Tuesday, December 11, 2012

አስቸኳይ እና የማንቀርበትን ቀጠሮ ! ቢያንስ ለ 10 ሰው ያሳዉቁ


አስቸኳይ እና የማንቀርበትን ቀጠሮ  ! ቢያንስ ለ 10 ሰው ያሳዉቁ 
kaliti


እኛ  በአዲስ አበባ እና አካባቢዋ የምንኖር ወጣቶች  በመጪው እሁድ ታህሳስ 7፣ 2005 ዓ.ም አለአግባብ የታሰሩ የሙስሊም ማህበረሰብ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትን፣ ጋዜጠኞችንና የተቃዋሚ መሪዎችን በቃሊቲ ተገኝተን ለመጠየቅና ለመዘከር አስበናል ።
ማንኛውም የህገመንግስቱን የእምነት እና ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት መከበር እንዳለበት የሚደግፍ ኢትዮጵያዊ በሙሉ ወደ ቃሊቲ በመሄድ ድጋፉን እንዲያደርግ እንጠይቃለን ። እነዚህ ታሳሪዎች ህገመንግስቱ የሰጣቸውን መብት በመጠቀም መላው ህዝባቸውን ሲያገለግሉ የነበሩ የሰላም እና የነጻነት ታጋዮች እንደሆኑ እና ህዝቡም ሰለማዊ አላማቸውን እንደሚደግፍ በእለቱ ማሳየት ይጠበቅበታል ።
ለዚህ የተቀደሰ የጥየቃ ፕሮግራም ያነሳሳን አልጀዚራ ባለፈው ሳምንት ለጠ/ሚ ሀይለማርያም ደሳለኝ በኢትዮጵያ ውስጥ  ስለታሰሩት የህሊና  እስረኞች  ጥያቄ ያቀረበ ሲሆን፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩም በእስር ላይ የሚገኙት አሸባሪዎችና ከአሸባሪዎች ጋር ግንኙነት ያላቸው እንጅ የህሊና እስረኞች አይደሉም በማለት የመለሰቱት የሃሰት መልስ ነው ።
የተከበራችሁ በአዲስ አበባ እና አካባቢዋ የምትኖሩ ኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ በዚህ ፕሮግራም ላይ በመሳተፍ የዜግነት ግዴታዎን ይወጡ !!!

ማሳሰቢያ-ከዚህ በተጨማሪ ይህንን አስቸኳይ እና የማንቀርበትን ቀጠሮ መልዓክት አንብበው ሲጨርሱ  ላልሰማው ወገን ያሰሙ ! በፌስቡክ ሸር  ( share ) ማድረግዎን እንዳይረሱ

No comments:

Post a Comment