Monday, January 28, 2013

ነገ ዋልያዎቹ ከንስሮቹ ጋር ይፋለማሉ


ጥር ፳ (ሀያ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-እየተካሄደ ባለው 29ኛው የ አፍሪካ ዋንጫ የ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የምድቡን የመጀመሪያ ዙር የመጨረሻ ጨዋታ ነገ ከናይጀሪያ ብሔራዊ ቡድን ጋር ያደርጋል።
ዋልያዎቹ እና ንስሮቹ የሚያደርጉት የነገው ጨዋታ በከፍተኛ ደረጃ በመላው ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ትኩረት ስቧል።
ምድቡን ቡርኪናፋሶ በ4 ነጥብ ስትመራ ዛምቢያና ናይጀሪያ በ2 ነጥብ ይከተላሉ።
ዋልያዎች  በ 1 ነጥብ 4ኛ ደረጃ ላይ  ይገኛሉ።
በመሆኑም በነገው ጨዋታ ዛምቢያ እና ቡርኪናፋሶ አቻ ከተለያዩ፤ወይም ዛምቢያ በቡርኪናፋሶ ከተሸነፈ-ዋልያዎች ወደ ቀጣዩ ዙር ለማለፍ ንስሮቹን በ 1 ጎል ልዩነት ማሸነፍ ይበቃቸዋል።
በነገው ጨዋታ ዛምቢያ አሸንፎ- ናይጀሪያ ዋልያዎችን ካሸነፈ ሁለቱ ቡድኖች ተያይዘው ሊያልፉ ስለሚችሉ ቡርኪናፋሶዎች ለራሳቸው ማለፍ ሲሉ ማሸነፍ ያ ካልተሳካ እኩል መውጣት ግዴታቸው ነው።
ከዚህ አንፃር ቡርኪናፋሶዎች ጠንክረው ስለሚጫዎቱ ቢያንስ እኩል መውጣት አይቸገሩም ያሉ የስፖርት ተንታኞች፤ዋልያዎች በስሜት፣ በ እልክና  በተረጋጋ መንፈስ ጠንክረው በመጫዎት ናይጀሪያዎችን ካሸነፉ ወደ ቀጣዩ ዙር በማለፍ ታሪክ ሊዒሩ እንደሚችሉ መክረዋል።
የ ኢሳት ቤተሰቦች በሙሉ ብሔራዊ ቡድናችን ድል እንዲቀዳጅ ልባዊ ምኞታቸውን ይገልጻሉ

No comments:

Post a Comment