Wednesday, January 30, 2013

ሚሚ ስብሐቱ እና የሙታን ዲሞክራሲ! (በዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ)


የዚህ ጽሑፍ ዓላማ ሚሚ ስብሐቱና ጓደኞቿ “የጋዜጠኞች ክብ ጠረጴዛ” በተሰኘ ፕሮግራም እኔ ላይ ለሰነዘሩት ስድብ በዋናነት መልስ ለመስጠት ሳይሆን ዘለፋቸውን በሚካሄዱበት ሰዓት እግረ መንገዳችውን ባነሱት የፖለቲካ አተያይ ላይ ሒስ ለማቅረብ ነው፡፡
ይህንንም እንድል ያስገደደኝ እኔ ከአዲስ አድማስ ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል ተደውሎ ለቀረበልኝ ጥያቄ በሰጠሁት መልስ ላይ ወይም ባነሳሁት ሐሳብ ላይ ትችት በማቅረብ ፈንታ በእኔ ስብዕና ላይ አሉታዊ በሆነ መልኩ ዘለፋ በመሰንዘራቸው ነው፡፡
ለአዲስ አድማስ ጋዜጣ የሰጠሁት አስተያያት ዋና ፍሬ ነገር እንደሚከተለው ይነበባል፡፡ “በሁለተኛ ሹም ሽር የተከናወኑትን የስልጣን መደላደል በምናይበት ጊዜ ህወሓት እንደ ቀድሞው በእጅጉ ተጠናክሮ ብቸኛ የሆነውን ስልጣኑን ተመልሶ ይዟል፡፡”
እንግዲህ እነ ወ፨ሮ ሚሚ ስብሐቱ በዚህ መሠረታዊ ሐሳብ ላይ ትችት በመሰንዘር ፋንታ የተሾሙትን ሰዎች ስም እየጠቀሱ ግነት በተሞላበት አኳኋን ማንነታቸውን ማለትም ችሎታቸውን፣ክህሎታቸውን ፣ዕውቀታቸውን ሲክቡ በአንፃሩ እኔ ያቀረብኩትን ሐሳብ ሳይተቹ ለአንድ የዩኒቨርሲቲ መምህር የማይመጥን (የወረደ) አስተያየት በማለት አልፈውታል፡፡
እሑድ በሚተላለፈው ፕሮግራም ላይ የሚቀርቡት ወ፨ሮ ሚሚ እና ሌሎች ሁለት ግለሰቦች ቢሆኑም ሁለቱ ሰዎች እንደ ሰው በፕሮግራሙ ላይ የሚያንፀባርቁት የራሳቸው የአስተሳሰብ ልዕልና የሌላቸውና ለሚሚ ልሳን ለማዋስ ወይም “ለማከራየት” የተሠማሩ ስለሆነ ይህ ጽሑፍ እነርሱን ሳይሆን በቀጥታ እርሷን የሚመለከት ይሆናል፡፡
ከሁሉ አስቀድሞ ግን ትችቴን ከመጀመሬ በፊት አንድ ነጥብ አንስቼ ማለፍ እፈልጋለሁ፡፡ይኸውም እነሚሚ በግለሰብ ደረጃ ለሰነዘሩት ዘለፋ በአደባባይ መልስ መስጠቱ ተገቢ አይደለም፡፡በመሆኑም “እኔ እንዲህ ነኝ፤እንዲያ ነኝ” ብሎ ስለራስ መናገር ከባሕልም አኳያ ሆነ ከሞራል እይታ አንፃር ተገቢ ሆኖ አናገኘውም፡፡ሆኖም ግን ሚሚ ካነሳችው “ዳኛቸው ‘ይገባኛል’ የሚለው ሹመት ስላልተሰጠው ነው፡፡ ኢሕአዴግን የሚተቸው” ለሚለው ገለፃ ፅብቴን ጥዬ ማለፍ እፈልጋለሁ፡፡
ከላይ እንደጠቀስኩት ራሴን በመከላከል “አይ እኔ ሹመት አልፈልግም” የሚል መልስ ለመስጠት ሳይሆን እዚህ በቆየሁባቸው ፮ ዓመታት ሹመት የሚፈልግ ሰው ማድረግ የሚገባውን ነገር አጥቼው ወደ ሒስና በመንግስት ላይ ትችት ወደ መሰንዘር የሄድኩበት እንዴት ሊመስላት እንደቻለ መገረሜን ለመግለፅ ያክል ነው፡፡
ምናልባትም በመንግስት ለመሾም፣ለመደጎምና ለመመስገን ያለውን መንገድ በሞኖፖል “እኔ ብቻ ነኝ የማውቀው” የምትል ከሆነ ስለ እኔ ሹመት ከጃይነት ያለችው እውነት ሊሆን ይችላል፡፡
የሙታን ዲሞክራሲ በገዢው ፓርቲ ልሂቃን አስተሳሰብ አሁን በኢትዮጵያ የተዘረጋው ሥርዓት ወሳኝ የሆኑትን የፖለቲካ ጥያቄዎች ስለፈታ ጊዜው የፖለቲካ ማቀንቀኛና “የማብጠልጠል” ሳይሆን ወደ ልማት የሚተኮርበት ነው፡፡
የዚህ ሐሳብ ዋነኛ ተጋሪ የሆነችው ሚሚ ስብሐቱ ጥያቄ በሚያነሱ ሰዎች ላይ ቁጣዋ የሚነሳው ከዚህ የመነጨ ነው፡፡የነሚሚ ስብሐቱ “የዚህ ጥያቄ አልቋል” የሚለው አስተያየት ጥያቄውን ለማፈንና ለመግደል ከመከጀል የመነጨ ነው፡፡
አንዳንድ ሰዎች እንደሚሉት እነሚሚ ማድረግ የሚፈልጉት ደርግ እንዳደረገው ጠያቂውን ሳይሆን ጥያቄውን እንደ ጥያቄ መግደል መፈለጋቸው ነው፡፡የዚህ ጽሑፍ ማተኮሪያ በሆነው ፕሮግራሟ ላይም ካነሳቻቸው ነጥቦች አንዱ “የብሔር ፖለቲካ መልስ ተሰጥቶበት ያበቃ ጉዳይ ነው የሚለው በምሳሌነት መቅረብ ይችላል፡፡”
“ፖለቲካ አልቋል”፣“ጥያቄዎች ተፈትተዋል”፣“ለአገሩቱ የሚበጅ ሐሳቦች ተገኝተዋል”፣“አሁን ትኩረታችን ከውይይት፣ከምክክር እና ከንትርክ ወጥተን ያገኘናቸውን የሚበጁ ሐሳቦች መተግበር ላይ ማድረግ ብቻ ነው የሚያስፈልገው”የሚል አካሄድ ነው የተያዘው፡፡እንዲህ ዓይነቱን አስተሳሰብ አንዳንድ ጸሐፍት ሕይወት አልባ እና የሙታን ዴሞክራሲ ይሉታል፡፡
በአንፃሩ ግን አንድ ማህበረሰብ ዴሞክራሲያዊና ሕያው እንዲሆን የሚከተሉትን ሦስት ንድፈ ሐሳቦች አቅፎ የያዘ መሆን አለበት፡፡እነርሱም አውጥቶ ማውረድና ምክክር (ደሊበራቲኦን) ፣ሐሳብን ማብላላት (ረፈለችቲኦን) እንዲሁም የሒስ መንፈስ (ጭሪቲቻል ጽፒሪት) ናቸው፡፡
ይህ እንግዲህ የሚያመለክተን ጉዳይ ማንኛውም ፍልስፍና ወይም የፖለቲካ ሂደት የሚነሱትን የኑሮ ተግባራዊ ችግሮች፣የሚታዩትን የፖለቲካ መሰናክሎች እንዲሁም የሚደቀኑትን የሞራል ክፍተቶች ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መፍታት ስለማይቻል ከላይ የጠቀስናቸው ሦስት ነጥቦች ለዴሞክራሲያዊ ማሕበረሰብ በጣም አስፈላጊ መሆናቸውን ነው፡፡
እንደሚሚ ስብሐቱ አቀራረብ ግን የኢሐአዲግ የፖለቲካ አካሄድ ብዙ ማሕበረሰባዊ ጥቄዎችን እየፈታ የሚሄድ ስለሆነ እንደገና ወደ ኃላ እየተመለሱ ጥያቄ ማንሳት የአድኃሪ ጠባይ ነው፡፡
በተለይም “አገሪቱ የብሔር ጥያቄን ተሻግራ ካለፈች በኃላ እንደ ዳኛቸው ዓይነቱ ሰዎች ለምን ወደ ኃላ እንደሚመልሱን አናውቅም” ማለቷ ፖለቲካ ማለቂያ የሌለው የሐሳብ ፍጭት የሚያስተናግድ መድረክ መሆኑን ነው የዘነጋችው፡፡ለውይይትና ለሐሳብ ፍጭት ደግሞ አቀጣጣዩ ነዳጅ ጥያቄ ነው፡፡በመሆኑም ውይይት፣ጥያቄ፣ምክክር፣ነቀፊታ፣ትችት ወዘተ።።ለአንድ ዴሞክራሲያዊ ማሕበረሰብ ወሳኝና አስፈላጊ ነገሮች ናቸው፡፡
“አትናገሩ”፣“አትጠይቁ”፣“አታንገራግሩ”፣“አትተቹ”፣“ዝም ብላችሁ ተገዙ” የሚለውን የጉልበተኞች ጥሪ ይበልጥ ለማብራራት የ፳ ኛው ክ፨ዘመን ታላቅ ደራሲ ከሆነው ፍራንስ ካፍካ ሥራዎች መካከል ትንሽ ትረካ ልጥቀስ፡፡
በአንድ እስር ቤት ውስጥ የሞት ፍርድ ተላልፎባቸው ቅጣቱን የሚጠባበቁ እስረኞች አንድ ቀን ከሰዓት በኃላ አመፅና ረብሻ ጀመሩ፡፡የከሰዓቱ ፈረቃ የዘብ አለቃ ካመፁት እስረኞች ዘንድ ቀርቦ “የእናንተ ጓደኞች ከዚህ በፊትም ሆነ ዛሬ ጠዋት እንኳ በነበሩት ረሻኞች ላይ ምንም ዓይነት ረብሻ ሳያነሱ ተረሽነው ሳለ እናንተ ግን በእኛ ተራ ላይ ረብሻ ማንሳታችሁ ተገቢ ያልሆነና አድልዎን የሚያሳይ ነው፡፡እንዲያውም ከሞራል አኳያ የሚያስጠይቃችሁን ሥራ እየፈፀማችሁ ነው፡፡የማታዳሉና ረብሻ ፈላጊ ባትሆኑ ኖሮ እንደዚህ ባለ የብጥበጣ ተግባር ውስጥ ሳትሳተፉ ዝም ብላችሁ ትገደሉ ነበር፡፡” ብሎ ወቀሳቸው፡፡
እነ ሚሚም አሁን የሚሉን “ባለፉት ስርዓታት ዝም ብላችሁ እኛ ስልጣን ስንይዝ በፊት ያላነሳችሁትን የጭቆናና የበደል አቤቱታ አሁን በእኛ ተራ ማንሳታችሁ ተገቢ አይደለም፡፡ጥሩ ሰዎች ብትሆኑ አርፋችሁ ትገዙ ነበር” እንደማለት ነው፡፡
ሚሚ ስብሐቱ ጋዜጠኛ ወይስ ሶፊስት
ጥንታዊው ትልቁ የግሪክ ፈላስፋ ፕሌቶ ዕድሜ ልኩን በሐሳብ ሶፊስቶችን ሲታገል ነው የኖረው፡፡በመሠረቱ ሶፊስት ማለት በተቀዳሚ አስመሳይ ማለት ነው፡፡ወይም አስመስሎ የሚያድር ማለት ነው፡፡
በዚህ ዙሪያ ዶ፨ር እጓለ ገ፨ዮሐንስ “የከፍተኛ ትምህርት ዘይቤ” በተባለ መጽሐፋቸው “የቀድሞ ዘመን ሶፊስቶች ያቀረቡት የጥቅም አገልጋይ የሆነ አሳሳች ትምህርት በጊዜአችንም ዘመናዊ ዳቦ ለብሶ ወደ እልፍኝ አዳራሽ ለመግባት ይጠይቃል፡፡ዳቦና ቆዳ ከለየን ግን ቆየን” ብለዋል፡፡
እኛም ታግለው የመጡትን ፋኖዎችና የከተማ “ፋኖዎች” ከለየን ቆይተናል፡፡በተጨማሪም እውነተኛ ጋዜጠኞችንና ፕሮፓጋንዲስቶችንም ጠንቅቀን ካወቅንም ውለን ከርመናል፡፡
እንደ እኔ አስተያየት ሚሚ ስብሐቱ በፕሮፓጋንዳ ሥራ ላይ የተሰማራች እመቤት ነች፡፡ሚሚ ተቀዳሚ ሥራዋ ፕሮፓጋንዳ ነው በምንልበት ጊዜ ምን ማለታችሁ ነው፧ ለዚህ ጥያቄ ቀጥተኛ መልስ ከመስጠታችን በፊት የእርሷ ሬዲዮ በአመለካከትና በአቀራረብ ከመንግስት ሚዲያ ጋር ዝምድና አለው ብለን ስለምናምን ከዛሚ በፊት ትንሽ ስለ ኢትዮጵያ ሬድዮና ቴሌቪዥን ብንናገር ጋሪውን ከፈረሱ ማስቀደም አይሆንብንም፡፡
ሚዲያና አታላዩ ጂኒ
በመሠረቱ የሚዲያው ዋና ሚናና ግብ ሥርዓቱ እራሱን እየወለደ (ረፕሮዱቸ እያደረገ) እንዲሄድና ሕልውናውን ለዘለቄታው ማስጠበቅ ነው፡፡ለዚህም ተልዕኮው መረጃ ከማቀበል መደበኛ ሥራው ጎን ለጎን የፕሮፓጋንዳ ተግባራትን ያከናውናል፡፡ለፕሮፓጋንዳ ሥርጭቶቹም ማሳነስ፣መጨመር፣ማጋነን፣ማንኳሰስ፣መደመር፣መቀነስ፣መፍጠር፣ማንፀባረቅ፣መወንጀል፣ማወደስ ዓይነተኛ መሣሪያዎች ናቸው፡፡
እነዚህን የፕሮፓጋንዳ ተግባራት ትንሽ ለማብራራት በአንድ ርዕስ ዙሪያ የተካሄደውን የሁለት ፈረንሳዮች ወግ መጥቀስ ተገቢ መስሎ ይታየኛል፡፡አንደኛው ፈረንሳዊ ሬኔ ዴካርት የተባለው የ፩፯ኛው ክ፨ዘመን ፈላስፋ ነው፡፡ይህ ፈላስፋ የሰው ልጅ ወደ ትክክለኛው ሐሳብ እንዳይደርስ የሚያደርጉ መሰናክሎች አሉ ይልና ከነኚህ መካከል ባህል፣ወግና የመሪዎች ጫና ተጠቃሾች መሆናቸውን ያስረዳል፡፡
ይኸውም የሚሆንበት ምክንያት በዋናነት የሰው ልጅ በስሎና ዐውቆ ስለማይወለድ የራሱን የአመለካከት ልዕልና እስከሚያገኝ ድረስ በማሕበረሰቡ ስለሚቀረጽ ውጫዊ የሆኑት የባሕል፣የወግ የታሪክ ጫናዎች በላዩ ላይ ያርፋሉ፡፡በመሆኑም በአንድ ማሕበረሰብ ውስጥ ያሉ ግለሰቦች ወደ እውነት እንዲቀርቡ ከተፈለገ በተቀዳሚነት የማሕበረሰቡ አመለካከት መታከምና መጽዳት አለበት ብሎ ያምናል፡፡
በተጨማሪም እንደሬኔ ዴካርት መላምት እንዲያውም ከባህል ውጭ አንድ ሆነ ብሎ አሳሳች የሆነ እርኩስ ሰይጣን ሊኖር ይችላል፡፡ማኅበረሰቡ ውስጥ ያሉ አሳሳች ነገሮች ዐውቀው ለማሳሳት ሳይሆን ካለማወቅ እና የጠቀሙ እየመሰላቸው የሚያሳስቱ ሲሆን፣በአንፃሩ የአሳሳቹ ጂኒ ተግባር ግን አስቦና ሆነ ብሎ የሚያደርገው ነው፡፡
ከሬኔ ዴካርት አስተምህሮት የምናገኘው ስሕተት እንደ ስሕተት የግለሰቡ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን ከማኅበረሰቡ አመለካከት ጋር የተቆራኘ መሆኑን ነው፡፡
በሌላ በኩል በ፳ኛው ክ፨ዘመን መባቻ ላይ የመጣው ፈረንሳው የማሕበረሰብ ጥናት ተመራማሪ ኤሚል ዴርካም፣ለዴካርት “አሳሳች ጂኒ ሊኖር ይችላል” ለሚል አስተያየት ሲመልስ “ጂኒውም ከጉም ፣ ከሰማይ ፣ከወንዝ፣ከተራራ ስር ከምትፈልገው እዚያ የፖለቲካ ማኅበረሰብ ውስጥ ብትፈልገው ታገኘዋለህ” በማለት ነበር፡፡
ወደ እኛ ጉዳይ በምንመጣበት ጊዜ እኛም አታላዩ ጂኒ እንደ ዴርካይም የፖለቲካ ሥርዓቱ አካባቢ በተለይም በሚዲያ ክፍል ሊገኝ ይችላል ብለን እናምናለን፡፡ከዚህ አኳያ እህታችን ከተሰማራችበት የፕሮፓጋንዳና የማነሁለል ተግባራት ስንነሳ የሬኔ ዴካርትን ጂኒ ሚና እንደምትጫወት ይሰማናል፡፡
ይህንኑ አሳሳች ጂኒ በመፍራት ማንኛቸውም የዴሞክራሲያዊ አገራት መንግስታት የራሳቸው ሚዲያ እንዳይኖራቸው በሕግ ተከልክሏል፡፡እንደ ቪኢኤ የመሰሉ የሚዲያ ተቋማት ዜናዎቻቸውን ለውጭ አድማጮችና ተመልካቾች እንጂ ለአገር ውስጥ ታዳሚያን ማሠራጨት የማይችሉት ለዚህ ነው፡፡
ህወሓት እና የትግራይ ሕዝብ
በመሠረቱ ህወሓት ትግርኛ የሚናገሩ ሰዎች የፈጠሩት የፖለቲካ ፓርቲ እንጂ የትግራይ ሕዝብ ማለት አይደለም፡፡ በሌላ በኩል ፓርቲው የተወሰኑ የትግሪኛ ተናጋሪዎች እንጂ የሁሉም የትግራይ ሰዎች ፓርቲ ማለትም አይደለም፡፡
ይህንን ለመለየት በጣም የላቀ ትምህርት አስፈላጊ ሆኖ አናገኘውም፡፡ሁለቱን መለያየት ካልቻልን እንደ ሚሚ ስብሐቱ ህወሓት ሲነካ ትግራይ ተነካ፤ስለ ህወሓት ሲወራ ስለ ትግራይ ማውራት ተደርጎ መቁጠር ይሆናል፡፡
ለዚህም ማሳያነት እንዲሆን ለጋዜጣው በሰጠሁት አስተያየት “ስልጣን ተመልሶ ወደ ህወሓት እጅ ገባ” ማለቴን “ዳኛቸው ስልጣን ወደ ትግራይ ተመለሰ አለ” ብላ አቅርባዋለች፡፡እዚህ ላይ አፅንዖት ለመስጠት የምፈልገው ያላልኩትን ማለቷ ላይ ብቻ ሳይሆን ፓርቲና ዘርን አንድ አድርጎ የሚያቀርብላት አዕምሯዊ ቀረፃ እንዳላትም ለማሳየት ጭምር ነው፡፡
ይህንንም ስል የሽተቷ ምንጭ ከአቀራረብ ወይንም ከማወቅ አለማወቅ (ዐፒስተሞሎጊቻል) ሳይሆን ያላት አዕምሯዊ ኑባሬ (ኦንቶሎግይ) ከዘርና ከነገድ ውጭ እንዳታይ እንደሚያደርጋት መግለፄ ነው፡፡ ሽተቷ “ያጋጣሚ” ሳይሆን “የተፈጥሮ” መሆኑን ልብ ይሏል፡፡
እንደዚህ ዓይነት አዕምሯዊ ኩነት የግድ ሚሚ ስብሐቱን ህወሓት ሲነካ ትግራይ ተነካ እንድትል፤ስለ ህወሓት ሲወራ ስለ ትግራይ የተወራ አድርጋ እንድትቆጥር ያደርጋታል፡፡በዚህ ረገድ ሚሚ ብቸኛ ሳትሆን በዛ ያሉ የአመለካከት ወንድምና እህቶችም እንዳሏት በእርግጠኛነት መናገር ይቻላል፡፡
ከአዕምሯዊ ግንዛቤ ውጭ የፖለቲካ ደጀን ይሆነናል ከማለትም ሆነ ተብሎ የትግራይን ሕዝብ “መጡባችሁ” በሚል ፈሊጥ እንደመሸሸጊያ ይጠቀሙበታል፡፡ከዚህ ጋር ተያያዥ ያለው የተማሪነት ገጠመኜን በምሳሌነት ማቅረብ እፈልጋለሁ፡፡
በአፄ ኃ፨ሥላሴ ዘመነ፡መንግስት የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ሳለን ብዙ ጊዜ በፖለቲካ ምክንያት ረብሻ ይነሳ ነበር፡፡አንድ ቀን ከሰዓት በኃላ የት፨ቤቱ አሜሪካዊ ዳሬክተር ሁላችንንም ሰብስበው ተግሳፅና ቁጣ ከሰነዘሩብን በኃላ ከመሐከላችን የነበረውን በጣም የታወቁ የአፄ ኃ፨ሥላሴ የቅርብ ዘመድ የራስነት ማዕነግ ያላቸውን ሰው የልጅ ልጅ ከሁላችንም በተለየ ነጥለው የሚከተለውን ተናገሩት፡፡
“አንተ ብዙ ጊዜ ረብሻ ላይ እፊት ፊት ትቀድማህ ሆኖም ግን ችግር በሚመጣብህ ጊዜ ከዚህ ቀደም ደጋግመህ እንዳደረግኸው አያጥ ጫማ ውስጥ ገብተህ ትደበቃለህ ፡፡”
አሁንም እኔ እንደሚታየኝ አንዳንድ የህወሓት አቀንቃኞች ፓርቲው ላይ ለሚሠነዘረው ሒስ መልስ መስጠት ሲቸግራቸውና የአመለካከት አጣብቂኝ ውስጥ ሲወድቁ ሮጠው የትግራይ ሕዝብ “ጫማ” ውስጥ ይደበቃሉ፡፡በመሆኑም ለእርሷ ህወሓትን የተቸ ሁሉ ፀረ፡ትግሬና ትምክህተኛ ነው፡፡
በፕሮግራሙ ላይ ከተነሱት ነገሮች በጣም የገረመኝ ሚሚ ስብሐቱ ሳትሆን ከተወያዮቹ አንዱ “እኔ የምፈራው አሁን እነዚህ ሰዎች(እነ ዳኛቸው) ክቡር ዶ፨ር ቴዎድሮስ አድኃኖምን ትግሬ ብለው እንዳያዋርዷቸው ነው፡፡” ሲል መስማቴ ነው፡፡ “እንዳያዋርዷቸው” የሚለው መቼስ የሚገርም ቃል ነው፡፡ እኔ እስከገባኝ ድረስ በዚህ አነጋገር ለማለት የተሞከረው ሦስት ጉዳኞችን ነው፡፡አንደኛ፡፡“የተሾሙትን ትግሬዎች እንበላቸው ” በማለት ሹመቱ የት ቦታ እንደሄደ ለማድበስበስ ነው፡፡ሁለተኛው፡፡ደግሞ የተሾሙትን ከብሔር በላይ የሆኑ ሰዎች አድርጎ ለማቅረብ ነው፡፡በሦስተኛ ደረጃ ትግርኛ የሚናገርን ሰው “ኤርትራዊ ነኝ” እስካላለ ድረስ ትግሬ ነው ብለን ብንገልፀው ሰውየውን “ማዋረድ” የት ላይ እንደደሆነ ሊገባኝ አይችልም፡፡
መደምደሚያ
ጤናማ የሆነ የፖለቲካ ውይይት ለማካሔድ ከስድብና ከዘለፋ ባሻገር በአስተያየትና በሐሳብ ላይ የተሞረኮዘ ሙግትና ውይይት ምንጊዜም ለዴሞክራሲ ማበብ ትልቅ አስተዋፅዖ ያደርጋል የሚል እምነት አለኝ፡፡ከዚህም በተጨማሪ ዴሞክራሲ ተመራጭ የሆነው የሐሳብ ልዩነት የሚያስተናገድበትን መድረክ አመቻችቶ ስለሚያቀርብ ነው፡፡
ሆኖም ከዚህ አኳያ የሚሚ ስብሐቱን የቅርብ የፖለቲካ አካሄድ ስንፈትሽ ለዴሞክራሲ ይበጃሉ ተብለው ከተቀመጡት ወሳኝ መርሆችዎች ያፈነገጠች መሆኗን እንገነዘባለን፡፡
አንደኛ፡፡የሐሳብ ልዩነትን በኃይልና በዘለፋ ለመወሰን መሞከር ኢ፡ዴሞክራሲያዊ መሆኑን ትዘነጋለች፡፡
ሁለተኛ፡፡የዴሞክራሲ ግብ ሄዶ ሄዶ ነጻነትን (ሊበርትይ) መጎናፀፍ ነው፡፡ነፃነት ስንል ደግሞ የቡድን ብቻ ሳይሆን የግለሰብም ነፃነት ማለታችን ነው፡፡እነ ሚሚ እንደሚያደርጉት ከእነርሱ ሐሳብ ውጪ የቀረበን ድምፅ እንዳይሰማ ለማፈን ከመሞከር በተጨማሪ “የብዙኃን መገናኛ በእጃችን አለ” በማለት የሐሳብ ብዝኃነትን ገድሎ አንድን ሐሳብ በብቸኝነት ለማንገስ የሚደርግ ሙከራ የነፃነት ገፈፋ ብቻ ሳይሆን ትልቅ የመብት ጥሰት መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡
ሦስተኛ፡፡ዴሞክራሲ ከሁሉም በላይ በሥነ፡ምግባር ፣በፖለቲካ እንዲሁም በማህበረሰብ ጉዳይ የተኮተኮተ መልካም ዜጋ ለማፍራት የሚያስችል ሥርዓት ነው፡፡ከዚህም አኳያ ስናየው ዴሞክራሲ ትልቅ ት፨ቤት ነው፡፡
ለዚህ የማስተማር ተግባሩ ሬዲዮን ጨምሮ ሎሎች መገናኛ ብዙኃን ዓይነተኛ መሳሪያዎች ናቸው፡፡ሚሚ ስብሐቱ ግን ይህንን መልካም ሚና ሙሉ በሙሉ ለመጫወት የፖለቲካ ድባቡ ባይፈቅድላትም በራሷ ተነሳሽነት ትንሽም እንኳ ጥረት ስታደርግ አይስተዋልም፡፡
እንዲያውም የሚሚን ፕሮግራም በምናይበት ጊዜ የመንግስት ሚዲያ የራሱን ሐሳብ ለማቅረብ የተሳነው ይመስል፤ እርሷም ተጨማሪ የግል ሬዲዮ በብዛት ሳይሆን በጥቂቱ በሌለበት አገር ውስጥ በሞኖፖል ለተያዘው የዜና አውታር አጋር መሆኗ የሚያሳዝን ነው፡፡
ዓለማየሁ ገ፨ሕይወት “እታለም” በተሰኘ ስብስብ ግጥሞች “በምድር ማሕፀን” በሚለው ግጥሙ በዋናነት የቀይሽብር ሰለባ የሆኑት ሰማዕታት አጽም ተቆፍሮ ሲወጣ በወቅቱ የተሰማውን ስሜት የገለጸ ሲሆን፣ወደፊትም ይኼ ነገር እንዳይደገም ያሰጠነቀቀበትን ምክር ያካተተ ግጥም ነው፡፡
ዓለማየሁ በግጥሙ በተለይም ስለወደፊቱ ያሰጠነቀቀበት እኔ ካነሳሁት ሐሳብ ጋር ተያያዥነት ስላላው ጥቂት ስንኞች “ከምድር ማሕፀን” ተውሼ ለአንባቢያን እጋብዛለሁ፡፡
…።አፈር ያደረግነው፤
ጭንጫ መሬት ያልነው
ያገራችን ምድር ፣ተራራው ሜዳችን
ሰርጡ ወጣ ገባው፣ለምለሙ መስካችን
በተማሰ ቁጥር፣ወጣ ታሪካችን፡፡
…ሰርዶና ቄጠማ
ሰንበሌጥ አክርማ
እሚያበቅለው አፈር፣
ዋንዛና ባህርዛፍ፣
ዳጉሳና ነጭ ጤፍ
እሚያፈራው ምድር ፣
ዳግም ተማሰና፣ተገኝ ሌላ እውነት
የአንድ ትውልድ ታሪክ
የአንድ ትውልድ ሃፍረት፦
ሕጻንና አዛውንት
ኮረዳና አሮጊት
ጎልማሳና ወጣት
እንበለ ርህራሄ፣የተጨፈጨፋ የተቀበሩበት፦
…ነገ እሚቆፈረው ፣እሚማሰው አፈር
ከህሊና ንቅዘት፣
እንዲሆን የጸዳ፣ከዘመን ቸነፈር
በምንወጥነው ግብር፣በምንተክለው ችግኝ
ተንኮል እንዳይገኝ፣
ህፀፅ እንዳይገኝ፣
ሰርክ ፀሎታችን፣
ነገ እሚነበበው፣ታሪክ ሕይወታችን
የሚያስደስት እንጂ ፣ላይሆን እሚያስከፋ
አንገት እሚያስደፋ፣
ሀገር እሚያለማ፣እንጂ እማያጠፋ
መሆኑን ማሳየት፣አለብን በይፋ፦
ከእንግዲህ ምድራችን፣ማሕፀኗ ሲቃኝ
በወርቅና በአልማዝ፣ ተገጥግጦ እንዲገኝ
ለእውነት እንቁምና፣ቸር ቸረሩን እንመኝ፡፡

ይህ ጽሑፍ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ቅጽ 7 ቁጥር 145 ጥር 2005 ዕትም ለንባብ የበቃ ነው፡፡

አቶ አሊ አብዶ ስዊዲን ደርሰዋል/ኢሳያስን ከድተዋል::INTERVIEW


To the left, Ali Abdu, one of Eritrea's dictator's closest collaborators, would have traveled to Eritrea on 26 November, but never showed up. Since then he has been missing. The picture in the middle, the Swedish journalist Dawit Isaak, imprisoned in Eritrea. To the right, can hit Ali Abdu have fled.


የኤርትራውየማስታወቂያ ሚኒስትር የነበሩት አይቶ አሊ አብዶ አህመድ ሃገሪቱን ለቀው ወጥተዋል የሚኖሩትን በስዊዲን በምስጢራዊ ቦታ ነው ሲል  Expressen የተባለ የስዊዲን ጋዜጣ ዘገበ::ለጛዜጣው ሪፖርተር ቃሲም ሃማዴ ጋር ቃለምልልስ አድርገዋል::

አቶ አብዱ እንዳሉት በኤርትራ እስር ቤት የሚገኘውን ዳዊት ኢሳቅ ምን አይነት ሁኔታ ላይ እንዳለ የስዊዲን መንግስት አለመጠየቁ እንደገረማቸው አስታውቀው ለቤተሰቡ ግን ምኒም ተስፋ ለመስጠት አልደፍርም ብለዋል::በህይወት መኖሩን እየተጠራጠሩ::ምንሊክ ሳልሳዊ 
የ47 አመቱ አሊ አብዱ በኖቮምበር ወደ ጀርመን ለስራ ጉድይ ከሄዱ በሁዋላ አልታዩም ነበር...እኚህ የኢሳያስ ለረዥም አመታት የቅርብ ሰው የሆኑት ሲለሳቸው ሚኒም ነገር አልተሰማም ነበር...ለጋዜጠኞችም ለመናገር አልደፈሩም ነበር...ቢሆንም አሜሪካን አገር ከሚኖሩት በወንድማቸው በአይቶ ሳላህ የሱፍ አማካኝነት ለስዊዲን ጋዜጣ ቃለምልልስ ሰተዋል::ምንሊክ ሳልሳዊ 
ማንኛውን ሰው ካለፍርድ ቤት ትዕዛዝ እና ካለ ማስረጃ በስልክ በሚሰጥ ትዕዛዝ ነው የሚያዘው ያሉት ሚኒስትሩ ከምዕራባውያን የደህንነት ሰዎች የሚመጣውን ጥያቄ በመፍራት የሚደረግ ሲሆን....ዳዊት ይሳቅን ጨምሮ ሌሎች የፖለቲካ እና የህሊና እስረኞች የት እንዳሉ ማንም አያውቅም ብለዋል::ለመጠየቅም የሚደፍር የለም ሲሉ አክለውበታል::በሃገሪቱ የጉረላ/ደፈጣ አይነት የፖለቲካ ባህል ያለ ሲሆን ማንኛውም ትዕዛዝ ሲመጣ ለምን ሳትል መፈጸም አለብህ ሲሉ ተናግረዋል::
በፖለቲካ እስረኞች ላይ ምን እንደተፈፀመ እንደማያውቁ እና ይህንን የሚያውቀው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ እና የደህንነት መዋቅሩ ብቻ ነው ብለዋል::የፖሊስ አዛዦች እንኳን ይህን አያውቁም::
አገሪቱን ለቀው ከወጡ ከኖቨምበር ጀምሮ አባታቸውን ጨምሮ ወንድማቸው እና የ15 አመት ሴት ልጃቸው በደህንነት ሃይሎች ተይዘው የት እንዳሉ አይታወቅም:: ምንሊክ ሳልሳዊ

በአሜሪካ የሚኖሩት ወንድማቸው ሳላህ የኑስ ወንድሜ ለመጪው የኤርትራ  ትውልድ ያለውን መጨነቅ እና ፍራቻ ስሜቱን ረብሾታል ብለዋል::
ENGLISH TRANSLATIONምንልክሳልሳዊ 




Journalist Dawit Isaak has been imprisoned in Eritrea: 

Tuesday, January 29, 2013

የኤርትራ ወጣቶች በሮም የሚገኘውን የኤርትራ ኢንባሲ ተቆጣጠሩት

       
They say that we are romantic revolutionaries. It is true we are so different, we are willing to give their lives for what we believe.

       

ምርጫ ቦርድ እንደተጠበቀው ተጨማሪ የመመዝገቢያ ቀን ሰጠ


ጥር ፳፩ (ሀያ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-በተመዝጋቢዎች ድርቅ የተመታው መጪው የወረዳና የአካባቢ ምርጫ ምዝገባ ለሁለት ቀናት የተራዘመ ሲሆን፣ የኢህአዴግ ካድሬዎች በዩኒቨርስቲዎች ሳይቀር እየገቡ፣ ግለሰቦች እንዲመዘገቡ ካልሆነ ግን ችግር እንደሚደርስባቸው እየገለጡ ነው።
የኢሳት ምንጮች እንደገለጡት ካድሬዎቹ በዩኒቨርስቲዎች እየዞሩ ሰራተኞችን ተመዝግባችሁዋል አልተመዘገባችሁም እያሉ ሲጠይቁ ውለዋል።
የኢህአዴግ ካድሬዎች በምርጫው ያልተመዘገቡትን ” ከእኛ ጎን ናችሁ ወይስ ከአሸባሪዎች ” በማለት እያስፈራሩ እንደሚገኙ ኢሳት ያነጋገራቸው በርካታ ሰዎች መግለጻቸውን መዘገባችን ይታወሳል።
33 የፖለቲካ ድርጅቶች፣ ለኢህአዴግ ምርጫ አጃቢዎች አንሆንም በማለት ራሳቸውን ለማግለል መወሰናቸውን መግለጻቸው ይታወሳል።
ኢህአዴግ በበኩሉ ተቃዋሚዎች በምርጫው የማይሳተፉት ጥቅም ስለማያገኙበት ነው በማለት ተቃዋሚዎች ለወሰዱት እርምጃ መልስ ሰጥቷል።
ምርጫ ቦርድ የተመዝጋቢዎች ቁጥር በእቅዱ የተቀመጠውን ያሟላ ነው በማለት ቢገልጽም ፣ ኢሳት ያገኘው መረጃ እንደሚያሳየው እስካሁን የተመዘገበው ህዝብ ከታቀደውም ከግማሽ በታች ነው።

ከግብርና የተገኘው የውጭ ምንዛሬ ከግማሽ በታች ቀነሰ


ጥር ፳፩ (ሀያ አንድቀን ፳፻፭ /

ኢሳት ዜና:-በግብርና ዘርፍ ባለፉት ስድስት ወራት የሆልቲካልቸር፣ሥጋና የቁም እንስሳት የወጪ ንግድ ገቢ
በአስደንጋጭ ሁኔታ ማሽቆልቆሉን አቶ ተፈራ ደርበው የግብርና ሚኒስትር ዛሬ ለፓርላማው ያቀረቡት ሪፖርት
ጠቆመ፡፡

2005 የኢትዮጵያ የበጀት ቀመር የመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት ከሥጋና ከቁም እንስሳት ከወጪ
ንግድ(ኤክስፖርት) 299 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ለማግኘት ታቅዶ ማሳካት የተቻለው ከግማሽ በታች
ማለትም 130 ሚሊየን ወይም የዕቅዱን 44 በመቶ ያህል ነው፡፡ከዚህ ገቢ ውስጥ 71 በመቶ የቁም እንስሳት
ድርሻ ሲሆን ቀሪው 29በመቶ ከሥጋ ኤክስፖርት የተገኘ ነው፡፡

በሆልቲካልቸር(አበባ፣አትክልትና ፍራፍሬዘርፍም በስድስቱ ወራት ከኤክስፖርት 105 ሚሊየን ዶላር የተገኘ
ሲሆን ይህም ከዕቅዱ ጋር ሲነጻጸር አፈጻጸሙ 46 በመቶ ነው፡፡

የኤክስፖርት ገቢው በምን ምክንያት እንደቀነሰ ሚኒስትሩ ለፓርላማው በንባብ ባቀረቡት ሪፖርት ላይ
የጠቀሱት ነገር የለም፡፡

በአምስት ዓመቱ የመንግስት መርሃግብርን የተለጠጠ ዕቅድ ለማሳካት በሚል ሁሉም መንግስታዊ ተቋማት
የተለጠጠና ሊፈጸም የማይችል ዕቅድ ከመያዛቸው ጋር በተያያዘ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለይ የኤክስፖርት
ገቢው ከዕቅዱ አንጻር ሲመዘን በከፍተኛ ደረጃ ማሽቆልቆል እየታየበት መሆኑን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው
ምንጮች በተደጋጋሚ መግለጻቸው የሚታወስ ነው፡፡

በዚህ ደካማ መንግስታዊ አፈጻጸምም ሶስተኛ ዓመቱን የያዘው የአምስት ዓመት የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን
ዕቅድ የመሳካቱ ጉዳይ ጥያቄ ምልክት ውስጥ መግባቱም በመታየት ላይ ነው፡፡

በኢትዮጵያ የሚታየው የውጭ ምንዛሬ እጥረት ከፍተ ደረጃ መድረሱን መረጃዎች አመልክተዋል። ችግሩ
በዚሁ ከቀጠለ መለስተኛ መሻሻል አሳይቶ የነበረውን የዋጋ ግሽበት ቀድሞ ወደ ነበረበት ቦታ ሊመልሰው
ይችላል የሚል ፍርሀት አለ።

አቶ ዱባለ ገበየሁና ሁለቱ ዐቃብያነ ህጎች ክስ ተመሰረተባቸው


ጥር ፳፩ (ሀያ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-በዳውሮ ዞን ተነስቶ የነበረውን ግጭት ተከትሎ አቶ ዱባለ ገበየሁ ፣  አቶ ጎሳሁን ዶሳ ዶሻና አቶ ግዛቸው ታደሰ ከበደ     ትናንት ከሰዓት በኋላ ክስ ተመስርቶባቸዋል። ግለሰቦቹ  ሕዝብን በመንግሥት ላይ በማነሳሳትና በማሳመጽ ፣ ሕገመንግስቱን በኃይል ለመናድ በመሞከር  እንዲሁም የመንግሥትን ንብረት በአመጽ በማስወደም ወንጀል ተከሰዋል።
ኢሳት ያለውን የመረጃ ሰንሰለት ተጠቅሞ አቶ ዱባለን በእስር ቤት ውስጥ አነጋግሮታል::
ከዳውሮ ዞን ፖለቲካ ክፍል በተገኘው ምስጢራዊ መረጃ መሠረት በታሰሩት በእነ አቶ ዱባለ ገበየሁና በሌሎችም ላይ የሐሰት ማስረጃ ለማዘጋጀት እየተሰራ ነው። ገንዘብ እየተከፈላቸው ለመመስከር የተዘጋጁ ሰዎች መኖራቸውን ለማወቅ ተችሎአል።
በዞኑ የሚታየው አለመረጋጋት ያሳሰበው መንግስት ግለሰቦቹ በአካባቢው የሚደረገውን ተቃውሞ በማደራጀት በኩል እጃቸው አለበት በሚል እንዳሰራቸው፣ ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ሀይሎች ድርጅት የደቡብ ክልል ዋና አደራጅ አቶ ዱባለ ገበየሁ መግለጻቸው ይታወሳል።
አቶ ዱባለ በክልሉ ያለውን የመልካም አስተዳደር ችግር እርሳቸው የኢህአዴግ አባል በነበሩበት ጊዜ በተለይም የክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት እና  የደኢህዴግ የፖለቲካ ጉዳይ ሀላፊ የሆኑት አቶ አለማየሁ አሰፋ ቤተሰቦቹን እያሾመ ነው በማለት ገምግመዋቸው እንደነበርና አሁን የሚደርስባቸው ነገርም የዚያ በቀል መሆኑን ገልጸዋል።
በማረቃ ወረዳ በማሪ አካባቢ ሰሞኑን በተነሳው የሕዝብ አመጽ ሕዝቡ በፖሊስ ላይ እርምጃ መውሰዱ ይታወሳል።
ዋካ የኔሰው ገብሬ ዲሞክራሲና ፍትህ በሌለበት ሁኔታ መኖር አልፈልግም በማለት ራሱን በእሳት አቃጥሎ ያጠፋበት ከተማ መሆኑ ይታወቃል።

ESAT Daily News Amsterdam 29 January 2013 Ethiopia


Monday, January 28, 2013

እነ አዳነ ግርማን ያፈሩ የደቡብ ኳስ ሜዳዎች እንደ አዲስ አበባ የሕንፃ ሲሳይ ሊሆኑ ነው



እነ አዳነ ግርማን ያፈሩ የደቡብ ኳስ ሜዳዎች እንደ አዲስ አበባ የሕንፃ ሲሳይ ሊሆኑ ነው
በኢብራሒም ሻፊ
ሙሉጌታ ምሕረት ወደ ደቡብ አፍሪካ የተጓዘው ብሔራዊ ቡድን አባል አይደለም፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ባደረጋቸው አራት የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታዎች ላይም አልተሰለፈም፡፡
እንዲያውም ለብሔራዊ ቡድኑ ከተጫወተ ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ ሆኖም ግን ይሄው የሐዋሳ ከነማ አምበል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ወደ ደቡብ አፍሪካ ተጉዞ እንዲፋለም ባለውለተኛ ነው፡፡

ሙሉጌታ በማጣሪያ ጨዋታዎቹ ባይሳተፍም በእርሱ ምክር የተገሩትና የእርሱን ፈለግ የተከተሉት አዳነ ግርማ፣ ሽመልስ በቀለ እና በኃይሉ አሰፋ የብሔራዊ ቡድኑ ቁልፍ ተጫዋቾች ናቸው፡፡ ሙሉጌታ ለእነዚህ ተጫዋቾቹ የሰጠው ምክሩንና ልምዱን ብቻ አይደለም፡፡ “ኮረም ሜዳንም” ጭምር እንጂ!

ኮረም ሜዳ የሙሉጌታ ሜዳ ነው፡፡ ከመኖሪያ ቤታቸው በዕርምጃዎች ርቀት የሚገኘው ይሄው ሜዳ ከአንዴም ለአሥር ጊዜያት በመንግሥት ለሌላ ዓላማ ታጥሮ ነበር፡፡ “ሜዳዬ ነው” ብሎ የሚያምነው ሙሉጌታ ግን እጅ አልሰጠም፡፡ ቀን የመንግሥት ሰዎች መጥተው ካጠሩት ማታ ሙሉጌታ እና ጓደኞቹ የታጠረበትን ዕቃ ያፈራርሳሉ፤ ሽቦም ከሆነ ይቆርጣሉ፡፡ ከሜዳው አጠገብ ትምህርት ቤት በመኖሩ ለረዥም ጊዜ ይሄንን ቦታ “ለማስፋፊያ” ብሎ የተመኘው ትምህርት ቤቱ ነው፡፡

ለዓመታት ቦታውን ሲያጥረው የነበረውም ይሄው ትምህርት ቤት ነው፡፡ ሙሉጌታ ግን ተፋለማቸው፡፡ ለረዥም ጊዜ ጓደኞቹን አስተባብሮ የሽቦ አጥርን ቆርጧል፤ የተገነባ አፈርሷል፡፡ የትምህርት ቤቱ ማስፋፊያ ኮሚቴ አባላት በድርጊቱ ሁሉም እየተማረሩ ነበር፡፡ አፍራሹን አለማወቃቸው ሌላ ሕመማቸው ነበር፡፡ በተለይ በኮሚቴው ተሰሚነት የነበራቸው የራሱ የሙሉጌታ አባት ምሕረት ምን ማድረግ ይሻላል? ብለው ብዙ ተጨንቀዋል፡፡ በወቅቱ በእግር ኳስ ትልቅ ደረጃ እደርሳለሁ ብሎ ይተጋ የነበረው ትልቁ ሙሉጌታ ይሄንን ተመልክቶ አላስቻለውም፡፡ “አፍራሹ እኔ ነኝ” አለ፡፡ “የማፈርሰውም እግር ኳስን መጫወት በጣም ስለምወድ ነው” ብሎ እቅጩን ተናገረ፡፡ አባት በመጀመሪያ ተቆጡ፡፡ ሆኖም ግን ልጃቸው እንዲህ ዓይነት ጥፋት ውስጥ ያገኘበትን ምክንያት በጥልቀት አሰላሰሉ፡፡ ለእግር ኳስ ያለው ጥብቅ ፍቅር በሜዳው ላይ ዓይናቸውን የሚጥሉ ሰዎችን እንደ ጠላት እንዲመለከት እንዳደረገው ተገነዘቡ፡፡ ይሄ ሜዳ የትምህርት ቤቱ ማስፋፊያ ቢሠራበት ልጄና ጓደኞቹ የት ሄደው ይጫወታሉ ብለው ራሳቸውን ጠየቁ፡፡ በቀጣይ ስብሰባ ትምህርት ቤቱ ለማስፋፊያ ሥራ ሌሎች ዘዴዎችን መጠቆም እንዳለበት አስረዱ፡፡ ኮረም ሜዳ መነካት እንደሌለበት በደንብ አብራሩ፡፡

ኮረም ሜዳ ነፃ ወጣ፡፡ ሙሉጌታ የሚጫወትበት ሜዳ አገኘ፡፡ እዚህ ሜዳ ላይ ወጣቱ ሙሉጌታ ተአምር ሲያሳይ አዳነ፣ ሽመልስ እና በኃይሉ ምነው እርሱን በሆንኩ ብለው ተመኙ፡፡ ከኮረም ሜዳ ወደ ሀዋሳ ከነማ ሲያመራ እነርሱ ታሪካዊውን ሜዳ ተረከቡ፡፡ በሙሉጌታ ጀግንነት ነፃ የወጣው ሜዳ ላይ እንደልብ ቦረቁበት፡፡ ዛሬ በደቡብ አፍሪካ የሚያሳዩን ተአምር የኮረም ሜዳ ጥንስስ ውጤት ነው፡፡

ደቡብ አፍሪካ የተጓዘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የደቡብ ኢትዮጵያ ተፅዕኖ ያጎላበታል፡፡ ሲሳይ ባንጫ፣ ደጉ ደበበ፣ አበባው ቡጣቆ፣ ጌታነህ ከበደ፣ ቢያድግልኝ ኤልያስ፣ ሽመልስ በቀለ፣ አዳነ ግርማ እና በኃይሉ አሰፋ የደቡብ ፍሬዎች ናቸው፡፡ ለጥንካሬና ቅልጥፍና ዓሣን እየተመገቡ በምቹ ሰፋፊ ሜዳዎች እግር ኳስን እየተጫወቱ ያደጉ ልጆች ናቸው፡፡ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ መድረክ አንገቷን ቀና እንድታደርግ ያስቻሉት እነዚህ ልጆች የአመጋገባቸው፣ ሲቦርቁ ያደጉባቸው ሜዳዎች እና የሙሉጌታ ምክር ውጤቶች ናቸው፡፡

አሁን ግን ችግር አለ፡፡ ኢትዮጵያ ለ29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ በቅታ ነገሮች ቢድበሰበሱም በመንግሥት የተረሳው ስፖርትና እግር ኳስ ትልቅ ችግርን የመጋፈጥ አደጋ ውስጥ ገብቷል፡፡ ላለፉት አሠርታት የእግር ኳስ ተጫዋቾች “ፋብሪካ” እስክትመስል በርካታ ተጫዋቾችን ያፈራችው ደቡብም የዚህ ችግር ገፈት ቀማሽ ለመሆን ተቃርባለች፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ወደ ደቡብ ተጫዋቾች ፊቱን ከማዞሩ በፊት የብሔራዊ ቡድኑ አለኝታ ተጫዋቾች በብዛት ብቅ የሚሉት ከአዲስ አበባና ከድሬዳዋ ነበር፡፡ መንግሥት በሁለቱ ከተሞች የመኖሪያ ቤቶችን ችግር ለመቅረፍ የእግር ኳስ ሜዳዎችን ለግንባታ ዒላማ ሲያደርግ፤ ከቤቶቹ ግንባታ በኋላ አነስተኛም ቢሆን የእግር ኳስ ሜዳዎችን እገነባለሁ ብሎ ያቀደ አይመስልም፡፡

በአዲስ አበባ ከ35 በላይ አንግል ያላቸው ሜዳዎች ሕንፃ ሲገነባባቸው “ይሄ ነገር ጥፋት ነው” ብሎ “ሀይ” ያለ የለም፡፡ ግንባታዎቹ ተጠናቅቀው ወደ ሥራ ሲገባ ለአካባቢው ሕፃናት መጫወቻ ወይም ስፖርት መሥሪያ ሜዳ አንዱም አላሰናዳም፡፡ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ያሉ መጫወቻ ሜዳዎች የማስፋፊያ ሜዳ ሲሠራባቸው ሕፃናቱ እግር ኳስን የመጫወቻ ሜዳ ይቅርና መቆሚያ እንኳን እንደሚያጡ ማንም አልተረዳላቸውም፡፡ ይሄ ችግር የድሬዳዋም ችግር ሆነ፡፡ ውጤቱ ደግሞ ወደ 29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ በተጓዘው ቡድን ውስጥ በግልፅ ታየ፡፡ ድሬዳዋ በዚህ ብሔራዊ ቡድን ውስጥ አንድም ተጫዋች አላስመረጠችም፡፡ አዲስ አበባ ደግሞ ጃንሜዳ እየተጫወተ ያደገውን አሉላ ግርማን፣ አልማዝዬ ሜዳ ቦርቆ ያሳለፈውን አሥራት መገርሳን፣ በመስቀል አደባባይ አስፋልት ሜዳዎች ላይ የፈነጨውን ዳዊት እስጢፋኖስን፣ በፈረንሣይ ለጋሲዮን ሰፋፊ ሜዳዎች የማግኘት ዕድል የገጠመውን ብርሃኑ ቦጋለን እና ለስታዲየም ግንባታ በሚል ኢምፔሪያል አካባቢ የታጠረ ሜዳን ያገኘውን ምንያህል ተሾመን ብቻ አስመርጣለች፡፡ አሁን ግን የአሥራት ሜዳ አልማዝዬ ሜዳ፣ የብርሃኑ የፈረንሣይ ሜዳዎችና የምንያህል ባለውለተኛ ቦታ የሉም፡፡ የአዲስ አበባ ሕፃናትም እግር ኳስን እንዳይጫወቱ የተፈረደባቸው ይመስላል፡፡ በተገኙ ክፍት ቦታዎች ሁሉ ያለምንም ማካካሻ ግንባታ ተለውጦባቸዋል ወይም ተጀምሮባቸዋል፡፡

ስለዚህም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ወደ ደቡብ፣ ቤኒሻንጉል ጉምዝና ጋምቤላ ፊቱን አዙሯል፡፡ የደቡብ የእግር ኳስ “ፋብሪካ” ግን እንደ አዲስ አበባው ሊቆም ተቃርቧል፡፡ በሀዋሳ እና አርባ ምንጫ ያለምንም ማካካሻ የእግር ኳስ ሜዳዎች መኖሪያ ቤቶችና ሕንፃ እየተገነባባቸው ይገኛሉ፡፡

የሀዋሳ ከነማው የመሀል ተከላካይ አንዷለም ነጋ (ቢጣ) የተገኘበት “አሮጌው ሜዳ” ትምህርት ቤት ተሠርቶበታል፡፡ ትምህርት ቤቱ ያለ እግር ኳስ ሜዳ በመሠራቱ በርካታ ወጣቶች ከእግር ኳስ ጋር ተራርቀው ቀርተዋል፡፡ አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው (ሞሪንሆ) በወጣትነቱ ሕፃናትን ሲያሰለጥንባቸው የነበሩ ሁለት ሜዳዎች ዛሬ የሉም፡፡ አንዱ አጠና ተራ ሆኖ እንጨት ይነገድበታል፡፡ ሌላኛው ተሸንሽኖ የሸቀጥ መሸጫ ሱቅና ልብስ ቤቶች ተወልደውበታል፡፡ የዘላለምን ፈለግ ተከትለው እዚህ ሜዳ ላይ ሕፃናትን ያሰለጥኑ የነበሩ እስከ “ቢ” ላይሰንስ ድረስ የነበራቸው አሰልጣኞች በአሁኑ ወቅት የባጃጅ ባለቤትና ሾፌሮች ናቸው፡፡ እግር ኳስን እርግፍ አድርገው ትተውታል፡፡

በሀዋሳ ከተማና በደቡብ ፖሊስ በዋና እና ምክትል አሰልጣኝነት የሠራው አዲሴ ካሳ እንኳን አሁን ሕፃናትን የሚያሰለጥንበት ሜዳ አጥቶ በምሬት ሙያን ስለመቀየር ያስባል፡፡ ሙሉጌታ ጉዳዩን “በጣም የሚያስፈራ” በማለት ይገልፀዋል፡፡ “እኔ ባገኘሁት አጋጣሚ በሙሉ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ግንባታ አስፈላጊነትና የሥልጣኔ ማሳያ አንድ ጎን እንደሆኑ እናገራለሁ” ይላል፡፡ ታዲያ ሰሚ የለም? ብላችሁ ስትጠይቁት “እስካሁን አላገኘሁም፡፡ አሁን ግን የከተማው ከንቲባ አቶ ብሩ ማሞ ጥሩ ነገሮችን እያሳዩኝ ነው፡፡ ቢሯቸው ጠርተው በደንብ ተወያይተናል፡፡ እንደ ጓደኛ ስለተቀራረብን በስፖርት ማዘውተሪያ ሥፍራዎች ግንባታ አስፈላጊነት ተማምነዋል” በማለት ይመልሳል፡፡ ከንቲባውንም እጅግ ያመሰግናል፡፡

በተከታታይ የኢትዮጵያ እግር ኳስንና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንን ለመምራት ዕድሉን ያገኙት የደቡብ ሰዎችስ ምንም ዓይነት ተፅዕኖ ለመፍጠር ሙከራ አላደረጉምን? የመፍትሔ አቅጣጫስ ለማሳየት አልሞከሩም? ሙሉጌታ እዚህ ጋር የንዴት ሳቅ አመለጠው፤ “ወጥተው እንኳን አይተው አያውቁም” በማለት ቁርጡን ተናገረ፡፡ “አሁን ኮረም እና ቄራ ሜዳ ቀርተውናል፡፡ በከንቲባው ዕርዳታ እነዚህን ሜዳዎች ካላቆየን…” በማለት ዝም አለ ሙሉጌታ… በረዥሙ ከተነፈሰ በኋላ “እንደ አዲስ አበባ እና ድሬዳዋ እግር ኳስ በሀዋሳም ይጠፋል…፡፡” ሐዘን የዋጠው ሙሉጌታ ዝምታው በጣም ያሳዝን ነበር፡፡

ከአዘጋጁ፡-
ኢብራሒም ሻፊ በሸገር ኤፍኤም 102.1 የኳስ ሜዳ ፕሮግራም ባልደረባ ነው
http://www.ethiopianreporter.com/index.php/sport/item/522

የከምሴ ነዋሪዎች የሀይማኖት መሪያችንን አናስወስድም በማለት ተቃውሞአቸውን ገለጡ


ጠቅላይ ሰፈሩን በኤርትራ እና ኢትዮጵያ ድበሮች ላይ አድርጎ ወደ ትግራይ እየዘለቀ ተደጋጋሚ ጥቃት በወያኔ ሎሌዎች ላይ በመፈጸም የሚታወቀው የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (TPDM) በቅርቡ እራሱን ይፋ ካደረገው የግንቦት 7 ህዝባዊ ሀይልና ሌሎችም ባካባቢው ከሚንቀሳቀሱ የነጻነት ተዋጊዎች ጋር ግምባር መፍጠሩ ታውቋል።



የከምሴ ነዋሪዎች የሀይማኖት መሪያችንን አናስወስድም በማለት ተቃውሞአቸውን ገለጡ


ጥር ፳ (ሀያ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-በኢሉባቦር ዞን ከመቱ ከተማ 15 ኪሜ ርቀት ላይ በምትገኘው ከምሴ  ቀበሌ ፖሊሶች  ሼህ ሳሊህ አብዱልቃድር የተባሉትን የእስልምና ሀይማኖት መሪ ለመውሰድ በሄዱበት ወቅት ህዝቡ ግለሰቡን አሳልፎ ለመስጠት ፈቃደኛ ባለመሆኑ ችግር መፈጠሩ ታውቋል።
ሼህ ሳሊህ አብዱልቃድር ከዚህ ቀደም በሽብርተኝነት ተከሰው 8 ወራት ከታሰሩ በሁዋላ መረጃ አልተገኘባቸውም በሚል በነጻ ተለቀው ነበር። ባለፈው ሳምንት ፖሊሶች እንደገና ወደ አካባቢው በመሄድ የእርሳቸውን ጓደኛ ያሰሩ ሲሆን፣ ዛሬ ደግሞ ሼኩን ለማሰር ወደ ቀበሌው ሲሄዱ ህዝቡ በነቂስ በመውጣትና ተክቢራ በማለት በመቃወሙ በህዝቡና በፖሊስ መካከል ፍጥጫ ተከስቶ ነበር። የህዝቡን ስሜት የተረዱት ፖሊሶች በቀጥታ ወደ ግጭት ከማምራት ይልቅ ከህዝቡ ተወካዮች ጋር ለመነጋጋር መምረጣቸ      ው ታውቋል።
በሽማግሌዎችና በፖሊስ መካከል ያለው ውይይት ይህን ዘገባ እስካጠናከርንበት ጊዜ ድረስ እንደቀጠለ ነው።
በሌላ ዜና ደግሞ ትምህርታቸውን አቋርጠው ወደ  መጡበት አካባቢ የተመለሱ ከ700 የማያንሱ የባህርዳር ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ፣ ጥያቄያቸው ካልተመለሰ ትምህርት ለመጀመር እንደሚቸገሩ እየገለጹ ነው። ኢሳት የነጋገራቸው ተማሪዎች እንደሚሉት በዩኒቨርስቲው በሙስሊም ተማሪዎች ላይ የሚደርሰው ጭቆና የሚጀምረው ” ወደ ግቢ ለመግባት በሚደረገው ፍተሻ  ነው”
በዛሬው እለት ወደ አዲስ አበባ የተመለሱ ተማሪዎች ከወላጆቻቸው ጋር በመሆን በትምህርት ሚኒስቴር በመገኘት ጥያቄያቸውን ለማቅረብ እቅድ ተይዞ እንደነበር ለማወቅ ተችሎአል። ይሁን እንጅ በተማሪዎች እና በመንግስት መካከል ስለነበረው ውይይት ለማወቅ የተደረገው ሙከራ አልተሳካም። የዩኒቨርስቲው አስተዳደር ሙስሊም ሴቶች ኒቃብ እንዳይለብሱ፣ ወንዶችም ሆኑ ሴቶች በጋራ በግቢው ውስጥ ስግደት ወይም ማንኛውም ሀይማኖታዊ ስነስርአት እንዳያካሂዱ ያወጣው መመሪያ እንደማይለወጥ አስታውቋል።

    በአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ 13 ሚሊዮን ብር በማውጣት ፎርጅድ ቀለሞችን የገዙ ሰዎች ተያዙ


    ጥር ፳ (ሀያ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
    ኢሳት ዜና:-ከዩኒቨርስቲው ምንጮች ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው በዩኒቨርስቲው ፋይናንስና ሂውማን ሪሶርስ ክፍል ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞች 13 ሚሊዮን ብር ዋጋ የሚያወጣ ፎርጅድ ( የተጭበረበረ)የፕሪንተር ቀለምና የኮምፒተር እቃዎችን ገዝተዋል ተብለው በፌደራል ፖሊሶች ቁጥጥር ስር ውለዋል። የተያዙት ግለሰቦች ከዚህ ቀደም በከፍተኛ የሀላፊነት ቦታዎች ላይ የነበሩና ላለፉት 20 አመታት በተለያዩ መንገዶች ለአካባቢው ህዝብ የሚላከውን ገንዘብ በመዝረፍ የሚታወቁ ናቸው።
    አንድ ስማቸው እንዳይገለጥ የፈለጉ ሰው እንደተናገሩት ገቢው በቀን አንድ ዶላር በሆነባት አገር ፣ ይህን ያክል የገንዘብ ዝርፊያ መካሄዱ አስገራሚ ነው ብለዋል። ግለሰቦቹ የኢህአዴግ ባለስልጣናት በመሆናቸው ህዝቡን ለማስደሰት ተብለው ታሰሩ እንጅ በቅርቡ ሊለቀቁ ይችላሉ በማለት ግለሰቡ አክለው ገልጸዋል።
    በኢትዮጵያ ውስጥ የሚታየው ሙስና ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመሄድ ላይ ነው።

    የኦሮሞ ተወላጆች የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ ጠየቁ


    ጥር ፳ (ሀያ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
    ኢሳት ዜና:-በኦሮሞ ጥናት ማኅበር፣ በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢዋ የኦሮሞ ማኅበረሰብ ድርጅት፣ የኦሮሞ ወጣቶች ራስ አገዝ ማኅበር፣ የአፍሪካ ቀንድ የሰብዓዊ መብቶች ሊግና የኦሮሞ ድጋፍ ቡድን የተዘጋጀው ደማቅ የተቃውሞ ሰልፍ አቶ በቀለ ገርባ እና አቶ ኦልባና ሊሌሳን ጨምሮ ሌሎች የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ ጠይቀዋል።
    የአሜሪካ ድምጽ እንደዘገበው ከአቶ በቀለ ገርባ እና ከአቶ ኦልባና ሌሊሣ በተጨማሪ በስም የተጠቀሱት ወልቤካ ለሚ፣ አደም ቡሣ፣ ሃዋ ዋቆ፣ ሞሐመድ መሉ፣ ደረጀ ከተማ፣ አዲሱ ምክሬ እና ገልገሎ ጉፋ በእሥር ላይ እንደሚገኙ የሠልፉ አስተባባሪዎች ተናግረዋል፡፡x
     የኦሮሞ ተወላጆች ሠልፍ በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት
    የኢትዮጵያ መንግሥት አቶ በቀለ ገርባን፣ አቶ ኦልባና ሌሊሣን፣ እንዲሁም ሌሎቹንም ሰባት የኦሮሞ ተወላጅ የሆኑ በፖለቲካ ምክንያት ተይዘው የረዥም ዓመታት እሥራት የተፈረደባቸውን ሰዎች ያለአንዳች ቅድመ ሁኔታ እንዲፈታ፤ የጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ መንግሥት የኢትዮጵያን ሕገመንግሥት እንዲያከብር፣ ከፍርድ ውጭ የሆኑ ግድያዎችንና ንፁሃን ሰዎችን ያለክስ ለተራዘመ ጊዜ ማሠሩን እንዲያቆም የዩናይትድ ስቴትስ መንግስት ጫና እንዲያደርግ ጠይቀዋል።

    ከዚህ በተጨማሪ ዩናይትድ ስቴትስ ለኢትዮጵያ የምጣኔ ኃብት ድጋፍ ከመስጠቷ በፊት የፖለቲካ እሥረኞች ሁሉ እንዲፈቱ አስገዳጅ ጫና እንድታደርግ፤ የኢትዮጵያ መንግሥት የኦሮሞን ሕዝብና የሌሎቹንም ሰብዓዊ መብቶች፣ ሃሣብን የመግለፅና የመደራጀት ነፃነቶችን እንዲያከብር አሜሪካ እንድትጠይቅ፣  የኢትዮጵያ መንግሥት መሠረታዊ የሆኑ የዜጎችን መብቶች የሚጥሱ አዳዲስ ሕግጋትን ሁሉ፣ በተለይ ፀረ-ሽብር የሚባለውን ሕጉን፣ የፕሬስ ሕጉን፣ የረድዔት ድርጅቶች በሃገሪቱ ውስጥ እንደልባቸው እንዳይንቀሣቀሱ የሚገድበውን የሲቪል ማኅበራት ማቋቋሚያ ሕጉን፣ እንዲሁም ስካይፕንና ሌሎችም የሚድያ አገልግሎት ዘዴዎችን መጠቀምን ሕገወጥ የሚያደርገውን በቅርብ ያወጣውን ሕጉን እንዲሠርዝ እንዲሁም መንግሥት የሃይማኖት ነፃነትን እንዲያከብር እና በሃይማኖታዊ ጉዳዮች ውስጥም ጣልቃ መግባት እንዲያቆም የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት እንዲጠይቅ የሚሉ ጥያቄዎች መቅረባቸውን  ሬዲዮው ዘግቧል።x
     የኦሮሞ ተወላጆች ሠልፍ በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት
    ድርጅቶቹ ለኢሳት በላኩት መግለጫ ላይ እንዳመለከቱት ደግሞ የአሜሪካ መንግስት የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በኢትዮጵያ ላኢ ትርጉም ያለው ጫና ማሳደር ካልቻለ የኢትዮጵያ መንግስት በኦሮሞ እና በሌሎች ብሄር ብሄረሰቦች ላይ የሚያደርሰውን ጥቃት ይቀጥላል።
     የኦሮሞ ተወላጅ ለስቴት ዲፓርትመንት በቀጥታ ለፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በግልባጭ  በላኩት ደብዳቤ ላይ አናሳው የትግራይ ነጻ አውጭ ድርጅት ( ህወሀት) 40 በመቶ የሚሆነውን የኢትዮጵያን ህዝብ በሚወከለው የኦሮሞ ህዝብ ላይ ጥቃት እየፈጸመ ነው ብለዋል።
    ደብዳቤው የሬቻን በአል ለማክበር በቢሸፍቱ የተገኙ 200 የኦሮሞ ተወላጆች ላለፉት አራት ወራት መታሰራቸውንና አሁንም አለመፈታታቸውን ጠቅሰዋል። እንዲሁም በየጊዜው ላለፈው አንድ አመት በየሳምንቱ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን እንደሚታሰሩ፣ በቅርቡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በተነሳው የዘር ግጭት 99 ተማሪዎች አብዛኛኦቹ የአሮሞ ተወላኮች መታሰራቸውን አውስተዋል። እንዲሁም የህወሀት አገዛዝ ባለፉት 21 አመታት በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ በአብዛኛው የአሮሞ ተወላጆችን ሲያስር፣ ሲያሰቃይና ሲገድል መቆየቱን ገልጸዋል።
    በቃሊቲ እስር ቤት ከታሰሩ እስረኞች ውስጥ ከ70 በመቶ በላይ የሚሆኑት የኦሮሞ ተወላጆች መሆናቸውን ከእስር ቤት ፖለቲከኞች መናገራቸው ይታወቃል።

    የአርቲስቷ ባል ኢትዮጵያ ውስጥ ታሰረ


    ጥር ፳ (ሀያ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
    ኢሳት ዜና:-ተቀማጭነቱ ለንደን የሆነው የኢትዮጵያ ዳንኪራ የዳንስ ግሩፕ አባል የሆነችው አርቲስት እስከዳር ታምሩ እና ባለቤቷ አበበ ወንድምአገኝ በደህንነት ሃይሎች የዛሬ ሳምንት ቦሌ አካባቢ ታሰሩ።
    እንደ ደብረ ብርሀን ብሎግ  ዘገባ ፤ጥንዶቹ የሁለት አመት ልጃቸውን ይዘው ከሎንዶን ወደ አዲስ አበባ የሔዱት  በአል ለማክበር ነበር።
    እዚያ እንደደረሱ  ከታሰሩ በሁዋላ አርቲስት እስከዳር ስትለቀቅ ባለቤቷ አበበ አሁንም እስር ቤት ይገኛል።
    አቶ አበበ ፍርድ ቤት ቀርቦም የሃያ ቀን ቀጠሮ የተጠየቀበት ሲሆን፤ቤተሰቦቹ  አዲስ አበባ ለሚገኘው ለእንግሊዝ ኤምባሲ ስለጉዳዩ አሳውቀዋል።
    <<ምክንያቱ ፖለቲካዊ ነው የሚል>> ጥርጣሬ ቢኖርም፤እስካሁን የታሰረበት ምክንያት ምን እንደሆነ በግልጽ የታወቀ ነገር የለም።
    ካሁን በፊት በተመሣሳይ ኮሜዲያን መስከረም በቀለ ከብዙ ኣመታት ቆይታ በሁዋላ የ አገሩንና የቤተሰቦቹን ናፍቆት ለመወጣት ወደዚያው ባቀናበት ጊዜ ገና ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ እንደደረሰ በሴኩሪቲዎች ተይዞ መታሰሩ ይታወሳል።
    ጭንቀትና ስጋት ውስጥ የገባው መንግስት ወደ ቤተሰብ ለመጠየቅም ሆነ ለተለያየ ጉዳይ ወደ አገራቸው የሚሄዱ ኢትዮጵያውያን እዛ እንደደረሱ ለቀበሌ ሪፖርት ማድረግ አለባቸው የሚል ህግ ድረስ ማውጣት መድረሱን ያስታወሱ አስተያዬት ሰጭዎች፤ የአርቲስቷ ባል መታሰር የሚያመለክተውም የመንግስት ጭንቀት፣ጥርጣሬና ስጋት እየጨመረ መምጣቱን ነው ብለዋል።

      ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበርነቱን ወሰደች


      ጥር ፳ (ሀያ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
      ኢሳት ዜና:-ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ ለመጪው አንድ ዓመት የ አፍሪካ ህብረትን በሊቀ-መንበርነትን እንዲመሩ ተመረጡ።
      እሁድ አዲስ አበባ  በተካሄደው የ አፍሪካ ህብረት 50ኛ ዓመት የመሪዎች ስብሰባ ኢትዮጵያ የሊቀመንበርነቱን ቦታ ከቤንን መረከቧን የኬንያው ዴይሊ ኔሽን ዘገቧል።
      ይህን ታላቅ ድርጅት ለመጪው አንድ ዓመት እንድመራ በመመረጤ ጥልቅ ደስታ ተሰምቶኛል ብለዋል-አቶ ሀይለማርያም።
      <<ሹመቱንም የምቀበለው በታላቅ አክብሮትን የደስታ ስሜት ነው>> ሲሉ አክለዋል።
      ኢትዮጵያ የ አፍሪካ ህብረትን የ አንድ ዓመት የሊቀመንበርነት ጊዜ ከቤኒን ለመረከብ ፍላጎቷን ያሳየችው ከሳምንታት በፊት በውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር አማካይነት በሰጠችው መግለጫ ነው።
      የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ << የሊቀ-መንበርነቱ ተረኛ ኢትዮጵያ ነች> በማለት ቀደም ብለው የሰጡት መግለጫ፤በህብረቱ አባል አገራት ዘንድ-<<የህብረቱን ፕሮቶኮል ያላከበረ>>ነው የሚል ትችት ማስከተሉ ይታወሳል።
      ትችት የሰነዘሩት አባል አገራት ፤ኢትዮጵያ ሊቀመንበርነቱን  ለመውሰድ ከፍተኛ ፍላጎት ያሳየችው ተራዋ ሆኖ ሳይሆን ህብረቱ 50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዩቤልዩ የሚያከብርበት ስለሆነ ሹመቱ ከዚያ ጋር እንዲገጣጠምላት በማሰብ ነው ባይ ናቸው

      ነገ ዋልያዎቹ ከንስሮቹ ጋር ይፋለማሉ


      ጥር ፳ (ሀያ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
      ኢሳት ዜና:-እየተካሄደ ባለው 29ኛው የ አፍሪካ ዋንጫ የ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የምድቡን የመጀመሪያ ዙር የመጨረሻ ጨዋታ ነገ ከናይጀሪያ ብሔራዊ ቡድን ጋር ያደርጋል።
      ዋልያዎቹ እና ንስሮቹ የሚያደርጉት የነገው ጨዋታ በከፍተኛ ደረጃ በመላው ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ትኩረት ስቧል።
      ምድቡን ቡርኪናፋሶ በ4 ነጥብ ስትመራ ዛምቢያና ናይጀሪያ በ2 ነጥብ ይከተላሉ።
      ዋልያዎች  በ 1 ነጥብ 4ኛ ደረጃ ላይ  ይገኛሉ።
      በመሆኑም በነገው ጨዋታ ዛምቢያ እና ቡርኪናፋሶ አቻ ከተለያዩ፤ወይም ዛምቢያ በቡርኪናፋሶ ከተሸነፈ-ዋልያዎች ወደ ቀጣዩ ዙር ለማለፍ ንስሮቹን በ 1 ጎል ልዩነት ማሸነፍ ይበቃቸዋል።
      በነገው ጨዋታ ዛምቢያ አሸንፎ- ናይጀሪያ ዋልያዎችን ካሸነፈ ሁለቱ ቡድኖች ተያይዘው ሊያልፉ ስለሚችሉ ቡርኪናፋሶዎች ለራሳቸው ማለፍ ሲሉ ማሸነፍ ያ ካልተሳካ እኩል መውጣት ግዴታቸው ነው።
      ከዚህ አንፃር ቡርኪናፋሶዎች ጠንክረው ስለሚጫዎቱ ቢያንስ እኩል መውጣት አይቸገሩም ያሉ የስፖርት ተንታኞች፤ዋልያዎች በስሜት፣ በ እልክና  በተረጋጋ መንፈስ ጠንክረው በመጫዎት ናይጀሪያዎችን ካሸነፉ ወደ ቀጣዩ ዙር በማለፍ ታሪክ ሊዒሩ እንደሚችሉ መክረዋል።
      የ ኢሳት ቤተሰቦች በሙሉ ብሔራዊ ቡድናችን ድል እንዲቀዳጅ ልባዊ ምኞታቸውን ይገልጻሉ

      ESAT Activist Tamagne Beyene Amsterdam tour Advert Ethiopia


      Sunday, January 27, 2013

      እነመለስ ስብሀት ትግል ሲጀምሩ“አማራው ካልተመታ.. የትግራይ ነጻነት የማይታሰብ ነው።


      እርግጥ የወያኔ መሪዎች የሚወዱት ወይም የቆሙለት የህብረተሰብ ክፍል አለ ማለት አይደለም። የሚወዱትም ራሳቸውን ነው። የቆሙትም ለጥቅማቸው ነው። አማራውን ብቻ ሳይሆን ኦሮሞውንም ጉራጌውንም ከንባታውንም አፋሩንም ሁሉንም በየጊዜው ይጨፈጭፉታል። እራሱን የትግራይን ህዝብም አይወዱትም። ሁለት ቀላል ማስረጃ እነሆ።
      በጦርነቱ ዘመን የትግራይ ህዝብ እጅግ የከፋ ድርቅና ረሀብ ሲፈራረቅበት፤ ከመሀል አገር የእርዳታ እህል እንዳይደርሰው መንገድ በመዝጋት፤ እነሱ በተቆጣጠሩት አካባቢና ባልተቆጣጠሩትም አካባቢ “እኛ ነን ለህዝባችን ረድኤት ድርጅቶች የሚያቀርቡትን እርዳታ ማደል ያለብን” ብለው የተባበሩት መንግስታትን አስጨንቀው ለረሀብተኛው እንዲያከፋፍሉ መድሀኒትና ምግብ ይሰጣቸው ጀመር። ያንን በብዙ ሚሊዮን የሚገመት የእርዳታ እህልና ቁሳቁስ ከአረብ ነጋዴዎች ጋር በመመሳጠር በቀጥታ ባህር እያሻገሩ በመሸጥ፤ በኩንታሎች አሸዋ እየሞሉ ለጋሾችን በማታለል እንዲገዙአቸው በማድረግ፤ በሚሊዮን ዶላር ሲንበሸበሹ፤ የጦር መሳሪያ ሲሸምቱ፤ የትግራይ ህዝብ እንደቅጠል ይረግፍ ነበር። እነሱ በየጫካው ከሰራዊቱ እየተሸሸጉ አረቄ ጠግበው ከውሽሞቻቸው ጋር ከረቦ እየደለቁ እየጨፈሩ ይዳሩ ነበር። ሱዳን እየሄዱ ውድ ሆቴሎች ውስጥ ይዝናኑ ነበር።
      ሕጻናት፤ እናቶች፤ አባቶች፤ በረሀብ ሲረግፉ፤…ለመዋጋት አቅም የነበራቸውን ልጆችና አዋቂዎች በእርዳታው ምግብ እያማለሉ ወደውጊያ ሲያስገቡአቸው፤ የቀሩት ሕጻናት፤ድኩም እናቶችና አባቶች በሙሉ፤… እንዲያልቁ አደረጉ። ይህ በሆነበት አካባቢ እነመለስ ስብሀት በዚያን ጊዜ አንድም ተቆጣጣሪ አካል ወይም የውጭም ሆነ የውስጥ ጋዜጠኛ እንዳይደርስ አድርገው የትግራይ ወገናችንን አስፈጁት። ይህንን አላደረግንም ካሉ በቀጥታ የዚህን ጽሁፍ አቅራቢ መሞገት ይችላሉ። እኔም ያደረጉትን በማስረጃ ማመላከት እችላለሁ።
      ሁለተኛው፤ የአውዚንን ጭፍጨፋ እንዴት አንዳቀነባበሩት ማየት ነው። በተባለው ቀን አውዚን ከተማ ገብተው ጉባኤ አንደሚያካሂዱ ወሬው በቅድሚያ እንዲሰራጭና ደርግ ጆሮ እንዲደርስ አደረጉ። አስራ ሁለት ሰዎች ሱዳን ሄደው በቪዲዮ ካሜራ ቀረጻ እንዲሰለጥኑ ተደረገ። ሁሉም ዝግጅት ከተጠናቀቀ በሗላ አንድ ቀን በጠራራ ጸሀይ በአውዚን ሞቅ ያለ የገበያ ቀን፤ በተለያየ አቅጣጫ የህውሀት ሰራዊት ተሰልፎ እየተኮሰ ከተማ እንዲገባና ወደገበያው እንዲያመራ ተደረገ። ወዲያውም የኢትጵያ አየር ሀይል በነሱ ላይ ጥቃት መሰንዘር ሲጀምር፤ ታጋዮቹ በያቅጣጫው እየተሯሯጡና እየተኮሱ ገበያተኛውን እንዲቀላቀሉ ተደረገ። ሕዝቡንም ተቀላቀሉ ። ያ ሁሉ ትርምስና እልቂት ሲፈጸም እነዚያ በቪዲዮ ቀረጻ የሰለጠኑት ተዋጊዎች ዶኩመንታሪ ፊልማቸውን ያነሱ ነበር።በዚያው እለት ነበር ወደ ሱዳን ልከው ድርጊቱ ለአለም መገናኛ ብዙሀን እንዲዳረስ ያደረጉት። ያ እንግዲህ በነሱ ተንኮል ላይ የደርግ ደደብነት ተጨምሮበት በህዝባችን ላይ የደረሰ መከራ ነበር። ታዲያ አነዚህ ለማን ነው የቆሙት? እና እነዚህ አማራውን ብቻ ነው የሚጠሉት? መልሱን ለአንባብያን እተወዋለሁ።
      ውድ አንባቢያን “ዘራፊ ሚሊየነሮች” ለሚለው ጽሁፍ ካደረሳችሁኝ መልሶች አጠር ያለውን አንዱን እንመልከትና ወደሚቀጥለው ጉዳይ እናመራለን። “ ወዳጄ ስለነዚህ እርጉም ሰዎች የጻፍከዉን ከማህደሬ አዉጥቼ ዛሬ አነበብኩት። እግዜር ይስጥህ። ምን እላለሁ። አፍዝ አደንግዝ እንደተደረገብን ሁሉ ዝም ብሎ ማየት ሁኗል ።ጉርሻ በሚሸጥበት አገር ሰዉ በቁንጣን አለቀ ሲሉን ለማመን ይዳዳናል። ምን አይነት እርጉም ወራዳ ትዉልድ እንደሆንን ነዉ የሚያሳየዉ።
      የትግሬ እና የሻቢያ ምሁራን ቀጥፈዉ ዋሽተዉ በድፍረት የሌለ ታሪክ ታሪክ አድርገዉ ተከታዮቻቸዉን እያሳመኑ ነዉ። የእኛ ምሁራን ደግሞ ሲሞዳሞዱ ጥቅም አይቅርብን ብለዉ ሲልከሰከሱ ስለኢትዮጵያ ከሞላ ጎደለ የሚጽፈዉ ያዘነልን ነጭ ሁኗል። ቢያስቡት ቢያስቡት መልስ የሌለዉ ነገር ነዉ። ነገር ግን ትግሬን ምን አደረግነዉ? ትግሬ ከሌሎች ወገኖች በላይ የደረሰበት በደል ምንድነዉ? ኢትዮጵያን ሊያጠፋ የተነሳበት ምክንያት ምንድነዉ? የሚለዉ ነገር ሁልጊዜ ጥያቄ ዉስጥ ይከተኛል።
      የሚገርመዉ በኢትዮጵያ አንድነት ከምንም በላይ ተጠቃሚ የነበረዉ ትግሬ እና ጉራጌ ነበር። ምክንያቱም ካካባቢያቸዉ ወደሌላዉ የኢትዮጵያ ክፍል እየተዘዋወሩ ይጠቀሙ ነበር። ታድያ እነዚህ ከተንኮል ድርና ማግ የተሰሩ ዘወትር ቢላ እየሳሉብን እኛ ስንገነባ እነሱ ሲያፈርሱን እዚህ ደርሰናል። በጽሁፍህ ያልተስማመሁበት የትግራይ ህዝብ ከፍተኛ በደል ላይ እንዳለ ጠቁመሀል።፡በዉነቱ ለእነሱ የዚህ አይነት አባባል ከማሳቅ አልፎ ሌላዉን ሽንታም እያሉ ያላግጡበታል። ከእዉነታዉ ጋር ስለማይዛመድላቸዉ አያምኑትም። የትግራይ ህዝብ በጣም ደስተኛ ነዉ። በፖሊሲ ደረጃ አቦይ ስብሀት አላማችን ለሚቀጥለዉ 10 አመት የትግራይን ህዝብ ወደ መካከለኛ የኑሮ ደረጃ ማሸጋገር ነዉ ብሏል። መቀሌ ዛሬ ደረጃዋ ከአዉሮፓ እኩል ነዉ። ለግንዛቤ እንዲረዳህ ተከታታይ እዛ የሚሰራ የአገር ቤት ትያትር ስላለ እሱን መመልከት ነዉ። የነጻ ትምህርት እድል 100% የሚሰጠዉ ለትግሬ ነዉ ይህም በስዉር አይደለም መለስ ዜናዊ አማራዉ ቀደም ባለዉ ጊዜ ስለተጠቀመ ነዉ ብሎ መልሷል። እዉነትነቱን እንድትመረምር ላንተ ትቸዋለሁ። ወደ አሜሪካ እና አዉሮፓ እየተዘዋወሩ የሚነግዱት ትግሬዎች ናቸዉ። ከትግራይ መጥተዉ ቦታ ተስጥቷቸዉ ሽጠዉ እንዲጠቀሙ የተደረጉት ትግሬዎች ናቸዉ። ብዙ ብዙ ብዙ ማለት ይቻላል። ትግሬ ተጠቃሚ ነዉ ያለዉንም መንግስት በጣም ይደግፋል። ተበድለናል ካሉም እነሱ እራሳቸዉን ለመከላከል ብቃቱ ስላላቸዉ እነሱዉ ይንገሩን እንጅ እኛ የሌለ በደል ባንፈጥርላቸዉ ጥሩ ነዉ። ያለበለዚያ ምንም አልበደልንም ማለት ነዉ በማለት ልጓሙን ያጠብቁብናል። አንዳንድ የዋሆች አዲስ አበባ ደርሰዉ ሲመለሱ ለማኙ ሁሉ ትግሬ ነዉ ይላሉ። እንዴት ያስቃል ያ በትግርኛ የሚለምነዉ ሰዉ ሚስቱን ተቀምቶ የተባረረ የወልቃይት እና ጠገዴ ህዝብ እንጂ ትግሬ አይደለም።
      በተረፈ ጽሁፍህ አንጀት ያርሳል። ጽሁፍህም የደረሰኝ በትግሬዎች አማካኝነት ነዉ። የዛን አይነት ድረ ገጽ እንኳን ለማዘጋጀት አልታደለንም። አብረሀ በላይ የፈለገዉን ያወጣል የፈለገዉን ይጥለዋል። ለምሳሌ ፐሮፌሰር ጌታቸዉ ስለ ምንሊክ እና ዮሀንስ የጻፉት በግማሽ ቀን ዉስጥ ተሰርዟል። የዮሀንስን ክፉነት ስላመላከቱ።”
      ውድ እንባቢያን ለደብዳቤዎቻችሁ ሉላችሁንም አመሰግናለሁ። ዛሬ ለመንገር ወደፈለኩት ጉዳይ እንሂድ፤ እነሆ…
      እንደ አውሮፓውያኑ ዘመን አቆጣጠር ጃንዋሪ 30 1939 ዓም አዶልፍ ሒትለር ሬግታንግ ጀርመን ውስጥ ንግግር ሲያደርግ “ከንግዲህ ጦርነት የሚነሳ ከሆነ ከጀርመን ውስጥ አይሁዳውያንን ነው የማጸዳው። አይሁዳውያን ናቸው ከምድርገጽ የሚጠፉት” ብሎ ተናግሮ ነበር።
      እነመለስ ስብሀት ትግል ሲጀምሩ በፕሮግራማቸው ጽፈው ካስቀመጡት ነገር አንዱ “አማራው ካልተመታ.. የትግራይ ነጻነት የማይታሰብ ነው። መጀመሪያ አማራው መመታት አለበት.. መንበርከክ አለበት” ብለው ነበር።”..አማራ..አማራ.አማራ..አማራ.. አማራ…” ሆነ ህልምና ቅዠታቸው ከውልደት እስከ እለተሞቻቸው።
      “”Holocaust History” በሚል ፕሮጀክት አይሁዶች ያለቁበትን ሁኔታ የሚያጠና የታሪክ ተቋምwww.holocaust-history.org “ለምንድነው ያሁሉ እልቂት በአይሁዶች ላይ የተፈጸመው?” የሚል ጥያቁ ባቀረቡለት ቁጥር የሚሰጠው መልስ “ሒትለር አጥብቆ ስለሚጠላቸው ብቻ ነበር” የሚል ነው። ቀጥሎ አንግዲህ የሚነሳው ጥያቄ “ለምን ነበር ሂትለር አይሁዶችን የጠላቸው” የሚለው ሆነ።
      በተመሳሳይ ሁኔታ መለስ ስብሀት ወደስልጣን አንደመጡ ባይሳካም(ለምን እንዳልተሳካላቸው ወደፊት እናወጋለን) ፍጅቱን ባማሮች ላይ ጀምረውት ነበር፤ “ለምንድነው አማራውን ሕዝብ ሊጨርሱ የተነሱት?” የሚል ጥያቄ ይህ ድርጅት ቢገጥመው “ መለስ ስብሀት አማራዎችን ስለሚጠሉአቸው ስለሚፈሩአቸው ብቻ ነው።” የሚል መልስ እንደሚሰጥ እኔ አልጠራጠርም። “ለምን አማራን ጠሉት?..ፈሩት?” ሁላችሁም የሚመስላችሁን ተናገሩ።
      ሂትለር አይሁዶችን የጠላበት የፈራበት ሁኔታ ሲነገር፤ ያንን ያክል ጥፋት የሚያስደርስ ነው ባይባልም፤ የታሪክ ተመራማሪዎቹ አንዲህ ይላሉ። በመጀመሪያ ደረጃ በ1930 ዎቹ ውስጥ በጀርመንም ሆነ በአውሮፓ ጸረ አይሁድነት አስተሳሰብ የተንሰራፋ ችግር ነበር።ለዚያም መሰረቱ በመጽሀፍ ቅዱስ ታሪከ ክርስቶስን የሰቀሉ ናቸው የሚለው መንፈሳዊ ትምህርት ዋናው ያስተሳሰብ ዘዋሪ እምነት ነበር። ሁዋላ ላይ ግን ያን ሀይማኖታዊ ጥላቻ አንዳንዶች ወደ ፖለቲካ አጀንዳ ለውጠውት ለእኩይ የፖለቲካ አላማ ህዝብን በስራቸው ማሰባሰቢያ ፕሮፓጋንዳ አደረጉት። (አሁን ባገራችን የጎሳ ባህላዊ ግጭቶችን ወያኔዎች የፖለቲካ ልዩነት ቅርፅ ለመስጠት እንደሚሞክሩት አይነት) አይሁዳውንያን በጀርመንም ሆነ ባውሮፓ የላቁ ምሁራን፤ የላቁ ሀኪሞች፤ ፕሮፌሰሮች ፖለቲከኞች በሁሉም መስክ የተዋጣላቸው ሰዎች ስለነበሩ፤ ብዙ ፖለቲከኞች ይፈሯቸው፤ ይቀኑባቸው፤ ይጠሏቸውም ነበር።ሂትለርም አንዱ እንደነበር ታሪኩ ያወሳል። ጀርመን በአንደኛው የአለም ጦርነት የተጠቃችው በነሱ ምክንያት እንደሆነ ያምን ነበር።”በስለላና በመረጃ ጠላትን እያገለገሉ..” ይላል። እናም አንዳንዶች ይህን በመላው አውሮፓ የነበረ ጸረ-ሴማዊነት ወረርሽኝ አንደ መሰረት አድርገው ሂትለር ያንኑ ነው ያጠናከረው የሚሉ አሉ።
      ሌላው ወገን ደግሞ ሂትለር አይሁዶችን የጠላበት ምክንያቱ ቪየና ውስጥ አንድ የስነጠበብ ትምህርት ቤት ለመማር ፈልጎ፤ተቋሙ፤ “ትምህርቱን መከታተል የሚያስችልህ ተሰጥኦና ችሎታ የለህም” ብሎ ማመልከቻውን ውድቅ አደረገበት። የኮሌጁ መምህራንና አስተዳዳሪዎች ባብዛኛው አይሁዳውያን ስለነበሩ በዚያው ቂምና ጥላቻ ቋጠረ።
      ገሚሱ ደግሞ እንደሚለው ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ቀድሞ ሂትለር ከመነሳቱ በፊት በነበረችው ጀርመን ህብረተሰብ ውስጥ፤ አይሁዳውያን በማናቸውም መስክ የተዋጣላቸው (አሁን በአሜሪካ እንዳሉት ማለት ነው) የተሳካላቸው ስለነበሩ፤ ከቁጥራቸው ማነስ አንጻር ከሌላው የጀርመን ዜጋ ጋር ሲያስተያዩዋቸው፤ በትምህርት፤ በንግድ፤ በማናቸውም የስራ መስክ የላቀውን ስፍራ ይዘው ሰለነበር፤ በሂትለር አስተሳሰብ በተንኮልና በሻጥር መላውን የጀርመን ዜጋ ቁልቁል ይዘው እነሱ የበላይ ሆኑ ብሎ ያምን በዚያም ምክንያት ይጠላቸው አንደነበር ተጽፏል።አሁን በኢትዮጵያ መለስ ስብሀት ከልት ስለ አማሮች እንደሚያስበው ማለት ነው። እርግጥ የአማራውን ሕዝብ ከሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ የተለየ ተጠቃሚም ሆነ ተጎጂ የሚያደርገው ምንም ነገር የለም። ድህነትና ጭቆና የዘጠና ሚሊዮን ሕዝብ የጋራ እሴት ናቸው።
      ናዚ ሂትለር ወደ ስድስት ሚሊዮን የሚሆኑ አይሁዳውያንን የፈጀበት ድርጊት ትምህርትነቱ ይላል ይኸው ፍጅቱን የሚያጠናው ተቋም፤ “በተወሰነ የህብረተሰብ ክፍል ጥላቻ የተመረዙ ግለሰቦች ወደ ስልጣን ሲመጡ፤ ሀገር የመምራት እድል ካገኙና አንድ ችግር ከተፈጠረባቸው፤ ለዚያ ችግር ምክንያቱ ነው ብለው የሚያምኑት ያ የሚጠሉት የህብረተሰብ ከፍል ስለሚሆን ሂትለር ባይሁዶች ላይ እንዳደረገው ተመሳሳይ እልቂት ሊፈጽሙ አንደሚችሉ ይታመናል” ይላል ሰነዱ።
      “ያንድ ህብረተሰብ ክፍል ጥላቻ ይዘው ወደ ስልጣን የመጡ…” የሚለው ነገር በቀጥታ ወደ እኛው ጉዶች ያመጣናል። መለስ ስብሀት የሚመሩት የወያኔ መሪዎች ቡድን አማራውን ከዘጠና ሚሊዮን ሕዝብ ነጥለው ለምን ይጠሉታል? ለምን ይፈሩታል? ያኔ በረሀ የነበሩ ጊዜ እንኳ “መላ ኢትዮጵያን ተቆጣጥረን ይህን እድል እናገኛለን” ብለው የሚያስቡ ስላልነበረ ያሻቸውን ይበሉ። ባለፉት ሀያሁለት አመታት ወደደም ጠላም የኢትዮጵያ ሕዝብ እጃቸው ላይ የወደቀ ህዝብ ነው። ሐገር አስተዳድራለሁ የሚል መንግስት የሚያስተዳድረውን ህዝብ አንዱን እያሞገሰ አንዱን ባደባባይ እየሰደበ የሚኖር ያለው ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ነው። “.. ገድለን የቀበርነውን አማራ አታንሱብኝ…..” ጀነራል ሳሞራ ዮኒስ። ‘’.. ለትምክተኛ አማራ ስልጣኑን አንለቅም….” መለስ ዜናዊ። “…ስልጣኑን ካማራና ከኦርቶዶክስ እጅ አውጥተነዋል…..” ስብሀት ነጋ። ‘’ ..ሱማሌ የከብት ጭራ መከተል እንጂ ራሱን ማስተዳደር አይችልም ይሏችሁ ነበር።… ዛሬ እራሳችሁን ማስተዳደር እንደምትችሉ አሳዩአቸው…ነፍጠኞችን..” ታምራት ላይኔ ጂጂጋ 1983። (አሁን እራሳቸው ጌቶቹ የጁን ሰተውታል፤..አያሳስብም)
      ልብ ይሏል፤ መለስ ዜናዊ አማራውን አንዴት ይጠላ እንደነበር። የወያኔ መሪዎች ስብሀት ነጋና ሌሎቹም ሁሉ፤.. ዋና ዋና የጦሩን አዛዦች ጨምሮ.. በዚህ ህዝብ ላይ ያላቸው ጥላቻና ፍራቻ ከቁጥጥራቸው ውጭ የወጣ በመሆኑ በያጋጣሚው በአንደበታቸው ሲገልጹት መስማት እንግዳ ነገር አይደለም። ሀያ ሁለተኛ አመታቸው። ለምን?.. መቼ ነው የሚማሩት? ..መቼ ነው የሚታረሙትስ? የኢትዮጵያ ህዝብ እነሱን ትምህርት ቤት ለመጨመር፡ ይህን የደንቆሮ ጡንቻቸውን ለማምከን እንደገና ጦርነት መክፈት ሊኖርበት ነው?
      ለምሆኑ የጥላቻቸው መሰረት ምንድነው?
      ሂትለር ሁለተኛው የአለም ጦርነት አካባቢ፤ “ጦርነት ከእንግዲህ በሗላ ከተቀሰቀሰ” አለ “አይሁዶችን አያድርገኝ”… እንዳለውም መጀመሪያ እራሱ ፖላንድን በመውረር ጦርነቱን ሲባርከው ሶስት ሚሊዮን የሚሆኑ አይሁዳውያን በቁጥጥሩ ስር ወደቁ። ከዚያ ወደ ሶቬት ሲዘምት ያንኑ ያህል ህዝብ እጁ ገባ። እነሱን እየመነጠረ ወደ መቀቀያ ካንብ ይሰበስባቸው ጀመር። ገድሎ ገድሎ መጨረስ ሲያቅተው።
      እነመለስ ስብሀት በጦርነቱ ወቅት፤ ጦርነቱ ሰልችቶት የኢትዮጵያ ጦር ሰራዊት በገፍ እየሄደ ሲማረክላቸው፤ “አማራ ነን” ያሉትን የዋሀን እየመረጡ በመርዝም በጥይትም ይፈጇቸው ነበር። ከባድ የጉልበት ስራ እያሰሯቸው ጉርጓድ እስር ቤት እያጎሯቸው ሰውነታቸው እስኪተላ እየደበደቧቸው ይገሏቸው ነበር።
      ሂትለር ስልጣኑን ከተቆጣጠረበት ጃንዋሪ 1933 ዓም ጀምሮ በአይሁዳውያን ላይ ባደባባይና በሀገሪቱ መገናኛ ብዙሀን ሽብር መንዛት ጀመረ።ባይሁዳውያንና በሌሎች የጀርመን ዜጎች መካከል የልዩነት ግንብ መገንባት ጀመረ።
      በተመሳሳይ ሁኔታ እነመለስ ስብሀት መላ አገሪቱን ተቆጣጥረው የሽግግር መንግስት መሰረትን ብለው አዲስ አበባ ምክር ቤት ገብተው፤ መለስ ዜናዊ ምክር ቤት ውስጥ ለተሰበሰቡት የዘር ድርጅቶች በሙሉ፤ ለነባሮቹም ወዲያው አዳዲስ ለተፈለፈሉትም ሁሉ ወንበር ሲያድል፤ አማራውን አላስጠጉትም ነበር። ሁሉም መንግስት ናችሁ ሲባሉ ዘለሉ፤ ጨፈሩ፤ ያለወያኔ በአለም ላይ ሰው አልተፈጠረም አሉ።የብሄር ብሄረሰብ ተወካዮች። አንዳንዶቹ “በቃ ከንግዲህ እንደብርቅየ አራዊተ ታየን” አሉ። ኖርናት ።ሗላ ላይ ወያኔ እንደ አራዊቱ እያደነ ሊበላቸው። በገሀድ ግንቡ ያኔ መገንባት ተጀመረ።
      ሂትለር ስልጣኑን እንደተቆጣጠረ አይሁዳውያንን በገፍ ከስራ ከትምህርት ተቋማት ከማናቸውም መስክ ማፈናቀሉን ተያያዘው።
      እነመለስ ስብሀትም በተመሳሳይ ሁኔታ አማሮችንና ያማሮቹን አስተሳሰብ ይጋራሉ ያሏቸውን አርባ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህራንና ፕሮፌሰሮችን በማባረር የሂትለርን ስራ ደገሙት።ጀመሩት።እስከመጨረሻው ተያይዘውታል።
      ሂትለር ወደ ስልጣን እንደመጣ ሰፊ የፕሮፓጋንዳ ሽፋን የተሰጠው ስራ አይሁዳውያን በጀርመን ህዝብ ዘንድ እንዲጠሉ ለማድረግ ሀያ አራት ሰአት የፕሮፓጋንዳ ስራ መስራት ነበር።እኛ ቤትም ወያኔያዊው ፕሮፓጋንዳ ባጼ ሚኒሊክ ጀምሮ መላውን አማራ ነፍጠኛ እያለ ስድብና የውሸት ታሪክ ያዘንብበትና ወደ ታዋቂ ግለሰቦች ተራ በተራ በመሄድ የሚያታክት ፕሮፓጋንዳ ይሰራ እንደነበር አይዘነጋም። እነ ጥላሁን ገሰሰ፤ እነ ፐሮፌሰር አስራት ወልደየስ፤ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪአም፤ ሚትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ፤ ሁሉንም መዘርዘር አይቻልም፤ በሀገሪቱ ውድ ዜጎች ላይ ይነዛ የነበረው ስም የማጥፋትና የማጥላላት ፕሮፓጋንዳ በነጻው ፕሬስ ጀግኖች ከመመታቱ በፊት ምን ያህል አማራው ላይ ያነጣጠረ እንደነበረ ኢትዮጵያውያን የቅርብ ጊዜ ታሪካችን ስለሆነ መደጋገም አያሻም።
      ሂትለር በአይሁዳውያን ላይ ያንን ሁሉ እልቂት ሲያደርስ ጀርመናውያን ባለመቃወማቸው ለድርጊቱ ተባባሪ መሆናቸውን አመልክተው ነበር። እርግጥ የኛ ህዝብ ከወያኔ ጋር አልተባበረም።
      የሂትለር ድርጊቱ የራሱ ብቻ የሆነ ግለሰባዊ እቅድ ከመሆን አልፎ የፓርቲው ማለትም የናዚ ሶሻሊስት ፓርቲ መርህ እንዲሆን በመደረጉ፤ በወቅቱ ጀርመናውያን ባብዛኛው የፓርቲው አባልና ደጋፊ እንዲሆኑ በመገደዳቸው፤ እናም ባንድ አንባገን ግለሰብ የሚመሩ በመሆናቸው የፓርቲያቸውን አቋምና ፍልስፍና ሊቃረኑ አልቻሉም። እንደ ሕውሀት ግንባር አባላት ደደብነት ማለት ነው።
      ይህ የህውሀት ሶሻሊስት ግንባር አባላትን ከመምሰሉ ባሻገር አሽከሮቻቸውን ደርበንላቸው ኢህአደግ እንበላቸውና፤ ባለፉት ሀያ ሁለት አመታት ህውሀት ያን ሁሉ ግፍ ባማሮች ላይ ሲፈጽም የተቃውሞ ድምጽ ያሰሙበት ጊዜ ነበረ? ከጉራፈርዳ ከሀያ ሺህ በላይ አማሮች ንብረታቸውን ተቀምተው ሲባረሩ ድርጊቱ እንዲቆም ወይም ልክ አይደለም ሲል የተደመጠ የኢህአደግ አባል ድርጅት አለ? የናዚ ፓርቲ አባላትም በዚህ መልኩ ነበር በአይሁዳውያን ላይ የደረሰውን የደገፉት። ኢህአደጎችስ ለምን? የህውሀት ፍልስፍና አማራውን በማጥፋት ላይ የተመሰረተ ስለሆነ መቃወም ተግባራቸው አይደለም? ወይንስ ለራሳቸውም የህሊና ባሮች ሰለሆኑ በጌቶቻቸው ቡራኬና ይሁንታ የሚጣልላቸውን ትርፍራፊ እየበሉ መኖር ብቻ ነው።
      በሂትለር እምነት አርያን የሚባለው የጀርመን ህዝብ ዝርያ በመላው ጀርመን ከሚገኙ ዘሮች ሁሉ የበላይነት አለው። ስለዚህ ሁሉም ዘሮች በስሩ ማደር አለባቸው። ሌሎቹ ዘሮች ስላቮችና ፖልስ የሚባሉት ዝቅ ያለ የሰውነት ደረጃ ስላላቸው ለአርያን ዘሮች ነው ማገልገል ያለባቸው። አይሁዶች ጭራሹኑ ጥገኛ ተውሳካት ስለሆኑ መጥፋት ነው ያለባቸው። ሂትለር ያኔ በሚፈልጋት የጀርመን አይነት እንደተመኘው ሁሉ በመለስ ስብሀት ሰራሿ ኢትዮጵያም እነሆ ሀያ ሁለት አመታት ወያኔ መላው ኢትዮጵያ በትግሬ ስር ነው ማደር ያለበት ብሎ እንዳመነና እንደተነሳ፤ ሁሉ በመንግስቱ ስራ ፈላጭ ቆራጭ ቀጣሪ አባራሪ፤ ትግሬ። በግሉ ክፍለ ኢኮኖሚ ፈላጭ ቆራጭ ተቆጣጣሪ ሰሪ ፈጣሪ፤ ትግሬ። በውትድርናው ዘርፍ ፈላጭ ቆራች ዘማች አዝማች መሪ ትግሬ፤ ሆንና አፈፍነው። እንደ ሂትለር ምኞት አርያኖች አልተሳካላቸውም። የመለስ ስብሀት ምኞት ግን በሚገባ ተሳክቷል።ለጊዜውም ቢሆን የኢትዮጵያ ህዝብ በነሱ ስር ወድቋል።
      ዛሬ በህይወት የሚገኙ የናዚ ወንጀለኞች ለፍርድ በሚቀርቡበት የኑረንበርግ ችሎት ላይ ኤሪክ ቮን ዴም የተባሉ ባለ ሶስት ኮከብ ጀነራል፡ በአይሁዳውያን ላይ ስላደረሱት እልቂት የምስክርነት ቃላቸውን እንዲሰጡ ሲጠየቁ “….ያ ፍጅት ሊቀር የማይችል የናዚ ፓርቲ ፍልስፍና መርህ ነበር ወይ?” ሲባሉ እንዳሉት “…ለአመታት…ለአስርት አመታት ስላቮች ከሰው በታች የሆኑ ፍጡራን መሆናቸውን ሰው እንዲያምን ተደርጎ ከተሰበከ፤ አይሁዶችም ጭራሽ ሰውም አይደሉም ብሎ ሰው እንዲያምን ከተሰበከ ያ እልቂት ሊቀር የማይችል ክስተት ነበር” ብለው እራሳቸው የጭፍጨፋው ተሳታፊ መሰከሩ። ሕውሀት ስለ አማራው ክፉ ነገር የሰበከውን ያህል የሰማው ኢትዮጵያዊ አለመኖሩ መበጀቱ፤ የከፋ ነገር ማድረግ እንዳይችል አድርጎታል።
      እርግጥ ህውሀቶች የሂትለርን ድርጊት ካሁን ቀደም ባርሲ አርባጉጉ፤ በበደኖ፤ ባሰቦት ደብረወገግ ገዳም ከኦነጎች ጋር በመተባበር በሚገባ ጀምረውት ሞክረውት ዳር አልደረሰላቸውም። አማራውን በመጥላት የኢትዮጵያ ህዝብ ሊያግዛቸው አልቻለም። በኢትዮጵያ የሚገኙት ሰማንያ አንዱም ብሄረሰቦች ተፋቅረው ተከባብረው የሚኖሩና የኖሩ በመሆናቸው። የነመለስ ስብሀት ፕሮጀክት አልሰራም። ወደፊትም አይሰራም። የራሳቸው መጥፊያ ግን ይሆናል። የኢትዮጵያ ህዝብ እንደ ሩዋንዳ ህዝብ ጎረቤት በጎረቤቱ ላይ አይነሳም። ተራ የጀርመን ዜጎች ሳይቀሩ አይሁዶችን በማሳደድ በመግደል ሂትለርን አግዘውታል። እኛ ፍቅር በፍቅር በመሆናችን ይህ በሽታ የለብንም። ይህ በሽታ ያለው በወያኔዎችና አንዳንድ በዘር ተደራጅተው ከሚገኙ ደደቦች ደም ውስጥ ነው። ነቀርሳ ነው።
      ለምሆኑ የወያኔ ጥቂት መሪዎች የአማራውን ሕዝብ ሊጠሉ የቻሉበት ምክንያት ምንድነው? ወደ ዘመነ መሳፍንት መለስ ብለን እስቲ አንድ ተያይዞ ሊመጣ የሚችል ነገር እንመልከት። በነበረው የርስበርስ ጦርነት ባጼ ቶዎድሮስ የተጀመረው ያሸናፊነት እና የበላይነት በአጼ ሚኒሊክ ሁሉንም ድል ማድረግ ሲጠናቀቅ፤ የየአካባቢው ንጉሶችና መሳፍንት የአሮሞውም የትግሬውም የከንባታውም ሁሉም ተሸንፈው ግዛቶቻቸው በአንድ ንጉሰነገስት ስር ሲወድቁ፤ አጼ ሚኒሊክ አገር የማቅናቱን ግዛት የማስፋቱን እርምጃ ቀጥለውበት ነበር። እናም በደቡብም በምስራቅም በየትም አቅጣጫ የሚልኩት ሰራዊት አብዛኛው አማርኛ ተናጋሪ ስለነበረ ተሸናፊዎቹ ቢገብሩም አማራውን አንደ ወራሪ መቁጠራቸውና መጥላታቸው አልቀረም ነበር።ያንኑ ጥላቻቸውን በህዝቡ ውስጥ ማሰራጨታቸውም አልቀረም።
      ወደ ትግራይ በሽተኞች የመጣን እንደሆነ ዛሬ ያሉት አንጋፋ የህውሀት መሪዎች የሞተውን ጨምሮ አያቶቻቸውና አባቶቻቸው ወገናቸውንና ሀገራቸውን ከድተው ለጣሊያን ያደሩ አሽከሮችና ባንዳዎች ነበሩ። አባቶቻቸው እንዳወረሷቸው የጥላቻ ወሬና የፈጠራ ታሪክ፤ የአድዋው ድል የሚኒሊክ ድል፤ በነሱ አስተሳሰብ ሚኒሊክ አማራ ስለሆኑ ያማራ ድል ነው። በሁለተኛው የአለም ጦርነትም ባምስት አመቱ የወረራ ዘመን የነመለስ ስብሀት ወላጆችና ቤተሰቦች የጣሊያን ተላላኪዎችና አሽከሮች ሆነው፤ በሰላም እነዚህን ዛሬ የሚያቃጥሉንን ከሀዲዎች ለማሳደግ ጎንበስ ቀና ሲሉ፤ አርበኞች (በነሱ እምነት አማሮች) ጌቶቻቸውንም እነሱንም በዱር በገደል አናስወጣ አናስገባ ብለው ጣሊያንን አባረው የኢትዮጵያን ነጻነት ስላስመለሱ፤ ባንዳነቱ የቀረባቸው ወገኖች በአማራው ላይ የመረረ ጥላቻ ይዘው፤ በዚያው ጥላቻ ልጆቻቸውን ኮትኩተው አሳደጉ። ጣሊያንን ያባረረው ግን መላው የኢትዮጵያ ጀግና ነው። ኦሮሞ፤ አማራ፤ ትግሬ ወላይታ ወዘተ….ቢሆንም የእነመለስ ስብሀት ወላጆች ጌቶቻቸውን ያባረሩባቸው አማሮች እንደሆኑ አድርገው፤ ልጆቻቸው በአማራ ጥላቻ ተኮትኩተው እንዲያድጉ አደጉ። አሳሳቢው ነገር እነዚህ ሰዎች ካባቶቻው የወረሱትን ጥላቻ እነሱም ላልታደሉት ልጆቻቸው ማውረሳቸው ነው። ያም አልበቃ ብሎ የትግራይን ህዝብ ለመመረዝ ባለመታከት ስለ አማራ ህዝብ ክፉ ሲናገሩ መደመጣቸው ነው። መልካሙ ነገር ህዝቡ ከነሱ የቀደመ በመሆኑ ሊሰማቸው አይችልም። ምክንያቱም አማራ የሚባለው ሁሉ እንደ ትግሬ ደሀ ነው። እንደ ኦሮሞ ድህ ነው። እንደሶማሌ ድሀ ነው። እንደ አፋር፡ እንደ ከምባታ፡ እንደሁሉም የኢትዮጵያ ህዝብ ድሀ ነው። ምን አይነት አማራ ነው ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ሁሉ ጠላት ነው ብለው የሚያስተምሩት? አማርኛው ቋንቋ የመንግስት የስራ ቋንቋ ስለሆነ ይሆን? ለልጆቻቸው አዝናለሁ። ገንዘብና ጥላቻን ለሚያወርሷቸው። አእምሮአቸው ተጋርዶ ለሚያመልኳቸው አዝናለሁ። ጥላቻን ለሚወርሷቸው፤ እናም በሰብአዊ ፍጡር ጥላቻ ታውረው ሕይወታቸውን ለሚያጨልሙ። በኢትዮጵያ ውስጥ የሚጠላ ዘር የለም። የሚጠላ እና መጥፋት የሚገባው ገዢ ቡድን እንጂ።