የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ፓትሪያርክ(ኢሬቴድ) |
ብጹእ አቡነ ማትያስ በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳማት ሊቀ ጳጳስ፤ብጹእ አቡነ ህዝቅኤል የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሃፊና የከፋ ሸካ ቤንች ማጅ ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤ ብጹእ አቡነ ዮሴፍ የባሌ ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤ ብጹእ አቡነ ኤልሳእ የሰሜን ጎንደር ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፤ ብጹእ አቡነ ማቴዎስ የወላይታ ዳውሮ ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በእጩነት ቀርበዋል ብለዋል የአስመራጭ ኮሚቴው የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ባያብል ሙላቴ ።
የፊታችን ሐሙስ የካቲት 21 አዲስ አበባና ድሬደዋን ጨምሮ ከሁሉም አህጉረ ስብከት የተወከሉ ሊቃነ ጳጳሳት ፤ የአህጉረ ስብከት ስራ አስኪያጆች ፣ ካህናት ፣ ምዕመናንና የሰንበት ትምህርት ቤት ተወካዮች በእጩዎቹ ላይ ድምጻቸውን ይሰጣሉ። ድምጽ ሰጪዎቹ ቁጥር ስምንት መቶ እንደሆነ ነው አቶ ባያብል የተናገሩት ።
በዚሁ ዕለት ምሽት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ስድስተኛው ፓትርያርክ ማን ይሆናል የሚለው ምላሽ እንደሚያገኝ ፋና ዘግቧል ። የሚመረጡት ፓትርያርክ እሁድ የካቲት 24/2005 በቅድስት ስላሴ ካቴድራል በሚደረግ ስነ ስርዓት በዓለ ሹመታቸው ይፈጸማል
ከኢሬቴድ
http://ethionetblog.blogspot.no/2013/02/blog-post_5738.html?spref=fb
No comments:
Post a Comment