Tuesday, January 22, 2013

“በአስመራ ሁሉም ነገር የረጋጋ ነው” ሲሉ የፕሬዚዳንቱ ጽህፈት ቤት ሃላፊ ተናገሩ


ጥር ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:- አቶ የማነ ገብረቀመስቀል ለኤኤፍ ፒ  አስመራ እንደትናንቱ ሁሉ ዛሬም የተረጋጋች ናት በማለት ተናግረዋል። በደቡብ አፍሪካ የኤርትራ አምባሳደር የሆኑት ሳሊህ ኦማር በበኩላቸው ምንም የመፈንቅለ መንግስት ሙከራም ሆነ ምንም አይነት የአመጽ እንቅስቃሴ  አልታየም ብለዋል።
ቢቢሲ ባሰራጨው ዘገባ ደግሞ የማስታወቂ ሚኒሰቴር መስሪያ ቤትን የተቆጣጠሩት አማጺዎች፣ መስሪያ ቤቱን ለቀው ወጥተዋል። ተቋርጦ የነበረው የአገሪቱ ቴሌቪዥን ስርጭቱን መጀመሩንም ገልጿል።
ኢሳት ከትናንት ጀምሮ አስመራ በመደወል ጉዳዩን ለማጣራት ተደጋጋሚ ሙከራ ቢያደርግም አልተሳካለትም፤ ይሁን እንጅ በከተማዋ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ” ምንም አይነት የተለየ እንቅስቃሴ አለማየታቸውን፣ ጉዳያቸውን ያለምንም ችግር ሲያከናውኑ መዋላቸውን” ገልጸዋል። አንድ ስሙ እንዳይገለጥ የፈለገ ኢትዮጵያዊ “ከአገሪቱ ቴሌቪዥን  መጥፋት በስተቀር፣ ስልኮች አለመቋረጣቸውን፣ ታክሲዎች ያለምንም ችግር አግልግሎት ሲሰጡ እንደነበር፣ ሱቆችም ተከፍተው መዋላቸውን፣ እንዲሁም የተኩስ ድምጽ አለመስማቱንም” ገልጿል”
የተለያዩ አለማቀፍ የመገናኛ ብዙሀን በኤርትራ መፈንቅለ መንግስት መኩራ መደረጉን በመግለጽ ዘገባዎችን ማሰራጨታቸው ይታወሳል። 

No comments:

Post a Comment