Monday, January 14, 2013

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የውሃ ያለህ ይላሉ


ጥር ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-በአዲስ አበባ በተለያዩ ቦታዎች ከፍተኛ የውሀ እጥረት ማጋጠሙን ዘጋቢያችን ገልጿል።
በስድስት ኪሎ፣  መነን፣ ፈረንሳይ፣ ጃን ሜዳ፣ ሽሮ ሜዳ፣ ሰሜን ማዘጋጃ እና በተለያዩ የሰሜን አዲስ አበባ  የሚገኙ ሰፈሮች ውሀ ለማግኘት ውሀ ያለባቸውን አካባቢዎች ማሰስ ግድ ብሏቸዋል።
በአንዳንድ አካባቢዎች ውሀ ለሳምንታት የማይመጣ ሲሆን፣ በሌሎች አካባቢዎች ደግሞ በሳምንት አንድ ጊዜ ጥሩ ከተባለም በሳምንት ሁለት ጊዜ ያገኛሉ። በተለይ ፈርንሳይና ሽሮ ሜዳ በከፍተኛ ሁኔታ የውሀ እጥረት ያጋጠማቸው አካባቢዎች መሆናቸው ታውቋል።
11 በመቶ እድገት እንደተገኘ በሚነገርባት የኢትዮጵያ ዋና ከተማ ውሀና መብራት ያለማቋረጥ ማግኘት ህልም እየሆነ ነው።
የውሀ መጥፋቱ በሰሜን አዲስ አበባ ብቻ ሳይሆን በደቡብ አዲስ አበባም የተለመደ ክስተት ሆኗል።
ውሀ ሲባል መብራት መብራት ሲባል ውሀ ይጠፋል፣ መስተዳድሩ ከተማዋን ለማስተዳዳር የተሳነው ይመስላል ይላሉ አንድ የሽሮ ሜዳ ነዋሪ። በእርሳቸው አካባቢ ውሀ ከተቋረጠ ድፍን አንድ ሳምንት ሞልቷል።

No comments:

Post a Comment