Saturday, January 19, 2013

ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች አንድ ነን አንከፋፈልም አሉ


ጥር ፲ (አስር) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-በአገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን “አንድነን አንከፋፈልም” በማለት የሰደቀና የአንድነት ፕሮግራም አዘጋጅተው ውለዋል።
በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች በአዲስ አበባ በኑር መስጊድ በተካሄደው የሰደቃና  የአንድነት ስነስርአት ላይ ተካፍለዋል። ድርጊቱ ገዢው ፓርቲ ሙስሊሞችን ከሁለት ለመክፈል የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ለመቃም የታለመ መሆኑን በስነስርአቱ ላይ የተካፈሉ ሙስሊሞች ገልጸዋል።
ተመሳሳይ ዝግጅቶች በሻሸመኔ፣ በጅማ እና በመቱ መካሄዱን ለማወቅ ተችሎአል።
ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ካለፈው  አመት ጅምሮ ድምጻችን ይሰማ በማለት ተቃውሞአቸውን እያቀረቡ ይገኛሉ።
በመንግስት በኩል የተያዘው ፖሊስ ” በትግስት እንያቸው” የሚል መሆኑን አዲሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሀኖም ተናግረዋል። ሙስሊሞቹ “ተቃውአቸውን ከጊዜ መርዘምና ከመሰላቸት አንጻር ያቆማሉ ተብሎ በመንግስት የተያዘው እሳቤ ትክክል አለመሆኑን በየሳምንቱ በሚደረጉ ተቃውሞዎች እንዲሁም መንግስት ሙስሊሙን በመክፈል እርስ በርሳቸው እንዲጣሉ በሚያደርገው እንቅስቃሴ መረዳት ይቻላል ” በማለት አንድ የእምነቱ አስተማሪ ለዘጋቢያችን ገልጸዋል።

No comments:

Post a Comment