ታህሳስ ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-በአዲሱ መልቲ ሞዳል ሲስተም መሰረት እቃዎችን ከጅቡቲ በመጫን ወደ መሀል አገር የገቡ ከ100 በላይ መኪኖች ውሳኔ የሚሰጥ አካል በመጥፋቱ ላለፉት 10 ቀናት አዋሽ አርባ ላይ መቆማቸውን ሾፌሮች ተናግረዋል።
ጭነቱ የመንግስት መሆኑን የተናገሩት ሾፌሮች በሞጆ ደረቅ ወደብና በአዲስ አበባ ደረቅ ወደብ መራገፍ ቢኖርበትም ውሳኔ የሚሰጥ አካል በመጥፋቱ እስካሁን ሊራገፍ አልቻለም።
የመኪኖቹ ባለንብረቶች ለመንግስት ባለስልጣናት ችግሩን ቢገልጹም ፣ ባለስልጣናቱ በቂ ምላሽ ሊሰጡ አልቻሉም።
መንግስት የመልቲ ሞዳል ሲስተምን የዘረጋው በጅቡቲ ወደብ ላይ የሚቆዩት እቃዎች ኪራይ ከፍተኛ እየሆነ በመምጣቱ መሆኑ ይታወሳል።
እቃዎችን ካለፈው አንድ አመት ጀምሮ በቀጥታ ከጅቡቲ ወደብ በማንሳት በሞጆ ደረቅ ወደብ ማራገፍ መጀመሩን የገለጡት ሾፌሮቹ፣ አሰራሩ ጥሩ ቢሆንም የአፈጻጸም ችግሮች ግን አሉ ብለዋል
No comments:
Post a Comment