Thursday, May 9, 2013

የመፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ኢቲቪን ጨምሮ የመንግስትአካላትን ለመክሰስ ለፍርድ ቤት ያቀረቡት ጥያቄ


የመፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ኢቲቪን ጨምሮ የመንግስትአካላትን ለመክሰስ ለፍርድ ቤት ያቀረቡት ጥያቄ የፍርድ ቤቱ ሬጅስትራር የተለያዩ ምክንያቶችን በመፍጠር የክስ ፋይል አልከፍትም ማለቱ ተሰማ፡፡
በፌድራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 4ተኛ ወንጀል ችሎት በሃሰት የሽብር ክስ የተመሰረተባቸው የህዝበ ሙስሊሙ የመፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴዎች በጠበቆቻቸው አማካኝነት በጀሃዳዊ ሃረካት በተሰኘው ፊልም ለተፈፀመባቸው የሥም ማጥፋት ተግባር ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ ማቅረባቸው የሚታወስ ነው፡
ሆኖም የቀረበውን ክስ እና ተከሳሽ የሆኑትን የመንግስት መስሪያ ቤቶች የፍርድ ቤቱ ሬጅስትራር ከተመለከተ ቡሃላ ከህግ አግባብ ውጪ በሆነ መልኩ ይህንን ክስ የፍርድ ቤቱ ፕሬዝዳንት ሊመለከቲት ይገባል በማለት ወደ ፕሬዝዳንቱ ከተወሰደ ቡሃላ ፕሬዝዳንቱም በሌላ ቀን ተመልሰው እንዲመጡ ጠበቆቻቸውን ቀጠሮ ይሰጣሉ፡፡ ቀጠሮውን አክብረው በተባሉበት ቀን ሲቀርቡም ፕሬዝዳነቱ ለግዜው ቢሮ አልገቡም በሚል ምክንያት የፍርድ ቤቱ ሬጅስትራር ቢሮ የክስ ፋይል ሊከፍትላቸው አለመቻሉን የኮሚቴዎቻችን ጠበቃ የሆኑት አለም አቀፉ የህግ ባለሙያ ዶ/ር ያዕቆብ ሃይለማርያም አስታውቀዋል፡፡
የኮሚቴዎቻችን ጠበቆች የቀረበው ክስ የጊዜ ገደቡ አልፎ እንዳይቃጠል በሚል ማቅረብ የሚገባቸውን ማስረጃዎች እና የህግ ሰነዶች አያይዘው ቢያቀርቡም ከተከሳሾቹ መካከል የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንትም በመኖራቸው የተለያዩ ምክንያቶችን በመፍጠር የክስ ፋይሉ እንዳይከፈት መደረጉን ምንጮች አስታውቀዋል፡፡ በክሱ መሰረት የኢትዬጲያ ራዲዬ እና ቴሌቪዥን ድርጅት፣የብሄራዊ ደህንነት እና መረጃ መረብ ኤጀንሲ፣የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት እንዲሁም ሌሎች መስሪያ ቤቶች ሊከሰሱ የነበረ ሲሆን ጠበቆቹም ጃሃዳዊ ሃራካት በደንበኞቻቸው ላይ ባደረሰው የሞራል ጉዳት ተከሳሾች የ 8 ሚሊዬን አንድ መቶ ሺህ ብር የሞራከል ካሳ እንዲከፍሉ እንዲደረግላቸው ለፍርድ ቤቱ በክሱ ላይ አስፍረው እንደነበር የኮሚቴዎቻችን ጠበቃ ዶ/ር
ያዕቆብ ሃይለማርያም አስታውቀዋል፡፡
አላህ ፍትህን ያስፍንልን!!!

No comments:

Post a Comment