Wednesday, December 5, 2012

የኢትዮጵያ ሙስሊም የጀመሩት ሰላማዊ ትግል ከዳር እንዲደርስ በስደት ላይየኢትዮጵያ መምህራን ማህበር የመምህራን የትግል አጋርነት አስፈላጊ መሆኑን አስታወቀ


ህዳር ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-በሙስሊሙ ማህበረሰብ ላይ የሚደርሰው በደል በሌላውህብረተሰብ ላይም እየተፈጸመ መሆኑንም ገለጸ::
የመምህራን ማህበሩ አስተባባሪ ኮሚቴ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀውበሙስሊሙ ማህበረሰብ ላይ መንግስት እያደረሰ ያለው ግድያ፡ እስራትና በደልበሌላው የህብረተሰብ ክፍልና ቡድን ላይ ሲደርስ የቆየና እየደረሰ ያለው ግፍአካል በመሆኑ በስደት ያለውን መምህራን የትግል አጋርነት ያስፈልጋል ሌላውምየህብረተሰብ ክፍል የትግሉ አጋር ሊሆን ይገባል ሲል ጥሪ አስተላልፋለሁ::
በተለያዩ ወቅቶች አንድ ላይ ሆነን ባለመነሳታችን የከሸፉትን የትግልእንቅስቃሴዎች ልናስታውስ ይገባል ያለው የመምህራን ማህበሩ መግለጫለስኬት በአንድነት ሆነን ልንነሳና ልንታገል ይገባል ብሏል::
በዘር ምንጫቸውና በቋንቋቸው ተነቅሰው ቤታቸው በብልዶዘር የፈረሰንብረታቸው የተዘረፈና ከኖሩበት ቀዬ የተባረሩ ኢትዮጵያውያኖችን ያወሳውመግለጫው በነጻ ሚድያ ጋዜጠኞች ላይ የተመሰረተው የአሸባሪነት ክስናየተወሰደው እርምጃንም በማስታወስ በገዢው ፓርቲ ያልተበደለ የህብረተሰብክፍል የለም ካለ በኋላ በጋራ ልንታገለው ይገባል ሲል አስታውቋል::
የመምህር የኔሰው ገብሬን የትግል ቆራጥነትና መስዋዕትነት በመግለጽመስዋዕትነቱ መና አልቀረም ያለው በስደት የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር አስተባባሪ ኮሚቴ መግለጫ ህዝባዊ አመጽ ደግሞ መስዋዕትነቱም ውጤቱምዘላለማዊ ነው ሲል የጋራ እንነሳ መልዕቱን አጠናቋል::

No comments:

Post a Comment