ጥር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የአለም ባንክ በኢትዮጵያ የሚታየው የሙስና ደረጃ እያደገ መምጣቱን ይፋ አደረገ:: በተለይ የቴሌኮም ዘርፉ ለከፍተኛ ሙስና የተጋለጠ መሆኑን አስታወቀ::
ባለፈው አርብ በአለም ባንክ ይፋ የተደረገ ሪፓርት እንዳመለከተው በተለይ በግዥና በአቅርቦት ሂደቶች የሚታዩት ክፍተቶች ለሙስና አደጋ በመጋለጥ ከፍተኛውን ድርሻ መያዛቸውን ሪፓርቱ አመልክቶል::
የሀገሪቱን የሙስና መጠን ላለፉት ስድስት ወራት ሲያጠና የቆየው የአለም ባንክ በተለይ አዳዲስ የኢንቨስትመንት መስኮች ብሎ በመደባቸው
ንዑሳን ክፍሎች ውስጥ የተካተቱት ቴሌኮም፣ የኤች አይ ቪ መከላከልና ህክምና የመድሀኒት ዘርፉን ጨምሮ በሙስና ቀለበት ውስጥ የወደቁ ናቸው ብሎል::
በመሰረታዊ አገልግሎት ሰጪ ተቆማት ብሎ ባንኩ በመደባቸው ትምህርት፣ ጤና፣ ፍትህና የመሳሰሉት ተቆማት ቀላል የማይባል ሙስና የሚታይባቸው መሆኑን አጋልጦል::
ባንኩ ያፋ ባደረገው በዚ ሪፓርት ከፍተኛ ሙስና ከሚታይበት ከቴሌኮም ኢንዱስትሪ ቀጥሎ መሬትና ኮንስትራክሽን ዘርፉ በሙስና መዘፈቁን ይፋ አድርጎል::
በኢትዮጵያ በደን የተሸፈነ መሬት ከ 40 በመቶ ወደ 2፡4 በመቶ ማሽቆልቆሉ ተገለጠ
ጥር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:- በቢዝነስ ዜናዎች ላይ እያተኮረ አዲስ አበባ የሚታተመው አዲስ ፎርቹን ጋዜጣ እንደዘገበው ባለፉት 60 አመታት ውስጥ ሀገሪቱ 37፡6
ከመቶ ደኖን አታለች::
በሀገሪቱ ያለው እንጨትን በማገዶነት የመጠቀም ፍጆታ በአመት 50 ሚሊዮን ቶን እንደሚገመት ያመለከተው ይህ ዘገባ የደን መጨፍጨፍ ዋነኛ ምክንያት አድርጎ ጠቅሶታል::
ይህም ሀገሪቱ ከምትጠቀመው አጠቃላይ ሀይል 80 ከመቶውን ከእንጨትና ከእንጨት ውጤቶች መሆኑ በዘገባው ተመልክቶል::
በኢትዮጵያ በደን የተሸፈኑ መሬቶች ተጨፍጭፈው በርካሽ ዋጋ ለውጭ ባለሀብቶች እየተሸጡ መሆናቸውን በተደጋጋሚ መዘገባችን ይታወሳል:፡
በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ ውርስና ቅርስ ማህበር ማህበሩን ለሚቀጥሉት ሁለት አመታት የሚመሩ 7 የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት መምረጡን አስታወቀ
ጥር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-በዚህ መሰረት ማህበሩ ከተቆቆመበት ጀምሮ ማህበሩን በፕሬዚዳንትነት በመሩት በዶ/ር ሼክስፔር ፈይሳ ምትክ አቶ አበበ ሀይሉ ም/ፕሬዚዳንት ደግሞ ዶ/ር ሰለሞን ረታ አድርጎ ሠይሞል::
በተዋረድ በዋና ጸሀፊነት፣ በህዝብ ግንኙነት፣ በፋይናንስ፣ በቢዝነስ ማኔጅመንትና በመድረክ አስተባባሪነት በቀድሞ የስራ አስፈጻሚዎች ምትክ አዲስ ተመርጦል::
የቀድሞ የማህበሩ የስራ አስፈጻሚ አባላት ለአዲሶቹ ተመራጮች የስራና የንብረት ርክክብ የፈጸሙ መሆኑን የገለጠው የማህበሩ መግለጫ የኢትዮጵያን ማህበራት፣ ተባባሪ አባላት፣ የቦርድ አባላት፣ የኢትዮጵያ ኮሙኒቲዎች ለአዲሱ አመራር የተለመደ የስራ ትብብር እንዲያደርጉላቸው ጠይቆል::
ማህበሩ ለዝግጅት ክፍላችን በላከው በዚህ መግለጫ የአድዋን ድል አስመልክቶ በች ሁለት ለሚኖረው ዝግጅት እየሰራ መሆኑን የገለጸ ሲሆን በዋሽንግተን ዲሲም ሶስተኛው ፊስቲቫል በሳምር እንደሚካሄድ አስታውቆል::
በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ ውርስና ቅርስ ማህበር የኢትዮጵያን ቅርሶችና ታሪኮን መጠበቅና ማስተዋወቅ ከአላማዎቹ በዋናነት ይዞ ለተግባራዊነቱ የሚንቀሳቀስ ድርግት መሆኑ ይታወቃል::
የኢትዮጵያ ፍ/ቤቶት ከአሸባሪ ቡድን ጋር በመተባበር የሽብር ጥቃት ለመሰንዘር አቅደው ነበር ባላቸው 10 ሰዎች ላይ ከ3 አመት እስከ 20 ዓመት የሚደርስየእስር ቅጣት ወሰነ
ጥር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዛሬ ባስቻለው ችሎት የእስር ቅጣት ከወሰነባቸው ውስጥኬኒያዊው ሀሰን ጃርሶ እንደሚገኙበት የአሶሼትድ ፕሬስ ዘገባ አመልክቷል::
ከፍተኛው ፍ/ቤት ዳኛ ባህሩ ዳርቻ በኬኒያው ጃርሶ ላይ የ17 ዓመት የ እስርፍርድ ወስነውበታል::
በዚህ ከአሸባሪነት ተግባር ጋር በተያያዘ ክስ በቅድሚያ የተካተቱት 11 ሰዎችእንደነበሩ ሲታወቅ አንደኛው በነጻ ተሰናብቷል ስድስቱ ደግሞ በሌሉበትተወስኖባቸዋል::
የኢትዮጵያ የስለላ ድርጅት በዚህ ወር መጀመሪያ አልሸባብ ከተባለውየሽብርተኛ ድርጅት ጋር ግንኙነት አላቸው ያላቸውን 15 ሰዎች መያዙንማስታወቁን ይህ የአሶሼትድ ፕሬስ ዘገባ አመልክቷል::
በምስራቅ አፍሪካ ሃገሮች የታጣቂዎች እንቅስቃሴ እየጎላ በመምጣበት ጊዜ ነውይህ የፍ/ቤት ውሳኔ የተላለፈው ያለው ዘገባ ኢትዮጵያ ሰራዊቱን በ2011 ወደሱማሊያ ዳግም መዝመቶንም አስታውሷል::
No comments:
Post a Comment