Thursday, January 10, 2013

የዋጋ ንረቱ መቀነሱን ስታስቲክስ ኤጀንሲ አስታወቀ::


ጥር ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:- ባሳላፍነው ወር የነበረው የዋጋ ግሽበት ወደ 12 ነጥብ 9 በመቶ ዝቅ ማለቱን የማእከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ አስታውቋል። አሀዙ ካለፈው ወር ጋር ሲነጻጸር በ1 ነጥብ ሁለት መቀነሱን ኤጀንሲው አስታውቋል። ይሁን እንጅ በምግብ ነክ ባልሆኑ ምርቶች ላይ የዋጋ ግሽበቱ ጭማሪ አሳይቷል። ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከ8 ወራት በፊት ሰኔ ወር ላይ ባደረጉት ንግግር የዋጋ ንረቱን ወደ አንድ አሀዝ እንደሚያወርዱት ተናግረው ነበር። በመስከረም ወር ላይ ግሽበቱ ቅናሽ ሊያሳይ አልቻለም ነበር። ባሳለፍነው ወር  በእህል ምርቶች ላይ የታየው መጠነኛ ቅናሽ መንግስት ስንዴ በገፍ ከውጭ አገር በማስመጣቱ የተገኘ ነው። በየትኛውም መመዘኛ 13 በመቶ የዋጋ ግሽበት አሁንም ከፍተኛ መሆኑን የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ይናገራሉ።
የኢትዮጵያ ህዝብ በዋጋ ንረቱ የተነሳ ኑሮውን ለመቋቋም እንዳላስቻለው በተደጋጋሚ በኢሳትና በሌሎች መገናኛ ብዙሀን ሲገልጽ መቆየቱ ይታወቃል።

No comments:

Post a Comment