Saturday, January 26, 2013

ካሚላት ላይ አሲድ የደፉት ወጣቶች ተያዙ:: የታሰረው ደምሰው ነፃ ይወጣልን??


Kamilat Mehdi knew her attacker??
ምንልክሳልሳዊ ብሎግፖስት
ከስድስት ዓመታት በኋላ ሰሞኑንካሚላት ላይ አሲድ የደፉት  “ድርጊቱን እኛ ነን የፈፀምነው” ያሉ ግለሰቦች መገኘታቸውን የተከሳሹ ወላጅ እናት ለአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን መጠቆማቸውን የሚናገሩትምንጮች፤ የተባሉት ሦስት ወጣቶች ጫት ቤት ተቀምጠው የፈፀሙትን ድርጊት እያነሱ ሲያወሩ የሰሙ ሰዎች፣ ለተከሳሽ ቤተሰብ በመንገር ጉዳዩ ክትትል እንዲደረግበት ጥቆማ መሰጠቱን ገልፀዋል፡፡ምንልክሳልሳዊ ብሎግፖስት / የተባሉት ወጣቶችም ተይዘው በሰጡት ቃል፤ ድርጊቱን መፈፀማቸውን አምነው ቃላቸውን መስጠታቸውን እና ትላንት ደምሰው ከማረሚያ ቤት ወጥቶ በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ቃሉን ሰጥቶ መመለሱን ምንጮቻችን ተናግረዋል፡፡ ምንልክሳልሳዊ ብሎግፖስት

በካሚላት መህዲን ላይ አሲድ ደፍቷል በመባል የተከሰሰው እና የዕድሜ ልክ እስራት የተፈረደበት ደምሰው ድርጊቱን እንዳልፈፀመና “የፈፀምነው እኛ ነን” ያሉ ወጣቶች ሰሞኑን ለፖሊስ ቃል መስጠታቸውን ምንጮች ጠቆሙ፡፡ ከዛሬ ስድስት ዓመት በፊት የፍቅር ጓደኛው በሆነችው ካሚላት ላይ የአሲድ ጥቃት ማድረሱ በሰው ምስክርና በማስረጃ ተረጋግጧል ተብሎ የተከሰሰው ደምሰው፤ጉዳዩን እንዳልፈፀመ በመናገር ቢከራከርም በሰውና በሠነድ ማስረጃዎች ተረጋግጧል በማለት ፍ/ቤት በሞት እንዲቀጣ ወስኖ ነበር፡፡ምንልክሳልሳዊ ብሎግፖስት

ተከሳሽ ይግባኝ ጠይቆ ቅጣቱ ወደ 20 ዓመት ዝቅ ብሎለት የነበረ ቢሆንም ዐቃቤ ሕግ እና የሕግ ባለሞያ ሴቶች ማኅበር ይግባኝ በማለት ተከሳሹ በዕድሜ ልክ እስራት እንዲቀጣ መወሰኑ ይታወቃል፡፡ ከስድስት ዓመታት በኋላ ሰሞኑን “ድርጊቱን እኛ ነን የፈፀምነው” ያሉ ግለሰቦች መገኘታቸውን የተከሳሹ ወላጅ እናት ለአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን መጠቆማቸውን የሚናገሩት ምንጮች፤ የተባሉት ሦስት ወጣቶች ጫት ቤት ተቀምጠው የፈፀሙትን ድርጊት እያነሱ ሲያወሩ የሰሙ ሰዎች፣ ለተከሳሽ ቤተሰብ በመንገር ጉዳዩ ክትትል እንዲደረግበት ጥቆማ መሰጠቱን ገልፀዋል፡፡ ምንልክሳልሳዊ ብሎግፖስት የተባሉት ወጣቶችም ተይዘው በሰጡት ቃል፤ ድርጊቱን መፈፀማቸውን አምነው ቃላቸውን መስጠታቸውን እና ትላንት ደምሰው ከማረሚያ ቤት ወጥቶ በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ቃሉን ሰጥቶ መመለሱን ምንጮቻችን ተናግረዋል፡፡ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጉዳዩን እያጣራ በመሆኑ መረጃ ለመስጠት እንደማይችል ገልፆልናል፡፡

No comments:

Post a Comment