Tuesday, May 14, 2013

አቶ ተመሰገን ጉልላት ወደ ጋምቤላ በመሸሽ ሱዳን ለመግባት ሁኔታዎችን ሲያመቻቹ በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡


በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በፖሊስ ሲፈለጉ የነበሩት የናዝሬት ጉሙሩክ የህግ ማስከበር ኃላፊ አቶ ተመሰገን ጉልላት በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡
ሰሞኑን በህግ ቁጥጥር ስር ከዋሉት ተጠርጣሪዎቸ ጋር ሲፈለጉ የነበሩት ግለሰቡ ከአዲስ አበባ ወደ ጋምቤላ በመሸሽ ሱዳን ለመግባት ሁኔታዎችን ሲያመቻቹ ነበር፡፡
ተጠርጣሪው በእጃቸው የተለያዩ ሰነዶችና 160 ሺህ ብር ይዘው ነበር የተሰወሩት፡፡ የጋምቤላ ጉሙሩክ ስራ አስኪያጅ ለሆኑት አቶ ጌታቸው አሰፋ 80 ሺህ ብር በመስጠት ወደ ሱዳን ለመግባት ጥረት አድርገዋል፡፡
ሆኖም ግን በህዝቡና በጸጥታ ኃይሉች ትብብር ዋንኛ ተፈላጊ የነበሩት አቶ ተመስገን ጉልላትም ሆኑ እሳቸውን ወደ ሱዳን ለማስገባት የተባበሯቸው አቶ ጌታቸው አሰፋ በቁጥጥር ሰር መዋላቸውን ኢሬቴድ ከፖሊስ ያገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

No comments:

Post a Comment