Saturday, February 23, 2013

14 አመት ወጣት ኢትዮዽያዊ በቤተሰብና ሀገር ናፍቆት ምክንያት እራሱን አጠፋ

The young man with the adoptive family ሀብታሙ የ 14 አመት ወጣት ነበር። ሁለት ሌላ ወንድሞች አሉት ከኢትዮጵያ ወላጆቹ ስለሞቱበት ሚላኖ በ(Paderno Dugnano) የሚኖሩ አሳዳጊዎች ከአንደኛው ወንድሙ ጋር ሊያሳድጉት ይዘዉት ይመጣሉ። የዛሬ 10 ወር የአገሩን ናፍቆትና ከውንድሙ መለየቱን ባለመቀበል በእግሩ ጉዞ ይጀምራል ከ አንድ ሳምንት ቀን ከ ለሊት ጉዞ በኋላ ናፖሊ በምትባል ባቡር ጣቢያ ፖሊሶች ይይዙታል አሳዳጊዎቹ መጥፋቱን አመልክተው ስለነበር። አሳዳጊዎቹ እነደሚሉት ሶስቱንም ለምን አንድ ላይ እንዳላመ ጧቸዉ እና ወደአገሩ መሄድ እንደሚፈልግ ይጠይቃቸው እንደነበር ነው ጉዞ ወደአገሩ ጀምሮ ሲመለስ የተናገሩት። ምንም ዕንኳን ከጣሊያን ወደ ኢትዮጵያ በግር መጓዝ የከበደ ቢሁንም ሀብታሙ ግን ሞከረ፤ ብዙ አስተያየት ነው የተሰጠበት ያገር የወገን ናፍቆት የማይታሰበዉን ጉዞ አስጀመረ በማለት ሌላም ሌላም … የሀብታሙ አሳዳጊዎች ተገኝቶ ወደቤት ሲመጣ የገቡለት ቃል ወዳገሩ እንደሚልኩትና ቤተሰቡን አይቶ እንደሚመለስ ነበር ግን ከ10 ወር የአገር ናፍቆት ጋር እራሱን ሰቅሎ ተገኘ። እንደናፈቀ ወደማይመለሱበት ተጓዘ። አሳዛኝ ፍፃሜ!!!

No comments:

Post a Comment