ጥር ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የፌደራል መስሪያ ቤቱ ዋና ሃላፊ ሚሸል ሁሬታ አንዳስታወቁት በአውሮፕላኑ ላይ በደረሰው የቴክኒክ ችግር ምክንያት የአውሮፕላኑን ዲዛይና ኣመራረቱ ምርመራ ይደረግበታል።
አውሮፕላኑ ባለፈው ሳምንት ሰኞ የጃፓን ኣየር መንገድ ቦስተን ላይ ከቶኪዮ ተመልሶ በሚያርፍበት ሰአት እሳት ፈጥሮ የነበረ ሲሆን ባለፈው አርብ የጃፓን ኦል ኒፖን አየር መንገድ ሪፖርት አንዳደረገው በሚበርበት ሰኦት በፓይለቱ በኩል ያለው መስኮት በመሰንጠቁ የመመለሻ በረራውን ለመሰረዝ ተገዷል።
ይኸው አየር መንገድ ድሪም ላይነር 787 አውሮፕላን በሞተሩ ውስጥ ዘይት በማፍሰሱ በረራውን ለማቋረጥ ተገዶ እንደነበርና የፍሬን ችግርም በማጋጠሙም ከያማጉቺ ወደ ቶኪዮ ያደርግ የነበረውን በረራ መሰረዙን ገልፆአል። እንዲሁም አውሮፕላኑ 151 ሊትር የሚሆን ነዳጅ በማፍሰሱ ምክንያት ማክሰኞ ከቦስተን ወደ ቶኪዮ ያደርግ የነበረውን በረራ ኣቋርጧል።
ባለፈው አመት በዩናይት ኤር ላይንስ በተፈጠረ የኤሌትሪክ ችግር ምክኒያት አውሮፕላኑ በድንገት አንዲያርፍ የተደረገ ሲሆን የካታር ኣየር መንገድም በዲሴምበር ወር ኣንዱ አውሮፕላኑ በደረሰበት የቴክኒክና የኤሌክትሪክ ችግር ምክኒያት ከበረራ አንዲቆም አድርጎታል የቦይንግ ካምፓኒ በሰጠው መግለጫ የአውሮፕላኑ ዲዛይን አስትማማኝና ለበረራም ከአደጋ ነፃ የሆነ ነው ብሎታል
ድሪም ላይነር 787 አውሮፕላን የተሰራው ካርቦን ከተባለውንጥረ ነገር ሲሆን በቴክኖሎጂም አጅግ ዘመናዊ የተባለለት ነው
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከኣፍሪካ የመጀመሪያ በመሆን 10 ድሪም ላይነር 787 አውሮፕላኖች ከ ቦይንግ የገዛ ሲሆን ባለፈው ነሐሤ የመጀመሪያውን አውሮፕላን ተረክቦ ወደ ሃገር ቤት በከፍተኛ የአቀባበል ስነስርአት አስገብቷል
በገበያ ላይ ውሎ ውጤቱ ያልተመሰከረለትን አዲስ አውሮፕላን መግዛት ዋጋ ሊያስከፍል እንደሚችል በሞያው ላይ የተሰማሩ የኤሮኖቲክ ኢንጅነሮች ያስጠነቅቃሉ።
No comments:
Post a Comment