Saturday, January 12, 2013

ሱሪዎች ዛሬ ከመከላከያ ሰራዊት አባላት ጋር ሲዋጉ መዋላቸው ታወቀ


ጥር ፬ (አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ከስፍራው የደረሰን ዜና እንደሚያመለክተው የመከላከያ ሰራዊት አባላት የሱሪዎችን የቤት እንስሶቻቸውን  በመውሰድ የአካባቢውን ህዝብ በግድ ወደ ሰፈራ ጣቢያ ለማንቀሳቀስ ባደረጉት ሙከራ ነው ዲማ በሚባለው አካባቢ የተኩስ ልውውጥ የተደረገው።
በግጭቱ ምን ያክል ሰዎች እንደተገደሉ ዜናውን እስካጠናከርንበት ጊዜ ድረስ ለማወቅ አልተቻለም።
ኢሳት ባለፈው ሳምንት የመከላከያ ሰራዊት አባላት ከ150 በላይ ሱሪዎች መገደላቸውን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።
 
  የባለራእይ ወጣቶች ማህበር ጉባኤ ተደናቀፈ
           ጥር ፬ (አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ወጣቶቹ ዛሬ በአንድነት ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሊያካሂዱት የነበረው አመታዊ ጉባኤ ገዢው ፓርቲ አስርጎ ባስገባቸው ወጣቶች መደናቀፉን ወኪላችን ከስፍራው ዘግቧል
በአዲስ አበባ ያሉ ሆቴሎች ለማህበሩ አዳራሽ ለማከራየት ፈቃደኛ አለመሆናቸውን ተከትሎ ወጣቶቹ ጉባኤያቸውን  በአንድነት ፓርቲ ጽህፈት ቤት ውስጥ ለማካሄድ ተገደው ነበር።
ይሁን እንጅ ዛሬ ጧት ስብሰባው በሚካሄድበት ወቅት የተወሰኑ  ወጣቶች ስብሰባውን  ማደናቀፋቸውንና ይህንኑ ተከትሎ የፌደራል ፖሊስ አባላት ወደ ስፍራው በፍጥነት በመምጣት 6 የአመራ አባላትን ወደ ፖሊስ ጣቢያ በመውሰድ ቀኑን ሙሉ ካሰሩዋቸው በሁዋላ በዋስ እንደለቀቁዋቸው የወጣቶች ምክትል ፕሬዚዳንት ወጣት ሚካኤል  ተናግራል።
           

    በ አዲስ አበባ የወላይታ ተወላጆች እየታፈሱ ነው

     ጥር ፬ (አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
    ኢሳት ዜና:- በተለያዩ ጥቃቅን የንግድ ሥራዎች ተሰማርተው የሚገኙ የወላይታ ተወላጆች”ወደ አካባቢያችሁ ትመለሳላችሁ”ተብለው ታፍሰው መታሰራቸውን ፖሊስ ምንጮች ገልጸዋል
    ከቅርብ ጊዜ ወዲህ  ኑሯቸውን ለማሸነፍ ሲሉ ወደ አዲስ አበባ በመምጣት በሊስትሮነትና በሌሎች ጥቃቅን ንግዶች ተሰማርተው የነበሩ በርካታ የወላይታ ተወላጆች “የጸጥታ ስጋት ናቸው”ተብለው  በፌዴራል ፖሊስ ታፍሰው ታስረዋል።
    እንደ ወኪላችን መረጃ በትናንትናው ዕለት ብቻ 130 የወላይታ ተወላጆች አራት ኪሎ አካባቢ በፖሊስ ታፍሰው ሜክሲኮ በሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ  ታስረዋል።
    መጀመሪያ በተደረገው አፈሳ እጅግ በርካታ በአነስተኛ ንግድ የተሰማሩ ዜጎች  በጅምላ መታፈሳቸውን የገለጹት የፖሊስ ምንጮች፤ ሁሉም ከታሰሩ በሁዋላ መታወቂያቸውን እንዲያሳዩ እየተደረገ የሌሎች ብሔረሰብ ተወላጆች ሲለቀቁ የወላይታ ተወላጆች ብቻ  እየተመረጡ ታስረው እንዲቆዩ  ተደርጓል።
    የወላይታ ተወላጆች በአካባቢያቸው ባለው አስከፊ ኑሮ የተነሳ በብዛት ወደ አዲስ አበባ እንደሚሰደዱ ይታወቃል።
    ተወላጆቹ በአዲስ አበባ ነዋሪዎች ላይ የጸጥታ ስጋት ደቅነዋል በሚል ሰበብ ታፍሰው ወደ መጡበት እንደሚለሱ ለማድረግ እንቅስቃሴ ቢጀመርም ዋነው ምክንያት ግን ለከተማዋ ገጽታ መበላሸት አስተዋጽኦ አድርገዋል በሚል ነው። አንዳንዶቹ  በድህነት ምክንያት  በቤተክርስቲአኖችና በጎዳናዎች ላይ እንደሚያድሩ ይታወቃል።
    ኢህአዴግ የሚከተለው ዘርና ቋንቋን ማዕከል ያደረገ ፌዴራሊዝም፤ ኢትዮጵያውያን ዜጎች በአገራቸው በነፃነት ተንቀሳቅሰው እንዳይሠሩ እንቅፋት መፍጠሩን፤ ፖለቲከኞች በተደጋጋሚ አብነቶችን በማሳየት ሲተቹ ይደመጣሉ።
    ጠቅላይ ሚኒስትር  ሀይለማርያም ደሳለኝ የወላይታ ተወላጅ መሆናቸው ይታወቃል።
        

      No comments:

      Post a Comment