Friday, January 11, 2013

ቴዲ አፍሮ ለብሔራዊ ቡድኑ ድጋፍ ለመስጠት ወደ ደቡብ አፍሪካ ሊያመራ ነው


ጥር ፫ (ሶስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን(ቴዲ አፍሮ) ለአፍሪካ ዋንጫ ያለፈውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በሙዚቃው ለማነቃቃትና ለመደገፍ በመጪው ቅዳሜ ወደ ደቡብ አፍሪካ እንደሚያመራ ቢቢሲ ዘገበ።
ከአርቲስቱ ጋር ቃለ-ምልልስ ያደረገው ቢቢሲ ፊከስ ኦን አፍሪካ፤ ቴዲ አፍሮን፦ “የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የአፍሪካ ልጅ የሆነ ድንቅ የፖፕ ስታር ሙዚቀኛ” ብሎታል።
ቀደም ሲል ባለለፈው የእስር ጊዜ እና በአዲሱ አልበሙ ዙሪያ  ከቢቢሲ ጋር ቃለ-ምልልስ ያደረገው አርቲስት ቴዲ አፍሮ  ለሁለት ዓመታት ታስሮበት ስለነበረው ሰው በመኪና  ገጭቶ የመግደል ክስ ለቀረበለት ጥያቄ፦ ክሱን ባያምንበትም ፍርድ ቤቱ የሰጠውን ውሳኔ ከመቀበል ውጪ አማራጭ እንዳልነበረው ተናግራል።
ጥቁር ሰው የተሰኘው አልበሙ በዋነኝነት ባነጣጠረበት መልእክት ዙሪያ ያብራራለት ዘንድ የቢቢሲው ዘጋቢ ላቀረበለት ተከታይ ጥያቄም፦” በ አፄ ምኒልክ ብልህ አመራር ጀግኖቹ ኢትዮጵያውያን አባቶች በወራሪው የጣሊያን ጦር ላይ አድዋ ላይ የተቀዳጁት ድል የ አፍሪካና የመላው ጥቁር ህዝቦች ድል መሆኑን በማንጸባረቅ፤ ያን ታላቅ ድል የተረቀዳጁትን ጀግኖች ማወደስ እንደሆነ አስረድቷል።

No comments:

Post a Comment