Tuesday, December 11, 2012

በእነ አቶ በቀለ ገርባ ላይ የቅጣት ውሳኔ ተላለፈ


ታህሳስ ፪(ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-በሽብረተኝነት ወንጀል ተከሰው በእስር ላይ የሚገኙት የኦፌዴንና የኦህኮ የአመራር አባላት የሆኑት አቶ በቀለ ገርባና አቶ ኦልባና ሊሊሳ ከሌሎች 7ተከሳሾች ጋር ዛሬ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ቀርበው የ8 እና የ13 ዓመት እስር ተፈርዶባቸዋል።
በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህር የሆኑት የኦፌዴን ም/ል ሊቀመንበርና የመድረክ አመራር አባል  የሆኑት አንደኛው ተከሳሽ አቶ በቀለ ገርባ በ8 አመት ፣ ሁለተኛው ተከሳሽ  የኦህኮ ምክትል ሊ/ር አቶ ኦልባና ሊሊሳ 13 አመት፣ አቶ ኦልቤካ ለሚ 7 አመት፣ አቶ አደም ቡሳ 3 አመት፣  አቶ ሙሀመድ  መሎ 10 አመት ፣ ወ/ት ሀና ዋቆ 5 አመት ከስድስት ወር፣ አቶ ደረጀ ከተማ 8 አመት፣ አቶ አዲሱ ምክሬ 10  አመትና አቶ ገልገሎ ጎፋ  12 አመት ጽኑ እስራት ተፈርዶባቸዋል። አቶ በቀለ እና አቶ ኦልባና ለ4 አመታት፣ ሌሎች ተከሳሾች ለ2 አመታት ከህዝባዊ መብታቸው እንዲታገዱ ተወስኖባቸዋል።
የኦፌዴን ሊቀመንበር አቶ በቀለ ነገዓ ዛሬ የተሰጠው የፍርድ ቤት ውሳኔ ትክክል አለመሆኑን ገልጸዋል::
ሌሎች ተከሳሾችም ቀድሞ የኦነግ አባላት የነበሩ ነገር ግን መንግስት ምህረት አድርጎላቸው የገቡ መሆናቸው ታውቋል። በሁሉም ተከሳሾች ላይ በቂ ማስረጃ አለመቅረቡ ታውቋል። አቶ ኦልባና ሊሊሳ በእስር ቤት ውስጥ እየደረሰባቸው ያለውን በደል በጽሁፍ ለፍርድ ቤት አቅርበዋል።

No comments:

Post a Comment