Friday, May 17, 2013
ሆድ ያባውን ብቅል ያወጣዋል
ህወሃት በእሱና በራሱ ጉጅሌ አባላቶቹና ሚዲያዎቹ “በአገራችን ታሪክ ያልታየክስሰት በዋናነት ዜጎች በአንድነት፣ ከድህነት በማውጣት በደስታ የተሞላ ህይወትንለማምጣት የኢኮኖሚ እድገታችን እያደገ ነው ይለናል” ይህ በሬዲዮ አዲስ አበባ፣በሬዲዮ ኢትዮጵያ እና በሬዲዮ ፋና ብቻ ነው። ይህ ውሸት እንደተጠበቀ ሆኖ አዲሱየለውጥ ምእራፍ ደግሞ የወያኔ ቡችሎች በየጊዜው ከህወሃት መጋረጃ በስተጀርባያለውን የተደበቀውን እውነት ወይም ግንቦት 7 ሲል የነበረውን የሚያረጋግጡመረጃዎችን መስማት መጀመራችን ነው።
ህወሃታዊ መነቃቃትን ለማምጣት ደካሞችንና ለሆዳቸው ያደሩ ባለስልጣናቱን ሰብስቦ ስለ እድገት ጎዳናና ኃይል የሚያመረቁትሩፋቶችን በሚዲያዎቹ ያስነግራል። የዜጎችን የስነ ልቦና ውድቀት በከፍተኛ ደረጃ የሚፈልገው ህወሃት ባሪያዎቹንና አገልጋዮቹንበጥቅማጥቅም በማሸነፍ እውነትን ይደብቁለት ዘንድ ሁሌም ሙከራ ያደርጋል። አንዱም ተሳክቶለት አያውቅም እንጅ።
የኢትዮጵያ ሕዝብ ጠላት የሆነው ህወሃትና የእነሱ ተላላኪ ወያኔዎች ጦር ሰብቀው፣ መሣሪያ ወድረውና በከፋፍለህ ግዛፖሊሲያቸው ተጠቅመው ሀገሪቷን እና ህዝቡን ከፋፍለው በዘር ካርድ ተጫውተው የስልጣን እድሜያቸውን ማራዘም ተቀዳሚአጀንዳቸው እንጂ መቼም ስለ ኢትዮጵያ አንድነትና እድገት አስበውም አልመውትም አይውቁም፡፡ የሶማሊያው ክልል ፕሬዝዳንትአብዲ ሙሃመድ የተናገረውም ይህንኑ ነው ተደጋገመ እንጂ።
የከፋፍለህ ግዛ የጫካ ፖሊሲያቸውን ተጠቅመው ሀገሪቷን እንደተቆጣጠሩ ለመዝለቅ በማስብ የግል የሥልጣን እርካታቸውንለመጠበቅ ብቸኛ ስልት ሆኖ ያገኙት የሶማሊያ ፕሬዝዳንቱ እንደሚሉት ለሶማሊያው “አማራው፣ ኦሮሞው፣ ጉራጌው፣ አፋሩከተባበሩ ለሶማሊያ አይመቹም። ስለዚህ ህወሃትን ደግፉና እነሱን ውጉ፤ አማራውና ኦሮሞው መቼም አይስማሙም።” በዚሁያልተገራ አንደበታቸው ደግሞ የህወሃቶቹ የአማራ ጎጅሌ ተላላኪ ባለስልጣናት አማራ ክልል ይሄዱና “የሶማሊያና የኦሮሞው ሰርቶአደር ህዝብ የእንገንጠል ጥያቄ ሊያቀርቡብህ ነው” ይላሉ፤ ለባለታሪኩ የኦሮሞ ህዝብም ሄደው “አማራ ሊገዛችሁ ነው” የሚል ቆሻሻየዘርን ክፍፍል መሰረት ያደረገ ፖለቲካዊ፣ ያልበሰለ ራእያቸውን ለማስፈጸም ሺ ምላስ ይሆናሉ።
የኢትዮጵያ ህዝብ በረዥም የታሪክ ዘመኑ ውስጥ በተደጋጋሚ የሚፈታተኑትን ጠላቶቹንና ተላላኪዎቹን የተንኮል አጀንዳ ቀድሞስለሚያውቅ ልዩነቱን አስወግዶና ቅድሚያ ለሀገሩ፣ ለአንድነቱ ሰጥቶ መሰሪ ጥቃታቸውን በማክሸፍና በማኮላሸት ረገድ ከፍተኛሚና ያለው ህዝብ፣ በእነዚህ የህወሃት/ኢህአዴግ የዘር ድብቅ አጀንዳ አይንበረከክም አይከፋፈልም። አማራውም፣ አሮሞውም፣ጉራጌውም፣ ትግሬውም፣ ቤንሻንጉሉም፣ ደቡቡ አንድ ነው። ተከባብሮ ያለ እና የሚኖር ታላቅ ህዝብ በመሆኑ ከጠላቶቹ ህወሃትከሀገር አጥፊ ዘረኞች የሚመጣበትን ቀድሞውንም ጠንቅቆ ያውቀዋልና አይገርመንም፡፡
ባለ ብዙ ምላሱ የወያኔ መንግስት መርዶ ነጋሪ እየሆኑ ያስቸገሩት ግለገል ፍየሎች የዚሁ የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ በሽታ ተጠቂ(victim) ናቸው። ብቻቸውን በተለቀቁ፣ ተንፍሱ በተባሉ ጊዜ በጀሮዎቻቸው የሚሰማቸው የተደበቀውን የእውነት ያለህ ጩኸትነው የሚናገሩት። የህዝባቸውን በደል፣ ሰቆቃ እና የወያኔን እውነተኛ ገፅታና ያለበትን ተጨባጭ የዕድገትና የልማት ሁኔታ ያወጣሉ፣ይናገራሉ።
ፕሬዚዳንቱ እፎይ ብሎ አዩኝ አላዩኝ ሳይል ያደረገው ንግግርም “ እኛ እንዳደግን ፣ ጥሩ ደረጃ ላይ እንደደረስን ተደርጎ በየጊዜውየሚቀርበው ሪፖርት ፍጹም ትክክል ያልሆነ ውሸት ነው። አሁን በእጄ የያዝኩት ሪፖርት እውነት ስለመሆኑ እርግጠኞችአይደለንም፤ ከአሁን በፊት ይቀርቡ የነበሩ ሪፖርቶችም እንዲሁ ናቸው። ግምገማ ለማለፍ ተብሎ በውሸት የተሞሉ በቁጥር የታጀቡየውሸት ሪፖርቶች ናቸው የሚቀርቡት እንጅ እኛ በድህነት አረንቋ ውስጥ ነን ” ብሏል። የሚገርመው ፕሬዝዳንቱ ይህንን ውሸትህዝብ የሚያውቀው አልመሰለውም፤ ለሁሉም በርታ አይዞህ ሆድ አይባስህ እኛም እያልን ያለነው ይህኑን አይን ያወጣ ውሸትእንታገለው ነው የምንለው።
አቶ አብዲና ሌሎችም ለሆዳችሁ ያደራችሁ ባለሰልጣናት ራሳችሁን ቀይሩ ውስጣችሁን አውሩ በታሪክ ተጠያቂ አትሁኑ፣ህሊናችሁን አዳምጡ እንጂ ለህዝብ ጠላት ለሆነው የህዝብ ድጋፍ ከሌለው ለህወሃት ፍርፋሪ በማደር ሀገራችን ለማጥፋት ሁሌከሚያስቡ ከህወሃት ቡድኖች ጋር አብራችሁ ወገንን ማታለልና በዘር ካርድ መጫዎት ይብቃችሁ። የዲሞክራሲ ሃይሉን ጎራተቀላቀሉ፣ መረጃ አቃብሉ።
የወያኔ እውነተኛ ገፅታ ራሳቸውም እንደሚያረጋግጡት ይህ በመሆኑ፣ በየቦታው ዜጋን በማፈናቀል ህዝብ በሀገሩ ስደተኛ እንዲሆንፊትም የጀመረውን ድብቅ ሥራ አማራውን በማሰደድ ያላቸውን ጥላቻ በእጥፍ በማሳደግ በርካታ አባዎራዎችን በሁሉም የሀገሪቱክፍሎች ህይዎታቸው ጉስቁል እንዲሆን እያደረጉ ነው። ታዲያ ይህን እውነት እየሰማን እሰከ መቼ እንተኛ ይሆን? ግንቦት 7ንቅናቄ ተነሱ ኑ! ተቀላቀሉን ብለናል።
ወያኔን ማስወገድ የሁሉም ብሄሮች ጥቅም ነው። ሁሉም ህዝብም፣ ሁሉም ፓርቲ በወያኔ መወገድ ይስማማል። ታዲያ ማንያስወግደው? ከጥንት ጀምሮ ብዙ ትውልድ ሀገሩን ከውስጥና ከውጭ ወራሪ ለመታደግ በዚህች የኢትዮጵያ ምድር ላይ መሰዋእትከፍሏል፡፡ ወጥቷል፣ ወርዷል አልፏል፡፡ የሰው ልጅ ተፈጥሮ የለገሰችውን የቅብብሎሽ ህግ ተቀብሎ ለነጻነቱ፣ ለማንነቱ መከበርእምቢተኝነትን ሲቀባበል፣ ሲተካካ ኖሯል፡፡ ወደፊትም ይኖራል፡፡ በዚህ የአሁኑ ሂደት ደግሞ እኛ ባለተራዎች ነን እማማኢትዮጵያን ከህወሃት መንጋዎች መንጋጋ ፈልቅቆ የማውጣት! ስለዚህ ለነጻነታችን ከሰማይ የሚወርድ ምንም አይነት መና የለም።እኛው ለእኛው ለራሳችን መሰዋእት ከፍለን ወያኔን እናስወገድ ዘንድ ትግሉ፣ ወቅቱ አሁን ነው።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment