Wednesday, January 23, 2013

ሰበር ዜና-አዲስ አበባ አጉስታ ጽዮን ማርያም ቤተክርስትያን ተቃጠለች


ትላንትና ከቀኑ 7 ሰዓት በተነሳ እሳት ቤተክርስትያኒቱ ውስጥ ከሚገኙ ታቦታት  ፤ ከመጽፍትና ከመስቀል ውጪ ሙሉ በሙሉ አውድሟታል :: ቤተክርስቲያኒቱ በጠራራ ጸሀይ ፤ በቆርቆሮ የተሰራው ግድግዳ እና ድንገት በተነሳ እሳት በአንድነት በመሆን የደረሰውነ ጉዳት  ከፍ አድርገውታል
  •      ከትላንት ማታ ጀምሮ የተጀመረው ስራ አሁንም ቀጥሏል ፤ ቤተክርስቲያኒቱ ከተቃጠለች 24 ሰዓት ሳይሞላት ማገር አቆመው የጎን ቆርቆሮ የማልበስ ስራ ተጠናቋል፡፡
    •     አካባቢው ያለው ሰው ስራውን ለሚሰሩት ሰዎች እንጀራ ወጥ ፤ ለስላሳ ውሃ እና አስፈላጊ ነገሮችን በማቅረብ ከ48 ሰዓት በፊት ስራን ለመጨረስ እየተረባረበ ይገኛል
    •                የእሳቱን መነሻ አሁንም እየተጣራ ይገኛል  ; እሳት አደጋ ተደውሎለት በሰዓቱ ባለመምጣቱ አደጋውን የከፋ አድርጎታል
    cherch
የእመቤታችን የቅዱስ ዮሃንስና የቅዱስ ኡራኤል ታቦቶች ምንም አለመሆናቸው እጅጉን አስገርሟል
በርካታ ሰዎች እሳቱን ለማጥፋት ተረባርበው ነበር
ትላንትና 70 ሺ ብር ከምዕመኑ መሰብሰብ ተችሏል ፤ ዛሬ ጠዋትም ቤተክርስቲያኒን ለመስራት ብር እየተሰበሰበ ይገኛል
ዛሬ ጠዋት በርካታ ወጣቶች ቤተክርስቲያኒቱን ዳግም ለማቆም እየተረባረቡ ይገኛ
የአካባቢው ወጣቶች እሳቱን ለማጥፋት ያደረጉት መረባረብ እጅግ ያስገረመ ነበር ፤ አሁንም ቤቷን ለማቆን ያለ እረፍት እየሰሩ ይገኛል ፤
እስከ ዛሬ ከቀኑ 6 ሰዓት ድረስ ከ200 ሺህ ብር በላይ ተሰብስቧል ፤ በአሁኑ ሰዓት በርካታ ምዕመናኖች ቦታው ላይ በመገኝት ቤተክርስቲያኒቱን እየሰሩ ይገኛሉ፡፡
by አንድ አድርገን

No comments:

Post a Comment