይላል፡፡ አየኽ! ያን ሁሉ ከዐድዋ የተጀመረ የፀረ ቅኝ አገዛዝ መሥዋዕትነት ድምጥማጡን አጥፍተውታል፡፡
ይህን የሚለው የትልቋ አገር የአሜሪካ የታሪክ ማስተማርያ መጽሐፍ ነው፡፡ እነርሱ ሳያውቁት ቀርተው ነው ማለት ይቻላል፡፡ ኾን ብለው ኢትዮጵያን የማንኳሰስ ዘመቻ ግን በብዙ ቦታ ይታያል፡፡ የቀደመውን ተወው፤ ሰሞኑን የኾነውንና የአንድ ሳምንት ዕድሜ ብቻ ያስቆጠረውን ጉዳይ በምሳሌ ላምጣልኽ፡፡ ኃይሌና ቀነኒሳ ከሞ ፋራኅ ጋራ ያደረጉትን ልዩ ውድድር አስታውሱ፡፡ ቢቢሲ ይህን ውድድር ምን ብሎ ዘገበ…‹‹ሞ ፋራኅ ተሸነፈ›› አለ፡፡ እንዲህ ያለው ቀነኒሳ አሸነፈ ላለማለት ነው፡፡ ይህ ብቻ አይደለም የሚገርመው ራሱ ቢቢሲ ‹‹የኬንያው አትሌት ቀነኒሳ አሸነፈ›› አለ፡፡ ይህ ትልቅና ዓለም አቀፍ ተሰሚነት ያለው የዜና ማሰራጫ ተቋም እንዴት ነው ቀነኒሳን ኬንያዊ የሚያደርገው? ‹‹ኢትዮጵያዊ›› የሚለው መጠሪያ፣ መለያ እንዴት ሊጠፋው ቻለ? ከዚህ ጀምሮ ስታይ ይህችን አገር ኾን ብሎ የማዳከም ነገር እንዳለ በብዙ መንገዶች እንዳለ ትገነዘባለኽ፡፡
እኔ ከፍተኛ ድጋፍ የምሰጠው ‹‹ይህችን አገር በምንም በምንም ብለን በኢኮኖሚውም ይኹን በሌላው ራሷን የቻለች አገር ማድረግ አለብን›› የሚለውን የዚህን መንግሥት አቋም ነው፡፡ ከሕዳሴው ግድብ ጀምሮ ያለውን ነገር ሁሉ የማንንም ድጋፍ ሳንጠይቅ መሥራት አለብን የሚለው ይስማማኛል፡፡ ለምን? ማንም በጎአችንን አይፈልግም፡፡ የትም ስለኢትዮጵያ ተብሎ የሚሰጠውን ትምህርት እንመልከት፤ በሁለት የአውሮፓ አገሮች የታሪክ ማስተማርያ መጻሕፍት አይቻለኹ፡፡ ስለአፍሪካ የሚገልጸው ንኡስ ክፍል ‹‹ግብጽ›› ይልና ‹‹መርዌ›› ይመጣል፡፡ በጭራሽ ስለ አክሱም ማውራት አይፈልግም፡፡ ለምን? ምን አደረገች? የኾነ ነው፡፡ የሐቅ ጥያቄ ነው፡፡ የምርጫ ጥያቄ አይደለም፡፡
ዕንቁ፡- እንደ ጀርመን የግዕዝን ቋንቋ በትምህርት ሥርዐታቸው ውስጥ ያስገቡትስ አገሮች?
ዲ/ን ዳንኤል፡- እርሱ በጣም ጥቂት በኾኑ በጎ አድራጊዎች የኾነ ነው፡፡ እንደዚያም ቢኾን ያ የተደረገበት የራሱ ምክንያት አለው፡፡ ለእኛ ተብሎ የተደረገ አይደለም፡፡ ከዚህ የሚሄድና የሄደ ስንት ጥበብ አለ፤ ነበር፡፡ ግእዙ የሄደውና የሚሄደው ጥበብን የመፍቻ ቁልፍ ስለኾነ ነው፡፡ እንደ ‹‹ባየር›› ያሉ የመድኃኒት ፋብሪካዎች ከየት ተነሥተው የመድኃኒት ማምረቱን ሥራ አሐዱ እንዳሉት፣ ምንን ወስደው አስተርጉመው እንደጀመሩት ይታወቃል፡፡ ያ ለራስ ጥቅም ሲባል የተደረገ ነው፡፡ የዚህችን አገር የዕድገትና የብልጽና ከፍታ የሚያመጣ አይደለም፡፡ የኢትዮጵያን ከፍታ የሚያመጣ ነገር ሲሞከር ግን፣ አገራችን ስትመታ ነው የሚታየው፡፡ ኢትዮጵያ በኢጣልያ ስትወረር ማን አብሯት ነበር? በወቅቱ የነበረው እውነት ጠፍቷቸው ነው? አይደለም፡፡ እና ይህችን ቤተ ክርስቲያን ከዚህች አገር ጋራ የማየት ጉዳይ ስላለ ምንጊዜም ቢኾን ሰበብ ፈጥረው መምታት ይፈልጋሉ፡፡ ይህ ደግሞ በውጭዎቹ ብቻ የሚፈጸም አይደለም፤ ወኪሎችም አሏቸው፡፡ ትግሉ ከሁለቱ ጋራ ነው የሚኾነው፡፡ ዓላማቸው መበተን ሳይኾን ይህችን ቤተ ክርስቲያን ማጥፋት ነው፡፡ ይህን ካልቻሉ ማደንበሽ!
ዕንቁ፡- በኢትዮጵያ ያለው የፖሊቲካ ነው የሃይማኖት አክራሪነት?
ዲ/ን ዳንኤል፡- እኔ የሁለቱም አለ ብዬ አምናለሁ፡፡ የእምነት አለ፡፡ የፖሊቲካ እንኳ ባንል የአስተሳሰብ አክራሪነት ይኖራል፡፡ በእኛ አገር የተለመደው የፓርቲ ፖሊቲካ ነው፡፡ አንዱም ትልቅ ችግር እርሱ ነው፡፡ ይህ ስላለ ‹‹እገሌ እንደዚህ ነው›› ሲባል ‹‹እገሌ መአሕድ ነው››፣ ‹‹እገሌ እንደዚህ ብሏል›› ሲባል ‹‹ኢሕአዴግ ነው፤ ቅንጅት ነው›› ይባላል፡፡ ለስላሳ ወይም ቢራ ይመስል የኾነ ሣጥን ውስጥ ካልገባኽ ብቻኽን አስተሳሰብኽን ሊመዝነው ወይም ሊያደምጠው አይፈልግም፡፡
በነገራችን ላይ እንዲህ ዐይነቱ ጠባይዕ ከባህላችንም የመጣ ነው፡፡ በገበያው ላይ ያታያል፡፡ የኾነ ነገር ለመግዛት ስትጠይቅ ‹‹በደርዘን ካልኾነ፣ ከነሣጥኑ ካልወሰድኽ፤ የጠርሙስ ማስያዣ ካላመጣኽ ወይም ይህን ያህል ክፈል›› ይልኻል፡፡ ነጥሎ ማየት አይወደድም፡፡ ጠቅልሎ የማየት በሽታ አለብን፡፡ ስለዚህ ከመኖር የመጣ የአክራሪነት አመለካከት አለ፡፡ አክራሪ ሰዎችም አሉ፡፡ ከጠቅላላው ማኅበረሰብ አንጻር ሲታዩ ግን ኢምንት ናቸው፡፡ ኾኖም አንዳንዴ የማኅበረሰቡን ሐሳብ የማግኘት ዕድል ያላቸው ሲኾኑ፣ ይህንንም ዕድል የምናመቻችላቸው እኛው ነን፡፡ ሰዎቹ አቅም ኖሯቸው አይደለም፡፡ በማንኛውም ሰዓት በአቅራቢያው ጉንፋን አማጭ ቫይረስ ሊኖር ይችላል…ያ ሰው ሲደክም፣ በጉዞ ወይም በከባድ የሥራ ጫና ሊኾን ይችላል በዚያን ጊዜ እርሱ በሽታ ኾኖ ይመጣል፡፡ የሰውዬው መድከም ነው ለበሽታው መከሠት አስተዋፅኦ ያደረገው፡፡ ሰውዬው ጠንካራ ከኾነ ግን በአካባቢው የፈለገው ነገር ቢኖር ምንም ሊያደርገው አይችልም፡፡ የአክራሪነትን ጉዳይ የማየው እንደዚህ ነው፡፡
በነገራችን ላይ ኢትዮጵያ ውስጥ ጠንካራ አመኔታ ያለው የዕምነት ተቋም የለም፤ ጠንካራ እምነቶች ግን አሉ፡፡ ጠንካራ የእምነት ተቋምና አስተዳደራዊ ኹኔታዎች የሉም፤ አንዱ ትልቁ ችግር ይህ ነው፡፡ ተአማኒነት ያለው ተቋም አለመኖር፡፡ ቤተ ክህነቱንም የእስልምና ጉዳዮችንም ፕሮቴስታንቱንም በምሳሌነት ብንወስድ ምእመናኑ በፍርሃት በጥርጣሬ የሚያዩት እንጂ የሚወዱት የሃይማኖት ተቋም የለም፡፡ ከምእመናኑ ጋራ በጣም ተቀራርቦ የሚሠራ የሃይማኖት ተቋም አይታይም፤ ምክንያቱም በዚህች አገር ላይ ብዙዎቹ ምእመናን ናቸው፡፡ ጳጳሳቱ ኀምሳ ያህል ናቸው፡፡ ካህናቱ ተሰፍረው ወይም ተቆጥረው የሚደረስባቸው ናቸው፡፡ ሕዝቡ ግን ብዙ ነው፡፡ ከላይ እስከ ታች በሚገባ፣ በታማኝነት፣ ከሙስና፣ ከዘረኝነት፣ ከፖሊቲካ አቋም የጸዳና ግልጽና ተጠያቂነት ያለው ጠንካራ የሃይማኖት ተቋም ቢኖር ኖሮ አሁን አሉ የምንላቸውን የአክራሪነት ዝንባሌዎች በጣም እንቀንሳቸው ነበር፡፡ ይህ ባለመኖሩ ከሃይማኖት ተቋሙ የሚነሣውን የአስተዳደር ችግር በሙሉ ሰውን የመገፋት፣ የመጨቆንና አደጋ ውስጥ የመግባት ስሜት እንዲያድርበት አድርጎታል፡፡ ይህ ለእነማን ዕድል ይሰጣል? የአክራሪነት ስሜት ላላቸው አካሎች ነው፡፡ ስለዚህ ትልቁ ነገር፣ የእምነት ተቋማት ተጠያቂነት፣ ግልጽነት ባለበት ኹኔታ በየራሳቸው ሃይማኖት ሥርዐት መሠረት የሚኾንና በሌላ የማይቀየር፣ የእምነቱን ታሪክ መነሻ ያደረገ፣ ግን ለማንኛውም ሰው ግልጽ የኾነ ራሳቸውን በራሳቸው ማረምና ማስተካከል የሚያስችላቸውን አሠራር መዘርጋት ይኖርባቸዋል፡፡ ዛሬ ስለእምነት ተቋማት ጉዳይ ተነሥቶ ጨዋታ ሲጀመር ምእመናኑ ፤ ስለሙስና፣ ስለገንዘብ፣ እገሌ በዘመድ ተሾመ፣ እገሌ ገንዘብ ተቀበለ፣ እገሌ የእነ እገሌ ወገን ነው የሚለውን ነው አብዝተው የሚናገሩት፡፡ እና ነገሩ ይጽዳ፤ ይወገድ ከተባለ ከዚህ ነው መጀመር የሚኖርበት፡፡

Tuesday, September 24, 2013

ከለውጡ በኋላስ? (ተመስገን ደሳለኝ)


My moments behind the walls of Kaliti prison – Part Four (Temesgen Desalegn)
ኢህአዴግ ወደ መጨረሻው ምዕራፍ (በውስጥም በውጪም ተግዳሮቶች) መገፋቱን በሚያመላክቱ የፖለቲካ አጀንዳዎች ላይ የሚያጠነጥን አንድ ፅሁፍ (‹የአብዮቱ የምፅዓት ቀን ምልክቶች›› በሚል ርዕስ) አቅርቤ እንደነበር ይታወሳል፤ ይዘቱም በመጪዎቹ ወራት ወይም ዓመት ስርዓቱ ‹ምርጫ› አሊያም ‹ህዝባዊ›  እምቢተኝነት ከሚያመጣው ‹ማዕበል› (እንደበረከት ስምዖን አገላለፅ ‹ናዳን በሚገታ ሩጫ›) የማምለጥ ዕድሉ የጠበበ መሆኑን የሚያመላክት ነው፤ ይሁንና አንድ አብዮት ታላቅ (ውጤታማ) ሊባል የሚችለው አምባገነን
ስርዓትን በመቀየሩ ብቻ ስላልሆነ (ሥር-ነቀል ለውጥ የሚፈጥር አብዮት ዋጋ የሚኖረው የዲሞክራሲ ተቋማትን መሰረት መጣል ሲችል ነውና) በቀጣይ መፃኢ ዕድሉ ላይ መነጋገሩ አስፈላጊ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡
በዚህ ፅሁፍህ ተጠየቅም ‹ከስርዓቱ ለውጥ በኋላ፣ ማን ነው አማራጩ?› የሚለው ጥያቄ ትኩረት ይደረግበት ዘንድ አመላክታለሁ፡፡ ምክንያቱም በጠለፉ መንገድ ከቀሩ አብዮቶች ታሪክ ተምረን፣ ‹መጥነን ካልደቆስን› የሚከፈለውን ዋጋ በብላሽ የሚያስቀር አሳዛኝ ሁናቴ ሊፈጠር ይችላልና (ቭላድሚር ኤሊች ሌኒን ‹‹አብዮት፣ ለአብዮት ብቻ ሲባል መካሄድ የለበትም›› እንዲል፣ ከኢህአዴግ መገላገሉ መልካም ቢሆንም፣ የአገላጋዩን ማቀፊያ ከወዲሁ መምረጡ ወይም የምንጠይቀውን ማወቁ ብልህነት ነው)
አማራጩ ተወልዷልን?
ከኢህአዴግ በኋላ የሚተካው አማራጭ ተዘጋጅቷል? …ይህንን ቀዳዳ አስቀድሞ መድፈኑን አስቸኳይ ያደረገው፣ ለውጡ የሚመጣበት መንገድ ‹ከህዝባዊ እምቢተኝነት› ይሆናል የሚለው ቅደመ-ግምት ነው፡፡ ከታዓማኒና በዕኩል አሳታፊ ምርጫ የሚነሳ ሽግግር (‹ሕዝብ የሚፈልገውን ያውቃልና ውሳኔው መከበር አለበት› ከሚለው የዲሞክራሲ ፅንሰ-ሃሳብ በመነሳት) አሳሳቢነቱ ከአደባባይ ተቃውሞ የሚመነጨውን ያህል አይደለም፤ ስለዚህም ከስጋት ነፃ መሆን የሚቻለው በሰላማዊ መንገድ ለመታገል መሰረታቸውን ሀገር ቤት አድርገው በህግ የተመዘገቡ የፖለቲካ ድርጅቶች የቤት ስራቸውን ሰርተው ዝግጁ ሆነው ሲጠብቁ ብቻ ነው፡፡ ይህ ግን የድርጅቶቹን ቁጥር ከሰማኒያ በላይ ከማሻቀብ ያለፈ አስተዋፅኦ የሌላቸውን አሰስ-ገሰስ ‹ፓርቲ›ዎች በሙሉ እንደሚመለከት ተደርጎ መወሰድ የለበትም፡፡ ነፍስ ይማርና በ‹‹ልዕልና ጋዜጣ›› እልፍ አእላፍ ችግሮቹን ማረም ከቻለ መድረክ ተስፋ ሊጣልበት ይችላል ብዬ እንደማስብ መፃፌን አስታውሳለሁ፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ የመድረክ አሰላለፍ ሊቀየር በማጋደሉ (ከአንድነት ጋ አብሮ መቀጠሉ ማጠራጠሩ) እና ሰማያዊ ፓርቲ አዎንታዊ እንቅስቃሴ ከማድረጉ አኳያ ተፎካካሪ ሊሆን የሚችልበት ዕድል በመፍጠሩ፣ በአጀንዳው ላይ ማካትቱን ተገቢ ሆኖ አግኝቸዋለሁ፡፡ ይሁንና ሌሎች ፓርቲዎችን እዚህ ጋ ያላነሳሁበት፣ ከላይ ከጠቀስኩት በተጨማሪ ሶስት ምክንያቶች አሉኝ፤ ቅቡልነትን ማጣት፣ እንቅስቃሴ አልባ መሆን እና በገዥው ፓርቲ ስፖንሰርነት መተንፈስ የሚሉ፡፡
መድረክ
የስድስት ፓርቲዎች ስብስብ ነው፤ በምርጫ ሁለት ሺህ ሁለት (ምንም እንኳ ከአንድ የምክር ቤት ወንበር በላይ ባይሳካለትም) ከሁሉም ተቀናቃኞች በላይ ጐልቶ መውጣት ችሎ እንደነበር ይታወሳል፡፡ የአምስተኛውን ዙር ሀገር አቀፍ ምርጫም ተስፋ አድርጎ ለመጠበቁ ማሳያዎቹ፡- አንድም ስብስቡ ዛሬም ህላዊ መሆኑ፣ ሁለትም ለበርካታ አባላቱና ደጋፊዎቹ ወደ ‹ግንባር ተሻጋገሩ› ግፊት ምላሽ መስጠት መቻሉ ነው፡፡
በምስረታው ዋዜማና ማግስት ብዙ የተነገረለት መድረክ እርስ በእርሱ (በአንድ ጠርዝ-የአንድነት አመራሮች፤ በሌላኛው-ኦፌኮ እና ኢሶዴፓ) የፈጠረው ውዝግብ በዙሪያው ለተሰለፉ አባላትና ደጋፊዎች ተስፋ አስቆራጭ ነው፡፡ ለግንባሩ ቅርብ የሆነ ወዳጄ የችግሩን መጦዝ የገለፀው ‹‹ሁለቱ ጎራዎች በስብሰባ ወቅት ‹በውሃ ቀጠነ› ለፀብ ሲገባበዙ የሚያይ እና ለስድብ የሚጠቀሙባቸውን ቃላት የሚሰማ በአንድ ግንባር የተሰለፉ ናቸው ብሎ ከሚያምን ‹ግመል በመርፌ ቀዳዳ መሽሎኩን› ቢቀበል ይቀለዋል›› በሚል ምፀት ነው፡፡ አደጋውን የከፋ የሚያደርገው ደግሞ ኩነቶቹ ከመለዘብ ይልቅ መባባሳቸው ይመስለኛል፡፡
በመሬት ያለው እውነታ ይህ ቢሆንም፣ ፓርቲው በ2005 ዓ.ም ወርሃ መጋቢት ወደ ‹ግንባር› መሻገሩን ከማብሰሩም በላይ፣ ‹‹የኢትዮጵያን ወቅታዊና መሰረታዊ ችግሮች የመፍቻ አጋጣሚዎች›› በሚል ርዕስ ይፋ ባደረገው ባለአራት ገፅ ‹ማኔፌስቶ›፣ የሀገሪቱን ችግር በሙሉ በአራት ክፍል ቀንብቦ ካስቀመጠ በኋላ፣ ጉዳዩን ፈረንጅኛው ‹የሲኒ ማዕበል› እንደሚለው አድርጎ በማለፍ የ‹ደግፉኝ› ጥሪውን እንዲህ ሲል አስተላልፏል፡-
‹‹ይህንን ፀረ-ህዝብና ፀረ-ሀገር የሆነውን ኢህአዴጋዊ ስርዓት በሰላማዊ አግባብ በምታደርገው ብርቱ ትግልህ መለወጥ እንደምትችል ካለፈው የትግል ተሞክሮህ ሆነ የአለም ህዝቦች ለነፃነት፣ ለዕኩልነትና ለፍትህ ብሎም ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት እውን መሆን ከሚያደርጓቸው እንቅስቃሴዎችና ከሚያስመዘግቧቸውም ድሎች ትገነዘባለህ፡፡ ስለሆነም መድረክ ይህንን ክቡር ትግልህን በመምራት ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝለስልጣን ባለቤትነት እንድትበቃ በፅናትህ ከጎንህ ሆኖ ለመታገለ መወሰኑን ተገንዝበህ ከምንጊዜም በላይ ሁለንተናዊ ድጋፍህን እንድትሰጥ ጥሪያችንን በከፍተኛ አክብሮትና በአንተም ላይ ባለን ሙሉ እምነት እናስተላልፋለን፡፡››
በግሌ መድረክ ራሱ በሁለት ምክንያቶች እምነት ሊጣልበት የሚችል አልመስለኝም፡፡ የመጀመሪያው ከአንድነት ጋር የገባበት ድምፅ የለሽ ውዝግብ ከዕለት ወደ እለት እያደገ መሄዱ ነው፤ አዲሱ የዶክተር መረራ ጉዲና መጽሐፍም ቅራኔውን ቢያሳፋው አይገርምም፤ ዶ/ሩ ስለ2002ቱ ምርጫ ባወሳበት ምዕራፍ ‹‹የ1997ቱ የቅንጅት ወራሽ ነው ብለን የተማመንበት አንድነት እውነተኛ ወራሽ ለመሆን በጣም ብዙ እንደሚቀረው ተረዳው›› ያለበት ግምገማ እና ‹‹ያልገባኝና የሚከነክነኝ አንድነት ኦሮሚያ ላይ በብዛት ያወዳደራቸው ኦህዴድ ያሰማራቸው ወሮበሎች ነበሩ›› ፍረጃው ‹ትችት›ን በቅንነት ለመቀበል ልምድ ከሌለው የሀገሪቱ ፖለቲካ አንጻር አቧራ ማስነሳቱ አይቀሬ ለመሆኑ መገመቱ አይከብድም፡፡ ይህ እንግዲህ አንድነትን የአማራ (የከተማ ልሂቃን) ተወካይ የሚያደረገውን ወቀሳ ሳይጨመር ነው (እዚህ ጋ የሚነሳው አስቂኙ ጉዳይ ወቀሳውን የሚሰነዝሩት አባል ፓርቲዎች አንድነት የብሔር ድርጅት ቢሆን ይበልጥ ተጠቃሚ ከመሆናቸው በተጨማሪ ለአብዛኛው ችግሮቻቸው በቀላሉ መፍትሄ የመስጠቱ ጉዳይ ሲታሰብ ነው)
ሁለተኛው መድረኩ ከለውጡ በኋላ ሀገር ለመምራት የሚያስችል የጠራ የፖለቲካ አመለካከት አለመከተሉ ነው፤ በውስጡ ያሉ ፓርቲዎች ቢያንስ ሁለት የተለያዩ ፕሮግራም የሚያራምዱ መሆናቸው ይታወቃል፡፡ የአንድነትን እና የኦፌኮን ፕሮግራም ብንወስድ የችግሩን ግዝፈት ያሳየናል፤ አንድነት መልካ ምድር ላይ ስለተመሰረተ ፌደራሊዝም አስተዳደር ጠቀሜታ ሲያብራራ፤ የኦፌኮ ባለስድስት ገፅ ፕሮግራም ደግሞ በማንነት ላይ ስለተመሰረተ ፌደራሊዝም ይሰብካል፡፡ በግልባጩ ውድሀት ይፈፅሙ እንዳይባል ደግሞ የእነ ዶ/ር መረራ ‹ከተዋህድን ኦሮሞ ተውጦ ይጠፋል› ስጋት ጋሬጣ ነው፡፡ አንዳንድ የአመራር አባላቱ ‹‹ዓላማችን ቅድሚያ ዴሞክራሲያዊ ተቋማትን መገንባት ነው›› የሚል መከራከሪያ ሲያቀርቡ ቢደመጡም፣ ከዚህ በኩል ከሚነሳው ተግዳሮት በቀላሉ የሚመለጥ አይመስለኝም (በነገራችን ላይ መድረኩ በወቅታዊው ቁመና ‹ግንባር› ለመመስረት የሚያስችለውን መስፈርት ሟሟላቱ ራሱ አጠራጣሪ ነው)
አንድነት
የአንድነት ተግዳሮት ወደ መድረክ ከመግባት ጋ ተያይዞ የመጣ ነው (ከጠዋቱ ሰማያዊ ፓርቲን የመሰረቱት ወጣቶች ከድርጅቱ ለመውጣት አንዱ ምክንያታቸው ይህ እንደሆነ ይታወሳል)፤ ትብብሩን ‹ያልተባረከ ጋብቻ› የሚያስብለው ደግሞ የዛሬ አራት ዓመት ‹ወደ መድረክ ካልገባን ትግሉን እናደናቅፋለን› ሲሉ የነበሩ አንዳንድ የአንድነት አመራሮች የውዝግቡ ተሳፊ መሆናቸውን ስንመለከት ነው፤ መተነኳኮሱ በ2002ቱ ምርጫ ማግስት የተጀመረ ቢሆንም፣ ባለፈው ዓመት ወደ መጦዝ ተሸጋግሯል፡፡ በተለይም አንድነት ‹‹የሚሊዮኖች ድምፅ ንቅናቄ›› በሚል መርህ ያካሄደው የሶስት ወር ዘመቻ መድረክን አለማካተቱ የሚያስተላልፈው መልዕክት ግልፅ ነው፡፡ በ‹‹ፀረ- ሽብር›› አዋጁ ላይ (ኢህአዴግንና ኢዴፓን ጨምሮ) በተደረገው ክርክርም አንድነት እና መድረክ በተለያዩ ሰዎች ተወክለው መቅረባቸው ግንኙነቱን እንደ ቀድሞ ለማየት አስቸጋሪ አድርጎታል፡፡
ይህም ሆኖ አንድነት በራሱ የተሻለ ፓርቲ ሆኖ ሊወጣ የሚችልበት ዕድል አለው፡፡ ምሁራዊ ስብስቡም ሆነ የኢኮኖሚ አቅሙ (የዲያስፖራ ድጋፉ) አንፃራዊ ጥንካሬ እንዲያገኝ ረድቶታል፤ ርዕዮተ-ዓለሙንም ከተቀናቃኝ ፓርቲዎች በጠበቀ መልኩ ማዘጋጀቱ ለቅቡልነቱ አስተዋፅኦ ሊያደርግለት ይችላል፤ ከመኢአድ ጋር የጀመረውን ውህደት (‹የአማራ ተወካይ› የሚለውን ፍረጃ ቢያጠናክረውም)  ከዳር ካደረሰ ደግሞ ከአቻዎቹ ጋ ያለው ልዩነት በእጅጉ መስፋቱ አይቀሬ ነው (መኢአድ የፈራረሰው ከአናት ነውና ግዙፍ መዋቅሩ ‹እረኛ አልባ› በመሆኑ፣ አንድነት በውህደት ስም ቢሰበስበው በከፍተኛ ደረጃ ይጠቅመዋል)
የወል-መንገድ
በቀጣይ የተሻለ አማራጭ ሆኖ ለመገኘት መድረክና አንድነት መቻቻላቸው ወሳኝ ነው፡፡ ይሁንና ኩነቱን በታዛቢነት መመልከት የመረጡት የአረና ሰዎቸ በግንባሩ ቢሮ ሰላም ለማውረድ የአስታራቂነት ሚና ቢጫወቱ ጠቃሚነቱ ለእነርሱም ነው፡፡ አንድነቶችም፣ በመድረክ ስም እዚህ ድረስ ለመጓዝ የከፈሉት ዋጋ ብላሽ ከሆነ ማንንም አያተርፍም፡፡ በአናቱም ወቅታዊው የኢትዮጵያ ፖለቲካ አስገዳጅ መሆኑ መረሳት የለበትም፡፡ ምክንያቱም አንድነት የሰበሰባቸው ልሂቃኖችም ሆኑ በሀገሪቱ የተለያዩ ከተሞች ያነበረው መዋቅር (ጥንካሬው ላይ ያለኝ ጥርጣሬ እንደተጠበቀ ሆኖ) ቅድሚያ ለብሔር ፖለቲካ ከሚሰጡ አካባቢዎች በ‹መድረክ ባርኔጣ› በሚገኝ ድጋፍ (ድምፅ)  ካልታገዘ በቀር አየር ላይ ተንጠልጥሎ ከመቅረት አይታደገውም፡፡
የመድረክ ተግዳሮትም ተመሳሳይ ነው፤ በፖለቲካው ላይ ውጤት የሚያዛባ ተፅዕኖ ማሳረፍ የሚቻላቸውንና አንድነት የራሱ ያደረጋቸውን ከተሜዎች ‹ቡራኬ› ሳይቀበል ወደ ውድድር መግባቱ ‹ውሃ በወንፊት…› አይነት ሊሆንበት ይችላል፡፡ የመድረክንና የአንድነትን የወል ቀዳዳ መዘርዘሩን እዚሁ ገትቼ፣ የተሻለ ጥንካሬና የመግባባት መንፈስ ለማስረፅ በቅድሚያ የችግሮቻቸውን መንስኤ ለይተው ማወቅ አለባቸው ብዬ ስለማስብ፣ በግሌ ‹ያለመግባባቱ መነሻ› ከምላቸው ዋና ጉዳዮች ሶስቱን በአዲስ መስመር እጠቅሳለሁ፡፡
የፕሮግራም መጋጨት ያመጣው ጣጣ አንዱ ነው፤ ይኸውም የፀቡ የቡድን አባቶች የ‹ሕብረ ብሔር› እና የ‹ክልል› ፖለቲካ አቀንቃኝነት፣ ሁሉም አባል ፓርቲዎች መድረኩን ሲፈጥሩ የየራሳቸውን ፕሮግራም እንደያዙ መሆኑ፣ ጥቂት የማይባሉ ልዩነታቸውን ሳይፈቱ ‹በይደር› ማስቀመጣቸው… እንደ ማሳያ ይጠቀሳሉ፡፡ ይህ ሁኔታም የእርስ በእርስ መተማማን እንዳይኖራቸው ያደረገ ይመስለኛል (ከዚህ አኳያም ለመፍትሄው ቅድሚያ ከልሰጡ በመድረክ በኩል ‹መጪው ጊዜ ብሩህ ይሆናል› ብሎ መጠበቅ ‹የዋህ› ሊያስብል ይችላል) የጫናው ተፅእኖ ደግሞ በሁለቱም በኩል (በአንድነትና በብሄር ድርጅቶቹ) ከሚከተሉት የፖለቲካ አመለካከት አንፃር ወደ ስልጣን የመምጣቱ አጋጣሚ ቢፈጠር፣ የታገሉለትን ስርዓት ማንበሩ ፍፁም አዳጋች መሆኑን በማስታወስ ነው፤ አንድነቶች ፓርቲያቸው ከመድረክ እንዲወጣ ይጎተጉታሉ፤ ብሔር ተኮሮቹ ደግሞ ‹አንድነት የነፍጠኛውን ስርዓት የሚመለስ በመሆኑ፣ ወይ ወደ ብሄር ድርጅት ራሱን ይቀየር፣ አሊያም ፕሮግራሙን ይከልስ› የሚለው ሙግታቸው በአሳማኝ ሁኔታ መፍትሄ አለማግኘቱ ራሱን የቻለ ሌላ ትግል ከሚፈልግ አጀንዳ ጋ አላትሟቸዋል፡፡
አንድነት በሚያራምደው የሊብራል ዲሞክራሲ እና አብዛኛው የመድረክ አባል ድርጅቶች በሚከተሉት የሶሻል ዲሞክራሲ መካከል ያለውን ልዩነት የማሰታረቅ ስራ አለመሰራቱ ነው፡፡ ‹‹የአንድነት ፓርቲ ስትራቴጂና የአምስት ዓመት ዕቅድ›› በሚል ርዕስ 246 ገፅ ይዞ በታተመው መፅሀፍ ላይ ‹‹አንድነት የሚመሰረትበት ርዕዮተ-ዓለም ሊበራሊዝም ሆኖ በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፖሊሲዎች የሶሻል ዲሞክራሲን ጠቃሚ ገፅታዎች ይወስዳል›› የሚለው አንቀፅ ቢጤን ለመልካም ግንኙነት መደላድል መሆን ይችላል (በነገራችን ላይ ‹እንዲህ የችግር ቋት ተሸክመው ስለምን በጋራ ለመስራት ተስማሙ?› የሚል ጥያቄ መነሳቱ አይቀርምና ግምቴን ላስቀምጥ፤ የብሔር ድርጅቶቹን እስትንፋስ የሚቆጣጠሩት ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ እና ዶ/ር መረራ ጉዲና ምርጫ 97ን ከሁለት አቅጣጫ ገምግመው ከደረሱበት ድምዳሜ ጋ የሚያያዝ ይመስለኛል፤ ይኸውም ‹አንድነት፣ የቅንጅት ወራሽ ነው› የሚለው የተሳሳተው ትንተና አንዱ ሲሆን፣ ሁለተኛው በዛው ምርጫ ተቀማጭነታቸው አውሮፓና አሜሪካ ከሆኑ አስራ ሁለት ፓርቲዎች ጋር መስርተውት የነበረው ‹‹ህብረት››፣ ፓርላማ በመግባታቸው፣ ከውግዘት ጋር እንዲባረሩ በማድረጉ ያሳደረባቸው መገለል ሊሆን ይችላል፤ በአንድነት በኩል ደግሞ ‹የመድረኩ
መሀንዲስ› ተደርገው የተወሰዱት ዶ/ር ነጋሶና አቶ ስዬ አብርሃ አንድነትን ለመቀላቀል ወደ መድረክ መግባትን እንደ መደራደሪያ በማቅረባቸው ሲሆን፣ ሌላኛው ደግሞ ዛሬም ያልተሸነፈው የ‹ተባበሩ ወይም ተሰባበሩ› ግልብ ግፊት ነው ብዬ አስባለሁ፤ የዚህ ድምር ውጤትም ከነርዕዮተ-ዓለም እና የፕሮግራም ልዩነት ወደ መድረኩ አምጥቷቸው አይን የሚገባ ሥራ እንዳይሰሩ አግዷቸዋል)

የመድረክ አባል ድርጅቶች መተዳደሪያ ደንብን አለማክበር ‹የፖለቲካ ብልጠት› በማድረጋቸው፣ ለራሳቸው ተጨማሪ የመናተረኪያ አጀንዳ ፈጥረዋል፡፡ ይህ አይነቱ ስርዓት አልበኝነት በጋራም በተናጥልም ተፈፅሟል፡፡ አንድነትን ጨምሮ የመድረኩ ስራ አስፈፃሚ ደጋግሞ ከመርሁ ሲያፈነግጥ ታይቷል፤ ለምሳሌ በደንቡ ላይ መሻሻል ያለበትን አንቀፅ የሚወስነውም ሆነ ከፍተኛው ስልጣን የጠቅላላ ጉባዔው መሆኑ በግልፅ ተቀምጦ ሳለ፣ ጉባዔው ከተሰበሰበባቸው በአንዱ ዕለት ‹የመድረኩ ሊቀ-መንበረ በዙር ከሚሆን፣ በብቃት ይሁን›፤ እንዲሁም ‹አዲስ ፓርቲ በአባልነት የምንቀበልበት መንገድ መሻሻል አለበት› የሚሉ አቋሞች ላይ ቢደርስም፣ ስራ አስፈፃሚው ቃል በቃል ‹ይህንን አሰራር ጉባኤው ሊቀይረው አይችልም› ሲል ውድቅ ያደረገበትን አጋጣሚ መጥቀስ ይቻላል፡፡
በተናጥል አንድነት፣ ኦፌኮ እና ኢሶዴፓ በአንቀፅ 21 ‹የአባል ድርጅቶች ግዴታ› በሚል ርዕስ ስር የተቀመጡትን፡- ‹ከአፍራሽና ተቃራኒ ከሆኑ እንቅስቃሴዎች መቆጠብ›፣ ‹በአባላት መካከል አለመተማመን ከሚፈጥሩ ማናቸውም ተግባር መቆጠብ›፣ ‹የግንባሩን አቋም የሚፃረር አቋም ያለማራመድ› እና መሰል ደንቦችን ደጋግመው በአደባባይ ሲጥሱ ታይተዋል፤ ይህ አይነቱ ስርዓተ-አልበኝነት መፍትሄ ሳያገኝ የተሻለና ጠንካራ ሆኖ መውጣቱ አዳጋች ይመስለኛል፡፡
ሰማያዊ
ሰማያዊ ፓርቲ አዲስ በመሆኑ ለወቀሳ መቸኮሉ አግባብ እንዳልሆነ ቢሰማኝም፣ ፓርቲው እያሳየ ካለው ፈጣን እንቅስቃሴ አኳያ፣ በፍጥነቶቹ መካከል የሚፈጥራቸውን ድክመቶቹን ቢያሻሽል ጠቀሜታው ለሀገር ስለሆነ የግል አስታየየት መስጠቱን አስፈላጊ ሆኖ አግኝቸዋለሁ፡፡
የሰማያዊ ዋናው ድክመት ከ‹ግንፍሌ ፓርቲ›ነት አልፎ የመሄድ ፍላጎት ያለው አለመምሰሉ ነው (ጽ/ቤቱ አራት ኪሎ /ግንፍሌ/ አካባቢ ይገኛል)፡፡ ከአዲስ አበባ ውጪ ለመንቀሳቀስ ሲሞክር አይታይም፤ በሌሎቸ የሀገሪቱ ከተሞች የተከፈተ ተጨማሪ ቢሮ ካለ፣ ከምስረታው በኋላ የአባላቱ ቁጥር ምን ያህል እንደደረሰ፣ እና መሰል መረጃዎችን ለማግኘት ወደ ፓርቲው ጽ/ቤት ሄዶ የነበረው የመፅሄቱ ሪፖርተር ‹እንዴት እንደምትጠቀሙበት ስለማናውቅ አንናገርም› በሚል ክልከላ በመመለሱ ስለወቅታዊው ቁመና እዚህ ጋ መጥቀስ አልተቻለም (ከዚህ ውጪ ሊቀ-መንበሩ ይልቃል ጌትነት ከ‹ሰንደቅ› ጋዜጣ ጋር ባደረገው ቃለ-መጠይቅ ‹‹ባለፉት 40 ዓመታት ከመጣው የፓርቲዎች
ጥንካሬ ይልቅ፣ በአንድ ዓመት ውስጥ ሰማያዊ ፓርቲ ብቻውን አምጥጦታል›› ያለው ሀረግ ስህተት ቢሆንም፣ አንድም በሂደት የሚታረም፣ሁለትም የአፍ ወለምታ፣ ሶስትም ከልምድ ማነስ የሚያጋጥም በመሆኑ ‹ፀጉር መንጨቱ› ፓርቲው ፍርሃትን ለመስበር ከሚያደርገው እንቅስቃሴ አኳያ ገንቢ አይደለምና አልፈዋለሁ፡፡)
‹እምነት ጨምሩልን›
‹ለውጥ! ለውጥ!› የሚል ድምፅ በመላ ሀገሪቱ የበረከተው የ‹ቡርዣ› ወይም ‹አድሀሪ› አብዮትን በመናፈቅ አይደለም፤ እንዲህ አይነት አብዮት፣ ከሰው ለውጥ በቀር ሕዝባዊ ጠቀሜታ የለውማና፡፡ የደርግም ሆነ የኢህአዴግ ‹አብዮት› የዚህ አምሳያ በመሆኑ ነው፣ ዛሬም ዘመን ተጋሪዎቼ ‹ፋኖ ተሰማራ!› ከማለት ነፃ ያልወጡት፡፡ ‹ሶስተኛው አብዮት› የማይሸነፍ እና የማይንበረከክ እንዲሆንልን ከምንመኘው በላይ ወደ ‹መፈንቅለ-መንግስት›ነት እንዳይቀየር መጠንቀቁንም ግዴታ ያደረገው ጠንካራ ፓርቲና የነቃ ማህበረሰብ ያለመኖሩ ስጋት ነው፡ ፡ ይህ ደግሞ ከወዲሁ ከአማራጩ ኃይል ጎን መቆም ይቻል ዘንድ ‹እምነት ጨምሩልን!› (ሀገር የመረከብ አቅማቸውን አሳዩን?) እንድንል
አስገድዷል (‹ጀግናው› ኢህአዴግ ወደ ማይቀረው ሽንፈት መንገዱን ከጀመረ ጥቂት ክረምቶች በማለፋቸው፣ ከለውጡ በኋላ የሚመጣው ኃይል ሁለንታው የተቃና መሆኑን ማስመስከር አለበት) መድረክ፣ አንድነት እና ሰማያዊ ወደራሳቸው ይመለከቱ ዘንድ ከሞላ ጎደል የወል ‹ክፍተቶች› ወይም ‹ድክመቶች› የምላቸውን ሶስት ጉዳዮች ከዚህ ቀጥሎ እጠቅሳለሁ፡፡
ሃሳብ-አልባ
ፓርቲዎቹ በምስረታቸው ዘመን ቅድሚያ የሚሰጡት ለምርጫ ቦርድ የእውቅና ሰርተፍኬት እና ‹ተቃዋሚ ድርጅት› ተብለው ለመጠራት በመሆኑ አንድም የሀገሪቱን አንኳር ችግሮች አጥንተው መፍትሄ በመያዝ አልተዘጋጁም፤ ሁለትም ከነባር ድርጅቶች ድክመትና ጥንካሬ ተምረው አልመጡም፤ በዚህም የሚፈልጉትን ሳያወቁ እና የተለየ አማራጭ ሳይይዙ ወደ ፖለቲካው ገብተዋል ወደሚል ጠርዝ እየገፋን ነው፤ ጠንካራና የተፍታታ የፖለቲካ ፕሮግራም የላቸውም፤ በንፅፅር ‹‹አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ›› የተሻለ ፕሮግራም ለመቅረፅ ከመሞከሩ ውጪ፣ የመንግስቱ ስልጣን ‹ገጭ-ቋ› ቢል ‹አማራጭ ሊሆኑ ይችላሉ› የሚባሉት ፓርቲዎች ‹እያሾፉ ነው› በሚል ችላ ካልተባሉ በቀር ‹ፕሮግራሜ› ብለው ያቀረቡትን ለተመለከተ ምን ያህል ሃሳብ አልባ እንደሆኑ ለመረዳት አይቸገርም፡፡ የሆነው ሆኖ ይህንን ፅሁፍ ሳዘጋጅ የነበረኝ አመለካከት ስለመድረክና አንድነት የፖለቲካ ፕሮግራም ደካማነት ከዚህ ቀደም ስለጠቀስኩ፣ ዛሬ ሰማያዊ ፓርቲን ብቻ አንስተን ብንነጋገር ይሻላል የሚል ነበር፤ ይሁንና የድርጅቱን ፕሮግራም ካነበብኩ በኋላ ግን ምንም ማውራት እንደማይቻል ተረዳው (ያውም ያየሁት ወረቀት ‹ፕሮግራም› ተብሎ ሊጠራ ከቻለ ማለት ነው)፡፡ ፓርቲው ለስልጣን የመብቃት ዕድል
ካገኘ፣ ለዘመናት ሲንከባለልና ሲደራረብ የመጣውን ዘርፈ ብዙ የሀገሪቷን ችግር የሚፈታው ‹‹የሰማያዊ ፓርቲ ፕሮግራም›› በማለት ርዕስ ባዘጋጀው ባለአስራ አምስት ገፅ ወረቀት ነው፡፡ መቼም በዚህ ፕሮግራም ‹ከሌሎች የተሻልኩ ነኝ-ምረጡኝ› የማለቱ ድፍረት ግራ አጋቢ ይመስለኛል፤ ምናልባት ‹የፖለቲካ ሳይንስ ምሁሩ ዶ/ር መረራ ጉዲና ካዘጋጀው አራት ገፅ ፕሮግራም፣ የእኛ የበለጠ ነው› የሚል መከራከሪያ ካልቀረበ፡፡ ስለርዕዮተ-ዓለሙም ቢሆን ‹ለዘብተኛ ሌብራሊዝም› ከማለት ያለፈ ያብራራልን ጉዳይ የለም (በዚህ በኩል ኢዴፓ ከሁሉም በተሻለ የተብራራና የጠበቀ ፕሮግራም አለው፤ ግና! ለአንድ ፓርቲ ከምንም በላይ አስፈላጊ የሆነውን ‹ታአማኒነት› አፍርሷልና ፕሮግራሙ ጠቀመ አልጠቀመ ፋይዳ አለው ማለት አይቻልም) በተቀረ ያለ ርዕዮተ-ዓለም ፓርቲ መስርቶ፣ ‹ሀገሬን፣ ሀገሬን…› ማለቱን ከቀረርቶ ለይቶ መረዳት ይቸግራል፡፡
መድረክ፣ አንድነት እና ሰማያዊ አሁንም ጊዜውም ዕድሉም አላቸውና ስልጣን ቢይዙ በዋና ዋና ሀገራዊ አጀንዳዎች፣ በፖሊሲዎች፣ በማህበራዊ ፍትህ እና መሰል ጉዳዮች ላይ ያላችውን የመፍትሄ ሃሳብ እና የተሻለ አማራጭ በትክክል ተንትነው ማዘጋጀቱን ቢያስቀድሙ መልካም ይመስለኛል፡፡ ቅንጅት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ በ1997 ዓ.ም ‹‹የምርጫ ማኒፌስቶ›› ብሎ ያዘጋጀው ሰነድ እንኳ ከ130 ገፅ በላይ የፈጀ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ነው፡፡ እናም ፓርቲዎቹ ‹ፕሮግራሜ› የሚሉትንም ሆነ፣ ከተራራ የገዘፈ ችግሮቻችንን በደቃቃ ግምገማ ለማብራራት መዳከሩን አርቀው በመስቀል ወደ ቁም-ነገሩ ቢያዘንብሉ ጠቀሜታው ለራሳቸው ነው፤ ‹የትም ፍጪው…› መረሳት አለበት፤ ለፖለቲካ ፓርቲ ሃሳብ ከምንም በላይ ወሳኝ ነው፡፡ ዳሩስ! በሰላማዊ መንገድ ለመታገል የተዘጋጀ ፓርቲ፣ የሚሸጥ ርዕዮተ-ዓለም ካላዘጋጀ በቀር ወታደራዊ ድርጅት አይደለምና ‹በኃይል ተጠቅሜ ፍላጎቴን አሳካለሁ› ሊል አይችልም፡፡ እውነት እውነት እላችኋለውም በዚህ በኩል ቀድሞ የነቃ፣ እርሱ አትራፊ ነው፤ ረቢው እንዳለውም ‹ላለው ይጨመርለታል›ና፡፡
ምሁር አልባ
የተፎካካሪ ድርጅቶች ሌላኛው ክፍተት ምሁራንን /ሙያተኞችን/ አለማቀፍ እንደሆነ ተደጋግሞ ቢነገርም፣ ዛሬም በዚህ በኩል የተሰራ ሥራ የለም፡፡ ይህንን ቀዳዳ ለመድፈን አመራሩና አባለቱ ከጽ/ቤት በመውጣት መቀስቀስ፣ ማሳመን፣ ማግባባት… አለባቸው ብዬ አስባለሁ፤ መቼም በሁሉም ዘርፍ ‹እኔ ብቻ ነኝ የማውቀው› ግብዝነትን የወረሱት ነፍሱን ይማረውና ከአቶ መለስ ይመስለኛል፤ ይህ አይነቱ አመለካከት ግን ወንዝ አያሻግርም፡፡ በርግጥ ‹ፖለቲካና ኮረንቲ…› በሚባልበት አገር፣ በደፍረት፣ ድርጅት እስከመመስረት መድረስ ትልቅ ታሪክ ቢሆንም፣ ጠንካራ መሆን ካልተቻለ ዞሮ ዞሮ ያው ክሽፈት ነው፡፡ አደባባዩም እንደቀድሞ ‹ድንጋይ ዳቦ ነው› ብለው ለሚከራከሩ አፈ-ጮማ ፖለቲከኞች ቦታ የሌለው መሆኑ ግልፅ ይመስለኛል፡፡ በተለያየ ሙያ የሰለጠኑ ምሁራኖችን ወደ ፓርቲያችሁ ለመሳብ መደላደሉን አመቻቹ፤ ፍርሃት መሰበር እንዳለበት አሳምኗቸው፤ አንኳኩ፤ ከልከፈቱም ደጋግሙት፡፡
የሴራ ፖለቲካ
ሌላው ድርጅቶቹ የሚጠነክሩት፡- ከሴራ፣ ከስርቻ ስር ፖለቲካ፣ ከጠልፎ መጣል ጨዋታ፣ ከአፍቅሮተ-ስልጣን አና ከመሳሰሉት ነፃ ሲሆኑ ነው፡፡ በአናቱም የጥናትና ምርምር ዘርፍ መሰል እያቋቋሙ እውቀትና መረጃን ወደላይም ወደታችም በማሰራጨት አመራሩንና አባላትን ማብቃት፣ እንዲሁም ግልፅነትን በመተግበር፣ የ‹ጀርባ ፖለቲካ›ን ማዳካም ይቻላል፡፡ ይህ ሲሆን ነው ኩነቶችን ከመበለጥና ያለመበለጥ፤ ከመሸነፍና ያለመሸነፍ አኳያ ብቻ የማየቱ አባዜ የሚለወጠው፡፡ ከእዚህ ሁሉ ስንክሳር በላይ ደግሞ በምሬቷ ብዛት
በአማራጩ ኃይል ላይ ተስፋ የጣለች ሀገር መኖሯም ከእያንዳንዷ እንቅስቃሴ ጋ መታወስ ይኖርበታል፡፡
በመጨረሻም-የአልባራዲ መንገድ
ሀገሪቱ ካለችበት ወሳኝና ታሪካው ወቅት አኳያ ቢያንስ በመንግስት ጥቁር መዝገብ ስማቸው ያልሰፈረ፣ እውቀትና አቅም ያላቸው፣ በየትኛውም ሀገር የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በራሳቸው መንገድ ወደ ሀገራቸው ገብተው ትግሉን ማገዝ የሀገሪቱ ወቅታዊ ሁናቴ የሚያስገድደው ነው፡፡ በተለይም በእንዲህ አይነት ጉዳዮች ከትምህርትም ሆነ ከመስክ ልምድ ያካበቱ ወንድምና እህቶች የግብፃዊውን መሀመድ አልባራዲ መንገድ ቢከተሉ፣ አንድም ሁኔታዎች ከቁጥጥር እንዳይወጡ ማገዝ ይችላሉ፤ ሁለትም አብዮቱን ከሽንፈትና ቅልበሳ
ይታደጋሉ፡፡
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!
ኢትዮሚድያ – Ethiomedia.com
September 23, 2013

Monday, September 23, 2013

አወይ ሶሪያ….የኢትዮጵያ ጠላት!

(በሰሎሞን ተሰማ ጂ.) http://semnaworeq.blogspot.com   Email:solomontessemag@gmail.com
የሶሪያ ጉዳይ ከዕለት ወደ ዕለት እየከፋ መጥቷል፡፡ በስልጣን ላይ ያለው ጎሳ “የአላዊት ጎሳ” ይባላል፡፡ አላዊቶችና በደዊኖች በሽፍትነትና በባህር ላይ ውንብድና ስማቸው የገነኑ ናቸው፡፡ በደዊኖች፣ ሶሪያን ለዘመናት ያህል ሲፈልጧትና ሲቆርጧት ኖረዋል፡፡ እንደነሱ ዘረኛ፣ እንደበደዊኖች ጠባብ፣ አክራሪና ቁመኛ ታይቶም-ተሰምቶም አይታወቅም፡፡ አላዊቶችም ቢሆኑ “አልሸሹም ዞር አሉ” ናቸው፡፡ እነዚህ ወገኖች፣ የሶሪያን ሀገረ-መንግሥት (State apparatus) ከተቆጣጠሩበት ዘመን ጀምሮ ለኢትዮጵያ በጎ ተመኝተውላት አያውቁም፡፡ ይባስ ብሎ ደግሞ፣ ከ1950ዎቹ መጀመሪያ ወዲህ እጅግ በከፋ መልኩ የኢትዮጵያን ጥቅምና ሉዓላዊነት በሚፈታተን መልኩ በግትርነት ቆመው ነበር፡፡ በጣም በተጋነነና በመረረ ኹናቴ መንቀሳቀስ የጀመሩት ግን ከ1953ዓ/ም ወዲህ ነው፡፡ በዚህ ዓመትም በጂዳ-ሳዑዲት ዓረቢያ የተቋቋመውን “የኤርትራ ነፃ-አውጪ ድርጅት” (ወይም በተለምዶ አጠራሩ ጀ.ብ.ሐ) እየተባለ የሚታወቀው፣ በአሳውርታ የሚኖሩት የቤንአሚር ጎሳ ተወላጆች ቡድን ለመደገፍ በደዊኖች ተሯሯጡ፡፡ ከእነርሱም ቀጥሎ ወደስልጣን የመጡት አላዊቶች ተመሳሳይ ተግባር ፈፀሙ፡፡ ያለምክንያት አልነበረም፤ በአሳውርታ የሚወለዱት ቤንአሚሮች “የበደዊንና የአላዊት ደም አላቸው” ከሚል ጎሰኛ ቀመር ተነስተው ነው፡፡ Syria officially the Syrian Arab Republic
ስለሆነም፣ በ1955ዓ/ም በይፋ ለጀ.ብ.ሐ አገናኝ ቢሮ በደማስቆ ከተማ ተከፈተለት፡፡ ከዚያም ጊዜ ጀምሮ፣ በርካታ ፀረ-ኢትዮጵያ እንቅስቃሴዎችን መደገፍ ጀመሩ፡፡ በ1960 እና 1961ዓ.ም ብቻ እንኳን፣ “ነፃነትን-መደገፍ” በሚል ስም፣ እ.አ.አ እስከ 1970 ድረስ በበደዊን ጎሳዎች የሚመራው የሶሪያ መንግሥት በርካታ የአጋሚዶ/የውንብድና ተልዕኮዎችን ከአፍ-እስከ-ገደፉ ደግፏል፡፡ (ይሄንን በተመለከተ፣ በ1933ዓ/ም በደቀሽሐይ-ሐማሴን የተወለደውና በጀብሐ ውስጥ የ5ተኛው ወታደራዊ ክፍል/ምድብ ዋና መሪ የነበረው፣ ወልዳይ ካህሳይ ብዙ-ብዙ ነገር ያወሳናል፡፡ ወደኋላ ላይ እንመለስበታለን፡፡) በዚህ የመቀራረብና የመተሳሰብ ዘመን በሆነው በ21ኛው ክፍለ ዘመን፣ በደዊኖችና አላዊቶች ከአንድ መንግሥት የሚጠበቀውን ዓለም አቀፍ ኃላፊነት ዘንግተው፣ ዓለም አቀፍ ውንብድና ውስጥ ሙጭጭ አሉ፡፡ በዘመናዊ አስተዳደር፣ ሃይማኖትና ጎሳ እምብዛም ቦታ እንደሌላቸው ያልተገነዘቡት በደዊኖችና አላዊቶች፣ በዘር፣ በጎሳና በሃይማኖት ጥላ ስር የተሰባሰቡትን ወንበዴዎች ሁሉ በወታደራዊ ስልጠናና በትጥቅ ሲረዱ ኖረዋል፡፡ በዚህም አቋማቸው የተነሳ በመካከለኛው ምስራቅ ውስጥ የተነሱትን ማናቸውንም ግጭቶች ቤንዚን በማርከፍከፍ ሲጋግሙት ኖረዋል፡፡ ወይም በሀገራችን አባባል ጭድ ሲነሰንሱበት ኖረዋል፡፡ ሊባኖስ ቀንደኛዋ ተጎጂ ናት፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሯ ሐሪሪ ሳይቀሩ የተገደሉት በሶሪያ ጎሰኞች መሰሪ ደባ ነው፡፡ (በአሜሪካዊያኑና በበርካታ የዓረቡ ዓለም ሰዎች የተጠላውና የተወገዘው-“ጫማ ሳይቀር የተወረወረበት”-ትንሹ ጆርጅ ቡሽ እንኳ፣ “የዳቢሎስ ዛቢያ (Evil Axes)” ብሎ እስኪጠራት ድረስ፣ የበደዊኖቹና የአላዊቶቹ ሶሪያ፣ እጅግ አገደኛ ምሳር ናት፡፡)

ከአላዊቶች ጎሳ/ወገን የሆነው የሶሪያው ፕሬዝዳንት፣ በሺር አላሳድ ይባላል፡፡ ከደማስቆ ዩኒቨርሲቲ በዓይን ሕክምና (Ophthalmology) ዶክተር ነው፡፡ እ.አ.አ ከ2000ዓ/ም እስካሁን ድረስ በስልጣን ላይ ተፈናጧል፡፡ ከእርሱ በፊትም አባትየው ሀፊዝ አላሳድ (እ.አ.አ ከ1971-2000) ሶሪያን አንቀጥቅጦ ገዝቷታል፡፡ የጦር ጀነራልና ከ1946 (እ.አ.አ ጀምሮ የባዐዝ ፓርቲ አባልና መሪም ነበር፡፡) አላዊቶችም የበደዊኖቹ በሽታ አለባቸው፡፡ እነርሱም ከላይ እንደገለጽነው-ዘረኝነት፣ ጠባብነትና አክራሪነት ናቸው፡፡ ከ1957ዓ.ም ጀምሮ በኮሚኒዝም ስብከትና አስተምህሮት ናላቸው የዞሩትን ተማሪዎችና ወጣቶች ለመደገፍ የሩሲያ፣ የቼኮዝሎቫኪያና የቻይና መንግሥታት ያልተገደበ ጥረት አድረገዋል፡፡ ለዚህም ማሳያው ደግሞ፣ በመጋቢት 4/1961ዓ.ም ሁለት የሩሲያ፣ ሦስት የቼኮዝሎቫኪያና ሁለት የቻይና ዜጎች ኢትዮጵያን በ24 ሰዓታት ውስጥ ለቀው እንዲወጡ ተደርገዋል፡፡ ሁሉም፣ ኮሚኒዝምን በየትምህርት ቤቱና በየኮሌጆቹ ለማስረጽ በመሞከራቸውና ወጣቶችን ለዓመጽ በመቀስቀሳቸው ነበር፡፡ ይህ ሴራቸው የተደረሰባቸው ሦስቱ አገሮች ጀብደኛውን የሶሪያ ጎሰኛ መንግሥት እንደፈለጉት ተጠቅመውበታል፡፡

እነዚህ  ጊዜ የሠጣቸው ኃያላን መንግሥታት፣ የራሳቸውን ተጽዕኖ ኢትዮጵያ ላይ ለመጣልና በሀገራችን ጉዳይ ጣልቃ ለመግባት ያልፈነቀሉት ነገር አልነበረም፡፡ ያ ስር የማይሰድላቸው ቢመስላቸው፣ የሶሪያን ጣልቃ ገብነት ተማፀኑ፡፡ አርቀው የማያዩትም የሶሪያ መሪዎች ዘው ብለው ገቡበት፡፡ ምክንያታቸው ግልጽ ነው፤ የሶሪያ ጣልቃ ገብነት ለሌሎች ኃያል ኮሚኒስቶች መሣሪያና ስልጠና መሸጋገሪያ ድልድይ በመሆን ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ፣ “ነጋዴ ራሱ ስለተቀማ ሳይሆን፣ ሌላው ነጋዴ ስለዳነ ይቆጫል፤” በሚለው የአገራችን ምሳሌ አማካይነት ሊተረጎምም ይችላል፡፡ የሶሪያ መንግሥት በሀገሩ ውስጥ ያለውን ሁከት፣ ትረምስና ብጥብጥ፣ ከዚያም አልፎ ከእስራኤል ጋር ከነበረው የተደጋገመ የተጠቂነት ሽንፈት የዜጎቹን አስተሳሰብ ለማስቀየስ፣ ሌሎች የእስራኤል መንግሥት ወዳጆች ናቸው ያላቸውን አገሮች በመተናኮል ሊወጣ ሞክሯል፡፡ ይህ አባዜ፣ “ወድቆ የቆመው እንደመጎተት” ዓይነት ነው፡፡

ከላይ እንደገለጽነው፣ የሶሪያ መንግሥት በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባት ከጀመረና ኢትዮጵያን መተናኮልም ከጀመረ ቆይቷል፡፡ በ1958ዓ.ም ከኢትዮጵያ ተጠልፎ ወደካርቱም የተወሰደውን የኢትዮጵያ አይሮፕላን የጠለፈው ወጣቱ ከበደ ደበላ፣ መጀመሪያ ጥገኝነት ያገኘው ሶሪያ ደማስቆ ነበር፡፡ የፈረንጆቹ 1969 ዓ.ም ደግሞ የሶሪያ የጠላትነት ሽፍንፍን ቅልጥጥ ብሎ የወጣበት ዓመት ሆነ፡፡ በዚሁ ዓመት ከተሞከሩት የኢትዮጵያን አየር መንገድ የማጥቃት አምስት ሙከራዎች ውስጥ አራቱ የሶሪያ መንግሥት ቀጥተኛ ድጋፍ ነበራቸው፡፡ በዕለተ ማክሰኞ መጋቢት 2/1961ዓ.ም ፈራንክፈርት አይሮፕላን ማረፊያ በቆመበት በሁለት ፈንጂዎች የተቀጣጠለውን ቦይንግ 707 አይሮፕላን በስልጠናና በትጥቅ የደገፈችው ሶሪያ ነበረች፡፡ በዚሁ ዓመት፣ በሚያዝያ 2/1961ዓ/ም በካይሮ ከተማ አቅራቢያ (105 ኪ.ሜ በስተደቡብ) ከወደቀው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋግላስ ሲ-47 አይሮፕላን አደጋ ጀርባም ያለችው መሰሪ ሶሪያ ነበረች፡፡ በሰኔ 11/1961ዓ.ም ከምሽቱ 1፡15 ላይ ካራቺ አይሮፕላን ማረፊያ እንደቆመ ነበር በእጅ መትረየስ ከ50 ሜትር ርቀት ላይ አደጋውን የያሉት፡፡ እነዚህ ሦስት ሽፍቶች ከሶሪያ ተነስተው ካርቱም ላይ ሴራቸውን ካቀነባበሩ በኋላ፣ ወደ ቤይሩት በረሩ፡፡ ከዚያም ፓኪስታን ሁለተኛዋ ከተማ ካራቺ ደረሱ፤ አደጋውንም ጣሉ፡፡ ስማቸውም-መሐመድ ኢድሪስ፣ ፍስሐዬ አብርሃምና ዓሊ አብደላ የሚባሉ ናቸው፡፡ ሦስቱም ስልጠናቸውንና ትጥቃቸውን ከሶሪያ መንግሥት ያገኙ የጀብሐ አባሎች ነበሩ፡፡

ከእነዚህም የሶሪያ ቅጥረኞች ቀጥሎ፣ በዕለተ ሰኞ ነሐሴ 5/1961ዓ.ም ከአስመራ ተነስቶ በባሕር ዳር በኩል ወደአዲስ አበባ ይጓዝ የነበረውን ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ የበረራ ቁጥር-231፣ DC-3 አይሮፕላን ባህር ዳር ከተማ ላይ ተሳፍረው ሲጠለፉትና ወደካርቱም ሲወስዱት ያሉት ነገር ቢኖር፣ “እኛ በማኦሴቱንግ ፍልስፍና የምናምን ኮሚኒስቶች ነን፡፡ አይሮፕላኑንም አስገድደን ወደካርቱም ያመጣነው ወደኮሚኒስት ቻይና ለመሄድ ላቀድነው ጉዞ ልንጠቀምበት ነው፤” ነበር ያሉት፡፡ እነዚህም የሲቪል አቬሽን ወንበዴዎች፣ በቀጥታ ከሶሪያ ጋር ግንኙነት ባይኖራቸው በርዕዮተ-ዓለማቸው የግራ ክንፍ አቀንቃኞች ነበሩ፡፡ የዚህኛው ጠለፋ አድራጊዎች ደግሞ፣ ሰባት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሲሆኑ፣ በአንዳንድ የባዕዳንን ሴራ ባልተረዱ ወገኖች በበጎ የሚነሱም ናቸው፡፡ ለምሳሌ በ1960 እና 1961ዱ የተማሪዎች ዓመጽ ዋነኛ አስበጥባጭና ተከሳሽ የነበሩት ዋለልኝ መኮንንና ማርታ ይገኙበታል፡፡ ከኋላቸው የነበሩት አገሮች ሩሲያና ቼኮዝሎቫኪያ ናቸው፡፡ በመስከረም 3/1962ዓ/ም ከድሬዳዋ ወደጂቡቲ ሲበር የነበረውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ DC-6B አይሮፕላን መንገድ አስቀይረው ወደ የመን-ኤደን የወሰዱት የጀብሐ ሰዎች ተቀማጭነታቸው ሶሪያ-ደማሽቆ ነበር፡፡ ይህ አይሮፕላን 39 መንገደኞችና አምስት የአውሮፕላኑን ሠራተኞች ይዞ የነበረ ሲሆን፣ ሁሉም በደህና ሁኔታ በመስከረም 5/1962ዓ.ም ከቀትር በኋላ ወደአዲስ አበባ ተመልሰዋል፡፡

አይሮፕላኑን ሳልይዝ ወደኢትዮጵያ አልመለስም ያሉት ካፒቴን ቀፀላ ኃይሌና ጠለፋውን ያከሸፈው ም/የአስር አለቃ ካሳዬ ታደሰ ኤደን ቀርተዋል፡፡ (በነገራችን ላይ፣ ካሳዬ ታደሰ የሻለቃ ማዕረግ አግኝተው በጡረታ ከሠራዊቱ ከተገለሉ በኋላ፣ ኑሯቸውን በሎስ አንጀለስ አድርገዋል፡፡) አደጋው በደረሰበት በመስከረም 3/1962ዓ/ም አመሻሹ ላይ መቀመጫውን ሶሪያ-ደማስቆ ያደረገው የኤርትራ ነጻ-አውጪ ድርጅት (ጀብሐ) ኃላፊቱን ወሰደ፡፡ ጠለፋውን ያደረኩት “እኔ ነኝ” አለ፡፡ ከነዚህ “የቻይና ኮሚኒስት ነኝ!” “የአልባኒያ ኮሚኒስትን የሚከተል ከኔ በላይ ላሳር!” “የሩሲያን ኮሚኒዝም ጡት እየመገመገ ያደገ ማን እንደኔ!” ወይም ደግሞ “በመኮሚኒስትነት እኔ የቼኩ ምልምል አሽከር ጋር የሚፎካከር ማነው?” የሚሉት ወገኖች ሁሉ አንድ ናቸው፡፡ ሁሉም የግለሰብን መብት ለመደፍጠጥና የመንጋ (“ተራማጅ ነን ባዮችን”) መዋቅር እንደሸረሪት ድር ለማቆሸሽ የሚተጉ ናቸው፡፡ በጋማል አብደል ናስር ኮትኳችነት የተጀመረውና የዓረቡን ዓለም በኮሚኒዝም ርዕዮት-ዓለም ለማስተሳሰር የጣረው ባአዝ (BAAZ Party) የሶሪያ አውራ ፓርቲ ሆኖ ነበር፡፡ በገለልተኛ ሀገሮች ስራችነቷ ፀንታ ለመቆም የምትፍጨረጨረውን ኢትዮጵያን ኮሚኒስቶቹ አገሮች በጥላቻ ነበር የሚመለከቷት፡፡

ለዚህ ብያኔያን ጥሩ ማሳያ የሚሆነን የጀብሐ 5ተኛ ወታደራዊ ምድብ/ክንፍ አላፊ የነበረውና ይህንን ቃለ-ምልልስ ሲያደርግ የ29ዓመት ወጣት የነበረው ወልዳይ ካሕሳይ ነው፡፡ እስከ 12ተኛ ክፍል ድረስ በአስመራ ኮምቦኒ ትምህርት ቤት ተምሯል፡፡ ከዚያም በትውልድ መንደሩ በደቀሽሐይ-ሐማሴን ለሁለት ዓመታት ያህል አስተምሯል፡፡ በጥቅምት 25/1960ዓ.ም ካርቱም ለሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ እጁን ሰጠ፡፡ ይህም ቃለ-ምልልስ የተደረገለት ካርቱም ሳለ ነበር፡፡ ወልዳይ ስለድርጅቱ እንዲህ አለ፤ “የጀብሐ መሪዎች እኔን የ5ተኛው ወታደራዊ ክፍል አላፊ ያደረጉኝ ወደው አይደለም፡፡ ‘በድርጅቱ ውስጥ አንድም ክርስቲያን ወታደራዊ መሪ የለም!’ ለሚለው የደጋው ኤርትራዊ ቅሬታ ማስተንፈሻ ሲሉ ነው እንጂ፤ በእውነተኛነት አስበውት አይደለም፡፡ እኔ ከምመራው ወታደራዊ ክፍል ውጪ ያሉት አራቱም ክፍሎች አንድም ክርስያቲያን ተዋጊ እንኳን የላቸውም፡፡ ለዚህ ደግሞ በቂ ምክንያት አለው፤ ድርጅቱ የሚሠራው ለአንዳንድ የዓረብ አገሮች ነው፡፡ ተዋጊዎቹም ሆኑ አመራሮቻቸው ስልጠና የሚያገኙት ወደሶሪያ እየሄዱ ነው፡፡ ለሽፍትነት ስልጠና ወደሶሪያ ከሄዱት 300 (ሦስት መቶ) ሰልጣኞች መካከል፣ አንድም ክርስቲያን አልነበረባቸውም፡፡ አምስት አረቢኛ ተናጋሪዎች ብንኖር እንኳን፣ ስማችንን እንድንለውጥ ተደርገናል፤” እያለ ያብራራል፡፡
ወልዳይ ለጀብሐ ርዳታ ስለሚያደርጉትም አገሮች ተጠይቆ ሲያብራራ  እንዲህ ብሎ ነበር፤ “ሶሪያና ኢራቅ ወታደሮችን በማሰልጠን በኩል ሲረዱ፣ ሶሪያ በተለይ የጦር መሳሪያም በገፍ ታቀብለናለች፡፡ እንደሚታወቀው፣ ጀብሐት እ.አ.አ በ1961 ጂዳ-ሳዑዲ የተመሠረተ በመሆኑ፣ የሳዑዲ መንግሥትና ሕዝብ በገንዘብ በኩል ይረዳል፡፡ ከጎረቤት አገሮችም መካከል ግብጽ፣ ሱዳን፣ ሶማሊያና ጅቡቲ ሽፍቶቹ በዓረብ አገሮች በሚዘዋወሩበት ጊዜ የሚያገለግላቸውን ፓስፖርት በመስጠትና በልዩ ልዩ መንገዶችም ይረዳሉ፡፡ በተለይም ግብፅ የመሳሪያ እርዳታዋን ነፍጋን አታውቅም፤”በማለት ገልፆ ነበር፡፡ “ቻይናም የወታደሮች ልብስ ሰጥታ፣ ልብሱ ግን ለበረሃው ሊያገለግል ሳይችል ቀርቷል፡፡ በቅርቡ ለከፍተኛ የወታደራዊ ስልጠና ስኮላርሺፕ ሰጥታ-20 ሰዎች ተመርጠው ወደቻይና ለመሄድ ወደሶሪያ እያመሩ መሆናቸውንም” አመልክቶ ነበር፡፡ ወልዳይ እንዲህም ሲል አከለ፣ “በአሁኑ ሰዓት በኤርትራ ውስጥ 65% ክርስቲያኖችና 35% ደግሞ ሙስሊሞች ይገኛሉ፡፡ እስከ 4ተኛ ክፍል ድረስብቻ የነበረውም ትምህርት እስከ ዩኒቨርሲቲ ድረስ አድጓል፡፡ ታዲያ እኔ ለምን ብዬ ይሄንን እውነታ ከካዱ ሰዎች ጋር እሰለፋለሁ?” ሲል ተደምጧል(አዲስ ዘመን፣ ጥቅምት 1/1960ዓ/ም፣ ገጽ-1፣5 ይመልከቱ)፡፡

ማጠቃለያ፤
ከሰሞኑ፣ የበሺር አላሳድ መንግስት ላይ የወታደራዊ ጥቃት ለመክፈት አሜሪካንና ፈረንሳይ ቆርጠው ተነስተዋል፡፡ የባዝ ፓርቲና የአላሳድ ወዳጆች ሩሲያና ቻይናም እየተከላከሉለት ናቸው፡፡ የፀጥታ ምክር ቤትም በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ከሳዳም ሁሴን የተቀበላቸውን የኬሚካል የጦር መሳሪያዎች የአላሳድ መንግስት እንዲያስወግድ ቀን ተቆርጦለታል፡፡ የምዕራባዊያኑ አካሄድ፤ ወድቆ የቆመውን እንደመጎተት ያለ ነው፡፡ ሳዳምንም እንዲሁ ነበር ያደረጉት፡፡ ከ80ኪ.ሜ በላይ የሚወነጨፉትን አልሳሙድ ሚሳይሎቹን እንዲያስወግድ ነገሩትና አስወገደ፡፡ ከዚያም፣ ወረሩት፡፡ ይህ ሶሪያም ላይ እንደሚደገም ቅንጣት ታክል ጥርጠሬ የለኝም፡፡ የኢትዮጵያና የኢትዮጵያውያን ታሪካዊ ጠላቶች አሳር መከራቸውን ሲበሉ በማየቴ ምንያህል እደለኛነት እንደሚሰማኝ ልሸሽገው አልዳዳም፡፡ ኢትዮጵያና ሰላም ወዳድ ኢትዮጵያውያን በነፃነታቸው ለዘላለም ትኑሩ! ጠላቶቻቸውም ኹሉ በሰፈሩት ቁና ይሠፈሩ!…..

የአንድነት ፓርቲ ቀጣይ እጩ ሊቃነመናብርት ተለይተው ታወቁ

የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት ፓርቲውን ለቀጣዮቹ 3አመታት በሊቀመንበርነት ለመምራት ከተወዳደሩት 5 ከፍተኛ አመራሮች ውስጥ 3ቱን ለመጨረሻው ዙር ውድድር እንዲያልፉ በዴሞክራሲያዊ መንገድ መርጧል፡፡ ፓርቲውን በሊቀመንበርነት ለመምራት የተወዳደሩት አቶ ትግስቱ አወሉ፣ ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው፣ አቶ ግርማ ሰይፉ፣ አቶ ሽመልስ ሀብቴ እና አቶ ተክሌ በቀለ ናቸው፡፡
ዛሬ የአንድነት ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት አባላት በሚስጥር ድምፅ አሰጣጥ ስርአት ባደረጉት ምርጫ 1ኛ.ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው 2ኛ.አቶ ተክሌ በቀለ 3ኛ.አቶ ግርማ ሰይፉ ለመጨረሻው ዙር ውድድር አልፈዋል፡፡
ለመጨረሻው ዙር ሳያልፉ የቀሩት አቶ ትግስቱ አወሉ እና አቶ ሽመልስ ሀብቴ ምርጫው ዴሞክራሲያዊ መሆኑን ተናግረው አንድነትን ለመምራት ከሚመረጠው ቀጣይ ሊቀመንበር ጋር ትግሉን ለማፋጠን እንደሚተጉ ለምክር ቤቱ ቃል ገብተዋል፡፡

ወላጆች ንበረቶቻቸውን ከዘራፊዎች ለማስጣል በሪያድ ከኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች ጋር እያደረጉ ያለው ትንቅንቅ ዛሬ ወደ ግጭት አመራ .

በወላጆች እና በሳውዲ አረቢያ የኢትዮጵያ በዲፕሎማቶች መሃከል ዛሬ ሴፕቴምበር 22 2013 ምሽት ተፈጥሮ የነበረው ግጭት ለግዜው ጋብ ቢልም መንግስት በጉዳዩ ጣልቃ ገብቶ የተማሪዎቹ ወላጆች በተደጋጋሚ ላቀረቡት ጥያቄ አስቸኳይ መላምት ካለፈላለገ ጉዳዩ የከፋ ሊሆን እንደሚችል የወላጆች ኮሚቴ አባላት ይገልጻሉ!
በተለይ ዛሬ ሴፕቴምበር 22/2013 ምሽት በሪያድ አለማቀፍ የኮሚኒቲ ት/ቤት ተማሪ ወላጆች ኮሚቴ የሳውዲ መንግስት በወጭ፡ሃገር ዘጎች ላይ ያወጣውን ህግ ተከትሎ በኤንባሲው የተመረጠው የት/ቤቱ ህገወጥ፡የቦርድ አስተዳደር «የመኖሪያ ፈቃድ አልተሞላም ፡ ፓስፖርት አልታደሰም ፡ ቦንድ አልገዛችሁም ፡ ወላጆቻችሁ የድምጻችን ይሰማ ደጋፊዎች ናቸው ……ወዘተ » በጣም አስዛኝ እና ግብረገብነት በጎደለው ሰንካል ምክንያት ከ 1ሺህ የሚበልጡ ተማሪዎችን ከትምህርት ገበታቸው ማፈናቀሉ ይታወሳል።
በመሆኑም የአያሌ ኢትዮጵያውያን ህጻናት በሰው ሃገር ከትምህርት ገበታቸው መፈናቀል የአብዛኛውን ወላጆች በልጆቻቸው ላይ ያላቸው ተስፋ እንዲጨልም አድርጓ። ይህንንም የተረዳው 11 አባላት ያሉት የት/ቤቱ የወላጆች ኮሚቴ ከ1 ሺህ የሚበልጥ የድጋፍ ፊርማ በማሰባሰብ ኤምባሲው በራሱ ስልጣን መርጦ ህገወጥ በሆነ መንገድ ያስቀመጠው የት/ቤቱ ቦርድ አዲስ የትምህርት ዘምን መጀመርን አስመክቶ ያወጣውን የአዲስ እና ነባር ተማሪዎች መመዝገቢያ ማመዘኛዎች ትክክለኝነት በመጠራጠር ኮሚቴው የሳውዲ ት/ሚኒስቴር መ/ቤት ድረስ በመሄድ ለማጣራት ባደረገው ሙከራ በኢትዮጵያ ኤምባሲ ዲፕሎማቶች በእጅ አዙር እንዳይ መዘገቡ ታግደው ከነበሩ 1ሺህ ኢትዮጵያውያን ህጻናት ውስጥ 8 መቶው የሳውዲ ት/ሚ ያወጣውን ህግ የሚያሞሉ መሆናቸውን በማረጋገጥ፡ ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ ኮሚቴው ማስቻሉን ተከትሎ ወላጆች በተጠቀሰው ቦርድ እና ከቦርዱ ጀርባ ሆነው በሪያድ እለም አቀፍ የኢትዮጵያ ኮሚኒት ት/ቤትን የመማር ማስተማር ሂደት እያመሰቃቀሉ ባሉ ወገኖች ዙሪያ ለመነጋገር ሴፕቴምበር 22 2013 የወላጅ ኮሚቴው በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አዳራሽ ስብሰባ ጠርቶ እንደ ነበር የወላጆች ኮሚቴ ተወካይ ይገልጻሉ ። ተወካዩም በማያያዝ ቀደም ብለው ስብሰባ ያደርጉባቸው የነበሩ ቦታዎች ወላጆች በግል በሚከራዮቸው አካባቢያቸው በሚገኙ የመዝናኛ ቦታዎች መሆኑንን ጠቀሰው በሪያድ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ሃላፊ የሆኑት አቶ ተመስገን ኡመር ይህ አዳራሽ እያለ ለምን ለድህነታችሁ አስተማማኝ፡ያልሆነ ቦታ ትሰበሰባላችሁ ከኤምባሲው እና ከኮሚኒቲው ርቃችሁ በድብቅ ስብሰባ ለምን ታደርጋላችሁ በሚል ቅን አስተሳሰብ ለወላጆ ኮሚቴው በሰጡት ሞራል እና ምክር ኮሚቴው ለእሁድ ቀን ሴፕቴምበር 22 2013 ከምሽቱ 7 ስዓት ጀምሮ ወላጆች በኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አዳራሽ፡ እንዲገኙ የስብሰባ ጥሪ በደብዳቤ እንደበተኑ ያወጋሉ።
እስከ ተጠቀሰው ቀን ድረስ ምንም አይነት ተቃውሞ ከኤንባሲው እንዳልነበረ የሚናገሩት የወላጅ ኮሚቴው ተወካይ በስበሰባው እለት ወላጆችን ለማስተናገድ ኮሚኒተው አካባቢ ወንበሮችን ስናስተካክል ውለን ለተለዩ ጉዳዩች ከግቢ ወጥተን ስንመለስ የግቢው በር ያለወትሮው በቁልፍ ተቆልፎ ጠበቀን። ጉዳዩን ለማጣራት ዘበኛውን በመስኮት ስንጠይቅ በአምባሳደር መሃመድ ሃሰን በተደገፈ ፌርማ በተጻፈ የደብዳቤ ተዕዛዝ መዘጋቱን ቢገልጽም በወቅቱ ጥሪ የተደረገላቸው ወላጆች ቁጥር እየጨመረ መምጣት አካቢው ተሽከርካሪ መተላለፊያ በመሆኑ ወላጆች ለአደጋ እንዳይዳረጉ ጠቅሰን በገዛ ቤታችን በር እንዲከፈትልን ብንማፀንም ዘበኛው ጉዳዩ ከአቅሙ በላይ ስለነበር ፈቃደኛ አልነበረም ብለዋል ። የኮሚኒቲው ሊቀመንበር አቶ ሙስጠፋ ሁሴን መጥተው በቁጣ የሚጉርመረመውን ወላጅ ለማረጋጋት ሙከራ በማድረግ የኮሚኒቲውን በር እንደሚከፍቱ እና ህዝቡ እንደሚገባ ቃል ገብተው ዲፕሎማቱን አነጋግሬ መጣሁ በለው ህዝቡን በር ላይ አቁመው በዛው መቀረታቸው አስነዋሪ እና አንድ የኮሚኒቲ ተወካይ ከሆነ አካል የሚጠበቅ አለመሆኑን ገልጸዋል።
ከሰአታት ቆይታ በሃላ አልፎ አልፎ አምባሳደር መሃመድ ሃሰንን ወክለው እንደሚሰሩ የሚነገርላቸው ዲፕሎማት አቶ ዘላለም እና ቀደም ሲል በአዳራሹ እንደ ዜጋ መገልገል « መሰብሰብ » መብታችን መሆኑንን ምክራቸውን ሲልግሱ የነብሩ የዲያስፖራው ሃላፊ አቶ ተመስገን ኡመር በወቅቱ ህዝቡን ለማነጋገር መጥተው እንደ ነበር ቢታወቅም የህዝቡ ስሜት ጥሩ አለምሆኑ መገድ ላይ እያሉ መርጃ ስለደረሳቸው እና በአንዳንድ ተእግስታቸው በተሞጠጠ ወላጆች በገዛ ቤታችን እንዴት እንከለከላለን በሚል ቁጣ እና ንዴት ሊፈጸምባቸው የሚችለውን እርምጃ በመስጋት በት/ቤቱ የጓሮ በር ድምጻቸውን አጥፈተው በመግባት ህዝቡ ከአካባቢው እስኪበትን እዛው ባሉበት ድምጻቸውን አጥፈተው ለመቆየት መገደዳቸውን የአይን ምስክሮች ገልጸዋል።
በመጨረሻ የወላጆች ኮሚቴው ወደፊት ተመሳሳይ የሆነ ስብሰባ እንደሚጠራ ጠቅሷ፡ህዝቡ እልህ ውስጥ፡ሳይገባ በሰከነ መንፈስ እና ህጋዊ እና ሰላማዊ በሆነ መንገድ አይን ባልገለጹ ሃገር ተረካቢ ታዳጊ ህጻናት ልጆቹ ላይ የተሰነዘረውን ጥቃት እና ንብረቱ የሆነውን በሪያድ አለም አቀፍ የኢትዮጵያ ኮሚኒት ት/ቤት ከዘራፊዎች ለማዳን እያደረገ ያለውን ትግል አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት በመገስጽ የኢትዮጵያ መንግስት ለጉዳዩ ትኩረት ስጥቶ አስቸኳይ የሆነ መፍትሄ እስካላበጀለት ድረስ በዲፕሎማቱ እና በተማሪ ወላጆች መሃከል የተፈጠረው ግጭት ወደ ከፋ ደረጃ እንደሚሸጋገር አበክረው አሳስበዋል።

መውጫ አበጅቶ መግቢያ የከለከለን አሳዳጁ ማን ነው? – ከግርማ ሠይፉ ማሩ

ከግርማ ሠይፉ ማሩ
Girma Siefuሀገራቸን ኢትዮጵያን ለቀው ለስደት የተዘጋጁት ዜጎችን ቁጥር መገመት አስቸጋሪ ቢሆንም በአንድ ወይም በሌላ ምክንያት መውጣት የቻሉት ግን ላለመመለስ ብዙ ምክንያቶች አሉዋቸው፡፡ ይህን የዜጎች (በተለይ የተማሩና ወጣቶች) ስደት ሀገራችንን ከፍተኛ ዋጋ እያስከፈላት እንደሆነ እና ወደፊትም ከፍተኛ ጉዳት እንደሚያስከትል ለማወቅ ሊቅ መሆን የሚያስፈልግ አይመሰለኝም፡፡ አሜሪካኖች በዲቪ እንኳን ሊወስዱት የሚፈልጉት ፊደል ቆጥሮ አንድ ነገር ሊያደርግላቸው የሚችለውን እንደሆነ እናውቃለን፡፡ ለዜጎች ስደት ምክንያቱ መንግሰት እንደሚለው ህገወጥ ደላሎች አይደሉም ይልቁንም የመንግሰት የተለያየ ፖሊሲ ውጤቶች ናቸው ብዬ ማሳየት ፈለኩኝ እና ይህን ፅሁፍ ጀመርኩ፡፡
የስራ ዋስትና በሀገራችን የተረጋገጠ አይደለም፡፡ ቀደም ሲል የመንግሰት ስራ ያልተመቸው ኢትዮጵያዊ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ገብቶ በሞያው ማገልገል አንድ የሚታይ ጠባብ አማራጭ ነበር፡፡ ይህ ጠባብ አማራጭ እንደሚታወቀው ከ1997 ምርጫ በኋላ ይህ “የኪራይ ሰብሳቢዎች ምሽግ እንዲፈርስ” በሚል በወጣ አዋጅ ጠባብ አማራጭነቱ ቀርቶዋል፡፡ የዚህ አማራጭ የተዘጋው ህጋዊ በሚመስል እና ለድሆች በማሰብ በሚል ነው፡፡ አዋጅ ቁጥር 621/2001 የበጎ አድራጎትና ማህበራት ምዝገባ አዋጅ እና ተከትለው የወጡትን መመሪያዎች ማየት በቂ ነው፡፡ ውጤቱ ግን ኢህአዴግ እንደሚያስበው የመንግሰት ተቀጣሪነት የሰለቻቸው ሰዎች ፀጥ ለጥ ብለው እንዲገዙ፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋሞች ውስጥም አንፃራዊ ነፃነት አግኝተው ይሰሩበት ከነበረበት ወደ መንገስት ተቋም በመምጣት የመንግሰትን ተቋምን አላሳደጉም፡፡በተቃራኒው የተገኘው ውጤት አቅም ያለው ሁሉ በአገኘው አጋጣሚ ሁሉ ሀገሩን ጥሎ ነፃነት ወደአለበት ምድር ሁሉ እየተሰደዱ ነው፡፡
የኪራይ ሰብሳቢ ምሽግ ለመናድ የተዘረጋው ወጥመድ በሀገራችን የሚገኙትን የመንግሰትም ሆነ መንግሰታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን በሰለጠነ የሰው ሀይል ከማሳጣት የዘለለ ፋይዳ አላመጣም፡፡ ያመጣው ጥቅም ግን ሳይጠቀስ መታለፍ የለበትም፡፡ መንግሰታዊ ባልሆኑ ተቋሞች የሚሰሩ ዜጎችም አንድ ቀን ውጭ የሚሄዱበት ዕድል እሰኪያገኙ ልኑርበት በሚል ባሉበት ዝም ብለዋል፡፡ አንድ በቅርቡ ያገኘኋት በቅርብ የማውቃት ልጅ ለምን ወደ ሀገር እንደማትመለስ ስጠይቃት አሁን የምትስራበት መሰሪያ ቤት አልተመቻትም፣ ከዚያ ወጥታ ሌላ ተመሳሳይ ቦታ ለመግባት ደግሞ አሁን ባለው ፖሊስ ሰራተኛ መቀነስ እንጂ መጨመር የብዙ መንግሰታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ፕሮግራም አካል አይደለም፡፡ ሰለዚህ አሁን ከምትኖርበት የባሰ ኑሮ ለመኖር ፈቃደኛ ስላልሆነች፤ “የሀገር ፍቅር የትም አይሄድም ነፃነት እና የስራ ዕድል ባለበት ብቆይ ይሻላል” ነው ያለችኝ፡፡ ሁለተኛ ዲግሪ በያዘችበት ሙያ ስራ ባታገኝም፤ አሁን የምትሰራው ስራ እንደተመቻት አጫውታኛለች፡፡ ይህ እንግዲህ አወጅ ቁጥር 621/2001 ያስገኘው ድል ነው፡፡ ይህችን ልጅ በፍፁም ህገወጥ ደላላ አላሳሳታትም፡፡ እርሷን እና መስሎቿን ያሳሳትው የመነግሰት የተሳሳተ የፖሊሲ አቅጣጫ ነው፡፡ የስራ ዋስትናን ማረጋገጥ የማይችል መንግስት ትክክለኛ የህዝብ ድምፅ የሚቆጠርበት የፖለቲካ ምዕዳር ቢኖር እንኳን ለተከታታይ አራት አይደለም አንድ ተጨማሪ ዙር ምርጫ ማሸነፍ የሚችልበት ዕድል አይሰጠውም፡፡ አሁንም መንግሰት ከጊዚያዊ የስልጣን ጥቅምና ፍላጎት ይልቅ ለዘላቂ ሀገራዊ ጥቅም ሲባል በዚህ ምክንያት ሀገር ጥለው የሚሰደዱትን ዜጎች ለመታደግ ይህን አዋጅ ሊያሻሽለው ይገባል፡፡ መንግሰታዊ ያልሆኑ ተቋማትም እሺ እያሉ ነፃነትን ሸጦ ከመኖር በቃን ብለው ድርጅት በመዝጋት ጭምር ተቃውሞ ሊያሰሙ ይገባል፡፡ ካላጎነበሳችሁ አትጫኑም ነው ያለው ማርቲን ሉተር ኪንግ፡፡

በሀገራችን የባለሞያ ስደት ልላው ምክንያት በቂ ክፍያ አለማግኘት እንደሆነ ይታመናል፡፡ በዚህ ምክንያት ከሚሰደዱት ዜጎች አብዛኞቹ የህክምና ባለሞያዎች እንደሆኑ ቢታወቅም በሌሎች መስኮቸም ይህ ችግር ጎልቶ ይታያል፡፡ እነዚህንም ዜጎች መንግሰት እንደሚለው ህገወጥ ደላሎች ያሳሳታቸው ሳይሆኑ መንግስት በሚከተለው ፖሊሲ ምክንያት በሞያቸው የድካማቸውን ያህል ስለማያገኙ፣ እንዲሁም በያዙት ሙያ በሌላ ቦታ የተሻለ ዕድል ስለሚያገኙ ጭምር ነው፡፡ ዘወትር የእኛ ሀገር የባለስልጣናት ደሞዝ ትንሽ ሰለሆነ እውነት የሚመስለው ብዙ ሰው አለ፡፡ ባለስልጣኖች ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ የሚያገኙት ደሞዝ (እዚህ አካባቢ ወ/ሮ አዜብ ትዝ እንደምትላችሁ ገመትኩ) በእርግጥ ትንሽ ነው፡፡ ደሞዝ የሚባለው ማለት ነው፡፡ ከዚህ ውጭ በተለያየ መንገድ የሚያገኙት ምንዳ ግን በጣም ብዙ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ለዚህም ዋነኛው ምሳሌ በቦርድ ሰብሳቢነት እና በውጭ ጉዞ የሚያገኙትን መጥቀስ ይቻላል፡፡ በውጭ ሄዶ መታከም፣ ነዳጅ፣ የመኖሪያ ቤት እና ሌሎች ብዙ ጥቅማ ጥቅሞችንም ማንሳት ይቻላል፡፡ ከዚህ አንፃር አንድ ባለሞያ ይህ ዕድል ሳይኖረው በወር ደሞዝ እንዲኖር ሲጠየቅ ጥያቄው የሀገር ፍቅር ሳይሆን የምንኩስና ይሆን እና ስደት አንድ አማራጭ ይሆናል፡፡ ከፍተኛ ሀብት ፈሶባቸው የሰለጠኑ ባለሞያዎች የተወሰነ የማጣሪያ ፈተና በማለፍ ብቻ ሌሎች ሀገሮችን ማገልገል አማራጭ እየሆነ ነው፡፡ አንድ በጥቁር አንበሳ የሚሰራ ሀኪም የነገረኝ ከካርድ ብቻ የሚሰበሰበው ገንዘብ ለሀኪሞች ደሞዝ ቢመደብ ሀኪሞች በደሞዝ ማነስ ምክንያት ከመልቀቅ ይድናሉ ነው የሚለው፡፡ በእውነት ለመናገር በየጤና ተቋሙ የሚመደቡ ካድሬዎች የሚፈጥሩት ጫና በዝቅተኛ ደሞዝ መቋቋም ግዴታ አይደለም፡፡

በነፃነት ለመስራት ያለመቻል በሀገራችን በመንግሰት መስሪያ ቤት ብቻ ሳይሆን በግል ተቋምም ቢሆን ዜጎች በነፃነት የሚሰሩበት የስራ ድባብ ባለመኖሩ አማራጭ ያለው ሁሉ ከሀገር ተሰዶ መኖርን አማራጭ ካደረገ ውሎ ሰንብቶዋል፡፡ ለኢህአዴግ ዳኝነት ቢሆን ህክምና ወይም ምሕንድስና አብዮታዊ ዲሞክራሲ አመለካከት ካልገባው ትርጉም ያለው ዕውቀት አይደለም፡፡ ለዚህ ነው ለኢህአዴግ አድረናል ብለው የነበሩ በአጋጣሚ ሁሉ የውጭ ሀገር ዕድል ሲያገኙ እየተንጠባጠቡ የሚቀሩት፡፡ በነገራችን ላይ በተደጋጋሚ ውጭ የሚመላለሱ እና ስልጣን ላይ ያሉ የገዢው ፓርቲ አባላት በጣት ከሚቆጠሩት በስተቀር አንድም ልጅ በቤታቸው የለም፡፡ ልጆቻቸው በሙሉ ውጭ ሀገር ላይመለሱ ሄደዋል፡፡ ይህ የባለስልጣኑ የነፃነት እጦት መገለጫ ነው፡፡ አንድ ቀን ምን እንደሚመጣ ያለማወቅ፡፡ ሁሌ በሀገራችን ይመጣል እያሉ የሚያሰቡት ሟርት ከመጣ ልጆቻቸውን እንዳይነካ በማሰብ የተደረገ ነው፡፡ አሁን በልማት ልናስመነድገው ነው የሚሉት ሀገር ለእነርሱ ልጆች ሳይሆን ለድሆች ልጆች ነው፡፡ ይህ በእውነት ደግነት ነው፡፡ ይህ ሁሉ ድካም ለሰው ልጅ ብሎ ስለሆነ፡፡ እኔ የምር የምላችሁ እነዚህ ባለስልጣናት በህይወት እያሉ ልጆቻቸው እንደሚያዝኑባቸው ጥርጥር የለኝም፡፡ የመንግሰቱ ኃይለማሪያም ልጆች ከሀገር ተሰደው በመኖራቸው ደስተኞች ሊሆኑ ይችላሉ ብዬ አላስብም፡፡ የማንም ባለስልጣን ልጅ ሀገሩን የሚናፍቅ እንዲሆን እኔ ፍላጎት የለኝም፡፡ ባለሀገር ልጆች እንዲኖሩን ሁላችንም ልጆቻችንን ለስደት ሳይሆን በሀገራችን በሚፈጠር ሀገራዊ ዕርቅ በነፃነት ሀገራቸው እንዲኖሩ ማበረታታ ያለብን ይመስለኛል፡፡ እባካችሁ ለንግግር እና ሀገራዊ መግባባት ለመፍጠር ጊዜ እንመድብ፤ ግንብና ግንባታ ይደረስበታል፡፡ “የሰላም እጆች ይዘርጉ የአዲስ ዓመት መልዕክቴ ነው”፡፡ የሶሪያ ዲሞክራሲና ሠላም ዕጦት ግንቡን ሁሉ ነው የበላው፣ እየበላውም ያለው፡፡

ሀገራችን ኢትዮጵያ ሀገር ለቆ ለመውጣት ብቻ ሳይሆን ለመግባት ፍላጎት ያለቸው እጅግ ብዙ ዜጎች አሉዋት፡፡ ዳሩ ምን ያደርጋል አሁን ያለው መንግስት እነዚህ በአንድ ወይም በሌላ መልክ ከሀገር ወጥተው የነበሩ ዜጎች (ዜግነትም ቀይረውም ቢሆን) አሁን እንዲመጡ የሚፈልገው ኪሳቸውን በዶላር ሞልተው ነፃነት ሲፈልጉ ደግሞ እዛው በለመዱበት ብቻ የሚል አቋም ይዞ ነው፡፡ ነፃነት በለመዱበት ሀገር ሆነውም ቢሆን ግን ገዢውን ፓርቲ በነፃነት መተቸት አይቻልም ከእነርሱ የሚጠበቀው የሚጠይቀውን ገንዘብ ሲጠየቁ መስጠት ብቻ ነው፡፡ የማያምኑበት ፖሊሲ እንዲፈፀም የእነርሱ ገንዘብ ማዋጣት ግድ ብቻ ሳይሆን ካላዋጡ ፀረ ልማት እና ለሀገር ጠላቶች የሚል ቅፅል ስም ሀቃቸው ይመስላል፡፡

በሰለጠኑበት ሙያ ለማገልገል የሚችሉበት ምቹ ሁኔታ ያለመኖር አንዱ ነው፡፡ በውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን በሰለጠኑበት ሞያ አገልግሎት መስጠት ቢፈልጉ አብዮታዊ ዲሞክራሲ መቀበል ይኖርባቸዋል፡፡ ይህም በቀጥታ የሚጠየቅ ሳይሆን የፈለጉ ሳይንቲስት ቢሆን መንግስትን መቃወም አይቻልም፡፡ ሞያቸውን ለሀገር ካለው ፋይዳ አንፃር ሳይሆን የሚመዘነው ለገዢው ፓርቲ ካለው የፕሮፓጋንዳ ጠቀሜታ አንፃር ነው፡፡ አንድ አንድ ባለሞያዎች ከዚህ አንፃር ትንሽ ቀደዳ ሳይኖር አይቀርም ብለው ወደ ሀገር ሲመጡ የመጀመሪያ ሰለባ የሚሆኑት በኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ወይም ኢቢኤስ ለሚባል የቴሌቪዥን ጣቢያ ነው (ይህ ጣቢያ በኢትዮጵያ የብሮድካስት ህግ መሰረት ህገ ወጥ ነው)፡፡ እነዚህ ዜጎች መስጠት የሚፈልጉትን ከመሰጠታቸው በተጨማሪ ገና እንደገቡ በሚከቧቸው አጫፋሪዎች ታጅበው ስለ ሀገሪቱ ዕድገት፣ ሰለ አለው ዲሞክራሲያዊ ስርዓት፣ ወዘተ ዲስኩር እንዲሰጡ በማድረግ ቅርቃር ውስጥ ይከቷቸዋል፡፡ ለዚህ ሁነኛ ምሳሌ የሚሆነው ኤርሚያስ አመልጋ ይመስለኛል፡፡ ሌሎችም ብዙ አሉ፡፡

አሁን በሀገራችን ያለውን ሁኔታ በተግባር ለመፈተን ብለው የፖለቲካ ብቻ ሳይሆን የኤኮኖሚ ምዕዳሩም ጠባብ እንደሆነ ብቻ ሳይሆን በፍፁም እንደማያንቀሳቅስ ተረድተው ከጫወታ የወጡትን ዜጎች ቤቱ ይቁጠራቸው በማለት የሚታለፍ አይደለም፡፡ እነዚህ ዜጎች በውጭ ደክመው ያገኙት ገንዘብ እንደዋዛ ከስረው ከጫወታ ሲወጡ ሌሎች መምጣት ለሚፈልጉት ምን መልዕክት እንዳለው መረዳት ተገቢ ነው፡፡ ይህን ፅሁፍ ስፅፍ ኤርሚያስ አመልጋ ወደ ሀገር የመኖሪያ ፈቃድ መልሶ ሲመጣ እና ዛሬ ምን እንደሚሰማው ጥያቄ ማቅረብ ተገቢ ይመስለኛል፡፡ በዚህ ጉዳይ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እንዲሁም በሀገር ውስጥ ያሉ ዜጎች በደረሰባቸው ጉዳት የኤርሚያስን ስም መስማት የሚያስጠላቸው ቢሆንም ይህ ለምን ሆነ ብለው ከስሜት በወጣ እርጋታ ሊያስቡት እንደሚገባ ይሰማኛል፡፡ የኦላንድ ካር ባለቤት የነበረው ኢንጂነር ታደሰም ቢሆን ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የሚሆን ይመስለኛል፡፡ እሲኪ ድምፃችሁን አሰሙና መንግሰት ምን ደገፋችሁ ምንስ አደረጋችሁ፡፡ እንግዲ የበሰበሰ ዝናብ አይፈራም ይባል የለ፡፡

ደቡቡ ሱዳን የምትባል አዲስ ጎረቤታችን ብዙ ኢትዮጵያዊያ ለስራ እንደሚሄዱ አውቃለሁ፡፡ አዲሷ ሀገር እንኳን አሁን ኢትዮጵያዊያ ወደ ሀገሯ ሲገቡ እንደማይቀሩ ለማረጋገጥ የባንክ አካውንት መጠየቅ ጀምራለች፡፡ እንደ አጋጣሚ እኔም ሄጄ ይህችን ጎስቋላ ሀገር አይቻታለሁ፡፡ ብዙ ኢትዮጵያዊያ እዚህች ሀገር ለምን ተሰደው ይሄዳሉ? ለሚለው ጥያቄ ሁሌ የምሰጠው መልስ ምንም ነገር ስለሌለ ሁሉ ነገር ስራ ነው በማለት ነው፡፡ ብዙ ትርፍ በአጭር ጊዜ ለማግኘት የፈለገ ከነስጋቱ ሄዶ በአጭር ጊዜ ሊከብር ይችላል፡፡ ይህ በኢህአዴግ ሰፈር “ኪራይ ሰብሰቢ” ያሰብላልና ማንም ብቅ አይልም፡፡

ሌሎች ሀገሮችን በተለይ አሜሪካን እና አውሮፓን ሳይ ቅናት ያድርብኛል ብዙ ስራ እንደሚቀረን ይስማኛል፡፡ በተነፃፃሪም ያለው ነፃነትና ዕድል ብዙ ሰው ሊያማልል እንደሚችል ይገባኛል፡፡ በተለይ ብራዚሊያ የምትባል ከተማ እና ብራዚል የሚባል ሀገር ካየሁ በኋላ ኢህአዴግ 22 ዓመት እንዳባከነ እና የብራዚሊያን ያህል 5 በመቶ እንዳልሰራ እርግጠኛ ነኝ፡፡ ብራዚሊያ የምትባለው የብራዚል ዋና ከተማ ከተመሰረተች ከ50 ዓመት ብዙ አትዘልም፡፡ ኢህአዴግ ባለፉት 22 ዓመት ግማሹን መስራት ይኖርበት ነበር፡፡ ለዚህም በውጭ የሚኖረ ኢትዮጵያዊያን እውቀትና ገንዘብ ብዙ ሚና ሊኖረው ይችል ነበር የሚል እምነት አለኝ፡፡ ማስተባበር የሚችል የፖለቲካ ሰርዓት መዘርጋት ቢቻል፡፡ በቅርቡ የአሜሪካው ፕሬዝዳን ባራክ ኦባማ ብራዚልን እንዲህ ብለው ገልፀዋታል “ከአንባገነን ስርዓት፣ በሰላም ወደ ዲሞክራቲክ ስርዓት የተሸጋገረች” እውነት ነው፡፡ የኢትዮጵያ ህገ መንግሰት በተወሰነ ማሻሻያ የብራዚል ዓይነት ዲሞክራሲ ሊያመጣ እንደሚችል እኔም ይሰማኛል፡፡ የብራዚል ህገ መንግሰት እንደ እኛው ህገ መንግሰት ፓርላሜንተሪ ነበር፡፡ መሪያቸውን በቀጥታ አይመርጡም ነበር፡፡ ህገ መንግስቱን አሻሽለው ብራዚላዊያን ዛሬ ማን እንደሚመራቸው በቀጥታ ይመርጣሉ፡፡ እኛም ሲናፍቀን ይኖራል ማለት አይደለም፡፡ አንድ ቀን ዘሩ/ጎሳው ማን ነው? ሳንል ለኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊያን ባለው ራዕይ መሪያችንን እንመርጣለን፡፡ ተሰፋ አለኝ፡፡

የተነሳሁበት ሀገር ለቆ የመሰደድ ምንጭ የሚያማልል ነፃነትና ዕድል ያለባቸው የአሜሪካና አውሮፓ ከተሞች ብቻ ሳይሆኑ ጎሰቋላዋ ደቡብ ሱዳን ጭምር ነች እያልኩ ነው፡፡ ኢትዮጵያዊያን በዚህም በዚያም ሀገራቸው ስትገፋቸው ለምቾት ብቻ ሳይሆን ችግርም ለመጋፈጥ በመወሰኝ በረሃና ውቅያኖስ አቋርጠው ይሰደዳሉ፡፡ መንግሰት ግን የችግሩ ምንጭ ህገ ወጥ ደላሎች ናቸው እያለ ትክክለኛ መፍተሔ ለመሻት ዝግጁ የሆነ አይመስልም፡፡ አሁንም ችግሩን ከስሩ ማየት ተገቢ ነው የሚል መልዕክት ለማስተላለፍ ነው ጊዜ ወስደን ሃሳባችንን የምናካፍለው፡፡

አንድ እናት ለፆም መፈሰጊያ ምግብ እያዘገጁ ሳለ መፈሰጊያ ሠዓት ሳይደርስ ጨው ለመቅመስ ብለው ቀመሱ፣ ፆም ሲያዝም እንዲሁ የተረፈው እንዳይደፋ ብለው ፆም ገደፉ፡፡ ደግነቱ ይህን ለንስሀ አባታቸው በሀቅ ሲናገሩ አንቺ ሴት ፆሙን እንዳይገባ እንዳይወጣ ከለከልሽው አሏቸው ይባላል፡፡ የእኛም መንግሰት ዜጎች በሀገር እንዳይቆዮ እና ወደ ሀገር እንዳይመለሱ ተግቶ እየሰራ ነው፡፡ ችግሩ ይህን ግልፅ አድርጎ የሚነግረው የንሰሃ አባት ያጣ ይመስለኛል፡፡ በእኔ እምነት የዚህ ድርጊት ጥቅም ጊዚያዊ የስልጣን ፍላጎት ብሎም ለግል ደህንንት ካለ ሰጋት ብቻ የሚመነጭ ነው፡፡ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር (እርሳቸው ከልባቸው ከሆነ የአሁኖቹም ሌጋሲ ማሰቀጠል ከፈለጉ) ይሉ እንደ ነበረው ሀገር ማለት ሰዉ እንጂ ጋራና ሽንተረር ብቻ አይደለም፡፡ ባለሀገር ሊሆን የሚገባውን ትውልድ እያባረሩ (የእራሳቸውን ልጆች ጨምሮ)፣ ሌሎች ያባረሯቸውም እንዳይገቡ በሩን ጥርቅም አርገው ዘግተው ሀገር ማለት ሰው ነው የሚለው አይገባኝም፡፡ በቅርቡ እንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ በመብራት ሀይል አዳራሽ በጠራው የህዝብዊ ስብሰባ ላይ ሀብታሙ አያሌው የሚባል ወጣት “ሀገር ማለት ልጄ” የሚል የአንድ እውቅ ገጣሚ ግጥም በሰሜት አንብቦ አስለቅሶናል፡፡ ሀገር ማለት ልጄ ለልጆች የሚተላለፍ ታሪክ ያለው ሲሆን ነው ልጄ፡፡

በሀገራችን በነፃነት ለመስራት ያለመቻል ያቀረበልን አማራጭ ከገዢው ፓርቲ ጋር ተናንቆ ለውጥ እንዲያመጣ መግፋት ወይም ሀገር ለቆ የመስራት ነፃነት እና ዕድል ወደአለበት መሰደድ ነው፡፡ ምርጫው የግል ቢሆንም መንግሰት ግን ዜጎች በዚህን ያህል ደረጃ ለስደት ሲዘጋጁ አሳዳጅ ሆኖ መገኘቱ ሊያሳስበው እና መፍትሔ ሊፈልግለት ይገባል፡፡ ይህ በምንም መመዘኛ “የኒዎሊብራል”፣ የኪራይ ሰብሰቢ፣ ወይም የህገ ወጥ ደላሎች ስራ አይደለም፡፡ መንግሰት የሚከተለው የልማት አቅጣጫ ዜጎችን የሚያገል እና የፓርቲ ደጋፊዎችና ጥቂት የሚባሉ ለገዢው ፓርቲ ለማጎብደድ የቆረጦ ዜጎች ብቻ ተጠቃሚ የሚያደርግ ሰለሆነ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ብዙ የሚሰራባት ሀገር ነች፡፡ እንደ ደቡብ ሱዳን ባንሆንም ምንም ከሚባለው ብዙ ከፍ የማንል ሁሉ ነገር ሰራ ሊሆን የሚችልባት ሀገር ነች፡፡ ይህችን ሀገር በጋራ ለማልማት መነሳት ይኖርብናል፡፡ ይህ የፖለቲካ ሹመት ጥያቄ አይደለም፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ዜጎች ሳይሸማቀቁ መሪዎቻቸውን የሚመርጡበት የፖለቲካ ምዕዳር መፍጠር ብቻ ነው፡፡ ለዚህም መተማመን እና ሀገራዊ መግባባት ማሰፈን ይቅር ባይነት በሁሉም በኩል የግድ ይላል፡፡
ይህ ካልሆነ ግን ወደፊት ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር በውጭ የሚኖሩ የነበሩ በእደሜያቸው የመጨረሻ ዘመንም ቢሆን በሀገራቸው ለመኖረ የቆረጡ እንዲሁም የትም መሄጃ አጥተው በሀገር የቀሩ የሰድተኛ ወጣቶች ወላጆች ሁሉም የሚያመርቱ ሳይሆን ጡረተኞች ሀገር እንዳትሆን ሰጋት አለኝ፡፡ ይህ ከስጋትም ያለፈ እውነት ነው፡፡ አንድ ዘመዴ ያለችኝ እዚህ ጋ መጥቀስ ተገቢ ነው፡፡ “ምርታማ ዕድሜን ውጭ አሰለፉ ለጡረታ ሀገር ከመሄድ የከፋ በደል የለም ነው” ያለችው በበዳይነት ሰሜት፡፡

ቸር ይግጠመን አዲስ ዓመት የመነጋገሪያ የመግባቢያ ዘመን እንዲሆን ሁላችንም የበኩላችንን መወጣት ይኖርብናል፡፡ ነፃነታችን በእጃችን ይዘን የሌሎችን ነፃነት እናክብር፡፡ ፈጣሪ ይርዳን፡፡ አሜን!!!!

Saturday, September 21, 2013

የግል ሐኪምዎ የሆነው ሙዝ!

የግል ሐኪምዎ የሆነው ሙዝ!
በስትሮክ የመሞት አደጋን ከ50-60 በመቶ ለመቀነስ ያስችላል
ለስኳር ህመምና ለደም ማነስ ሙዝን መመገብ ይመከራል
በኢትዮጵያ እንደተገኘ የሚነገርለትና በዓለማችን በስፋት እየተመረተ ለምግብነት የሚውለው ሙዝ እጅግ በርካታ ጠቀሜታዎች አሉት፡፡ ሙዝ ከምግብ ይዘቱ በተጨማሪ ለተለያዩ በሽታዎች ፈውስ ሊያስገኙ የሚችሉ ንጥረ ነገሮችንም አካቶ ይዟል። እነዚህ ንጥረነገሮች ለበርካታ በሽታዎች ፈውስ ከመሆናቸውም በላይ፣ በሽታው ከመከሰቱም በፊት ለመከላከል የሚያስችለንን አቅም ያጐናጽፉናል፡፡ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በጠቅላላ ህክምና ክፍል ሐኪም የሆኑት ዶ/ር ታዬ አለማየሁ እንደሚናገሩት፤ ሙዝ በስትሮክ ምክንያት ሊከሰት የሚችለውን ሞት በግማሽ መቀነስ ይችላል፡፡

ሙዝ በውስጡ የካርቦሃይድሬት ንጥረነገሮችን የያዘ በመሆኑ ከፍተኛ ሃይል እንድናገኝ ይረዳናል። ሁለት ሙዝ በልተን በምናገኘው ሃይል ለዘጠና ደቂቃ አድካሚ የጉልበት ሥራዎችን መሥራት እንደምንችል ዶ/ር ታዬ ይናገራሉ፡፡
ብዙዎቻችን ሙዝን ለምግብነት በማዋል ለሰውነታችን ሃይልና ሙቀት ለማግኘት እንደምንችል ከማወቅ የዘለለ ነገር አስበን አናውቅም፡፡ ነገር ግን ሙዝ በውስጡ የያዛቸው ተፈጥሮአዊ የስኳር ወይም የጣፋጭ ምንጭ የሆኑት ግሉኮስ፣ ስክሮስ፣ እና ፍሩክቶስ የተባሉት ንጥረነገራት ከሙዝ የፋይበር (የቃጫነት) ተፈጥሮ ጋር ተዳምረው መጠነሰፊ ጠቀሜታዎችን ይሰጣሉ። ከበርካታ የሙዝ ጠቀሜታዎች መካከል ጥቂቶቹን ከዚህ እንደሚከተለው ለማየት እንሞክራለን፡፡
1. ለአእምሮ እድገት
ሙዝ በውስጡ ከፍተኛ የፖታሺየም ንጥረነገርን ይዟል፡፡ ይህም ንጥረ ነገር የአንጐልን የሥራ ብቃት ለማሻሻል እና ለማሳደግ እንዲሁም ንቁና ጤናማ አዕምሮ እንዲኖረን በማድረግ ረገድ ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው፡፡
2. ለስትሮክ
በሙዝ ውስጥ ያለው ፖታሺየም፣ የደም ሥርዓትን በማስተካከል ባልታሰበ ሁኔታና በድንገት የሚከሰተውን የስትሮክ ችግር ለመከላከል ያግዛል። ሙዝ በሰው ልጆች የአመጋገብ ሥርዓት ውስጥ ተካቶ ዘወትር ለምግብነት የሚውል ከሆነ፣ በስትሮክ ምክንያት የሚመጣውን ድንገተኛ ሞትና የአካል ጉዳት ከ50-60 በመቶ ለመቀነስ ያስችላል፡፡
3. ለደም ግፊት
ሙዝ በተፈጥሮው በውስጡ የሚይዘው ዝቅተኛ የጨው መጠን በመሆኑ የደም ግፊትን ለማረጋጋት ይረዳል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በውስጡ ያለው ፖታሺየም የደም ግፊትን ለማስተካከልና በግፊት ሳቢያ የሚከሰቱ ከባድ የጤና ችግሮችን ለመከላከል ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው፡፡
4. ለጨጓራ ህመም
አብዛኛዎቻችን ሙዝ ከበድ ያለ ምግብ እንደሆነ በማሰብ፣ ሙዝ የጨጓራ ህመማችንን እንደሚያባብስብን ስንናገር እንደመጣለን፡፡ ይሁን እንጂ ሙዝ ለጨጓራ ችግሮች ሁነኛ መፍትሔ ነው። ሙዝ በባህርይው በጣም ለስላሳ በመሆኑ በጨጓራ ላይ መጨናነቅን የማይፈጥር ሲሆን የጨጓራ አካባቢን በመሸፈን፣ የጨጓራ ውስጥ አሲድን በማስተካከልና በማመጣጠን የጨጓራ ቁስለት እንዳይፈጠር ለማድረግ ያስችላል፡፡
5. ለድብርት
ሙዝ በውስጡ የሚይዘውና ትራይፕቶፋን የተባለው ንጥረ ነገር በሰውነታችን ውስጥ ሴሮቶኒን የባለ ሆርሞን እንዲፈጠር ያደርጋል፡፡
ይህ ሆርሞን አይነተኛ ተግባሩ ሰውነታችንን ከድካምና ከድብርት በማላቀቅ ወደተሻለ ስሜት ውስጥ እንድንገባ ማድረግ ነው፡፡
6. ለሆድ ድርቀት
በሙዝ ውስጥ የሚገኘው ፋይበር ለምግብ መፍጨት ሥርዓታችን ከፍተኛ ጠቀሜታን ይሰጣል፡፡ የምግብ መፍጨት ሥርዓትን የሚያከናውኑት የሰውነታችን ክፍሎች በቂ የውሃ መጠን እንዲኖራቸው በማድረግ ሆድ ድርቀትን ይከላከላል፡፡ አንጀት የተለሳለሰ እንዲሆን በማድረግ ከሰውነታችን መውጣት የሚገባቸው አላስፈላጊ ነገሮች (ቆሻሻዎች) እንዲወገዱ ለማድረግ ይረዳል፡፡
7. ለስኳር ህመም
ሙዝ በውስጡ ከፍተኛ ቫይታሚን B6 የያዘ ነው። ይህም በደም ውስጥ የሚኖረውን ከፍተኛ የስኳር መጠን እንዲቀንስ በማድረግ፣ በሰውነታችን ውስጥ የሚገኘውን የስኳር መጠን ለመቆጣጠር ያስችለናል፡፡ ከስኳር መብዛት ጋር ተያይዞ የሚከሰተውን የጠዋት ህመምንም ያስቀራል፡፡
8. ሙዝና ደም ማነስ
በሙዝ ውስጥ የሚገኘው የብረት ማዕድን ጠቀሜታው በደማችን ውስጥ ከፍተኛ መጠን ያለው የሔሞግሎቢን ምርት እንዲኖር ማድረግ ነው፡፡ ይህም በሔሞግሎቢን እጥረት ሳቢያ የሚከሰተውን የደም ማነስ እንዳይከሰት ያደርጋል፡፡
9. ሙዝ ለስካር
ሙዝ ከወተትና ከማር ጋር ተደባልቆ ለምግብነት ሲውል በከፍተኛ መጠጥ ወይም በስካር ሳቢያ የሚከሰትን ሃንግኦቨር (ያደረ ድምር) በቀላሉ ያስወግዳል፡፡ በመጠጥ ሳቢያ የተጐዳን ሰውነት እንዲነቃቃና ብርታት እንዲያገኝ በማድረግ ረገድም ሙዝ ከፍተኛ ሚናን ይጫወታል፡፡ የሲጋራ እና መሰል ሱሶች ተጠቂ የሆኑ ሰዎች ሱሱን ለማቆም እንዲችሉ ሙዝ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋል፡፡
10. ለሞቃታማ አየር
በሞቃታማ የአየር ንብረት ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች ሙዝን ቢመገቡ ሰውነታቸው ሙቀቱን እንዲቋቋም በማድረግ፣ የተረጋጋና የተስተካከለ የሰውነት ሙቀት እንዲኖረን ያደርገናል፡፡
11. የሙዝ ተጨማሪ ጠቀሜታዎች
በወባ ትንኝ የተነደፈ ሰው ወይንም በማንኛውም ተናካሽ ወይም ተናዳፊ ነፍሳት የተነደፈ (የተነከሰ) ሰው በሙዝ ልጣጭ የውስጠኛው ክፍል የተነደፈበትን (የተነከሰበትን) ቦታ በደንብ በማሸት እብጠቱን መቀነስ ይችላል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ንድፍያው (ንክሻው) የፈጠረበትን የማቃጠልና የመለብለብ ስሜት ለማስወገድ ይችላል፡፡ ጫማዎን ከጠረጉና ቆሻሻውን ካስወገዱ በኋላ በሙዝ ልጣጭ ቢወለውሉት ጫማዎ እንደመስታወት ያበራልዎታል።
ፍሪጅዎ መጥፎ ጠረን (ሽታ) ካመጣብዎ አንድ ሁለት ሙዞችን ያስቀምጡበት፡፡ የፍሪጅዎ ጠረን በቅጽበት ይቀየራል፡፡
ሰውነትዎ በድካም ወይም በህመም ከተጐዳና የምግብ ፍላጐት ከሌለዎ አንድ ሙዝ እንደምንም ይመገቡ፡፡ ሰውነትዎ ሲበረታና የምግብ ፍላጐትዎ ሲጨምር ይታወቅዎታል፡፡
በአጠቃላይ ሁላችንም እንደቀላል የምናየውና ብዙም ትኩረት የማንሰጠው ሙዝ ለከፍተኛ የጤና ችግር የሚዳርጉንን በሽታዎች ለመከላከልና ለማስወገድ ይረዳናል፡፡
ታዲያ ይህን የግል ሐኪምዎ የሆነ ፈዋሽ ፍሬ በፍሪጅ ውስጥ ከተው አያበላሹት፡፡ ንፋስ ያለበት ያልታመቀ አየር ለሙዝ የሚስማማ ነውና - በዚያ ያኑሩት፡፡

ሕይወቱ የተቃወሰው የሐረር ሰው በአሜሪካ(ከኢየሩሳሌም አርአያ)


መሓሙድ ይባላል፤ ተወልዶ ያደገው ሐረር ነው። እድሜው 52 ሲሆን አሜሪካ መኖር ከጀመረ 30 አመት እንደሞላው ይናገራል። የ27 እና 23 አመት ወጣት ልጆች አሉት። የራሳቸውን ኑሮ ነው የሚኖሩት። በዲሲ ጎዳና አንድ ጥግ ስር ኩርምት እንዳለ ያገኘሁት መሓሙድ፣ ሁኔታውን በማየት አሳዛኝ ሕይወት ውስጥ መሆኑን በቀላሉ መረዳት ይቻላል። ከአንደበቱ የሚወጡት ቃላት አፍ ከማስከፈታቸው በተጨማሪ ጠለቅ ያለ መልክት ያዘሉ ናቸው። መሓሙድ ስለገጠመው ችግር እንዲህ አለኝ፤ «..ከወጣትነቴ ጀምሮ ከማውቃት፣ የቀዬ (ሐረር) ፍቅረኛዬ ጋር ነበር ወደ አሜሪካ የመጣነው። ከእርሷ በቀር ሌላ ሴት በጭራሽ አላውቅም። በፍቅር የአብሮነት ትዳር ዘመን ለሰላሳ አመታት ኖረናል። የነበረን ፍቅር በቃላት አይገለፅም!!» …አንገቱን አቀርቅሮ ለደቂቃዎች ዝም አለ፤ በሃዘን ስሜት ተውጦ ቀጠለ፥ «.. ከስድስት ወር በፊት ድንገት ታመመችና ሆስፒታል ገባች። በተኛች በሶስተኛው ቀን ጠዋት ሆስፒታል ስደርስ ዶክተሩ በጣም አዝኖ መሞትዋን ነገረኝ። የምናገረው ጠፋኝ፤ “ዶ/ር ልቋቋመው የማልችለውን ነገር ነው እየነገርከኝ ያለኸው፤ እባክህ ውሸት ነው በለኝ?..” ብዬ እግሩ ስር ወድቄ እየተንሰቀሰቅኩ ለመንኩት። …ግን የሚለውጥ ነገር አልነበረም። የ30 አመት ፍቅሬ በዛ መልኩ ጥላኝ ሄደች። አላህ የጀነት ሰው ይበላት።…» አለኝ። መሓሙድ ከዛ በኋላ ሕይወቱ እንደተቃወሰ ይናገራል። እንዲህም ይላል፥ « የምትወደውን ማጣት እጅግ ከባድ ነው። ዛሬ ብወድቅም እነሳለሁ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ!! …የምትሞት እንኳ ከሆነ ከንፈርህን ጥረግ፤ ..ወደታች እንዳትወድቅ የምትሄድበትን መንገድ እወቅ።..» ..መሓሙድን ተሰናብቼው መንገዴን ስቀጥል.. “ውስጠ ወይራ” ቃላቱን እያሰላሰልኩ ነበር።
( መሓሙድ ይኸውላችሁ…)

Gov’t rents 500,000 br/month mansion for outgoing president


By Muluken Yewondwossen   

The Office of the President is in the process of leasing a mansion for the outgoing president Girma Woldegiorgis with a monthly rate of 500,000 birr, Capital learnt.

Reliable sources indicated that the presidential office has already finalized the proper documentation process at the head office of the Documentation and Authentication Registration Office (DARO) early this week with Elias Arega, who was indicated as the owner of the house selected for the outgoing president.
Sources claimed that the house is fully equipped with the necessary amenities that suit an outgoing president. The deal also mentioned every goods that will be rented in detail.
Sources did not mention about the location of the residential house but they confirmed that it is in Addis Ababa.
The ‘Proclamation No. 255/2001 Administration of the President of the Federal Democratic Republic of Ethiopia’ states that the government have to deliver up-to-the standard residential house and other facilities for the outgoing head of state. The other proclamation issued in September 2009 stated that the government will provide benefits for outgoing head of state, heads of government and other top government officials.
Based on that the Office of the President, which is commonly known as ‘Palace Administration’ is now in the process of renting a residential house for president Girma, who will be completing his two, six-year terms.
The Office of the President has confirmed that it is assessing houses that are worth for an outgoing president.
“The proclamation states that an outgoing government official has to get full benefits for their service during the rest of their life. Due to this fact we are looking for a proper house that suits president Girma, who will step-down from his position in the beginning of October,”  Gebru Abraha, Public Relation and Communication Affairs Head of the Office of the President told Capital.
“We have been assessing about five houses in different parts of the city to select the one that meets the standard” Gebru added. “We did not come to any final decision but in the coming week we will finalise the process.”.
However the head confirmed that the house of Elias Arega is one of the short listed places.
Officials at DARO declined to comment about the issue saying that it is the secret between the two parities.
President Girma, who is also popular on his environmental activity, has severed for the last 12 years. According to the country’s constitution the president shall not be on the position for more than two terms or over 12 years. He is the first president that managed to complete two terms after the constitution was ratified. The first president Negaso Gidada (PhD) only served one term and resigned in 2001.
According to the proclamation number 653/2009 under article ‘Rights and Benefits of Outgoing Heads of State and Government, Senior Government Officials, Members of Parliament and Judges Proclamation’ an outgoing President, Prime Minister or Deputy Prime Minister shall be provided with a residential house having four-to-five bedrooms, the administrative costs of which, including remunerations of housekeeping staff, shall be covered by the government.
The proclamation also states that that an outgoing President, Prime Minister or Deputy Prime Minister and his family shall get local and overseas medical services at the expense of the Government.
“An outgoing President, Prime Minister or Deputy Prime Minister shall be provided by the government with three high standard transport vehicles,” the 2009 proclamation also states.

ኦሮማይ፣ ትግሉ በሚቻለውና በማንኛውም መንገድ!

ከቴዎድሮስ ሓይሌ (tadyha@gmail.com)
ሠሞኑን የግንቦት ሰባት ዋና ፀሐፊ የሆኑት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ስለ ኤርትራ ቆይታቸውና ስለድርጅታቸው ቀጣይ የትግል እንቅስቃሴ ሠፊ ገለጻና ማብራሪያ በኢሣት ቴሌቪዠን ከሠጡ ወዲህ የዘረኛው የትግሬ ነጻ አውጪ ግንባር ደጋፊ የሆኑት መርገማዊ ልሳኖች( አይጋ ፎረም ፤ ትግራይ ኦላይንና አውራንባ ታይምስ) እና አንዳንድ ተንበርካኪ የመንደር ሬድዮኖች ሰፊ የውግዘትና የህዝብን መንፈስ ያሸብርልናል በተቃዋሚዎችም ላይ ጥርጣሬ ይዘራልናል በሚል ደካማ ግንዛቤ እያካሄዱ ካለው አሰልቺና ኋላቀር ፕሮፓጋንዳ እጅግ ተጋኖ እየቀረበ ያለው ከሻብያ ጋር አብሮ መስራት ታላቅ የሃገር ክህደት ስለመሆኑ እፍረት የለሽ ኡኡታ በማሰማት ላይ ይገኛሉ።Ato Andargachew Tsige, Ginbot 7
ይህንን ጽሑፍ እንድጽፍም ያነሳሳኝ ይህ የወያኔ በቀቀኖች ልቅ ያጣ የፀረ ሻብያ ውትወታ ወያኔ የምትባለው የጠባብ ዘረኞች ቡድን ለዚህ ዛሬ ለደረሰችበት የዘረፋና የልዕልና ደረጃ የበቃችው ከቶ በማን ትከሻ ሆነና ነው ። ዛሬ ሌሎች ኢትዮጽያውያን ወደ ኤርትራ ስለሄዱ ይህ ሁሉ ውንጀላ ደጋፊ ተብዬቹ የሚነዙት ወያኔ በሻብያ ሁለገብ ድጋፍ የማቴሪያል የትጥቅ የዕቅድና የሃሳብ መመሪያ ውጪ እንኳን ሚኒሊክ ቤተመንግስት ልትደርስ ቀርቶ ተከዜንም ባልተሻገረች ነበር።በአንድ ወቅት የኤርትራው መከላከያ ሚንስትር ጀነራል ስብሃት ኤፍሬም ስለ ወያኔዎቹ ያለውን እጅግ የወረደ ንቀት የገለጸበትን አባባል እንዳስታውስ አሰገደደኝ ‘’እኛ ከነጀነራል ደምሴ ቡልቱና ከነጀነራል ረጋሳ ጅማ ጋር በመዋጋታችን ኩራት‘’ የሚሰማን በመሆኑ ከነዚህ የፍየል እረኛ ወያኔዎች ጋር ፈጽሞ ለንጽጽር የማይቀርቡ እጃቸውን ይዘን ለዚህ ያደረስናቸው እኛነን ሲል ነበር ከአመታት በፊት የተናገረው። ወያኔዎች በሻብያ የበላይ ሹማምንት ብቻ ሳይሆን በተራው ተጋደልቲ ጭምር የሚናቁና እንደ ሻብያ አገልጋይ የሚታዩ ስለመሆናቸው ከሁለት አስዕርተ አመታት በኋላ እንኳ አለመለወጡን በረባው ባረባውም በባነኑ ቁጥር የሻብያ ስም እንደሚያስበረግጋቸው ዘወትር ከአፋቸው አለመጥፋቱን የምናስተውለው ሲሆን የሰሞኑ ደግሞ ተባብሶ የሚታየው ጫጫታ አንዱ የወያኔዎች የፍርሃት ማሳያ ይመስለኛል።
የወያኔ መሪዎች የትግራይን ገበሬ ልጆች በግዴታ ለሻብያ አሰልፈው እያዘመቱ ፈንጅ ማምከኛና በማስደረግ የፈጸሙት የሎሌነት አሳፋሪ ገሃድ እየወጣ ባለበት በአሁኑ ወቅት አበው በቆማጣ ቤት አንድ ጣት ብርቅ ነው እንዲሉ እሱ ብቻ ሕልመኛ እሱ ብቻ ባለራዕይ የነበረውና በሞት ተለይቶ እንኳ ወሬው የገነነለት መለስ ዜናዊ እንዲህ ለራሱ የሚያሸረግድ አድርባይ የሎሌ መንጋ ትቶ እንደሄደ ትላንት እርሱም ለሻብያ ካድሬዎች ይንበረከክ እንደነበረ ታሪኩን የሚያውቁት ሲመሰክሩ ቆይተዋል በተለይም ወያኔዎች ከሻብያ ጫማ ስር ለመዋላቸው የሚቀርብባቸው ማስረጃ የኢትዮጽያን ተፈጥሯዊ የባህር በር አሣልፈው ከመስጠት አልፈው የኤርትራ ነጋዴዎች የጅማን ቡና የለገደንቢን ወርቅ ከማህል ሃገር በብር እየገዙ ለውጭ ገበያ በዶላር ያቀርቡ የነበረበትን ሁኔታ አንድ እግር ቡና የማታብቅለው ኤርትራ ከቡና ላኪ ሃገሮች ተርታ መሰለፍ እስክትደርስ ድረስ የተካሄደውን የወያኔ ተንበርካኪነት ስናስታውስ ሻብያ በአዲስ አበባው ኤንባሲ ውስጥ የጥቁር ገበያ የዶላር ምንዛሬውን ሲያደራ እዚያው ኤንባሲ ውስጥ እስር ቤት አቋቁሞ የፈለገውን ሲያደርግ የነበረበት የጌታና የሎሌ ታሪክ የተዘነጋ ይመስል ወያኔና ጭፍሮቿ ሻብያን ቀንድና ጭራ ልትቀጥልልለት የምታደርገው መፍጨርጨር ተመልካች የማይታደምበት ተራ ኮሜዲ ከመሆኑም በላይ እውነተኞቹ የትግራይ ልጆች እንደ አስራት አብረሃምና እንደ ገብረመድህን አርዐያ ያሉት ይህንን የሚታወቅ ታሪክ በተባ ብዕራቸው ትውልድ እንዲያውቀው ከትበው ያስቀመጡት በመሆኑ ዝርዝር ሃተታ አያስፈልገውም ።
ዘረኝውና ዘራፊው የወያኔ ጥርቃሞ በእንዲህ ያለ የሻብያ የጭን ገረድነት የገለማ ታሪክ እያለው ዛሬ ሌሎች ኢትዮጽያውያን ከሻብያ ጋር ቢተባበሩ ከኢሳያስ ጋር ቢነጋገሩ ከቶ ሊቃወም የሚችልበት የሞራል መሠረት የሌለው መሆኑን ወናፍ ፕሮፓጋንዲስቶቹ ሊረዱ በተገባ ነበር። የኢትዮጽያ ልጆች በመረጡት አጀንዳ በመሰላቸው የትግል ስትራቴጂ ከማንኛውም ምድራዊ ሃይል ጋር የመነጋገር የመተባበር ሙሉ መብትና የተሟላ የሞራል የበላይነት ስላላቸው ላለፉት 22 አመታት የህዝባችንን ደም በመምጠጥ ላይ ያለውን ዘራፊ ሌባና ሰውበላው ወያኔን ለማስወገድ ከሻብያ ጋር አይደለም ከሴጣንም ጋር ቢዋወሉ የሚያስመሰግን እንጂ ከቶም የሚያስወቅስ አለመሆኑን ማንም ሊያሰምርበት የሚገባው አብይ ነጥብ ሃገራችንና ሕዝባችን ከወያኔ የከፋ ምድራዊ ጠላት የለውምና ነው። ኢትዮጽያዊ ሃይሎች ከማንኛውም ወገን የሚደረግላቸውን የገንዘብ የማቴሪያልና የስልጠና እገዛ ሃገርና ወገንን ለመታደግ እስካዋሉት ድረስ ከማንም ጋር ቢተባበሩ ከቶም በታሪክ ሊያስወቅሳቸው የሚያስችል ባለመሆኑ በያዙት ጎዳና በልበሙሉነትና በወኔ ሊጓዙ በመቃተት ላይ ያለው የወገናቸው የሰቆቃ ድምጽ ግድ ይላቸዋል። ነገር ግን የሃገርን ብሄራዊ ጥቅም በሚጎዳ ማናቸውም ውልና ስምምነት ውስጥ ቢገቡ ወያኔ ለሻብያ ቂጣ ጋጋሪና መንገድ መሪ በመሆን እንደፈጸመው የውርደት ታሪክ እነሱም እንዳይደግሙት ሊጠነቀቁና አካሄዳቸውን ከጊዜያዊ ፍላጎት አንጻር ሳይሆን ከዘላቂ ጥቅም አንጻር እንዲያደርጉ ይጠበቅባቸዋል።
ከዚህ ባሻገር ወያኔን ለመደምሰስና ለማስወገድ የሚደረገው ትግል በተቀናጀና ሁሉን ወገን ባሳተፈ መልኩ እንዲሆን ሠፊ የፖለቲካ የዲፕሎማሲና የፕሮፓጋንዳ ስራ በስፋትና በጥራት እንዲካሄድ ከህዝቡና ከአጋር ወገኖች የሚገኝ ትግሉን በጥንካሬ ለመወጣት እንዲቻል የሚያግዝ ከፍተኛ የገንዘብ አቅም በማፈላለጉ ላይ ያለይሉኝታ ሊንቀሳቀሱ ይገባል። እዚህ ላይ ባለፈው ሰሞን እንደትልቅ የሃገር ክህደት ወያኔዎችና አንዳንድ ህዝባችን የተጫነበት ድቅድቅ የዘረኝነትና የግፍ ጭለማ ያልታያቸውና የሃገራችን እጣፋንታ ያልገባቸው በተቃውሞው ጎራ የተሰለፉ ቅንጡ ፖለቲከኞች ሲያራግቡት የሰነበቱት የማጥላላት ዘመቻ ግንቦት 7 ከሻብያ ግማሽ ሚለዮን ብር የመቀበሉ ቱማታ በእኔ እምነት የሚያስወቅስ ሳይሆን የትግሉ እድገት አንድ ደረጃ እንደደረሰ ማሰያ በመሆኑ ከወያኔ ጋር ለሚደረገው እልህ አስጨራሽ ትግል የገንዘብም ሆን የቁሳቁስ ድጋፍ ከሻብያ አይደለም ከሠይጣንም ቢገኝ አመስግኖ መቀበል የሞራል ድጋፍ ያለው አካሄድ በመሆኑ አስፈላጊ አይደለም እንጂ የተገኘው ድጋፍ በአደባባይ ቢገለጽ የሚያኮራ እንጂ የሚያሳፍር አይደለም። በተለይ በተቃውሞው ጎራ ያለው ወገን ቆም ብሎ ሊያስብ የሚገባው መሠረት በሌለው እንቶፈንቶ ለመነታረክ ግዜ ከማጥፋት ይልቅ በየራሳችን ይዝን የተነሳንውን አላማ ከግብ ለማድረስ መትጋት ላይ ትኩረት ማድረግ ቢቻል ወያኔ ይህን ያህል ችግር አትሆንብንም ነበር ። ስለሆነም ከኛ ቁጥጥር ውጪ የሆነንን የሌሎችን እንቅስቃሴ ሂደቱን ባንደግፍ እንኳ ተቋዋሚ ልንሆንበት የሚያስችላን አንዳች የፖለቲካ አመክንዮ ስለሌለን በመተባበር በጋራ መቆም ባንቸል በመከባበር በየራሳችን መንገድ መጓዙ የመከራውን መንገድ የሚያሳጥር በመሆኑ ላይ ግንዛቤ ሊኖረን ይገባል።
በኤርትራ በኩል የአመጽ ትግሉን እናካሂዳለን ብለው በድፍረት የቀረቡትን ወገኖች ስለቁርጠኝነታቸው አድናቆት መቸር ሲገባ አንዳንደ የዘረኛው ቡድን ተላላኪዎችና የመንደር ራድዮ ጣቢያዎች ጉዳዩን አጣመው ስላቀረቡት ብቻ ያን ይዞ የትችትና የስድብ ዘመቻ ማካሄድ ተገቢም ካለመሆኑም በላይ በእርስ በርስ ሽኩቻ የሕዝባችን መከራ እንዲራዘም ማድረግ ስለሚሆን ሁሉም ወገን ተገቢነት ባለውና ስልጡን በሆነና መቻቻልን ባሰላሰለ መንገድ ሁሉም የትግል ሃይሎች ቢቻል ጎን ለጎን ካልሆነም በመከባበር ግባቸው ላይ ብቻ ትኩረት በማድረግ ከጎንዮሽ መጠላለፍ እንዲታቀቡ የደጋፊው ህብረተሰብ አሰላለፍ ከስሜታዊነትና ከጠባብ የቡድን አመለካከት ባሻገር ሠፊውን አላማ ላይ ያነጣጠረ ብልህ አካሄድን ማቀናጀት ሁሉም አትራፊ የሚሆንበት የፖለቲካ ሂሳብ በመሆኑ ላይ ትኩረት መስጠት ይኖርብናል። ከዚህ ባሻገር ካሮጌ ፖለቲካችን የወረስነው የስማበለው የባልቴቶች የአሉባልታ ተረት ተረት ይዞ መጓዝ የደረስንበት ዘመን የማይዋጀውና የንቃተ ህሊና ደረጃ ወደማይፈቅድበት የማሰብ አድማስ የሰፋበት ሁኔታ መከሰቱን በመረዳት በሎጅክና በትንተና ሃሳባችንን እስካላስረገጥን ድረስ አዲሱ ትውልድ የማይቀበለው ባለመሆኑ በተለይ እድሜ ጠገብ ፖለቲከኞቻችን ከዚህ አንጻር የትውልድና የአመለካከት መጠነሰፊ ሽግሽግ በግዜ ሂደት መከሰቱን አውቃችሁ በየአቅጣጫው እየተካሄደ ያለውን ትግል በጥራትና በግልጽ ለውይይት እንዲቀርብ በማድረግ በአመጽ ጎዳና እንዘምታለን የሚሉትን ሃይሎች በነጠረ ሂስና ግለሂስ ጥንካሬና ድክመታቸውን እንዲለዩ ህዝባችንም አቅጣጫውን እንዲያስተካክል የሚረዳ ተሳትፏችሁ በጥበብ የተሞላ መሆን ይኖርበታል። አለያ የኔብጤው ወኔና እውቀት አጠር ዲያስፖራ ሠልፍ እንኳ ለመውጣት በደረቅ በጋ ስካርቭ የሚደርብና አርቴፊሻል ጢም የሚቀጥል ፍርሃት ያራደው አውታታ ፤ የወያኔን አገዛዝ ለመደምሰስ ዱር እንገባለን የሚሉትን ሃይሎች መደዴ በሆነ ቋንቋ ሲዘልፍና የግለሰቦችን ስብዕና ሲዘልፍ ላስተዋል ምን ያህል ከሞራል አልባነት ከኋላቀርነት ያልተላቀቀ ምስኪን ወገን በመኖሩ እንዲህ አይነቱ የስድብ ሱሰኛ በምክር አይደለም በጸበልም የሚተወው ባለመሆኑ ለእንዲህ አይነቱ የአስተሳሰብ ድውይ ከማዘን በስተቀር ሌላ ሃይል ማበከን ተገቢ አይመስለኝም ።
አዲሱ ትውልድ ይጠይቃል በበቂ መልስለት ይከተልሃል፤ ይህ ነው መሬት ላይ ያለው ሃቅ ቅንጅት ሚሊዮኖችን ያነቃነቀው ሕዝባዊ አጀንዳና የሚታይ ራዕይ ስላስቀመጠ ነበር። በቅርቡ የተመሠረተው ሠማያዊ ፓርቲ በመሪዎቹ ቁርጠኝነትና ባቀረቡት ወቅታዊ አጀንዳ አንጻር ከስምንት አመታት በኋላ ታላቅ ህዝባዊ ሠልፍ በማድረግ የፈጠሩት መነቃቃት ፓርቲው ከተመሰረተ አጭር ግዜው ቢሆንም ያለው ተደማጭነቱ ከአንጋፋዎቹ ልቆ እንዲገኝና ተስፋ እነዲጣልበት ያደረገው የድርጅቱ መርሆ በሎጅክ የተቃኘና አላማውን ግልጽ በማድረጉ ይመስለኛል። ሕዝብ የሚከተለው ትውልዱ ለትግል የሚነሳው ወቅቱ ከፈጠረው አዲስ ሁኔታ አንጻር እንጂ በታሪክ ቡልኮ ተጀቡኖ በተረትና ሃሜት በሚነዳ የፖሮፓጋንዳ ዘመቻ አይደለም፤ ያ በስማ በለው በደመነፍስ ትውልድ ከሚነዳበት የስብስቴ አመለካከት ላያዳግምና ተመልሶ ላይመጣ በማስተዋልና በስልጣኔ እየተሻረ በመሄድ ላይ በመሆኑ ብዙዎች ያወሩለትን ጥቂቶች ጀምረው ያቆሙትን የአመጽ ትግል በአዲስ መልክ እናስቀጥላለን ብለው የተነሱትን ሃይሎች የማይደግፍበት ምክንያት ቢኖረው እንኳ ከመርህ አንጻር ሊቃወም የሚችልብት ምንም በቂና ውሃ የሚቋጥር አሳማኝ ምክንያት ባለመኖሩ ሂደቱን በጥንቃቄ ይከታተላል።
በዚህ የስልጣኔና የጥበብ ዘመን ላይ ቆመን ከቶስ ስል አመጽ ትግል ማንሳት ለምን አስፈለገ ጦርነት የሰውን ልጅ የሚበላ እሳት ነው። አመጽ ሃገር የሚያወድም መሠረተ ልማትን የሚንድ ኋላቀር መፍትሔ ነው፤ የሰላሙን ትግል ማበረታታት ሲገባ ለምን የአመጽ መንገድ እንደ መፍትሔ ይቀመጣል የሚሉ ወገኖች በርካቶች ናቸው። እርግጥ ነው ዲያቢሎስ ካልሆነ በቀር ጦርነትን መልካም ነው የሚል አንዳችም ጤነኛ አዕምሮ ያለው ፍጡር አለ ለማለት አይደፈርም። እንደምኞታችን ነገሮች በተቃውሞ ሠልፍና በሕዝባዊ እንቢተኝነት ቀለውልን ከላያችን የተጫነው ግፈኛ አገዛዝ አሽቀንጥረን ብንጥል መልካም ነበር። ይህ ግን ቀላል ሆኖ አልተገኘም የተከፈለውና በመከፈል ላይ ያለው መስዋዕትነት አንሶ አልነበረም አመጽ ታሳቢ የሆነው። ሃገራችንን የወረረው የወያኔ ቡድን ፖለቲካና ርዕዮተ ዓለምን መሠረት ያደረገ ሣይሆን ፤ የዘር አመለካከትን ዶግማና ቀኖናው በማድረግ ኋላቀር አካሄዱንና፤ ኢ ዲሞክራሲያዊነቱን የተቃወመውን ወገን በሙሉ የሚመለከትበት ሸውራራ አተያይ ፀረ ትግራይ በሚል በመሆኑ ከእንዲህ አይነቱ ጠባብና ድኩማን አመለካከት ባለው ሃይል ከሚመራ ቡድን ጋር የሚደረግ ስልጡን የፖለቲካ ትግል ውጤቱ ፍሬ አልባ በመሆኑ ሊገዳደረው የሚችል የሃይል እንቅስቃሴ አማራጭነቱ ሁሉን ወገን ከተረዳው የከረመ ቢሆንም አለመታደል ሆኖ የትግሉን እንቅስቃሴ ማቀናበሪያ ወሳኝ ኮሪደር በማግኘት ዙሪያ ስንቸገርና ባለውም ጠባብ አማራጭ ለመጠቀም ሳንችል የቆየንባቸው ትርምስ የተሞላ ሰፊና ወርቃማ ግዜያቶች ባክነዋል።
አመጽ የጭቁኖች ድምጽ ነው ሲል የተናገረው ጠቢብ ማን ነበር ፤ አዎን አመጽ የሰውነት ክብርን ማረጋገጫ የነፃነት እስትንፋስ ማግኛ የባርነት ሰንሠለትን የሚበጥስ ጽኑ መዶሻ ነው። በሃገራችን የዛሬን አያድርገውና እንኳን ሃብትና ንብረቱ እየተቀማ ከነ ቤተሰቡ ጎዳና ሊጣል ቀርቶ ክፉ ቃል ተናግሮ ስብዕናውን የተዳፈረውን አደብ ሳያስገዛ የማይኖር ከምንም ነገር በላይ ለክብሩ ዘብ የሚቆም ማንነቱ ተዋርዶ በሞቀ ጎጆው ከመኖር ይልቅ ክብሩን ለማስመለስ ዱርቤቴ ማለትን የሚመርጥ ጀግና ሕዝብ እንደ እባብ ተሽሎክሉኮ በገባው የማንም መደዴና ቀን የሰጠው ወፍዘራሽ ዘረኛ የወያኔ መቀለጃ ሆኖ ለስደት ለሞት ለእስርና ለምድራዊ ስቃይ የተዳረገው መብቱን ለማስከበር አመጽን አማራጭ ባለማድረጉ መሆኑን እያየንው ነው።
ወያኔዎች በለስ ቀንቶዐቸው ድፍን ኢትዮጽያን ሲወሩ በየሄዱበት ያገኙትን አሮጌ አካፋና ቀደዳ በርሜል ሳይቀር እየጫኑ ወደትውልድ ስፍራቸው ሲያግዙ ከነበረበት ቅራቅንቦ ሰብሳቢነት እድሜ ለታላቋ ሃገራችን ዛሬ ይህው እኒያ ከገላቸው እድፍና ከጎፈሬያቸው ተባይ ውጪ የረባ ጃኬት እንኳ ያልነበራቸው ሽፍቶች ይህው ዛሬ ድፍን ሃገር በጠኔ እየተመታ በረሃብ አለንጋ በሚለበለብበት ልጆቹን በፈረቃ የሚቀልብበት የኑሮ ምስቅልቅል ውስጥ ወድቆ ልጆቹ በየትምህርት ቤቱ ደጃፍ ረሃብ አዙሮ እየጣላቸው ባለበት ሁኔታ ላይ የወያኔው አባላት ጉቶ እየሞቁ ድብዳብ ላይ ተወልደው እዛው አጎዛ ላይ እንዳላደጉ ይህው የህዝብን ሃብት በመዝረፍ በህንጻ ላይ ህንጻ በሃብት ላይ ሃብት እያከማቹ ከራሳቸው አልፈው በድብቅ ላስቀመጧቸው እቁባቶቻቸው ወርቅና አልማዝ መኪናና ቪላ ስጦታ የሚያቀርቡበት ታጋይ ከበርቴዎችና ልማታዊ ዘራፊዎች ሕገ ወጥ ብልጽግና አካብተው ቅንጦት የሚያደርጋቸውን ባሰጣበት በዚህ ወቅት ትውልዱ ኑሮ ዳገት ሆኖበት የከፋውን ስደት ተያይዞት የሲናይ በርሃ አሸዋ ሲሳይ የቀይባህር አሳ ቀለብ እየሆነ እንደወጣ የቀረው የእምዬ ኢትዮጽያ ልጅ የሚደርስበት ሰቆቃ ዓለምን እስኪሰለች ድረስ የተለመደ የሰርክ ተግባር በመሰለበት በዚህ ዘመን ፤ በሃገር ውስጥ ያለው በገፍ በሚቀርብለት ጫት ደንዝዞ በምዕራቡ ዋልጌ ባህል ነፍዞ ከሞቱት በላይ ከቆሙት በታች በሆነ የሞራልና የተስፋ መቁረጥ ጭለማ ተውጦ የትግሬው ነጻ አውጪ አባላት ልጆች ከህዝብ በሚዘረፍ ገንዘብ በአውሮፓና በኣሜሪካ ውድ ኮሌጆች እንዲማሩ እየተደረገ ባለበት የፋሽስት አገዛዝ ውስጥ የአንድ አናሳ ብሄር ሰዎች ተጨፍልቆ እየቃተተ በስቃይ በሚኖርበት ሁኔታ ውስጥ ህዝባችን ቢያምጽ ይነሰው በእውነቱ ይህ ትውልድ እነዚህን የቀን ጅብ ወያኔዎች ለመታገል ከሰይጣንስ ጋር ቢተባበር ከቶ ወንጀሉ ምኑ ላይ ነው?
ተወልደው ካደጉበት ጎጆ ቀልሰው ትዳር ይዘው ጫካ መንጥረውና ከአውሬ ታግለው ከባዱን የኑሮ ዳገት በላብ በወዛቸው አቅልለው በሰላም ሃገሬ መንደሬ ብለው የእርሻን ጥበብ የአኗኗር ዘይቤን ሃይማኖትንና ግብረገብነትን በየሄዱበት አስተምረው በቋንቋና በባህል የተለያቸውብ ወገን የራሳቸው አድርገው ተዛምደውና ተጋብተው በሰላም ለዘመናት ከኖሩበት ቅዬ ሃገራችሁ አይደለም በሚል ያፈሩትን ሃብት ነጥቆ ተማሪዎች ከትምህርታቸው በግድ እንዲፈናቀሉ በማድረግ በክፋትና ቂም በቀል አንድን ህዝብ ለማጥፋት የሚያደባውን እርጉሙን የትግሬ ነጻ አውጪ ቡድን ይህ ሕዝብ መፋለም ይነሰው በጉራፈርዳ በቤኒሻንጉል በአፋርና በጋንቤላ እንዲሁም በሌሎች ቦታዎች የተፈጸመው የዘር ማጥፋትና ሁን ብሎ በድህነት የመቅጣት ወያኔያዊ ሴራ በእውነቱ ከወንጀልም ወንጀል ከሃጢያትም ሃጢያት የሚሆነው ይህንን ሳጥናዔላዊ ቡድን አለመታገል ብቻ ነው።
ነብሳቸውን ይማረውና አያቴ ‘’ ጣሊያን ምን አጠፋ በከንቱ ኩነኔ ሃገሩን አጠፉት መለስና ላይኔ’’ ብለው ነበር ያኔ ገና ወያኔ ሃገር ስትወር ፋሽስት ጣሊያን ያልፈጸመውን ግፍ ኦርቶዶክስና አማራ የሚባል ተቋምና ህዝብን ለማጥፋት እቅድ ነድፎ መርዝ አዘጋጅቶ የመጣን አርዮሳዊ ሃይል ለሺህ ዘመናት የውጪና የውስጥ ሃይሎችን በጽናት በመመከት ህልውናዋን አስጠብቃ የኖረችውን የታሪክ ማህደሯን ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እንድትከፋፈል የዘረኞች ምሽግ በመሆን ሃዋርያዊ ሃላፊነቷን ዘንግታ የጥፋት አላማው ማራመጃ ለማድረግ በመለመላቸው ጥቅመኛና ዘረኛ ጻጻሳትና ፓትርያርክ ተብዬ በማዘጋጀት በቤተክርስቲያኒቱና በምዕመኑ ላይ ሲደርሰ የቆየው በደልና ግፍ በቀላሉ ተዘርዝሮ አያልቅም። ወያኔ በቤተክርሰቲያኒቱ ላይ ያለውን ጥላቻ በማስፋፋት ይደረጋል ተብሎ አይደለም ሊታሰብ እነኳ የማይሞከረውን ታላቁን የዋልድባ ገዳም ለስኳር ልማት በሚል በገዳሙና በመናኝ ባህታውያኑ ላይ የተፈጸመው ግፍ ስንቃኝ የውጭ ወራሪ ሃይል ይህን ያህል ይዳፈራልን? ታዲያስ ይህ ጉግማንጉግ ፀረ ኦርቶዶክስ የሆነ የወያኔ መንጋ ከቶስ ከሰይጣን የሚለየው በምንድን ነው? ይህንን ወንጀለኛና መንጋ ዘረኛ ይወገድ ዘንድ የዚህች ታላቅ ሃይማኖት ካህናትና ምዕመናን አድዋ ላይ ጌቶቹ ጣሊያኖችን በጸሎትና በሰይፍ እንዳሸነፈ በዚህም ሃገር በቀል የፋሽስት ሎሌን ለማስወገድ የሚደረገውን ትግል በውግዘትም በሞራልም ማገዝ ለቤተክርስቲያኗ ሰላም መረጋገጥን ለምዕመኖቿ መረጋጋትን የሚያስገኝ ትርጉም ያለው መልካም ሁኔታ ሊገኝ የሚችለው ይህ የዘረኛ መንጋ ተጠራርጎ ሲወገድ ብቻ በመሆኑ ይህንን ትግል ማገዝ የቤተክርስቲያኒቱና የምዕመናኑ መንፍሳዊ ግዴታ ጭምር ነው።
የሃይማኖት ተቋማትን ማጥፋት የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር እኩይና ሠይጣናዊ አላማ ሌላው ያነጣጠረበት የኢትዮጽያ ሙስሊም ማህበረሰብ ከአመታት በፊት ይህው ከፋፋይ ዘረኛ የወያኔ ቡድን የሙስሊሙን ማህበረሰብ የስልጣኑ ማደላደያ በማድረግ ከጎኑ ለማሰለፍ የሞከረበት እኩይ አላማው ከቅርብ አመታት ወዲህ ከታወቀ በኋላ መላው ሙስሊም በአንድ ድምጽ ያቀረበውን የሃይማኖት ነጻነት ጥያቄ በሃይለ ለመጨፍለቅ ከምዕመኑ ጋር ያደረገው ትንቅንቅ የሙስሊም ወንድሞቻችን ዓለምን ያስደመመ እጅግ ዘመናዊና ሰላማዊ የትግል እንቅስቃሴ ቢያደርጉም ጨዋነትን ምንም ያህል መርሐቸው ቢያደርጉም የወያኔ ቡድን ሠላማዊ ቋንቋ የሚገባው ባለመሆኑ ለሠላት የወጣውን የሙስሊም ማህበረሰብ ህጻን ከአዋቂ ሣይመርጥ በተለያዩ ቦታዎች የፈጸመውን ጅምላ ፍጅት የምታስታውስ ሙስሊም ወገን ይህንን የደደቢት ጭራቅ ለማስወገድ የሚደረገው ትግል በመንፈሳዊ ቡራኬም ሆነ በቀጥተኛ ተሳትፎ
ክንድህን ሠብስበህ እንዳትታገለው ከቶስ የሚያግድህ ምንድነው? እየተጨቆኑ መኖር ለሃገርህና ለእምነትህ ታግለህ በክብር ማለፍ ነው።
ለማጠቃለል ኢትዮጽያ እንደሃገር ትቀጥል ዘንድ ትውልዷም ተሰዶ ከማለቁ በፊት ይህን ሃገር አፍራሽና መንጋ ቅጥረኛ ከቅድስት ሃገራችን ለማስወገድ እየተካሄደ ያለውን ማንኛውም እንቅስቃሴ ዘር ሃይማኖት ሳንለይ በጋራ ቆመን በጽናትና በብርታት የመደገፍ የማበረታታት የማገዝ ታሪካዊም ሞራላዊም ሆነ መንፈሳዊ ግዴታ አለብን። በትግል አለም መውደቅ መነሳት ያለና የነበረ በመሆኑ ትላንት በሄድንባቸው መንገዶች ውጤት ባናገኝም ስልታችንን በማስተካከል ጥበብ በተሞላበትና ቁርጠኝነት ባለው መልኩ እንጓዝ ዘንድ መሪ ሃይል ሆናችሁ የወጣችሁ ሃይሎች በየትኛውም የትግል ስልትና ያላችሁ ያለ የሌለ ሃይላችሁን በማስተባበር የወያኔን ተፍጻሜተ መንግስት ለማቅረብ የሚረዳ አመራር በመቀየስ ታግላችሁ እንድታታግሉን ግዜው ግድ ይላችኋል።
ታላቁ ደራሲ ኦሮማይ በሚለው መጽሃፉ የሳላቸው የገሃዱ ታሪካችን አካል የነበረው ቀይ እንቡጥ የተባለው በለጋ ወጣቶች የተመራው የሃገር ፍቅር ሰራዊት ውጤቱ የማታ ማታ ቢበላሽም በለጋ እድሜያቸው በቆራጥነትና በጀግንነት አንድ ስትራቴጂክ ተራራ ለማስለቀቅ የከፈሉት ወደር የሌለው መስዋዕትነት ይህ ትውልድ ዞር ብሎ በማሰብ ነፃነቱን ረግጠው በሃገሩ ባይተዋር ባደረጉትና ሃገራዊ ድርሻውን ነጥቀው ባቋቋሙት የንግድ ኢንፓየር እነሱ በቁንጣን ሲወጠሩ የሃገሬ ወጣት ከረሃብ ጋር ሲታገል በየድልድይ ስር የሚያድርበት የአፓርታይድ አገዛዝ እንዲያከትም መፍትሄው ያለው በአዲሱ ትውልድ መዳፍ ውስጥ በመሆኑ ያአህዛብ አሽከርና የችጋር ጓደኛ ሆኖ ተሰቃይቶ ከመሞት ታሪክ ሰርቶ ለታሪክም ለህሊናም የሚጠቅም በጎ ተግባር ፈጽሞ ለመገኘት በሚቻለውና በማንኛውም መንገድ የሚደረገው ትግል በማገዝ ህዝባችንን ልንታደግ ሃገራችንን ልንጠብቅና ሃይማኖታችንን አስከብረን በነጻነት እንድንኖር ወያኔን ለማስወገድ የሚካሄደውን ሁለገብ ትግል በትጥቅ ይሁን በሰላም ከኤርትራ ይሁን ከሱዳን ከሱማሌ ይሁን ከጅቡቲ በሚነሳ የአመጽ ሃይል ይሁን በሕዝባዊ ንቅናቄ ሁሉን ባለን አቅምና ጉልበት ልናግዝ ታሪክ ትውልድ ሞራልና መንፈሳዊ ሕይወታችን ግድ ይለናል። በጽናትና በጋራ ቆመን ጠላቶቻችንን ለመደምሰስ እግዚያብሄር ሃይልና ብርታት ይሁነን።
ኢትዮጽያ ለዘላለም ትኑር!!!