Thursday, May 30, 2013

መንግስት በጉምሩክ ባለስልጣናት ላይ የወሰደውን እርምጃ ወደ ሌሎች ባለስልጣናት ማዞር ፈርቷል ተባለ



ግንቦት ፳፪ (ሀያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-መንግስት በቅርቡ በገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ሥራ ኃላፊዎችና ባለሃብቶች ላይ የወሰደውን እርምጃ ወደሌሎች በሙስና የሚጠረጠሩ ባለስልጣናት ለማስፋት ፍርሃት እየታየበት መሆኑን ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ በአዲስአበባ ዩኒቨርሲቲ የፍልስፍና መምህር ከኢትዮምህዳር ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለምልለስ ገልጸዋል፡፡
ዶክተሩ ግንቦት 20 ለወጣው ኢትዮምህዳር ጋዜጣ እንደተናገሩት “በሙስና ተከስሰው ወደወህኒ የወረዱት የአንድ መ/ቤት ሠራተኞችና ከእነርሱ ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ ሐብታሞች ናቸው፡፡ የሙስናው ደረጃ በጣም የተስፋፋና የአገሪቱን አብዛኛውን ተቋማት ያዳረሰ ለመሆኑ ከኦዲት ሪፖርቱ ፍንጭ አግኝተናል፡፡ ይሁንና የክሱን ውስንነት በምናይበት ጊዜ ከጉምሩክ ውጪ ያሉ ስማቸው በሙስና የሚነሳ ተቋማትን ለመንካት ፈራ ተባ የተባለ ይመስለኛል” ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡
ዶ/ር ዳኛቸው አያይዘውም በአንድ ስርዓት ውስጥ የፖለቲካዊና የሕግ አይነኬዎች ከኖሩ ስርዓቱ ትልቅ ችግር ውስጥ የወደቀ መሆኑን እንደሚያሳይ ጠቁመዋል፡፡
መንግስት በራሱ ውስጥ ሙስና መኖሩን ማመኑ በራሱ ትልቅ ነገር መሆኑን ዶ/ር ዳኛቸው ጠቁመው ነገር ግን መንግስት በሙስና ዙሪያ የሚሰጠውን መግለጫ ዜጎች አሜን ብለው መቀበል እንደሌለባቸው መክረዋል፡፡
“በአሁኑ ወቅት እንደሚታየው ጥቂት ሰዎችን ከተወሰኑ ተቋማት በመውሰድ በማስር ብቻ ችግሩ የግለሰቦች የሞራል ዝቅጠት አድርጎ የማቅረብ ነገር እያየን ነው፡፡ ነገር ግን በኔ አስተያየት ሙስናው ከስርዓቱ ጋር በእጅጉ የተያያዘ ነው” ብለዋል፡፡
“ሁሉም ሹመኞች ሙሰኞች ስለሆኑ በምን የሞራል መመዘኛ አንዱ ከሳሽ ሌላው ተከሳሽ ይሆናል” በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄም “ሁላችንም የሰው ልጆች እስከሆንን ድረስ እርስበርሳችን ተካሰን ለመተራረም እንሞክራለን እንጂ ከሰማየሰማያት የመላዕክት ዐቃቤ ሕግ አምጥተን ችሎት ልናቆም አንችልም” ሲሉ አስረድተዋል፡፡
በተያያዘም ያለፉት 22 ዓመታት የኢህአዴግ የአገዛዝ ዘመን ሕዝቡን ፍርሃት ውስጥ እንደጣለው ዶ/ሩ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል፡፡ “…ልክ የገንዘብ የመግዛት አቅም እንዳሽቆለቆለው ሁሉ የሕዝቡም በነጻነት የመናገር ድፍረት እየወረደ መጥቷል” በማለት አስረድተዋል፡፡
ይህንን አባባላቸውን በምሳሌ ሲያስረዱ “ ለሶስት አመታት ያህል በሕዝብ ትራንስፖርት ስገለገል ቢያንስ ቢያንስ ከምኖርበት አሮጌው አውሮፕላን ማረፊያ እስከ ስድስት ኪሎ ድረስ
ስሄድና ስመለስ ስድስት ታክሲዎችን ስለምጠቀም ከበርካታ ሰዎች ጋር የመገናኘት ዕድል ነበረኝ፡፡ ይህንኑ ዕድል ተጠቅሜ አንዳንድ የፖለቲካ ጨዋታዎችን ስጀምር አብረውኝ የሚጓዙ ሰዎች ለማናገር ወይንም ከእኔ ጋር ለመወያየት እንደሚፈሩ ለመረዳት ችያለሁ፡፡ ይህ የፍርሃት ድባብ በታክሲ ውስጥ ብቻ ሳይሆን በሬስቶራንት፣ በቡና መጠጫ ስፍራዎች፣ በአጠቃላይ በሕዝብ መሰብሰቢያ ቦታዎች የሚስተዋል መሆኑን ተረድቻለሁ፡፡ ምናልባት እዚህ ላይ
የሶስዮሎጂ መምህራን አቀራረብህ ሳይንሳዊ አይደለም፣በቂ መረጃ የለህም ሊሉ ይችላሉ፡፡ ሆኖም ግን በተለይ ከምርጫ 97 በኃላ የአፈናና የፍርሃት ድባቡ እንደተጠናከረ ከመንግስት ውጪ ያሉ ዜጎች እንደሚመሰክሩ ጥርጥር የለኝም” ሲሉ ተናግረዋል፡፡
እንደዶ/ር ዳኛቸው ገለጻ ሕዝብን የማስፈራራትና የማቀብ ስርዓት በትክክል እየሰራ ነው የሚባለው ሕዝቡ ይህንን አድርግ፣አታድርግ ተብሎ ሳይታዘዝ ከፍርሃት በመነጨ ራስን ማገድ ሁኔታ ላይ ሲወድቅ ነው በማለት አገሪቱ የምትገኝበትን ተጨባጭ ሁኔታ ዳስሰዋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት የኢንተርኔት ድህረ ገጾችን ለማፈን 26 ቢሊዮን ብር ክፍያ ለቻይና መንግስት ፈጸመ

ግንቦት ፳፪ (ሀያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ኢሳት ከአስተማማኝ የኢትዮጵያ የመረጃ መረብ የደህንነት ሰራተኛ ባገኘው መረጃ መንግስት ለስርአቱ አደጋ ይሆናሉ ብሎ የገመታቸውን የመገናኝ ብዙሀን ወደ አገር ቤት ሰርገው እንዳይገቡ ለመከላከል ከ1.2 ቢሊዮን ዶላር ወይም ወደ 26 ቢሊዮን የሚጠጋ ገንዘብ መክፈሉን ለማወቅ ተችሎአል።
በቁጥር አንድ እንዲታፈን ትእዛዝ የተላለፈበት ኢሳት ሲሆን ድህረገጹ ራዲዮው እና ቴሌቪዥኑን ሙሉ በሙሉ  እንዲታፈን ስምምነት ላይ ተደርሷል።  ፣ የአሜሪካ ድምጽ  እና የጀርመን ድምጽ የራዲዮ ጣቢያዎች ደግሞ በሚያቀርቡት ዝግጅት ይዘት አይነት አፈና እንዲካሄድባቸው ሲወሰን አሁንም ድረስ ስርአቱን የሚጻረሩ ድረጎች ሙሉ በሙሉ እንደታፈኑ ይገኛሉ።
ኢሳት ድረገጹ ቢታፈንበትም ራዲዮ እና ቴሌቪዥኑ ካለፉት 5 ወራት ጀምሮ ያለ ምንም ችግር እየተላለፈ ይገኛል።
የኢትዮጵያ ህዝብ የዲሽ አቅጣቻውን በየጊዜው በመቀያየር ኢሳትን በመከታተል ላይ ይገኛል። አንድንድ ባለስልጣናትም ኢሳትን እየተከታተሉ አንዳንድ እርምጃዎችን መውሰድ መጀመራቸውን የሚደርሱን መረጃዎች ያሳያሉ።
በተመሳሳይ ዜናም መንግስት በፊስ ቡክ እየደረሰበት ያለውን ውግዘት እና የለውጥ ማእበል ለመግታት ‹‹ ሬሳው ›› ሲል ስም የሰጠውን የአፈና ቴክኖለጅ ተግባራዊ ለማድረግ እንቅስቃሴ ጀምሯል፡፡ ሙከራው ተግባራዊ ከሆነ ሙሉ ለሙሉ የፊስ ቡክ ግንኙነቶችን ለመገደብ እድል እንደሚያገኝ የደረሰን መረጃ ያሳያል። ካለፈው ወር ጀምሮ ስራውን ለማስጀመር የተደረገው ተደጋጋሚ ጥረት አለመሳካቱ ታውቋል።
በጉዳዩ ዙሪያ የመንግስት ባለስልጣናትን ለማነጋገር ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

ESAT Daily News Amsterdam May 30, 2013 Ethiopia


የግንቦት ሰባት አራተኛ ጉባኤ አቋም መግለጫ | Official Site for Ginbot 7 Movement for Justice, Freedom and Democracy

የግንቦት ሰባት አራተኛ ጉባኤ አቋም መግለጫ
የግንቦት ሰባት የፍትህ ፤ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ አራተኛ ጉባኤ ቅዳሜ ግንቦት 17 ቀን 2005 ዓም ተጀምሮ ለሦስት ተከታታይ ቀናት ከተካሄደ በኋላ ህዝባዊ ትግሉን ወደፊት የሚያራምዱ ዉሳኔዎችን ካሳለፈ በኋለ ባለፈዉ ሰኞ ምሽት እጅግ በጣም በደመቀ ሁኔታ ተጠናቀቀ። ይህ የንቅናቄዉ አራተኛ መደበኛ ጉባኤ ንቅናቄዉ ባለፉት ሁለት አመታት የተጓዘባቸዉን መንገዶች፤ ያቀዳቸዉን ስራዎችና የዕቅዱን አፈጻጸም በጥልቀትና በስፋት በመዳሰስ መጪዉ የትግል ወቅት የሚጠይቀዉን የመስዋዕትነት ደረጃ ከወዲሁ ተመልክቶ ዘረኛዉን የወያኔ አገዘዝ በማስወገድ የኢትዮጵያን ህዝብ የፍትህና የዲሞክራሲ ጥማት ሊያረኩ ይችላሉ ብሎ ያመነባቸዉን አበይት ዉሳኔዎች አሳልፏል።
የግንቦት ሰባት አራተኛ መደበኛ ጉባኤ የንቅናቄዉን የአለፉት አምስት አመታት ጉዞና በዚህ በአራተኛዉ ጉበኤ ላይ የስልጣን ዘመናቸዉን የጨረሱት የንቅናቄዉ ምክር ቤትና የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የስራ ዕቅድና የስራ አፈጻጸም ሪፖርት አዳምጦ ሰፊና ጥልቅ ዉይይት ካካሄደ በኋላ በጉባኤዉ ላይ አዲስ ለተመረጡ የአመራር አባላት ንቅናቄዉ የታሰበበትን ግብ እንዳይመታ አንቀዉ የያዙትን እንቅፋቶች እንዲያስወግድና እንዲሁም የንቅነቁዉ ጥንካሬ በታየባቸዉ መስኮች አቅሙን አጣናክሮ በይበልጥ በመስራት የኢትዮጵያ ህዝብ ከንቅናቄዉ የሚጠብቀዉን የታሪክ አደራ እንዲወጣ አሳስቧል። በጉባኤዉ ወቅት አባላት ያደረጉት አመራሩን የመንቀፍ፤አቅጣጫ የማሳየት፤ ሀሳብ የማመንጨትና በአጠቃላይ በእያንዳንዱ የጉባአዉ ስብሰባ ላይ ባሳዩት ንቁ ተሳትፎ ንቅናቄዉ በህዝባዊ አመጽና እምቢተኝነት ዘርፎች ብቻ ሳይሆን በዲሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍም እያደገ መምጣቱን አሳይተዋል።
የግንቦት ሰባት አራተኛ መደበኛ ጉባኤ የምክር ቤትና የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ፤ ኦዲትና ቁጥጥር ኮሚቴ እንዲሁም የስነ ስርአትና የግልግል ኮሚቴ ሪፖርቶችን አዳምጦ ሰፊና ጥልቅ ዉይይት ካካሄደ በኋላ ሪፖርቶቹን አጽድቋል። ከዚህ በተጨማሪ የንቅናቄዉን እስትራቴጂና ይህንኑ እስትራቴጂ ተሸክሞ በተግባር የሚተረጉመዉን መዋቅር በአጽንኦት ከፈተሸ በኋላ በስትራቴጂዉ ላይ መጠነኛ ለዉጥ በማድረግ የእስትራቴጂዉንና የመዋቅር ለዉጡን ተቀብሎ አጽድቋል። ይህ የንቅናቁዉ አራተኛ ጉባዜ ንቅናቄዉን ላለፉት ሁለት አመታት የመሩትንና ያገለገሉትን የምክር ቤት፤ የኦዲትና ቁጥጥር፤ የስነ ስርአትና ግልግልና የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ላደረጉት አስተዋጽኦ አመስግኖ በማሰናበት በምትካቸዉ ንቅናቄዉን ለሚቀጥሉት ሁለት አመታት የሚያገለግሉ የምክር ቤት አባላት፤ የኦዲትና ቁጥጥር፤ እንዲሁም የስነ ስርአትና ግልግል ኮሚቴ አባላትን መርጧል።
አራተኛዉ የግንቦት ሰባት መደበኛ ጉባኤ ኢትዮጵያ ዛሬ የምትገኝበትን ሁኔታ በዝርዝር ከቃኘ በኋላ ዘረኛዉ የወያኔ አገዛዝ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ዉጊያ የተያያዘዉ አገር ዉስጥና በዉጭ አገሮችም ስለሆነ ወያኔን በእነዚህ ሁለት የትግል መስኮች እንደአመጣጡ ከገጠምነዉ የሚሸነፍ ድርጅት መሆኑን ሙሉ በሙሉ በመቀበል አባላቱ ባሉበት ቦታ ሁሉ የሚሰሩት ስራ ወያኔን በማስወገድ ላይ እንዲያተኩር አሳስቧል። ከአለም ዙሪያ ከተለያዩ አገሮች የመጡ የግንቦት ሰባት አባላትን ያሰባሰበዉ አራተኛዉ የግንቦት ሰባት መደበኛ ጉባኤ የትግል ቃል ኪዳን የታደሰበት፤የመስዋዕትነት ዝግጅት የታየበትና አባላት የትግልና የስራ ልምድ የተላዋወጡበት ከምን ግዜዉም ባላይ የተሳካና የተዋጣለት ጉባኤ ነበር። በመጨረሻ ጉባኤዉ የግንቦት ሰባት የፍትህ ፤ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ አራተኛ ጉባኤ ለአባላቱና በአጠቃላይ ለኢትዮጵያ ህዝብ አዲስ የትግል ጥሪ በማስተላለፍ ደማቅ በሆነ ስነሰርአት ተፍጽሟል።
የግንቦት ሰባት የፍትህ ፤ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ
የግንቦት ሰባት አራተኛ ጉባኤ አቋም መግለጫ | Official Site for Ginbot 7 Movement for Justice, Freedom and Democracy
ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ
H.I.M. Haile Selassie and bronze statue of Ghanaian President Kwame Nkrumah
ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ: ፕሬዚደንት ንኩሩማ ሃዉልት
የአፍሪካ አንድነት ድርጅት (ኦ ኤ ዩ) የአፍሪካ ሕብረት (ኤ ዩ በየአፍሪካ አንድነትን የተካው) ባለፈው ሳምንት በአዲስ አበባ ከተማ  የወርቅ ኢዩቤልዩውን በማክበር ላይ ነው፡፡ በሜይ 1963 አፍሪካ አንድነት ሲመሰረት፤የጋናው ፕሬዜዳንት ክዋሚ ንኩርማ የመዝጊያ ንግግሩን የደመደመበት በተለይ በእድገት ላይ ያለችውንና ተቀኚ የነበሩትን የአፍሪካ ሃገራት ወደ ነጻነት ለመራችው ኢትዮጵያ ለክብሯ በመረጠውና ባዘጋጀው ግጥሙ ነበር፡፡ ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን አስመልክቶ ንኩሩማ  ሲናገር: ‹‹ግርማዊ ሆይ! በጓደኞቼና በራሴ ስም የሚቀረኝ ለኢትዮጵያና ለሕዝቦቿ በተለይም ለግረማዊነትዎ ያለኝን አክብሮት በመግለጽ በዚህች ታሪካዊ ሃገር ባደረግነው ቆይታ የተቸረንን አቀባበልና መስተንግዶ ሳላመሰግን ማለፍ አይቻለኝም፡፡ ንኩሩማህ ዘወትር ባነበብኩት ጊዜ ትውስታ የሚያጭርብኝን ይህን የግጥሙን ስንኝ አሰማ፡፡  የራሱ የንኩሩማህ ቃላት እነዚህ ናቸው፡፡
ኢትዮጵያ ትነሳለች!
ኢትዮጵያ የአፍሪካ ብሩህ አንቁ
ከለምለሞቹ ተራሮች መሃል
የጨለመባቸውን በነጻነት ጎዳና ስታጓጉዝ
የአባይ ወንዝ አናት
ኢትዮጵያ ትነሳለች!
ኢትዮጵያ የብልሆች ምድር
ኢትዮጵያ፤ የቀደምት አፍሪካ ሕግጋት ማሕደር
ለምለም የእውቀት ገበታ
የእኛ አፍሪካ የባህሏችን  አለኝታ
ብልኋ ኢትዮጵያ ትነሳለች፤ ገና
ደምቃ በሙሉ ክብር
አቤት የአፍሪካ ተስፋ
መዳረሻዋ  እድል
በ2011 በአፍሪካ ሕብረት ግቢውስጥ የግ ቀ.ኃ.ሥ. ሃውልት እንዲቆም ሃሳቡ ሲቀርብ፤የኢትዮጵያ ‹‹ታላቁና ባለራዕዩ መሪ›› በመቃወምና ኢትዮጵያዊነቱን በመርሳትና በመካድ  ሲናገር ምንጊዜም ስለ ፓን አፍሪካኒዝም ስናነሳ የሚታወሰን ክዋሚ ንኩሩማ ነው፡፡ ይህን ለመቀበል መቸገር አሳፋሪ ነው የሚሆነው›› በማለት የራሱን አሳፋሪ ክህደት ፈጸመ፡፡የከሰለ ልብ ባለቤት መሆን እንዴት ያሳፍራል! ሃፍረተ ቢስነት እንዴት ያሳፍራል! ቀደምት የአፍሪካ እንድነትን ምስረታና ተግባራዊነት ያረጋገጠን መሃንዲስ እውነታ መካድስ እንዴት ያለ አሳፋሪ ተግባር ነው፡፡የማይቻለውንና የማይሞከረውን የሁለት ጎራ ፍጥጫ፤ የ “ሞኖሮቪያ”ንና የ “ካዛ ብላንካን” ቡድናዊ መራራቅን አቀራርቦና አስማምቶ፤ አስታርቆና አዋህዶ የአፍሪካ አንድነትን ምስረታ እውን ስለመደረጉ ታሪክ የግርማዊ ቀ ኃ ሥን ውታ ጨርሶ የማይዘነጋው ነው፡፡ የአፍሪካ እንድነትን እውን ለማድረግ ያለመሰልቸት በትጋት ጥረዋል፡፡የአፍሪካ አንድነትን ለመመስረትም ስለ ፓን አፍሪካኖዝምም ለአፍሪካ ምሉእ ነጻነትም ታላቅ አስተዋጽኦ ያደረጉና አሁን ለደረሰበትም ደረጃ ተጠቃሽና ባለውለታነታቸው የማይዘነጋ ነው፡፡
….የወደፊቷን የአፍሪካን ራዕይ ከነጻነት አኳያ ብቻ ሳይሆን በአንድነታችንም አኳያ ነው የምናየው፡፡ይህን አዲስ ትግል በማወቅ ካለፈው ባገኘነው ውጤት መበረታታትና ጥንካሬ ተስፋ እናደርጋለን፡፡በመሃላችን ልዩነት እንዳለ እንገነዘባለን፡፡ አፍሪካውያን የተለያየ ባህል ባለሃብቶች ነን፤ልዩ ተሰጥኦና ልምዶች ያሉን ነን፡፡ ያም ሆኖ ሰዎች በበርካታ የሚያለያያቸው ሁኔታ ቢኖረንም በመግባባትና በመተሳሰብ አንድነት ማምጣትም እንደምንችል እንገነዘባለን፡፡… ታሪክ እንደሚያስተምረንና እንደሚያስታውሰን አንድነት ሃይል መሆኑን፤በመገንዘብ ግባችንን በማስቀደም፤ለጣምራ ግባችን የተባበረ ሃይላችንን ለዚሁ በማዋል ለዕውነተኛው የአፍሪካ ወንድማማችነት አንድነት ልንቆም ግድ ነው፡፡ …እንደ ነጻ ሰብአዊ ፍጡራን ጥረታችን አዲስ ግንኙነት ለመፍጠር መቆም ይገባናል፡፡በራሳችን መተማመንን፤ግባችን በማድረግ እኩልነትን ከሌሎች በእኩልነት ላይ መሰረት ካደረጉ ጋር ሁሉ አንድ ልንሆን ተገቢ ነው………
በግንባር ቀደም የአፍሪካ አንድነት አመሰራረት ላይ የምስረታውን አባቶች በምቃኝበት ወቅት፤ ለግላቸው የመዳብ ሃውልት ይቁምላቸው በሚል ሙግት ለመግጠም አይደለም፡፡እኔን አጅግ ያሳዘነኝ፤እራሳቸውን በከለላ ውስጥ እሰገብተው፤ እራሳቸውን መሆን ስለሚቸግራቸው፤ አጋጣሚውን በመጠቀም፤ታሪክን በማወላገድና መሰረቱን በማሳት፤ጭፍን ‹‹ራዕይ›› አለን የሚሉት በአፍሪካ መስራች አባቶች ስምና ተግባር ተከልለው፤(ይልቁንስ በራሳቸው ስምና ማንነት መቆም ባለመቻላቸው) የኢትዮጵያን የኖረና የዘመናት መታወቂያ ለማፈራረስ የቆመውንና የቆሙለትን ትልማቸውን ለማሳካት መጣራቸው ነው፡፡ ታሪክ ስለሥልጣንና ማንነት ቢሆን ኖሮ ቀ ኃ ሥን ማንም ቀድሞ አይገኝም፡፡ ቀ ኃ ሥ ከማንም የአፍሪካ መሪ የላቀ አስተዋጽኦ አላቸው፡፡ በዘመኑ የአፍሪካ አንድነትን ከመሰረቱት አቻ መሪዎች ‹‹የአፍሪካ አንድነት አባት›› ተብለው በ1972 ዓም በተካሄደው 9ኛው የአፍሪካ መሪዎች ስብሰባ ላይ በይፋ ተመርጠዋል፡፡ ቀደም ሲል በምስረታው ወቅት በ1963 ዓም የመጀመርያው የአፍሪካ አንድነት ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል፡፡ ዳግመኛም በ1966 ድጋሚ ሊቀመንበር ሆነው እንዲመሩ ዳግም ተመርጠው በሁለት ዘመናት በሊቀመንበርነት ተመርጠዋል ፡፡ የአፍሪካን ኮሎኒያሊዝም ቅስም ለመስበርና ከአፍሪካ ምድር ጨርሶ እንዲጠፋ ለማድረግ ግንባር ቀደሙ ናቸው፡፡ከኋላ የመጣ አይን አወጣ እንዲሉ የማንም ጭራ ነስናሽ ጥብቅና የሚሹ አይደሉም ይሄው ጭራ ነስናሽ የራሱን ሃውልት ለማቆም የነግ ድጋፍ ለማግኘት የተደረገችው ይቺ በንኩሩማህ ስም የተቸረች ሙስናዊ አካሄድ የትም አታደርስም፡፡
ታሪክ በርካታ እንቆቅልሾች አሉት፡፡ምናልባት በሃውልቱ መቆም ወቅት ንከሩማህ ወይ ሞት በማለት አጥበቀው ሲሞግቱ የነበሩ ስለፓን አፍሪካኒዝም በተነሳ ቁጥር መታወሱን ብቻ ያቀነቀኑት ንክሩማህ ስለ ኢትዮጵያ ያለውን ስር የሰደደ ፍቅርና አክብሮት ቢያውቁ ኖሮ በመቃብራቸው ውስጥ መንደፋደፋቸው አይቀርም፡፡ንክሩማህ በልቡ ውስጥ ለኢትዮጵያ የተለያ ጓዳ ነበረው፡፡ምንም እንኳን ስለ ፓን አፍሪካኒዝም ቀደምት ቢሆንም ኢትዮጵያን ደግሞ እንደ አፍሪካ አንጸባራቂ የጸረ ኮሎኒያሊዝም ብርሃን በመመሰል ከቅኝ ገዢዎች ጋር ሲያደርጉ በነበረው ትግል ወቅት የዚህች የነጻ ኢትዮጵያ ኮከብነት መሪያቸው እንደነበረ ያስታውሳሉ፡፡ከዚሁ አኳያ የኢትዮጵያን የጸረ ኮሎኒያሊዝምን ጥቃት በመታገል ነጻነቷን ጠብቃ መቆየቷ የሚያኮራ መሆኑን በማስገንዘብ፤የአፍሪካ አንድነት አሽከርካሪ መሆኗንም አረጋግጠዋል፡፡
እርግጥ ንክሩማህ ስለ ፓን አፍሪካኒዝም ንቁ ተሟጋች መሆናቸው ባይካድም፤ ለፓን አፍሪካኒዝም ግን አንድም ግጥም አላበረከተም፡፡ አፍሪካ ስለአፍሪካ ብሩህ እሳቤ ያለው ቢሆንም ለአፍሪካ ግጥም አላሰፈረም፡፡ ንክሩማህ ፓን አፍሪካኒዝምንና አፍሪካ ይወድ ነበር፤ለኢትዮጵያ ግን የበረታ ፍቅር ነበረው፡፡ለዚህም ነው በምስረታው ወቅት በመዝጊያው ላይ ባደረገው ንግግሩ ላይ ስለኢትዮጵያ ግጥም ጀባ አለ፡፡ ከዓለም መሪዎች መሃል ለኢትዮጵያ ታሪካዊነትና ግንባር ቀደምትነት፤ ስለ ሕዝቦቿ መስተንግዶ የጻፈ ብቸኛ መሪ ንክሩማ ነው፡፡
ቀ ኃ ሥ ወቅቱ ሲመጣ ሃውልታቸው እንደሚገነባ አያጠራርም ምክንያቱም ‹‹እውነት በርብራብ ስር ወድቃ አትቀርም፤ ቅጥፈትም በዙፋን ላይ ተኮፍሶ አይኖርምና››::
ወደኋላ መለስ ብለን ስናስታውስ፤ ንክሩማህ የበረታ ፓን አፍሪካኒስት ብቻ ሳይሆን የአፍሪካ ‹‹ትንቢተኛም›› ነበር፡፡ ንክሩማህ ማየት የተሳናቸው ባለራዕዮች ኢትዮጵያን ወደ ዘር ፖለቲካ አረንቋ ውስጥ ከመድፈቃቸው አስቀድሞ ኢትዮጵያ ገና እንደምትልቅ ያወቀ ነበር፡፡ንክሩማሕ የኢትዮጵያን ገኖ መዝለቅ ሃፍረት ለባሾች ‹‹የአፍሪካ ትንሳኤ …. ከማለታቸው በፊትና ከመቀላመዳቸው አስቀድሞ ያውቅ ነበር፡፡ንክሩማህ ባለጊዜ አስመሳዮች ለራሳቸው ስም ለመገንባት ጉብ ቂጥ ከማለታቸውና ‹‹ኒዮሊቤራሊዝም›› ከመዝፈናቸውና ደሟን ጨርሰው እንባዋን ከመምጠታቸው አስቀድሞ ስለማንኛውም በዝባዢና አስመሳይ ለቀስተኛ ጠንቅቆ ያውቅ ነበር፡፡
በእርግጥም የንክሩማህ ግጥም ‹‹ትንቢት›› ነበር፡፡ ‹‹ኢትዮጵያ ትነሳለች እንደ ንጋት ጸሃይ በርታ እንደ ውድቅት ጨረቃ ደምቃ ኢትዮጵያ ትነሳለች! ከምር ገና በላይዋ ላይ ያጠላውን ጥቀርሻ ዲክታተርሺፕ አስወግዳ ት ትነሳለች፡፡ኢዮጵያ ካጠመዳት ክፉ ደዌ ተላቃ እንደገና እንደ ብርቅዬ አልማዝ ታበራለች! ከዘረኝነትና ሃይማኖት ክፍያ ትላቀቃለች፡፡ ኢትዮጵያ ከወረራት የመከራ ከበባ ተላቃ፤ ልጆችዋን ካስመረራቸው ክፉ አሳቢና እኩይ ምርጊት አላቃ እጆችዋን ከተበተባት የዘርና የጎሳ ፖለቲካ፤ ከችግርና ከመከራ፤ ከእልቂትና ከደዌ ነጻ አድርጋ ልጆችዋን በአንድነት ታቅፋለች፡፡  ኣምላክም መልሶ ያቅፋታል::
ንክሩማህ እውነተኛው የኢትዮጵያ ልጅ ነው፡፡መጤዎቹ ኢትዮጵያ የ100 ዓመት ታሪክ ነው ያላት ቢሉም ንክሩማ ግና አስቀድሞ ሃሰት በማለት ኢትዮጵያማ የሰው ዘር መገኛ ማዕከል ነች ብሏቸዋል፡፡ ኢትዮጵያን በፈላጭ ቆራጭነት ሊገዙና ሕዝቦቿንም ለመራና ሰቆቃ ሲዳርጉ ንክሩማ ግን አስቀድሞ ‹‹እምቢኝ! ኢትዮጵያማ የአፍሪካ አንጸባራቂ ሉል ናት፡፡ ማንጸባረቅ ማብራት አለባት! ልቀቋት ትግነንና ታብራ ብሏል፡ ንክሩማ ‹‹ ኢተዮጵያ የብልሆች ሃገር ናት፤አባይን የጦር መንስኤ ሊያደርጉ ሲዶልቱ ንክሩማ እምቢኝ! ‹‹ኢትዮጵያ የአባይ መመንጫ ናት›› አባይ ደሞ የህይወትን ስጦታ ለአፍሪካ ያድላል ብሏቸዋል፡፡ መንፈሳችንን ለማጉደፍና ለማጣጣል ሲሸርቡና ለመከራና ለስቃይ ሲያዘጋጁን፤ ንክሩማ እምቢኝ!‹‹ኢትዮጵያማ የአፍሪካ ራዕይ ተስፋ ነች›› አላቸው፡፡ ንክሩማ የጋና ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያም ልጅ ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ በተስፋ አስቆራጭ ትቢያዎች ልንቆሽሽ መስሎ ሲሰማን በንክሩማ ትንቢታዊ አባባል ብርታት እናግኝ፡፡ ‹‹ኢትዮጵያ ገና ትትነሳለች›› ስለዚህም በግርማዊ ቀ ኃ ሥላሴና በንክሩማ  መሃል ውድድር የለም፡፡ ሁለቱም የኢትዮጵያ የተከበሩ ልጆች ናቸውና:: ንክሩማን ማክበር ማለት ቀ ኃ ሥላሴን ማክበር ነው፡፡ የሜይ 1963ቱን የንክሩማን ግጥም ሳነብ፤ ቀ ኃ ሥላሴ በኦክቶበር 1963 በተባበሩት መንግሥታት ስብሰባ ላይ ያደረጉት ንግግር ትዝ ይለኛል፡፡ በዚያ ንግግራቸው ቀ ኃ ሥላሴ ለአፍሪካን ፓን አፍሪካኒዝም ጥብቅና ከመቆማቸውም ባሻገር የአፍሪካን  ነጻነት ጠብቆና አክብሮ ለማቆየት የሚያስፈልገውን አይዲዮሎጂ በሚገባ አስገንዝበው ነበር፡፡
…አንዱን ዘር ከፍተኛ ሌላውን ዝቅተኛ አድርጎ የሚያሳየው ፍልስፍና ጨርሶ እስካልተወገደ ድረስ፤ አንደኛ ዜጋና ሁለተኛ ዜጋ የሚለው ደረጃ እስካልፈረሰ ድረስ፤ የአንድ ፍጡር ቀለም ከዓይኖቻችን ቀለም የተለየ ትርጉም እንደሌለው እስካልተረጋገጠ ድረስ፤ሁሉም ሰብአዊ መብቶች ከዘርና ከጎሳ ከቀለም ልዩነት ባሻገር ለሁሉም እኩል እስካልሆኑ ድረስ፤ በተስፋነት ብቻ የሚታሰቡ እንጂ አንዳችም እርባና አይኖራቸውም… እኛ አፍሪካዊያን አህጉራችን ከዳር እስከዳር ሰላም እስክትሆን ድረስ አስፈላጊ ከሆነ ትግላችንን አናቆምም፡፡ ደግሞም ድልን በእጃችን እንደምናደርግ ጥርጥር የለንም፡፡ መልካምነት እኩይነትን እንደሚረታው ስለምንገነዘብ ድል እንደማይርቀን እርግጠኞች ነን፡፡
ቦብ ማረሊም እነዚህን ቃላቶች ለዜማው ‹‹ዋር›› (ጦርነት) ለሚለው የአፍሪካ የትግል ዜማ የሆነውን  ሙዚቃውን አጅቦበታል፡፡(ምናለ አንድ ባለሙያስ የንክሩማን ግጥም ወደ ዜማ ቢለውጠው… ኢትዮጵያ ትትነሳለች፤ ትገናለች…  ታበራለች…. ወደ ላይ ትወጣለች::)
በምትገነዋ ኢትዮጵያ አንድን ጎሳ፤ ሃይማኖት፤ቋንቋ፤ጾታ ከሌላው አብልጦ የሚያጎላ፤ ፍልስፍና አይኖርም፡፡ በኢትዮጵያ አንደኛ ደረጃ ዜጋና ሁለ፤ተኛ ደረጃ ዜጋ አይኖርም፡፡በነገዋ ገናና ኢትዮጵያ ዘር ጎሳ፤ ሃይሞኖት፤ወረዳ፤ጾታ፤ሁሉ ከዐይኖቻችን ቀለሞች መለያየት ያለፈ ትረጉም አይኖራቸውም፡፡ በምትገነዋ ኢትዮጵያ ሁሉም እኩል የሰብአዊ መበት ባለቤት ይሆናል፡፡
ወይ ጉድየአፍሪካ አንድነት ድርጅትየአፍሪካ  ሕብረት
ወይ ጉድ! የአፍሪካ አንድነት ድርጅት/ የአፍሪካ ሕብረት ስለ አፍሪካ አንድነት/አፍሪካ ሕብረት አስተያየት ማስፈር ልብ ሰባሪ ጉዳይ ነው፡፡ በ2013 በዓለም ካሉት 47ሃገራት እድገት ከማያሳዩት ሃገራት መሃል 36ቱ በአፍሪካ ይገኛሉ፡፡ በአንድ ወቅት የታንዛኒያ መሪ የነበሩት ጁሊየስ ኔሬሬ የአፍሪካ አንድነት ድርጅትን ‹‹የመሪዎች የወሬ ማሕበር›› በማለት ጠቅሰውት ነበር፡፡ ሌሎች ደግሞ‹‹የፈላጭ ቆራጭ ጋጠወጥ ራስ ወዳድ መሪዎች ክበብ›› ይሉታል፡፡ጋናዊው ታዋቂ ኢኮኖሚስት ጆርጅ አይቴ ‹‹እባካችሁ ስለ አፍሪካ አንድነት ድርጅት ማውራት ይብቃን፡፡ በአህጉራችን ካሉት ድርጅቶች ሁሉ አዘቅዝቆ የሚሄድና እርባና ቢስ የሆነ ድርጅት ነው፡፡‹‹ዴሞክራሲን›› እንኳን በሚገባ ሊተረጉም ያልቻለ ድርጅት ነው፡፡ የራሱ የሆነ ወጥነት ያለው ተግባር ጨርሶ የሌለው ነው›› ይለዋል፡፡
የአፍሪካ ሕበረት ዋና መስሪያ ቤት በቻይና መንግሥት ምጽዋት በ200 ሚሊዮን ዶላር ተሰራ በተባለና የቻይና ስጦታ “ለታዳጊዋ” አፍሪካ በተበረከተ ጊዜ ቅሬታዬን አስቀምጬ ነበር፡፡ የቻይና የግንባታ ኩባንያ ስራውን በአጠቃላይ ከቻይና በተገኘ ቁሳቁስና ቻይናዊያን ዜጎች ሰራተኞች ገነባው ሲባልና አስፈላጊውን ቁሳቁስ ሁሉ ያሟላውም ያው ቻይና ኩባንያ ነው ሲባልና ወንበርና ጠረጴዛም ሳይቀር ከቻይና ተጓጓዘ መባሉም ክፉኛ አሳዝኖኝእንደነበር ገልጫለሁ፡፡ በስጦታው ርክክብ ወቅትም የአፍሪካ ‹‹ሃፍረተ ቢስ መሪዎች›› ተርታ ገብተው እንደ ውሃ ወረፍተኛ ለቻይና የምስጋና ውርጅብኝ ሲያጎርፉ  ‹‹የአፍሪካ ትንሳኤ… የአፍሪካ ሬኔሳንስ ተጀመረ ለማስቀጠልም መንገዱን አግኝተናል በማለት አሸሸ ገዳሜ ሲሉ ነበር፡፡››
አፍሪካ አልተነሳችም አልኩ፡፡ አፍሪካ ለልመና ተዳርጋለች፡፡‹‹የቻይና ትንሳኤ በአፍሪካ ተጀምሯል›› በአዲስ አበባ የተገተረው አዲሱ የአፍሪካ ሕብረት ግንብ የአፍሪካ የሃፈረት ግንብ  እንጂ የአፍሪካ ኩራት ግንብ አይደለም፡፡ የአፍሪካ መሪዎች በአንድነት ለአፍሪካ ሚሆን ቋሚ ቢሮ ለመገንባት አቅሙን ካጡ፤ ለአፍሪካ ትንሳኤ የሚሆነውን መስራት ከተሳናቸው ያሁኑን ግንብ ‹‹የአፍሪካ ምጽዋተኞች አንድነት አዳራሽ›› ከማለት አላልፍም:: የአፍሪካ አንድነት ድርጅት/ የአፍሪካ ሕብረት እና ሰብአዊ መብት የአፍሪካ አንድነት ድርጅት/የአፍሪካ ሕብረት በአፍሪካ የፖለቲካ፤ የኤኮኖሚ እና የሶሻል ግንኚነቶችንና ነጻነትን ከማጠናከርና ተግባራዊ በማድረግ ወደ ልማት አቅጣጫውን ከማራመዱ አስቀድሞ ማከናወን ያለበት ሰብአዊ መብትን ነው፡፡ የአፍሪካን  ልማት  ለማከናወንም ሆነ አቅዶ ወደ ግብ ለማድረስ የሰብአዊ መብት መከበር ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ተግባር ነው፡፡ ሕዝቦች በነጋ በጠባ ለመከራና ስቃይ እየተዳረጉና የግፍ ኑሮ፤ የባርነት ቀንበር ተሸክመውጀርባቸው በተደራራቢ ችግር ጎብጦ ልማትን አመጣለሁ ብሎ ሩጫ ለመውደቅና ለከፋ መከራ ለመዳረግ መጣር ብቻ ነው፡፡
የአፍሪካ አንድነት ጸረ ኮሎኒያሊዝም፤ኒዮ ኮሎኒያሊዝም ጸረ ጸረ ጸረ ብሎ የሚደረድራቸው ማለቂያ የሌላቸው ጸረዎች በችግርና በመከራ ላሉ ሕዝቦች አንዳችም ጠቀሜታ የሌላቸው ልፈፋዎች ብቻ ናቸው፡፡ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት/ የአፍሪካ ሕብረት ጤት አልባ ከዚያም አልፎ ዋጋ ቢስ መሆኑን ለሰብአዊ መብት ካለው አመለካከትና ከከወነው ተግባር ነው፡፡ በበርካታ የአፍሪካ ሃገራት ክፍሎች ጦርነት የየቀናት ክስተት ነው፡፡ሰዎች በየቦታው ሲተላለቁ የአፍሪካ አንድነት እጁን አጣጥፎ ከመመልከት ውጪ አንዳችም እርምጃ አልወሰደም፡፡ የአፍሪካ ጉልበተኛና ፈላጭ ቆራጭ ገዢዎች ከውጪ ወራሪ በከፋ መልኩ ሕዝቦችን ሲጨፈጭፉ ለስደት ሲዳርጉ በግፍ ከመኖሪያቸው ሲያፈናቅሉ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት አይኑን ጨፍኖ፤ ጆሮውን ደፍኖ፤አፉን ለጉሞ የድርጊቱ ተባባሪ መሆንን የመረጠ ነው፡፡ ለሕዝቦች እልቂት ደንታ የሌ፤ልው ድርጅት/ ሕብረት፡፡ የሩዋንዳ እልቂት በሚሊን የሚቆጠሩትን ንጹሃን ዜጎች በሞት ሲቀጥፍ የአፍሪካ አንድነት ቢሮውን ዘግቶ አርቲ ቡርቲ ከማራገብ ውጪ ምንም ያደረገው አልነበረም፡፡ ሌላው ቀርቶ የአፍሪካ አንድነት ግድያውን ‹‹ጄኖሳይድ›› ለማለት እንኳን ድፍረቱና ወኔው አልነበረውም፡፡!
የአፍሪካ አንድነት ድርጅት/ የአፍሪካ ሕብረት ሶማልያ ለሁለት አሰርት ዓመታት በመበታተን ላይ ሳለች፤ የጎሳ መሪዎች ተቀራምተዋት ለጥፋት ሲዳርጓት እንኳን መድረስ ቀርቶ ከሩቅ ሆኖም ማስጠንቀቂያም ሆነ ማስፈራሪያ አልሰነዘረም፡፡ ለተፈጠረው ችግር ሌሎች ሃገራት ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ በሚያመቻቸው መንገድ ጣልቃ ገብተው ሲያማትሩ የአፍሪካ አንድነት በቂ ጦር እንኳን ለመላክና ሕዝቡን ከመከራ ለመታደግ አልሞከረም፡፡ በኮት ዲቭዋር የተፈጠረውን ችግር የፈረንሳይ ወታደሮች ገብተው ሲፈነጩበት የአፍሪካ እንደነት በስፋራው ቀርቶ በአካባቢውም አልደረሰም፡፡ በማሊም የተፈጠረውን ሽብር ለማስታገስና ስርአት ላመስያዝ የፈረንሳይ 5000 ወታደሮች ሲዘልቁ የአፍሪካ አንድነት ከጠቅላይ ቢሮው ንቅንቅም አላለም፡፡ በኢትዮጵያም የምርጫ  በጠራራ ጸሃይ ሲሰረቅና ተሸናፊው አሸናፊ ሆኖ ሲወጣ በዝምባብዌ፤በኬንያ፤ በዩጋንዳ ተመሳሳይ የምርጫ ውጤት ዘረፋ ሲካሄድ የአፍሪካ አንድነት በገለልተኛነት ከዳር ቆሞ ከተመልካችነት አላለፈም፡፡
የአፍሪካ ሕብረት የሰብአዊ መብትን ጥሰት በተመለከተ፤ ወንጀለኞችን መደገፍን  ሙያ ብሎ ይዞታል፡፡ የሱዳኑ ኦማር አል በሺር በሰብአዊ መብት ጥሰትና በጦር ወንጀለኛነት በግፍ ጭፍጨፋ በዓለም አቀፍ ወንጀለኞች ፍርድ ቤት ተከሰው መያዣ ሰነድ ሲተላለፍባቸው ‹‹የአፍሪካ ሕብረት አባል ሃገራት በሮም የተፈረመውን የፍርድ ቤቱን ስምምነት አናከብርም በማለት የሱዳኑን አልበሺርን አሳልፈን አንሰጥም አቋም ያዙ›› ይህ ደግሞ ነግ በኔ በሚል ስጋትና አስቀድሞ መንገድ ለመዝጋት ሲሉ ተመሳሳይ ወንጀለኛ መሪዎች የወሰዱት አቋም ነበር፡፡ በዚህም የአፍሪካ ሕብረት ተግባሩን መወጣት ባለመቻሉና ፍላጎትም በማጣቱ አይ ሲ ሲ ዓለም አቀፍ የወንጀል ፍርድ ቤት ጣልቃ መግባቱ አስፈላጊ ሆነ፡፡ ከ2011 አንስቶ በሰባት የአፍሪካ ሃገራት ውስጥ ይሄው ፍርድ ቤት የማጣርያ ምርመራውን በማካሄድ ላይ ነው፡፡
የአፍሪካ ሕብረት የሌለው ቢሮ ያላቋቋመው የመብት ማስከበርያ ጽ/ቤት የለም ግን አንዳቸውም ለተግባር አልበቁም፡፡ የአፍረካ ሕብረት የሰብአዊ መብት ቢሮ፤ የአፍሪካ ሕብረት የልጆች መብት፤ የሴቶች መብት፤ በማለት በርካታ ኣዋጅ አውጥቷል ቢሮም አቋቁሟል፡፡ የአፍሪካ ሕብረት የፖለቲካ ቢሮም አለው፡፡ የዚህም ቢሮ ተግባሩ ሰብአዊ መብትን ማስከበር፤ የዴሞክራሲ ስርአትን ትግበራ ማረጋገጥ፤ምርጫዎችን በአግባቡ ተካሂደው የህዝብ ፍላጎት ማሟላት ቢሆኑም አንዱንም አላከናወነም፡፡ በአባል ሃገራት ምርጫ ወቅት ዳጎስ ያለ ወጪ በመመደብ ታዛቢዎች ቢሊክም ታዛቢዎቹ ሆቴላቸውን ሳይለቁና ምርጫ ጣቢያዎችም ቢሆን እንደነገሩ ደረስ መለስ ከማለት አልፎ አንዳችም ውጤት ያለው ትዝብት አላከናወኑም፡፡ በየሄዱበት ሃገር ያለው ገዢ ፓርቲ የሚሰጠውን መግለጫ ደግፈው ተጋብዘውና ተሸልመው ከመመለስ ውጪ ምንም አላደረጉም:: በ2010 ነፍሳቸውን በተገቢው ቦታ ያኑረውና መለስ ዜናዊ 99.6 በመቶ ምርጫ አሸነፍኩ ሲል፤በቀድሞው የቦትስዋና ፐሬዜዳንት ማሲሬ ለታዛቢነት የተሰማራው ቡድን ምርጫው ፍትሃዊና ሰላማዊ ነበር፤ የምንግስት መዋቅርን መጠቀምና ሕገ ወጥ የሆነ ሂደትም መራጩንም ማስፈራራትና መስገደድም ያልነበረበት ምርጫ ነበር በማለት ማሲሬ ቀልማዳ ትዝብቱን ተፈራረመ፡፡ ሲደመድምም ምርጫው የአፍሪካን አንድነት የምርጫ ደንብና ስርአት ያሟላ፤ የመራጩን ሕዝብ ፍላጎት ያካተተ፤… የአፍሪካ ሕብረት ተቃዋሚዎች ከምርጫው አስቀድሞ ያሰሙትን ቅሬታ የሚያረጋገጥ አንዳችም ሁኔታ አልታየም፡፡ ክሱን ወይም ውንጀላውን የሚረጋግጥ አንዳችም ሁኔታ አላየንም በማለት ነበር፡፡
አፍሪካ ከመቼውም በከፋ መልኩ አሁን ተበታትናለች፡፡ፓን አፍሪካኒዝም አፈር ዲቤ በልቷል፤ እድሜ ለአፍሪካሕብረት፡፡አሁን በአፍሪካ ላይ በማንዣበብ ላይ ያለው አዲስ አየዲዮሎጂ ነው፡፡ የአፍሪካ ጨቋኝ ገዢዎች በድፍረትናበማን አለብኝነት የዘር ብሔርተኝነትን በስልጣን ለመቆየት አመቺ ስለሆናቸው በመንዛት ላይ ናቸው፡፡ የዘርማንነት፤ የዘር ጥራት፤የዘር መኖርያ፤ በሚል ሰበብ ሕዝብን መጨፍጨፍና ከራሳቸው ከገዢዎች ውጪ ያለውን ዘር በሚልያስቀመጡትን ሁሉ ለማጥፋትና ብቸኛ ዘር ሆነው ለመኖር እየገሰገሱ ነው፡፡
በኢትዮጵያም ‹‹የብሔር ፌዴራሊዝም›› በሚል ቆንጆ መጠቅለያ የተጀቦነ ፖለቲካዊ ሂደት እየተንደረደረነው፡፡ኢትዮጵያዊያን በማንነታቸው በትውልዳቸው በቀያቸው መገለልና መገፋት መፈናቀል እየደረሰባቸው ነው፡፡በክልልተደልድለው ያለፍላጎታቸው ስም ወጥቶላቸው ለጥቃት ተዘጋጅተዋል፡፡ ጥቂት የገዢው መደብ አባላት በድሎት እንዲኖሩናያለሃሳብ እንዲንደላቀቁ 80 ሚሊዮን ሕዝብ ለግፍ ተዳርጓል፡፡እንዳይናገር በሆዳም ካድሬዎችና ለጊዜው ገዢዎችእራሳቸውን በሸጡ አጎብዳጆች ተወጥሮ መከራ እየወረደበት ነው፡፡ ሆዳሙ ያዜማል ሆዳሙ ይገጥማል፤ ሆዳሙ ይጨፍራል፤ሆዳሙ ቅኔ ያፈሳል ሆዳሙ ያጨበጭባል ሆዳሙ ይደሰኩራል፤ ሆዳሙ ሆዱን ይሞላል ሕዝቡ ግን ለመከራና ስቃይተዳርጓል፡፡
ታላቁ የአፍሪካ ደራሲ ቺኒዋ አቼቤ  (Things Fall Apart) ለምንድን ነው በአፍሪካ ሁሉም ነገርየሚፈራርሰው በሚል መነሾ ጻፈ፡፡የኔ መለስ አጭር ነው፡፡ባለፈው የግናሽ ምእተ አመት ነጻነት የአፍሪካን ግፈኛገዢዎች ተጠያቂ የሚያደርግ ድርጅት ለመፍጠር ባለመቻሉ ነው እላለሁ፡፡ላለፉት 50 ዓመታት የአፍሪካ መሪዎችተጠያቂነትን አሻፈረን ብለዋል፡፡ የዚህ ተጠያቂ ሕዘቡ እንደሆነ ለማሳመን ጠረታቸው መጠን የለውም፡፡አፍሪካ ከቅኝገዢዎች በተተወለት ሁኔታ ውስጥ ነው ያለው፡፡ሰበብ እየተደረገ ዘወትር በማያልቅ ጥሪ የሚጠቆመው፤ ነጮች፤ የቅኝገዢዎች ቅሪት፤ ካፒታሊዝም፤ ኢምፕሪያሊዝም፤ ኒዮ ሊቤራሊዝም፤ ግሎባላይዜሽን ነው መሸሻው፡፡ ….. የዓለምየገንዘብ ተቋም ነው፤የዓለም ባንክ ነው፤……የአህጉሩ ያለማደግና ያለመልማት ሰበቡ  የመኑስናው፤ የመልካምአስተዳደር እጦት ሁሉም በመጥፎና እርኩስ መንፈስ የመጡ እንጂ የአህጉሩ አይደሉም ማለት ይዳዳቸዋል፡፡ነገሮች ሁሉ በአፍሪካ ፍርስርሳቸው የሚወጣበት ሰበብ የአፍሪካ ‹‹መሪዎች›› የሕዝቦቻቸውን ሰብአዊ መብትባለማክበራቸው ነው፡፡የአቼቤን አባባል ለማጠናከር፤ አፍሪካ አሁን ያለችበት ሁኔታ ውስጥ ያለችበት መንስኤየአፍሪካ መሪዎች እንደመሪ ሊሆኑና ሊያደርጉ የሚገባቸውን የመሪነት ሚና መጫወት ባለመቻላቸው ነው፡፡ ‹‹ጥቂትየአፍሪካ መሪዎች የሕዝቦቻቸውን ክብርና ሰብአዊ መብት በአግባቡ ያከብራሉ፡፡ አፍሪካ መሪዎች ናቸው በሚባሉትገዢዎቿ እያደናቀፉ እየጣሏት እንዴትስ መነሳትና መግነን ትችላለች? ለመነሳት በሞከረች ቁጥር ያንን የመርገምትቦት ጫማቸውን ማጅራቷ ላይ አሳርፈው እንዳትነሳ፤ እንዳታድግ፤ እንዳትለማ ረግጠው ይዘዋት እንዴት ብላ ነውየምታድጋው? ያም ሆኖ ጊዜው ሲደርስ አፍሪካ ፍርስርሳቸው የወጡባት አፍሪካ ተሰባስበው አንድ የገነነች አፍሪካሆና ትነሳለች!ስለዚህም ለአፍሪካ አንድነት/ አፍሪካ ሕብረት 50ኛው ዓመት የወርቅ ኢዩቤልዩ ለግ ቀ ኃ ሥላሴና ለክዋሚህንክሩማህ የማበረክተው ስንኝ
ኢትዮጵያ ከፍ በይ! የኢትዮጵያ ትንሳኤ! የአፍሪካ ትንሳኤ
ኢትዮጵያ የአፍሪካ አንጸባራቂ ማዕድ ትነሳለች ትገናለች
ከፈላጭ ቆራጭ ስርአት ተላቃ
የግድበ አፍሪካ ምድር እንደሚበራው የበጋ የንጋት ፍንጣቂ
በአፍሪካ ምሽት ሰማይ እንደምትበራው የጨረቃ
ብርሃን አንቂ ኢትዮጵያ ትንሳኤዋ ያበራል ትገናለች::
ኢትዮጵያ ከራስ ደጀን ጉብታ ጫፍ ትንሳኤዋ ይታያል
እስከ ኪሊማንጃሮ ዘልቆ ይጠራል
ከፖለቲካው አረንቋ መታወቂያነት
እስከ ሀገራዊ ኩራት በልዩነት
ኢትዮጵያ አስከብራ የሁሉንም ማንነት ትነሳለች::
በአፍሪካ ምድር የነጻነት ብርሃኗን ትረጫለች
የሊቃውንት ሃገር ኢትዮጵያ ከመንደርተኛ አዋቂዎች በላይ ተንብያ
ህዝቦቿ ተሰባስበው ተዋህደው ተፋቅረውና ተግባብተው
ሰብአዊነትን ወግነው አንድነትን መቻቻልን አንግበው
ኢትዮጵያ ትነሳለች ትገናለች::
ኢትዮጵያ የነግህ የአፍሪካ ተስፋ
በትንሳኤዋ የረገጧትን የጨፈለቋትን  አልፋ
ቅጥፈታቸውን ጭካኔያቸውን ሙስናቸውን
ያን ያለፈ ዘመናቸውን ከነምኞታቸው ገንዛ በብረት ሳጥን
የሕግ የበላይነትን አስከብራ፤ኢትዮጵያ እንደ ጸሃይ ታበራለች::
በምድሯም ሰላም እስከ ዘልዓለሙ እንዲሰፍን ታደርጋለች
የኢትዮጵያ ትንሳኤ በማይደፈሩት ሃቀኛ ወጣቶቿ
ከፍ ትላለች ተደግፋና ተሞሽራ በልጆቿ
ኢትዮጵያ እስከማዕዜኑ ትገናለች
ለወጣቱ ትውልድም  የዘልአለም ቤቱ ትሆናለች::
*የተቶረገመው ጽሁፍ (translated from):

ጋዜጠኛ ተመስገን ደስአለኝ ለሃምሌ ሁለት ተቀጠረ : የፍርድ ቤት ውሎ

394711_184013551696255_1365830121_n
ፍርድ ቤቱ የተከሳሽን  ቃል ሲሰማ እና ጠበቆች ስለምስክሮቹ መግለጫ ሲሰጡ ሰዓቱ ስላለቀ ሃምሌ 2 የምስክሮቹን የምስክርነት ቃል ለመስማት ቀጠሮ ተሰጥቷል፡፡ የተመስገን ጠበቃ ምስክሮቹ በምን ጉዳይ ላይ ምስክርነታቸውን እንደሚሰጡ ከተናገረ በኋላ አቃቢ ህግ የሁለቱ መስካሪዎች እንዳይመሰክሩ በምክንያት አስደግፈው ተቃውመው ነበር::  በዚህም መሰረት አንደኛው ምስክር ዶ/ር ያሬድ ከህገ መንግስቱ እና ኢትዮጵያ ከፈረመቻቸው ሃሳብን የመግለፅ መብቶች ከሚደነግጉ ህጎች አንፃር ተመስገን የተከሰሰባቸው ፅሁፎች ከህግ ውጪ እንዳልሆኑ ያስረዳሉ ::  ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም ደሞ ኢሰመጉ ይሰሩባቸው በነበሩበት ወቅት በኢሰመጉ ሪፖርት የቀረቡ በኢትዮጵያ መንግስት ስለተጣሱ ሰብአዊ መብቶች ያቀርባሉ:: አቶ እንዳልካቸው ሃ/ሚካኤል ክስ የቀረበባቸውን ፅሁፎች ከጋዜጠኝነት ስነምግባር እና አሰራር ከሙያ አንፃር እንዴት መታየት እንዳለበት ያቀርባሉ:: አቃቤ ህጎች የሁለቱ ምስክርነት ቃል እንዳይሰማ ብለው ተቃሟቸውን አቅርበው ነበር በ1ኛ እና 2ኛ ምስክሮች ላይ::
ጠበቆቹ ስለምስክሮቹ መግለጫ ካቀረቡ በኋላ አቃቤ ህጎቹ በ1ኛ እና 2ኛ ምስክር ላይ ተቃሞ እንዳላቸው ተቃሟቸውን አቀረቡ:: 1ኛ ምስክር ዶ/ር ያሬድ የህግ ባለሙያ ቢሆኑም ህገመንግስቱን የመተርጎም ስልጣን የላቸውም :  ህገመንግስቱን የመተርጎም ስልጣን ያለው የፌዴሬሽን ም/ቤት ብቻ ነው ስለዚ የሳቸው ምስክርነት አያስፈልግም:: 2ኛ ምስክር ፕ/ር መስፍን ኢሰመጉ ሊቀመንበር ሆነው የሰሩ ቢሆንም ከ97 በኋላ ባላቸው የፖለቲካ እንቅስቃሴ እና አቋም ገለልተኛ ሆነው መመስከራቸው ያጠራጥረናል ስለዚህ የሁለቱን ምስክር ሆኖ መቅረብ ፍ/ቤቱ ውድቅ እንዲያደርግ ጠይቀዋል::
የተከሳሽ ጠበቆችም ምላሽ ሲሰጡ : 1ኛ ምስክር ዶ/ር ያሬድ ህገመንግስቱን እንዲተረጉሙ ሳይሆን ደንበኛቸው የተከከሰሰባቸው ፅሁፎች ከህገመንግስቱ እና ኢትዬጵያ ከፈረመቻቸው ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ከሚደነግጉ አለም አቀፍ ህጎች አንፃር እንዴት ትክክል እንደሆኑ ለማስረዳት መሆኑን 2ኛ ምስክር ፕ/ር መስፍን ደግሞ የሚያቀርቡት ኢሰመጉ ሲሰሩ በነበሩባቸው ጊዜያቶች ያዩትን የሰሙትንና ድርጅቱም በሪፖርቱ ያካተታቸውን ጉዳዮች እንጂ ሌላ ነገር አለመሆኑም..የገለልተኝነታቸው ጉዳይ በተመለከተ ደግሞ በህጉ ምስክሮች ገለልተኛ መሆን አለባቸው የሚል እንዳልተጠቀሰ ..አቀረቡ:: ዳኛውም ግራ ቀኙን ካዳመጡ በኋላ የሚከተለውን ውሳኔ አስተላለፉ:: በአቃቤ ህግ ተቃሞ የቀረበባቸው ምስክሮች 1ኛ ምስክር ዶ/ር ያሬድ ህገመንግስቱን መተርጎም እንደማይችል ነገር ግን ከዛ ውጪ ባለው እውቀት ክስ የቀረበባቸውን ፅሁፎች ከህገመነግስቱ እና ሌሎች ህጎች አንፃር እንደማያስከስሱ ብቻ ማቅረብ እንዳለባቸው 2ኛ ፕ/ር መስፍንም ኢሰመጉ ሲሰሩ በነበሩበት ወቅት የሚያቁትን ብቻ እንዲያቀርቡ፡፡ ገለልተኛ ለተባለው…መስካሪዎች ገለልተኛ እንዲሆኑ የሚል ደንብ ስለሌለ ማንኛውም ሰው ያለምንም ልዩነት የምስክርነት ቃል መስጠት ይችላል::
በፍትሕ ጋዜጣ ላይ፣ የተዘገቡ ”የካቲት 23 2004 ዓ.ም በተሰራጨው የፍትህ ጋዜጣ ቅጽ 05 ቁጥር 177 እትም የፈራ ይመለስ በሚል” : ”በቅጽ 5 ቁጥር 179 መጋቢት 7 2004 ዓ.ም ዕትም መጅሊሱና ሲኖዶሱ የአብዮታዊ ዲሞክራሲ ማጥመቂያ” እና “ ሐምሌ 22 ቀን 2003 ዓ.ም የሁለተኛ ዜግነት ህይወት በኢትዮጵያ እስከመቼ?”  በሚሉ ርእሶች በወጡ መጣጥፎችን ተከትሎ ”የሕዝብን ሐሳብ ማናወጥ፣ሕዝቡን በሕገ-መንግስቱ ላይ ማነሳሳትና የመንግስትን ስም በማጥፋት” በሚሉ ሶስት ክሶች ነው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የተከሰሰው::

የአሜሪካ የህግ ባለሙያዎችና አኢጋን በኅብረት ስራ ጀመሩ!


ዓርብ የፖለቲካና የሙስሊም እስረኛ ጠበቆችን ያነጋግራሉ
aba nsmne


በኢትዮጵያ በግፍ የታሰሩ የፖለቲካና የህሊና እስረኞችን በተመለከተ የአሜሪካን የህግ ባለሙያዎች ማህበር (ABA – American Bar Association) ሙሉ በሙሉ ድጋፍ ለማድረግ የሚያስችለውን ስራ አርብ እንደሚጀምር ተገለጸ። አዲስ አበባ ካሉ የፖለቲካና የሙስሊም ወገን እስረኞች ጠበቆች ጋር የመጀመሪያ ስብሰባ አርብ ግንቦት 23፤2005ዓም ያደርጋሉ። አቶ ኦባንግ ሜቶ የተረሱ እስረኞች ጉዳይም እንደሚካተት ጠቅሰው በፖለቲካ ጉዳዮች ዙሪያ ለታሰሩ ዜጎች ጥብቅና የቆሙ ካሉ የአዲሲቷን ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ /አኢጋን/ በቀጥታ እንዲገናኙ ጥሪ አቅርበዋል።
(ABA) በሚል ስያሜ የሚታወቀውና ከተቋቋመ 135ዓመታትን ያስቆጠረው የአሜሪካ የሕግ ባለሙያዎች ማኅበር ከ400 ሺህ በላይ የህግ ባለሙያ አባላት አሉት። ይህ በአሜሪካ ትልቅ የተባለ ማህበር በግፍ ለሚሰቃዩ ኢትዮጵያዊያን እስረኞች ድጋፍ ለማድረግ የወሰነው የአኢጋን ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ በይፋ የድጋፍ ጥያቄ ባቀረቡ በቀናት ውስጥ ሲሆን፣ በጋራ በተከናወኑ ንግግሮችና የሰነድ ውይይቶች በወር ጊዜ ውስጥ ወደ እንቅስቃሴ ለመግባት እንደተቻለ ለማወቅ ተችሏል።
ከወር በፊት በተካሄደ የማህበሩ ዓመታዊ ጉባኤ ላይ ንግግር እንዲያደርጉላቸው በተጋበዙት መሰረት አቶ ኦባንግ ህግን abaእየተንተራሰ ዜጎችን በቁም እስርና በወህኒ ቤት እያሰቃየ ስላለው የኢህአዴግ አገዛዝ በስፋት ባስረዱበት ወቅት ማህበሩ እሳቸው ከሚመሩት ድርጅት ጋር በትብብር ለመስራት ፈቃዱን አሳይቶ እንደ ነበር አቶ ኦባንግ ለጎልጉል ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ ያለውን የሰብዓዊ መብት ረገጣ፣ ኢህአዴግ ህግን ከለላ በማድረግ በዜጎች ላይ የሚፈጽመውን ግፍና ወንጀል፣ ለአፈና ተግባሩ ማስፈጸሚያም የጸረ ሽብርተኝነትን፣ የመያዶችን፣ ወዘተ ህጎችን በማውጣት ዜጎችን ለወህኒ ቤትና ለቁም እስር፣ ለስደት፣ ለስቃይ መዳረጉን፣ የፍትህ አካላቱን ህግን በሚያከብሩና ፍትህ በሚያስፈጽሙ ገለልተኛ አካሎች ሳይሆን ራሱ በመሠረተው ተቋም እያመረተ የሚጠቀምባቸው የፖለቲካው መሳሪያዎቹ ስለመሆናቸው፣ በመዘርዘርና ማስረጃ በማጣቀስ አቶ ኦባንግ ለጉባኤው መናገራቸውን አመልክተዋል።
ቀደም ሲል ጀምሮ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ የስራ አስፈጻሚዎች የሚታወቁትም ሆነ ሚዲያው የዘነጋቸው ዜጎች ጉዳያቸው ዓለም ዓቀፍ ትኩረት እንዲያገኝ በያቅጣጫው እየተደረገ ካለው የተለያየ  ጥረት በተጨማሪ ሲመክርበት የነበረው ጉዳይ እንደሆነ በመግለጽ አስተያየታቸውን የሰጡት አቶ ኦባንግ “ተጽዕኖ ሊፈጥሩ የሚችሉት አካላት በራሳቸው ሰዎች በቂ መረጃ እንዲያገኙ ማድረግ ታላቅ ተግባር ነው። ድርጅታችን እንደ ስኬት ይቆጥረዋል። ዓርብ በዝርዝራችን ካገኘናቸው የታዋቂ ጋዜጠኞችና የፖለቲካ መሪ ጠበቆች ጋር የስካይፕ ስብሰባ ይካሄዳል። በቀጣይ አገር ቤት በመሄድ ባመቻቸው መንገድ ስራቸውን ያከናውናሉ” ብለዋል።
በአሁኑ ጊዜ በእስር ላይ የሚገኙ ጋዜጠኞች፣ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች፣ የሙስሊሙን ህብረተሰብ ጥያቄ በማንሳታቸው የታሰሩት ወገኖች፣ ወዘተ ጠበቆች ጋር በስካይፕ ንግግር እንደሚደረግ አቶ ኦባንግ አስታውቀዋል። እስከዛሬ ጆሮ ያልተሰጣቸው ወገኖች ጉዳይ አደባባይ ከማውጣት በተጨማሪ የጋራ ንቅናቄው ባቋቋማቸው ግብረኃይሎች አማካይነት ወደ ህግ የሚሄዱ፣ ሌሎች አብረው መስራት የሚፈልጉ አካላት የሚያቀርቧቸውን አገራዊ ፋይዳ ያላቸውን ጉዳዮች በአገር አቀፍም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ ክስ መስርቶ ለመሟገት ማህበሩ ዝግጁ መሆኑንን ያመለከቱት አቶ ኦባንግ “አስፈላጊውን የህግ ድጋፍ የሚፈልጉ ድርጅቶችም ሆኑ ግለሰቦች ጥያቄያቸውን ለጋራ ንቅናቄው ማቅረብ ይችላሉ” ሲሉ ጥሪ አስተላልፈዋል።
ማህበሩ መንግስትን የሚያማክሩ፣ የሚመክሩ፣ ፖሊሲ በማርቀቅ ስራ ላይ የተሰማሩ ታዋቂ የህግ ባለሙያዎች፣ ለዓለም ዓቀፍ ሚዲያና ኔትወርኮች ቅርበት ያላቸውና ተሰሚነታቸው የጎላ በመሆኑ እንዲህ ካሉ አካላት ጋር በጨዋነት መስራት በወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ያለውን በደል ለማስተጋባት መልካም አጋጣሚ ማመቻቸት እንደሆነም አቶ ኦባንግ አመልክተዋል።
“… ኢህአዴግ በስደተኛነት ስም ደጋፊዎቹን በስርዓቱ የተገፉ በማስመሰል የሃሰት ማስረጃ እያስጨበጠ በአሜሪካ፣ በካናዳና በተለያዩ የምዕራብ አገራት ያሰማራቸውና በተቀነባበረላቸው መረጃ የስደት መኖሪያ ፈቃድ ካገኙ በኋላ ስደተኛውን እንዲሰልሉና ለሥርዓቱ እንዲሰሩ እያደረገ መሆኑ፤ በተለያዩ አገራት በገቢር የተያዙ መረጃዎችና ዋቢ ክስተቶች መኖራቸውን የተረዳው የባለሙያዎቹ ማኅበር ጉዳዩን በጥልቀት እንደሚያየውና ያለውን ከፍተኛ የሰው ኃይል በመጠቀም ከአኢጋን ጋር እንደሚሰራ ከሌሎች ማኀበራት ጋር በመሆንም በተለይ በምዕራቡ ዓለም የተሰገሰጉትን አስመሳይ ስደተኞች ወደ ፍትህ የማምጣቱ ጉዳይ ቅድሚያ የሚሰጠው መሆኑን ለድርጅታቸው አረጋግጠዋል” በማለት ከዚህ ቀደም ለጎልጉል ስለተናገሩት አስተያየት እንዲሰጡ አቶ ኦባንግ ጥያቄ ቀርቦላቸው ነበር።
“ኢህአዴግን የሚደግፉ ዜጎችም ቢሆኑ ለጋራ ንቅናቄያችን ልጆቹ ናቸው” በማለት አስተያየታቸውን የጀመሩት አቶ ኦባንግ “ለመጀመሪያ ጊዜ በዚህ ጉዳይ ላይ ምስጢረኛ ለመሆን እገደዳለሁ። አንድ ነገር ለማስታወስ ያህል ግን ምዕራባውያን አሠራራቸው መጭበርበሩን ካረጋገጡ ምህረት የላቸውም። ከሰብአዊነትም አንጻር ቢሆን አገሩ መኖር ያልቻለን ዜጋ ስደት አገር ድረስ እየተከታተሉ ማሳደድ በየትኛውም መስፈርት ተቀባይነት የለውም። በህግም አይፈቀድም። እንደዚህ ካሉት ጋር የሚተባበሩ አገሮችን ህግ ፊት በማቆም በህግ ስለፍትህ እንከራከራል” የሚል መልስ ሰጥተዋል።
ABA የሚባለው የህግ ባለሙያዎች ማህበር ዓመታዊ ጉባኤ ላይ ከሁለት ሳምንት በፊት ሲያከብር ንግግር እንዲያደርጉ የተጋበዙት አቶ ኦባንግ ሜቶ በርካታ ጉዳዮችን በማንሳት ድጋፍ ጠይቀው አዎንታዊ ምላሽ እንዳገኙ፣ ጠቅሰን መዘገባችን ይታወሳል። አቶ ኦባንግ እንደሚሉት አርብ የሚደረገው ንግግር የድጋፉና አብሮ የመስራቱ ሂደት መጀመሪያ ነው። ሥራው ጊዜ የሚወስድና እልህ የሚያስጨርስ መሆኑን ሁሉም እንዲያስተውለውና ፈጣን ውጤት በመጠበቅ ቶሎ ተስፋ ከመቁረጥ ይልቅ ሁሉም ዜጋ አለኝ የሚለውን መረጃ ለጋራ ንቅናቄው በመላክ ትብብሩን እንዲቀጥል ጨምረው ገልጸዋል፡፡

Wednesday, May 29, 2013

ኢህአዴግ የሚያሸንፈው መቼ ነው?

ጌታቸው ሽፈራው

መቼም ይህን ጥያቄ ስጠይቅ የግንቦት 20ን ‹‹ድል››፣ የ2002ና የባለፈውን ሚያዚያ 2005 ዓ/ም የቀበሌ፣ የወረዳ……ምርጫም ጨምሮ በመከራከሪያነት በማንሳት ምን ነካው ኢህአዴግ እኮ እያሸነፈ ነው የሚሉ አይጠፋም፡፡ ለእኔ ማሸነፍ ማለት የህዝብን ልብና አዕምሮ (hearts and minds) መያዝ ሲቻል ነው፡፡ በሀይልማ ከሆነ ጣሊያን፣ ጀርመን፣ እንግሊዝ በአጠቃላይ ቀኝ ገዥዎቹ አፍሪካውያንን በወታደራዊ ሀይልና በሌሎች አቅሞቻቸው በመብለጣቸው እስከ መቶ አመት ድረስ ገዝተዋል፡፡ በኤሲያን ደቡብ አሜሪካ ደግሞ ከ200 እስከ 800 አመትም የተገዙ ህዝቦች ነበሩ፡፡ ለጊዜው አሸናፊ የመሰሉት ቅኝ ገዥዎች የእነዚህን ህዝቦች ልብ መግዛት ባለመቻላቸው ጊዜ ጠብቀውም ቢሆን ተሸናፊዎች ሆነዋል፡፡ ኢህአዴግ አሸነፍኩት የሚለውን የመንግስቱ ሀይለማሪያም ደርግ ጨምሮ ህዝባቸውን በሀይል ጨምድደው የኖሩ ስርዓቶች የኋላ ኋላ ተሸንፈዋል፡፡ እነዚህ አካላት የተሸነፉት ህዝብን በሀይል እንጂ በሀሳብ ማሳመን ባለመቻላቸው ነው፡፡ ሰውን በሆዱ አሊያም በግድ ለዘላለም መግዛት አይቻልም፡፡ አንድም የሚፈልገው ነገር በየጊዜው ስለሚጨምር ይህን በየጊዜው የሚጨምርን ነገር ማሟላት አይቻልም፡፡ ማሟላት ቢቻል እንኳ ሰው የመጨረሻ ፍላጎቱ ነጻነት ነውና ዳቦ ጠግቦም ሆነ ሳይጠግብ ነጻነቱን መጠየቁን አያቆምም፡፡
ኢህአዴግም እስካሁን የኢትዮጵያውያንን ልብ በሀሳብ መግዛት አልተቻለውም፡፡ በብሄር፣ በስራና ጥቅማጥቅም፣ በማሳፈራራት፣ የሌሎቹ አስተሳሰብ እንዳይደርስ በማገድ ስልጣኑን ለማራዘም ቀና ደፋ እያለ ነው፡፡ ኢህአዴግ በዋነኝነት አሸንፍበታለሁ ብሎ የጀመረው የብሄርን ፖለቲካ ቢሆንም ይህ ቀመር የኢትዮጵያውያንን ልብ ሊገዛለት አልቻለም፡፡ ይህ እንደማያዋጣው ያሰበው ኢህአዴግ ኢትዮጵያውያን ሊሸነፉበት የሚችሉትን አስተሳሰቦች ለይስሙላህም ቢሆን ከጀመረ ጥቂት አመታት ተቆጥረዋል፡፡ ከእነዚህም መካከል የሚሊኒየም በዓልና የሰንደቅ አላማ ቀን የመሳሰሉትን አገራዊ እሴቶች ማንሳት ጀምሯል፡፡ ይሁንና እነዚህንም ቢሆን ከልብ ሳይሆን ለመቀስቀሻነት ብቻ እየተጠቀመባቸው በመሆኑ ሊያሸንፍባቸው አልቻለም፡፡ በመሆኑም ኢህአዴግ  እስካሁን ኢትዮጵያውያንን ማሸነፍ አልቻለም፡፡
ኢትዮጵያውያን የሚሸነፉት መቼ ነው?
ኢህአዴግ ለጊዜው ኢትዮጵያውያንን በበላይነት መራ እንጂ አላሸነፋቸው እያልን ነው፡፡ ምክንያቱ ደግሞ በአንድ አካል በሀይል ቁጥጥር ስር የወደቀ ሰው በዚህ አካል ሀይል ቁጥጥር ስር እንዲገባ ያደረገውን እምነቱን ጣል እርግፍ አድርጎ እስካልጣለ ድረስ ተሸናፊ ሊባይ አይቻልም፡፡ በመሆኑም ለእኔ እነ እስክንድር ነጋ፣ ርዕዮት አለሙ፣ ውብሸት ታዬ፣ በቀለ ገርባ የመሳሰሉት ዜጎች በኢህአዴግ ቁጥጥር ስር ቢሆኑም ከአካላቸው ውጭ እምነታቸውን መቆጣጠር እስካልቻለ ድረስ ተሸናፊዎች አይደሉም፡፡ በተቃራኒው ትናንት  ‹‹ዜሮ ዜሮን›› ዘፍነው ዛሬ ‹‹ይቀጥል!›› ያሉት እነ ሰለሞን፤ ትንንት ለኢትዮጵያ ህዝብ አንድ ድምጽ የነበሩትና አሁን በክብ ጠረጴዛ ለስርዓቱ ድምጽ የሆኑት እነ ሚሚ እንደልባቸው ቤተመንግስት መግባት ቢችሉም ኢህአዴግ ከልብና አዕምሯቸው በላይ ገዝቷቸዋል አሳዛኝ ተሸናፊዎች ናቸው፡፡ አሳዛኝ ተሸናፊ መጀመሪያ የተነሳበትን አያውቅም አሊያም ሲሸነፍም ድሮ ከነበረው አመለካከት በተቃራኒ ሁለመናውን የሚማረክ ነው፡፡ የእነዚህ ኢትዮጵያውያን ሽንፈት ጠንካራ ወታደር እያለው እራሱን ለጠላት በምርኮ እንዳቀረበ ጀኔራል እቆጥራቸዋለሁ፡፡ በተቃራኒው እነ እስክንድር ምንም ወታደር በሌለበት ብቻውን ከጠላት ጋር የሚፋለም ሲፋለም ተይዞ ስለ ክብሩ ሞትን ከሚጠባበቅ ጀግና ጀኔራል ጋር ቢመሰሉ አያንስባቸውም፡፡ ሽንፈት እንዲህ ለእየቅል ነው፡፡ ለአብዛኛዎቹ በተለይም ለታዋቂዎቹ መሸነፍ ጥቅም፣ ዝና ቀዳሚው ሲሆን በርካታዎቹ ኢትዮጵያውያን እንዳይሸነፉ ያደረጋቸው ኢትጵያውይነት ነው፡፡
አንድ ሰው በራሱ ኦሮሞ፣ አማራ፣ ትግሬ፣ ጉራጌ.. መሆኑን በማመኑ አሊያም ሌሎች በዚህ ምድብ ውስጥ ስላስገቡት ብቻ በብሄር ስም ሊጠራ ይችላል፡፡ አምኖም ሆነ ተወናብዶ በብሄር ማመኑ በራሱ ችግር ላይኖረውም ይችላል፡፡ ብሄር ችግር የሚያመጣው የመከፋፈያ መንገድና ለፖለቲከኞች መጠቀሚያ በሚያመች መልኩ ሲመነዘር ነው፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ብሄር ለመከፋፈያና ለፖለቲከኞች መጠቀሚያ በሚያገለግል መልኩ ቢመነዘርም አብዛኛዎቹ ኢትዮጵያውያን በዚህ ደስተኛ ባለመሆናቸው ኢህአዴግም ለማስመሰያነት  የሚጠቀምበት የአንድነት አጀንዳ ለማንሳት ፈራሁ ተባሁ እያለ ይመስላል፡፡ ኢትዮጵያውያን በዚህ በኩል ከመሸነፍ ይልቅ ማሸነፍ ወደሚችሉበት መንገድ ተቃርበዋል ማለት ይቻላል፡፡
በተቃራኒው ግን ብሄርን በዋነኛ መሳሪያነት የሚጠቀመው ኢህአዴግ ያሸነፈ የመሰላቸው ‹‹እሳትን በእሳት›› በሚል ይህን ቀመር የመረጡ አልጠፉም፡፡ ኢህአዴግ ያደርጋቸውን እያንዳንዱን እንቅስቃሴዎች ከብሄር አይን ብቻ በማየት በብሄር ቀመር ለመፍታት መጣር እስካሁንም ተቃውሞው ጎራ ውስጥ አልጠፉም፡፡ ይህ አንድ ስልት አይደለም ማለት አይቻልም፡፡ ሆኖም በተለይ በኢትዮጵያውይነት እናምናለን የሚሉትም አጀንዳ ሲያደርጉት ፖለቲካውን መርህ አልባ ያደርገዋል፡፡ ለአብነት ያህል ከየክልሉ የሚባረሩ ኢትዮጵያውያንን በኢትዮጵያውይነታቸው ሳይሆን በአማራነታቸው ብቻ መመንዘር እየተበራከ ነው፡፡ በእርግጥ ኢህአዴግ በተወሰነ ማህበረሰብ ላይ የሚያደርገው ይህ እርምጃ ተቃዋሚዎችን ወደዚህ የኢህአዴግ መስመር ሊጎትት ይችል ይሆናል፡፡ ኢህአዴግ የሚፈልገውም እያንዳንዱ ጉዳይ በአገር ማዕቀፍ ሳይሆን በብሄር አይን እንዲመነዘር ነው፡፡ ለተቃዋሚዎች ውድቀቱ የሚሆነውም ኢህአዴግም ይህን አንድ ማህበረሰብ ላይ የሚያደርገው እርምጃ የብሄር ፖለቲካውን እንዳይበርድና ኢትዮጵያውያን በአንድ ማዕቀፍ ይልቅ በቋንቋ የሚከፋፈሉበትን ‹‹የእኛ›› እና ‹‹እነርሱ›› ፖለቲካ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ለማድረግ  ስለሆነ በእሱ መስመር መግባታቸው ነው፡፡ በዚህ የኢህአዴግ ቀመር መሰረት ‹‹አማራ›› በመሆናቸው ‹‹ከቤንሻንጉል››፣ ከደቡብ ብሄራዊ ክልሎች ተባረሩ የሚል ክርክር አሸናፊ ሊሆን አይችልም፡፡ እነዚህን ህዝቦች በብሄር አምኖ የመደበ ተቃዋሚ ‹‹ውጡልን›› ያላቸው ፖለቲከኞች ወክለነዋል የሚሉትን ብሄር መብት ኢህአዴጋዊ በሆነው በዚሁ ቀመር ሊያምን ነው ማለት ነው፡፡ በመሆኑም ጉዳዩ መታየት ያለበት በኢትዮጵያዊ መዕቀፍ እንጂ በብሄር ማዕቀፍ አይደለም፡፡ ተቃውሞው በብሄር ማዕቀፍ ሳይሆን በኢትዮጵያውይነት ከዚያም አለፍ ሲል በሰብአዊነት ሲሆን የትግል አንድነቱ በመርህ ላይ የተመሰረተ ያደርገዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያውያን ተቃዋሚዎችም ወደውም ሆነ በግድ ወደ ኢህአዴግ ቀመር እየተንፏቀቁ በመሆኑ ኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪ በደል ሲደርስበት ይህን ህዝብ እንወክላለን የሚሉት አካላት ብቻ በቀዳሚነት ድምጻቸውን ያሰማሉ፡፡ አማርኛ ተናጋሪው ላይ በደል ሲደርስ በብሄርና አንድነት መካከል ግራ የተጋቡት ተቃዋሚዎች ድምጽ ሲያሰሙ ‹‹ሌላውን›› ህዝብ የሚወክሉት አካላት ድምጻቸው እምብዛም አይሰማም፡፡ በትግራይ ህዝብ ላይ በደል እንደሚደርስ የሚያምኑ ኢትዮጵያውያን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሱ ነው፡፡ በዚህ በኩል ህውሃት/ኢህአዴግ ባያሸንፍም ለጊዜው የተሳካለት ይመስላል፡፡ በቅርቡ ወደ ተቃውሞ ጎራው ለመቅረብ እየሞከሩ ያሉት ትግርኛ ተናጋሪዎች የትግራይን ህዝብ በደል ብቻቸውን የሚናገሩ ሆነዋል፡፡
ኢላማውን ያልለየ ተቃውሞ
አንድ ትግል እንደ ትግል ውጤታማ ለመሆን ኢላማውን መለየት ይገባዋል፡፡ ካልሆነ ከእንሰሳ መንጋ ውስጥ ገብቶ ያየውን ሁሉ ለመያዝ የሚቋምጥና ሁሉን ሲያሯሩጥ ውሉ ደክሞ የሚመለስ አዳኝ እንሰሳ መሆን ነው፡፡ የሚይዘውን ታዳኝ ቀድሞ ያልለየ አዳኝ ትርፉ ድካምና ታዳኙ ማንቃት ብቻ ነው፡፡ በፖለቲካ ስልትም ቢሆን ተለይተው መቀመጥ ያለባቸው ኢላማዎች ይኖራሉ፡፡ ከአንድ በላይ መለየት ያለባቸው እንኳ ቢኖሩ በቅደም ተከተል መቀመጥ የግድ ይላቸዋል፡፡ ይህ ገንዘብን፣ የሰው ሀይልንና ጊዜን ለመቆጠብም ሆነ በአጭር ጊዜ ውጤት ለማምጣት አይነተኛ መንገድ ነው፡፡ ይህ ካልሆነ ግን የሚከተለው ተስፋ መቁረጥና መጀመሪያ ከተመረጠው የትግል ስልት ማፈንገጥ ሲብስም ከተቃውሞው ጎራ መውጣትና እንዋጋዋለን በሚሉት ሀይል መዋጥ ወይንም መሸነፍ ነው፡፡
ይህ ችግር በአገራችን የተቃውሞ ጎራም ተከስቷል፡፡ በተለይ ብሄር ለዚህ አላማውን ያልለየ የፖለቲካ ኪሳራ የሚዳርግ የመጀመሪያው ምክንያት ነው፡፡ ብሄር ስስ፣ የፖለቲከኞች መጠቀሚያና እንደፈለገው የሚጠመዘዝ በመሆኑ ኢላማን ለመለየት እንዳይቻል ያደርጋል፡፡ በኢትዮጵያ ብሄርን  በቀዳሚነት የጀመሩ ሀይሎች  ተሸንፈዋል፡፡ ተሸንፈዋል ስንል ሀሳባቸውም ማለታችን ነው፡፡ ለብነት ያህል ለመጀመሪያ ጊዜ ብሄርን ወደ ኢትዮጵያ ፖለቲካ ይዞ ብቅ ያለው ጀብሃ አስከፊ ሽንፈት ከገጠማቸው ፓርቲዎች መካከል ቀዳሚው ነው፡፡ ይህ ፓርቲ በኤርትራና ኢትዮጵያ ህዝቦች መካከል ብቻ ሳይሆን ትግርኛ ተናጋሪውን የኤርትራ ህዝብ ሲከፋፍል ኖሯል፡፡ ለኤርትራ ችግር የገዥዎችን ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያን ህዝቦች ራሱ ባስቀመጠው የብሄር ቁና እየሰፈረ ሁሉም ላይ ለመዝመት ሞክሯል፡፡ በአሁኑ ወቅት መሳሪያና ስንቅ ሲያስታጥቀው ከነበረው ህውሃት በታች የሆነው ሻቢያም በኢትዮጵያ ገዥዎች ብቻ ሳይሆን በአማርኛ ተናጋሪው ህዝብ ላይ የመረረ ጥላቻ የነበረውና  ኢላማውን መለየት ያልቻለ ፓርቲ ነው፡፡ ምንም ያህል ስልጣን ላይ ቢወጣም ሻቢያ ያኔ ‹‹ከአማራ ነጻነት አወጣችኋለሁ›› ብሎ ያታለላቸው ህዝቦችን ልብ መግዛት ባለመቻሉ አሁን በመሸነፍ ላይ ይገኛል፡፡ ከ30 በመቶው በላይ የኢትዮጵያ ህዝብ ስም የተቋቋመው ኦነግ ከነገስታቱም ይሁን በጊዜው ከነበሩት ልሂቃን ይልቅ ‹‹አማራ›› መባሉን በማያውቀው ኢትዮጵያዊ ላይ ሁሉ በመዝመት ጊዜ፣ ጉልበቱንና አቅሙን አዳክሟል፡፡ ከምንም በላይ ወክየዋለሁ ከሚለው ኦሮምኛ ህዝብ ሳይቀር ይህ ህዝብን በጅምላ የማስጠላት ፖለሲው ላይ ተቃውሞ ገጥሞታል፡፡ በየትኛውም አለም ሰፊ ህዝብ እወክላለሁ የሚል ፓርቲ አንድነትን በማጠናከር እንጂ በጠባብነት ሁሉ ላይ በመዝመት አይታወቅም፡፡ በጠባብ ብሄርተኝነት ተራው ህዝብ ላይ ሲዘምት የነበረው ኦነግም ከኢትዮጵያ ፖለቲካ ለመውጣት ተገዷል፡፡ በቅርቡ ይህን ስህተቱን ያመነ የሚመስለው ኦነግ ህዝብ ላይ ሳይሆን አላማውን ልሂቃን ላይ በማድረግ በኢትዮጵያውይነት ማዕቀፍ ወደፖለቲካ መድረኩ እንደገና መመለሱ እየተነገረለት ነው፡፡
በብሄር ላይ የተመሰረቱ ፓርቲዎች የጊዜ ጉዳይ እንጂ መሸነፋቸው የግድ መሆኑን  ታሪክ ያስረዳል፡፡ ሶቬት ህብረትና ዩጎዝላቪያ በአንድ ወቅት ታላቅ ቢመስሉም በዚህ ኢላማውን በማይለይ የፖለቲካ ቀመር ምክንያት ተበታትነዋል፡፡ ሶቬት ህብረት በወቅቱ  አሜሪካን የምትገዳደር አገር ለመሆን ብትበቃም የኋላ ኋላ ተፈረካክሳ ግዛቶቿ ከአሜሪካ ስር ሆነዋል፡፡ ተከፋፍላ የነበረችው ጀርመን አውሮፓን መግዛት የቻለችው አንድ በመሆኗ ነው፡፡ የፋሽስትና ናዚ ፓርቲዎች  ኢላማ ለይተው ሳይሆን  በአለማቀፋዊ ‹‹የእኛ›› እና ‹‹እነርሱ›› ዘረኝነት ፖለቲካ ህዝብን ለጥቂት ጊዜ ማንቀሳቀስ የቻሉ ቢሆንም ሲሸነፉ ይከተሉት የነበረው ስርዓት የሚወገዝ፣ የሚናቅና የሚያስቀጣ ሆኗል፡፡ ጀብሃ፣ ሻቢያ፣ ኦነግ፣ ኦብነግ በብሄር ፖለቲካቸው ምክንያት ተሸንፈዋል፡፡ ህውሃት እስካሁን በሀይል ቢገዛም የሻቢያ መስራች ጀብሃ፣ ከዚያም የህውሃት አጋዥ ሻቢያ ክስረት ሽንፈቱ ወደማን እየመጣ ለመሆኑ ጠቋሚ ነው፡፡ ምን አልባት እነሻቢያ ብቻ ሳይሆን እነኢህአፓ፣ መኢሶንና የመሳሰሉትን አልተሸነፉም? የሚል ጥያቄ ሊቀርብ ይችል ይሆናል፡፡ ለእኔ የእነዚህ ፓርቲዎች ሀሳብ ሙሉ በሙሉ ጠፍቷል ማለት አልችልም፡፡ ከአሁን በኋላ ኢትዮጵያ እንጀብሃ፣ ሻቢያ፣ ህውሃት፣ ኦነግና ኦብነግ ያሉ ተገንጣይ ፓርቲዎችን ጸረ ኢትዮጵያዊ አቋም የምታስተናግድበት ቦታ ያላት አይመስልም፡፡ ለዚህም ህውሃት ለይስሙላህም ቢሆን የጀመረው የአገራዊ አንድነት፣ የኦነግ የስልት ለውጥ እና የአብዛኛዎቹ ሽንፈት ዋነኛ ማስረጃ ነው፡፡ ምንም እንኳ እነ መኢሶንና ኢህአፓ በፓርቲነት ባይኖሩም ጀምረውት የመነረውን ኢትዮጵያን ለክፉ የማይሰጥ ‹‹የብሄር›› ፖለቲካቸውን የአሁኑ ኢህአዴግ እንኳን አውን ሊያደርገው አልቻለም፡፡ ምን አልባት ከቀደም ፓርቲዎች ስህተት መማር ከቻሉ ተቃዋሚዎች የኢህአፓንና መኢሶንን አንዳንድ መስመሮች መፍታት የሚችሉ ይመስለኛል፡፡ በተለይ እነዚህ ቀደም ፓርቲዎች ብሄርን ከጠባብ ብሄርተኝነት ይልቅ ለአገር አንድነት  በሚጠቅም መልኩ  ለማዋል ጥረት  ማድረጋቸው የሚታወቅ ነው፡፡
በአሁኑ ወቅት ባለው ፖለቲካችንም አላማን ያልለየ ፖለቲካ ይስተዋላል፡፡ በእርግጥ ለዚህ ዋነኛ ምንጩ ህውሃት/ኢህአዴግ ነው፡፡ ህውሃት ትግርኛ ተናጋሪውን ህዝብ ከቀሪው የኢትዮጵያ ህዝብ በመነጠል ለመያዣነት እየተጠቀመበት ይገኛል፡፡ ይህም በብሄር ስም በተወናበደው ህዝብና በአንዳንድ ተቃዋሚዎች ዘንድ ትግርኛ ተናጋሪው ህዝብ ተጠቃሚ እንደሆነ ተደርጎ እየቀረበ ነው፡፡ ይህን ህውሃት ይፈልገዋል፡፡ ምክንያቱም ትግርኛ ተናጋሪውን ህዝብ ልብ ለማግኘትም ሆነ ሌላውን ለማሸነፍ የሚጠቅመው ይህ ስልት በመሆኑ ነው፡፡  የሌላ ቋንቋ ተናጋሪ ህዝቦችም ይወክሉናል በሚሉት ስር ከመስራት ውጭ በኢትዮጵያውነት ማዕቀፍ ለመታገል አማራጭ እንደሌላቸው ያምናሉ፡፡ ከኢህአዴግ አባል ድርጅቶች ውጭ ሌሎች ተቃዋሚዎች  በአገር ማዕቀፍ የሚታገሉ በመሆኑ በብሄር ስም የሚታገሉትም በመዳከማቸው የኢትዮጵያ ህዝብ ከኢህአዴግ አባል ድርጅቶችም ጎን ተስልፎ የአገሪቱን ኬክ ለመካፈል፣ ራሱን ለመከላከልና ለጥቅም እንዲቋምጥ ያደርገዋል፡፡ ማህበራዊ ድህረገጾችን ጨምሮ በአገር ውስጥ በሚደረገው ተቃውሞ ጠባብ ብሄርተኝነት የወለደውን እሳት በሌላ ጠባብ ብሄርተኛ እሳት ለመዋጋት የሚደረግ ጥላቻ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ በንጉሳዊያኑ ዘመን  አማርኛ ተናጋሪ ህዝብ አልተጠቀመም ብለው የሚከራከሩ ሀይሎች በኢህአዴግ ዘመን ትግርኛ ተናጋሪው ህዝብ ተጠቅሟል ወደሚል መርህ አልባ ፖለቲካ እያዘነበሉ ነው፡፡ ህወሓት ከሌሎቹ ‹‹የኢህአዴግ አባል›› ድርጅቶች በላቀ መከላከያውን፣ ደህንነት፣ የውጭ ጉዳይ፣ ፍርድ ቤት በአጠቃላይም የኢትዮጵያን ተቋማ ይዟል፡፡ በእርግጥ ቅጥር በዘመድ አዝማድ፣ በጓድነት፣ በፖለቲካዊ ቅርርብ ነውና እነዚህ ሰዎች በርካታ ሰዎችን (የህወሓት አባላትን) ስበዋል፡፡ ይህ ከህወሓት የበላይነት እንጅ ትግርኛ ተናጋሪው ኢትዮጵያዊ እንደ ህዝብ ገዥ በመሆኑ የተፈጠረ አይመለኝም፡፡ በአሁኑ ወቅት ከህውሃት ጎን ባለመሆናቸው እንደሌሎች ኢትዮጵያውያን ጥቃት እየደረሰባቸው የሚገኙ ትግርኛ ተናጋሪዎች  የብሄር ፖለቲካ ለመጠቀሚያነት ብቻ እያገለገለ የሚገኝ ቀመር መሆኑ እየተዘነጋ ይመስላል፡፡ ይህ የኢህአዴግን ቀመር መጠቀም ኢህአዴግን እቃወማለሁ የሚል አካል ሁሉ ኢትዮጵያውያንን ወደ ብሄር ፖለቲካ በመግፋት የራሱን ሽንፈትና የኢህአዴግን ድል ማፋጠኑ የግድ ነው፡፡ በአንድ ወቅት በብሄር ሳይሆን በኢትዮጰያውነት ማዕቀፍ ይህን ብልሹ ፖለቲካ ሲታገል የነበረው የአውራምባው ዳዊት  ሌሎች ባደረጉበት ግፊት (የራሱ ጽናት ማጣትም ተጨምሮበት) የብሄር ፖለቲካውን እየታከከ ነው፡፡ ይህ የኢህአዴግ ቀመር ነው፡፡ ይህ ብሄርን መሰረት ያደረገና አላማውን ያልለየው ‹‹የእኛ›› እና ‹‹እነርሱ›› ፖለቲካ በኢትዮጵያውያን ላይ የሚፈጥረው ሽንፈትን ብቻ ነው፡፡ የኢህአዴግ የብሄር ፖለቲካም የሚያሸንፈው ያኔ ነው፡፡

የአለም ባንክ እና ኢትዮጵያ ውዝግብ ውስጥ ገቡ

ላለፉት 20 አመታት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ከሞላ ጎደል ጥሩ የሚባል ግንኙነት የነበረው የአለም ባንክ በሀይል ከሚፈናቀሉ ዜጎች ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ውዝግብ ውስጥ መግባቱ ታውቋል።
ሂውማን ራይትስን ጨምሮ ሌሎች አለማቀፍ የሰብአዊ መብቶች ተከራካሪ ድርጅቶች የኢትዮጵያ መንግስት በጦር ሀይል በመታገዝ ከ45 ሺ በላይ የጋምቤላ ተወላጆችን በግዴታ ማስፈሩን ተቃውመው ነበር።
የአለም ባንክ አንድ ገለልተኛ ቡድን በማቋቋም ክሱን ለማጣራት ባለፈው ጥቅምት ወር እንቅስቃሴ የጀመረ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ መንግስትም ከአጣሪ ቡድኑ ጋር እንደማይተባበር ይፋ አድርጓል።
የጠቅላይ ሚ/ር ሀይለማርያም ደሳለኝ ቃል አቀባይ የሆኑት አቶ ጌታቸው አረዳ ከአጣሪ ቡድኑ ጋር እንደማይተባበሩ ዘገባውን ላወጣው ብሉምበርግ ገልጸዋል። “ከአለም ባንክ ጋር እንተባበራለን
ነገር ግን አለም ባንክ ካቋቋመው አጣሪ ኮሚቴ ጋር አንተባበርም” ብለዋል ቃል አቀባዩ።
የአለም ባንክ አጣሪ ቡድን በመጀመሪያ ሪፖርቱ ባንኩ የሚሰጠው ገንዘብ ዜጎችን በሀይል ከማፈናቀል ጋር የሚያያዝ መሆኑን ማመልከቱ የኢትዮጵያን መንግስት ሳያስቆጣ አልቀረም።
የኢትዮጵያ መንግስት አጣሪ ቡድኑ በኢትዮጵያ ላይ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ከጀመሩት ከእነ ሂውማን ራይትስ ጋር ግንኙነት አለው ይላል።
አንድ የሰብአዊ መብት ድርጅት ተከራካሪ የአለም ባንክ አባል የሆነ አገር ባንኩ ካቋቋመው አካል ጋር አልተባበርም ማለቱ ያልተጠበ ነው በማለት ለብሉምበርግ ገልጸዋል።
የአለም ባንክ ” አትጠይቁኝ” የሚለውን የኢትዮጵያን መንግስት ከዚህ በሁዋላ ሲረዳ አይታየኝም በማለት ባለስልጣኑ አክለዋል።
አትዮጵያ አምና ብቻ 3 ቢሊዮን 5 መቶ ሚሊዮን ዶላር ወይም ከ60 ቢሊዮን ብር ያላነሰ ገንዘብ በእርዳታ አግኝታለች።

ማንዴላ በመጨረሻዋ የፍርድ ቀን ለዘረኞች ያለው


ሉሉ ከበደ
ኢትዮጵያን በቁጥጥሩ ስር ያዋላት የትግራይ ዱር አራዊት ቡድን ዛሬ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እየጫነ ያለውን የአፓርታይድ አይነት ስራት እነ ኒልሰን ማንዴላ ከደቡብ አፍሪካ ምድር ከስሩ መንግለው ለመጣል እጅግ ብዙ መስዋእትነትና ምእተ አመት የሚጠጋ ጊዜ ነበር የወሰደባቸው።Former South African president Nelson Mandela
ምእራቡም ሆነ ምስራቁ አለም ለአፍሪካውያኑ የነጻነት ትግል ፈጥኖ እውቅናና ድጋፍ አለመስጠቱና በተለይ ምእራቡ ከነጮቹ ጋር ተመሳጥሮ በተዘዋዋሪ እነሱን መደገፉ ትግሉ ረጅም ጊዜ እንዲወስድና የነጻነቱም ቀን እንዲርቅ ቢያደርገውም፤ በትግሉ መሪዎች ፍጹም ቆራጥነትና ለሞት መዘጋጀት እንዲሁም በህዝቡ አንድነትና ጽናት አፓርታይድ ተወግዶ የደቡብ አፍሪካ ህዝብ መሪ መሾምና መሻር ችሏል በነጻነት።
እርግጥ  በኢትዮጵያ የበላይነቱን የተቆጣጠሩት የህውሀት ዘረኛ ሰዎች ከደቡብ አፍሪካ ነጮች ጋር ሊያነጻጽራቸው የሚያስችል ስልጣኔና ለነጩ አለም ቀረቤታ አላቸው ባንልም፤ ለሀያላኑ መንግስታት በሎሌነት እስከቀረቡና የሚታዘዙትን እስከፈጸሙ ድረስ ድጋፋቸውን እንደማይነፍጓቸው ባይናችን እያየነው በመኖር ላይ ነን። ይሁንና ከሁሉም በላይ ለወያኔ መቅበጥና ከልከ ማለፍ፤ ለነሱ የልብልብ ማግኘትና በላያችን ላይ መግነን ተጠያቂው እራሳችን ነን። አንድ ሆነን በቶሎ እነሲህን የኢጣሊያ ጣእረመንፈስ ነጋሲያን ፋሺሽቶች ማስወገድ ተስኖን የህዝቡን ደም እየጠቡ፤ የሀገሪቱን ሀብት እየዘረፉ መወፈራቸውን ቀጥለዋል።
የደቡብ አፍሪካውን የጥቂት ነጮች አፓርታይ መንግስት ለማስወገድ ኤ ኤን ሲ በ1912 ዓም ኢ ኤ አ ከተቋቋመ ጊዜ ጀምሮ ከአርባ አመት በላይ ሰላማዊ የትግል ስልት ነበር ሲከተል የቆየው። ህዝባዊ እንቢታ፤ እቤት የመዋል አድማ፤ የሥራ ማቆም አድማ፤ ይለፍ ወረቀት ሳይዙ በጅምላ ሆ ብሎ የተከለከለ ቦታ ሄዶ መታሰር፤ ወዘተ…. ያሁሉ ግማሽ ምእተ ዓመት ለሚጠጋ ጊዜ የተካሄደው ሰላማዊ ትግል የህዳጣኑን መንግስት ጭቆናና ጭካኔ አባባሰው እንጂ ለደቡብ አፍሪካ ህዝብ የፈየደው ነገር አልነበረም።
ኋላ ላይ ግን እነማንዴላ ሀሳባቸውን ለመቀየር ተገደዱ። ሰላማዊው ትግል በትጥቅ ትግል መደገፍ እንዳለበት አመኑ። ይህንንም ወሰኑ። የሽምቅ ውጊያ ለመጀመር በርካታ የ ኤ ኤን ሲ ታጋዮች ማንዴላን ጨምሮ ወደተለያዩ ሀገሮች ለወታደራዊ ስልጠና ተሰማሩ። ማንዴላም ወደ ኢትዮጵያ አቀና። እናም እ ኤ አ በ1961 ዓም የ ኤ ኤን ሲ ወታደራዊ ክንፍ በማንዴላ መሪነት ተመስርቶ በመንግስቱ የኢኮኖሚና ወታደራዊ ተቋማት ላይ አደጋ መጣል ጀመረ።
የነጮቹ መንግስት የትግሉ ትኩሳት እየተሰማው በመጣ ቁጥር ወያኔ እንደሚያደርገው በየጊዜው አዳዲስ ህግ ማውጣትና ድርጅቶችን ሁሉ ማገድ፤ ህዝቡንና ታጋዮቹን ማሳደድ፤ ማሰርና ማዋከቡን በሙሉ ሀይሉ ቀጠለ። የትግሉን መሪዎች የደረሰበትን በቁጥጥር ስር አዋለ ያልተያዘውም ከሀገር መሰድድና ትግሉን ከጎረቤት ሁኖ መምራት ግድ ሆነበት። የታሰሩት መሪዎች የሀገር ክህደትና መንግስትን በሀይል ለማስወገድ መሞከር  በሚል ክስ ለሞትና ለድሜልክ እስራት ያዘጋጃቸው ጀመር አፓርታይድ ።
እ ኤ አ አቆጣጠር 1962 ዓም ማንዴላ ያለፍቃድ ከሀገር ወተሀል፤ ህዝብን ለአድማ አነሳስተሀል ተብሎ አምስት አመት ተፈርዶበት እስር ላይ እንደነበረ ነበር ይህ አዲሱ ክስ የተደረበለት። ከዘረኞች ፍርድ ቤት ለነጻነት ታጋዮች ፍትህ የለምና ከረጅም ጌዜ ከንቱ ክርክር በኋላ እነማንዴላ ጥፋተኞች ናቸው ብሎ ነጩ ዳኛ ፈረደ። የፍርዱን ልክ ከመበየኑ በፊት ተካሳሾች የፍርድ ማቅለያ ክርክራቸውን እንዲያሰሙ በታዘዙት መሰረት ማንዴላ አራት ሰአት የፈጀ ታሪካዊና ድፍረትና ሀቅ የሞላበት ንግግር  በጽሁፍ  አቅርቦ ነበር።
በዚያ የመጨረሻዋ የፍርድ ቀን ለችሎቱ የተናገረውን ማንዴላ በጻፈው መጽሀፍ ውስጥ አሳጥሮ አቅርቦታል። ያ የአላማ ጽናትና ቆራጥነት የተሞላበት ንግግር አንዷለም አራጌን እስክንድር ነጋን ያስታውሳል። በሀገራችን ካለው ሁኔታ ጋር ምን ያህል እንደሚመሳሰል ለማስገንዘብ ወደ አማርኛ መልሸዋለሁ።
ማንዴላ ተከሳሽ ሳጥን ውስጥ ቆሟል። ተራው ደርሶ የክርክሩን ማክተሚያ ያነብ ጀመር።
አንደኛ ተከሳሽ ነኝ። በባችለር ኦፍ አርት የመጀመሪያ ዲግሪ አለኝ። ጆሀንስበር ውስጥ ከሚስተር ኦሊቨር ታንቦ ጋር በሽርክና ሆነን ለተወሰኑ አመታት የጥብቅና ሙያ ሰርቻለሁ። በ 1961 ግንቦት መጨረሻ ላይ ህዝብን ለአድማ ማነሳሳት እና ካለፍቃድ ከሀገር መውጣት በሚሉ ክሶች የአምስት አመት ፍርድ ተፈርዶብኝ በእስር ላይ የምገኝ ፍርደኛ ነኝ።
ነሀሴ ወር 1962 ለእስር እስከተዳረኩበት ድረስ በጉዳዩ ከፍተኛ ሚና የተጫወትኩና ኡምኮንቶ ሱዚዌ፤ የኤ ኤን ሲን ወታደራዊ ክንፍ ለማደራጀት ከረዱት መካከል አንዱ መሆኔን እቀበላለሁ።
ከሁሉ በፊት መንግስት በመግቢያው ላይ በደቡብ አፍሪካ የሚካሄደው ትግል፤በውጭ ሀይሎች ወይም  በኮሙኒስቶች ተጽእኖ ስር ያለ ነው የሚለውን ሀሳብና ግምት ባጠቃላይ ስህተት ነው ለማለት እሻለሁ። ያደረኩትን ነገር አድርጌአለሁ። እንደ ግለሰብም እንደ ህዝብ  መሪነትም። ይህንን ሳደርግ በደቡብ አፍሪካ ውስጥ ባለኝ ተሞክሮና በፍጹም አፍሪካዊ ኩራትና ክብር እንጂ የውጭ ወገኖች ባሉትና በሚሉት ተመርቼ ተነሳስቼ አይደለም።
በወጣትነት ዘመኔ ትራንስኪ ውስጥ የጎሳችን  አረጋውያን ስላለፈው የጥንት ዘመን ታሪክ ወግ ሲነግሩን እሰማ  ነበር። ሽማግሌዎች ከሚያወሷቸው የሗላ ታሪካችን ከኔ ጋር የሚያመሳስሉት የነበረው “ ያባትን ሀገር “ ለመከላከል ያደረጓቸውን ጦርነቶች ሲያነሱ’ የእነ ደንጌ እና ባንባታ፤ ሂንሳና ማካና፤ ኩንቲና ዳላሲል፤ ሞሾሾና ሲሁሁኔ ስሞች ሲጠቀሱ፤ የመላው አፍሪካ ክብርና ኩራት ሆነው ይሞገሱ ይወደሱ ነበር። ያኔ ያን ታሪክ ሥሰማ ተስፋ አደርግ  ነበር። ለህዝባችን የነጻነት ትግል የበኩሌን ጥቂት አስትዋጾ እንዳበረክት፤ ህይወት አንድ አጋጣሚ ትቸረኝ ይሆናል እያልኩ። በዚህ ጉዳይ ላይ ክስ ሲመሰረትብኝ እንደጥፋት የተጠቀሰውን ሁሉ እንዳደርግ መነሻና ግፊት የሆነኝ ይኸው የኋላ ታሪካችን ነበር።
ይህን እያልኩ የአመጹን  ጥያቄ አነሳና ፈጥኜ ጥቂት ዘለግ ላለ አፍታ ያለውን  ነገር ላስረዳ ግድ ይለኛል። እስካሁን ለችሎቱ ከተነገሩት ነገሮች ገሚሱም እውነት ገሚሱም እውሸት ናቸው። የሆነው ይሁንና ሻጥር ( በመንግስት የኢኮኖሚ ተቋማት ላይ አደጋ መጣል) ማቀዴን አልክድም። ይህንንም ሳቅድ በግዴለሽነትና በዘፈቀደ መንፈስ ተሞልቼ ወይም ደግሞ አመጽን የምወድ ሰው ሁኜ አይደለም። የረጅም ዘመን አንባገነንነት ያስከተለውን የነጮች  ብዝበዛና ጭቆና የተንሰራፋበትን የፖለቲካ ሁኔታ በሰከነ  አእምሮና  በተረጋጋ ሁኔታ ስገመግም ከኖርኩ በኋላ ነው በውጤቱ ይህን እርምጃ ለማቀድ የወሰንኩት።
ለችሎቱ ለማስረዳት የሞከርኩት ይህን የአመጽ እርምጃ ስንወስድ ሀላፊነት ሳይሰማንና ያልተጠበቀ ውስብስብ ችግር ሊያስከትል እንደሚችል  ሳናስብ ቀርተን እንዳልነበር ነው። አንድም አይነት ጉዳት በሰው ህይወት ላይ እንዳይደርስ ለማድረግ መወሰናችንን አጽንኦት ሰጥቼ ነበር።
እኛ ኤ ኤን ሲዎች ምንጊዜም የቆምነው ከዘረኝነት የጸዳ ዲሞክራሲ  እንዲሰፍን ነው። ጎሳዎችን እስካሁን ካሉበት ሁኔታ  በባሰ መልኩ ከሚያራራርቅ ማናቸውም ድርጊት እንታቀባለን። ጠጣሩ እውነታ ወይም ሀቅ ግን የሀምሳ አመት ሰላማዊ ትግል ለአፍሪካውያን ያተረፈው ያስገኘው ነገር ቢኖር እየበዛ እየበዛ የመጣ የመጨቆኛ ህግና እያነሰ እያነስ የሄደ መብት ብቻ ነው። ለዚህ ችሎት ይህን መረዳት ቀላል ላይሆን ይችላል። ህዝቡ ለረጅም ዘመን ሀይል ስለታከለበት አመጽ ሲነጋገር መኖሩ እሙን ነው። የአመጽን አማራጭ ተተው በሰላማዊ ትግሉ እንዲቀጥሉ እኛ የ ኤ ኤን ሲ መሪዎች ብንመክርም፤  ከነጮች ጋር ተዋግተው የሀገራቸው ባለቤት ስለሚሆኑባት ቀን ይወያያሉ። ግንቦትና ሰኔ 1961 ዓም ገሚሶቻችን ይህን እየተነጋገርን በነበረ ወቅት ከዘረኝነት የጸዳ መንግስት እንዲኖረን ለማድረግ የሰላማዊ ትግሉ ፖሊሲ ምንም ውጤት እንዳላመጣ መካድ አልተቻለም ነበር። ተከታዮቻችን በዚህ ፖሊሲ ላይ መተማመን እያቃታቸው፤ የሀይልን አመጽ እንደአማራጭ በአእምሮ ውስጥ ማጎልበት ጀመሩ። የሚረብሽ የአሽባሪነት እሳቤ።
የ ኤ ኤን ሲ ወታደራዊ ክንፍ ህዳር 1961  ዓም ተመሰረተ። ይህን ውሳኔ ስናስተላልፍና በተከታታይ እቅዳችንን ስንነድፍ የ ኤ ኤን ሲ ሌጋሲ ከአመጽ  በጸዳ ትግል ህብረ ዘርነት እውን የሚሆንበት ሀሳብ አብሮን እንዳለና እንደያዝነው ነበር። ሀገሪቱ በጥቁሮችና   በነጮች መካከል ወደሚቀሰቀስ የርስበርስ ጦርነት በሚያስኬድ ጎዳና ላይ እየተጓዘች እንዳለች ይሰማናል። ነገሩን የምንመለከተው በማስጠንቀቂያ ደወል ነው። የርስ በርስ ጦርነት ማለት ኤ ኤን ሲ የቆመለትን እሴት ማውደም ማለት  ነው። የርስ  በርስ ጦርነት ከተነሳ ማናቸውም ዘር ሰላም የማግኘት እድሉ እጅግ የከፋ ይሆናል። ጦርነት የሚያስከትለውን የከፋ ነገር ለማወቅ በደቡብ  አፍሪካ ታሪክ ውስጥ በቂ ምሳሌ አለን። በደቡብ አፍሪካ አንግሎ – ቦር  ጦርነት ያስከተለው ጠባሳ ለመሻር ከሀምሳ አመት በላይ ወስዷል። ዘር በዘር ላይ ተነስቶ ከሁሉም በኩል በቀላል የማይገመት ህዝብ በሚያልቅበት ሁኔታ ጦርነት ቢካሄድ ጠባሳው ለመሻር ምን ያህል ዘመን ይፈጃል?
በተግባር አይተን እንዳመነው፤ አመጽ፤ ለመንግስት፤ ህዝባችንን በጅምላ መጨረስ የሚያስችል ገደብ የሌለው እድል ይሰጠዋል። በርግጥም የደቡብ አፍሪካ ምድር፤ አፈር፤ ዱሮ በንጹሀን አፍሪካውያን ደም ጨቅይቷል። ሀይልን በሀይል መክተን ራሳችንን ለመከላከል የመዘጋጀት የረጅም ጊዜ ስራ መስራት ተግባራችን እንደሆነ ይሰማናል። ጦርነት አይቀሬ ከሆነ ጦርነቱ መመራት ያለበት ለህዝባችን ሁኔታ በተመቸ መልኩ እንዲሆን እንሻለን። ለኛ አንድ ነገር ያጎናጽፋል፤ እናም በሁለቱም ወገን አነስተኛ የህይወት መስዋእትነት የሚያስከፍል ይሆናል  ብለን ያልነው የሽምቅ ውጊያ ነው። ለዚሁ ዝግጅት ለማድረግ ወሰንን።
ነጮች  በሙሉ የግዴታ ወታደራዊ ስልጠና ይሰጣቸዋል። ለጥቁሮች ይህ ነገር አይደረግም። የሽምቅ ውጊያውን ሊመሩ የሚችሉ፤ ወታደራዊ ስልጠና ያላቸው ሀይሎችን መገንባት መሰረታዊ እሳቤአችን ነው። ሳንዘገይ ለዚህ መዘጋጀት አለብን።
ውይይታችን በዚህ ደረረጃ ላይ እንዳለ በአፍሪካ ሀገሮች ልዩ ልዩ ጉባኤዎችን ለመካፈልና ወታደራዊ ስልጠና ለመውሰድ ካገር እንደወጣሁ አስረዳሁ። የሽምቅ ውጊያ ቢጀመር ከህዝቤ ጋር አብሬ ለመቆም ለመዋጋት እንድችል፤ ወታደራዊ ስልጠና መውሰዴን ተናገርኩ።( ማንዴላ ወታደራዊ ስልጠና የወሰደው ኢትዮጵያ ነበር ) በ ኤ ኤን ሲና በወታደራዊ ክንፉ መካከል ያለውን የሚለያቸውን መስመር ለችሎቱ ገለጽኩ። ሁለቱ እንዴት የተለያዩ መሆን እንዳለባቸው እንዳደረግን ተናገርኩ። ፖሊሲያችን  ነበር። ተግባር ላይ ለማዋል ቀላል አልነበረም። በህግ መታገድ መታሰር ሁሉ ስለነበረ ሰዎች በሁለቱም ውስጥ መስራት  ነበረባቸው። የኮሙኒስት ፓርቲውና ኤ ኤን ሲ አንድ ዓላማ አላቸው የሚለውን የመንግስት ክስ ተከራሬዋለሁ።
የ ኤ ኤን ሲ ርእዮተ ዓለም መርህ ምን ጊዜም አፍሪካዊ  ብሄረተኝነት ነው። “ ነጭን ወደ ባህር ንዳው “ የሚለው አይነት የአፍሪካ ብሄረተኝነት ጩኽትም አይደለም። ኤ ኤን ሲ የቆመለት አፍሪካዊ ብሄረተኝነት፤ አፍሪካውያን በምድራቸው ምሉእ ሆነው በነጻነት እንዲኖሩ የሚያስችል ጽንሰ ሀሳብ ነው። የ ኤ ኤን ሲን ዓላማና አቋም የሚያንጸባርቀው ሰነድ በ ኤ ኤን ሲ የጸደቀው የነጻነት ቻርተር ሰነድ ነው። በምንም መልኩ የሶሻሊስት መንግስት እቅድ አይደለም። ለሀገሪቱ ታሪክ  ለሀገሪቱ የኢኮኖሚ መዋቅር ኤ ኤን ሲ መቼም አብዮታዊ ለውጥን ደግፎ አያውቅም። እስከማውቀው የካፒታሊዝምንም ስራት አውግዞ አያውቅም።
ከኮሙኒስት ፓርቲው በተለየ መልኩ ኤ ኤን ሲ በአባልነት አፍሪካውያንን ብቻ ነው የሚቀበለው። ዋና አላማውና ግቡም አፍሪካውያን አንድነትና የተሟላ የፖለቲካ መብት እንዲቀዳጁ ማድረግ ነው። የኮሙኒስት ፓርቲ ዋና አላማ  በሌላ መልኩ ካፒታሊስቶችን ማስወገድና በሰራተኛው መደብ መንግስት መተካት ነው። የኮሙኒስት ፓርቲ ለመደብ ልዩነት አጽንኦት ሲሰጥ ኤ ኤን ሲ በህብር አብረው የሚጓዚበትን ሁነት ይፈልጋል።
እርግጥ ነው በ ኤ ኤን ሲና  በኮሙኒስት ፓርቲው መካከል የቅርብ ትብብር አለ። ትብብሩም የጋራ የሆነ ግብ  መኖሩን የሚያረጋግጥ ነው።  ጉዳዩ የነጮችን የበላይነት ማስወገድ  ነው። ይህ ማለት በሁሉም አቅጣጫ የጋራ አቋምና የጋራ ግብ እንዳለ ያረጋግጣል ማለት አይደለም። የአለም ታሪክ በተመሳሳይ ምሳሌዎች የተሞላ ነው። ምናልባትም ስሜት የሚሰጠው ስዕል፤ ታላቋ ብሪታንያ፤ አሜሪካና ሶቬት ህብረት ናዚ ሂትለርን ለመውጋት ያደረጉት ትብብር ነው። ሂትለር ብቻ ካልሆነ በስተቀር፤ ቸርችልን ወይም ሩዝቬልትን ወደ ኮሙኒስትነት ተቀየሩ ብሎ ማንም ሰው ለመናገር የሚደፍር አይኖርም። ወይም ደግሞ አሜሪካና እንግሊዝ የኮሙኒዝምን ስራት ለማስፈን እየሰሩ ነው የሚል አይኖርም። ልምድ ያላቸው አፍሪካውያን ፖለቲከኞች ኮሚኒስቶችን ለምን ጥሩ ወዳጅ አድርገው እንደሚቀበሏቸው ስር የሰደደ መጥፎ አመለካከት በነሱ ላይ ላላቸው የደቡብ አፍሪካ ነጮች መረዳት በጣም ሊከብዳቸው ይችላል። ለኛ ግን ምክንያቱ ግልጽ ነው። በደቡብ አፍሪካ ውስጥ ለብዙ አስርት አመታት ጥቁሮችን እንደሰው ለማስተናገድ የተዘጋጁ፤ ኮሙኒስቶች ብቻ ነበሩ። እኩልነታቸውን የተቀበሉ፤ አብረውን ለመብላት ለመጠጣት የተዘጋጁ፤ አብረውን ለማውጋት፤ አብረውን ለመስራትና ለመኖር የተዘጋጁ። በዚህም ምክንያት ዛሬ ብዙ አፍሪካውያን ናቸው ኮሙኒዝምን ከነጻነት ጋር እኩል አድርገው የማየት ዝንባሌ ያላቸው።
እኔ ምንጊዜም ራሴን እንደአፍሪካዊ አርበኛ የምመለከት እንጂ ኮሙኒስት አለመሆኔን ለችሎቱ አስረዳሁ። መደብ አልባ ስራት  በሚል አስተሳሰብ መማረኬን ወይም ደግሞ የኮሙኒስት አስተሳስብ ተጽእኖ እንዳሳደረብኝ አልካድኩም።
ካነበብኳቸው የኮሙኒዝም ጽሁፎችና ከተወያየሗቸው ማርክሲስት ግለሰቦች እንደተረዳሁት ኮሙኒስቶች የምእራባውያንን የፓርላማ ስራት ኢዲሞክራሲያዊና አድሀሪ እንደሚሏቸው ተገንዝቤአለሁ። በተቃራኒው ግን እኔ የዚያ አይነቱ አሰራር አድናቂ ነኝ።
ማግና ካርታ ( መሰረታዊ መብት ማረጋገጫ ሰነድ)፤ ፔቲሽን ኦፍ ራይት፤ ቢል ኦፍ ራይትስ፤ የሚባሉት ሰነዶች  በመላው ዓለም የሚገኙ ዲሞክራቶች ዘንድ በክብር የሚያዙ ሰነዶች ናቸው። ለብሪታንያ የፖለቲካ ተቋማት ታላቅ አክብሮት አለኝ። ለሀገሪቱ የፍትህ ተቋማትም እንደዚያው። የብሪያንያን ፓርላማ በዓለም ከፍተኛው ዲሞክራሲያዊ ተቋም አድርጌ  ነው የምመለከተው። የፍትህ ተቋማቷ ራስ ገዝነትና ያለ ወገንተኝነት መስራት አድናቆቴን ሳያጭሩ የቀሩበት ጊዜ የለም። የአሜሪካን ኮንግረስ፤ የሀገሪቱ ስልጣን ክፍፍል፤ የፍትህ ተቋማቷ ራስ ገዝነት ተመሳሳይ አድናቆት በውስጤ ያጭራሉ።
በደቡብአፍሪካ ውስጥ በጥቁሮችና  በነጮች ህይወት መካከል ያለውን አስደንጋጭ ልዩነት ዘረዘረኩ። በትምህርት፤ በጤና፤ በገቢ፤ በየፈርጁ ጥቁሮች በህይወት ለመቆየት ብቻ  በሚያስችል ደረጃ ሲኖሩ፤ ነጮች በአለም ያለውን ከፍተኛ ደረጃ  ይኖራሉ። እናም ህይወት በዚሁ መልኩ እንድትቀጥል የማድረግ ዓላማ አለ። “ነጮች” አልኩ። ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ያሉት ጥቁሮች በሌላው አፍሪካ ካሉት ጥቁሮች የተሻለ ኑሮ የሚኖሩ ናቸው ብለው ያስባሉ። የኛ እሮሮ አልኩ፤ ከሌላው የአፍሪካ ህዝብ ጋር ስንነጻጸር ድሆች ነን አይደለም። በሀገራችን ውስጥ ካሉት ነጮች ጋር ስንነጻጸር ድሆች ነን ነው። ይህንን የተዛባ ሁኔታ እንዳናርም እንዳናስተካክል በህግ ተከልክለናል ነው።
አፍሪካውያን በሀገራቸው ክብር ያጡበት ሁኔታ ነጮችን የበላይ የማድረጉ ፖሊሲ ቀጥተኛ ውጤት ነው። የነጮች የበላይ መሆን የጥቁሮችን የበታችነት ያስከትላል። የነጩን የበላይነት ለመጠበቅ የሚወጣው ህግ ይህን እምነት ስር እንዲሰድ ያደርገዋል። በደቡብ አፍሪካ ውስጥ ማናቸውም ዝቅተኛ ስራ  በጥቁሮች ነው የሚሰራው። አንድ ነገር መነሳት ወይም መጽዳት ካለበት  ያን ስራ እንዲሰራለት ነጩ ጥቁሩን ገልመጥ ገልመጥ ብሎ ይፈልገዋል። አፍሪካዊው የርሱ ተቀጣሪ ሆነም አልሆነም።
ድህነትና የቤተሰብ መፍረስ የሚያስከትሉት ነገር አለ። የሚሄዱበት ትምህርት ቤት ስለሌላቸው፤ ወይም ትምህርት   ቤት እንዲውሉ የሚያስችል ገንዘብ  ወላጆቻቸው ስለሌላቸው፤ ህጻናት በየጎዳናው ሲንከራተቱ ይውላሉ። እቤት ውስጥም ተገኝተው ልጆቻቸው የት እንደሚውሉ ሊያዩ የሚችሉ ወላጆች የሉም። እናትም አባትም ያውም ሁለቱም ካሉ ቤተሰቡን በህይወት ለማቆየት ስራ  ብለው ውጭ መዋል አለባቸው። ይህ የወደቀ የሞራል ደረጃን ያስከትላል። በፖለቲካ  ብቻ ሳይሆን  በየአቅጣጫው ህገወጥነት፤አመጽና ሁከት እንዲንሰራፋ ያደርጋል።
አፍሪካውያን   በመላዪቱ ደቡብ አፍሪካ እኩል ድርሻ እንዲኖራቸው ይሻሉ። በህብረተሰቡ ውስጥ የደህነነት ዋስትናና ድርሻ እንዲኖራቸው ይሻሉ። ከሁሉም በላይ እኩል የፖለቲካ መብት እንዲኖረን እንሻለን። ያለዚህ መብት ስንኩልነታችን ዘለአለማዊ ነው የሚሆነው። በዚህች ሀገር ውስጥ ላሉት ነጮች ይህ አብዮታዊነት እንደሚመስላቸው አውቃለሁ። ምክንያቱም ብዙሀኑ መራጭ የሚሆነው ጥቁሩ አፍሪካዊ ስለሚሆን ነው ነጩ ዲሞክራሲን እንዲፈራ የሚያደርገው።
ይህ ኤ ኤን ሲ የሚዋጋለት ጉዳይ ነው። ትግላቸውም እውነተኛ ብሄራዊነት ነው። ባፍሪካውያን በራሳቸው ተሞክሮና በደረሰባቸው ስቃይ የተቀሰቀሰ የአፍሪካ ህዝቦች ትግል ነው። በህይወት የመኖር መብት ትግል ነው።
ንግግሬን አነበብኩ። እዚህች ነጥብ ላይ እንደደረስኩ ወረቀቶቼን ተከላካይ ጠረጴዛ ላይ አስቀመጥኩና ፊቴን ወደ ዳኛው መለስኩ። ችሎቱ ፍጹም ጸጥ እረጭ አለ። የመጨረሻዋን ንግግር ከትውስታዬ ስናገር ፊቴን ከዳኛ ዴዊት ላይ ዘወር አላደረኩም ነበር።
በህይወት ዘመኔ ለዚህ የአፍሪካ ህዝብ ትግል ህይወቴን አሳልፌ ሰጥቻለሁ። የነጮችን የበላይነት እየተዋጋሁ ነው። የጥቁሮችን የበላይነት እየተዋጋሁ ነው። ሁሉም ሰው ተዋህዶ፤ ሰምሮና አብሮ እኩል እድል እየተጋራ አንድ ላይ መኖር አለበት የሚል አስተሳስብ አለኝ። የምኖርለትና እንደግብም ልለቀዳጀው ተስፋ የማደርግበት አስተሳሰብ  ነው። አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘም ለመሞት የተዘጋጀሁለት አስተሳሰብ ነው።
አሁን  በችሎቱ ፍጹም ጸጥታ ሆነ። የመጨረሻዋን ከተናገርኩ  በኋላ ቁጭ አልኩ። በችሎቱ ውስጥ የነበሩ ታዛቢዎች ሁሉ አይናቸው እኔ ላይ ያረፈ መሆኑ  ቢሰማኝም ቤቱ ውስጥ ወዳለው ህዝብ ዘወር ብየ አላየሁም። ጸጥታው ለበርካታ ደቂቃዎች የዘለቀ  ቢመስልም ግን ምናልባትም ከሰላሳ ሲኮንድ በላይ አልቆየም ነበር። በረጅሙ የሚተነፍስ፤ ቁናቁና የሚተነፍስ፤ የሕብር ጉምጉምታ፤ የሴቶች ለቅሶ ተከትሎ በፍርድ ቤቱ ውስጥ ይሰማ ጀመር….
“LONG WALK TO FREEDOM” NELSON MANDELA (PAGE 432-438)
lkebede10@gmail.com

Tuesday, May 28, 2013

ኢትዮጵያዊቷ ወጣት በአትላንታ 25 ዓመት እስር ተፈረደባት


ኢትዮጵያዊቷ ወጣት ሮዳስ ተክሉ እዚህ አትላንታ ከተማ በዋለው የወንጀል ጉዳዮች ችሎት ቀርባ ጉዳይዋ ሲታይ ከቆየ በኋላ ባለፍው ሰኞ MAY 20/2013 ….. 25 ዓመት እስር ተፈረደባት። ሮዳስ ተክሉ ይህ የተፈረደባት የሰው ነፍስ በማጥፋቷ ወንጀሉንም መፈጸሟን በማመኗ ነው።
የኋላ ታሪኩ እንዲህ ነው። ፌብሩዋሪ 5 ቀን 2009 አመሻሽ ላይ በአትላንታ የተፈጸመው ወንጀል መላው የአትላንታ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያንን በቅርብ፣ ነገሩን የሰሙና በሌሎች ከተሞች ያሉትን ደግሞ በሩቅ ያስደነገጠ ነበር። 3754 ቢፈርድ ሃይዌይ የሚባለው የአትላንታ መንገድ ላይ የጸጉር መከርከሚያ ሱቅ ከፍቶ በመስራት ላይ የነበረው ኤርሚያስ አወቀ ፣ ማምሻውን ጭምር አምሽቶ እየሰራ ነበር። ከምሽቱ 8 ፒ ኤም አካባቢ ሮዳስ ተክሉ ሱቁ ድረስ መጣች።
የፖሊስ ሪፖርት እንደሚያሳየው ሮዳስ ሱቁ ድረስ ከመጣች በኋላ ጭቅጭቅ ተጀመረ። እሱ እንድትወጣለት ቢጠይቃትም አልወጣችም። ይልቁኑ በእጇ ሽጉጥ ይዛ ስለነበር ፣ ስልኩን አንስቶ 911 ደወለ፣ ስልኩን ላነሳችው ኦፕሬተር “አንዲት ሴት ሱቄ ድረስ መጥታ ልትገለኝ እያስፈራራችኝ ነው፣ መሳሪያ ይዛለች .. እያለ ገና ተናግሮ ሳይጨርስ ስልኩ ተቋረጠ። ከዚያ በኋላ በአካባቢው የነበሩ ሰዎች የጥይት ድምጽ መስማታቸውን ይናገራሉ።
ፖሊስ ካለበት፣ ነገሩን የሰሙም በጸጉር ቤቱ አካባቢ ሲደርሱ ኤርሚያስ በደም ተነክሮ ወድቋል፣ ወዲያው ወደ ሆስፒታል ተወሰደ ፣ ሆስፒታል ሲደርስም ህይወቱ አለፈ። በወቅቱ አንዲት ሴት ከቤቱ ወጥታ ስትሄድ አይተናል ከሚል ጥቆማ ውጪ ማን ገደለው የሚለው ጥያቄ እንቆቅልሽ ሆነ።
በማግስቱ ፌብሩዋሪ 6 ግን ፖሊስ ሮዳስ ተክሉ የተባለችና የቀድሞ ፍቅረኛው ነች የተባለች ሴት በጥርጣሬ መያዙን አስታወቀ። እሷም ወደ እስር ቤት ተወሰደች። ኤርሚያስም የፖሊስ ምርመራ ከታወቀና ዶክተሮች የሞቱን መንስኤ ካስታወቁ በኋላ ፌብሩዋሪ 11 ቀን በርካታ የአትላንታ ነዋሪ ኢትዮጵያውያን በተገኙበት በጸጉር ቤቱ ደጃፍ የሻማ ማብራት ሰነ ስር ዓት ተካሄደ፣ በማግስቱ ፌብሩዋሪ 12 ጸሎተ ፍትሃት ከተደረገለት በኋላ አገር ቤት ተወስዶ እንዲቀበር በተያዘለት ፕሮግራም ይሄዳል ሲባል ፣ ፖሊስ ተጨማሪ ምርመራ ያስፈልገኛል በማለቱ እስከ ፌብሩዋሪ 24 ሳይላክ ቆየ። ፌብሩዋሪ 24 ቀን ግን አስክሬኑ ወደ አገር ቤት ለቀብር ተላከ።
ከዚያ በኋላ ዜናው በአድማስ ሬዲዮም ሆነ አትላንታ ባለው ድንቅ መጽሔት ከወጣ በኋላ በወቅቱ የወጣት ሮዳስ ተክሉ ቤተሰቦች “እሷ በግድያው የለችበትም፣ ይህንን ድርጊት እሷ ትፈጽማለች ብሎ ማሰብ ትክክል አይደለም” ሲሉ ተናግረው ነበር። ሆነም ቀረ ላለፉት አራት ዓመታት ነገሩ ከፍርድ ቤት እስር ቤት ፣ ከ እስር ቤት ፍርድ ቤት ሲንከባለል ቆየ፣ የ ኤርሚያስ አወቀ የቅርብ ቤተሰብ የሆኑት አቶ ላቀው ለአድማስ ሬዲዮ እንደገለጹት በመካከል ተጠርጣሪዋ ልጅ፣ በጠበቆቿ አማካኝነት “አእምሮዋ ትክክል አይደለምና ለፍርድ ልትቀርብ አይገባም” ብለው ሲከራከሩ የቆዩ ሲሆን፣ ዳኞቹም የ አ ዕምሮዋ ነገር በሃኪሞች እንዲታይ ፈቅደው ቆይተዋል። በኋላ ግን ችሎት መቆም እንደምትችል በመታመኑ ፣ ጉዳዩ በከሳሽ አቃቤ ህግ እና በተከሳሽ ሮዳስ ተክሉ ጠበቆች መካከል ክርክሩ ቀጥሎ አራት ዓመት ከፈጀ። እንደ አቶ ላቀው ገለጻ ፣ በመጨረሻ ላይ ሮዳስ ወንጀሉን መፈጸሟን እንድታምን ተጠይቃ “አዎ ፈጽሜያለሁ፣ ነገር ግን በደም ፍላትና ሳላስበው ያደረኩት ነው” ስትል በማመኗ ዳኛዋ 25 ዓመት ጽኑ እስራት ፈርደውባታል። ምናልባት ጥፋቷን ባታምን እና ነገሩ በክርክሩ ብትሸነፍ የሞት ፍርድ ሊጠብቃት ይችልም ነበር ብለዋል።
ዳኛዋ በፍርድ ውሳኔያቸው እንደገለጹት “ ኤርሚያስ ገበየሁን በ 10 ጥይት መግደል ሳይታሰብ፣ ባጋጣሚ የተደረገ አይደለም” ሲሉ ውሳኔያቸውን አጽንተዋል።
በተያያዘ ሁኔታ ሮዳስ ተክሉ እዚያው እስር ቤት እያለች አንዲት ሴት ልጅ መውለዷም ታውቋል። የወለደችው ግሬዲ ሆስፒታል በፖሊስ ታጅባ ሄዳ ሲሆን፣ ባሁኑ ሰአት ህጻኗን አንዲት ነርስ እዚያው ግሬዲ እያሳደገቻት መሆኑ ሲታወቅ፣ የህጻኗን አባት በተመለከተ ዳኛዋ “የቀረበልኝ የዲ ኤን ኤ ምርመራ ስለሌለ፣ በልጅቷ አባት ጉዳይ የምሰጠው አስተያየት የለም” ሲሉ መናገራቸውም ታውቋል። (ምንጭ አድማስ ሬዲዮ አትላንታ)

ለብዙ ኢትዮጵያውያን ግንቦት 20 ካለፈው ይልቅ መጪውን የሚፈሩበት ጊዜ ነው


ጌታቸው, ከኦስሎ
ዛሬ ግንቦት 20 ነው።ግንቦት 20 የኢትዮጵያ የፖለቲካ መዘውር የተዘወረበት ለመሆኑ አሌ አይባልም። ዕለቱ እንደ አቶ ሃይለማርያም የመጀመርያ በጠቅላይ ሚኒስትርነት ማዕረግ እንዳደረጉት ንግግር ” ኢትዮጵያ ልትበታተን ስትል የዳነችበት ቀን” ነው ለብዙ ኢትዮጵያውያን ግን ግንቦት 20 ካለፈው ይልቅ መጪውን የሚፈሩበት ጊዜ ነው።ይህንን ሁለተኛውን ሃሳብ እኔም እጋራዋለሁ። ካለፈው ይልቅ መጪው ይቀርበናል።ያለፈውማ አለፈ።መጪው ግን ቢዘገይም ቢፈጥንም አይቀርም።እና ግንቦት 20 ካለፈው ይልቅ ለመጪዋ ኢትዮጵያ እንዴት አስጊ ያደርገዋል። ይህንን ለማብራራት ግንቦት 20 እንደ ሀገር ለኢትዮጵያ ይዞት የመጣውን በጥቂቱም መጥቀስ ይፈልጋል።ስለተሰራው የመንገድ እርዝመት፣ህንፃ፣ወዘተ ማተት ይቻላል።እርግጥ ነው መንገድ ተስርቷል።ህንፃ ተገንብቷል።ከተሞች ሰፍተዋል።ይህ ሁሉ  ግን መጪውን አስፈሪ ጊዜ ለሀገር ከመተው አልገታውም።
መጪውን አስፈሪ የሚያደርገው የግንቦት 20 ውጤቶች ምን ምን ናቸው?
እንድሜ ለግንቦት 20 ብዬ ብጀምርስ-
  • እድሜ ለግንቦት 20 ዛሬ ኢትዮጵያ በአለም ታይቶ በማይታወቅ መልክ በቁጥር ተከልላ ክልሎች ስለ ድንበሮቻቸው ሲደራደሩ አንዳንዴም ሲጋጩ ለማየት በቅተናል። ምሳሌ የአፋር እና ትግራይ፣ የሱማሌ እና ኦሮሞ፣ የአማራ እና አፋር ወዘተ መጥቀስ ይቻላል።
  • እድሜ ለግንቦት 20 አንድሰው ከአንዱ የሃገሪቱ ክልል ተነስቶ እንበል ደቡብ ወይንም ጅጅጋ  ገብቶ መሬት ገዝቶ ልረስ ወይንም ልነግድ  ቢል እርሱ ከመምጣቱ በፊት ከ 60 እና 70 አመት በፊት የሰፈሩቱ ከጉርዳፈርዳ፣ጋምቤላ፣ጅጅጋ እና አሶሳ ካለምንም ካሳ ሲባረሩ ያያል እና መጪው እያስፈራው አይሞክረውም።
  • እድሜ ለግንቦት 20 ወላጆች ልጆቻቸውን በፈለጉት ቋንቋ ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ለማድረግ በታሪካዊ አጋጣሚ የሚኖሩበት ክልል ቋንቋ ውጭ እንዳይስተምሩ ታግደዋል።ለምሳሌ ኦሮምኛ ተናጋሪ ልጁ በአማርኛ እንዲማር ቢፈልግ ግን በኦሮምያ ክልል ቢኖር አማርኛ ወደምነገርበት ክልል መሄድ ብቸኛ አማራጩ ነው።በምዕራቡ አለም የሚኖር አንድ ኢትዮጵያዊ ግን ልጁን በሀገሩ ቋንቋ እንዲያስተምር ባህሉን እንዲጠብቅ ድጋፍ ይደረግለታል።
  • እድሜ ለግንቦት 20 ኢትዮጵያ ወደብ አልባ ሆና የባህር ኃይሏን በትና  30 እና 40 ኪሎሜትር እርቀት የባህሩ ማዕበል ሲማታ እየተሰማ ከ85ሚልዮን በላይ ሕዝብ ወደብ አጥቶ የጅቡቲን እና የሱዳንን ወደቦች በከፍተኛ ገንዘብ እንዲከፍል ተወስኖበታል፣
  • እድሜ ለግንቦት 20  ጦርነት ቆመ በተባለበት ጊዜ በአዲስ አበባ ብቻ ከ 100ሺህ በላይ ”ጎዳና ቤቴ” ያሉ ሕፃናት መንገድ ላይ ፈሰው ኃላፊነት የሚወስድ መንግስት አጥተው ለማየት የበቃነው በግንቦት 20 ፍሬ ነው። (በቀድሞው መንግስት የተመሰረተው የሕፃናት አንባ እንዴት በአሁኑ መንግስት እንደፈረሰ ይህንን ሊንክ ከፍተው ቪድዮውን ይመልከቱ (http://gudayachn.blogspot.no/2013/05/main-play-list-on-home-page-playlist.html)፣
  • እድሜ ለግንቦት 20 ከሃያ ሁለት አመት በፊት ”የጫት ቤት” ብሎ በር ላይ መለጠፍ የምያሳፍርባት አዲስ አበባ ዛሬ ጫት በየዘርፉ ”የበለጩ ፣የባህርዳር፣ የወልሶ ጫት ቤት” ብቻ ተብሎ ሳይሆን የሚለጠፈው ”ጫት እናስቅማለን፣ እንፈርሻለን” ተብሎ የተፃፈባቸው ባብዛኛው ትምህርት ቤቶች የሚገኙበትን ቦታ ፈልገው የሚከፈቱ የጫት ቤቶች በዝተው ለመታየት በቅተዋል። ምን ይህ ብቻ ዩንቨርስቲዎቻችን በየዶርሙ ጫት ሸጉጠው ሲገቡ- ሲ ቃምባቸው ደጉ መንግስታችን በዝምታ አልፎ ትውልዱን ጫት ቃሚ አድርጎታል።
  • አድሜ ለ ግንቦት 20 ምሳ ሰዓት ላይ ከቢሮ ወጥተው ጫት ቅመው የሚመለሱ የባንክ ሰራተኞች፣መሀንዲሶች ወዘተ አፍርቷል ግንቦት 20።ከደንበል ህንፃ ጀርባ የሚገኙ የመቃምያ ቦታዎችን ብንመለከት በምሳ ሰዓት ደንበል ህንፃ የሚሰሩ ምሁራን ዩንቨርስቲ ሳሉ በተፈቀደላቸው የመቃም መሰረት ሥራ ከያዙ በኃላም ለመላቀቅ ትቸግረው ይታያል።እረ  እንዲያውም በሥራ ሰዓት ሾለክ ብለው የሚቅሙ ሰራተኞች መኖራቸውን የእዚህ ፅሁፍ ፀሐፊ እማኝ ነው። እድሜ ለግንቦት 20።
  • እድሜ ለግንቦት 20 ወላጅ አልባ ሕፃናት ጎዳና እንዳይወጡ በሕዝቡ የሚደገፍ እንደ ሕፃናት አምባ መስርቶ ከማሳደግ ይልቅ ለአንድ ሕፃን እስከ 25000 ዶላር መንግስት እየተቀበለ በጉዲፈቻ ስም ለአሜሪካ እና አውሮፓ የተቸበቸቡት እና ብዙዎች በህሊና ስቃይ እና የማንንነት ጥያቄ እንዲሰቃዩ የተደረጉት በግንቦት 20 ፍሬ ነው (ሰኔ 25/2012 እአአቆጣጠር  በቢቢሲ ድህረ ገፅ ላይ በወጣ አንድ ዘገባ መሰረት ኢትዮጵያ በአመት 5ሺህ በላይ ሕፃናት በማደጎነት ወደ አሜሪካ  ብቻ እንደሚሄዱ  እና አሜሪካ ከዓለም ላይ በማደጎነት ከምትወስደው ሕፃናት ኢትዮጵያውያን ሕፃናት ከ አምስቱ አንዱ እንደሆኑይገልፃል።(http://www.bbc.co.uk/news/world-africa-18506474)
  • እድሜ ለግንቦት 20 ሴት እህቶቻችን ተስፋ ቆርጠው ለአረብ ሀገር ባርነት  በአስርሺዎች የተጋዙት በሄዱበት ሀገርም ስበልደሉ የሚሰማቸው አጥተው አሳር ፍዳቸውን የሚያዩት ከግንቦት 20 ፍሬ ወዲህ ነው።
  • እድሜ ለግንቦት 20 ”የኤርትራ ጥያቄን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መፍታት የሚቻለው የ ሻብያን ሃሳብ በመቀበል ነው” ብለው ስያግባቡን የነበሩት  አቶ መለስ- ጦርነቱ አበቃ ከተባለ ከ ሰባት አመታት በኋላ ለዳግም እልቂት ”ድንበር” በሚል ሰበብ ዳግም የኢኮኖሚ ፀባቸውን ወደ ወታደራዊ ግጭት ቀይረው በአስር ሺዎች የረገፉት በ ግንቦት ሃያ ውጤት ነው፣
  • እድሜ ለግንቦት 20 ስደት ቀድሞ የነበረ ቢሆንም በከፍተኛ ተስፋ መቁረጥ በባህር፣በእግር ወዘተ ወጣቱ ከሀገር የሚወጣው ከግንቦት 20 ፍሬ ወዲህ ነው (ወደየመን በጀልባ ተሳፍረው ከገቡት ስደተኞች ከ 70%በላይ ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ኮሚሽን በዘንድሮው ዘገባው መጥቀሱን ልብ በሉ) ፣
  • እድሜ ለግንቦት 20 ወጣቶች ተምረው በእውቀታቸው ሀገርንም መጥቀም ሲገባቸው፣የስራ ዕድል የሚያገኙበት ወይንም  ስነልቦናቸውን የሚጠብቅ ግን ለፈጠራ የሚያዘጋጅ የስራ መስክ ከመፍጠር ይልቅ በምረቃቸው ጊዜ (የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ  2004ዓም ምረቃ ላይ አቶ ጁነዲን ለተማሪዎቹ እንደተናገሩት)ከዩንቨርስቲ ሲወጡ  የኮብል ስቶን ሥራን መስራት እንደሚገባ የተነገራቸው በግንቦት 20 ውጤት ነው።
  • እድሜ ለግንቦት 20 በሚድያውስ ቢሆን (ጎረቤት ኬንያን ለማነፃፀርያ እንጠቀም) ኬንያ የህዝብ ብዛቷ 30 ሚልዮን ሲሆን እኛ 85 ሚልዮን መሆኑን እናስታውስ እና ኬንያ በይዘታቸውም ሆነ በአቀራረባቸው የመንግስት እጅ ያልተጫናቸው 8 የቴሌቭዥን ጣቢያ፣ 38 ራድዮ ጣብያዎች፣ ከእሩብ ሚልዮን በላይ አንባቢ ያላቸው በየቀኑ የሚታተሙ 4 ጋዜጦች (http://www.pressreference.com/Gu-Ku/Kenya.html#b) ሲኖሩ ሃሳብን የመግለፅ መብት እና በሀገሪቱ የፖለቲካ ጉዳይ ላይ የመወያየት ነፃነት ከእኛ ጋር ሊወዳደር የማይችል መሆኑን ስናስብ እና ጋዜጠኞች መንግስትን ወቀሱ ተብለው በአሸባሪነት ዘብጥያ መውረዳቸውን ስናስብ እድሜ ለግንቦት 20 እንላለን።
  • እድሜ ለ ግንቦት 20 ጋና ነፃነቷን ስታገኝ የገነባነው ስታድዮም ዛሬ ጋና ከነፃነት አልፋ እስከ መቶ ሺሕዝብ የሚይዝ ስታድዮም ስትገነባ እኛ አሁንም አንድ ለእናቱ በሆነ ስታድዮም መገኘታችን የግንቦት 20 ውጤት ነው።እርግጥ ነው በዛሬው የግንቦት 20 በዓል የስፖርት አካዳሚ ምረቃ በአል እየተከበረ ነው። ስታድዮምስ ?
  • እድሜ ለግንቦት 20 ቀድሞ ጉቦ የሚለው ቃል ሲነሳ ስለ 20 እና 30 ብር ጉቦ እናስብ ነበር። ዛሬ ጉቦ፣ሙስና እና ዝርፍያ ማለት አድገው ተመንድገው  ዝርፍያ ማለት የብሔራዊ ባንክን የወርቅ ክምችት በወርቅ መሰል ነገር መቀየር ሲሆን ጉቦ ማለት ደግሞ የሀገር መሬት እና ውሃን  ለሕንድ እና ለአረብ በርካሽ መቸብቸብ ፣ በባለስልጣናት ቤት እንደባንክ ቤት በኢይሮ ብሉ በዶላር ቢሉ በፈለጉት የገንዘብ አይነት ከቤት ማስቀመጥ ማለት ነው (በቅርቡ የግምሩክ ባለስልጣናት ቤት  ተገኘ የተባለውን ብር ያስታውሱ)።
ይህንን ሁሉ ስናስብ ነው እንግዲህ ግንቦት 20 ካለፈው ይልቅ መጪውን የሚያስፈራ የሚያደርግብኝ።ከሁሉ የከፋው ግን መንግስት ስለሰራሁት መንገድ እና ድልድይ ስታመሰግኑኝ መስማት ብቻ ነው የምፈልገው ከማለቱም በላይ መሰረታዊ ስህተቶችን ”የጨለምተኞች አመለካከት’፣ የአመለካከት ችግር” እያለ ማጣጣሉን መቀጠሉ ነው አሳዛኙ።