ጥር ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:- ግድያው የተፈጸመው ሀሙስ ጧት ሲሆን ሶስቱም ግንባራቸው ላይ በጥይት ተመትተዋል። ከማቾቹ መካከል አንደኛዋ የኩርድ የሰራተኞች ፓርቲ መስራች ናቸው።
ሳኪና ካንዚስ የተባለችዋ ሟች ፒኬኬ በአውሮፓ ውስጥ ለሚያደርገው እንቅስቃሴ ቁልፍ ሰው እንደነበረች ዘገባዎች ያመለክታሉ።
በሶስቱ ሴት ታጋዮች ላይ የተፈጸመው ግድያ የቱርክ መንግስት በእስር ላይ ከሚገኘው የፒኬኬ መሪ አብደላ ኦቻላን ጋር ንግግር በጀመረ ማግስት ነው።
ብዙ ኩርዶች ግድያውን አስፈጸመው የቱርክ መንግስት ነው በማለት ተቃውሞ እያሰሙ ነው፡፡ የቱርክ መንግስት በበኩሉ የኩርድ አማጽያን እርስ በርሳቸው መገዳደላቸውን ይገልጻል።
ፒኬኬ በተለያዩ አገሮች የሚገኙ ኩርዶችን በማሰባሰብ ነጻ የኩርዶች አገር ለመመስረት የሚንቀሳቀስ ድርጅት ነው። አብዛኞቹ የምእራብ አገሮች ድርጅቱን በአሸባሪነት ቢፈርጁትም በአባላቱ ላይ እርምጃ ሲወስዱ አይታዩም።
የአላማጣ ወረዳ ነዋሪዎች የተቃውሞ ድምጻቸውን አሰሙ
ጥር ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-በትግራይ ክልል በአለማጣ ወረዳ የሚኖሩ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ተቃውሞአቸውን እያሰሙ ያሉት ፣ የወረዳው የቤት አፍራሽ ግብረሀይል አባላት በህገወጥ መንገድ ተስርተዋል ያሉዋቸውን ቤቶች ለማፍረስ በሄዱበት ወቅት ነው።
ተማሪዎች፣ ህጻናት ፣ አዋቂዎች ከጧቱ 3 ሰአት ጀምሮ እስከ አመሻሹ ድረስ መንገዶችን በመዝጋት ተቃውሞአቸውን የገለጡ ሲሆን፣ ወደ ሰሜንና ወደ ደቡብ የሚተላለፉ መኪኖች መተላለፊያዎች ተዘግተውባቸው ውለዋል።
ቤቶችን ለማፍረስ የተንቀሳቀሱ የወረዳው ባለስልጣናት የህዝቡን ቁጣ በመፍራት ስራቸውን ሳያከናውኑ ወደ መጡበት ተመልሰ ዋል። ተማሪዎች “ቤታችን ፈርሶብን ትምህርት አንማርም” የሚል መፈክሮችን ሲያሰሙ ፣ ወላጆች ደግሞ በለቅሶ ተቃውሞአቸውን ገልጸዋል:: አንድ የአንደኛ ደረጃ ተማሪ የወላጆቹ ቤት ፈርሶ መማር ስለማይችል፣ የመንግስትን ፖሊሲ ለመቃወም መውጣቱን ተናግሯል።
ከቀኑ 11 ተኩል በሁዋላ ከመቀሌ የመጡት የፌደራል ፖሊስ አባላት በህዝቡ ላይ አስለቃሽ ጪስ በመተኮስ ህዝቡን እንዲበተን አድርገዋል። ብዙ ሰዎች ተዘርረው መውደቃቸውን አይን እማኞች ገልጸዋል
የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚሉት ከ25 አመታት በፊት ጀምሮ የተሰሩ ቤቶች ህገወጥ ናቸው በሚል እንዲፈርሱ መንግስት አዟል።
በጉዳዩ ዙሪያ የመንግስት ባለስልጣናትን ለማነጋገር አደረግነው ጥረት አልተሳካም። በአዲስ አበባ በተመሳሳይ መንገድ ቤታቸው የፈረሰባቸው ግለሰቦች በከፍተኛ ችግር ውስጥ እንደሚገኙ ይታወቃል።
አላማጣ ቀድሞ በአማራ ክልል በወሎ አውራጃ ስር ይገኝ ነበር። ህወሀት ኢህአዴግ አዲስ አበባን ሲቆጣጠር አካባቢው ወደ ትግራይ ክልል እንዲዞር ማድረጉ ይታወሳል።
No comments:
Post a Comment