ዓለም አቀፉ የጸረ-ሙስና የአገራትን የመልካም አስተዳደር ይዞታ የሚከታተለው ተቋም Transparency International ዓመታዊውን የዓለም አገሮች የሙስና ደረጃና ሪፖርት ይፋ አደረገ።
አሉላ ከበደ
05.12.2012
የ177 አገሮችን ዓመታዊ የሙስና ደረጃ የመረመረውን ሪፖርት አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት የTransparency International ሊቀመንበር Huguette Labelle እና የድርጅቱ የዩናይትድ ስቴትስ ቅርንጫፍ ሊቀመንበር Alan Larson ናቸው።
«ሙስና በከፋባቸው አገሮች የሰብዓዊ መብት አያያዝም ያንኑ ያህል የከፋውን መስመር ይይዛል፤» ሲሉ የ2012ቱን ዓመታዊ የአሮች ገጽታ በመግቢያቸው

የቃኙት ካናዳዊቷ የድርጅቱ ሊቀመንበር Labelle ናቸው።
ከሰሃራ በስተደቡብ ከሚገኙ የአፍሪካ አገሮች ትልቋ የዩናይትድ ስቴትስ እርዳታ ተቀባይ የሆነችው ኢትዮጵያ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የሲቪል ማኅበረሰብ ይዞታዋ እየተዳከመ መምጣቱን የሚናገሩ ተችዎቿ፥ “በጸረ-ሙስና ዘመቻውም ክፉኛ ወድቃለች፤ ይላሉ። ለዚህም አንዱ ምክኒያት፤ የሙስናው ተዋናዮች በተለያየ ደረጃ የሚገኙ የመንግስት ባለሥልጣናት ጭምር መሆናቸው ነው፤” ሲሉ ይወነጅላሉ።
ኢትዮጵያ የህዝቧን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል በእጅጉ ስትጥር መቆየቷን ያመለከቱት Labelle ባለፉት ጥቂት ዓመታት የሚታየው ግን አሳሳቢ ሁኔታዎች ጎልተው መታየት መቀጠላቸውን አመልክተው፤ “ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ሲቪል ማኅበረሰቦች ያላቸው ሥፍራ እየጠበበ መምጣቱ አንዳንድ አሳሳቢ ሁኔታዎችን ከስቷል። ያ ጤናማ አይደለም። ጥሩም አይደለም። መንግስት ያ አቀራረብ ለኅዝቡም ሆነ ለመንግስት ጥሩ ያለመሆኑን አጥኖ የተሻለ አቀራረብ መከተል ይመርጣል፤ ብዬ ተሥፋ አደርጋለሁ። ስለሆነም ነጻ፥ ግልጽና የህዝቡን ድምጽ ያለማቀፍ የተሻለው አማራጭ አይደለም። አስተዋይ መንግስታት ለመረጋጋት ጭምር የሚመርጡት ይሄን ሳይሆን የሚበጃቸውን ነው።”
ሙስና በዓለም ዙሪያ ለዲሞክራሲ ተቋማት አደጋ የሚደቅን መሆኑን፤ ሙስና ለሚሠራ ምጣኔ ሃብት ህልውና አደጋ ደቃኝ መሆኑንና በመጨመሻም ለአገሮች ደህንነትና ጸታ አደጋ መሆኑን፤ አሜሪካውያን ሊረዱ ይገባል፤ ሲሉ ያስገነዘቡት የድርጅቱ የአሜሪካ ቅርንጫፍ ሊቀመንበር Larsen በበኩላቸው የመንግስታትን ተጠያቂነት ማረጋገጥና ሙስናን መዋጋት የሁሉም ድርሻ መሆኑን ጠቁመዋል።
ኢትዮጵያ በአገሮች የሙስና ሰንጠረዥ ደረጃዋ ከቀደሙት ዓመታት በመጠኑ መሻሻሉን ነገር ግን በተለይ የተዳከመውን የሲቪል ማኅበረሰቦች የነጻነት ይዞታ አስመልክቶ ብዙ ሥራ እንደሚጠብቃት ሊቀመንበሯ ተናግረዋል።
“በዘንድሮው የዓለም አቀፍ የአገሮች የሙስና ሰንጠረዥ የኢትዮጵያ ደረጃ ከ177 አገሮች 113ተኛ ነው። ስለዚህ መሻሻል የሚችልበት ሥራ አለ ማለት ነው።” ያሉት Ms Labelle “የተወሰኑ ዓመታት በፊት ከዚህም የባሰ ነበር። የሙስና አመላካች ደረጃዎች በዓመታት ጊዜ ውስጥ መሻሻል አሳይተዋል። ስለዚህ ኢትዮጵያ በተለይም የሲቪል ማኅበረሰቦትን ይዞታ አስመልክቶ እየወሰደች ባለችው እርምጃ ሳቢያ ወደ ኋላ እንዳታፈገፍግ ማረጋገጥ አለባት።” ብለዋል።
በዓመታዊው የአገሮች የሙስና ሰንጠረዥ ደረጃና ሪፖርት ዴንማርክ፥ ፊንላንድ፥ ኒው ዚላንድ፥ ስውዲንና ሲንጋፖር እንደ ቅደም ተከተላቸው ዝቅተኛ የሙስና ምግባር በማስመዝገብ ቀዳሚው አምስት አገሮች ሲሆኑ፤ ማይናማር፥ ሱዳን፥ አፍጋንስታን፥ ኮርያና ሶማሊያ ደግሞ ከመጨረሻው ረድፍ ከተሰለፉት ውስጥ ናቸው።

SOURCE: http://amharic.voanews.com
No comments:
Post a Comment