Thursday, January 24, 2013

“የትግራይ ክልል ተወላጅ ካልሆናችሁ በዚህ ገዳም መኖር አትችሉም” ተብለናል፤ የዋልድባ አብረንታንት ገዳም ቤተ-ሚናስ ማኅበረ መነኮሳት


የዋልድባ አብረንታንት ገዳም ቤተ-ሚናስ ማኅበረ መነኮሳት አቤቱታቸውን ለክልሉ መንግሥት አቀረቡ
· “የትግራይ ክልል ተወላጅ ካልሆናችሁ በዚህ ገዳም መኖር አትችሉም” ተብለናል፤
· “ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ዋልድባ የሚለውን ስም መጥራት ሁሉ የተለየ ይዘት እየተሰጠው” ነው፤
መነኮሳት ይታሰራሉ፤ ይደበደባሉ፤
ከክልሉ ፕሬዚዳንት ጋር ተነጋግረዋል ተብሏል።
(ደጀ ሰላም፤ ጥር 12/2005 ዓ.ም፤ ጃኑዋሪ 20/2013/ PDF)፦ የዋልድባ የዋልድባ አብረንታንት ገዳም ቤተ-ሚናስ ማኅበረ መነኮሳት አቤቱታቸውን ለአማራ ብሐየራዊ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት እና ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አቀረቡ። በመነኮሳት ላይ የሚደርሰውን የሰብዓዊ መብት ረገጣ የዘረዘረው ደብዳቤው የክልሉ መንግሥት በሰላማውያን መነኮሳት ላይ የሚደርሰውን እንግልት እንዲያስቆም ጠይቀዋል። የታሰሩ፣ የተንገላቱ፣ ሰብዓዊ መብት ጥሰት የደረሰባቸውን መነኮሳትም ዝርዝር አቅርበዋል። ሙሉ የደብዳቤው ሐሳብ ቀጥሎ ሰፍሯል።
የክልሉ መንግሥት የመናንያኑን አቤቱታ ይቀበል ይሆን? የምናየው ይሆናል።
ቸር ወሬ ያሰማን አሜን  read full…  http://www.dejeselam.org/

No comments:

Post a Comment