Thursday, January 10, 2013

በትግራይ ያላማጣ ህዝብ አቤቱታ እና ተቃውሞ መነሾ



ምንሊክ ሳልሳዊ /አላማጣ 
ታህሳስ 15 ቀን 2005 ዓ/ም
ለኢፌድሪ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት
ለኢፌድሪ የፌደሬሽን ም/ቤት
ለኢፌድሪ የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት
አዲስ አበባ


ጉዳዩ፡- የታወጀብን የቤት ማፍረስ ድርጊት እንዲቆምልን አቤቱታ ስለማቅረብ


አመልካቾች በክልል ትግራይ፤ ደቡባዊ ዞን ፤የወረዳ ራያ አላማጣ ፤ ጣቢያ ሰላም ብቓልሲ ፤ የጋርቤ አከባቢ ነዋሪዎች በተወካዮች 5 ሰዎች የምናመለክተው ፍሬ ነገር እንደሚከተለው ነው፡፡ምንሊክ ሳልሳዊ /አላማጣ
እኛ በዚሁ ገበሬ ማህበር ከ1984 ዓ/ም ጀምሮ በህጋዊ መንገድ የተሰጠን የመኖሪያ ቦታ እስከ አሁን ለ21 ዓመታት እየኖርንበት ያለ ነባር ህጋዊ ይዞታችን ሲሆን አሁን ግን የወረዳው መሬት አስተዳደር ዴስክ ይህ ነባር ይዞታችን እስከ 15/4/2005 ዓ/ም ድረስ ካላፈረሳችሁ በአፍራሽ ግብረ ኃይል እንደሚፈርስ ማስጠንቀቂያ ተጽፎብናል፡፡ነገር ግን ይህ ነባር ይዞታችን እስከ አሁን ድረስ ሰባት የገጠር ወረዳ አስተዳደሮች ሲፈራረቁ የመኖሪያ ሰፈር ሆኖ የቆየ እንጂ የሚታረስ መሬት አልነበረም፡፡ በወረዳ ምክር ቤት እና የገበሬ ማህበሩ ም/ቤት ደረጃ ህጋዊ ነባር የመኖሪያ ቦታ መሆኑ አረጋግጠዋል፡፡ ህጋዊነቱ በመረጋገጡም መንገድ፤ ውሃ፤መብራትና የመሳሰሉት መሰረተ ልማቶች የተዘረጋለት ሕጋዊ የመኖሪያ ሰፈር ነው፡፡ ስለዚህ የመጀመሪያዎቹ የወረዳና የገ/ማ ምክር ቤቶች የወሰኑት ውሳኔ የአሁኑ የወረዳ ካቢኔ ማፍረሱ የትግራይ ክልላዊ መንግስት ህግና አዋጅ የሚጻረር ይሆናል፡፡ በዚህም መሰረት ይህ ህጋዊና ነባር የመኖሪያ ይዞታና ለ21 ዓመታት የኖርንበት በእየንዳንዱ ቤት ከ 5 እስከ 10 ቤተሰብ በተለያዩ ዕድሜ የሚገኙ ህጻናትና ሽማግሌ የሚገኝበት ቤት መጠለያ አይገባችሁም በማለት መብታችን ተረግጦ የማፍረስ ዘመቻ ታውጆብናል፡፡
ምንሊክ ሳልሳዊ /አላማጣ 
ስለሆነም እውነትነት በሌለው በወረዳ መሬት ዴስክ ብቻ የወረራ መሬት ነው በማለት ይህ ህጋዊ የመኖሪያ ቦታና ይዞታ እንዲፈርስ መወሰኑ ህገመንግስታዊ መብታችንን እዲጣስና መጠለያ እንድናጣ የታወጀብን ስለሆነ የሰላም ብቓልሲ ከጣቢያ እስከ ቀጠና ያሉት የመሬት ጥበቃ ኮሚቴዎች ህጋዊ መኖሪያ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡ በተጨማሪም የሰላም ብቃልሲ ጣቢያ 15 አባላት ያሉት መሰረታዊ ኮሚቴ እና የ3 የሃገር ሽማግሌዎች ተብለው የተመለመሉ ይህ መኖሪያ ቦታ በአካል አይተው ነባር ይዞታ መሆኑንና የወረራ መሬት አለመሆኑን አረጋግጧል፡፡ ለዚህም በወረዳ ራያ አላማጣ አቃቢ ህግ ፊርማቸው ይገኛል፡፡ምንሊክ ሳልሳዊ /አላማጣ

 እንዲሁም ከላይ የተጠቀሱት ኮሚቴዎች
በ15/3/2005 ዓ ም ስለ ጋርቤ መንደር ተጠይቀው ትክክለኛ ነባር የመኖሪያ ይዞታ መሆኑ አረጋግጠዋል፡፡ በተጨማሪም በቀን 01/04/2005 ዓ ም የጣቢያው ድርጅት አባላት ህጋዊ ነባር የመኖሪያ ቦታ መሆኑን በሚገባ አረጋግጠዋል፡፡
የማፍረስ አዋጅ እንደታወጀብን ለትግራይ ክልል ቅሬታ ሰሚ ቢሮ ስናመለክት ወደ ክልል መሬት ዴስክ እንድንሄድ ተነገሮን ለመሬት ዴስክ አቤቱታችንን ስናቀርብ ካርድ ስለሌላችሁ ህጋዊ አይደላችሁም በማለት የወረዳውን ውሳኔ አጽድቆ ጽፎ ሰጥቶናል፡፡ ይህንኑ ይዘን ወደ ክልሉ የቅረታ ሰሚ ቢሮ ስንሄድ ከሳምንት በኋላ እንዲንመለስ ተነገረን፡፡ እኛም ቤታችን ከሳምንት በፊት ወረዳው አንደሚያፈርስብን ስላሳወቀን ክልሉ ውሳኔ እስኪሰጠን ድረስ ወረዳው እንዳያፈርስብን መመሪያ እንዲሰጥልን ብለን ስንጠይቅ ተቀባይነት አላገኘንም፡፡ ውሳኔያቸውም በጽሁፍ እንዲያሳዉቁን ብንጠይቅም የቅሬታ ሰሚ ቢሮ ሊቀበሉን ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ቤታችን ከመፍረሱ በፊት የሚመለከተው አካል እንዲያውቀውና መፍትሔ እንዲሰጠን ወደ ሚመለከታቸው አካላት አቤቱታችንን ለማቅረብ ግድ ሆኖብናል፡፡ ስለዚህ የሚመለከተው አካል የደረሰብንን በደል ተመልክቶ እኛ ህጋዊ ነዋሪዎችና ከዚህ ሌላ የመኖሪያ አማራጭ የሌለን ድሆች መሆናችንን በመገንዘብ ከዚህ ከታወጀብን የመፈናቀል ድርጊት እንዲታደገን አቤቱታችንን እናቀርባለን፡፡
የአመልካቾች ወኪሎች ፊርማ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
 ምንሊክ ሳልሳዊ /አላማጣ

No comments:

Post a Comment