Wednesday, May 22, 2013

የአያት አክሲዮን ማህበርና የስራ አመራሮቹ ላይ በእስርና ከፍተኛ በገንዘብ ተቀጡ


http://www.zehabesha.com/amharic/wp-content/uploads/2013/05/ayat-real-estate.jpg
(ፍኖተ ነፃነት) የአያት አክሲዮን ማህበር፣ በስራአስኪያጁ አቶ አያሌው ተሰማና በሌሎች ማህበሩ አመራሮች ላይ ላይ በገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን በተመሠረቱባቸው  ክሶች ጥፋተኛ በመባላቸው ዛሬ በልደታ ፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 8ኛ ወንጀል ችሎት በእስርና ከፍተኛ በገንዘብ እንደተቀጡ የፍኖተ ነፃነት የፍርድ ቤት አስታወቀ፡፡
የፍኖተ ነፃነትየፍርድ ቤት ዘጋቢ እንዳስታወቀው የልደታ ፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 8ኛ ወንጀል ችሎት ባስተላለፈው ውሳኔ መሰረት አያት አክሲዮን ማኅበር 90 ሚሊዮን ብር፣ የአያት አክሲዮን የማኅበሩ መስራችና ከፍተኛ ባለድርሻ እንዲሁም ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አያሌው ተሰማ 12 ዓመት እስራት እና 3.2 ሚሊዮን ብር ቅጣት፣ ዶ/ር መሐሪ መኮንን 12 ዓመት ፅኑ እስራት እና 436,646 ብር ቅጣት፣ አቶ ጌታቸው አጎናፍር 10 ዓመት ፅኑ እስራት እና 411,969.60 ብር ቅጣት ተወስኖባቸዋል፡፡  የአያት አክሲዮን የማኅበሩ መስራችና ከፍተኛ ባለድርሻ እንዲሁም ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አያሌው ተሰማ እና ሌሎች ታዋቂ ነጋዴዎች ላይ ክስ በማቀናበርና በየሚዲያው ማብራሪያ ሲሰጡ የነበሩት የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ምክትል ዳይሬክተር አቶገብረዋህድ ገ/ጊዮርጊስ በሙስና ተጠርጥረው በቅርቡ መታሰራቸው ያስታውቃል፡፡

No comments:

Post a Comment