ቴዎድሮስ የተባለው ተማሪ ተነሳና “ሦስት ጥያቄዎች አሉኝ” በማለት ንግግሩን ጀመረ። መለስም እንዲጠይቅ ፈቀዱለት፤ “1ኛ. እንዴት ኢ.ህ.አ.ዲ.ግ. 99.9% ምርጫውን ሊያሸንፍ ቻለ?
“2ኛ. ለምንድነው የፀረ-ሽብርተኝነት ሕጉን የህዝቡን፣ የጋዜጠኞችን እና የጋዜጦችን ሃሳብን በነፃነት የመግለፅን መብት ለመገደብ የምትጠቀሙበት?
“3ኛ. ህወሓት ለምን በሰላማዊ መንገድ ሥልጣኑን አይለቅም?” … ይሄኔ ደወል ተደወለና ተማሪዎቹ ለእረፍት ከክፍሉ ወጡ።
ከእረፍት መልስ፣ መለስ “ቅድም ውይይታችን ስለተቋረጠ አዝናለሁ! አሁን የፈለጋችሁት ልትጠይቁኝ ትችላላችሁ” አሉ። ቅድስት የተባለች ትንሽ ልጅ ተነሳችና “አምስት ጥያቄዎች አሉኝ” አለች። “ቀጥይ” አሏት ጠ/ሚ።
“1ኛ. እንዴት ኢ.ህ.አ.ዲ.ግ. 99.9% ምርጫውን ሊያሸንፍ ቻለ?
“2ኛ. ለምንድነው የፀረ-ሽብርተኝነት ሕጉን የጋዜጠኞችን እና ጋዜጦችን ሃሳብን በነፃነት የመግለፅን መብት ለመገደብ የምትጠቀሙበት?
“3ኛ. ህወሓት ለምን በሰላማዊ መንገድ ሥልጣኑን አይለቅም?
“4ኛ. ለምን የእረፍት ሰዓታችን ከ20 ደቂቃ በፊት ቀደም ብሎ ተደወለ?
“5ኛ. ቴዎድሮስ የት ገባ?”
No comments:
Post a Comment