Friday, February 8, 2013

ከመቼውም ጊዜ የላቀ ህዝብ በአንዋር መስጂድ መንግስትን በመቃወም ተሰለፈ


በመላሀገሪቱ የተጠራው የሙስሊም ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ በአንዋር መስጊድም እየተካሄደ ነው፡፡ በአንዋር መስጊድ ከመቼውም ጊዜ በላይ የከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ መበገኘት በመንግስት ላይ ተቃውሞውን እያሰማ ሲሆን፣ ምዕመናኑ ኢቲቪ በቅርቡ ያስተላለፈውና የታሰሩትን የሙስሊሞች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትን በአሸባሪነት የፈረጀውን ዶክመንታሪ ፊልም በእጅጉ ተቃውመዋል፡፡ በህዝበ ሙስሊሙ በጉልህ ከተስተጋቡት መፈክሮች ውስጥ  “አሁንም ወኪሎቻችን ናቸው”፣ “ኢቲቪ ሌባ”፣ “ህግ ተጥሷል የሚሉት”፣ “እኔ አቡብከር አህመድ ነኝ”፣ “የማክሰኞው ድራማ ነው” የሚሉት ይገኙበታል፡፡  ተቃውሞው እንደተጠናቀቀ በህዝቡ መሀል ግጭት ለማስነሳትና ባስ ለማሰበር ሶስት የአንበሳ አውቶብሶችን (ማለትም 41፣12፣13 ቁጥር) ባሶችን እንዲገቡ ተደርጎ ከይርጋ ሃይሌ ህንፃ ላይ በቪዲዮ ለመቅረፅ ጥረት ቢደረግም ህዝቡ “አንሰብርም፣አንሰብርም” በማለት ባሶቹን በሰላም አሳልፏል ሲሉ ምንጮቻችን ከስፍራው ዘግበዋል፡፡
source fnotenetsanet.com

No comments:

Post a Comment